tgindex
📚 አዳም ረታ ™

📚 አዳም ረታ ™

Статистика
@AdamuRetaанглийский

Quotes ✒️ | Reviews 📝 | Poetry 📖| Research | Literary Discourse A hub for readers and thinkers. 📚

Последний пост
09:05
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
26
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 502
+16 за 3 дн.
Сутки
+9
+0,26%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
897
25 постов
Вовлечённость
25,6%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 26
Упоминаний
3
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
325
1/48двое суток
372
1/72трое суток
401

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 09:0513692

    видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • የዱር አበባ ዝምታ (የመንገደኛ አንባቢ ግብዣ) ይህቺን ሰሞን “የዱር አበባ” መኾን የሚመኘውን የሞክሼዬን የቴዎድሮስ ካሳን ግጥሞች እየገረብኹ ነው፤ ስለወደድኳቸው። “የዱር አበባ” ቴዎድሮስ ካሳ ( Tewodros Kassa) በ2017 ዓ.ም. ያሳተማት፣ የግጥሞቹን ስብስብ የያዘች መጽሐፍ ናት። ቢሮ <-> ቤት ስመላለስ እያነበብኳት፣ አንዳንድ ነገሮች ገርመውኝ በእርሳስ ሳሰማምርባት ሰነበትኹ። እንዲያው ለግጥም ቀልብ ያለው ጎበዝ በጥልቀት ቢያነባቸውና ቢያመሳጥራቸው ብዬም እየተመኘኹ፣ ዐይኔ የገባውን ላካፍላችኹ። “ሕይወት”፣ ቅዝቃዜ፣ ዝምታ፣ ሕማም ይበረታባቸዋል፤ እንደዋዛ ልብ እንዳልኩት “ሕይወት” የሚለው ቃል የሌላቸው ግጥሞች ሦስት አራት ቢሆኑ ነው። ሕማሞቹ ሳይወዱ በግድ የሚጋቡ፣ የተረሳ/የሻረ ቁስል ሳይቀር የሚነካኩ ናቸው። ስንኞቹ በዝምታ ማዜምን፣ በዝምታ መቀኘትን፣ በዝምታ መጮኽን የሚቃትቱ ናቸው። አስረጅ ይኾኑን ዘንድ እነዚህን ስንኞችና አንጓዎች እንያቸው፦ ጡንቻዬ ፈርጥሟል ብቻ በሆንኩበት ትንሽ ፈገግታና ብዙ ዝምታ ነው ጥሩ ኑሮ ማለት። (“በሪ ጠፊ ፍቅር”) *** አካልህን ጥለህ ሁነው ለሌቱ ኩል፤ ግጥም መጻፍ ልመድ ፤ በዝምታህ በኩል። (“የሌሊት ሹክሹክታ”) *** ደንሱ ምሽቱ ሳይጎህ፤ አንጎራጉሩ ድምፅ ምን ያሻል!? ልባችሁ ከልቤ ላይሻል፤ የዝምታን [እሩ---ቅ] መንገድ አትጋፉት ተዉት ይቅር፤… (“የአብሮነት መለከት”) *** ምርጥ ግጥም ማለት በሁለት ፍቅሮች መኃል ያለ ዝምታ ነው። (“እነኾ የሰው ልጅ…”) እነዚህ መንገድ ለመንገድ ሳነብ ምልክት ያደረግሁባቸው #ዝምታ በቀጥታ የተጠቀሰባቸው ስንኞች ናቸው። መጽሐፏ ግን ቃሉ ሳይጠራ (implicitly) ዝምታ የተናፈቀባቸው ሌሎች አንጓዎችና ስንኞችም አሏት። በስንኞች የተቀመሩ ርእሶቹ፣ ዐዳዲስ ምሰላዎቹ፣ የስሜት አያያዙ ለቴዲ መለዮዎቹ ይመስላሉ። ግጥም ተንታኝ ከ“ማኮብኮቢያ”ው እስከ ማረፊያው ያሉትን ኅፅን በኅፅን አንብቦ እንዲተነትናቸው፤ ሊሪካል ግጥም አፍቃሪውም ስሜት በስሜት አዳምጦ እንዲደመምባቸው እጋብዛለሁ። በርታ ሞክሼ! ©️Tewodros_Atlaw

