tgindex
ሐሽማል ቤተ-መዘክር

ሐሽማል ቤተ-መዘክር

Статистика

👉Only for readers 👋መግቢያ👋 መግቢያ ለመግባቢያ ገታ አርገነዋል የቃላትን ግልቢያ እናም በዚህ ሀሳብ ከተስማማህበት ያንኳኳኸዉን በር የገለፅከዉን ገፅ ፈቅደናል ግባበት ምንጭ - ካልታወቀ ገጣሚ Join the group @amharicbooksforeadersgroup አድሚኑን በ ቀጥታ ለማናገር ይህንን ቦት ተጠቀሙ @Digitallibraryofhashmal_bot

Последний пост
11 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
7 883
+24 за 5 дн.
Сутки
+13
+0,17%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 993
22 постов
Вовлечённость
25,3%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
603
1/48двое суток
691
1/72трое суток
745

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 11 авг.699из ጽ ጌ ❤

    без подписи

  • 11 авг.669из ጽ ጌ ❤

    без подписи

  • 11 авг.679из ጽ ጌ ❤

    без подписи

  • ኮርሶችን በአጭር ጊዜ ለመጨረስ እንደዚህ ባለ መልኩ የተዘጋጁ Short ኖቶች ለሁሉም ኮርስ ! አሁንም አልረፈደም ! ምዝገባው አልተጠናቀቀም ... ቶሎ ተመዝግበው ጥናቶን ያጧጡፉ !!! 📢 ለመመዝገብ 250 ብር በ Telebirr እና CBE ክፍያውን ከፈፀማችሁ በኋላ ክፍያውን መፈፀማችሁን ማረጋገጫ Screenshot በ @kelemesupport ይላኩ ! Tlebirr : 0991182353 (Danial ) CBE : 1000286598076 ( Daniel A. ) 🤗 በቡድን ለምትመጡ የ 50% ቅናሽ ! ( አንድ ሰው 3 ሰዎችን ካስመዘገበ የ 50% ቅናሽ ያለው ሲሆን ከዛ በላይ ከሆነ እስከ 25% ድረስ !!! ) ሁሌ እንደምንለው ከናንተ የምንፈልገው ጥረታችሁን - ለሥኬታችሁ ነው !

  • 9 авг.966155

    ስንቶቻችንነን #በትላንትናው ጠባሳችን ፍቅር እየገፋን ያለነው ? ስንቶቻችን ነን በትላንትናው ህይወታችን ምክንያት በፍርሀት ሰው ማቅረብ ማመን የተውነው?? ሰንቶቻችን ነን መልካም ሰዎች እንዳሉ ማመን ያቃተን በትላንትናችን ምክንያት ? ስንቶቻችንነን እሚወዱን እንዳሉ መቀበል ያልቻልነው ? ሁሉም ነገር ልክ አለው እራሳቹን አክሙ ለመዳን አንድ እርምጃ ተራመዱ<<< ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራም ለሚመጣው እንጂ....... ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ

  • 6 авг.1 38710

    без подписи

  • 5 авг.1 475117

    እነሱ : ለምንድነው ሁልጊዜ የምታገኛት ? እኔ : ምክንያቱም ለእኔ ጊዜ ለመስጠት ብላ ብዙ ሰው ርቃለች ። ብቻዋን ልተዋት አልችልም። የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ

  • 2 авг.2 00831

    ምዝገባ ተጀመረ !!! ለ Exit Exam ተፈታኞች 🔷Accounting & Finance 🔷Computer Science 🔷Information Technology 🔷Economics 🔷Management 🔷Nursing በእናነተ ተደጋጋሚ ጥያቄ መሠረት ከላይ የተጠቀሱትን ዲፓርትመንቶች ኦንላይን/ Private ጥናት ጀምረናል ። 💥 በዚህ የኦንላይን ጥናት ምን ምን ያገኙበታል ? 🏷 በአጭር ጊዜ ፈተናውን በሙሉ የራስ መተማመን ያለምንም ስጋት 💯 በ 💯 የሚሰሩበትን ስልቶችና ቴክኒኮችን 🏷 ለማዳረስ ወራት የሚፈጅባችሁን ብዛት ያላቸውን ኮርሶች ከእኛ ጋር በፍጥነት፣ በትኩረት እና በቅልጥፍና ከእኛ ጋር ሆናችሁ በተጠና መልኩ 🏷 በግልፅና በተብራራ መልኩ በየጊዜው የሚዘጋጁ አዳዲስ ጥያቄዎችን 💥Guys ይሄ ከ VVIP ም በላይ ነው! እንደ ሌሎች ብዙ ብር ጠይቀን ያልሆነና ጥራት የሌለውን ነገር አናቀርብም !!! ☝️☝️☝️ ከላይ የተቀሱትንና መሰል እገዛዎችን ለወራት ለናንተ ለማድረስ ስንዘጋጅ ባለው የ " Rekik Success Online Study " ያገኛሉ ! 📢 ለመመዝገብ 250 ብር በ Telebirr እና CBE ክፍያውን ከፈፀማችሁ በኋላ ክፍያውን መፈፀማችሁን ማረጋገጫ Screenshot በ @kelemesupport ይላኩ ! Tlebirr : 0991182353 CBE : 1000286598076 🤗 በቡድን ለምትመጡ የ 50% ቅናሽ ! ( አንድ ሰው 3 ሰዎችን ካስመዘገበ የ 50% ቅናሽ ያለው ሲሆን ከዛ በላይ ከሆነ እስከ 25% ድረስ !!! ) ሁሌ እንደምንለው ከናንተ የምንፈልገው ጥረታችሁን - ለሥኬታችሁ ነው ! https://t.me/kelemeakadami

  • 2 авг.1 60393

    መሄዷ ላይቀር እኔ እንዲህ መታገሌ    ላስቀራት ባልችል እንኳን ላዘገያት ነበር ሀሳቤ            ደቂቃም እድሜ ነው እንዲሉ      ጥቂት አብሪያት መሰንበት ብችል ብዬ.... 💔 ✍️Gosaye 📌ማጋራት አይዘንጋ

