✨𝕪𝕖 ግጥም 𝕛𝕚ረት✨
Статистикаጦቢያ የ ግጥም ጅረት ከ ✨ጥበብ✨ማእድ....✍️ @Mepoemer 👶ተቀላቀሉን..✍️ https://t.me/yegixemjiret
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 246
- 1/48двое суток
- 281
- 1/72трое суток
- 304
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ወተቷን ለማግኘት እናትና ልጅን - እየነጣጠለ አላቢ ማንነት - 'አርቢ' ከተባለ ለልጇ የማይሆን - ግት ያጋተች ሀገር ስሟ #ላም ይባላል እሷ እየታለበች - ጥጃዋ ሲታሰር።
<<ሰው የሚወደው፤ #ሚወደውን ሳይሆን፤ #የሚወደውን ነው>> ለዘመኑ አናት - ለዚ'አይነት ጭንቅላት፤ ህብረ ቃልዋ ጥቂት- ቅኔዋ እልፍ ናት። የዘመኔ አናት ከ "ጭን" ስር አርግደው ወርሶ ደቂ - ቅ- ላት እኔም ብል አይግረም ግ.ጥ.ሜ ቅኔ አላት ግልጡን ለመናገር ፀሀይን ለማድነቅ፤ ጨረቃን አልንቅም ኮከብን ለማድመቅ፤ ጨለማ አልፍቅም፣ ሰማይን ለማቀፍ፤ ምድሬን ጥዬ አልሄድም የፈለገው ይምጣ፣ ራሴን ከቶ አልክድም። ግልጡን ለመናገር!! እንደ ሊስትሮ እቃ..... ጫማ ያለው ሁሉ፤ ከቶ እንደማይረግጠኝ ለውበት የማልሰግድ፤ እራሴ ውበት ነኝ ሰው መሆን መልኬ ነው፤ "ምን ይመስላል!!" ላለኝ። እድሌን እያወኩ፤ እጄን አልዘረጋም፤ ሎተሪ ለመቁረጥ ንፁህ ሀበሻ ነኝ፤ በክብሬ ላይ ማልቀብጥ። አቧራ ላዘለ፤ ለመኪና ኮቴ ብናኙን አልሆንም፤ ውብ ነው ማንነቴ ሰፊ ሂወት አልስልም፤ በጠባቧ ቤቴ። ድሃ እያፈረሰ፤ ሀብታም እንደ ሚያድስ አርጋቹ አትዩኝ ፤ የሀገሬን መሀንዲስ። ፎቅ ቤት ለመግንባት፤ ጭቃ ቤት አልረግጥም ቀን ቢያሳልፍልኝ፤ ቀን ጠባቂ አልንቅም! ግልጡን ለመናገሮ ኢላማ ካለምኩኝ፤ አላማ እንደማልስት ቀስትን ለቀሰቱ፤ ጋሻ እንደምመክት መድረስ ምን ቢሳነኝ፤የምደርስ በድርሳን ዘማዊ በልብሴ ፤ በነብሴ ግን ካህን ለቁም ሂወ፡ ገናዥ ፤ ሱባኤ ብገባም በጥጋብ ለሞተው ፤ ከቶ አላነባም ግልጡን ለመናገር.. ሄዶ የመመለስ፤ ስለሌለኝ ልምዱ መሄድ የከጀለ፤ ቀድሞኝ ኮቴ ያንሳ_ክፍት ነው መንገዱ። ግልጡን ለመናገር ሰው የሚወደው፤ ሚወደውን ሳይሆን፤ የሚወደውን ነው እኔ ግን ምወደው፤ ምወደውን ሳይሆን፤ የሚወደኝን ነው። 🙃
