😘❤️ፍቅር እና ፍልስፍና
Статистикаአርት ነክ የሆኑ ጉዳዮችን ግጥም እጥር ምጥን ያሉ አጫጭር ፁሑፎች ስለ ደራሲያ እና ፈላስፋዋች
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 570
- 1/48двое суток
- 653
- 1/72трое суток
- 704
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
አንዳንድ መንጋቶች ግዜ እየጠበቁ አይናችንን ሳንገልጥ በትዝብት አለቁ 121(አኮብ)
ደብዳቤ ስጽፍ ለስንተኛ ግዜ እንደሆነ አላቅም ግን ለመጀመሪያ ግዜ የጻፍኩት አማርኛ መምህራችን ጻፉ ያለችን ቀን ነው ብቻ ብዙ ተሳስቼ ነበር መሰል ከዛ በዋላ ደግሞ ምስጋና ላንቺ ይሁንና ብዙ ታስጽፊኝ ጀምረሻል. . . አንቢቢው አታንቢቢው ገድ ሰቶኝ አያቅም እያንዳንዱ መስመር እያንዳንዱ ቃል ለኔ ትርጉም አለው. . . አንዳንዴ የጻፍኳቸውን ተራ በተራ አንብና ዝም እላለው በዛ ዝምታዬ ውስጥ ያንቺን ትዝታዎች ነው በመላ ህዋሳቶቼ ማደምጠው። የሆነው ሆኖ ሁል ግዜ መጠበቅ ያማል አደል. . . ያቆስላል አደል ይገድላል አደል. . . እኔስ አንቺን ካጣው ወዲህ በህይወት አለው ማለት ችላለው? . . . . ብቻ የስራሽን ይጥሽ ልል ፈልግና በዋላ ተጎድሽ ሳስበው እኔኑ መልሱ ያመኛል አለ አደል እዛ እንደ ጥዋት ጸሀይ ሙቀቱ ና ብርሀኑ ሚናፍቀው ሳቅሽኝ ማጨለም አልፈግልም. . . ግን እውነት ስልሽ አወራር ጠፍቶብኛል . . . ቃሌ ከነፍሴ በፊት ሊሞት እያጣጣረ ይመስለኛል . . .። ግን እኮ እንደ ድሮው መሳቅ ፈልጋለው. . . እንደድሮው ነገ የተሻለ ይሆናል ማለት ፈልጋልው . . . አለ አይደል. . . ብዙ ተስፋዋቼ አንቺ ያጣውሽ ቀን አብረው ከስመዋል . . . ግን ስንቶቻቹ በትናታቹ ታስራቿል? 121(አኮብ)
ላገኝሽ ነው ብዬ ጠመንጃ አንግቤ ለነፍዬ ማቆያ ጭቅና ጠግቤ በየተራራው ስር በየ ጉራንጉሩ ውርጩ ሲበረታ ሲያይል ሀሩሩ ስቶክስ ሳስቶክስ የጥይት እሩምታ አካላቴ አይዝል ልቤ ተሎ አይመታ ከጠላት አቃጣጫ መድፍ እየተመታ ስዞረው ጮካውን ስዘለው ገደሉን ተኩሱ ይበርድ ና ሳርፍ ግዜ አንዱን ናፍቆትሽ ይመጣል ጓዙን ጠቅልሎ ልቤን ሊያሸፍተው መዳፉን ጠምልሎ ደሞ ሌላ ውግያ * 2 ከቀድሞው የከፋ ምሽግ የሌለበት ጥይቱም ለከፋ ስታንጋጊው ከርመሽ ሳቅን ከፈገግታ አካላቴ ሲሞቅ ከውጊያው ፌርማታ የናፍቆትሽ ጥይት ልቤ ውስጥ ተቸክሎ የሚያወጣው ጠፋ በትዝታሽ መግሎ 121(አኮብ)