  • 8 авг.962223

    ስብሃት:- ''የሚጥል በሽታ ነበረብኝ። የእኔ እንደ ዶስቶየቪሲኪ እያነሣ የሚያፈርጥ አይነት አይደለም። እኔ ላይ የደረሰብኝን ወንድሞቼ እንደነገሩኝ ሌሊት እነሳና በኃይል! በኃይል እጮሃለሁ። ተነስቼ እሮጣለሁ። ይዘውኝ ያስተኙኛል። ጡንቻዬ ደግሞ የዛን ጊዜ በጣም ጠንካራ ነው። ጠዋት ስነሣ በጣም ድክም ያደርገኛል። አንዳንዴም ጉንጬን እነክሳለሁ። አንዳንዴ ጧት ስነቃ ለመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሰከንዶች ማን እንደሆንኩና የት እንደሆንኩ አላውቅም። በዚህ በሽታ ምክንያት ልጅ ላለመውለድ ወስኜ ነበር። ዘነበ ወላ : ''ለምን?'' ስብሃት : በምወልደው ልጅ ይተላለፋል የሚል እምነት ነበረኝ። ዘነበ ወላ : ባለቤትህ በዚህ ተስማማች?'' ስብሃት : ምን አማራጭ አላት? የሚቸልኮትስ ቼርማን እንደ አባቷ ነበር። ኤውሮፓ ውስጥ ከሚገኙት አራት ዋነኛ የንዲህ አይነት በሽታዎች እስፔሻሊስት አንዱ ከሆነው ሀኪም ጋር ሚስተር ዲክ ቀጠሮ ያዘልን። ''በሽታህ በዘር አይተላለፍም'' አለን ''ነገር ግን ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ኤፕሌፕቲክ ለመሆን ሦስት ከመቶ እድል አለው። ስለዚህ ምናልባት ያንተ ልጅ ኤፕሌፕቲክ ቢሆን፣ ሎተሪው ሦስት ከመቶው ደርሶት ነው እንጂ ካንተ ወርሶት አይደለም'' አለኝ። መድኃኒት አዘዘልኝ በቀን አንዴ ጊዜ የሚዋጡ። ''ለብላታ ደሬሳ ያመኛል ሳልላቸው ላማክራቸው ወሰንኩ። ይህ በሽታ በእኛ ሀገር <የባርያ በሽታ> ይባላል። አነሣሁና ጠየቅኳቸው። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንደ ማርኮ ፖሎ ጉዞ ከአንድ ሰአት በላይ በባርያ በሽታ ትንታኔ ይዘውኝ ተጓዙ። በመጨረሻ መልሣቸው እኔ ሠርቼበት አላውቅም ሆነ። እንደኔው የሀገራችንን መድሃኒት የሚያውቅ ጓደኛዬ እገሌ እንደነገረኝ ብለው አንድ መድሃኒት ጠሩ። ተጠቀምኩባት። ብዙም ሳልቆይ ከበሽታዬ ዳንኩኝ። ኬኒኑን መዋጥ አቆምኩ። ከሃና ጋርም የመጀመሪያ ልጃችንን ያለምንም ስጋት ለመውሰድ ተስማማንን። ዘነበ : መድሃኒቱን ብትነግረኝ ስብሃት : ታስሬበታለሁ ዘነበ : ለምን? ስብሃት : ፖሊስ ተወው ብሎ ዘነበ : በሕግ የተከለከለ ነው? ስብሃት : ይላሉ ዘነበ : ታዲያ አንተ በተፈጥሮህ ሕግ አክባሪ ሰው ነህ ለምን ሕገ ወጥነቱን መረጥከው? ስብሃት : መድሐኒቴ ከሕመም ፈውሶኛል። ደስታንም ይፈጥርልኛል። ዘነበ : መድሃኒቱን አልነገርኸኝም ስብሃት : አንዳንዱ ሰው በሰው ሕይወት ውስጥ ገብቶ ይፈተፍታል። ዘነበ : በምን? ስብሃት : ደግሞ እኮ ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው ሲል ትሰማዋለህ ዘነበ : አልገባኝም? ስብሃት : ግን የእኔም በባሕሪዬ አደባባይ መሆን የጎዳኝ መሰለኝ ዘነበ : አዎን እንደሀበሻ በአደባባይ ተከናንበህ ጨለማን ተገን አርገህ የልብህን መከወን ስብሃት : እንደዛ ነው የሚደረግ፣ ሰው ምን ይለኛል እያልክ ዘነበ : መድሃኒቱን ግን አልነገርከኝም ስብሃት : አልነግርህም ዘነበ : ለምን? ስብሃት : ዘነበ አምንሃለሁ። አንተም ሌላ የምታምንም ወዳጅ አለ። ስለዚህ ትነግረውና ሳይታወቅ መድሐኒቱን ታረክሱብኛላችሁ። (ማስታወሻ - ዘነበ ወላ)