መንገድ ስጡኝ የማርያምን፣ ብሎ መሮጥ የኣቅምን፣ ልጅ እያለን ድሮ ቀርቷል፣ #በዘመኑ_ፍኖት_ጠፍቷል። ግዜ የለም ፣ ሚደርስልን፣ ዳጃ አይመጣ ፣ ሚፈርድልን ሳቅ ቢከመር ፣ ሳግ አያጣም #የተሻለ_ነገ_አይመጣም። 'እንቆቅልሽ ፣ በሆነ ሂወት ከንቱ ሆኖ ፣ ወጣትነት አገር የለም ፣ የምንሰጠው፣ #ሳንኖር_ነው_የምንሞተው'።
https://t.me/yeamagnuqne
〖couples mini blog d/t reason, z same feelin'🤦♂️〗 ዜማ እወዳለሁ ዜማ ትጠላለች፤ በድርጊቴ ሁሉ ትብከነከናለች፤ እርጋታ የላትም እርካታ የላትም፤ ሆኖም አልጠላትም፤ ታስጨንቀኛለች ፋታ አትሰጠኝም፤ የገዛ ዕድሜዬ ላይ እኔ መብት የለኝም፤ ወይ ቁንጅና ማድነቅ ወይ ሌላ ሴት ብ'ያ'ት፤ እሷ ፍላጎቷ እሷን ብቻ እንዳያት፤ ስልክ መያዝ ሃራም፣ TV ማየት ሃራም፣ መፃፍ ማንበብ ሃራም፣ ፍልስምናንም ክልክል፤ እሷው ነች ትክክል፤ ከቅጥሯ እንዳይወጣ ልቤን ታዘዋለች፤ ፍቅሯ እኮ ደስ ይላል ግን ታበዛዋለች፤ ጁመዓ ነው ብዬ ሀገር ሰላም ብዬ ባዳምጥ ነሺዳ፤ "አትወደኝም" ብላ ጨመረችኝ እዳ፤ "እውነት ትወደኛለህ? ይደንቀኛል ስራክ፤" For the rest of my life እንደሚለው track፤ maherም ባይገድሽ፤ እንዲያ ነው ምወድሽ፤ ሰምተሽዋል እሱን? "መልስልኝ መልሱን! ከሚዲያ ለቅመህ አታሰማኝ ቅጂ፤ ጊዜ ስጠኝ እንጂ፤ ትኩረት ስጠኝ እንጂ፤ እንደው አቅም ኖሮኝ በእጄ በጨመኩህ እንደ በሶ ጭኮ፤" እሺ ምን ልበልሽ አስጨነቅሽኝ እኮ፤ "እወድሻለሁ በለኝ!" ሁሌም እልሽ የለ? "ብትደግመው ምና'ለ'?" እሺ እወድሻለሁ ከራሴም አብልጬ፤ አንዴ የጀመርኩትን ልጨርስ አድምጬ? "አንተ መቼም አትለወጥም😡" አይ እዳ! በቃ ትቼዋለሁ ምንም ካንቺ አይበልጥም
✨𝕪𝕖 ግጥም 𝕛𝕚ረት✨: ``ፈገግ ለማለት ለምትሞክር ጥርስህ የሳቅ ክምር ዓይንህ የደም ባህር ደስተኛ ባትሆንም ያሰብከውን ምሰል እንባ የሳቅ ደዌ ሆድ ከሞት ይከፋል እንኳንስ ያቀፉት የራስ ሆድ ይገፋል ያኔ ይለቀሳል ሂያጅ ይወቀሳል ህመም ይወረሳል ቢሆንም ቢሆንም ይህንን ተረዳ አታልቅስ አልልም ግን በእንባህ መካከል እያነባ ፈ ገ ግ በል
እኔ ያንተው ዳዒ ምስኪን የምገፋ አንተ እንደው አታጠፋ እኔም ደጅህ አልጠፋ የመቅደስ ስር ግርድፍ ከፊት ተሰላፊ አታድርግ ያልከኝን እንዳልሰማ አላፊ ራሴው ባበጀሁት ጎዳና ማዘግም ልክ እንደ ውዳሴ ሀጥያት የምደግም መደዴው አምላኪ ሊያጠራ ሲሞክር አቤት በለው እስኪ ሁንልኝ ምስክር ነፃ ፍላጎቴን ሸርሽሮ ሸርሽሮ ግዜ ማይፈውሰው ሆኖብኛል ምሽሮ ውስጤ ቅጡን አጣ በደስታ ረወጠ ጌታውን በነፃ በስሜት ለወጠ ይሁዳስ ነግዶ አትርፏል መሰለኝ ምነውሳ እኔጋ አምላኬ ቀለለኝ ከሁሉ አብልጬ ወድሃለው እያልኩት በነፃ ለወጥኩት በምንም ቀየርኩት። የኔ በኔ ይብቃ... ለትውልድ አሻግረህ አታድርገኝ 'ረድ የተደገፈኝን ቁልቁል ይዤ እ ን ዳ ል ወ ር ድ
