tgindex
ከፍልስፍና ዓለም™

ከፍልስፍና ዓለም™

Статистика
@Philosophyofworld1Книгианглийский

A wise man is one who has learned to restrain his desires.The lowest level of life is to live only within the bounds of desire.Most people have many desires but little knowledge wisdom belongs to those who have much knowledge and few desires -Schopenhauer

Последний пост
18:50
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
31
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
25 048
+161 за 4 дн.
Сутки
+28
+0,11%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
5 152
30 постов
Вовлечённость
20,6%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 31
Упоминаний
3
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
3 275
1/48двое суток
3 753
1/72трое суток
4 047

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 18:501 709865

    አርስዬ ነዉ ጉጉ ከትሪ እስከ ጆጉ መብላት ብቻ ወጉ አጀማመራችንን እንዳማረዉ አጨራረሳችንም ያምራል #COYG❤️⚽⚽⚽

  • 14 авг.2 917503

    ከሆኑ አመታቶች ወዲህ የሀገር ዉስጥ ልቦለድ ማንበብ አቁሚያለሁ ከአዳም ረታ መፅሐፍቶች ዉጭ እናም አንዳንድ ደግሞ እንደዚች ዓይነት በመጠን አነስ ብላ ግን በይዘት ግን ዉስጥን በሀዘን የምትሟላ እና ስቃይን መቋቋም የሚቻለዉ እስከምን ድርስ ነዉ የሚል ጥያቄ እስካነሳ ድርስ ያስገረመችኝ መፅሐፍ ናት ። ታዉቃላችሁ ባጠቃላይ በዉስጥ የተሸከመችዉ የሐዘን ክምችት ነዉ እናም የሆነ ያዕክል ማንኛዉም ሰዉ ሀዘን እንዲሰማዉ ታደርጋለች ። ከነበብኳት ቆይቻለሁ እናም ዛሬ እዚህ ለማቅረብ የፈለኩት ለረጅም ጊዜ ገቢያ ለይ ጠፍታ ነበር እናም ደራሲዋ ይሄችኑ መፅሐፍ በሁለተኛ ዕትም እና አዲስ መፅሐፍ አዉጥታለች በግልፅ ለመናገር ያዕክል ብታነቧት ጊዜዬ ባከነ ብላችሁ አትፀፀቱም " የባሲሊቆስ ዕንባ " ለእኔ ግሩም ናት ። እንዳዉም መፅሐፉ ዉስጥ ያለዉን በሙሉ ላይገልፅ ይችላል ግን እንደቅምሻ እንካችሁ ፦ ዛሬ ሞት ተፈርዶብኛል በቃ በሰይፍ ተቀልቼ እንድሞት ፣ በሕይወት ከሚኖሩት ወገን እንድሰረዝ ተበይኗል ። እሺ መሞቱን ልሙት ለምን ሰይፉን አይስሉትም ? ይኼም ተንኮል እኮ ነዉ ቶሎ ሲጥ እንዳልል የተሸረበ ሴራ በህይወት እና በሞት መካከል ያለን በግ እያየ የሚስቅ በግ አራጅ አለ ? እኔን የገጠሙኝ ግን እየገዘገዙ የሚገድሉ ሰዉ አራጆች ናቸዉ ። " ትላለች ።

  • 13 авг.3 71113

    без подписи

  • 13 авг.3 6934713

    "ታሪክ እራሱን ይደግማል" ሲባል ዘበት አይደለም። የሰዉ ልጆችን ታሪክ ስራዬ ብሎ ያጠና ሰዉ የእያንዳንዱ የታሪክ ዘንግ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሚደጋገም መዋቅራዊ ዘይቤ እንዳለ ልብ ይሏል። እነዚህ ሁለት አካላት "በስጋ የተገለጥን አምላክ ነን" ያሉ ሁለት ጎረቤታሞች ናቸዉ።የግሪኩ አንቲኪየስ አራተኛ እና የአይሁዱ ናዝሬታዊዉ እየሱስ። አንቲኪየስ አራተኛ ከክርስቶስ ልደት 180 አመታት በፊት ገደማ የነበረ የሴሌዉሲድ የሚባል ግዛት ንጉስ ነበር። እራሱንም በመንበር ስሙ Epiphanes(በስጋ የተገለጠ አምላክ) እያለ ያስጠራ ነበር። አንቲኪየስ እራሱን የዚዉስ ምድራዊ ተገልጦ አድርጎ ለህዝቡ ያስተዋዉቃል፤በሚያሳትማቸዉ ገንዘቦች ላይም የእሱን እና የዚዉስን አምሳል በማቀናጀት "ንጉስ አንቲኪየስ የተገለጠዉ አምላክ" የሚሉ ፅሁፎችንም አብሮ ያሳትምበታል። በጊዜዉም የይሁዳ ምድር ከግብፅ(ቶሎሚዎች ግዛት) እጅ  ወጥቶ በሴሌዉሲድ ግዛት ስር ነበርና አይሁዶችን የማስገበር፣የማስተዳደር እና የቤተመቅደሳቸዉን የበላይ መሪ የመምረጥ ስልጣን ነበረዉ። ይህንንም ስልጣኑን ተጠቅሞ በአይሁድ ቤተመቅደሶች ላይ የዚዉስ ሃዉልት በሚል የሱን ምስል የያዘ ሃወልት እንዲቆም አደረገ። በአይሁድ ህግ የረከሰዉን እና የማይፈቀደዉን አሳማን በመሰዊያው ላይ እያረደ በቤተመቅደሳቸዉ አርከፈከፈ፤ አይሁዳዊያኑም ያህዌን ክደዉ እሱን ማለትም ዚዉስን እንዲያመልኩ ያስገድዳቸዉ ጀመር። ቶራዎች ይቃጠላሉ፣ይዘዉ ሲያጠኗቸዉ የተገኙት ሰዎችም ይገደላሉ። አይሁዳዊያኖች ስለ ሃይማኖታቸዉ ሲሉ መሞትን እና ሰማዕትነትን መለማመድ የጀመሩበት ጊዜም ይሄ ነበር። ከመቶ አመታቶች ቡሃላም ክርስቶስ የይሁዳ ምድር በሮማዉያን እጅ ባለችበት ሰዓት ተወለደ፣አደገ፣አስተማረ እና ተሰቀለ። አንቲኪየስ "እኔ እና ዚዩስ አንድ ነን" እንዳለዉ ፤ ክርስቶስም "እኔ እና የሰማዩ አባቴ/ያህዌ/አብ አንድ ነን አለ"። በግሪክ ቃና የተፈጠረዉ ታሪክም እራሱን በአይሁድ ቃና ደገመዉ።

