tgindex
ጥበበ ሠናይ 🥀

ጥበበ ሠናይ 🥀

Статистика

ጸጥታ የሰፈነበት የትህትና እና የጸጋ ግዛት ወደ ሆነው የዘረ ሠናይ መቅደስ እንኳን በደህና መጡ። የትህትና ቃላት ውበትን እና እውነትን ወደሚያንሸኳሽኩበት፣ጸጥ ወዳለው የዘረ ሠናይ መቅደስ ይግቡ። በዘረ ሠናይ ቃላት ውስጥ፣ መፅናናትን እና ነጸብራቅን ያግኙ፣ የህይወት ትንንሽ ተአምራትን ረጋ ብለው ያስቡ። እያንዳንዱ ስንኝ ለአለም ተወዳጅ ስጦታ የሚያቀርብበትን @Prince_Zeresenay ስራ ያጣጥሙ።

Последний пост
20 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
885
−1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 199
20 постов
Вовлечённость
135,5%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
323
1/48двое суток
370
1/72трое суток
399

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ሲዖል ስትገባ ከረፋት እግዜሩን ለመነች ሰማት ዘለቀች ወደ ገነቱ ግን እዚያም... ብሶ ቢቆያት ክርፋቱ አንድ ነው ብላ ሁለቱ ለአምላኳ ሰደደች ክሷን ምስኪን... ያሸተተችው ራሷን Red-8

  • ሰበራት ክፋቱ ፅገሬዳይቱን ቅንጥስ አረገና ይብላኝ ለዛ ገልቱ እሷስ ተነስታለች ሽቶ እና ማር ሆና

  • 10 июл.2 55720

    የ self development መፅሀፍ ይፈልጋሉ እንግዲያውስ ይቀላቀሉ https://t.me/Amharic_Books_storee

  • 31 мая991113

    እስኪ ምን ላርግልሽ ካንቺ የተፀናወተኝ ማፍቀሬ እንዲገባሽ ከአይኖችሽ የያዘኝ መውደዴ እንዲታይሽ ንገሪኝ የኔ ዓለም እስኪ ምን ላርግልሽ ከሰማይ እስከ ምድር ወጥቼ ወርጄ ስልጣን ተበድሬ በዓለም ሚኖሩትን ሕዝቡን ሚገዙትን ነገስታትን ሽሬ ለዘውድሽ እንድትሆን ከሰማየ ሰማይ ፀሐይን አውርጄ ግርማሽ እንዲያስፈራ መጎናፀፍያሽን በእሳት ጋርጄ ከሰው ሁሉ እንድትልቂ ተከብረሽ ተነግሰሽ ዉበትሽ እንዲታይ እንዲጎላ መልክሽ ጨረቃን አውርጄ ልሰራት ካንገትሽ ? ኮከብ አዋቅሬ ልብስሽን ልስራልሽ ? ከእሳት እና ከዉሃ ዙፋን ልገንባልሽ ? ስምሽ እንዳይረሳ ዓለም እንዲያስታውስ ትውልድ ሁሉ እንዲያውቀው ቃላት እየመረጥኩ ግጥም እየፃፍኩኝ መልክሽን ልሳለው ማፍቀሬ እንዲገባሽ መውደዴ እንዲታይሽ ንገሪኝ ፍቅሬ ሆይ እስኪ ምን ላርግልሽ ? ንገሪኝ ዓለሜ የሚሆን ባይመስልም እኔ አደርገዋለው