ለሚኖር መሰንበት አጥሮ ፥ አርባና ሰማንያ 'ራቀው በለሱን አንቆሮ ተፍቶ ፥ በዋጠ ማግስት አነቀው፤ ሙታንም ለራስ አንብቶ ፥ በቁሙ ህይወት ተራበ ሰማየ ሰማያት ሲመኝ ፥ ከጽድቁ ውድቁ ቀረበ፤ ያ ምስኪን ድሃ ገበሬ ቢጸልይ ለመኖር ዛሬ ምሽቱን ሽፍታ ላከበት ተኝቶ በደረቅ ቁርበት ቀረለት ዛሬን መሰንበት ማጣት ላይ ሞት አክሎበት። እናማ እንዲህ ቢገጥመው ፥ አምላኩን ቆሞ ከሰሰው አምላክም የዋዛ አይደለም ፥ ድጋሚ በመኖር ካሰው፤ መታተር የማይሰለቸው ፥ ይህ ምስኪን ድሃ ገበሬ ሰማይን ዝናብ ሲለምን ፥ ማዕልቱን አጥምዶ በሬ ምሽቱን ገዳይ ላከበት ፥ ከስቃይ ሊገላግለው አምርሮ አምላኩን ሲከስ ፥ ዘላለም ህይወት አደለው። ነገር ግን ደስ አላለውም ፥ አምርሮ ቃሉን ደገመ በስጋው ስቃይ የበላ ፥ ከነፍሱ ያላገገመ ድጋሚ መኖር መቀጣት ፥ መሰንበት የተረገመ.. ነገር ግን ደስ አላለውም ፥ ይልቅ ይህን አነሳ በደሌን ይቅር ብትለኝ ያንተንም እንደምረሳ አባት ሆይ ፈተና በቅቶ ፥ ከክፉ የምታድነን ሞት የለሽ ሞት እየሰጠ ፥ መከራን 'ምትገላግለን ዘላለም ህይወት ሰርዘ ፥ ከመኖር ቀድመ ግደለን
« መቼም ሆነ የትም ከባለ ጋራው ጋ፡ ባለቃል ቢገጥም ጣዕም እስካለ ድረስ፥ ቃሉ እጅ አይሰጥም! » እል ነበር በልቤ « ለም ዐፈር ሕሊናው ፡ ማሕጸነ ልቡ ዘር ይዞ መዘርዘር ፡ ስለሆነ ደንቡ ጣዕም እስካለ ድረስ ፡ ማረፊያ ለቀልቡ ሰርክ እየጠለቀ ፡ ዝንታለም ቢጽፍም ላይን ይረቅቃል እንጂ ፡ባለቃል አይነጥፍም። » እል ነበር ለልቤ የባለቃል ኩታ ፡ ለራሴ ደርቤ ለቃል ረድኤቱን መስጠት ማበርከቱን ስለተካንኩበት ፡ ሲጎህ መቀተሩን ፡ ሲያካፋ ማዝነቡን ሲፈገግ መሳቁን ፡ ሲበቅል ማበቡን ቅር ሲል መጥላቱን ፥ ቅርር ሲል ማልቀሱን ጠብ ሲል መሙላቱን ፡ ከፍ ሲል ማፍሰሱን ከሐቁ መላቁን ፡ ከሆነው መባሱን ዲያቆን እውነታ ላይ ፡ በቃል መቀሰሱን ስለተካንኩበት ፡ እንኳንስ ያለፈው፡ እንኳን ያለሁበት የሚመጣው ነገም ፡ ገና የምደርሰበት ከልቤ ውስጥ ታስሮ፡ ሙቶ የተቀበረ ሲያሻኝ የምፈታው ፡ ይመስለኝ ነበረ። እስኪገጥመኝ ድረስ፡ የገበሬው እጣ ለካ አያርስም ኖሯል ፡ የሚዘራው ያጣ?! የሚገጥመው ሁሉ ፡ ወይ ሀዘን ወይ ቁጣ ወይም ስቃይ ስጋት ፥ ወይ ሳቅ ካላመጣ የሚታየው ሁሉ፡ ካልሳበ ካልገፋ የሚሰማው ሁሉ ፡ ካልቆጨ ካልከፋ ባለቃል እፍ ቢል ፡ ቢያራግብ ቢለፋ ለካ አይነድም ኖሯል፡ መጫሪያው ከጠፋ።? የጠፋ ጊዜ ላይ ፡ ጉልቻ ተማግዶ እሳት በሌለበት፡ ባዶ ድስት ተጥዶ ሳማስለው ውዬ ፡ ቢያቃጥለኝ ጥሙ ጨልፌ ስቀምሰው ፡ ወና ወና ጣሙ፣ ወና ወና ጣዕም ፡ ጥም የማያረካ ወይ አንጀት አያርስ፡ ወይ ልብ የማይነካ ወይ ቅጠል አይረግፍ፡ ወይ ጽጌ አያፈካ፤ ወና ወና የሚል ፡ ስሜት ባጣ እድሜ ሙት ስንኝ በጩኸት፡ ልቀሰቅስ ቆሜ ራሴን ባገኘው ፡ የባለ ቃልነት ፡ ክህነቴን ፈታሁ። አወይ የቅኔ እድል፡ አወይ የቀን እጣው... ጣፍጦ እንዳላነቃኝ፡ መርሮ እንዳልበረታሁ ወና ወና ቢለኝ ፡ጣ'ም ባጣ ተረታሁ።
ሺ አመት አይኖር ለማንፏቀቅ ህይወት ለማይሞላ ኑሮ ከዛሬ ቆንጥሮ ስለ ነገ ቆጥሮ ለነገ እያልኩኝ አምሮት አቃጠለኝ ዛሬን ልኑር እንጂ ከነገ ምን አለኝ ልቤ ስንቱን ነገር ፈልጎ እያጣ እስከመቼ ድረስ ፣ባምሮት ልቀጣ፣ ማነህ አስተናጋጅ..... . . . . . . ሺ አመት አይኖር ሻይ በዳቦ አምጣ!!!🙂
#ያው_እንደኛው_ናቸው በሰማይ አዋፋት፣ አይዘሩም አያጭዱም አገር አቆራርጠው፣ ሲራራ አይነግዱም ግን ከኛ ኑሮ ምን ልዩ አረጋቸው? ለእፍኝ እድሜ ሲባል፣ የሳር ጎጆ ማልማት ሞላሁ ለማይል ሆድ፣ እህል በመሻማት ያው እንደኛው ናቸው። ያለም ከበርቴዎች በፈጣን ጀታቸው፤ ሰማዩን ቢገምሱም ርካታ ካለበት፣ ቀድመውን አይደርሱም ሻርክ ተፈናጠው፣ ከባህር ቢጠልቁም መንኰራኩር ጋልበው፣ ከጠፈር ቢመጥቁም እኛን ከሚያሰጋን፣ አንድ ርምጃ እይርቁም። የምድሪቱ ጌቶች ለሰው ዐይን ሞልተው ትልልቅ ቢመስሉም፣ በኩራት ተነፍተው ተራራ ቢያከሉም፣ ከተሸከሸኩ፣ አንድ እፍኝ አይሞሉም። ፍትወትና ፍራት፣ የሚጎትታቸው ያው እንደኛው ናቸው፣ ባለስትንፋስ ሁላ፣ ቢታይ ተመንዝሮ ለየቅል መሳዩ፣ ያው ነው ዞሮ ዞሮ።
ባመነ አይደለም ፥ በተጠመቀ ባወቀ አይደለም ፥ በተጨነቀ ያመነ አይድንም ፥ የጠረጠረም ሰው ነገን እንዲያውቅ ፥ አልተፈጠረም ። ፈዛዛው ፥ ንቁም መሐይም ፥ ሊቁም ህይወት ላይ ሲሆን ምንም አያውቁም ። ለጽድቅ የሰሩት ፥ ሲዖል ይጥላል ለሞት የዋጡት ፥ ከሞት ያድናል ታዲያ ማን ደፍሮ እውነት ነኝ ይላል ? አይሆንም ያሉት ፥ ሊሆን ይችላል ። ሎሬት ሀብታሙ