  • 10 авг.4 6474713

    ነገረ ፍትህ ♎️ የሰው ልጅ በዘመናት ጉዞው ዉስጥ ከሁሉ በላይ አጥብቆ የፈለገው፣በአይምሮዉ መሻት የተለመዉ እና በልበሙሉነት የሚያሳድደዉ ግን አንድም ጊዜ ሊጨብጠዉ ያልቻለዉ አንድ ምስጢር ቢኖር «ፍትህ» ነው። ፍትህ ምንድን ናት? የጠንካራው ፈቃድ ወይስ የደካማው መፅናኛ? የመለኮት ረቂቅ ህግ ወይስ የሰው ልጅ ስልጣኔ የፈጠራት ተሰባሪ ህልም? ​የጥንት ጥበበኞች ፍትህን ሲስሏት ዓይኖቿ የተሸፈኑ፣ በእጇ ሚዛንና ሰይፍ የያዘች እንስት አድርገው ነው። ይቺ እንስት አንድም በጥንት ግሪካዊያን የፍትህ አማልክቷ ተሚስ አንድም ደሞ በሮማዊያን የፍትህ አማልክቷ ጀስቲሺያ የምትመሰል ናት። ዓይኗ መሸፈኑ ለሰው ልጅ አድሎአዊ እንዳትሆን፣ ማንነቱን፣ ሀብቱን እና ማዕረጉን ሳታይ በተግባሩ ብቻ እንድትፈርደው ሲሆን፤ ሚዛኑ ደግሞ እውነትና ሀሰትን፣ በደልና ካሳን በትክክል ለመመዘን ነው። ነገር ግን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ይህች ሚዛን አብዛኛውን ጊዜ በኃያላን እጅ ወደ አንዱ ወገን ስታደላ ታይታለች።ሪፐብሊክ በተሰኘዉ መፅሀፍ ላይም እንደሰፈረዉ ታላቁ ፈላስፋ ፕሌቶ «ፍትህ ማለት ለእያንዳንዱ ሰው የሚገባውን መስጠት ነው» ሲል፤ ተቃዋሚው ትራሲማከስ ደግሞ «ፍትህ ማለት የኃያላን ጥቅም ብቻ ናት» በማለት የመራራውን ዓለም እውነታ ገልጦታል። በእርግጥም፣ በስልጣንና በሀብት ጥላ ስር ፍትህ ብዙ ጊዜ የእውነት ሚዛን መሆኗ ቀርቶ የኃይልና የጥቅም ማስጠበቂያ መሳሪያ ስትሆን እንመለከታለን።​እዚህ ላይ ነው ህግና ፍትህ የሚለያዩበት መሰረታዊ መስመር የሚሰመረው። ህግ በወረቀት ላይ የተፃፈ የስርዓት ደንብ ሲሆን፤ ፍትህ ግን በሰዉ ልጆች መሻት ውስጥ ያለች የእውነት ብርሃን ናት። ህግ አንዳንዴ በደልን ህጋዊ ሊያደርግ ይችላል፤ ፍትህ ግን ከተፃፉ ረቂቆች በላይ ለሰው ልጅ ክብርና ህሊና ትቆማለች። ታላቁ ራሺያዊ ደራሲ ዶስቶየቭስኪ በስራዎቹ አጥብቆ እንደሞገተው የሰው ልጅ ከውጭ ካለው ስርዓትና ፍርድ ቤት ቢያመልጥ እንኳ በነፍሱ ውስጥ ካለችው «የህሊና ፍርድ ቤት» ማምለጥ አይችልም። በደል የፈፀመ ሰው የውጭውን ህግና ዳኛ ቢያታልል እንኳ፣ በውስጡ ባለው ዘላለማዊ መዳኛ ሚዛን ለጥፋተኝነት ስሜት መጋለጡ አይቀሬ ነዉ። ​በመሆኑም ፍትህ በበደለኛውና በተበደለው መካከል ያለውን ሚዛን ማስተካከል፣ ለእያንዳንዱ ሰው የሰው ልጅነቱን ክብር እኩል መስጠት እና ያለፉ ስህተቶችን አግባብ ባለዉ ሚዛናዊ አካሄዶች ማረም ነው። ፍትህ ከሌለችበት ማህበረሰብ ውስጥ ሰላም የለም፤ ያለው ጊዜያዊ ፍርሃትና የፀጥታ እፎይታ ብቻ ነው። ካንት እንደሚገልፀዉ ፍትህ የጎደለው ዓለም የሰው ልጅ እንደ እቃ የሚታሰብበትና የሞራል ዋጋው የወረደበት ባዶ ስፍራ ይሆናል። ፍትህ በምድር ላይ ፍፁም ሆና ላትገኝ ትችላለች፤ ምክንያቱም እሷን የሚተገብረው የሰው ልጅ በራሱ ጎዶሎና አድሏዊ በመሆኑ ነው። ሆኖም ግን የሰው ልጅ ወደተሻለ የሞራል፣ የህግና የስልጣኔ ማዕረግ የሚያደርገው ታሪካዊ ጉዞ በሙሉ የዚችው ፍትህ ፍለጋ ጉጉት ውጤት ነው።

  • 9 авг.4 5695021

    መልካምነት ለምን ዓለምን ማሸነፍ አቃተዉ ? መፅሐፉ The idiot ይሰኛል ደራሲዉ ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ ነዉ ። ምናልባትም በእኔ አመለካከት ድንቅ የትርጉም መፅሐፍ እንደሆነ ይሰማኛል ተርጓሚዉም ብዉ መፅሐፍቶችን ከእንግሊዝኛ ወደ አማረኛ በመተርጎም የሚታወቀዉ ሙሉቀን ታሪኩ ነዉ ። እናም ይህን መጠነኛ ፅሑፍ ለማዘጋጀት የፈለኩት በዉስጡ አንድ ምስኪን ገፀባህርይ አለ እናም ይሄ ገፀባህርይ መልካም ሆኖ ወደ ዓለም እንዲገባ አድርጎታል ዶስቶቭስኪ ታድያ መልካምነት ለምን ዓለምን አላሸነፈም የሚል ጥያቄ በእኔ ዘንድ ይመላለሳል እናም እናንተ ዘንድ የሆነ ያዕክል ምላሽ ይኖራችሁ ይሆን በማለት ነዉ ለማቅረብ የፈለኩት ወደ ፅሑፉ እንዝለቅ ፦ በእኔ የንባብ ህይወት ጉዞ ዉስጥ ከብዙ ገፀባሕርያት ጋር ተዋዉቂያለሁ ( በምናብ ) አንዳንዶቹን አድንቂያለሁ አንዳንዶቹን ጠልቻለሁ አንዳንዶቹ ደግሞ ከመፅሐፉ ገፅም ወጥተዉ በአዕምሮዬ ዉስጥ ተቀምጠዋል ። ሆኖም ግን የልዑል ሚሽኪንን ያህል የወደድኩት ገፀባህርይ እስካሁን አልገጠመኝም ። ዶስቶቭስኪ ሚሽኪንን የተለየ ሰዉ አድርጎ ነዉ ወደ ዓለም ያመጣዉ ሰዎችን የሚያምን ፣ ለሁሉም ቅን የሆነ ፣ ሰዎች በዉስጣቸዉ የተሸከሙትን ቁስል መረዳት የሚችል እና ለሁሉም ትሁት የሆነ ገፀባህርይ ነዉ ። ዶስቶቭስኪ ልዑል ሚሽኪንን ወደዚህ ጨካኝ ዓለም ያመጣዉ ሰዎችን ለመበቀል እና ራሱን ከሌሎች ጋር ለማወዳደር አይደለም ይልቁንም ያመጣዉ በፍቅር እና በመልካምነት እንዲኖር ነዉ ። ምናልባትም በግሌ እንዲህ አስብ ነበር ይህ ዓይነቱ ሰዉ ዓለምን ማሸነፍ ይችል ይሆን ? እላለሁ ። በ the idiot ዉስጥ ያለዉ ሚሽኪን መልካም ሆኖ ተላከ ነገር ግን መልካምነቱ ዓለምን አልለወጠም ሰዎችን ለማዳን ምከረ በመጨረሻ ግን ራሱን አሰቃየ ለሌሎች የሚሰጠዉ ፍቅር ወደ ራሱ ሲመለስ ደስታን የሚሰጥ ሆኖ አልተገኘለትም ። እናም በዚህ ሁኔታ እኔን የሚያስገርመኝ ጥያቄ ከች ይላል ፦ ሰዉ መልካም ሲሆን ለምን እንደ ደካማ ይታያል ? ሰዎች መልካም ሲሆኑ ለምን እንደ ነሆለል ይቆጠራሉ ? ተበድለዉም ይቅርታ ሲያደርጉ ለምን እንደ አቅመቢስ እና ፈሪ ይቆጠራሉ ? አንድ ሰዉ ራሱን ለሌላ ሲሰጥ ለምን ዋጋዉ እንዳነሰ ይቆጠራል ? እንደተረዳሁት የሰዉ ልጅ በተፈጥሮዉ መልካምነትን ከኃይል ጋር የሚያይዘዉ አይመስለኝም ። ኃያሉን እና የሚገዛዉን ያከብራል የሚቃወመዉን እንኳን ኃይለኛ ከሆነ ትልቅ ዋጋ ይሰጠዋል ። ቅን እና መልካም ሰዉ ሲያገኝ ግን በቀላሉ አጣጥሎትና ተጠቅሞበት ይወረዉረዋል ። የ ዘ ኢዲዬቱ ሚሽኪን ለሰዎች የሚሰጠዉ እምነት እና ቅንነት ድንበር አልነበረዉም ። ሰዎች ግን የእርሱን ቅንነት እንደ ዕድል ይመለከቱታል እርሱ ሌሎቹን ከራሱ በፊት ሲያስቀምጥ ሌሎቹ ደግሞ እርሱን ለራሳቸዉ ይቀሙበታል ። ሌላዉ ደግሞ እዚህ ላይ ሚሽኪን የተሸነፈዉ መልካም ስለሆነ ብቻ አይመስለኝም ይልቁንም መልካምነቱ ድንበር ስላልነበረዉ ሁላ ነዉ የሚመስለኝ ። እንዳይረዝም ጠቅለል ለማድረግ ያዕክል መልካምነት ማለት ሁሉንም ነገር መታገስ ከሆነ ሁሉንም ሰዉ ማዳን ከሆነ ሁሉንም ቁስል በራስ ላይ መሸከም ከሆነ ምናልባትም ያ መልካምነት ራስን የሚያጠፋ ( መስዋዕት የሚያደርግ ) መልካምነት ይሆናል ። ስለዚህ ይህ መልካምነት እንዴት ነዉ ዓለምን ሊለዉጥም ሆነ ሊያድን የሚችለዉ ? መፅሐፉን ብታነቡት ይመረጣል ይሄን መፅሐፍ ሳነብ በታሪክ የማዉቀዉን የኢየሱስ ክርስቶስን የህይወት ነፀብራቅ ቁልጭ አድርጎ ያስመለክተኛል ። እናም ልዑል ሚሽኪን የኔ ምስኪን ነሆለል በመልካምነቱ እና በቅንነቱ መጨረሻ ላይ ባዶ እጁን የቀረ ምስኪን ነሆለል ።