  • видео или голосовое, без подписи

  • 8 авг.659103

    ‹‹በአንድ በኩል ስታስበው ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀምጦ እኔ የትግራይ ሰው ነኝ፣ እኔ አማራ ነኝ ብሎ አፍ ሞልቶ መናገሩም አለማወቅ ይመስለኛል፡፡ በሴት አያቶቻችን በራፍ ላይ ማን እንዳለፈ ስንቶቻችን ነን የምናውቀው? የእኔን ጥሩ ኦሮሞነት እግዚአብሔር እና የሴት አያቶቼ ናቸው የሚያውቁት፡፡ የሁሉንም እንዲሁ፡፡››¹ «ወደድንም ጠላንም በመኖር ኪነጥበብ ተነካክተናል።»² 1 ሰሎሞን ደሬሳ 2 አዳም ረታ

  • видео или голосовое, без подписи

  • 31 июл.1 098218из Jafbok

    የተወዳጁ አዳም ረታ አዲሱ መጽሐፍ ነገ ቅዳሜ በሁሉም የጃዕፈር መጻሕፍት መደብሮቻችን ለሽያጭ ይቀርባል :: በቅርብ ቀናት ደግሞ ከደራሲ አዳም ረታ ጋር በመነጋገር የፊርማ ስነስርአት ዝግጅት ይኖረናል :: በድጋሚ ለማሳወቅ ያክል በአዲስ አበባ ኤግዝቢሽንና ባዛር ላይ አልተሳተፍንም :: ምክንያቱንም ሌሎች ተሳታፊዎች ከከፈሉት እጥፍ ክፈሉ ስለተባልን ነው :: ይህንንም በተደጋጋሚ የምናሳውቀው ጃዕፈር መጻሕፍትን ብላችሁ ሄዳችሁ ውድ ጊዜያችሁንና ገንዘባችሁን እንዳታባክኑ በማሰብ ነው :: ከመደበኛው ሽያጭ ባለፈ ባሉን ሁሉም ቅርንጫፎቻችን እስከ እሁድ ድረስ ልዩ ቅናሽ አድርገናል ይህን አጋጣሚ ተጠቅማችሁ ከ 30% እስከ 50 % ቅናሽ መጻሕፍትን መሸመት ትችላላችሁ :: እናመሰግናለን !

  • 28 июл.1 364195

    እስቲ ዛሬ ደግሞ ለለውጥ ያክል አለቃ ክንፌ የላኩልኝን ግጥም መሳይ ምክር ልጋብዛችሁ! ©️(በዕውቀቱ ስዩም) (ለለጅ ምክር የአባት መታዘቢያ) ልዠ ሆይ! ሙቫይልህን አስቀምጥ ምክሬን አድምጥ ! ጦርነትን የሚጠምቀው እድሜውን ብትጠይቀው የማቱሳላ ገራዥ የአብርሀም ዣንጥላ ያዥ በጎሽ ያረሰ አዳምና ሄዋን ገምጠው የተፉትን በለስ አንስቶ የጎረሰ የሎጥን ሚስት ሀውልት የላሰ ሆኖ ታገኘዋለህ ፤ ልዠ ሆይ! ጦርነትን የሚያውጀው ያረጀው ነው የጃጀው ግና ጦርሜዳ ላይ የሚዋጋው ያንተ ብጤ ነው ለጋው፤ ሜሲ አንደመታት ኩዋስ ወደ መቃብር የሚልለጋው፤ ልዠዋ! በጀግኖች ዘመን እንኩዋ-“ከመሞት መሰነበት” ይባላል የሰማእት ሀውልት ሆኖ ተመቆም ህያው ሆኖ መተኛት ይሻላል ልዠ ሆይ! በሀያላን እንዳትታፈስ ሁንባቸው መንፈስ መንፈስ መሆን ቢሳንህ ; ሁንባቸው የጎመን ፈስ ቀን እስኪያልፍ ድረስ ወደ ጎረቤት አገር ንፈስ፤ ልዠ ሆይ ! ጦርነት ማለት አንድ ሀሙስ የቀራቸው ሸባዎች፣ አንድ ሀሙስ ብቻ የኖሩትን አበባዎች የሚያስቀጥፉበት አዝመራ ነውና በሰማእትነት ስም ምትክ አልባ ሕይወትህ ሳይከስም እሸት አካልህን ሳይለውጡት ወደ ፍግ ተግተህ አፈግፍግ፤ ልጄ ሆይ! ለማንም ኩስለመናም ነፍስ ይማር ለማለት አንኩዋ ጊዜ ለሌለው የሙቫይልህን ካሜራ አንጂ ጠመንጃህን አትወልውለው፤ አለቃ ክነፌ በተሳትፎዎ ይቀጥሉበት!