አንድ ታካሚ ከባድ የሆነ የወገብ አደጋ ደርሶበት ዶክተር ጋር በጠዋቱ ይመጣል:- ዶ/ር:- "ወገብህ እንዲህ እስኪሆን ድረስ ምን ገጥሞህ ነው?" ታካሚ:- "ይሄወልህ ዶክተርዬ ስራዬ ሌሊት ነው ታዲያ ዛሬ ጠዋት ኮንዶሚኒዬም ቤታችን ስገባ መኝታቤት ከሚስቴ ጋር የሆነ ሰው ሲያንኮሻኩሽ ሰማሁኝ: መኝታ ቤቱን ከፍቼ ዘው ብዬ ስገባ ሚስቴ ብቻ ነው ያለችው። 🚢🚢🚢 የቤቱ ሁኔታ ግን የሆነ ሰው እንደነበረ ያስታውቃል: ከመኝታ ቤት ወጣሁና በረንዳው ላይ ሆኜ ወደታች ስመለከት የሆነ ሰው ሱሪውን እየታጠቀ ሲሮጥ አየሁኝ... ዶክተርዬ በጣም ተናድጄ ስለነበር ጉልበቱን ከየት እንዳገኘሁ ሣላውቅ ሳሎን ያለውን ፍሪጅ አንስቼ ወረወርኩበት... ያንን ከባድ ፍሪጅ ሳነሳ ነበር ታዲያ ወገቤን ያመመኝ" ዶክተሩ ይሄን ታካሚ ካከመ በሁዋላ ሌላ ታካሚ መኪና የተገጨ በሚመስል ሁኔታ ሰውነቱ ቆሳስሎ ይገባል:- ዶ/ር:- ምንድነው የመጀመሪያው ታካሚዬ ሲገርመኝ ያንተ ደግሞ ባሰ! ምን ሆነህ ነው? 🚢🚢🚢 ታካሚ 2:- "ይሄውልህ ዶክተር ዛሬ አዲሱን ስራዬን የምጀምርበት ቀን ነበር ድንገት አርፍጄ ተነሳሁኝና ከቤቴ ስወጣ ሱሪዬን እየለባበስኩኝ እየሮጥኩ እያለ ከየት መጣ ያላልኩት ፍሪጅ ላዬ ላይ ወደቀብኝ!" ዶክተሩ ይሄንንም አክሞ ከሸኘ በሁዋላ ሌላ ታካሚ ይገባል:- ይሄኛው ታካሚ ደግሞ ከሁለቱ በባሰ እና በሚዘገንን ሁኔታ ቆሳስሎ ነበር የገባው:- ዶ/ር:- ኧረ ዛሬ ምን አይነት ቀን ነው!? አንተ ደግም ምን ሆነህ ነው? ታካሚ 3:- "ዶክተር ለምን? እንዴት? ማን? ብለህ እንዳትጠይቀኝ: ዛሬ ጠዋት ፍሪጅ ውስጥ ገብቼ እያለ ከፎቅ ላይ ተከስክሼ ነው! 😶
አዳም ምን ይል ይሆን የመጀመሪያው ሰው ዝንጀሮ ነበረ ከእለታት በኋላ እየተቀየረ እየተቀየረ የፍጥረታት አባት አዳምን መሰለ ይህን አውቆ ቢሆን አዳም ምን ይል ይሆን ነጭነት ንጉስ ነው ጥቁር ደግሞ ባርያ ታላቅ ቋንቋ እንትን ነው ታናሽ የነእንትና ሰው ከሰውነቱ በልጦ ሀይማኖቱ ተቀልቶ አንገቱ በብሔር በጎሳ በአገር ተከፋፍለን ይህን አውቆ ቢሆን አዳም ምን ይል ይሆን ሰውና እንስሳ አንድ ላይ ሲ፡ዳሩ ወንድ ከወንድ ጋር ሴት ከሴት እያሉ ተፈጥሮን ታሪክን እረስተው ሲኖሩ እንትና ይገደል ሺ አመት ይንገስ እሱ የኔ አምነት ትክክል ህግን እየጣሱ ባልኖሩበት ሰአት በታሪክ አሻራ ውለታ እየረሱ በዛኛው ጊዜ ቂም ዛሬን ሲያቆሽሹ ይህን አውቆ ቢሆን አዳም ምን ይል ይሆን ልገምት አዳም " ከፍጥረታት ሁሉ ዘሬ ያስፈራኛል ስለ ሰው ስለሰው የሚስቴ ይበቃኛል ደፍሬ አሎጣም ከዘሬ ለመዋል እንኳን እኔን ቀርቶ ፈጣሪን ሰቅለዋል"
