ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚
Статистикаይህ የኖህቶኤል ሀሳቦች የሚንፀባረቁበት ቻናል ነው። በማንበብ ብቁ እና ጤናማ እውቀት ያላቸውን ትውልድ እናፍራ! @noahtoael for anything https://telega.io/c/Noahtoaels_Idea I blog about marketing and sales Buy ads: https://telega.io/c/Noahtoaels_Idea
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Маркетинг
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 138
- 1/48двое суток
- 158
- 1/72трое суток
- 170
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
ሺዎች የሚወዱትን የንባብ ማህበረሰብ ይቀላቀሉ! በየቀኑ ምርጥ ታሪኮችን እያነበቡ አእምሮዎን ያዝናኑ። የቻናላችን አባል ለመሆን ሊንኩን ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Fiction_123
የሆነ ቀን የሙጥኝ ያልኩባቸው ነገሮች ደርሰው ከእጄ እንደገቡ ሲሰማኝ ሰው ነኝና ሰውነቴ መስመር ስቶ እንዳልንቃቸው ዋጋ እንደሌላቸው እንዲሰማቸው ፣ የውሀ ሽታ የሆነ ደስታም ተስፋም እንዳልሰጣቸው እሰጋለሁ ሰው ነኝና ሰውነቴን የሳትኩ ቀን ራስ ወዳድ የሆንኩ እለት ያቃኑኝን እንዳልሰብር የኖሩልኝን እንዳልገድል አጥብቄ እፈራለሁ ለዚህ ደግሞ መሸሽ ደጉ መሄድ ደጉ ሰውነቴን ለመቀበል ከሰው መራቅ በጀኝ ••• ••• ••• በሰምሐን……✍🏻
ከሰዎች ቁጥጥር ነጻ የመሆኛው መንገድ ሰዎችን ለመቆጠጠር በሞከራችሁ ቁጥር እናንተ በእነሱ ቁጥጥር ስር እየሆናችሁ ትሄዳላችሁ፡፡ ይህ የሚሆነው፣ ትኩረታችሁን በራሳችሁ ዓላማ እና ጉዳይ ላይ ከማድረግ ይልቅ እነሱን በመከታተል ላይ ስለምታሳልፉ ነው፡፡ ሰዎች ምርጫና ውሳኔያቸውን እንዲኖሩ ፍቀዱላቸው! መልካም ምሽት!!!
ሀዘን ቤቴ ሆኖ ሀሴት ይቀፈኛል፣ መወደድ መፈቀር መሳቅ እና ማረፍ፣ ዉሸት ይመስለኛል ዛሬን ደስ ካለኝ እንደው ፈገግ ካልኩኝ …አላቅም ብቻ ግን ከደስታ… ሀዘን ደስ ይለኛል
The Overview effect ለዘመናት የሰው ልጅ አእምሯዊና ስነ ልቦናዊ መዋቅር በወሰኖች፣ በጥበቃዎችና በክልከላዎች ግንብ የታጠረ ነበር። ማንነታችንን የምንተርከው በካርታዎች ላይ በሰፈሩ የድንበር መስመሮች፣ በጎሳና በፖለቲካ የጎራ ክፍፍሎች፣ እንዲሁም በጠበቡ የማህበረሰብ ቡድኖቻችን ጭፍን ወገንተኝነት (tribal biases) ነው። ሁላችንም እንደየምርጫችን የተሰነጠቀ መስታወት ይዘን ያንን የያዝነውን ስባሪ ብቻ ሙሉው ሰማይ አድርገን የመቁጠር ስህተት ውስጥ እንወድቃለን። ነገር ግን ከዚህ ከከበበን የዕለት ተዕለት ውክቢያ ወጣ ብሎ በጥቁሩና ማለቂያ በሌለው የህዋ ባዶነት ውስጥ ይህንን የሰው ልጅ የስባሪ አስተሳሰብ በአንድ ቅፅበት የሚያክም፣ የአመለካከት አድማስን ሙሉ በሙሉ የሚገለብጥ አንድ አስደናቂ ስነ ልቦናዊ ክስተት አለ፤ እርሱም {ኦቨርቪው ኢፌክት} (The Overview Effect) ይባላል። ይህንን