  • 27 июл.979127из literatureandpoet_ry

    "Sisyphus & Jesus" by artist Saeed Sadeghi

  • °°°ሜታሞደርኑ ስብሃት_በሌቱም አይነጋልኝ°°° °°°°(Sebhat__The Metamodern)°°°° ከመረዳታችን የቀደመ ቅንነት፣ምስቅልቅልን የሰደረ ባለጥበብ፤ ሁሉ በውቤ በረሃ ሊሰሙት የከበደ፣ጆሮን ጭው የሚያደርግ ቢሆንም፤ በንፁህ የዋህነት እሞክረዋለሁ ያለው ስብሃት ገ/እግዚአብሄር _ ደስታ አልባ ኑረታችን ውስጥ ሁሉ እንደ ምናነውረው ስራ የመጨረሻውን ዝቅተኛ የማህበረሰብ ደረጃ የምትወክል፣የብዙ ነገር ርሃብና ጥማት ያረበበባት በረሃ ጥገኛ ሆኖባት ራሱን በመስጠት በሁለት ፅንፍ ቆመን እንዳንሰበር ሲያስታርቅ የተራቀቀበት ምናቡ መዳረሻ... 'ውቤ በረሃ' የሌቱም አይነጋልኝ መሥፈሪያ ደሴት ሆና ተገኝታለች።በስብሃት ትዝብት እና መገረም ውስጥ የተከለለ (ፈረንሳይ በነበረበት ጊዜ በብርቱ ያደንቀውና ያነበው የነበረው) Albert Camus አልያም Emile Zola አለ። በ Naturalist' ምልከታው እድገትና ለእነዚህ ጠቢባን ባለው አድናቆትና የበዛ ንባብ ያዳበረው የውስጥ ዝምታ ማንም ሴት በሸር*ጣነት ብትቀርበው በሴትነት ሊመለከታት፤ በእንባ ብታስደነብረው በሽሙጥና ቀልዱ ህይወትን እንዲዘራባት አስችሎታል።(Camus believed that the essence of man was irrational and life is nonessential, but one should face life with a sort of courageous humanism).ይህንን ስብሀት ይጋራዋል።ለሱ ግን ሁሉ ሚቀበሉት ነው በዝምታ ሚያስተናግዱት ልክ እንደ ካሙ ሲሲፈስ (sisiphus but even still all is OK within him). ይህንን እውቀቱን ለኛ የሰጠበት መንገድ ዘመናዊነትን ከድህረ ዘመናዊነት ያስታረቀ ሆኖ አጊንቼዋለሁ።ለሁሉ በመሠጠትና በዝምታ በመታዘብ ችሎታው እውነተኛውን የወሲብ ፍላጎቱን ሳያግድ እውነታዊ ልቦለዱን (Naturalist fiction) ሌቱም አይነጋልኝን ከትቧል። ይህን መልኩን ሰለሞን ደሬሳ እንዲህ ብሎ ገልፆታል(“He has successfully managed to make perversity rub shoulders with sanctity and find explosive humor in the quiet shortcomings of the national character"). በማሚት እሹሩሩ ቤት ለስብሃት የሚታየው ውርደት፣ዘማዊነት፣ፀብ እና ክብሯን የማትጠብቅ ሴት አይደለችም።መኖር በተጣለበት የሰው ልጅ የማያልቅ የስጋና የነፍስ ፍላጎት እስር ሰበብ የሚሸጡ ሴቶችን ከገምድል ፍርድና ከማህበረሰብ የሞራል ጥያቄ አፈንግጦ የታዘበበት ጥልቀት ታሪኩን ውብ አርጎታል።የድርሰቱ መዳረሻ ግን ሴተኛ አዳሪዎችን ከወንደኛ አሳዳሪዎቻቸው ጋር መተረክ አይደለም።በርካታ መጠይቆች አሉት።እውነትን ፍለጋ ይሰማራል። "...ሕይወት እንደ ቡና በወተት ነው።ወተቱ እውነት ቡናው ውሸት ይሁን።ግን ይሄ ልዩነት በአንጎላችን ውስጥ ይኑር እንጂ ሲኒው ውስጥ ባንድ በኩል ቡና በሌላው ወተት የለም።" ሌቱም አይነጋልኝ ገጽ-212 እውነትና ውሸትን ብቻ አይደለም ክብርና ፀበኝነትን፣ ቅናትና ፍቅርን፣ብቸኝነታቸውን ለማምለጥ በሚጥሩ ግን ደሞ የእለት እንጀራቸውን ያላገኙ ሰዎች አንፃር ያስቃኘናል።ይህ ሁሉ የመኖር ጥያቄ ወጣት መሆናችን እንዳታልፍ በመፍጨርጨር ውስጥ ቢሆንም 'የወጣትነት ጥቅታ' ከብጉር ወደ ማድያት የምንሄድበት የህይወት ፍጥነት፤እሱንም ስብሃት ድንቅ አድርጎ ተጠቦበት አይቻለሁ። "እርጅና ሳስበው ያስጠላኛል። አየህ፣ አሁን ወጣት ነኝ። ቆንጆ ነኝ። ወንዶች ውሀ ይሆኑልኛል። የጠየኩትን ይከፍሉኛል። ግን ቁንጅና እንደ ፍሬ ነው። እየበሰለ ሲሄድ በጣም ያስጎመጃል። አንድ ሀሙስ ቆይቶ ይበስላል፣ ይረግፋል። መልኬ ሲጨማደድ፣ ቁንጅናዬ ሲረግፍ ምን እሆናለሁ? ያኔ 'ንግዲህ ወንዶች አይፈልጉኝም፣ የሚጦረኝ ልጅ የለኝም። ምን እሆናለሁ? እንደ 'ንኮዬ ወለቱ ሰው ቤት እንጀራ 'ጋግራለሁ? ምን እሆናለሁ? እየዞርኩ እለምናለሁ? እርጅናው እየተጫጫነኝ፣ እግሬ አልሸከምሽ እያለኝ ሲሄድስ? ብቻዬን መንገድ ዳር ኩርምት ብዬ እለምናለሁ? ምን እበላለሁ? ከማን ጋር እነጋገራለሁ?" ሌቱም አይነጋልኝ ገጽ-269 በመጨረሻም ምእራፍ ሰባት ተኩል_ 'መጪው ትውልድ' ብሎ ባስቀመጠው ምእራፍ መግቢያ ላይ ባለች የ Robert Browning አባባል ልጨርስ "Ah, but a man's reach should exceed his grasp, or what's a heaven for?" -ሰው ከሚደርስበት በላይ መንጠራራት ይገባዋል ፤ እንዲያ ካልሆነማ መንግስተ ሰማያት ምን ፋይዳ አለው?" ©️ Dehab