  • 9 авг.3 369197

    без подписи

  • 8 авг.4 5807512

    በፌሚኒስት አክቲቪስቶች አስተባባሪነት ከሰኞ ጀምሮ ሊደረገ የታሰበዉ የስራ ማቆም አድማ ላይ የተደረገ ገለልተኛ ትንተና በጆርዲን በዛብህ(ቱንቡ የማህበራዊ ሚዲያ ፌሚኒዝም አቀንቃኝ) አነሳሽነት ሊደረገ የታቀደ የሶስት ቀን ገደማ የስራ ማቆም አድማ አለ። ይህም የሚከናወነዉ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በመሆኑ ስለ እዚህ እንቅስቃሴ አንድ አንድ ነገር ለማለት ወደድኩ። ይሄ የተቃዉሞ ስልት በአለም ደረጃ ተደርጎ ያዉቃል ወይ? ለሚለዉ ጥያቄ አዉ ያዉቃል እንደዉም በዝናዉ እና በትልቅነቱ የሚነሳዉ የ 2023ዉ የአይስላንድ 100ሺህ ሴቶች(ጠቅላይ ሚኒስተሯን ጨምሮ) ያረጉት አድማ ነዉ። ይህም ቁጥር ከ ጠቅላላ የህዝብ መጠኑ 25%ን የሚያካትት በመሆኑ ከሃገሪቱ አንፃር በግዙፍነቱ የሚታማ የስራ አድማ አልነበረም። ምንም ያህል አይስላንድ በፆታ እኩልነት ዘንድ ከአለም ቀዳሚዋ ሀገር ነሽ ተብላ በ WEF ranking የ 14 አመት ተከታታይ ሻምፒዮን ብትሆንም፤ በዛ የከተሙ ሴቶች ግን እኩሌታዉ ፍፁም ካልሆነ እና ጥቂቱ የደሞዝ ልዩነት ካልጠፉ አናርፍም በሚል ነበር የስራ ማቆሙን አድማ ያረጉት። እንደዚህ አይነት የስራ ማቆም አድማዎች የሚደረጉት ኢኮኖሚው ላይ ጫና በማሳደር የመንግስትን ትኩረት ለማግኘት እና የፖሊሲ ብሎም የ ህግ ስርአቶች ላይ ለዉጥ ለማምጣት ሲፈለግ ነዉ። እና ጆርዲን በዛብህ በቅስቀሳዉ ላይ እንዳለቹ (አንቺ ስራ ብታቆሚ ኢኮኖሚዉ ቀጥ ይላል) 25%ዉ ህዝቧ በጎዳና ላይ ስራ ፈቶ በመዋሉ ብሎም ኢኮኖሚዉ ዉስጥ ከሌላዉ ሃገር አንፃር ከፍተኛ ተሳትፎ አላቸዉ የሚባሉት የአይስላንድ ሴቶች የስራ ማቆም አድማ የታሰበዉን የኢኮኖሚ ጫና አምጥቷል? መልሱ አላመጣም ነዉ። ይሄዉላቹ ማነኛዉም ሀገር ላይ በአመት ዉስጥ ቢያንስ ከ 10 ቀን ያላነሰ የ holiday day offዎች አሉ፤ሁለቱም ፆታዎች ስራ የማይገቡበት ማለት ነዉ። እነዚህ የበዓል ቀናት ኢኮኖሚዉ ላይ ያን ያህል ተፅህኖ እንደማያሳድሩ ሁሉ የ ሁለት እና ሶስት ቀናት የስራ አድማ specially የሀገሪቷ ኢኮኖሚ ላይ አነስተኛ ተሳትፎ አለዉ የሚባለዉ የፆታ ክፍል የሚያረገዉ የስራ ማቆም አድማ significant የሆነ የ macro economy መናወጥ እና ክፍተት አያመጣም። ምንም ያህል ኢኮኖሚዉ ቀጥ ባይልም የአገልግሎት ዘርፉ እና መሰል sectorዎች ላይ ግን መጠነኛ መስተጓጐል ሊታይ ይችላል። የስራ ማቆም አድማዉ የቤት እና የኩሽና ስራዎችንም የሚያካትት በመሆኑ ትልቁ ችግር የሚፈጠረዉ በቤተሰብ ደረጃ ባሉ መስተጋብሮች ነዉ የሚሆነዉ። እንደሚታወቀዉ ምግብ ማብሰል፣የቤት ዉስጥ ጉዳዮችን ማስተዳደር፣ልጆችን መንከባከብ የአብዛኛዉ የኢትዮጵያ ቤት እመቤቶች ሃላፊነት ነዉ፤ይሄን ሃላፊነት በማይወጡበት ጊዜ በቤተሰቡ መሃል ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት መፈጠሩ አይቀሬ ነዉ። ስለዚህ ይሄ አድማ ከመንግስት ይልቅ የያንዳንዱን አባወራ ጓዳ ጎድጓዳ የሚያናዉጥ ነዉ የሚሆነዉ ማለት ይቻላል። በተጨማሪም እንደ ኢትዮጲያ አይነት አብዛኛዉ ህዝቧ conservative የሆነባት ሀገር ላይ እንደዚህ አይነት አድማዎች በትዳር ዉስጥ በቀላሉ ታይተዉ የሚታለፉ እና የሚስተባበሉ አይነት አይደሉም። ስለዚህ የዚህን አድማ የመጨረሻ ዉጤት ስንተነብየዉ ከመንግስት የፓሊሲ ለዉጥ እና የህግ ስርአት ማስተካከያ ይልቅ መጠነ ሰፊ የሆኑ ፍቺዎች፤የቤተሰብ መበተኖች እና ትዳር ላይ ጠባሳ የሚጥሉ አለመግባባቶችን የመፍጠር እድሉ የእትዬለሌ ነዉ። ይህ ደሞ ባንድም ሆነ በሌላ በኩል "በኢኮኖሚዉ ዘንድ አናሳ ተሳትፎ አላት" ለምትባለዉ የኢትዮጵያ ሴት ችግሯ ላይ ነዳጅ የሚያርከፈክፍ፣ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የሚፈጥር አካሄድ ነዉ። ሆነም ቀረ የአድማዉ ቅዱሱ አላማ እንዲሳካ እየተመኘን ይህን ማስረጃን የተመረኮዘ ትንበያ እና መሬት የረገጠ እዉነታን መዳሰስ ግድ ስለሚለን ለማስፈር ወደናል።