  • 30 июл.1 89224из azop78

    በኢግዚቢሽን ማዕከል 23-26 አይቀርም

  • 24 июл.2 512317

    “ምነው አምና በሞትኩ፥ እንዲያ እንዳማረብኝ!?” ዝምታ ይረብሸኛል። ለዚያም ነው፥ መንገድ ስሔድ መጽሐፍ ይዤ የምዞረው፣ ሁሌም ጆሮዬ ውስጥ ‘ኤርፎን’ የምወትፈው፣ ልተኛ ስል፥ ያለችውን ፀጥታ እንኳን ላለማስተናገድ፥ የኾነ ነገር ከፍቼ ነው የምተኛው ... በዝምታ ውስጥ ከመኾን፥ ዝም ብሎ ከሚቀደደው ቱሪናፋው ከቤ ጋር ብውል እመርጣለሁ። ዝምታ ሽሽት የማልደውልበት፣ የማላነበው፣ የማልሰማው ዜና የለም። ዝምታ እፈራለሁ! መንገድ ስሔድ… ስቀመጥ! የማነበው መጽሐፍ ካልያዝኩ፣ ስራመድ የምሰማበት ኤርፎን ካልወተፍኩ…. ፖሊሶች አቻኩለው ከቤት አስወጥተውኝ ነው የሚሆነው! ዝምታ እፈራለሁ! አስታውሳለሁ፤ 12ኛ ክፍል ነበርኩ። ሙዚቃ ከፍቼ እያጠናሁ፥ የአጎቴን የለቅሶ ሳግ ሰምቼ ደንግጬ “ምነው አመመህ?” አልኩት፤ እሱ ሙዚቃ እየተጫወተበት ያለውን ‘ቴፕ’ ዐየት አድርጎ፥ ወደ ጣርያው አፍጥጦ፣ እምባው ቁልቁል ወረደ! አሞት መስሎኝ ነበር… ከዚህ በፊት ሲያመው ያቃስታል፤ ሲብስበትም ማስታገሻ ይውጣል እንጂ አያለቅስም ነበር። አጎቴ ጥቁር ነው፤ ፊቱ ክስክስ ያለ… ሲያወራ ግን እንደሚታየው ኮስተር ያለ ማንነት እንደሌለው የሚያስታውቅበት፥ ቁጥብ፣ ደስ የሚል ሰው ነው። ልጅ እያለሁ የገዛልኝን ቼኮሌት እና ብስኩት፥ ታሞ አልጋ ሲይዝ ሲጋራ እያመጣሁ ክሼዋለሁ ። ቤቢ፥ “ያቺን ነገር አትገዛልኝም?” ይላል፤ እገዛለታለሁ። ሲጋራውን በእጁ እያገላበጠ ካያት በኃላ፥ አፉ ላይ እንዳለ እለኩሰለታለሁ። ዐብሮን ማንም በሌለበት ጊዜ ሁሉ፥ “አትብላ” የተባለውን፣ “አትንካ” የተባለውን ሁሉ እሰጠው ነበር። እያጠናሁ ስለነበረ፣ ሲያለቅስ አይቼው ስለማላውቅ፣ ደንግጬ ስለነበረ፣… ዘፋኟን ባውቃትም ግጥሙን አላጤንኩትም ነበር፤ ዘፈኑ እንደረበሸው ሲገባኝ፥ ወተት እንደገነፈለበት ሰው፥ ስበር ሔጄ የቴፑን ሶኬት ነቀልኩለት ። የማባብልበት መንገድ ስለጠፋኝ፥ “ምግብ ላምጣልህ?”፤ “ውሃ ላምጣ” አልኩት። ጣርያ ጣርያ ዕያየ ዝም ሲለኝ ከፊቱ ዞር አልኩለት። በዚያው ሰሞን፣ ሲብስበት ሐኪም-ቤት ደግመው አስገቡት፤ አልቆየም፤ ሞተ! የኾነ ቀን ... አባቴ፥ ስለወንድሙ ቸርነት፣ ዘናጭነት፣ ስፖርተኛነት፣ ሰው ወዳድነት፣ አለኝታነት፣ ስለጓደኞቹ ብዛት፣… ሲተርክልኝ ያስለቀሰቺው ዘፋኝ፥ የዝና ነጋሽ ትዝ አለቺኝ። ያስለቀሰውን የዘፈን ካሴት ከፈትኩት፤ ሆዱን ያባባው “ገዳሙ” ዘፈን ጋ ደረስኩ። እስክስታ ሚያስመታ ‘ሪትም’ ያለው ዘፈን ነው “.........አሆዬ እኔ ላንተ ብዬ፣ መጣሁኝ ጠቅልዬ አዬዬ፥ እኔ ላንቺ ብዬ፥ መጣሁኝ ጠቅልዬ “እሀሀ ገዳሙ፥ አሀሀ ገዳሙ እሀሀ ገዳሙ፥ አሀሀ ገዳሙ “አላስኬድ፣ አላስኬድ አለኝ፥ ይሄ ጫማ እኔም ልበቢስ ነኝ፥ ቢመክሩኝ አልሰማ “እሾህ ብቻ ኾኖ፥ እግሬን ብዳብሰው እንዴት መራመጃ፥ መሔጃ ያጣል ሰው? “ኧረግ እናናዬ፣ አረግ እናናዬ ኧረግ እናናዬ፣ አረግ እናናዬ “አሄ አሄ አሄ አሄ አሄ ኡሁ “ይወዘውዘኛል፥ ይወዝውዝ አባቱ እህል አሸክሞኝ አርጎኝ ጎረቤቱ አሞኝ፣ አሞኝ ውሎ፥ አሞኝ ሊያድር ነወይ? እህል ሰርቶ መብላት፥ ጤና ላይሆን ነወይ? “ምነው አምና በሞትኩ፥ እንዲያ እንዳማረብኝ መለየት በሽታ፥ እንዲ ሳይጠናብኝ “ያመኝ የነበረው፥ አያመኝም ተውኩት ያስታማሚ ነገር ሲቸግር አየሁት “እህህህ ገዳሙ ጠይሙ፣ ጠይሙ..........” ይላል ከዛ ቀን በኋላ፥ ተረጋግቼ ሥራዬ ብዬ ሰምቼው ዐላውቅም፤ ነገር ግን ሁሉም ስንኞች ልቤ ውስጥ በአግባቡ ከመሰነድ አላዳነኝም ድንገት ከተከፈተ፥ የሚረብሸኝ ዘፈን ኾነ .... “ድል ስቀዳጅ፣ ደስ ብሎኝ ስጠጣ፣ እንዳማረብኝ ግደለኝ አስታማሚ ሳታሳየኝ!” ማለት ጀመርኩ። “ያደረ የዋለ በሽታ አትሰጠኝ” እለው ጀመር “ይህ ዘፈን ምን ያህል ይረብሽሃል?” ስባል “ከዝምታ በላይ!” ማለት ጀመርኩ። የግጥሙ ኀይል ነው፥ ወይስ የአጎቴ ኹኔታ ሕይወትን እንድፈራት ያደረገኝ? ሕይወትን ምን ያህል ባካብዳት ነው፥ እያሸነፍኩ እንኳን “ምነው አምና በሞትኩ፥ እንዲያ እንዳማረብኝ…” የምትል ስንኝ የምታሳድደኝ? ፈሪ ሰው እንዲህ ነው፤ ከ ጠ’መንጃ በላይ ፥ ቃል ያሳድደዋል! © Adhanom Mitiku

