ህብረ ቀለማት
СтатистикаContact 👉 @Natiaba ምርጥ ግጥሞችን፣ አጫጭር ታሪኮችን፣ የተለያዩ ልቦለዶችን፣ አነቃቂ መልዕክቶችን፣ አስተማሪና አዝናኝ ፁፎችን፣ ከፈለጉ አሁኑኑ ይቀላቀሉን። ህብረ-ቀለማት የሁሉ ድምቀት ናትናኤል አባይነህ 👑
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 8
- Всего постов
- 39
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 169
- 1/48двое суток
- 193
- 1/72трое суток
- 208
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ይህን ያህላል የምንወድህ ዕድሜ ተጎምዶ ከራስ ገላ ላይ ላንተ ቢለገስ እንደኩላሊት እልፍ ማለዳ እልፍ ሺህ ለሊት ቆጥረህ ለክተህ የማትደርስበት ደምረህ ሰፍረህ የማትጨርሰው ይህን ያህላል የሚወድህ ሰው ፍቅርን ውበትን የምንገልፅበት ምንቆዝምበት ምንተክዝበት ምንፅናናበት ትንፋሽ አድለህ ብትሰወርም ካይናችን ጎድለህ፤ ባታወጋንም ባንጠይቅህም ረግቶ ቢንሳፈፍ ዝምታ ውስጥህ እኛ ግን አንተን እንደመዝሙር ነው የምናደምጥህ። እንኳን በተራ ባልቀና ጆሮ የምትታፈር በሊቅ ባዋቂ ልክህን ያህል ሰርተሃል በቂ። ዜማ ቢነጥፍ ከጉሮሮህ ላይ እንደትናንቱ ድምፅህ ባይሰላም ዝም ብለህ ክረም ቆየን በሰላም ከፍቶህ እንዳናይ በስህተት እንኳ እንዳይደብርህ ይህን ያህል ነው የምናከብርህ። @getmnaleloch
በየትኛው Department እንደተመረቅኩ ሁላ በረሳሁበት ሰዓት COC አለ አላሉም 🥺 ጥያቄው ስለጋዜጣኝነት መሆን አለበት... እኔ የማውቀው በዛ ዙሪያ ያሉትን ነገሮች ብቻ ናቸው🙄 ይድረስ ለጤና ሚንስቴር 😁 @Getmnaleloch
.... አይበገሬው እኔ አንቺን በማጣቴ ለ'ሲቃ' ብደርስም፣ _ ወንድ ልጅ ነኝና እራቅሽኝ ብዬ ለአንቺስ አላለቅስም! @getmnaleloch
ምን ቢባል ምን መወደድ ያኮራል፣ ደረት ያስነፋል። መውደድ ግን ዋጋ ያስከፍላል። ነገር ግን ይሄ ህግ ተፈጻሚ የሚሆነው ሁሌ አይደለም። አንዳንዴ ነገሮች ተጋላብጦሽ ይሆናሉ። አንድ ከልብ ያፈቀረ ሰው በራሱ በፍቅሩ እርግጠኛ በመሆኑ ደረት ነፍቶ ሲያወራ፣ ያ ግን የተፈቀረ ሰው እንደወዛገበ ይኖራል፣ ይወዛወዛል፣ ግራ ይጋባል። ይሁንና ያኔ ግራ ያጋባሁሽ የኔ ተፈቃሪ ሆይ... እኔ እርግጠኛ ነኝ አሁንም እወድሻለሁ❤ @getmnaleloch
በቂ ነገር ሳይኖርህ አግባኝ እንደምትል ሴት አጥፍቶ ጠፊ የለም🙄😁 @getmnaeloch
እወድሻለሁ ማለት አይጠቅም አይበቃ፣ ፍቅሬ ነሽ ማለትም አይጠቅም አይበቃ፣ ነብሴ ነሽ ማለትም ልቤን አያረሳው፣ የፍቅራችን ነገር ዝም ነው ዝም ነው🥺 Sweat dreams🥰 @getmnaleloch