  • 7 авг.4 602357

    ስነ -ሂስ ኤኬሌ ትችት ሰነዘረ ወይንም ሂስ አቀረበ ሲባል ሁሌም እንሰማለን ግና አንድ ሂስ ሂስ ለመባል መሟላት ያለባቸዉ ነገሮች አሉ ወይስ የሉም ብለን ስንቶቻችን ጠይቀን እናዉቃለን? እርግጥ ነዉ በአብዛኞቻችን ዘንድ ያለዉ የሂስ ግንዛቤ ነገሩን ሲያዉጠነጥኑት እና ሲቀኙት ከሚኖሩት የዘርፉ ባለሞያዎች(ሃያሲያን) ጋር በፅኑ የተራራቀ ነዉ። በሰፊዉ ማህበረሰብ ዘንድ "ሂስ" እና "ነቀፌታ" የተለያዩ ናቸዉ ተብሎ አይታሰብም ዳሩ ግን በመካከላቸው መጠነ ሰፊ የሆነ ልዩነት መኖሩ ነዉ። አንድን ሂስ እንደ ሂስ ሊያስቆጥሩት ከሚችሉት ነገሮች ዉስጥ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል ሚዛናዊነት፣አመክንዮአዊ ማስረጃ፣ሰፊ አዉዳዊ ዳሰሳ እና ገንቢነት ናቸዉ። ለምሳሌ እትዬ ፋጡማ የጎረቤታቸዉ እትዬ አስካለ የእድር ቤት አስተዳደራዊ አፈፃፀም ላይ ሂስ ቢጤ ሊያቀርቡ ተነሱ እንበል፤ እትዬ ፋጡማ ከሁለት ቀን በፊት ያዩት የእትዬ አስካለ እና እትዬ ሙሉ(የላይኛዉ ሰፈር የእድር አስተዳደር) አፍ ለ አፍ ገጥሞ ማዉራት ስጋት ሆኖባቸዋል። በአይምሯቸዉ ዉስጥም "በዚህ አይነት የኛ ቤት የእድር እቃ እዛኛዉ እድር ቤት ጥቅም ላይ እየዋለ ይሁን እንዴ" የሚል ግላዊ ጥርጣሬ ያድርባቸዋል። ይህን ጥርጣሬያቸዉንም በማበልፀግ በእድሩ ስብሰባ ላይ የአፈፃፀም ጉድለት በሚል ምክንያት ትችት/ሂስ ቢጤ ሊሰነዝሩ ይሰናዳሉ። ምንም እንኳን እድሩ በቀድሞ አስተዳደሮች ዉስጥ እያለ ከሚጠፋዉ የተመዘገበ እቃ ባልበለጠ ሁኔታ ቢሆንም በእትዬ አስካለ አስተዳደር ስር የጠፋዉ፤እትዬ ፋጡማ ግን  ከዚህ ቀደም በአገልግሎት ላይ የጠፉ የእድር ኩባያዎችን ጉዳይ ለአብነት በመጥቀስ እነዚህ እቃዎች እየጠፉ ያሉት ከዚህ እድር በተጨማሪ ለሌላ እድር አገልግሎት ላይ እየዋሉ መሆኑን በመጠቆም ከግል ጥርጣሬያቸዉ የመነጨዉን ትንተና ለእድር ቤቱ ያቀርባሉ። አሁን የእትዬ ፋጡማ ሂስ ሂስ ተብሎ መቆጠር ይችላል ወይ? የሚለዉን እንዳሰዉ አንደኛ የአመክንዮአዊ ማስረጃ እጥረት ነዉ! የእትዬ ፋጡማ ሂስ የሚነሳዉ ከግላዊ ጥርጣሬያቸዉ ነዉ የሚያበቃዉም ግላዊ ጥርጣሬያቸዉ ባፈራዉ መደምደሚያ ላይ ነዉ። የእትዬ አስካለች እና እትዬ ሙሉ አፍ ለ አፍ ገጥሞ ማዉራት እትዬ አስካለች ወደ እተዬ ሙሉ እድር እቃ ታግዛለች ለሚለዉ መደምደሚያ የሚያደርስ በቂ ማስረጃ አይደለም። ስለዚህ ከግላዊ የቢሆናል እሳቤያቸዉ በመነሳት እትዬ ፋጡማ የ አስተዳደራዊ አፈፃፀም ጉድለቶች ያሉትን ትችት ተብዬ አቅርበዋል፤ ይሄንንም አመክንዮአዊ ያልሆነ እና ማስረጂያን ያልተመረኮዘ ትችት ከመደበኛ ሂስ ዉስጥ መመደብ አይቻልም። ሁለተኛዉ ደሞ ሚዛናዊነት ነዉ። የእትዬ ሙሉ እና እትዬ አስካለች አፍ ገጥሞ ማዉራት በተለያየ መንገድ ሊታይ ይችላል። ስለ ግል ጉዳያቸዉ፣ስለ ወዳጅነታቸዉ፣ ስለ ሌላ የስራ ጉዳይ እና መሰል ነገሮች እያወሩ ሊሆን ስለሚችል የነሱን አፍ ገጥሞ ማዉራት በእድርተኛዉ ላይ ከሚደረግ አሻጥር ወይ ሴራ ጋር ብቻ አገናኝቶ መተርጎም ሚዛናዊነት ያልታከለበት እና የግል ምልከታን አዝማሚያ(personal bias) ያስታከከ ተፋልሷዊ ትችት/ሂስ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። በዚህም የተነሳ ስለ አንድ ነገር የምናረገዉ መደበኛ ሂስ አመክኖአዊ ማስረጃን የታከከ እና ከግላዊ ምልከታ አድልኦዎች የፀዳ መሆኑን አበክረን ልንገመግም ይገባል።