  • 21 июл.2 25772из Jafbok

    የመጽሐፍ ፊርማ ስነስርአት ደራሲ እሱባለው አበራ በቅርቡ ያሳተመው " ጠይም ትውስታዎች " የተሰኘው መጽሐፉን ለገሃር በሚገኘው አዲሱና ዘመናዊው መደብር በመገኘት ከተደራሲያን ጋር የትውውቅና የፊርማ ስነስርአት ሊያደርግ የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 18 ተዘጋጅቷል ::

  • 15 июл.2 771103из EsubalewAberaN

    🌻 Nostalgia ⁶

  • 11 июл.3 036147

    “ቀኖቹን እቆጥራለሁ ብለህ ታስባለህ? አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረው፣ ሁልጊዜም እንደገና ይጀምራል፤ ጎህ ሲቀድ የተሰጠን ሲሆን ፀሐይ ስትጠልቅ ከእኛ ይወሰድብናል።” — ዣን-ፖል ሳርትሬ         📌ማጋራት አይዘንጋ

  • 9 июл.3 262226

    በረንዳ (በእውቀቱ ስዩም) ባለፈው ከያሬድ ሹመቴ እና ከምኡዝ ጋራ የሆነ ምግብ ቤት በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን ምሳ ስንበላ አንድ ጎስቆል ያሉ አዛውንት መጡና “ልጆቸ ርቦኛል “አሉን ምኡዝ ፣ “ካለ ይስጥዎት” አላቸውና መብላቱን ቀጠለ፤ ያሬድ ምኡዝን ክፉኛ ገላመጠውና’ ‘ አባቴ ቁጭ በሉና ከኛ ጋር ይብሉ” ብሎ ጋበዛቸው፤ እኔ አዛውንቱ እንዲበሉ ፈልጊያለሁ፤ ግን አብሮ መብላቱን ልቀበለው አልቻልኩም፤ ስለዚህ “በልተን ሲበቃን የተረፈውን እንሰጣቸዋለን” የሚል ለጽድቅ የማያበቃ ለኩነኔም የማይዳርግ ሀሳብ አቀረብኩ፤ ያሬድ ግን አመረረ “ሂዱና ታጥበዎ ይምጡ አባቴ” አላቸው፤ ምኡዝ በንዴት ጨሰ፤ “ለምን ሜቄዶኒያ ቁጥር 2 ብለህ አትከፍትም?” ብሎ አንባረቀበት፤ “ምንድነው ችግርህ ? “ አለው ያሬድ; ምኡዝ ለወሬ የማይመች ሰፊ ሀተታ አቀረበ፤ ሲጨመቅ ይህን ይመስላል፤ (አንድ ሰው ራሱን መመገብ የማይችል ከሆነ፤ ሰነፍ ነው፤ አለያም ደደብ ነው፤ አለያም አቅመቢሰ ነው፤ ወይም አመለ ቢስ ነው፤ ከሰዎች ጋር ተስማምቶ መስራት አይችልም፤ ታድያ አንዲህ ያለው ሰው ለመኖር አይመጥንም፤ ብትረዳው አታሻሽለውም፤ ስታበላው በምድሪቱ ላይ ሸክም የሚሆንበትን ጊዜ ታራዝምበታለህ እንጂ አትጠቅመውም ) ሰውየው ታጥበው መጥተው ከኛ ጋራ መብላት ጀመሩ፤ ሰማንያ ያህል የቴኒስ ኩዋስ የሚያካክሉ ጉራሾችን ወዳፋቸው ከወረወሩ በሁዋላ በረጅሙ ተንፍሰው “ ሆሆ ለዚህ ሆዴ ይጠላኛል ዘመዴ አለች እርያ” ብለው ተረቱ፤ ከዚያ ወደኔ ዞር ብለው - “ አጅሬው ለካ ይቺን እየዋጥህ ነው የጉሬዛ ሙሽራ የመሰልከው” አሉና ብቻቸውን ሳቁ፤ ከዚያ ወደ አስተናጋጁዋ ዞረው “አንቺ ቂንጥራም እስቲ አንድ ሲንግል ድራፍት ወዲህ በይ “ ብለው ጮሁ፤ ‘አባቴ ስሚናገሩት ነገር ጥንቃቄ ያድርጉ፤ ደሞ እዚህ ድራፍት አይሸጥም” አለ ያሬድ፤ አዛውንቱ የያሬድን ግሳፄ ከመ ገብስ አልቆጠሩትም፤ በር ላይ ቆሞ ለውዝ ወደ ሚሸጠው ልጅ ልጅ እየጠቆሙ” ያን ጥንዚዛ ባርያ ብንለከው ከጎረቤት አያመጣልንም ?” አሉ፤ በመጨረሻ ያሬድ “ሚስት አለዎት ? ` በማለት ጠየቃቸው፤ “እሱማ አለችኝ” አሉ በታከተ ድምጥ፤ “የተረፈውን ይውሰዱላት” አዛውንቱ ፈገግ ብለው የመለሱትን ባልፅፈው ደስ ይለኝ ነበር; “ምሽቴማ ይሄን ተቀመሰች ጥጋብዋን አልችለውም፤ ባይሆን ለውሽማየ እቁዋጥርላታለሁ’

  • 9 июл.2 376132

    ልቤ እየመታ፣እግሮቼ እየተብረከረኩ፣እጆቼን እያላበኝ፣ እንደምንም እያበድኩኝ ሆስፒታል ስደርስ ፤ የጠበቀኝን ነገር ማመን ከበደኝ። "እኔን ጥላ ሌላ ወንድ ጋር ሄዳለች።" ብዬ የፈረድኩባት ፍቅረኛዬ፣ባልዋለችበት ያዋልኳት ንፁህ ሴት...የመጨረሻው የሕይወት እስትንፋሷ ላይ ሆና ፤ ነብስ-ውጭ ፣ ነብስ-ግቢ ላይ ናት። ለካስ...ጥላኝ የሔደችው ሌላ ወንድ አግኝታ አልነበረም።የካንሰር ህመምተኛ መሆኗን እና ቀኗ እንደደረሰ ስላወቀች፣ እኔ እሷን እያስታመምኩ እንዳልሰቃይ ፣ ወጣትነቴን እንዳላባክን እና ህመሟን እያዬሁ እንዳልታመምባት ነበር ከእኔ የራቀችው። እኔ እዛ ከማንም ጋር ስማግጥ ፣ስረግማት እና በማንም የፌስቡክ ፅሑፍ ስመዝናት...እሷ ግን ለእኔ ስትል የብቸኝነትን ህመም ውጣ ፤ ብቻዋን ከሞት ጋር ስትታገል ነበር። ሰማይ ምድሩ ተደፋብኝ። ስሜቱን የሚከተለው እንስሳ ፤ እኔ ሆኜ ራሴን አገኘሁት። እጆቿን ያዝኳት። ሰውነቷ በረዶ ሆኗል። እንባዬ የአልጋውን አንሶላ እያጠበው፣ይቅር እንድትለኝ ልለምናት ቃል ስመርጥ ሳለሁ ገና ማውራት ሳልጀምር ፣ አይኖቿን ፍቅሬ ለዘላለም ጨፈነች።ሞተች። ታዴዎስ አዲሱ