ፅንሰ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ ያፈለቀው የህዋ ፈላስፋው ፍራንክ ኋይት ሲሆን፣ ክስተቱም ጠፈርተኞች መሬትን ከህዋ ምህዋር ላይ ሆነው በሚመለከቱበት ጊዜ የሚገጥማቸውን ጥልቅና ስር-ነቀል የአእምሮና የንቃተ-ህሊና መለወጥ የሚገልፅ ነው። ይህ የፕላኔታችንን ውበት ዝም ብሎ በአድናቆት መመልከት ብቻ አይደለም፤ ከዚያ በላይ የሆነ የሰው ልጅን መኖርና ምንነት ዳግም የሚመረምር ህልውናዊ መናወጥ (existential rupture) የሚፈጥር ነዉ። መሬትን ከሩቅ፣ ከናኘው የአፅንፈ-ዓለም ፀጥታ ውስጥ ሆኖ መመልከት ሁሉንም ነገር አቅፎ የያዘን አንድ ወጥና የተሟላ ስርአት እንደማየት ነው። እዚያ ላይ የፖለቲካ ድንበሮች፣ የብሄር ክፍፍሎች ወይም ቀጠናዊ አጥሮች የሉም። የሰው ልጅ በጥቃቅን ነገሮች ተከፋፍሎ የሚኖርበት ያ አሮጌ ቅዠት በአንድ አፍታ ይበራል፤ በእርሱም ምትክ ፍፁም የሆነው ሁለንተናዊ አንድነት ጉልህ ሆኖ ይታያል። ይህ ክስተት አእምሯችንን ነገሮችን ለያይቶና ነጣጥሎ ከማየት ወደ አጠቃላይ ስርአታዊ ውህደት እንዲሸጋገር ያስገድደዋል። በምድራዊ ህይወታችን የሰው ልጅ አስተሳሰብ በአብዛኛው የሚመራው {እኛ እና እነሱ} በሚል የጎራ ክፍፍል ነው። ይህ ደግሞ በዝግመተ-ለውጥ ሂደት ውስጥ ራሳችንንና ቡድናችንን ለመጠበቅ ከአባቶቻችን የወረስነው አሮጌ አሻራ ነው። ነገር ግን ይህ ክስተት ያንን ጥንታዊ መዋቅር ሙሉ በሙሉ ያፈርሰዋል። የ{እኛ} የሚለውን ትርጉም አስፍቶ የአፅንፈ-ዓለሙን የመጨረሻ ጫፍ እንዲነካ ያደርገዋል። ይህ ታላቅ ሽግግር በሶስት ዋና ዋና አእምሯዊ ለውጦች ውስጥ ያልፋል። በመጀመሪያ፣ ከህዋ ምህዋር ላይ ሆነው ሲመለከቱ በሰዎች ታሪክ ውስጥ ለብዙ ጦርነቶችና እልቂቶች ምክንያት የሆኑት ፖለቲካዊ መስመሮች ሙሉ በሙሉ የማይታዩና የሌሉ ይሆናሉ። በምድር ላይ በደም የተፃፉት ድንበሮች ውቅያኖሶችን፣ ከባቢ አየርንና አህጉራትን ብቻ ከሚያውቅ ፕላኔት አንፃር ሲታዩ ምንኛ የሞኝነትና የከንቱነት ማሳያ መሆናቸው በግልፅ ይጋለጣል። በሁለተኛ ደረጃ፣ ተመልካቹ ሰፊና ሁለንተናዊ ወደሆነ ማንነት ይሸጋገራል። ከዚያ በኋላ ግለሰቡ ራሱን የአንድ የተወሰነ ሀገር ዜጋ ወይም የአንድ ጠባብ ርዕዮተ-ዓለም አራማጅ አድርጎ ማየት ያቆማል። ይልቁንም በጥቁሩ ህዋ ውስጥ እየተጓዘች ያለች በውስጧ ህይወትን ያቀፈች አንዲት ደካማና ውብ የጠፈር መንኮራኩር አካልና ተጓዥ አድርጎ ራሱን ይቆጥራል፤ ይህንን {መርከባዊዋ-መሬት ንቃተ ህሊና} (Spaceship Earth) እንለዋለን። በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ፣ በግለሰቡ {እኔነት} እና በውጪው ዓለም መካከል ያለው ጠንካራ አጥር መፍረስ ይጀምራል። የአፅንፈ-ዓለሙ ግዙፍነት በአእምሮ ውስጥ ጥልቅ የሆነ ትህትናንና የመገረም ስሜትን ይፈጥራል። በዚህ ጊዜ ምድራዊና ጥቃቅን የሆኑት የዕለት ተዕለት ጭንቀቶቻችን በጠቅላላው ስርአት ውስጥ ቀልጠው ይጠፋሉ፤ በእነርሱም ምትክ ለዚህች ፕላኔትና በውስጧ ላለው ህይወት ሁሉ ጥልቅ የሆነ የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነት ይተካል። ይህ ስነልቦናዊ ክስተት የሰዉ ልጆች ምን ያህል መሻሻል የሚችል {progressive} የሆነ ዝግመተ-ለዉጣዊ የስነ ልቦና አጥሮች እንዳሏቸዉ በዉል ማረጋገጥ የቻለም ጭምር ነዉ።