  • 23 июл.1 027256

    ወጣቶች ነበርን በእውቀቱ ስዩም ----------------------------- ጊዜ ሲራመድ ኮቴው ድምጥ አልባ ከየት ተነስቶ ወደ የት ገባ ከየት ተነስቶ ወዴት ደረሰ ጠጉር መንጥሮ፣ ፊት እያረሰ፤ ወጣቶች ነበርን ቅጽር የሰራን ፤ አምባ የሰበርን ኮካ ኮላውን ባሲድ በርዘን ብንጎነጨው፤ የማይመርዘን፤ በራዱን ያጋልን፣ ሙት ልብ ያስነሳን ግራዋ በልተን ፤ ሎሚ ያገሳን፤ ተስፋችን ብዙ፤ እድሚያችን ለጋ ስንሰማራ፣ ትርጉም ፍለጋ ገላችን አይፈዝ፣ ጭቃ ቢለሰን የማናስቀይም፤ ቡትቶ ለብሰን ገጻችን ብሩህ፤ ልባችን ሽፍታ ስንመነጠቅ፤ ወደ ከፍታ የስኬት ገነት፣ ደጃፏን ከፍታ ምትቀበለን ፣ እየመሰለን ከቁመታችን በላይ፣ የዘለልን፤ ወጣቶች ነበርን ዛሬ እንደዋዛ ዘንድሮን ምሰን፤ ታችአምናን ቀበርን።

  • 23 июл.89910из wisdomseker

    ጦቢያ:- በሕይወትዎ ውስጥ የሚናፍቁትና የሚጠሉት ነገር ምንድነው? የሚያስቀናዎትስ ነገር አለ? ሎሬት ፀጋዬ፦ ጥበብ ይናፍቀኛል። ተቻችሎ መኖር የሚያውቅ ሕዝብ ያስቀናኛል፡፡ ድንቁርና ያስፈራኛል፡፡ ጦርነት ደሞ ያስጠላኛል፡፡ አባቴ ከማይጨው ሳይመለሱ ገና በአራስነቴ ያባቴን ቤት የጣልያን ባንዳዎች ስላቃጠሉትና እናቴ ወይዘሮ ፈለቀች ዳኜና ታላቅ እህቴ ወይዘሮ አስካለ ገብረመድሀን ብቻቸውን በአገልግል አዝለውኝ ስለተሰደዱ ይመስለኛል እሳት፣ ጦርነትና ስደት የሚያስጠላኝ። (ፈገግታ) © ጦቢያ መጽሔት 1990 ዓ.ም 📚