አስደግማብኝ ነው... ለሰባት ጠንቋይ ልጅ ለደብተራ ምርኩዝ ጠጠር ገበጣ አርጋ ላኬር ዕጣው እርኩዝ "ይቺን ያየ' አስብላ መሬት ልታስገባ ድቼ ልታስበላ የስር ማሽ እንጉዳይ የኮከብ ቆጣሪ የነ መገን ቦቃ የነ ጥና ጠሪ ያንደርቢ ቁጣ የአመድ ላይ ዘዋሪ የመዳፍ አንባቢ የሞራ መርማሪ ለመቃብር አፈር መንገድ ላይ ቀጣሪ መተተኛ ፍቅር ልብ ላይ ቀባሪ የቀን ስደተኛ አርጋኝ የሌት ዟሪ አቅሌን እያሳተች ምታስብለኝ እሪ አስደግማብኝ ነው... አስደግማብኝ ነው "በርሶ መጀን" ብላ "ላሜ ላቴ ዱርዱራ ገደፈሬ ኡብዝራ ጮርቃ ጩቃ ገጠ ለፌ ሊስ መላሌ ወአክናፌ" "በርሶ መጀን" ብላ የልቤ ሳይበቃት ልቦናዬን በልታ ጨፌ እየነከሰች በጉልበት ተደፍታ ኩራቴን ልትነጥቀኝ ኮርታ ልትማታ ተማ'ታም ልትረታ... ጥላዬን ጀማው ፊት መሬቱ ላይ ዘርታ "ያዙልኝ" እያለች በጠንቋይ ቱፍታ መለመላ ነፍሴን ወናየን ዘርግታ "ታሞ ይኑር" ብላ እኔን አስወግታ እርጋታዬን ነጥቃ እኔን ከኔ አጣልታ በደብተራው ምርኩዝ ባስነካችው ኩታ እንዳነክስላት ጅስሜን አስመትታ ህልሜን እንዳልሰማ ልቤን አስደምታ አስደግማብኝ ነው ''ናልኝ'' ብላ ጠርታ የሆንኩ አንገት ደፊ የሆንኩት ከርታታ መለየት ያቃተኝ ቀኑንና ማታ አስደግማብኝ ነው... አስደግማብኝ ነው ለነ ጥላ ወጊ ለመጫኛ ነካሽ ለነ አፍዝ አደንግዝ ለዱር ቅጠል በጣሽ ላውልያ ለጠንቋዩ ለኑግ ቂጣ ቆራሽ ለመንገድ ገርጋሪ ለውቃቢ ዘራሽ ለገሃድ ስውሩ ለነ ጽናት አፍራሽ ለምድር ላየሩ ለየሎስ አጎንባሽ ለባሕር ለየብሱ ለጠቋሪት ደጋሽ አስደግማብኝ ነው ወለም ያላለኝን ዘላለም የምታሽ አስደግማብኝ ነው👨🦯 -ሰለሞን
🍶 ያረቄ ቤት ስንኝ ብንጠጣም ባንጠጣም የሚወራ አናጣም ባልኮል በጅን ቀርቶ ስካር ክብሩን አቶ በነገር ስንሰክር አለን ድንቅ ወሬ ሊቅ የሚያከራክር ደሞም እንደወጉ መለኪያ ገልብጠን ከሚጠጣው ጋራ ሻጯንም አግብተን ካሻን ከበርሜሉ ሳንታክት ተግተን ጠጥተን.. ጠጥተን ጠጥተን ጠ.ጥ.ተን እንኳን ሚዛን ቀርቶ ቤታችንን ስተን ብንጨብስ አይገርመን ብንሰክር አይደንቀን ሚያዳምጥ ነው እንጂ ሚወራ መች አተን!! ቁም ነገር ያዘለ ስንኝ ተሸክመን አንባቢ እስክናገኝ ተግተን እንጠጣለን። እንጠጣለን አቦ ትርጉም እስኪሰጠን ገጻችን ተነቦ።