  • 9 июл.2 151105

    ፍቅረኛዬ ያለ ምንም ማብራሪያ ፣ ያለምንም የስንብት ቃል፣ እንዲሁ ብቻ እንደ ዋዛ "ደከመኝ!" ብላ ጥላኝ ከጠፋች ዛሬ ፤ ድፍን 335 ቀናት ፣ 47 ሳምንታት ከ 6 ቀናት፣ 8,035 ሰዐታት፣482,112 ደቂቃዎች እና 28,926,720 ሰከንዶች ሞላት። ከእኔ ጋር ለምን መለያየት እንደፈለገች ላለፉት አስራ አንድ ወራት በእያንዳንዷ ቅፅበት ልቤን ብጠይቀውም ፤ አንድም አጥጋቢ ምላሽ ግን ከልቤ አግንቼ አላውቅም። ከእኔ ያጣችውን እና ያጎደልኩባትን ነገር ልትነግረኝ ፍቃደኛ አይደለችም። "ካልፈለግኩኝ አልፈለኩም ነው።መብቴ መሰለኝ አለመፈለግ አ?" ነበር ብላኝ የሄደችው ከአስራ አንድ ወር በፊት። እኔ ግን አንድም ቀን ሳልናፍቃት መሽቶ ነግቶ አያውቅም። በእያንዳንዱ ቀን መልሳልኝ ባታውቅም ፤ የልመና ቴክስት እልክላታለሁ። ቀን ቀን ስፎክር ውዬ ፤ ማታ ማታ ናፍቆቷ ሲከብደኝ ስልኳን አንስታ ፣ ድምጿን ባልሰማውም እደውልላታለሁ። አለ-መወደድ ህመም ነው። የማይፈልግህን ሰው መፈለግን ግን የሚበልጥ ስቃይ የለም። እንድትደውልለት የማይፈልግን ሰው ድምፅ ለመስማት እንደመጓጓት ያለ ፤ ራስህን ሊያስጠላህ እና ሊያስንቅህ የሚችል ነገር አላውቅም። በጣም አፈቅራታለሁ። እንድለውጠው የምትፈልገውን ወይም እንዳስተካክል የምትፈልገውን ነገር ብትነግረኝ ደስ ይለኝ ነበር ከምትለየኝ። ዛሬ ደግሞ ከወትሮው በተለዬ መንገድ ናፍቆቷ አቅም አሳጥቶኛል። መልኳ፣ ሳቋ፣ጠረኗ....ሁሉም ነገር ልረሳት በሞከርኩኝ መጠን ፊቴ ድቅን እያለ ያሰቃየኛል። ናፍቆቷን መታገስ ሲያቅተኝ ስልኬን አውጥቼ ደወልኩላት። እኔን ማውራት ካልፈለገች ለምን ብሎክ እንደማታደርገኝ ግራ ይገባኛል። ምናልባት ብሎክ ብታደርገኝ ተስፋ ቆርጬ ሰላም አገኝ ይሆናል። እሷ ግን የእኔን ስቃይ ታጣጥመዋለች መሰለኝ ፤ ተስፋ ቆርጬ እንድተዋትም የምትፈልግ ሴት አይደለችምና ስልኳ ባይነሳም ሁሌ ይጠራል። አንደኛው 'ጢን' ብሎ የሚጠፋው እና ቀጥሎ የሚመጣው 'ጢን' የሚለው የስልኳ ጥሪ መሐከል ላይ ስንት ድምጿን የመስማት ተስፋዬ ሞቶ እንደተቀበረ እኔ እና ፈጣሪ ብቻ ነን የምናውቀው። ደጋግሜ ደወልኩ።እሷም እንደተለመደው አላነሳችም። እኔም እንደተለመደው በራሴ ላይ አለመናደድ አልቻልኩም።ስለዚህ ንዴቴን ለማብረድ ሰፈር ወዳለች አንዲት ትንሽ ግሩሰሪ አመራሁ። የግሮሰሪዋ በር ላይ ካለች ዛፍ ስር ተቀምጬ ቀዝቃዛ ቢራዬን በብቸኝነቴ ላይ እየቸለስኩኝ ስጨልጥ ናፍቆቷ እና ቁጣዬ ይረግባል። ልክ እንደ ቀንድ አውጣ አንገቱን ብቅ የሚያደርግ ናፍቆት .... ብቅ-ጥልቅ ካለም፤ በፌስቡክ እና ቲክቶክ ደልዬው በሰላም እተኛለሁ። ሞቅ እያለኝ ሲመጣ ስልኬን አውጥቼ ፌስቡክ ማዬት ጀመርኩኝ።ቀልቤ አንድ የማላውቀው ልጅ ያጋራው ፅሑፍ ላይ አረፈ።ፅሑፉ... "ሴት ልጅ ሰይጣን ናት።ወንዶች ራሳችሁን ጠብቁ።" ከሚል ማስጠንቀቂያ ጋር የተለጠፈ የቴሌግራም ወሬ ስክሪንሻት ነበር። ፅሑፉን ማንበብ ጀመርኩኝ። "ባለትዳር ነበርኩኝ። ባለቤቴም የበዛ ፍቅር ነበረው ለእኔ። እኔ ግን ልወደው አልቻልኩም። ድሮም ያገባሁት እልህ ይዞኝ እንጂ አፍቅሬው አይደለም። ግን የሆነ ጊዜ ሌላ ሌላ ልጅ ጋር አወራ ነበር።ያንን ልጅ በጣም አፈቀርኩት። ባሌንም 'ፍታኝ!' ማለት ጀመርኩኝ። 'ባሌ ግን 8000 ሪያል ክፈይኝ! አለኝ። እሱንም ከፈልኩት። ግን አልፈታኝም። ብሩን አስቀምጦታል። "ለቤታችን መስሪያ ይሆናል።" ይለኛል።