  • 23 июл.1 01952

    A Poem Is A City a poem is a city filled with streets and sewers filled with saints, heroes, beggars, madmen, filled with banality and booze, filled with rain and thunder and periods of drought, a poem is a city at war, a poem is a city burning, a poem is a city under guns its barbershops filled with cynical drunks, a poem is a city where God rides naked through the streets like Lady Godiva, where dogs bark at night, and chase away the flag; a poem is a city of poets, most of them quite similar and envious and bitter… a poem is this city now, 50 miles from nowhere, 9:09 in the morning, the tast of liquor and cigarettes, no police, no lovers, walking the streets, this poem, this city, closing its doors, barricaded, almost empty, mournful without tears, aging without pity, the hardrock mountains, the ocean like a lavender flame, a moon destitute of greatness, a small music from broken windows… a poem is a city, a poem is a nation, a poem is the world… and now I stick this under glass for the mad editor’s scrutiny, and night is elsewhere and faint gray ladies stand in line, dog follows dog to estuary, the trumpets bring on gallows as small men rant at things they cannot do. Charles Bukowski

  • видео или голосовое, без подписи

  • the Master Plan: starving in a Philadelphia winter trying to be a writer I wrote and wrote and drank and drank and drank and then stopped writing and concentrated on the drinking. it was another art-form. if you can't have any luck with one thing you try another. of course, I had been practicing on the drinking-form since the age of 15. and there was much competition in that field also. it was a world full of drunks and writers and drunk writers. and so I became a starving drunk instead of a starving writer. the best thing was the instant result. and I soon became the biggest and best drunk in the neighborhood and maybe the whole city. it sure as hell beat sitting around waiting for those rejection slips from The New Yorker and The Atlantic Monthly. of course, I never really considered quitting the writing game, I just wanted to give it a ten year rest figuring if I got famous too early I wouldn't have anything left for the stretch run like I have now, thank you, with the drinking still thrown in. ~ Charles Bukowski