  • 5 авг.4 8984915из thehumanistroad

    "አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት የባሏን መፅሀፍ አጠበች" የፌሚኒዝም እንቅስቃሴን ሀ ብሎ ያስጀመሩት እና ችቦዉን የለኮሱት እንስቶች አሁን በስመ ፌሚኒዝም እየተደረገ ያለዉን ተአምር ቢያዩ የሚገረሙ እና የሚደመሙ ይመስለኛል። በ18ኛዉ ክፍለዘመን ላይ የነበሩ ፌሚኒስቶች የፌሚኒዝምን ፅንሰሀሳብ ይዘው ሲነሱ በዉስጡ ያዘለዉ ዉጥን የማህበራዊ ፍትህ እና የእኩል መብት ተጠቃሚነት ጥያቄን እንጂ ከወንድ እኩል መሆኔ ይታወቅልኝ ዘንድ "እንደ ወንድ ቆሜ ልሽና" የሚል አልነበረም። እርግጥ ነዉ ማነኛዉም ፅንሰሃሳብ በጀመረበት አይቆምም እንደማነኛዉም ነገር ዝግመተ ለዉጥን ያካሂዳል፤ ግን አንድ ነገር በጣም ከተለወጠ እና ከመነሻዉ ሀሳብ መሰረታዊ ልዩነት ላይ ከደረሰ ያ ነገር በቀደመዉ ስም መጠራት ያቆማል፤አዲስ ባህሪዉን የሚገልፅ ስያሜም ይሰጠዋል። ስለዚህ ፌሚኒዝም እንደ ፅንሰ ሃሳብ ካዘለዉ ትርጓሜ ተነስተን አሁን በበይነ መረብ ላይ ዉርዉር የሚሉ ወንድን ሲራገሙ እና ሲሳደቡ በመዋል የበታችነት ስሜታቸዉን ለማስታገስ የሚሞክሩ በሃገሬዉ ቅኔያዊ ስያሜ ስንጠራቸዉ "ጋለሞታዎች"፤ ፌሚኒስቶች ናቸዉ ማለት እንችላለን? መልሱ አንችልም ነዉ! ምክንያቱ እነሱ የሚያሳዩት ባህሪ፣የአስተሳሰብ ምህዋር እና ግብረመልስ ከ ፌምኒዝም ይልቅ ለ ሚሳንድሪ(misandry) የሚቀርብ ስለሆነ ነዉ። በዚህም የተነሳ የሚያገባት ስታጣ አባቷን፣አጎቷን፣ወንድሟን እና ዘር ማንዘሯን የሚወክለዉን ፆታ እጅ እየጠቆመች ደፋሪ ለማለት የሚቃጣት፤ ጠዋት ላይ ፊቷን ሳትታጠብ ሮጣ ወንድ ለመሳደብ በይነ መረብ ላይ የምትጣድ፤ማሰብ ሲያቅታት በጭፍኑ ማመፅን የመረጠች እንስት ሁሉ ፌሚኒስት ልትባል አትችልም። በመጨረሻም በዘመናዊ ፌሚኒስት ነን ባዮች ገፀባህሪ ላይ የተፃፈ አንድ elite satire የያዘ መፅሀፍ ልጋብዛቹ፤አንብቡት ትዝናኑበታለቹ😄

  • 4 авг.5 941828

    ስነ ግጥም ነዉ ።

  • 3 авг.6 0912511

    በቅርቡ ሰይፉ ላይ የቀረበዉን እንግዳ አቀንቃኝ ወንድሙ ጅራ ያለበትን ሁኔታ ሳይ በጣም ነዉ ያዘንኩት፤ እዚች ሃገር ላይ ትልቅ አሻራን ያሳረፉ ሰዎች ስራቸዉ የሚገባቸዉን ዋጋ ሳይከፍላቸዉ ሲቀር ማየት በጣም ያሳዝናል። ይቺ ሃገር ካፈራቻቸዉ የሚመቹኝ ጥቂት ነገሮች አንዱ የወንድሙ ጅራ ዘፈኖች ናቸዉ።በኢትዮጵያ የዘፈን ኢንዱስትሪ ዉስጥ ለእኔ እንደ ግለሰብ በሱ ልክ ግጥሙ ከዜማዉ የተዋደደ እና በጆሮ ሲዘልቅ…

  • 3 авг.6 333666

    በቅርቡ ሰይፉ ላይ የቀረበዉን እንግዳ አቀንቃኝ ወንድሙ ጅራ ያለበትን ሁኔታ ሳይ በጣም ነዉ ያዘንኩት፤ እዚች ሃገር ላይ ትልቅ አሻራን ያሳረፉ ሰዎች ስራቸዉ የሚገባቸዉን ዋጋ ሳይከፍላቸዉ ሲቀር ማየት በጣም ያሳዝናል። ይቺ ሃገር ካፈራቻቸዉ የሚመቹኝ ጥቂት ነገሮች አንዱ የወንድሙ ጅራ ዘፈኖች ናቸዉ።በኢትዮጵያ የዘፈን ኢንዱስትሪ ዉስጥ ለእኔ እንደ ግለሰብ በሱ ልክ ግጥሙ ከዜማዉ የተዋደደ እና በጆሮ ሲዘልቅ የማይጎረብጥ ዘፈን የሚዘፍን ዘፋኝ የለም። እነዛን የመሰሉ ስራዎችንም ለአድማጭ ተመልካቹ ያበረከተ እንቁ አርቲስት ለስራዎቹ ይሄ ነዉ የሚባልን ክፋያ አለማግኘቱንና ምንም እንዳላበረከተ ዜጋ በችግር ሲማቅቅ ማየት ሃገሪቱ እንደለመደቹ ለባለዉለታዎቿ አመድ የማሳፈሷን ጉዞ ተግታ እንደቀጠለችበት የሚያሳይ ነዉ። አንድ እና ሁለት አመት ቲክቶክ ላይ እትት ብለዉ በባሌም በቦሌም ነጠላ ለቀዉ ሚሊየነር የሚሆኑ ሰዎች ባሉባት ሃገር ዉስጥ ለአስርት አመታት ጆሮ የማይሰለቸዉ ጊዜ የማያደበዝዉ የጥበብ ስራን ለህዝብ ያበረከተ ቱንቡ አርቲስት "ባዶ እጄን ነዉ ያለዉት፤ ከጥበብ ስራዎቼ ዱንቡሎን አላገኘዉም" ሲል እንደመስማት የሃገሪቷን ስሁት ኢኮኖሚያዊ መዋቅር የሚያሳይ ነገር የለም። ካበረከታቸዉ ዘፈኖች ዉስጥ ለአብነት ያህል ለመጥቀስ ጉዳዬ ነሽ፣አለች አንድ ቦታ፣አይኔ እየጠበቀሽ ነዉ፣ካንቺ ጋራ ስሆን፣ይቀመጣል እንዳደራ.... ይገኙበታል ከነሱም ዉስጥ "ይቀመጣል እንዳደራን" ልጋብዛቹ ወደድኩ