ሳላውቅህ በፊት ጨለማ እፈራ ነበር። ጨረቃ ወጣች፣ መሸ፣ ነጋ... ግድ የሚሰጠኝ ምንም አልነበረም። ለኔ ምሽትና ንጋት የቀን መለዋወጥ ብቻ ነበሩ፣ ትርጉም የለሽ ዑደት። አንተ ግን በህይወቴ ገብተህ ሁሉንም ለወጥከው። አሁን መስኮቴን ከፍቼ ጨረቃዋንና ጨለማውን ሳያቸው "ይሄን ያህል ተጉዘን ነበር?" እላለሁ። ትዝ ይልሃል? እጅ ለእጅ ተያይዘን ማርጀት ነበር ፍላጎታችን። ለልጆቻችን የምንተርክላቸውን ተረት የሚመስል ታሪካችንን ስትተርክልኝ፣ ድምጽህ አሁንም ድረስ በጆሮዬ ያስተጋባል። መድረስ የምትፈልግበትን ቦታ ስትነግረኝ፣ እጄን ይዘህ ላግዝህ ስጣጣር የነበርኩበት ስሜት አሁንም በአእምሮዬ ይዋልላል። ብቻ... ልክ ኮምፓስ እንደጠፋበት መርከብ፣ አሁን ወዴት እንደምሄድ አላውቅም። እጄን ይዘህ ያደረስከኝ ቦታ ላይ ቆሜ መንገዱን ከማማተር ውጪ ምን አማራጭ አለኝ? አዎ... አንተ ኮምፓሴ ነበርክ! 🧭 አሁን ጨረቃን ሳያት አንተ ትዝ ትለኛለህ። አንዳንዴ ካለህበት ጎትቼ ላወጣህ እፈልጋለሁ፣ ግን አልችልም። ምናልባት. . . ጥላ ከለላ የሆኑን ሰዎች ሲርቁን ነው፣ የህይወት ዱላዋ በትክክል የሚሰማን። ዛሬም ጨረቃዋ ወጥታለች። ግን ዛሬ... ብቻዬን ሆኜ ነው የማያት። 121(አኮብ)
በግጥም ተውበው በዘነጡ ቃላት አስሰው ገርበው ትዝታን ሲያነቋት እንባ ተናነቀኝ እሄድበት ጠፋኝ ድሮም ትዝታ ሲነቃ ከምሽጉ ከርሞ እንዲው አይመለስም የሰው ግምባር ስሞ 121
"የድሮ ደብተሬን ስገለጥ፣ 'ፍቅር እያደር ወጣት ይሆናል እንጂ እንደ ሰው አያረጅም' የሚል ጽሁፍ አገኘሁ። የኔስ ፍቅር የት ደረሰ? እንደ እድሜ ጠገብ አዛውንት መቋሚያ ተደግፎ ይሆን ወይ? 'ገና አልሞትኩም' እያለ ለማትረፍ የሚታገል... አንዳንዴ በውስጥ ያለን ስሜት አለመናገር፣ ከልብ የማይጠፋ የዘወትር ጠባሳ ሆኖ ይቀራል። እናንተስ? የውስጣቹን ሳትናገሩ ግዜ የሸበለለባቹ ነገር አለ?" 121
ሬድዮ አዳምጬ ማቅባቸው ቀናቶች በጣት የሚቆጠሩ ትንሽ ናችው ዛሬ ግን መክፈት ፈለኩ መስማት ፈለኩ የሆነ ምስሉን የማላየው ድምጽ ፈለኩ እሱነቱን በለበሰው ጨርቅ ሳይሆን በንግግሩ መመዝን ፈለኩ አንዳንዴ ምናለ የዘመኑ social mediaዋች በድምጽ በሆኑ እላለሁ ብቻ ከፈትኩት አንድ ሰው በደስታ ተሞልቶ ዛሬ ታሪካዊ ቀን ነው ሲል ይደመጣል ታሪካዊ ቀን ማለት የማይረሳ በጥሩ ም በመጥፎም የሚታወስ አደል እንዲ ካልን ስንቱ በልቡ ከትቦ የያዘው ታሪካዊ ቀን አለው የማይረሳው. . . የማይዘክረው. . . የማይረግመው. . . ሊፍቀው ቢሞክር የማይፋቅ በልቡ የተነቀሰው ጥቁቁር የጠለሹ የህይወቱ ቅንጥብጣቢዋች ሆነው ለመንቀል ያዳገቱ ብቻ እግዜር መቶ ለሁሉም ብእር ወርቀት የታሪካዊ ቀናቹን ገጠመኝ አስፍሩ ቢል ወረቀቱ ይበቃቸዋል? እንጃ የኔዋ ታሪካዊ ቀን ግን ታሪከ ብዙ ናት ቢጨልፏት የማታልቅ ውቅያኖስ የናተስ? ስንት ታሪካዊ ቀን . . . አላቹ ? አኮብ(121)
🌙 ኢድ አል-አድሃ ሙባረክ ለመላው የሙስሊም ወንድሞቻችን ና እህቶቻችን መልካም እና የተባረከ 1447ኛ ኢድ አል-አድሃ ቀን ይሁንላችሁ!