  • видео или голосовое, без подписи

  • 21 июл.1 0941

    <unknown> – Mulugeta_Tesfaye_The_Poet-2

  • 20 июл.1 307133

    ◉ የእዮባ ጥያቄ [Missing someone ] እዮብ ምሕረተዓብ ዮሐንስ አምለሶም... ደፋር፣ ነገሮችን ሳያሽሞነሙን ወይደሞ ሳይሸፋፍን ፊት ለፊት የሚያስቀምጥ ፀሀፊ ነበር። የራሱን የስነፅሁፍ ዘውግ «ቀደዳ» ብሎ የቀደደ ነው። ነገሮችን በአዲስ መንገድ ለመመልከት ንቁ የሆነ አእምሮ ያለው... ጨዋታ አዋቂ ነው። በፅሁፎቹ እዮባ ራሱን መስሎ ራሱን ኮርጆ የዘለቀ ነው። የእሱ የግሉ ብቻ የሆኑ አገላለፆች ያሉት። «የዝንጆሮ ፌደራሊዝም... የኤቲስቱ ገብርኤል... ቀይ ሞንዳላ ...አትፍዘዝ ታመጣለህ መዘዝ...ጥሬ ሀቅ ነው ዋጠው!...» ብዙ ብዙ... ◉ ይሄ ሰው አንዲት መፅሐፍ ብቻ ሰጥቶን እንደሄደ ሳስብ እቆዝማለሁ። ግን ደግሞ ይቺው አንድ መፅሀፍ እንደ ዶላር የምትመነዘር ስራ መሆኗን ስረዳ እፅናናለሁ። «ቼ በለው!» በጣም ፀዴ መፅሐፍ ናት። ከዚች መፅሐፍ ደግሞ አንድ የሚያስገርመኝ ስቶሪ አለ። ደጋግሜዋለሁ ብዙ ግዜ። "Gender - of the Urban Context" ይሰኛል። የከተማ ህይወት በሴቶችና ወንዶች ግንኙነት ላይ ያለውን ተጽዕኖን ይፈተፍታል። የዘመናዊነት እና የማንነት ቀውስን ያስተነትናል። እና እኔ ቀደዳ ብቻ አድርጌ አላየውም። ጥናታዊ ፅሁፍም ይመስለኛል። እንዴት? ➊ ታሪኩ በአጭሩ ይሄን ይመስላል? ታሪኩ ሂሩት ስለምትባል የተማረችና በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ ስለምትሰራ ስኬታማ ሴት ይተርካል። ግና...ቅሉ...ህይወቷ በተከታታይ ውድቀቶችና ስብራቶች የተሞላ ነው። ● ሂሩት ከራሷ በታች ለነበረ ነገር ግን ጎበዝና ታታሪ ለሆነ ወንድ የትምህርትና የኑሮ ወጪውን በመሸፈን፣ አስተምራ አሰልጥና ሰው አደረገችው። እሱ ግን እግሩ ተውተርትሮ እንደቆመ ፍላጎቶቹና የሴቶች ምርጫው እየጨመረ ስለመጣ እሷን ክዶ ሌላ ጓደኛ ይዞ ጥሏት ሄደ። ​ ● በወንዶች ላይ ባደረባት ከፍተኛ ጥላቻ የተነሳ "Radical Feminist" ሆነች። ወንዶችን ማጥላላትና መጠየፍ ጀመረች። እዮብ ይሄንን የተሰማትን የወንድ ጥላቻ በአይረሴ ቃላት አስፍሮታል። «ብቻዋን አልቀረችም። መሰሎቿንም ፈላልጋ አገኘች... ባል፣ ጓደኛ፣ መልክ፣ ወጣትነት፤ ፈገግታ፣ ወግ፣ አመል Femininity፣ ደስታ፣ ፍቅር፣ ሰላም፤ ፈላጊ፣ ለካፊ፤ አሽኮርማሚ፣ ሞካሪ፣ አፍቃሪ ካጡ... ተናዳፊ ጊንጥ የመሰሉ ብስጩ ፌሚኒስቶች ጋራ ገጠመች:: የግሩፓቸው አባል ሆነች። ወንድ የባሰ ጠላች። አቤት አጠላል... ... አውራ ዶሮ ሴት ዶሮን ሲያሽኮረምም ካየች በድንጋይ ታባርረዋለች:: ባጋጣሚ መኪናዋ ተበላሽታ በታክሲ ተሳፍራ ስትሄድ ወያላው ትርፍ ሰው ለመጫን 'እሙ ትንሽ ተጠጊለት' ሲላት "እምቢ! ሴት ስለሆንኩኝ ነው አይደል?" ብላ ኡኡ ትላለች። እንዳው በስህተት እንኳ ትንሽ ዘነጥ ነገር ያለች መስላ ቢሮ ከሄደችና የሥራ ባልደረቦቿ በአድናቆት ዓይን ከሾፏት፡ this is harassment! ብላ ታምባርቃለች....