  • 3 авг.5 7363416

    የ "ኢዝም" ጠንቆች ይህ ቅጥያ ማነኛዉም ማህበራዊ፣ግላዊ፣ፍልስፍናዊ፣ስነምግባራዊ፣ባህላዊ እሳቤዎችን ለመግለፅ የሚገባ ቅጥያ ነዉ። ዳሩ ግን ይሄ ቅጥያ በሰዎች ስነልቦናዊ የአስተሳሰብ ስርአት ላይ ድንበርን፣ እነሱ እና እኛን፣ ፅንፈኝነትን የመፍጠር ምሉዕ ሃይል አለዉ። ከዛም በዘለለ ግራጫ የሆነዉን የአለምን ችግር ጥቁር እና ነጭ በሆነ መንገድ ለመግለፅ በመሞከር ሁለት "እኔ ነኝ ልክ" ፣ "እኔ ነኝ ልክ" የሚሉ ጎራዎችን ከመፍጠር ባሻገር የሚመነዘር ለዉጥ በምድር ላይ ሲያመጡ የሚታየዉ እምብዛም ነዉ። አንድ የ ኮሚኒዝም ተከታይ ካፒታሊዝም ያመጣዉን የግል ንብረት ባለቤትነት መብት እና የኢኮኖሚ እድገት(ምንም ያህል የመደብ ልዩነት ቢኖርም) ማድነቅ ካልቻለ እና ጥሩ ጎኑን ከራሱ እሳቤ ጋር ሊያቀናጅ ፍቃደኛ ካልሆነ፤ አንድ የካፒታሊዝም ተከታይም የኮሚኒዝም የሰዎችን የመደብ መራራቅ እና ጭቆና የማስቀረት "ቅዱስ አላማ" ሳይታየዉ ቀድመዉ በተደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ተመስርቶ በጥላቻ ካደባበት፤ ሁለቱም እንደ ቁራ ፅንፍ ይዘዉ የራሳቸዉን ድምፅ የሚያስተጋቡ የገደል ማሚቴዎች እንጂ ላለዉ መሰረታዊ ችግር መፍትሄ ሊፈጥሩ የቆሙ አካላቶች አይደሉም። ሰዎች ርዕዮተዓለማቸዉን እና እሳቤዎቻቸዉን እንደ ፍፁም አርገዉ ሲቀበሉ መሻሻልን ወይም ተጣጣፊነትን ሲነፍጉት ሃይማኖታቸዉ ሆኖ ይቀመጣል። ካፒታሊስት ከሆንክ ለምን የካፒታሊዝምን ክፍተት ትናገራለህ፤ ኮሚኒስት ከሆንክ ለምን የኮሚኒዝምን ክፍተት ትናገራለህ የሚለዉ አስተሳሰብ የ አመክኖ ህግ እስኪመስል ድረስ ያለዘለቀበት የሰዉ ልጅ አይምሮ የለም። አንድ ርዕዮተዓለም ስለተመቸን ወይ ከኛ የአስተሳሰብ ዘዉግ ጋር ስለገጠመ ብቻ ጉድለቶቹን እና ግድፈቶቹን በእዉር ድንብር ስንከላከል መኖር አለብን ማለት አይደለም፤ግድፈቶቹን ነቅሰን አዉጥተን ተችተን ትሩፋቶቹን ደሞ አበረታተን ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ወደ ሚያመጣ እሳቤ ማሳደግ እንጂ ጎራ ተከፋፍሎ "እኔ ነኝ ትክክል"፣ "አንተ ነህ ትክክል" መባባል ለዘመናት ካሳለፍነዉ የእጅ መጠቋቆም ጉዞ በዘለለ የሚፈጥረዉ እዚህ ግባ የሚባል ለዉጥ የለም።

  • 31 июл.6 4305314

    "This is a man's world" ይሄን ዓ.ነገር ስሰማ ትዝ የሚለኝ ዘፈን ይሄ ነዉ።በሰዉ ልጆች የታሪክ ጉዞ ዉስጥ የወንድ ልጅ አስተዋፅኦ የማይካድ እና ጉልህ መሆኑን የሚያወሳ በተመሳሳይ ሁኔታ ለሴቶች ተገቢዉን እዉቅና የሚሰጥ እንጉርጓሮ ነዉ። አሁን አሁን እየተነሱ ያሉ እንቅስቃሴዎች ላይ ግን ይህንን አስተዋፅኦ negative connotation ከተሰጠዉ የአባታዊ ስርአት(patriarchy) ጋር በማገናኘት የ disparagement ስራዎች ሲሰሩ እናያለን። "man made cars because patriarchy enlightened him" "Man made trains because patriarchy revealed it to him" "man made money not to trade with other man but to oppress woman" በሚል የዘፈኑ lyrics ቢቀየር ዉስጣቸዉ የሆኑ አካላትን ቤት ይቁጠራቸዉ።እርግጥ ነዉ የጥንቱ አባታዊ አገዛዝ በእንስቶች ላይ ያደረሰዉ ጭቆና የሚካድ አይደለም፤ አለምም ብትሆን አይደለም ለሴቶች ለወንዶች እንኳን safe heaven የሆነችበት ጊዜ የለም። በታሪክ ዉስጥ ጥቂት ወንዶች መአት ወንዶችን በባርነት ገዝተዋል፤ በታሪክ የፈለቁ ሴት ነገስታትም በተመሳሳይ ሁኔታ እልፍ አእላፍ ወንዶችን አስተዳድረዋል። የተረጋጋና እና የሰለጠነ ማህበረሰብ ከመምጣቱ በፊት መብት የሚባለዉ ነገር የቅንጦት ጥያቄ ነበር። ባርነት፣ሎሌ እኔ ጌታ፣ገዢ እና ተገዢ ባለበት ስርአት ዉስጥ ያለፈች አለም ላይ ያለን የአንድን ፆታ ታሪካዊ አስተዋፅኦ እንዳለ "የሱ ፆታ ስለገዛ ነዉ ያን ሁሉ ማረግ የቻለዉ" ብሎ መደምደሚያ መቀለስ ዉሃ የማይደፋ እና ምክንያታዊነትን ያልታከከ አስተሳሰብ ነዉ። it's a man's world because they built it from scratch to live in it with their women, this doesn't mean women have done nothing, though.

  • 30 июл.6 6994714

    ይህ ስዕል ለረጅም ጊዜ በዚህ ቻናል ተቀምጧል ምናልባትም በሰዉ ልጅ ታሪክ ዉስጥ አንዳንዶች መፅሐፍ ይፅፋሉ ። ሌሎች ደግሞ ህግን ያወጣሉ በጣም ዉስን ሰዎች ደግሞ በአንድ ስዕል ጥበብን ፣ ፍልስፍናን ፤ ሃሳብን ፣ ታሪክን ፣ ስነ ፅሑፍን በአንድ ሰንደዉ ያስቀምጣሉ ስራቸዉም ለዘላለም ህያዉ ሆኖ ይቀጥላል ... ከነዚህ ዉስን ሰዎች መካከል የህዳሴዉ ዘመን ስዓሊ ራፋኤል ይገኝበታል ። ይህ ስዕል the school of Athens ይሰኛል ከ50 በላይ ገፀባሕርያት symbolized ተደርገዋል ። ስለዚህ ስዕል እና ስለ ገፀባሕርያቶቹ በሌላ ጊዜ በሰፊዉ ለመፃፍ አስቤያለሁ ስዕሉ እጅግ ጥልቅ እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ መግለፅ እፈልጋለሁ ። ምናልባትም ይሄን ለመፃፍ ያነሳሳኝ አንድ ጎበዝ ሰዓሊ እና የጥበብ ሰዉ አለ እናም እርሱ የጥንት የግሪኮቹን አሳቢያን በራፋኤል በ the school of Athens እንደተገለፁት ሁሉ ለምን የኛን ሀገር ( ኢትዮጵያውያንን ) አሳቢዎች "በዘርዓያዕቆብ የፍልስፍና ትምህርት ቤት" ዉክልና ሰጥተን አድስ አመለካከት አንፈጥርም የሚል ትልቅ ፕሮጀክት ነድፏል ። ( በዚሁ አጋጣሚ ወዳጄ በርታ ማለት እፈልጋለሁ ) እኔ በበኩሌ በዚህ ፕርጀክት ማን ዉክልና ቢሰጠዉ ትመርጣለህ ብባል ሁለት ሰዎችን እመርጣለሁ ነጋድራስ ገብረ ህይወት ባይከዳኝ እና ዘርዓያዕቆብ ( ወርቄ ) እናንተስ እነማነን ትመርጣላችሁ ?