ከልቤ ላይ አንተን ማዉጣት ማለት…… ገቢዎች ሰምተዉኝ ያላመንኩበትን ጉዳዬን መቀልበስ ቀበሌ ገብቼ በደስታ መመለስ መርጌታ ከሚል ቻናሎች ላይ መዉጣት የተበደርኩትን ስመልስ በብቃት ከ crash ኤ ጋራ እራት እንደመዉጣት ለእናቴ በአደራ ሚስጢር እንደማዉራት አንተን መርሳት ለኔ…… አለቃዬን መዉደድ እብድ ሰዉ ማሳበድ ዛፍና ፓል መግጨት ተምሬ በድፍረት ያልፍልኛል ማለት እርሺኝ ብሎ ማሰብ……… ወፍ በእግሯ ስትሳብ ተኩላ በዉበት ሲሳብ ቴሌ በትክክል ሲያመጣልኝ ሂሳብ እኒህ ሁሉ ተቀይረዉ ምድር ቀዉጢ እስካልሆነች- አንተን መርሳት ዉዴ የሚቻል አደለም። ትዝታ ወልዴ✍️ @getmnaleloch
🔴ሱስ(ሲጋራ፣ጫት፣መጠጥ......) ሲጠምድህ በመጀመሪያ መጥላት የምትጀምረው አስተዋይ የሆኑ የቅርብ ጓደኞችህን ነው። ባየሃቸው ቁጥር ትሸሻቸዋለህ!! ድንገት ቢያዩህ አንገትህን ትደፋለህ!! @getmnaleloch
አብጄ ከሆነ ወስደሽ አስጠምቂኝ፥ አብደሽ ከሆነ ግን፣ በስተርጅና አያምርም ሀገሬ አታስቂኝ፥😁 @getmnaleloch
ሰሞንኛ በአገራችን በተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ ወጣቶች የአካል ብቃት ፉክክር ሲያደርጉ በቲክቶክ ሳይ ደስ ይለኛል ፤ የሆነ ቦታ ጡንቻቸውን በስሚንቶ በተበጀ ዳምቤል ያጠጠሩ፣ ከወገባቸው በላይ የተራቆቱ ጎረምሶች ወደ ካሜራው አየሾፉ እንዲህ ይላሉ፤ ‘ ኢስቲ ወንድ ናን የሚል ካሌ ኢሂንን ቻሌንጂ ይሞኪር፤ የኛ ጀማ! ማኒንም አይሰማ ! “ ስክሮል ሳደርግ ሌላው ቡድን ከሆነ አካባቢ ብቅ ይላል፤ የቡድኑ መሪ በዳጉሳ ቂጣ ዳጎስ ያለውን ደረቱን እየመታ ‘’ እስቲ ይህንን ደረት አጣብረው፤ ሰባ አመት ብትማስን ምታመጣው ይመስልሀል፤ የልምጥ ልይ ! የኛ ዠማ ! ማንንም አያምጥ፤ ደሞ ሸር ኮቢሊንክ ማረግ እንዳይዘነጋ” የሚል መልክት ያስተላልፋል፤ ይህ በአንዲህ እያለ፣ የሚመለከተው አካል ቁጭ ብሎ ‘ያኛው ለአየር ወለድ፤ ይሄኛው ለኮማንዶ” እያለ ይመዘግባል፤ እኔ ጎረምሳ እያለሁ በሰፈራችን ልጆች መካከል የነበረው ብቸኛ ቻሌንጅ ብይ ጨዋታ ነበር፤ በቀለጠ የስኪብርቶ ቀፎ በተሰራ ብይ፣ የውሀ ብይ ለመብላት ስንንፉዋቀቅ ያለ እድሚያችን የጉልበታችንን ሎሚ አሙዋሙዋነው፤ ከዚያ አንድ ቀን መንግስት አዘናግቶ የሰፈራችንን ጎበዝ ብይ ተጫዋቾችን አፈሳቸው፤ በብይ አንዲህ ካንከረባበቱ በክላሽማ የሚችላቸው የለም ብሎ ይመስለኛል፤ በነገራችን ላይ ጦርነትን የምጠላውን ያክል የድብድብ ስፖርት ገዳፊ ነኝ፤ ቀጣዩ የርግጫና የቡጢ ግጥምያን በጉጉት እየጠበቅሁ ነው፤ ወንድ ልጅ በመን ፈቅ አንዴ አንኩዋ ክንዱን በእኩያው ላይ አንስቶ መፈተን አለበት ባይ ነኝ፤ አንዱ፤ የመግቢያ ዋጋቸው መቶሺ ብር ነው ብሎ ተቀድዶልኝ ደንግጨ ነበር፤ በነካ እጃቸውና እግራቸው በልጀነቴ ቡሊ ያደረገኝን ሙሉጌታ ቡሊን ቢደበድቡልኝ ራሱ ያንን ያክል አልከፍልም ብየ አመረርሁ፤ በቪቪአይፒ መግብያው አምሳሺ ሆኖ ለታዳሚው መጠጥ ይቀርባል የሚል መረጃ ስሰማ ግን ተጥናናሁ'; ይሄ ሸጋ ነው፤ ችግሩ ምንድነው- ትንሽ ከቀማመስኩ የአንዱ ተደባዳቢ ተቀያሪ ቤንች ልሁን ማለቴ አይቀርም፤ እኔ ከግጥሚያው በላይ ደስ የሚለኝ የተጋጣሚወች የዛቻ መርሀግብር ነው፤ ህዝብና ጋዜጠኛ ግጥግጥ ብሎ በታደመበት መድረክ ላይ አንዱ ሌላውን ምንሲለው ሰማሁ፤ “ እግርህን ሰብሬ አካለ ስንኩል አደርግሀለሁ”😟 ምነው ጎበዝ! ስፖርት ላይ ህግ፤ ፖሊስ ፤ ፍታብሄር ምናምን የሚባል ነገር የለም አንዴ ? ለማንኛውም የአጥንት ህክምና ክሊኒክ ያላችሁ ፣ ወይም የዊልቸር አስመጭ የሆናችሁ፤ ተሸናፊውን ተጋጣሚ የብራንድ አምባሳደር ለማድረግ ተሰናዱ! (በእውቀቱ ስዩም) @getmnaleloch