እኔ ግን ፍቺ ብቻ ነበር የምፈልገው። አልፈታም ሲለኝ እኔም የወንድ ፎቶ መፖሰት ጀመርኩ። በጣም እያለቀሰ ለመነኝ። "ተይ! ፍታኝ አትበይኝ ፣ ካጣሁሽ እሞታለሁ ወይም አብዳለሁ።" አለኝ። ምንም አልመሰለኝም። ተፋታን እና ይሄኛውን ልጅ አገባሁት። ይሄኛውን ካገባሁት ኋላ የመጀመሪያው ባሌ አመት ሙሉ ድምፁን አጥፍቶ ጠፋ። "ባልሽኮ ጠፋ!" ይሉኝ ነበር አብረን እያለን የሚያውቁን ሰዎች። እኔም ትዳሬን እየመራሁ እያለ አንድ ቀን ከኢትዮጵያ ተደወለልኝ። "ባልሽኮ አብዶ ውርማ ገብቷል። አልሰማሽም እንዴ?" ተባልኩኝ። አሁን ስጠይቅ እውነት ነው። ቤተሰቦቹም የእኔን ቤተሰቦች ሊገድሉብኝ ነው ግን አሁንም ኑሮው አልተመቸኝም። በአዲሱ ትዳሬ ደስተኛ አይደለሁም። ባገኘሁት እና "አፉ በለኝ!" ባልኩት" ይላል። አንብቤ ስጨርስ ደሜ ፈላ። በልጅቷም፣በአዲሱ ባሏም፣በቤተሰቦቿም ላይ ተቆጣሁ። የራሴን ታሪክ በቀጥታ ከእሱ ጋር ስላያያዝኩት ከሁሉ በላይ ግን በመጀመሪያ ባሏ ላይ ሃዘን የቀላቀለው ቁጣ ተቆጣሁ። "የእኔዋም ሌላ ወንድ ለምዳ ነው ጥላኝ የሔደችው።" ብዬ ደመደምኩ። ሴት ልጅ በብዙ ትናንሽ ምክንያቶች ጥላህ ልትሔድ ትችላለች። እንደኔዋ እና ይሔ የመጀመሪያ ባል ግን ያለምንም ምክንያት ጥላህ ከሔደች ፤ በእርግጠኝነት ሌላ ወንድ ለምዳ ነው። ሞቅ እያለኝ ሲመጣ ቁጣዬም እየጨመረ መጣ። ሴት ልጅ የሚያፈቅራት ባል እና ልጅ ቢኖራትም ስሜቷን ብቻ የምትከተል ከንቱ ፍጥረት መሆኗን ማረጋገጥ አማረኝ። በሆነ መንገድ ይሔንን እውነት ማረጋገጤ ፣ የእኔዋንም ከሃዲ ስለሆነች እንጂ ፤ ሌላ እኔ የማላውቀው ምክንያት ስላላት እንዳልሆነ ራሴን አሳምኜው ፤ ጨክኜ ልረሳት እንደምችል ተሰማኝ። ከአስራ አንድ ወራት በፊት ጥላኝ የሄደችው ፍቅረኛዬን ከማግኜቴ በፊት ፤ በጣም የሚወዳትን እሷ ግን የማታፈቅረውን ሃብታም አግብታ የምትኖረው የድሮ ድሮ ፍቅረኛዬ ጋር ደወልኩ። "በአስቸኳይ ቤቴ ነይ! የማማክርሽ ትልቅ ጉዳይ አለ።" ብዬ ለመንኳት። እንኳን ዛሬ ያኔ ፍቅረኞች በነበርንበት ጊዜም እንኳን ፤ እሷ ሳትፈልግ ምንም ነገር እንደማላደርግ እንደምታምነኝ አውቃለሁ። ========================= መጀመሪያ ላይ መለማመጡ ትግል ሆነብኝ። እሷም ለምን እንደጠራኋት ሲገባት ደነገጠች።እንቢ አለችኝ። "ባሌን እወደዋለሁ።ይሄ በፍፁም ልክ አይደለም።" እያለች አላስጠጋ አለችኝ።እኔ ግን የሴቶችን እንስሳዊ ባህሪ ለማወቅ ባደረብኝ ጥልቅ ፍላጎት፣ስካር እና እልህ ተነሳስቼ እንደምንም አሳምኛት አብራኝ እንድታድር አደረኳት። ተዋስበን ከጨረስን በኋላ አልጋዬ ላይ ራቁቴን በጀርባዬ ተኝቼ ጣሪያውን እያዬው ሳለ ፣ ደረቴ ላይ ለመተኛት እየተመቻቸች በአድናቆት እንዲህ አለችኝ... " ልጅቷ ግን ሴክስ ላይ እንደዚህ ጀግና ሆነህ...ጥላህ መሔዷ በጣም ይገርማል!" እውነትም ሴቶች ስሜታቸውን ብቻ የሚከተሉ፣ ከንፈር እና ጡታቸውን ከተነኩ የትም የሚጋደሙ እንስሳ መሆናቸውን በተግባር አረጋገጥኩኝ። ያገኘሁት ግን እንደጠበኩት እፎይታ እና ሰላም ሳይሆን ጥልቅ የራስ ጥላቻ ነበር። ራሴን በጣም ጠላሁት። ምክንያቱም ከዚህ ሁሉ ኋላም ያቺን ክፉ ልረሳት አለመቻሌ ነው። ከዚያች ቀን ወዲያ በተደጋጋሚ መገናኘት እና መዋሰብ ጀመርን። ነገር ግን እሷ እኔን እያከበረች ቤቴ ድረስ ስትመጣ ፤ ያንን ሁሉ ፍቅር የሚሰጣትን ፣ የሚያከብራትን ባሏን እያታለለች አዘውትራ ወደ ቤቴ መምጣቷ በጣም እንድንቃት አደረገኝ። የሰዎችን እውነተኛ እንስሳነት እያዬሁት እና እየተገለጠልኝ ሲመጣ ፣ ዐለሙን በሙሉ ጠላሁት።አንድ ቀን ድንገት ተነስቼ ለማንም ምንም ሳልናገር ፣ሰፈር ቀይሬ ጠፋሁ። ብዙ ቀናቶች አለፉ። ራሴን ደብቄ ፣ በፈጠርኩት የብቻነት ዐለም ውስጥ ስኖር ሳለ ፣ አንድ ቀን ድንገት ከድሮ ፍቅረኛዬ ቤተሰቦች ስልክ ተደወለልኝ። የሰማሁትን ማመን አቃተኝ። "እባክህ...አሁኑኑ በአስቸኳይ ሆስፒታል ድረስ" አሉኝ፤ድምፃቸው ውስጥ በሰላም እንዳልጠሩኝ ፤ ንግግራቸውን የተሸከመው ሃዘን ነግሮኛል።