  • 28 июл.6 4875114

    ከዚህ በፊት የቶማስ ፔን the age of reasonንን በህይወቱ እና በመፅሐፉ ዙሪያ የተወሰነ ብለናል ከዛም ክርስቶፎር ሂችንስን ህይወቱን በመጠኑም ቢሆን አመለካከቱን በተወሰነ ያዕክል አቅርቢያለሁ ። የዚህኛዉ መፅሐፍ መከራከሪያዎች ከቶማስ ፔን ከ the age of reason ጋር በሆነ ያዕክል ይቀራረባሉ ልዩነቱ ቶማስ ፔን በአምላክ መኖር ሲያምን ሂችንስ ደግሞ በአምላክ አለመኖር ነዉ የሚያምነዉ ከማመን አንፃር ሁለቱም እምነት አላቸዉ ። ( ያዉ ዕምነት ማለት አንድን ነገር እዉነት ነዉ ብሎ መቀበል አይደል ) ለመንኛዉም ወደ መፅሐፉ እንዝለቅ ፦ God is Not Great ማንኛዉም አንባቢ መፅሐፉን ሲያነብ በፍጥነት መረዳት ያለበት ነገር ሂችንስ በተወሰነ ሃይማኖት ላይ የሚያተኩር ፅሐፊ አይደለም ። እስልምናን ፣ ክርስትናን ፣ ይሁዲነት እና ሌሎች ሃይማኖቶችን በአንድ መስፈርት ( መለኪያ ) ለመፈተሽ ነዉ የሚሞክረዉ ። የእርሱ ዋና ጥያቄ ሃይማኖት እዉነት ነዉ ወይስ ሰዉ የፈጠረዉ ስርዓት ? ይሄን ጥያቄ ያነሳና መከራከሪያዎችን ያቀርባል ፦ 1 ሃይማኖት ሁሉንም ነገር ይመርዛል ፦ መፅሐፉ በዚህ ሀረግ ይታወቃል ። ሂችንስ ሃይማኖት ከግለሰብ እምነት በላይ ማህበረሰብን ፣ ፖለቲካን ፣ ትምህርትን ፣ ሳይንስ እና ስነ ምግባርን የሚነካ ተቋም መሆኑን ያስረዳል ። ሂችንስ እንደ ችግር የሚቆጥረዉም " አንዳንድ አማኞች መጥፎ መሆናቸዉ ሳይሆን ሰዎች ያለ በቂ ማስረጃ አንድን ነገር እንዲያምኑ የሚያበረታታዉ የእምነት ስርዓት ራሱ ነዉ " በማለት ያቀርባል ። በእርሱ ዕይታ አንድ ሰዉ " ይሄ ቅዱስ ነዉ ስለዚህ አይጠየቅም አይመረመርም " ብሎ ሲያምን ከዚያ ወዲያ ምክንያታዊ ዉይይት ወዲያዉ ይቆማል ከዛ በኋላም ልዩነት ወደ ግጭት ይለወጣል በማለት ይከራከራል ። 2 የአምላክ መኖር ማስረጃ ያስፈልጋል ፦ ሂችንስ ከሚያቀርባቸዉ መከራከሪያዎች ዉስጥ በጣም ዝናኛ ሀሳቡ ይሄ ይመስለኛል ። እርሱ አምላክ የለም ብሎ ብቻ አይደለም የሚከራከረዉ የአምላክ መኖርን ሊነግረኝ የሚፈልግ ሰዉ የግዴታ ማስረጃ ማቅረብ አለበት ይላል ። ከዚህም የተነሳ ታዋቂዉን የመከራከሪያ መርህ ያቀርባል ። " ያለ ማስረጃ የቀረበ ክርክር ያለ መስረጃ ሊታለፍ ይችላል " በማለት ያስቀምጣል ። ሂችንስ ለየትኛዉም ሃይማኖት ልዩ መብት አይሰጥም ። የፖለቲካ የሳይንስ ወይም የታሪክ ክርክር ማስረጃ እንደሚፈልግ ሁሉ ሃይማኖታዊ እምነትም በተመሳሳይ መስፈርት ሊፈተሽ ይገባል ይላል ። 3 ቅዱሳን መፅሐፍቶች መለኮታዊ አይደሉም ፦ ከላይ እንደጠቀስኩት በዚህኛዉ መከራከሪያ ከቶማስ ፔን ጋር የሚጋራዉ ሃሳብ አለዉ ምንም እንኳን የሂችንስ መከራከሪያ ጠንከር ያለ ቢሆንም ሂችንስ መፅሐፍ ቅዱስን ፣ ቁርዓን እና ሌሎች ቅዱሳን መፅሐፍት የሰዉ ልጆች በተለያዩ ዘመናት የፃፏቸዉ ፅሑፎች እንጂ በቀጥታ ከአምላክ የመጡ አይደሉም ይላል ። ሂችንስ የሚያነሳቸዉ ምሳሌዎች በታሪክ ዉስጥ የተከሰቱ ጦርነቶች ፣ የባርነት ጉዳይ ፣ በሴቶች ላይ የሚታይ የመድሎ አመለካከት እና ከባባድ የሞት ቅጣቶች በሂችንስ ዕይታ ፍፁም እና ሁሉን አዋቂ ከሆነ አምላክ የሚጠበቅ ሥነ ምግባር ሊሆን አይችልም ሲል ይከራከራል ። 4 ስነ ምግባር ከሃይማኖት ሊወለድ አይችልም ፦ ሂችንስ " ሰዎች አምላክን ስለሚፈሩ መልካም ይሆናሉ " የሚለዉን አስተሳሰብ በግልፅ ይቃወማል ። እርሱ እንደሚለዉ ሰዉ ርህራሄን ፍትህን እና ትብብርን ከማህበራዊ ህይወትና ከሰዉ ተፈጥሮ ሊማር ይችላል ። እንዲያዉም አንድ ሰዉ መልካም የሚሆነዉ ሽልማት ለማግኘት ወይም ቅጣትን በመፍራት ብቻ ከሆነ ያ እዉነተኛ ስነ ምግባር ሊሆን አይችልም በማለት ይሟገታል ። 5 ሂችንስ ሃይማኖትን እንደ ጥቃት አድራሽ ይቆጥረዋል በታሪክ የተከሰቱ ጦርነቶችን በምሳሌ በስፋት ያቀርባል ። የመስቀል ጦርነቶችን ፣ የካቶሊክ የፕሮቴስታንት ግጭቶችን የሻዒ የሱኒ ሙስሊሞችን ፣ የሂንዱ እና የሙስሊሞችን ... የሌሎችንም እያነሳ እንዲሁም የሃይማኖት ስደቶች እና ዘመናዊ አክራሪነት በሃይማኖት ስም መፈፀማቸዉን በማንሳት የተለዩ የተፈጥሮ አደጋዎች ሳይሆኑ የሃይማኖት ስርዓት ዉጤት እንደሆኑ በአፅንኦት ይገልፃል ። 6 ሳይንስ እና ምክንያታዊነት ፦ በሂችንስ ዕይታ ሳይንስ ከሃይማኖት ጋር የሚፎካከር ዕምነት አይደለም እዉነትን ለመፈለግ የተሻለ እና ሁነኛ ዘዴ ነዉ ይላል ። አያይዞም ሳይንስ ስህተቱን ያርማል አዲስ ማስረጃ ሲገኝ አቋሙን ይቀይራል ። ይህ የሚያሳየዉ ሳይንስ ድክመቱን ለማረም ሁልጊዜ ክፍት መሆኑን ነዉ ። በተቃራኒው ግን ሃይማኖት ብዙ ጊዜ ጥያቄዎችን እንደ አደጋ ይመለከታቸዋል በማለት ይከራከራል ። ሌሎችም መከራከሪያዎችም አሉት በእኔ በኩል ግን በቂ መስሎ ተስምቶኛልና በዚሁ ለማጠቃለል እሞክራለሁ ። ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም ነጥቦች አንድ ጠንካራ መልዕክት ይፈጥራሉ ምናልባትም ሂችንስ እያለ ያለዉ እንዲህ ነዉ ፦ " ሃይማኖት ከማስረጃ በላይ ቦታ ሲያገኝ የሰዉ ልጅ ነፃነት ፣ ምክንያታዊነት እና ስነ ምግባር አደጋ ዉስጥ ይወድቃሉ ።" ይሄ መፅሐፍ ከላይ በተጠቀሱት እና ሌሎች እኔ ያልጠቀስኳቸዉ መከራከሪያ ሃሳቦቹ በዓለም ዙሪያ ዉዝግብ እና ከፍተኛ ዉይይት አስነስቷል እንዲሁም ዉይይት እና ዉዝግብ እንዳስነሳ ሁሉ ጠንካራ እና ከፍተኛ የሆነ የተቃዉሞ ግብረ መልሶችን አስከትሏል ። በእኔ በኩል ጨርሻለሁ! ምናልባትም አስፈላጊ ከሆነ የተቃዋሚ ምላሾች ወይም ለተነሱት የመከራከሪያ ሀሳቦች ተቃዋሚዎች ምን ምን ምላሾችን ሰጡ የሚለዉን በሌላ ጊዜ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ ። እስካዛዉ ቸር ሰንብቱ!