без подписи
без подписи
ትርፍ ጊዜዎን የሚያስደስት አዲስ ልማድ ይጀምሩ! በየቀኑ በሚለቀቁ ድንቅ ታሪኮች አእምሮዎን ያዝናኑ፣ እውቀትዎን ያዳብሩ። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Fiction_123
без подписи
እህታችን ትፈልገናለች እንድረስላት 🙏 የምትመለከቱዋት ወጣት ታዳጊ ኤልሮኢ ቅዱስ ትባላለች በአጥንት ካንሰርን ህክምና ላይ ትገኛለች በሽታው ከታወቀ አንድ አመት ሆኗታል በበሽታው ምክንያትም የግራ እጇ ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ተደርጓል ሆኖም ግን ኤልሮይ ተስፋ ሳትቆርጥ ህክምናዋን እየተከታተለች ነው አሁን ግን በሽታው ወደ ሳንባዋ በመሠራጨቱ የመተንፈስ ችግር ስላጋጠማት በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ Heal Venture Medical and Surgical Center በ ICU ትገኛለች CBE - 1000487578828 TeleBirr - 0911179293 Awash Bank - 013471629151800 ሁሉም አካውንት ስም - Rahel Aregay
አለምን የምናያት እንደ እውነታዋ ሳይሆን እንደ ውስጣችን ብርሃን ነው ትሁት መሆን እፈልጋለሁ ፣ ለክፋት በደግነት ፣ ለጩኸት በዝምታ ምላሽ የምሰጥበት ልብ እንዲኖረኝ እመኛለሁ Positive thinking isn't about ignoring the struggle; it's about mastering your reaction to it. My goal is to be a sanctuary of peace in a world full of noise. 🏛️🥀
የንቃተ-ህሊናህ አስተምህሮ ከሌሎች አስተምህሮቶች የሚለየው ነገ ከነገ ወድያ የሆነ ነገር ስታገኝ፣ የሆነ ባታ ላይ ስትደርስ የሆነ ነገር ስትሆን፣ ከዛም ደስታን ሀሴትን፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ መሞላትን ታገኛለህ ብሎ ያ ቃልን አይገባልህም ተስፋንም አይሰጥም። ለሁሉም ጊዜው አሁን ነው!!!
ልብ የሚነኩ፣ ሳቅ እና እንባ ያዘሉ ድንቅ ልቦለዶች ከገፀ-ባህሪያቱ ጋር አብረው የሚኖሩበት ልዩ የንባብ ቦታ። አሁኑኑ ይቀላቀሉን 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Fiction_123
እየኖራችሁ 🥹
እየኖራችሁ 🥹
ስሙ ሰዎች ታሪክ ልጀምርልቻሁ እንዴ ማለቴ በትረካ አንድ መፅሀፍ ላስጨርሳችሁ እእ ምን ታስባላችሁ ምን ያህል ሰው ይፈልጋል ራሴ እየተረኩኝ በpart አንድ ቆንጆ መፅሀፍ ላስጨርሳችሁ?
Hey everyone! 👋🏻 I’m Vita, one of the new admins here.......🤍 Happy to be part of this channel. Stay tuned! 😊
ስሙ ሰዎች ታሪክ ልጀምርልቻሁ እንዴ ማለቴ በትረካ አንድ መፅሀፍ ላስጨርሳችሁ እእ ምን ታስባላችሁ ምን ያህል ሰው ይፈልጋል ራሴ እየተረኩኝ በpart አንድ ቆንጆ መፅሀፍ ላስጨርሳችሁ?