  • 24 февр.1 526114

    [ እንዴት አመሻችሁ ፥ ግጥም እንገርብ እስኪ] የስለት ልጅ የሆንኩ ይመስል በጠዋት ማታ ስቆስል ሥጋዬ የልመት ፥ ነፍሴ የድባቴ ከናቴ ነው ወይስ ካባቴ ከማን ቢጠጋ እጣዬ እንዲህ የበዛው ጣጣዬ? ኩሬ እንኳን ሲሆን አስጣሚ ዕድል ነው ወይ አጋጣሚ? ድር እንኳን ሲጥለኝ ጥልፎ ሁልጊዜም ባይሆን አልፎ አልፎ አልፎ አልፎ [ስስቅ] አልፎ አልፎ አልፎ አልፎ [ሳለቅስ] አልፎ አልፎ ድብታ እምባዬን ልፎ ሲሸቀሽቀኝ እንደ ጦር ባልጋ ላይ ተኝቼ ስጦር እንቁዬን ለማንም ስጥል እንደ ባላባት ቅምጥል ልክ እንደ አመለ-ቅንጡ ኧረ ምኑ ቅጡ! ኧረ ምኑ ቅጡ! ጌታዬ አንተ ጌታዬዋ አትሞላልኝም ወይ የተስፋዬን ፅዋ? ባላድርም እንኳን ለማምሻ ተስፋ ስጠኝ እንጂ ለቅምሻ ምን አልኩኝ የነፍሴ ልምሻ አብሮኝ ሲያድግ እንደ መንታዬ? ተስፋ እኮ ነው የሚርበኝ ጌታዬ! ተስፋ እኮ ነው የሚጠማኝ ጌታዬ! መቅደስ እንደገባ ውሻ እንድ ሰካራም ቅርሻ "ክፍ" አልባል "እንትፍ" አትስጠኝ የዕድሜ ትርፍ ልክ እንደ ጨርቅ ስተረተር ልታድነኝ አትውተርተር ልትጠግነኝ ተው አትልፋ ብቻ ስጠኝ ተስፋ ትንሽ ተስፋ ብቻ አትተወኝ ለብቻ! አባብለኝ ጌታዬ ፥ አባብለኝ ደልለኝ ጌታዬ ፥ ደልለኝ ባታድነኝ እንኳን ፥ "ትድናለህ" በለኝ! 🖤 🖤 🖤 ዮናታን

  • 17 февр.1 27683

    በቀን ወይ በሌሊት በፆም በቅበላ የበላ ይኖራል ይብላኝ ለተበላ ጋጋሪው ቢራቀቅ ቢሰወር ምጣዱ የዕለት እንጀራ ነው አንደኛው ሰው ላንዱ በዕውቀቱ

  • 12 февр.1 45199

    "ትንሽ ቅር ብሎኛል, ግን ደስም ብሎኛል:: ትዝታሽ እየደበዘዘ ናፍቆትሽ እየፈዘዘ ነው :: ከመልክሽ በላይ የተሰሙኝ ስሜቶች ብቻ ትዝ ይሉኛል:: ተረስቶ ለማስታወስ እንደምንሞክረው የሌሊት ህልም, ልትጠፋ እንደደረሰች እንደሻማ ብርሃን:: ትንሽ ጭላንጭል ብቻ. . . ትንሽ ትውስታ ብቻ . . . እየረሳሁሽ ነው"

  • 6 февр.1 44452

    ወደ እኔ እስክትመጪ ስንት ቀለም ይንጠፍ ስንት ብዕር ልጨርስ ስንት ግጥም ልፃፍ ስንት መጽሃፍ ልድረስ እስክታዪ ናፍቆቴን እስክትመጪ ድረስ ልብሽ እስኪወስን ስንት ቃላት ልድማ እስክትወጂኝ ድረስ ስንት ሀረግ ላስማማ ወደ እኔ እስክትመጪ ስንት ግዜ ኪሪያላይሶን ስንቴ እግዚኦ ልበል ሱባኤ ገብቼ ስንት አመት ልከልከል ወደ እኔ እስክትመጪ ስንት መስክረም ይጥባ ስንት አደይ ይርገፍ ስንት ክረምት መጥቶ ስንት በጋ ይለፍ ስንት ዝናብ ይምታኝ ስንቴ ልደር ዉጪ መወደዴ አሸንፎሽ ወደ እኔ እስክትመጪ @Prince_zeresenay

  • 29 дек.1 465107

    ልጅ ሆኜ ስማር በሂሳብ ቀመር "እዚህ ጋር አንድ አለኝ" የሚል ስሌት ነበር ዛሬ በዙሪያዬ በከበበኝ አለም አንድ ነገር አለኝ ብዬ የምመካበት አንድም ነገር የለም (ካንቺ በስተቀር !) ይሄን ወና ህይወት ስደምር ሳባዛ ደሞም ሳካፍለው "እዚህ ጋር አንድ አለኝ" የምለው አንቺን ነው ! ኤላ

  • 24 дек.1 476131

    ወደ እኔ እስክትመጪ . . .