ባህር ለሙሴ ተከፈተ.. አንበሶች ለዳንኤል ትራስ ሆኑት ዓሳ ለዮናስ ማደርያ ፀሀይ ለኢያሱ ቆመችለት (ቁራ ደግሞ ኤልያስን መገበው...) እኔ ግን ቁራ ደጄ ላይ በክንፉ መዞሩ ይብቃኝ #ክርስቶስ እራስህ ወርደህ ምናለ ቤቴን ብትቃኝ ለሙሴ በትር ያበደርክ ለዳንኤል አውሬ ያራራህ የችኩል ኑሮ ሲጠልፈን በኔ ላይ ታሪክ ምን ሰራህ?? ፀሀይን ቁሚ አልላትም ብትፈልግ ስትሄድ ታንጋው ይልቅስ ሺ ጥያቄዬን #ይሁን ብቻ በማለት ምኞቴን ባንድ ቃል ዝጋው በኔ ላይ ምን ፀጋ አወረድክ??? በኔ ላይ ምን ፀጋ አወረድክ ከጀምበር እስከ አመሻሽ ድመትም ያበራየኛል እንኳንስ አንበሳ ላሻሽ ምን አደረክ በዶሴዬ ሚፃፍ መች ቸርከኝ የጀግና ገድል ስፍቅ ነው እየኖርኩ ያለሁ ቢደርሰኝ የአንድ ቀን እድል #ስላልኩኝ መልሱን ጥበቃ አይኖቼን ከላይ ባንጋጥም ከሰማይ ድምፅ መጣልኝ አደመጥኩ ሰማሁ በርግጥም #እርሱም እንዲህ ይላል... ማናባህ በሰጠህ #ቃል ነው የፃፍከው ይህንን ግጥም #አስታወሰኝ🙂
በዚያ ሄድኩ አትበይ በዚህ አትለፊ ከመንጋው ተነጠይ ቤትሽን ቆልፊ ስልክ አትጠቀሚ ፕሮፋይልሽ ጋር አንዳች አትለጥፊ ውቅያኖስ አቋርጭ ባህሩን ቅዘፊ ቁራኑን ተቀሪ ፆመ ድጓ ቀፅይ መወድስ ዝረፊ ግና አደራ እምልሽ ከሱባኤ ማግስት በኔ ስም ግደፊ
☕️ Biological Magnification (Bio-Magnification) 📚 ባዮሎጅካል ማግኒፊኬሽን ሚለውን concept ለመጀመሪያ ጊዜ ያወኩት "እመጓ" በአለማዬሁ ዋሴ እሸቴ ላይ ነበር ። 🗝️ ሃሳቡምንድነው? ✍🏽 ሃሳቡ አንድ ቁስ አካል ለምሳሌ መርዝ ከትንሽነት ወደ ትልቅነት በምግብ ትስስር ሂደት (food chain ) ማለትም እንበል እና አንድ አይጥ መርዝ በልታ ብትሞት፤ የመርዙ መጠን በአይጧ ሰውነት ልክ ያድጋል። እና ከዛ በአካባቢው የሚገኝ አሞራ እሷን ቢበላት ያቺ ትንሽ የነበረች መርዝ አሁን ላይ ከአይጡ ሰውነት size ሁላ በልጣ ያንን አሞራ ወደ ማከል አድጋለች። ከዛ ደሞ ይሄ አሞራ በቀበሮ ቢበላ የመርዙ መጠን ወደ ቀበሮው size አደገ ማለት አይደለ። ✍🏽 ይሄንን concept ወደ ሰው ሕይወት አምጥቼ ለማየት ሞክሪያለሁ እንዴት relate አረከው አትሉም? 👉🏽 አንዳንዴ እኛ በስህተትም ሆነ ሆን ብለን ሰውን ለመጉዳት ብለን ምናደርጋት ክፋት ወይም ትንሿ መጥፎ ንግግር የዛንን ሰውዬ ሕይወት ሙሉ በሙሉ የመረበሽ አቅም አላት። ከዛ ይሄ ሰውዬ በኛ ሰባሪ ንግግር ወይም ድርጊት የደረሰበትን በደል ሌላ ሰው ላይ ቢወጣው ወይም እሱ ራሱ ሌላ ሰው ላይ እኛ ያረግነውን ነገር ቢያደርግ( ከሰው ያየነውን ነውና ምናደርገው) እና ከዛ 3ተኛው ሰውም ተመሳሳይ ነገር ቢያደርግ ያቺ ትንሽ ንግግር የሰውን ባህሪ ከአንድ አንድ እየቀየረችው እንደምትሄድ አስቡት ። ምናልባት ይህን በሌላ መንገድ ላሳያቹ ልሞክር 🧘🏾..