ማሳሰቢያ ይህ መጽሀፍ ከመጭበርበር ዠጄዎች ለመከላከል እንጂ ሰውን ለማጭበርበር አይደለም የተጻፈው ዳርክ ሳይኮሎጂ (Dark Psychology) ወይም ስውር ሥነ-ልቡና፣ ሰዎች ሌሎችን ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለመቆጣጠር፣ ለማታለልና ተፅዕኖ ለማሳደር የሚጠቀሙባቸውን ድብቅ እና ተንኮል አዘል ዘዴዎች የሚያጠና የሥነ-ልቡና ዘርፍ ነው። በዚህ ርዕስ ዙሪያ የሚጻፉ መጽሐፍት ዋና ዓላማ አንባቢዎች የማጭበርበር (Manipulation) ሰለባ እንዳይሆኑ ራሳቸውን እንዲከላከሉና የሰዎችን ድብቅ ማንነት እንዲረዱ ማገዝ ነው። የዳርክ ሳይኮሎጂ መጽሐፍትን ይዘትና ዋና ዋና ነጥቦች በጥንቃቄ የተነተነ ዳሰሳ ከዚህ በታች ቀርቧል። 1. የዳርክ ሳይኮሎጂ አራት ምሶሶዎች (The Dark Tetrad) መጽሐፍቱ የሰዎችን ክፉ ባህሪ ለመረዳት አራት ዋና ዋና የስብዕና ጉድለቶችን (Personality Traits) ያስረዳሉ፦ ናርሲሲዝም (Narcissism): ራስን ብቻ መውደድ፣ ከመጠን በላይ ታዋቂነትን መፈለግ እና ለሌሎች ስሜት ግድ አለመስጠት። ማኪያቬሊያኒዝም (Machiavellianism): የራስን ፍላጎት ለማሳካት ማንኛውንም ዓይነት ማታለል፣ ውሸት እና ስውር ዘዴ መጠቀም ህጋዊ ነው ብሎ ማመን። ሳይኮፓቲ (Psychopathy): ለሌሎች ሰዎች ምንም ዓይነት ርኅራኄ ወይም የጥፋተኝነት ስሜት አለማሳየት እና ጨካኝ መሆን። ሳዲዝም (Sadism): ሌሎች ሰዎች ሲጎዱና ሲሰቃዩ በማየት መደሰት። 2. መጽሐፍቱ የሚያጋልጧቸው ዋና ዋና የማታለያ ታክቲኮች (Manipulation Techniques) በነዚህ መጽሐፍት ውስጥ ሰዎች ሌሎችን ለመቆጣጠር የሚጠቀሙባቸው ስውር ስልቶች በዝርዝር ይዳሰሳሉ፦ ጋዝላይቲንግ (Gaslighting): ተጎጂው ስለ ራሱ ማስታወስ ችሎታ፣ አስተዋይነት ወይም እውነታ ጥርጣሬ እንዲያድርበት በማድረግ አእምሮን የመቆጣጠር ዘዴ። የፍቅር ቦምብ መጣል (Love Bombing): መጀመሪያ ላይ ከመጠን በላይ ፍቅር፣ ስጦታ እና ትኩረት በመስጠት ሰውን ማጥመድ እና በኋላ ላይ ግንኙነቱን ለመቆጣጠር ያንን መከልከል። ጥፋተኝነትን ማጋባት (Guilt Tripping): አንድ ሰው ሁልጊዜ ስህተት እንደሰራ እንዲሰማው በማድረግ የሚፈልጉትን ነገር እንዲያደርግ ማስገደድ። የዝምታ ቅጣት (Silent Treatment): ከሰውየው ጋር መነጋገር በማቆም ከፍተኛ የጭንቀት ስሜት መፍጠር እና እጅ እንዲሰጥ ማድረግ። 3. የመጽሐፍቱ ጠቀሜታ (The Value) ራስን መከላከል፦ ስውር ጥቃቶችን እና የማታለያ ወጥመዶችን ቀድሞ በመንቃት ከአእምሮ ብዝበዛ መዳን። የሰዎችን ባህሪ ማንበብ፦ በቃላት ከሚነገረው በስተጀርባ ያሉትን እውነተኛ ፍላጎቶች እና የሰውነት ቋንቋዎችን መረዳት። ግልጽ ድንበር ማበጀት፦ በግንኙነቶች ውስጥ ተገቢ ያልሆኑ ተፅዕኖዎችን በመለየት "አይሆንም" የማለትን ጥበብ ማዳበር። 4. ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች (The Critical Caveat) የዳርክ ሳይኮሎጂ መጽሐፍትን ሲያነቡ ትልቁ አደጋ፣ እውቀቱን ሰዎችን ለመጉዳት ወይም ለመበቀል መጠቀም መጀመር ነው። ዋናው ግብ የመከላከያ ጋሻ መታጠቅ እንጂ ሌሎችን የሚያጠቃ "መሣሪያ" መያዝ መሆን የለበትም ። https://t.me/Amharic_Books_storee ማሳሰቢያ ይህ መጽሀፍ ከመጭበርበሩር ዠጄዎች ለመከላከል እንጂ ሰውን ለማጭበርበር አይደለም የተጻፈው 📚 ማጋራት አይዘንጋ !