  • 22 дек.1 165106

    እኔን ብለሽ እንደማትመጪ ፥ አይኖችሽን እንደማላያቸው ፥ አቅፌሽ ናፍቆቴን እንደማላሳይሽ ፥ ስሜሽ የፍቅሬን ጥማት እንደማልቆርጠው ፥ መጥተሽ የፍቅር ቁርባን እንደማንቆርብ ፥ አብረን እንደማንሆን አውቃለሁ. . . ግን ይህን ልንገርሽ ከዋክብት ሞልተው በፈሰሱበት ሰማይ ብቸኛዋ ጨረቃዬ እንደሆንሽ ፥ ሚሊዮን ፊቶች በሞሉባት ዓለም አንድ ያንቺን ዉብ ፊት ስፈልግ እንደምኖር ከብዙ ዝናብ እና መብረቅ በኃላ እንደምትወጣ የክረምት ፀሐይ እንደምናፍቅሽ ፥ እንደምቃጠል እያወቅኩ ያለፍርሃት እጄን የምሰድባት እሳት እንደሆንሽ ፥ ማርና ወተት እንደሚፈልቅባት የከንአን ምድር ተስፋዬ እንደሆንሽ ልንገርሽ ፥ እንደማትመጪ ፀሐይ ስትጠልቅ አብረን እንደማናይ ምድርም እንደማትችልሽ አውቃለሁ ግን ተናፍቀሽ ባማታውቂው ልክ እንድናፍቅሽ ተፈቅረሽ በማታውቂው ጥልቀት እንዳፈቅርሽ ፍቀጂልኝ. . . ለአንዴም ቢሆን. . . @Prince_Zeresenay

  • 18 дек.1 080112

    ራሴን እንዳነበብኩት...የዓለምን ልብ ወለድ ናቅሁት። ረገምኩ ላሥሥ መድከሜን ፣ እንቁ ላይ ፈዞ መቆሜን ፣ በወርቄ ጠጠር መልቀሜን ፣ ኮንኘ ገለጥኩ ራሴን... @Prince_Zeresenay

  • 15 дек.1 12063

    ያንቺ ሥለሆነ ነው ከስጋ ፀባያት፣ ከባህርያተ ነፍስ እንደተሰራ ሰው ከአይኔ ፍህም እሣት፣ ከልቤ ዉቅያኖስ ከጥልቁ ሚፈሰዉ በመሬቱ ገላዬ፣ በሀሳቤ ነፋሳት በብርቱ ሚነፍሰዉ ከነፍሴ ነፍስ ነስቶ ካንቺ አይን ሚታየው ከእኔ ፀሐይ ሠርቆ ባንቺ የሠረፀው ካንቺ በላይ አንቺን ፍፁም የሚወደው የልቤ ሙሉ ልብ ያንቺ ስለሆነ ነው።                  @Prince_Zeresenay

  • 11 дек.1 164108

    አሁንም ትናፍቂኛለሽ . . . እንደ ትንናት አይደለም ፥ እንደ አምናው አያመኝም ፥ የናፍቆሽ ህመም በየዕለቱ ጀንበር ጠልቃ በወጣች ቁጥር ቀንሷል . . . በእኩለ ሌሊት ከእንቅልፌ ስባንንም እንደድሮው ያንቺን መልዕክት በማሰብ ስልኬን ለማየት አልጓጓም ፣ ባለፈው መንገድ ላይም የምንወደውን ሙዚቃ ስሰማ ዉብ ፈገግታን ቸረኝ እንጂ እንደድሮው አልከፋኝም . . . የጠረንሽ ጥፍጥና የፈገግታሽ ዉበት ከህሊናዬ እጅጉን ርቀዋል ፣ የድምፅሽ ቃና እንደሚያልፉት ቀናቶች ከአዕምሮዬ ማህደር ሸሽቷል። ነገር ግን አሁንም ትናፍቂኛለሽ. . . ደስ ሊለኝ እንደሚገባ ባውቅም እየረሳሁሽ እንደሆነ ሳውቀው ጥቂት ከፍቶኛል፣ ጥቂት ቅር ብሎኛል። @Prince_Zeresenay

  • 9 дек.1 0168

    " ትንሽ ሰክራለች። በመንገድ ላይ ከሌላ እሷነቷ ጋር እየተነጋገረች ነው መሰል ዝም ብላ  ትራመዳለች። ከዋክብት በሀዘኗ ምክንያት መሬት የተነጠፉ ይመስላሉ ነፍሴ ነፍሷን እየታከከች ሀዘኗን ታሰማኛለች።ሀዘኗ እንደ አርያም እማይመረመር ጥልቅ ይሆንባትና በገዛ እንባዋ ውስጥ ሰጥማ ስትሰቃይ ይሰማኛል. . . "

