ቶጳዝዮን
Статистика"ቶጳዝዮን"ማለት ቢጫ የከበረ ድንጋይ ፣ዕንቍ ማለት ነው። በተስፋ የተቃኘዉን ሀሳባችንን እና ስሜቶቻችንን በዕንቊ ቃላቶች እያዋዛን በብዕራችን የምንገልፅበት ምርጥ ቻናል ነው። ለማንኛውም አስተያየት👇👇 @Ediwub @Tirrubel
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 7
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 582
- 1/48двое суток
- 666
- 1/72трое суток
- 719
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
🗒 . . ላይድን ቁስል፤ ጨዉ መነስነስ፤ ከድንጋይ ላይ፤ ዉሃ ማፍሰስ ፤ ለሟች ዘመድ ፤ ዳግም ማልቀስ፤ መኖር ካሉት፤ እንደዚህ ነው፤ ሳቅን ትቶ፤ መንሰቅሰቅ ነው። 🖊ዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn
መውደዴን ለንፋስ ነግሬው - ይዞብኝ ሄደ መልክሽን በብራና ስዬው - ተቀደደ ስስቴን ባሰፍረለት ለባህር ሳቀብኝ እንደክፉ መምህር ስላንቺ ሚሰማኝን ለሰማይ ብነግረው አመቱን በሙሉ - ክረምት አደረገው በነፍሴ ያመላለስኩት በአጥንቴ የታመምኩት ለሳር ለቅጠሉ ብለፍፍ ተቆጠረ እንደሴተኛ አዳሪ እድፍ! አየሽ ! ለዚህ ነው የምጎዳው - ለዚ ነው ምትጎጂው ለማይሰማኝ ነውና የማወራው ለማይሰማሽ ነውና የምታስረጂው! እወቁልን አያሻንም ይቅር አንታይ ከጫፍ ጫፍ ብንታመም ዝም እንበል እንደሚጠረብ ዛፍ አንዳንድ ልክ አለ ቢነገረም የማይጠቅም - ቃልን ዝምታ ያሳከለ አንዳንድ እውነት አለ አንዳንድ ህመም አለ - ብንለፋ ብንጥር እያነሰ ሚሄድ ባስረዳነው ቁጥር! ኤልያስ ሽታኹን @topazionnn
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የምትመለከቱዋት ወጣት ታዳጊ ኤልሮኢ ቅዱስ ትባላለች በአጥንት ካንሰርን ህክምና ላይ ትገኛለች በሽታው ከታወቀ አንድ አመት ሆኗታል በበሽታው ምክንያትም አንድ እጇ ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ተደርጓል ሆኖም ግን ኤልሮኢ ተስፋ ሳትቆርጥ ህክምናዋን እየተከታተለች ነው አሁን ግን በሽታው ወደ ሳንባዋ በመሠራጨቱ የመተንፈስ ችግር ስላጋጠማት በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ Heal Venture Medical and Surgical Center በ ICU ትገኛለች ሆኖም ግን በአሁን ሰአት ላይ የሆስፒታሉ ወጪ በቀን ከ50.000ብር ነው ከቤተሰብ አቅም በላይ ስለሆነ የኛን እርዳታ ትሻለች CBE - 1000487578828 TeleBirr - 0911179293 Awash Bank - 013471629151800 ሁሉም አካውንት ስም - Rahel Aregay እህታችን ትፈልገናለች እንድረስላት 🙏
https://vt.tiktok.com/ZS4nCewBf/
ቶጳዝዮን pinned an audio file
ይህችን ጥዑም ግጥም ተጋበዙልኝ🥰 ✍ዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn
ትንሣኤሽን ልየዉ ውዳሴሽን አንብቤ ቅዳሴሽን ሰምቼ፣ በዝግ ባዕት በሱባኤ ሰንብቼ። ትንሳኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። ስብሐተ ነግህ ን አድርሼ፣ ድርሳን ስንክሳሩን ከልሼ። ቅዳሴን ላስቀድስ ከበራፉ ታዛ፣ አለሙን አስትቶ ለነፍስ የሚያስገዛ። ትንሣኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። እንደ ሐዋርያዉ ትንሣኤሽ ይታየኝ፣ ከነጩ ሰበናት በረከቱ ይድረሰኝ። ዕርገትሽን እንዳይ ፍቀጂ እናቴ፣ በጸሎት በምልጃሽ ይሞላልኝ ቤቴ። እንኳን አደረሳችሁ🙏 ✍ዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn
@topazionnn @topazionnn
'ማር' ጣፍጦን ቀደመ 'ቃል'ን ስናስከትል፣ 'ኪዳን'ን ረስተን እንኖር ይመስል፤ ...... አልፎ አልፎም ብናስብ አጭር ጊዜም ቢሆን ትዝታም ባይኖረው፣ የአንዳንድ ሴት ቃላት እልፍ ልቦችን ነው አዙሮ ሚሰብረው፤ ....... መጀን ለሷ በሏት እኔስ ታምኛለው እኔነቴን ትቼ በሷ የመጣውን፣በሷም ያወኩትን እምነቴን ፈርቼ፤ አመስግኗት እሷን! መንገድ ለሆነችኝ ለንሰሀ ደጁ ሀጢአቴን እንዲሽር ለለመንኩት ልጁ፤ እሷ ግን.... በየተባእት ልብ መትረፍረፉ ይብቃት ንሰሀዋም ይድረስ ምህረቱም አይራቃት ደግሞም ይመርባት ከያኔው ደምግባት ልቧ ቢጨንቀውም ሀቄም ቢኖርባት! በቃ ትዝታም አትሆንም 'ማነች?' እንጂ! @Weyblann ✍️
@topazionnn @topazionnn
መሳሳት ክልክል ነው! (elias shithaun)
እሾህ ነው (ኤልያስ ሽታኹን)
አልሰጋም ይሄን ዱር አልርድም ለጥሻው .. ለፅልመት ጭለማው ለመናፍስት ውጊያው ሰው መሆኔን ብቻ እኔ የምፈራው !! (ሚካኤል. አ) @topazionnn
ፈረሰኛው ሰባት አክሊል ተጎናፅፎ አተረፈኝ ከ ዓለም ዘንዶ እኔን አቅፎ የተፈጨው በ ጣኦታት መንኮራኩር ደረሰልኝ በቀማኛ ስመዘበር ገበዝዋ ነው ለ ኢትዮጵያ ለሀገሬ በፈረስህ ጊዮርጊስ ደርሰህ ቁም ከበሬ 23 🔥 ሰማዕቱ አባቴ🙏🏻! እንደ ተፃፈ... ✍ @Seb_at7 ✍ @truthwater
.... እንደ ሬትም 'ቢመር' ጣፍጦ እንኳን 'ቢያቅር' ለኔ... አይጎዳም ፣አይጠቅምም ትምህርት ነው 'ፍቅር'! @Weyblann
ሊጤን.... ባልተቤትሽ ገባ ቤቱን አሟሟቅሽው ቡናውን አቡነሽ ወጡን ወጠወጥሽው ራትም ተበላ ሳቅ ደስታው ፈሰሰ እጣን ጭሳጭሱም ከቤቴ ደረሰ እቃው ተነሳስቶም አልጋው ተሰናዳ የውል ደንብ ሊደርስ ተገባ ወደ ሜዳ፤ .... (ጩኸት ይሰማል! ) እኔ ላጤው እኔ ጅሉ ቀስሬ አለው!..ከደውሉ 'ወጡን ስትወጠውጥ' የጀመረ ጆሮ አቦል ቶና እስኪሉ አለ ተገትሮ ጩኸቱ በርትቶም አቀስሬ ሳለ የታጠፈ አንጀቴ አላስጨርስ አለ፤ (በሉ እንግዲ!) የረሀብ አለንጋ ሆዴን ከሚልጠው፣ እኔም.... እጄን ተጣጥቤ 'ሊጤን ልለጥልጠው'! ያቡ✍️ @Weyblann
.... አልደውልብሽም «እናቴ ትሙት»ብየ፣ ይሄው ደወልኩኝ ዛሬ ቀድሜያት ሞቻለው ብየ፣ ውሸታም እንዳትይኝ!... አልሆንልህ ቢለኝ ትዝታሽ ከምሞት ገድያታለው፣ «ከልዤ በፊት» እያለች ስትፀልይ ሰምቻታለው። 𝑏𝑦 𝑔/𝑚𝑒𝑑ℎ𝑖𝑛 𝑎 @gtmnbegtm @topazionnn @topazionnn