በጠቅላላው የወንድ ፍጡር ጠላች!» ይለናል። ሆኖም አብረዋት የነበሩት ፌሚኒስቶች አንድ በአንድ ትዳር ይዘው ሲቀነጠሱ ተስፋ ቆርጣ ያንን መስመር ተወችው። [በወንዶች ተስፋ የቆረጡ አኩራፊ ሴቶች ወደ ፌሚኒዝም ባስ ሲልም Radical Feminist የመሆን እድል አላቸው? Maybe ●​ ከፌሚኒዝም በመቀጠል ፍጹም ወደሆነ መንፈሳዊ ህይወት ዞረች። እዚያም በቤተክርስቲያን ውስጥ መንፈሳዊ ሰው መስሎ የቀረባትንና የታመነ የመሰላትን ወንድ አምና ብር አበደረችው። እሱ ግን ገንዘቡን ይዞባት ወደ ውጭ ፈረጠጠ። ​ ● በአገር ውስጥ ወንዶች ተስፋ የቆረጠችው ሂሩት፣ "የሴትን መብት ያከብራል" በሚል እሳቤ ከአንድ የውጭ ሀገር ዜጋ ጋር ፍቅር ጀመረች። ነገር ግን ያ ነጭ ለትዳር ስትጠይቀው እሱ የሚፈልገው ጊዜያዊ መዝናኛ ብቻ ነበር። ● ​በመጨረሻም ሂሩት ብቻዋን ለመሆን ወስና፣ ከአንድ ያገኘችው ወንድ አርግዛ Single Mother ለመሆን ትገደዳለች። አታሳዝንም? ❷ የእዮብ ጥያቄ እዮባ የዚችን ሴት ታሪክ ሲቋጨው አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ጠይቆ ነው። «ከተማሩና በትልቅ የሥራ ሃላፊነት ላይ ከሚገኙ ጨዋ ላጤ ሴቶች ይልቅ አለሌ፣ መሃይም፣ ጋለሞታ፤ ቅናተኛ፤ መልከ-ጥፉ፣ ወንድን አሰቃይ ወይንም ዱርዬ ሴት! ሲሆን አሪፍ ትዳር፣ ካልሆነም ቢያንስ መውደቂያ ባል አጥታ የማታውቀው ስለ ምንድን ነው?» አለም ላይ የሆኑ ሀቆች አሉ አይደል? እንዲሁ የምንስማማባቸው? ከአከባቢያችን ከዙሪያችን አስተውለን የምንቀስማቸው! ጥናት ያልተሰራባቸው! Data የሌላቸው! እዮብ እነዚህን ነው ፈልፍሎ ማሳየት የፈለገው። ሁሉንም ነገር በሪሰርች፣ በቁጥር...በግራፍ ብቻ መለካት አይቻልም። ​እውነት ሪሰርች ባይሰራበትም፣ በዙሪያችን የምናያቸው ተጨባጭ ሁኔታዎች የራሳቸው የሆነ ትልቅ Data ናቸው። እኔ በዓይኔ የማየው፣ በህይወቴ የማውቃቸው ሰዎች ታሪክ ከማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ጥናት በላይ እውነተኛ ነው። ​ደመ-ነፍሳዊ መግባባት አላቸው። አእምሮአችን "መረጃ አምጣ?" ሳይለን ደመ-ነፍሳችን ወዲያውኑ "አያስፈልግም ማስረጃ። ልክ ነው!" ብሎ የሚቀበላቸው ናቸው። ● ያው ይሄንን የእዮባ ጥያቄ ስንመለከተው ሀቅነት አያጣውም። ​በእኛ ማህበረሰብ አስተዳደግ ወንድ ልጅ ሁልጊዜ በቤቱ ውስጥ መሪ እና የበላይ እንዲሆን ነው የሚጠበቀው። ሴቷ በጣም የተማረች፣ በኢኮኖሚ ራሷን የቻለች ስትሆን፣ የብዙ ወንዶች Ego ያነጥሳል። በርበሬ እንደሸተተው አፍንጫ። ​ያልተማሩ ወይም ራሳቸውን ካልቻሉ ሴቶች ጋር ሲሆን ደግሞ ወንዱ ሙሉ የበላይነቱን በቀላሉ ያገኛል። ሴቷ ሙሉ በሙሉ በእሱ ላይ ጥገኛ ስለምትሆን የሚሰማው የጀግንነት ስሜት ለትዳሩ መቆየት (ጤናማ ቢሆንም ባይሆንም) እንደ ሰበብ ሆኖ ያገለግላል። በሌላ በኩል ደግሞ ​ታሪኩ ላይ እዮባ "አለሌ" ወይም "ጋለሞታ" ያላቸው ሴቶች ወንዶችንም ህይወትንም እስኪበቃቸው እየሾሩ ከብዙ አንግል ስላዩዋቸው ከወንድ ልጅ የሚጠብቁት መስፈርት በጣም አነስተኛ ነው። ​ወንዱ ጥቂት ነገር ሲያደርግላቸው በቀላሉ ይረካሉ (ያንን ነገር አይጨምርም) ... ፍፁም የሆነ ወንድ አይጠብቁም። ​በአንጻሩ የተማሩት...ጨዋዎቹ ሴቶች ግን ከፍ ያለ የህይወት መርህና መስፈርት ስላላቸው፣ የወንድን ስህተት በቀላሉ አያልፉም። ይህ ጥብቅ መስፈርት ደግሞ ወንዶች ረጅም ርቀት አብረዋቸው ለመጓዝ እንዲፈሩ ያደርጋቸዋል። [ እዩባ መሠረታዊ ጥያቄ ነው ያነሳ አይመስላችሁም? ዛሬ ላይ ደግሞ ጉዳዩ ያሳስባል። ያው ​የስነ-ጽሑፍ ዋናው ውበትና ጥቅሙ ጥናትና ምርምርን መተካት አይደለም። ማህበረሰቡ እያየው ግን ደፍሮ የማይናገረውን ሀቅ መስታወት ሆኖ ማሳየት ነው። እዮባ እነዚህን ሀላፊነቶች ሲወጣ የነበረ ሰው ነው። ©️Mes oud

  • видео или голосовое, без подписи

📚 አዳም ረታ ™ — tgindex