  • 30 июн.2 9603210

    ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘኋት መንገድ ላይ የሴት መቀመጫ እያዬሁ ስሔድ ገጭቻት ነው። «ኧረ መንገዱን እያዬህ» አለች እየተንገዳገደች። «በጣም ይቅርታ! ባለቂጧ ከመታጠፏ በፊት አንዴ ልያት ብዬ ነው» አልኳት። ደግሜ አላገኛት!...ብትታዘበኝ ምን ታመጣለች? «እና ምህዋርህን እየጠበቅክ ተጓዝ እንጂ ብራዘር! አባረህ እኮ ነው የገጨኸኝ!» «አጋጣሚ ሁኖብኝ ነውጂ...እኔስ 'ቂጥ እያዩ የመራመድ ጥበብ' የሚል መፀሀፍ ማሳተም የምችል ሰው ነኝ» ሰው ሁሉ ዙሮ እስኪያት ድረስ ሳቀች። ሳቋ ካለፈችው ልጅ መቀመጫ የበለጠ ያፈዛል። «መሔጃ ከሌለህ ዙርና እኔጋ እንሒድ! እስክትጠፋን ድረስ ቂጧን ማዬት እንችላለን!» አለችኝ። መሔጃ ነበረኝ። አባባሏ ገርሞኝ የለኝም ብዬ ተከተልኳት። ከኔ እኩል የዳሌ አቀማመጦችን እየተነተነች ሁለት ፌርማታ ወክ አደረግን። ልንለያይ ስንል ዝም ብላ እንድትሔድ አልፈለኩም። «በይ ስልክሽን አምጭ ሌላም ቀን ወክ እናድርግ!» «ሌላ ጊዜ አንገናኝም ብዬኮ ነው እንደዚህ በነፃነት ያወራሁህ! በል እያዬህ ሒድ ሶዬ!» «የምሬን ነው!» እጇን ያዝኩት። «እኛ ከተግባባን ምን የሚያሳፍር ነገር አለው? ይሔ ትንተና ዕለታዊ እንዲሆን ነው የምፈልገው» አሳቅኳት። ሳስበው ለመሳቅ ሰበብ ነው የምትፈልገው። «ይቺ ለመብላት ብዙም አታስቸግርም» ስል አሰብኩ። አልተሳሳትኩም ነበር። በቀጣዩ ቀጠሮ አብራኝ አደረች። ሌላ ቀን እንደማላገኛት እርግጠኛ ነበርኩ። ከሶስት ቀን ቡኃላ «አንዴ ብቻ ልድገማት» ብዬ ደወልኩ። 'እንቢ'ን አታውቀውም። ነይ ስላት ተንከልክላ ትመጣለች። ሒጂ ስላት ትሔዳለች። የሚገርመኝ ግን እንደ እሽታዋ ብዛት አትሰለችም። እንደ ጨዋማ ውሀ እየጠጣኋት ትጠማኛለች። ምኗን ነው የወደድኩት? እላለሁ አንዳንዴ! በማያስቀው ቀልዴ የምትስቅልኝን? አልፎ አልፎ የምትነክሰኝን ነገር? እንደ ሌሎቹ ሴቶች ስለቁምነገር አለማውራቷን? ለመጀመሪያ ጊዜ ትክክለኛ ግኑኝነት ውስጥ መግባት ፈለኩ። ማመን አልፈለኩም ነበር። ከአልጋ ወርዳ ስትሔድ ውስጤ የሚረበሸውን ነገር አልተው አለኝ። ውስጤ አፍ አውጥቶ «ባልወጣች...እዚሁ ብርድ ልብስ ውስጥ አብራኝ በበሰበሰች!» ይለኛል። «ኧረ ሰውዬ ተረጋጋ የትም አትሔድም ሳሎን ነች» ብዬ እገስፀዋለሁ። ከዚህ ሁሉ ለምን መውደቄን አላምንም ብዬ አፈረጥኩላት። የሷን መልስ ግን ካልገመትኳቸው የህይወቴ ክስተቶች ሁሉ ቅድሚያ የምሰጠው ነገር ነው። «ሌሎች ሰዎችን የመጥበስ መብታችን መጠበቅ አለበት...ይሔ ይከብደኛል ካልክ ሁሉም ነገር ሊቀር ይችላል» ነበር ያለችኝ። «እንዲሁ ብንቀጥል ይሻላል?» አልኩ ማመን እያቃተኝ «ይሔ ለኔ አማራጭም አይደለም። ከዚህ የተለዬ ግኑኝነት አልፈልግም!» ለመጀመሪያ ጊዜ እምቢ አለች። ታዲያ ያ ሁሉ እሽታ ለምን ነበር? ከዛ ቀን ጀምሮ ስናወራ ላዬን ሰው እኔ ነኝ ሴቷ የምመስለው። «ቆይ ምን እየሰራን ነው?...ምንድን ነው ግኑኝነታችን?» ስላት «ጀመረህ ደሞ!» ብላ ልብሷን ትለባብስና ትወጣለች። ቆይ ምኔ ነው የጎደለባት? የእሷን ያህል ስለ ሳይንስ ስለማላውቅ ፋራ መስያት ይሆን? እነዚህ ናቹራል ሳይንስ ያጠኑ ሰዎችኮ ሶሻል ያጠናነውን የሚንቁን ነገር አለ! የሆነ ቀን ጀርባዋ ላይ ያለውን ክብ ታቱ እያዬሁ «የኳስ አድናቂ ነሽ እንዴ?» ስላት የሳቀችብኝን ሳቅ መቼም አልረሳውም። «ብላክ ሆል ሲባል ሰምተህ ታውቃለህ?» አለችኝ። «አላውቅም!» «ስፔስ ላይ ያለ ጥቁር አዘቅት ነው። ወደዛ የገባው ሁሉ ይሰለቀጣል። ይሁን እንጂ ጠፍቶም አይጠፋም። የገባው ነገር ሁሉ የተሰራበት መረጃ ተቀይሮ በሌላ ቅርፅ ይቀመጣል። ስለዚህ 'ብላክ ሆል' ውስጥ የገባ ነገር ሁሉ 'አለ'ም 'የለም'ም ማለት አይቻልም። ሰው እና ህይወት እንደዚ ናቸው ለኔ። በህይወታችን የገባን ሰው ሁሉ መለያዬት የሚባል አዘቅት ይሰለቅጠዋል። ቅርፁ ወደ ትዝታ ተቀይሮ አብሮን ይኖራል። ያ ሰው 'አለም' 'የለም'ም ማለት አንችልም!» የገባኝ ለመምሰል በአግራሞት ራሴን ነቀነቅኩ። እንዳልገባኝ ገብቷታል። የፌዝ ሳቅ ሳቀችብኝ። አንድ ምሽት የመጨረሻ አቋሟን እንድታሳውቀኝ ለመጠዬቅ ቤቴ ራት ጋበዝኳት። እንደመጣች ጠረንቤዛ ላይ ያዘጋጀሁትን እያዬች ፊቷን ከሰከሰች። ቤቱን ሮማንቲክ ሳደርገው ደስ አይላትም። «ምናለ ይሔን የሻማ መአት ብትተወው?» «በእውነት አጋጣሚ ነው። መብራት ጠፍቶ እያነበብኩበት ነበር» «አይደል? ወይኑን የከሸንከውስ ባጋጣሚ ነው?» «የምር ፍሪጅ ውስጥ የቆዬ ስፕራይት አግኝቼ ከሚባክን ብዬ ነው ወይንና በደሌ ገዝቼ የጨመርኩበት!» ልቀልድ ሞከርኩ። «አቦ ሙዴን ጦለብከው!!! እንዲያውም እዚህ ቤት አላመሽም። ክለብ እንውጣ!» እምቢ ብዬ የመለያያ ምክኒያት ልሰጣት አልፈለኩም። እልኋን ነው የማስጨርሰው ብዬ ጃኬት ደርቤ ወጣሁ። ገና ከመግባትችን ያዩዋት ሁሉ በአይናቸው ልብሷን ሲያወልቁባት...ከውጭ ብርዱ ሲያፍሳት ያልሰጠኋትን ጃኬት አውልቄ ሰጠኋት። በደነሰች ቁጥር ፊትለፊት ያለው ልጅ የሚያያት አስተያዬት ሰላሜን ሲነሳኝ አመሸ። ይባስ ብሎ ሒዶ ሰላም አላት። ተገርማ ሰላም አለችው። ጭራሽ እያወቃት ነበር ይሔን ያህል ጊዜ ዝምብሎ ሲያያት የነበረው? ንዴት ቢጤ ሞካከረኝ። እያወራ ሲያስደንሳት ሳይ ወንድነቴ ተፈታተነኝ። በግኑኝነታችን ህግ መሰረት እሷን መቆጣት እንደማልችል ትዝ ሲለኝ ራሴን ተቆጣሁት! ከዚህ ሁሉ ቢቀርስ?! ማሪያምን ቢቀርስ? 'ተከተይኝ' እንዳይመስልብኝ 'ሔድኩ' ሳልላት ወደ በሩ ገሰገስኩ...ሮጣ ተከተለችኝ። «ምን ሁነህ ነው? የግቢ ክላስሜቴ ጋርም ላልደንስ ነውዴ?» «ምን አጎደልኩብሽ ፍሬህይወት? ከዚህ ሁሉ ችግሬ ምን እንደሆነ ለምን አትነግሪኝም?» ልጁ ተከትሎን ወጣ! «ወንድሜ ትቼለሀለሁ እንደፈለክ አድርጋት!» አልኩት በእልህ እየተወጣጠርኩ። «ኧረ እንደምታስበው አይለም። እኔ ሔሉን? በፍፁም አላደርገውም! ጀርባዋ ላይ የተነቀሰችው የጓደኛዬ ፊት ምን ይለኛል?!» አለ በፈገግታ እያዬን! አናቴን የተመታሁ ይመስል ጭልም አለብኝ። መልሶ ሲበራ አዕምሮዬ በጥያቄዎች ጎርፍ ተጥለቀለቀ። ማንን ነው የተነቀሰችው? ለምን አጠፋችው? ማናት ሔለን? ስሟን እንኳን አላውቀውም? እሷ ያን ስትሰማ ጆሮዋን ይዛ እየበረረች በጨለማው ተሰወረች። በሔደችበት አቅጣጫ ሒጄ ፈለኳት። የገባችበት ጥቁር አዘቅት ግን ውጦ አላዬሁም አለ። እኔ በቂ ያልሆንኩላት መስሎኝ ነበር...ለካስ እሷ ከትላንቷ ማምለጥ ያልቻለች ባተሌ ነች። ፍቅር የማይገባት ገገማ ብዬ ወቅሻት ነበር...ለካስ እሷ ልቧን በሙሉ ቆምራበት ተበልታው ነው። የአሁኗ ሚስቴ እኔጋ ወክ መውጣት አትፈልግም። «ወክ እናድርግ» ስላት «አንተ ጋር ወክ? ወይ ሳወራ አትሰማኝ...ወይ ከቀልብህ አትሆን! የመታህ የመንገድ ጋኔን ሳይለቅህ አንተ ጋ ወክ አልወጣም!» ትለኛለች። እንዳልሰማሁ ሁኜ ትቻት እወጣለሁ። ምናባቴ ላድርግ? አቀርቅሬ ስሔድ መንገደኛው ሁሉ እሷ ነች። ቀጥ ስል ሌላ ሰው ይሆናል። አምጥቶ የወሰዳት ጎዳና ደግሞ መልሶ ያመጣታል በሚል ተስፋ ስደናበር ነው የምውለው። ለዛ ነው አሁንም ድረስ ስለታቱው እንዳልዋሸችኝ የሚሰማኝ። በህይወታችን የገባን ሰው ሁሉ መለያዬት የሚባል አዘቅት ይሰለቅጠዋል። ቅርፁ ወደ ትዝታ ተቀይሮ አብሮን ይኖራል። ያ ሰው 'አለ'ም 'የለም'ም ማለት አንችልም። https://www.facebook.com/share/p/1DCGGWSW65/