የወንድ ልጅ ውበቱ ስራው ነው 😊! በሌላ ነገር አትጃጃል ቤብ። @getmnaleloch
በምታገባህ እቀናለሁ! 🥺 ከመሄድህ በላይ እንደ እግር እሳት የሚፈጀኝ አዲሷ ሚስትህን ማሰብ ነው። እድለኛ ናታ! ዝቅታህን የማውቅ እኔ፤ አፍቃሪነትህን የማውቅ እኔ ከአዲሱ ቤትህ ለምትሾማት እንስት እንስፍስፍ አባወራ መሆንህ በሃሳቤ ይመላለስና ፀፀት ያንገበግበኛል። 😔 እህል ውሃ መንገዳችንን ለየቅል አደረገው። መልካምነትህ ግን በመሄድህ አይሻርም። አንዳንድ መልካም ጊዜዎች፣ መልካም ልቦች በመለያየት አይፋቁም። ልብ ላይ ቀሪ ናቸው። ❤️❤️🩹 ክፉ ሰው ቢጎድል አይቆጭም። ቢቆጭም ቶሎ ይረሳል። በእለት ክፉ ከእጅ የወጣ እንቁ ልብ ግን የማይኳረፉት የእግር እሳት ነው። ❤️🩹 የኔ ልብና ያንተ ምስል ለዘላለም ላይፋቱ ቃል አላቸው። መሄዱን ሂድ! 😔 . . . ግን እንደ ሃሳብ . . ባታገባስ? 😒🥺 ©️ሊና አርጋው✍️ @getmnaleloch
ከነድካምህ የሚወድህ ጓደኛ ያ የልብህ ሰው ነውና አጥብቀህ ያዘው🥰 መልካም ቀን🤝 @getmnaleloch
ይዘጋል ሲሉ ይዘምናል👌 ባሉበት ሆነው ጤናዎን በነፃ ስልክ #6289 ይከታተሉ! የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የነፃ ስልክ አገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን በደስታ ያበስራል። መቸም ከየትኛውም ቦታ ሆነው በነፃ #6289 ላይ በመደወል የሚከተሉትን መረጃ በነጻ ያግኙ፦ 📅 የህክምና ቀጠሮ ማስያዝ፦ አዲስ ቀጠሮ ለመያዝ ወይም የነበረዎትን ለማስተካከል። ℹ️ ስለ ሆስፒታሉ መረጃ፦ ስለሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶች ሙሉ ማብራሪያ ለማግኘት። 🩺 የህክምና ምክር፦ ስለ ጤናዎ ሁኔታ ባለሙያዎችን በቀጥታ ለማማከር። 💬 አስተያየትና ጥቆማ፦ ቅሬታዎችን፣ ገንቢ አስተያየቶችን እና ጥቆማዎችን ለማቅረብ። • ከክፍያ ነፃ ነው ። • ሰልፍ ሳይጠብቁ ጊዜዎን ይቆጥባሉ። • ካሉበት ሆነው ቀጥታ ከሆስፒታሉ ጋር ይገናኛሉ። 📞 አሁኑኑ ይደውሉ፡ 6289 🏥 "ጤናዎ ቀዳሚ ትኩረታችን ነው!" #ኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት @getmnaleloch
እውነት እናውራ ካልሽ “በይ” ስልሸ … – “ወዶኝ ነው!” “ተይ” ስልሽ. “ቀንቶ ነው!” ባልሽበት አንደበት፥ ዝም ስል. . . “ንቆኝ ነው!” ብትይ ምናለበት ?! @getmnaleloch