የብቸኝነት ካባ ሰውነቴን ሲጫጫነኝ ተስቼ ወጣው ሰማዩ ሰዋችኝ በጎርናና ድምጹ ካሁን ካሁን ዘነብኩ እያለ ማስፈራራት ጀምሯል. . . . በዚ መሀል ሰው መራራጥ ጀመረ የዛኔ ወድሃለው ያለቺኝ ልጅ በፍጥነት ብስክሌት ስነዳ አየዋት በዛው ቅጽበት ትዝታዎቼ መጣን መጣን ማለት ጀመሩ ለመጀመሪያ ግዜ ወድሀለው ያለቺኝ ቀን የሳልኳት ቀን ምናምን ምናምን ትርኪሚርኪ ትዝታ . . . ግራ ተጋባው የተዳፈነው ፍቅሬ አፈር ልሶ ሲነሳ ይታወቀኛል ሰው እንዴት የላፈ ታሪኩን መርሳት ባይችል መተው ያቅተዋል እላለው ዝም እልና ደግሞ "የተፋቀረ ሁሉ አብሮ አይዘልቅም" በሚለው ቢሂል እጽናናለው ትንሽ ጋብ ሲልልኝ ደሞ ምን አልባት ትወደኝ ይሆናል ምን አልባት እረስታኝ ይሆናል ምን አልባት ታቂዋለሽ ብትባል አላቀውም ብላ ትክድ ይሆናል እንዴት ሰው ከ8 አመት ቢፊት ስላሳለፈው ግይሰጠዋል እላለው ብቻ . . . አንዳድ ፍቅር ልተውህ ሲሉት አተን ለማ ትቼ ሚል የሚል ይመስለኛል 121
ፍቅር ግን ልክ እንደማያድግ ሰው ዘወትር መሸንገያ እና ማባበያ ሚፈልግ ህጻን ይሁን? . . . . ብቻ ያማል እየተዋደዱ መለያየት ያማል . . . ያላንቺ አልኖርም ያላንተ አልኖርም እየተባባሉ መለያተት ያማል . . . ሆነው እንዳለ ሆኖ ማፍቀር ምን አልባት ለሁሉ አልተፈቀደ ይሆናል 121
ስልኬን እዘጋለሁ ፤ እስልኬን እከፍታለሁ ከጣፍሽልኝ ብዬ ፤ አስሬ አፈጣለሁ አይኔ እስኪቀላ ፤አስኪጠፋኝ መላ ስጠብቅ ቃልሽን ፤ የዋላ የሀዋላ በዋዛ ፈዛዛ ፤ ዘመኑ ነጎደ ነፍሴ በቃልሽ ጥም ፤ ላይሽር ነደደ በትዝታሽ እቶን አቅሉን እየሳተ ዛሬም ስፅፍልሽ አንድም አልታከተ ዳሩ ... ኩራት በሚሉት ፤ ቃል ልቦናሽ ታውሮ አመጤፍ አትቆጥሪ ፤ የውጤን ሮሮ ቢገባሽ ኖሮማ አውቀሽ ቢሆንማ ትይኝ አልነበረ ! መጣፍ አይኑ ይጥፋ ይጣ ኢሚንት ተስፋ እኔስ እመጣለሁ ካለህበት ስፍራ እራስህን ጠብቅ የኔ ውድ አደራ ምናምን... ምናምን... ብቻ... የአንደበትሽን ዜማ ፤ ስሻልሽ ዳክሬ ዝምታሽ ገደለኝ ፤ ተዘረርኩኝ ዛሬ። 121
በወሬ መሀል እንደቀልድ በዋዛ ፈዛዛ ስምሽን ሲያነሱ ድንገት ነበር ሳቄ ከገፄ ላይ የተራገፈው... ድንገት ነበር ጨዋታ የጠፋብኝ... ድንገት ነበር በዝምታ ባህር ውስጥ የሰጠምኩት... ብቻ ከምሸሸው እኔነቴ ጋር ነው ያላተሙኝ.. አላወቁትም እንጂ ማባርያ ከሌለው ዶፍ ትዝታ ውስጥ ነበር የዘፈቁኝ... "!አንዳንዴ የተዳፈነ ትዝታ ሰው ፊት ሲነቃ አንገት ያስደፋል '' 121