  • 27 июн.3 029218

    1. እህቴ! የ 2 ነገሮችን ትርጉም ልነግርሽ ነው። የፍቅር እና የሞት። ፍቅር ማለት ባልሽ ከሌላ ወንድ ጋር ራቁትሽን ሆነሽ ካገኘሽ በኋላ፣ "ማሬ! አይዞሽ! ልብስሽን ልበሺና ወደ ቤታችን እንሂድ" ካለሽ አትጠራጠሪ ይሄ ፍቅር ነው። ሞት ማለት ደግሞ አንቺ እሺ ብለሽ ባልሽን ተከትለሽ ወደ ቤት ከሄድሽ አሁንም አትጠራጠሪ ይሄ ሞት ይባላል። 2. አንድ ጊዜ "ሙስና በአፍሪካ" በሚል ርዕስ አንድ የፓናል ውይይት ላይ ተሳትፌ ነበር። ስብሰባውን ጨርሼ ስወጣ በሩ ላይ አንዷ ጋዜጠኛ አገኘችኝና እንዲህ ብላ ጠየቀችኝ፣ "አቶ ተስፋዬ! በውይይታችሁ ላይ በአፍሪካ በሙስና የታወቁ አገሮችን አንስታችሁ ተወያይታቾሁ ነበር?" "አዎ! በሙስና የታወቁ 5 አገሮችን አንስተን ተወያይተናል" "አምስቱ አገራት እነማን ናቸው?" " ሶማሊያ፣ ሊቢያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ጊኒ" "አቶ ተስፋዬ! ኢትዮጵያ አሁን ባሉት ሙሰኞቿ የተነሳ ስሟ ከእነዚህ አገራት ውስጥ እንዴት አልተካተተም?" "የኔ እህት! የኃጢአተኞች ስም ዝርዝር ሲጠቀስ የሰይጣን ሰም አብሮ ሲጠቀስ ሰምተሽ ታውቂያለሽ?" ባሻዬ! .......... Tesfaye Hailemariam

  • 21 июн.3 448208

    ማወቅና ማድረግ ለየቅል ነዉ! ብዙ የማዉቀዉ ግን የማላደርገዉ አለ። መወሰን እየከበደኝ። መጨከን እየደከመኝ። መፀፀት እየፈራሁ . . . እልፍ ጊዜ ደግሞ እየሰነፍኩ! እንደማትመጪ አዉቃለሁ . . . ግን አልተዉኩሽም። እንደማልረሳሽ ታዉቂያለሽ. . . ግድ አላለሽም። አዎ . . . ማወቅና ማድረግ ለየቅል ነዉ! የማዉቀዉን እንደማላደርገዉ ፣ እያረኩት ፥ የማላዉቀዉ ደሞ እልፍ ነዉ። አንቺን መዉደድ እንደዛ ነዉ… . . @samuel_dereje