  • 26 июл.6 1425518

    God is Not Great << Christopher Eric Hitchens >> " How religion poisons everything " ይህ አንድ አጭር አረፍተ ነገር ብቻ አይደለም ይልቁንም በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ስለ ዕምነት ፣ ስለ ምክንያታዊነት እና ስለ ሰዉ ልጅ ህልዉና የተነሱ ትልልቅ ዉይይቶችን ያቀጣጠለ የክርስቶፎር ሂችንስ የአስተሳሰብ ማዕከል ነዉ ። ይህን አረፍተ ነገር ባአጋጣሚም ይሁን ፈልጎ የሰማ ሰዉ ሁለት ምላሾችን ይሰጣል አንድኛዉ በፍጥነት ይቆጣል ሌላኘዉ ደግሞ " ለምን እንዲህ አለ ?" ብሎ ራሱንም ሆነ ሌሎችን ይጠይቃል ። ፍልስፍና የሚጀምረዉም ከዚህ ከሁለተኛዉ ጥያቄ ነዉ ። ብዙ ሰዎች ክርስቶፎር ሂችንስን " አምላክ የለም " የሚል ፅሐፊ ብቻ አድርገዉ ይቆጥሩታል ። ይህ ድምዳሜ ግን የእርሱን ሃሳብ ከመጥን በላይ ማሳነስ እንደሆነ ነዉ የሚሰማኝ ። ሂችንስ የሚያነሳዉ ጥያቄ አምላክ አለ ወይስ የለም ብቻ አይደለም ሃይማኖት የሰዉን ልጅ ነፃ ያወጣዋል ወይስ ያስረዋል ? ስነ ምግባር የግድ ከሃይማኖት መምጣት አለበትን ? ሳይንስ እና ምክንያታዊነት ከሃይማኖት የተሻለ የዕዉነት መፈለጊያ መንገድ ናቸዉን ? የሚሉ ጥያቄዎችን ያቀርባል ። ክርስቶፎር ሂችንስ በ1949 በእንግሊዝ ፓርትስማዉዝ ተወለደ ። በኦክስፎርድ ዩንቨርስቲ ፖለቲካ ፣ ፍልስፍና እና ኢኮኖሚክስ አጥንቷል ( ተምሯል ) ። በመጀመሪያ የታወቀዉ በጋዜጠኝነት እና በፖለቲካ ተንታኝነት ነዉ ። በኋላ ግን በሃይማኖት ፣ በፖለቲካ ፣ በሰብዓዊ መብቶች እና በነፃ አስተሳሰብ ላይ በፃፋቸዉ መፅሐፍትና በሚያቀርባቸዉ ክርክሮች በዓለም ታዋቂ ሆኗል ። ሂችንስ መከራከር የሚወድ አሳቢ ነዉ ። የሚከራከረዉም ተቃዋሚዉን ለማሸነፍ ሳይሆን ሀሳቡን ለመፈተን እና ለመረዳት ይከራከር ነበር ። የእርሱ ንግግሮች ቀጥተኛ እና እንደ ጦር የሚዋጉ አንዳንዴም የሚያስቆጡ እንደሆኑ ታዛቢዎች ይመሰክራሉ ። በአንድ በኩል በኤቲስቶች ዘንድ እንደ ጀግና ሲቆጠር በሌላ በኩል በብዙ አማኞች ዘንድ እንደ ከባድ ተች ይመለከቱት ነበር ። ከ2000ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ ሂችንስ ከሪቻርድ ዳዉኪንስ ፣ ከሳም ሀሪስ እና ከዳንኤል ዴኒት ጋር በመሆን " አዲስ ኤቲዝም ( New Atheism )" አቀንቃኝ ተብሎ የሚጠራዉ ታዋቂ እና ፊታዉራሪ ሆነ ። እነዚህ ፅሐፊዎች ( ፈላስፎች ) ሃይማኖት የግል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ማህበረሰብን የሚነካ ስለሆነ ለትችት ክፍት መሆን አለበት ብለዉ እንደሚከራከሩ በግልፅ የሚታወቅ ነዉ ። በፈረንጆቹ አቆጣጠር መስከረም 11 2000 የአልቃይዳ የሽብር ቡድን በአሜሪካ ላይ ከፍተኛ የሽብር ጥቃት በመሰንዘሩ በወቅቱ ደርጊቱ ዓለምን አናዉጦ ነበር ። ከዚያ በኋላ በሃይማኖት ስም የሚፈፀሙ ግጭቶች ሽብርተኝነት እና አክራሪነት በዓለም አቀፍ የዉይይት ርዕሰ ጉዳይ ሆኑ ። ሂችንስ ይህን ሁኔታ ከተመለከተ በኋላ " ችግሩ አክራሪዎች ብቻ አይደሉም ችግሩ እራሱ የሃይማኖት አስተሳሰብ ነዉ " ብሎ አመነ ። ከዚህ ዓመለካከት ተነስቶ በ 2007 God is Not Great ፡ How religion poisons everything የተሰኘዉን አወዛጋቢ መፅሐፍ አሳተመ ። መፅሐፉ በጥቂት ጊዜያት ዉስጥ በዓለም አቀፍ የሽያጭ ዝርዝር ላይ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሆነ እንዲሁም በአድናቆት እና በትችት በኩል ሁለቱንም ያስተናገደ ስራ ሆነ ። ሂችን ይሄን መፅሐፍ ሲፅፍ የነበረዉ ዓላማ አንድን ሃይማኖት ሌላዉን በማሸነፍ ለማስተዋወቅ አልነበረም ይልቁንም ሁሉንም የተደራጁ ሃይማኖቶች በአንድ የምክንያት መስፈርት ለመፈተሽ ታስቦ የተፃፈ ነዉ ። " እምነት እዉነት ነዉ የሚለዉ በማስረጃ መረጋገጥ አለበት እንዲያ ሊረጋገጥ ካልቻለ ግን ለትችት መጋለጥ አለበት " በማለት አቋሙን ይገልፃል ። በዚህም መሰረት መፅሐፉን ስናነብ ወደ ሁለት ግዙፍ ጥያቄዎች ይወስደናል እነርሱም ፦ ሃይማኖት በእርግጥ የሰዉን ልጅ ያሻሽላልን ? ወይስ እንደ ሂችንስ አባባል ሁሉንም ነገር ይመርዛል ? ፅሁፉ ረዘም ስለሚል በሌላኛዉ ክፍል እነዚህን ጥያቄዎች እና የመፅሐፉን ዋና ዋና ክርክሮች በዝርዝር የማቀርብላችሁ ይሆናል ። በሶስተኛዉ ክፍል ደግሞ በተቃዋሚ ጎራ የተሰጡ ምላሾችን በመጠኑም ቢሆን የማቀርብላችሁ ይሆናል .... ይህን ያዘጋጀዉ ግለሰብ በየተኛዉም ጎራ አይገኝም ተቃዋሚም ደገፊም አይደለም ።

  • 26 июл.4 5371

    без подписи

  • 26 июл.5 62951

    без подписи