ፍቅር አልባው እኔነቴ አለት ልቡ ማንነቴ እንዳልበር ድሮ ገና ስትመጪ አልል ቀና ይሰማኛል እፍረት ቢጤ እደነካው እልፍ ቃጤ ቀናት አልፎ ቀን ሲተካ አለት ልቤ ፈርሷል ለካ 121
እውነት ነው መለያየት ያማል ያቆስላል ብቻ አንዳንድ ግዜ በወጉ እራሱ መለያየት ይናፍቃል አለ አደል ብዙ ግዜ ምናለ ከዚ በዋላ እንዳታወራኝ... ምናምን ብትለኝ ብዬ አስቤ አቃለው.... ብቻ ስንብት ከሌለው መለያየት ይጠብቃቹ😊
አንዲት እኳ ቀን የሌለው ለመፈገግ ለመጫወት ካላደለው መዳፍ ጥሎሽ ብትከፊ ከእግዜሩ ደጅ ብታኮርፊ ፈዋሽ የለው አንዳች መድን ከትዝታሽ እልፍ እርቆ ለሚመንን 121
ከፈገግታህና ከኔ የቱን ትመርጣለህ አለቺኝ አንቺን አልኳት.. እንዴ ለምን አለቺኝ ምክንያቱም ያለአቺ መሳቅ ስለማልችል አልኳት..
ትግስተኛ ሰው አደለሁም ግን እስካሁን የአንቺን ምላሾች እየተጠበኩ ነው... እመኚኝ አንቺ ለኔ መተኪያ የሌለው ልዩ ሰው ነሽ
3 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው። ለፈተና በቂ ዝግጅት ስላላደረጉ ለመሸወድ ፈለጉ። በዚህም ምክንያት አንድ መላ ዘየዱ። ራሳቸውን ግሪስ ቀቡና ራሳቸውን በሚገባ በማቆሸሽ ከሌክቸረሩ ፊት በመቅረብ እንዲህ ሲሉ ምክንያታቸውን አቀረቡ፦ ኢንስትራክተር በጣም እናዝናለን፤ ፈተናውን ለመፈተን የማያስችል እንከን ገጥሞናል። ምክንያታቸውን አስከተሉ፦ አንድ ሰርግ ላይ ታድመን ነበር፤ እናም ከፕሮግራሙ በኋላ በመመለስ ላይ እያለን በመንገዳችን ላይ መኪናችን ብልሽት ገጠማት። የመኪናችንን ብልሽት ለመጠገን እንደምትመለከተን በአስቀያሚ ሁኔታ ቆሽሸናል። #ሌክቸረሩም ከምክንያተቸው በመነሳት ተረዳቸውና ወደቤታቸው እንዲመለሱ ለፈተና ዝግጅት 3ት ቀን ሰጣቸውና አሰናበታቸው። ከ3ት ቀን በኋላ ለተዘጋጀላቸው ፈተና በበቂ ሁኔታ አጥንተውና ተዘጋጅተው መጡ። ሌክቸረሩ አንድ ውሳኔ ወሰነና እንዲህ አደረገ ... ሶስቱም ተራርቀው የተለያየ ወንበር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ። ተማሪዎቹም በጣም ተራርቀው ተቀመጡ፤ የፈተና ወረቀትም ተሰጣቸው። ጥያቄዎቹ የሚከተሉት ነበሩ፦ ጥያቄ ቁጥር 1 - ማን ነበር ያገባው ? (25 % ማርክ) ጥያቄ ቁጥር 2 - የት ነበር የሠርግ ፕሮግራሙ የተካሄደው ? (25 % ማርክ) ጥያቄ ቁጥር 3 - መኪናዋ የተበላሸችበት ትክክለኛ ቦታ የት ነው ? (25 % ማርክ) ጥያቄ ቁጥር 4 - የተበላሸችው መኪና ሞዴሏ ምን አይነት ነው ? (25% ማርክ) ከጥያቄዎቹ መጨረሻም #ማስጠንቀቂያው እንዲህ ይላል - መልሳችሁ የግድ ተመሳሳይ መሆን አለበት !!! ___ Africa 10 ን ላይ - ተወስዶ የተተረጎመ #Tom1_Tube