ከጥንት ጀምሮ በተለይ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 6ኛው ክፍለ ዘመን የአምላክን ህልውና የመጠራጠር ትንሽ መርዝ ነበረች በ 17ኛውና 18ኛው ክፍለ ዘመን ላይ የብርሃን ዘመን በማለት የፈጣሪን አለመኖር የሚሰብኩ ብዙ ህዝብ እንደነበር.....! አእምሮን እና ሳይንስን መሰረት ያደረገ አስተሳሰብ መብዛት ጀመረ... አሁን መርዙ የት ደርሶ ይሆን በጥንተኛው ዘመን የፈጣሪን ህልውና መኖር የሚጠራጠሩ ያልተደራጀ የግል እሳቤ ያላቸው ጥቂቶች ነበሩ አሁን ባለንበት ክፍለ ዘመን ደሞ በአለም አቀፍ 82% ያክል የአለም ህዝብ ሀይማኖተኛ አልያም ፈጣሪ አለ ብለው የሚያምኑ(Religious /Believes in a creator)ሲሆን ከ5-7% ያክል የአለም ህዝብ ደሞ አሁን ላይ የፈጣሪን መኖር የማይቀበሉ (Atheist) እንደሆነ ጥናቱ ያሳያል። በBio-magnification :- food chain የሚለውን concept ወደ Idea_chain ቀይረን ስናየው ሃሳብም ይህን አይነት እየሰፋና እየበዛ የሚሄድ ሰንሰለት መሆኑን መረዳት ይቻላል። (አንዴ በሰው ልጅ አእምሮ የታሰበና በቃል ተደግፍ የወጣ ማንኛውም ነገር ቀስ በቀስ እየሰፋና size እየጨመረ ይሄዳል እንጂ የሚሞት አይደለም።) 🔓ሀሳብም አንደበትም እሳት ናቸው ወይ ብርሐን ይሆናሉ አልያም የፍጥረትን ሩጫ ያቃጥላሉ። ቅዱስ መጣፍ🪞
😶 ከእልፍ አመፃ ድምፅ ውስጥ፥ ጎዳቸው የኔ አርምምታ ጠየቁኝ ስለ ሀቅ መውደቅ፥ <ፍትሃት አላት ወይ ዝምታ¿> መለስኩ ... ቃልስ ምን ትርጉም አላት፥ የሆነን ከማውራት በላይ እውነትን የሰበኩትስ፥ እውን ቤት አላቸው በሰማይ⁈ ይህንን አውቃለው ደግሞም አምናለሁ... ወንጭፍ ወርውረዋል፥ ተማምነው በእግዜር ኃያልንን አቅም ነስተዋል፥ግዙፉም ወድቋል በጠጠር ይ'ንንም አውቃለው.... ደሞም አይቻለው፥ ተሟሽቶ ባልበቃው ዐይኔ.. ጎልያድ በሰይፍ የቀላው፥ ብዙ አንገት በዚች ዘመኔ እኔስ ዝምታን ክጄ፥ እኔስ አርምሞን ትቼ ልናገር ስልጣን ቢኖረኝ.... በቃሌ መች አስሬ ? በቃሌ መች ፈትቼ ታድያ.. ነፍሴ በላይዋ ትሰይጥን ፥ መለኮት ኃይሉን ገፍታ ወይንስ በእምነት ትፅና ፥ ከቀንዳም ጭራቋ ጠፍታ⁉ እንጃ ብቻ... .ምን ገድል ፥ ጎልቶ ቢፃፍም ካላለው ግን ፥ ግብሩ አያልፍም ምን ቀልቤ ፥ ረግቶ ቢያርፍም ያቃጥላል ፥ ውስጤ ከፍም በዚች አለም- ተጋድሏቸው ፥ ወድቆ ባይቀርም በዘመኔ.. እኔ እንጂ ፥በኔ ነብስ ዳዊት አይኖርም