አንድ ሰው ክቡር ሚኒስትሩን 'አሳማ' ብሎ በመጥራቱ ፍርድ ቤት ይቀርባል። ይህ የመጀመሪያ ጥፋቱ ነበር እና ዳኛው በጥሩ ስሜት ውስጥ ስለነበሩ በይቅርታ እንዲፈታ ወሰኑ። ወደፊት ክብረ ነክ የሆኑ ቃላትን እንዳይናገር ካስጠነቀቁት በኋላ ከእስር አሰናበቱት። ሰውየው ኮፍያውን አውልቆ ደጉን ዳኛ "አመሰግናለሁ፣ ክቡር ዳኛ፤ እውነቱን ለመናገር 'ክቡር ሚኒስትሩን' አሳማ ብሎ መጥራት ስህተት እንደሆነ አላውቅም ነበር። ዳግመኛ አላደርገውም። ይቅርታ።" "ችግር የለውም" አሉ ዳኛው "መሄድ ትችላለህ።" "ጌታዬ፣ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?" ""ትችላለህ" ሲሉ ዳኛው መለሱ። ''አሁን ክቡር ሚኒስትርን አሳማ ብዬ መጥራት ስህተት እንደሆነ አውቄያለሁ... አሳማን ግን 'ክቡር ሚኒስትር' ብዬ ብጠራው ወንጀል ይሆንብኝ ይሆን?'' ዳኛው በመገረም "አሳማን ለምን 'ክቡር ሚኒስትር' ብለህ እንደምትጠራ አላውቅም። ግን አሳማው ግድ እንደማይሰጠው አስባለሁ። በነገራችን ላይ አሳማን 'ክቡር ሚኒስትር' ብሎ መጥራት ሕገወጥ አይደለም።" ሰውየው ፈገግ ብሎ ራሱን ነቀነቀ፣ ከዚያም ዞሮ ከሳሹን ሚኒስቲር በትኩረት ተመለከተና "ደህና ይሁኑ ክቡር ሚኒስትር!" 👍 @getmnaleloch
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ሰኔት በተቋሙ የልየታ ትግበራ ፍኖተ ካርታ ላይ አስቸኳይ ውይይት አካሂዶ ውሳኔዎችን አሳልፏል ። የዩኒቨርሲቲው ሰኔት በ2026–2032 ዓ.ም የልየታ ትግበራ ፍኖተ ካርታ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት የተመደበው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፤ የአካባቢውን የልማት ፍላጎት፣ የሰው ሀብት እድገትና የኢኮኖሚ ተጽዕኖ መሠረት በማድረግ የወደፊት ትኩረቱን በአምስት ቁልፍ ዘርፎች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል። በዚሁ መሠረት፥ 1) ኢንጂነሪግና ቴክኖሎጂ 2) ግብርና (Agriculture) 3) ስነ-ምድር (Geology) 4) ሥነ-ሰብ (Humanities) እና 5) ጤና (Health education) እንደሆኑ ተገልጿል። ውሳኔው በቀጣይ ቀናት ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል ። ይሄ መረጃ ፕሮፓጋንዳ ከሆነ አንላቀቅም! ሰምተሃል🤲 @getmnaleloch
አቻሽን ፈልጊ... @getmnaleloch
. . አንቺ ጋር ስጣላ... መንግስትን ተሳደብ ፣ ተሳደብ ይለኛል ከሰደብኩት ደሞ ፣ አስሮ ይገርፈኛል ከገረፈኝ ደሞ... ለጊዜውም ቢሆን ፣ አንቺን ያስረሳኛል! ከረሳሁሽ ደሞ... አጣኋትኝ ብዬ ፣ አላስብም ቅንጣት ተሳድቦ መገረፍ.... ሳይሻል አይቀርም፣ አፍቅሮ ከማጣት፡፡ (በላይ በቀለ ወያ) @getmnaleloch
ባንድ ጭንቅላት በጠባብ ደረት ስንቱን ስሸከም ስንቱን ስደርት ለመሀላንኳ ምሳሌ ሚሆን ህያው ምልክት አንድም ሳላስቀር በሁሉም ሳጌጥ አጣሁኝ የክት እግሬ በመራው በነዳው ሲሄድ ጢሻ ለጢሻ ልቤም እንደ ዘር የትም ሲበተን ባገኘው እርሻ ለፈጠረኝም ለገደለኝም ስቆም ላምልኮ ስንት ብሆን ነው?.... አንድ ሰው ብቻ አልመስልምኮ!! @getmnaleloch