የዚህች አለም የአሸናፊነት ሚስጢር ሴት ልጅ ጋር ብቻ ነው!! የትኛው ሀብታም ነው ፣ የትኛው ባለ ስልጣን፣ የትኛው ባለ ዝና ፣ የትኛው ጀግና፣ የትኛው ተዋጊ ነው በሴት ልጅ ፍቅር ያልተሸነፈ? ወንድ ልጅን ያለ ጦር መሳሪያ መማረክ የምትችል ፍጥረት ሴተ ልጅ ብቻ ነች!! ...Masayoshi Kobayashi ይባላል ታዋቂ የጃፖናዊ ቢሊየነር ነው...የስራ ሰው እንደሆነ አለም ይመሰክርለታል...ለጃፖናዊያን ህብረተሰብ ለሚሊዮኖች የስራ እድልም ፈጥሯል እየፈጠረም ይገኛል። ፍቅር ግን ጅ'ል ያረጋል መሰለኝ Masayoshi Kobayashi ከአንዲት ቀበጥ ወጣት ፍቅር ያዘው...ልጅቷ በጣም ቀበጥ ከመሆኖ የተነሳ በቀን ውስጥ የመኪና ውድድር የሚካሄድበት ቦታ ሄዳ መኪኖች ሲወዳደሩ ካላየች ቀኑን ሙሉ ይደብራታል ዘመድ እንደሞ''ተበት ሰው ቤቷን ዘግታ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች የመኪና ውድድር እንኳን ባይኖር ለመኪና ውድድር ልምምድ ሲያረጉ ማየት ትወዳለች😂😂 ጃፖናዊው ባለ ሀብት እሷን ከሚያገኝበት ቀን የማያገኝበት ቀን በለጠበት ለእሷ ብሎ አንድ ሁለት ቀን የመኪና ውድድር የሚካሄድበት ቦታ ላይ ተገኝቶ ነበር ነገር ግን ሰዎቹ እሱን ሲያዩ የሰጡት ከፍ ያለ ቦታ ነፃነቱን ገደበውና አልተመቸውም ስለዚህ መሄድ አቆመ። ፍቅረኛውን ደሞ አትሂጂ ቢላት ተነጫንጫ አኩርፋ በሯን ዘግታ እያለቀሰችበት ተቸገረ....ተጨነቀ በመጨረሻም አንድ ሀሳብ አመጣ ከቅርብ ሰዎቹ ጋርም ተነጋግሮ ተገበረው ቤቱ ግቢ ውስጥ 200ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር አውጥቶ መኪና መወዳደሪያ ትራክ ሰራና ፍቅረኛውን ሰርፕራይዝ አረጋት😂😂😂 እውነትም ሀብታም ቀልብ የለውም የሚባለው እውነት ነው አስቡት 200ሚሊየን ዶላር አውጥቶ ቤቱን አፈራርሶ የመኪና መወዳደሪያ ሰርቶላት ከፍቅረኛው ጋር ቢለያይ ከብሩም፣ ከቤቱም፣ ከፍቅረኛዎም ሳይሆን መሀል ላይ ቀረ ማለት አይደል😂😂😂 አረ እባካችሁ ወንዶች ፍቅር ሲ ይዘን የምናረገውን እንወቅ ስሜታዊ አንሁን😂😂😂😂😂
видео или голосовое, без подписи