  • 5 дек.1 167112

    ልቤ ሆይ ስለምን አብዝተሽ ትጨነቂያለሽ ? የመንፈስሽን ጥንካሬ አይተሽዋል ፣ የራስሽን ዉበት ተመልክተሽዋል ፣ ወርቃማ ክንፎችሽን ከንፈሽባቸዋል። ታድያ ስለምን ትጨነቂያለሽ ? ዙሪያሽ ጨለማን ሲለብስ ፣ አለም ሲጨልም ፀሐይዋ አንቺ መሆንሽ ስለምን ትዘነጊያለሽ ? @Prince_Zeresenay

  • 4 дек.1 04242

    አይላክብሽም ህመሜም ቢጠና ከልቤ ወድያ ሰው አያውቅሽምና . . . በልቤ ሰማይ ላይ ከሐምሌ ደመና የከበደ ፍቅርሽን ፤ ለሽራፊ የጊዜ ጠለል ፣ ለአንዲት አፍታ ለአንዲት ቅፅበትም ቢሆን ከምዕናቤ የማይርቅ ናፍቆትሽን ቃላቶቼ አቅም ኖሯቸው ከ ውቅያኖስ ሚጠልቀውን ናፍቆቴን ሳይገልፁ ፤ ሀረግ እና ዓረፍተነገሮች  ከዓለም ስፋት ሚልቀውን መውደዴን ሳያሳዩ ባልፍ ፤ ከእኔ በቀር ሚያውቅሽ የለምና . . . ህመሜ መፅናቱን በብርቱ መናፈቄን እንድታውቂ ምን ላድርግ ? @Prince_Zeresenay

  • 26 нояб.1 07482

    ሙዚቃ ትመስለኛለች . . . አረ ሙዚቃ ነች፡፡ ሙሉ ኦርኬስትራ፡፡ሐምሳ ምናምን ሰዎች ሆነው የድምፅ መአት አቀናብረውና አሰናስለው የሚሰሯት ሙዚቃ፡፡ ስታወራ ቃሏ ይጣፍጣል፡፡ ቃሏ ከማር ሰፈፍ ተሰርቶ እየጣፈጠ በጉሮሮ በኩል ነው የሚገባው፡፡ እየተስረቀረቀ በምልዐተ ማስለምለሙ ሙሉ አንጀትን ይበላል. . . ሳቋ ይታያል፡፡ ሷቋ በፊቴ ፅናውን ይዞ ፥ በተክሌ አቋቋም እያረገደ ፥ ያሬድኛ ማኀሌቱን ሲያቀርብ ይታየኛል. . .

  • 26 нояб.1 091106

    ዝም ስል መናፈቄን ታውቂያለሽ ? ቃላት ከአንደበቴ ባይወጣኝም ላይሽ መጓጓቴን ? ላገኝሽ መቃተቴን ታምኛለሽ ? ሳስታውስሽ ከልብ የተወለደች ውብ ፈገግታ መፈገጌን ታውቂያለሽ ? ዉዴ ዝምታዬ የፍቅር እንደሆነ ይገባሻል ?

  • 26 нояб.1 050101

    ስሜያት ፡ ሞትን ፡ ረሳው ሰውነቷ ፡ ፀሐይ ፡ ጨለማ ፡ ሚያበራ ፣ ፈገግታዋ ፡ ብርሃን ፡ የመስቀል ፡ ደመራ ፣ ድምጿ ፡ ደምፀ ፡ አማልክት ፡ ነፍስ ፡  የሚዘራ ፣ አይኖቿ ፡ ከዋክብት ፡ ለእልፍ ፡  ሚያንፀባርቅ ፣ አንገቷ ፡የቀና ፡ ሰናዖር ፡ የሚያስንቅ ፣ ትንፋሿ ፡ ናርዶስ ፡ እቅፏ ፡ ከነዐን ፣ ፀጉሯ ፡ የሐር ፡ ነዶ ፡ ቃላቶቿ ፡ ወይን ፣ ከንፈሯ ፡ እፀ ፡ ሕይወት ፡ ከንፈሬን ፡ ሲነካው ፣ መፍራቴ ፡ ቀረና ፡ ስሜያት ፡ ሞትን ፡ ረሳው ።    ዘረ-ሠናይ