tgindex
ግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

Статистика

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
6
Всего постов
33
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
63 359
+2 за 3 дн.
Сутки
+9
+0,01%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
6 509
33 постов
Вовлечённость
10,3%
к подписчикам
Постов в день
0,9
всего 33
Упоминаний
6
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
4 314
1/48двое суток
4 943
1/72трое суток
5 332

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 14 авг.2 558242

    የመፅሐፉ ርዕስ :- የርሷ ስም ገጣሚው / ፀሐፊው :- ዳዊት ጥዑማይ በገበያ ላይ ውሏል መፅሐፋን ማግኘት ለምትሹ አዲስ አበባ ለምትገኙ 👉 + 2519 47 15 39 95 ወይንም 👉 +2519 45 52 52 49 ሐዋሳ ለምትገኙ ....... +251949002056 👉 +2519 47 15 39 95 ወይንም 👉 + 2519 49 00 20 56 @faberfortunae በመደወል ማዘዝ ትችላላችሁ ። ( መልካም ንባብ )

  • 12 авг.3 9613013

    ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ እኔ ያንቺን ውበት በቋሚነት ማደንቅ፣ ብዙ ሰው አየሁኝ እውነትን ሲደብቅ፡፡ እኔስ አያስችለኝ፧ መኳል ነው ማስሸብረቅ ባለቀው ማማርሽ፣ አይቶ ዝም ሲል ግን ስንቱን ታዘብኩልሽ?! ይቺ ጠባብ ቤቱ ትዕቢቱ ከልክላው እንጂ የማይስልሽ፧ ዝምታ ሲያበዛ መልስ ያጣ እንዳይመስልሽ፨ //ክብሬን ክሬን ሲል ነው የማያወድስሽ// (ወትሮም በዚ አገር           አብሰልሳይ ይቀድማል፧                                     ከሚያቆላጵስሽ!) @mypoems396 @getem @getem @getem

  • 12 авг.4 4997232

    ረሳኋት (ሚካኤል አ) ጤዛ እኮ ነው ገጽዋ በማለዳ ረጥቦ ፣ ቀትር የሚሰዋ። ጉም ነው የሷ መውደድ ጋርዳዋለች ሲሉ ፣ እኔ አለው ስራመድ። ጣሟን ዘነጋሁት ፣ እንደ በዓል ዶሮ ዛሬ እንኳ ብቀምሳት ፣ እኩል ነች ከሽሮ። ጠረኗ ጠፍቶኛል ፣ አዲስ ነኝ ለራሴ እሰይ ከስማ ቀረች ፣ ያቺ የሰው ከሴ ! ጆሮዬን አልሰጥም ስሟን እየጠሩ ፣ ተቀምጠው ጎኔ እዛው ጨፈርኩበት ፣ በአምና ድንኳኔ። ፡ እያየኋት ከሳች ፡ እያየኋት ጠፋች ፡ እንደ አየር ጢያራ፣ ደመናማው ሰማይ ይብላኝ ለሷ ፣ ጠራ። : እያልኩኝ ደንፍቼ ላገኘሁት ሁሉ ፣ ጉራዬን ስነፋ “ረሳኋት “ በሚል አንድ ከንቱ ግጥም ፣ ብቅ አለች ተጽፋ። ኡፋ 🥹 @getem @getem @paappii

  • 10 авг.5 4407033

    የምጓጓለትን ባውቅስ እንዴት ልሻው? መውደቅ ሆኖ ቀርቷል፤ ምኞት መጨረሻው። By Red-8 @getem @getem @paappii

  • 10 авг.5 364237

    ያላሉትን ነገር አዳምጥ የማይሉትን ነገር ስማ. ተብዬ ነው ያደኩት ፤ . ዕንባሽ እርግማን ሲመራ .እንዴት ነው ያላወኩት ? . አየሽ ሳትከብጂበትም በፊት እንዲሁ ሰው ፤ ' ሰው መሆኑ' አድክሞታል መንቃት ነውር ሆኖበታል ። አየሽ ሰሞኑን በባሰው የሚኮረሸም ጨለማ . የሚያጨራምት ዝምታ ውስጤን ወሮታል . አየሽ ዕንባሽ ድንቃር ሆኖ ፤ ውስጤ እረፍት ነውር ሆኖበታል ። (አንዱ ጌታቸው) @getem @getem

  • 10 авг.5 229268

    𝙞𝙣𝙨𝙥𝙞𝙧𝙚𝙙 𝙗𝙮 አያሙሌ'𝙨 𝙥𝙤𝙚𝙢 @mypoems396 @getem @getem @getem

  • 9 авг.5 7476426

    ነገን ኑረን ፥ ዛሬን ሞትን ትላንትናን እየለፋን ፥ በቀደም 'ለት ተቀበርን መሞቻና መሰንበቻው ፥ ሳይታወቅ የውል ፍቺው ቀን ልንጨብጥ በቀናችን ፥ ቀን አስጣለን መኖራችን። By ፍቅረ-ማርያም ተሾመ @getem @getem @paappii

  • 7 авг.7 68510740

    ትንሣኤሽን ልየዉ ውዳሴሽን አንብቤ ቅዳሴሽን ሰምቼ፣ በዝግ ባዕት በሱባኤ ሰንብቼ። ትንሳኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። ስብሐተ ነግህ ን አድርሼ፣ ድርሳን ስንክሳሩን ከልሼ። ቅዳሴን ላስቀድስ ከበራፉ ታዛ፣ አለሙን አስትቶ ለነፍስ የሚያስገዛ። ትንሣኤሽን ልየዉ ከመቅደሱ ቆሜ፣ ከመሳጭ አንድምታ እዉቀትን ቀስሜ። እንደ ሐዋርያዉ ትንሣኤሽ ይታየኝ፣ ከነጩ ሰበናት በረከቱ ይድረሰኝ። ዕርገትሽን እንዳይ ፍቀጂ እናቴ፣ በጸሎት በምልጃሽ ይሞላልኝ ቤቴ። እንኳን አደረሳችሁ🙏 ✍ዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem

  • 6 авг.7 93610458

    ተኳረፉ ብሎ ፡ ሊያስማማ ሊዳኘን ህይወት ስንት መንገድ ፡ ፈጥሮ ሲያገናኘን የልጅ ነገር ብለን፡ ጥሪውን ንቀናል ከእንግዲህ በኋላ... ሽማግሌ ሆኖ፡ ሞት ያስታርቀናል። by red-8 @getem @getem @paappii

  • 6 авг.7 9688349

    ጌታህ ስንት ያወጣል???✍️ ያ እንቁ..ያ ሽቶ ፣              ከእግሩ ስር ሲጣል የይሁዳ ጥያቄ ፣            ይሄ ስንት ያወጣል??                           ፐ !!... ስንት ድሃ የታረዘ መጠለያው የነቀዘ በሞላበት በዚህች ዓለም እግር ሽቶ ልክ አይደለም።                ፐ !! በሉ ለይሁዳ                 ደግነት ለዳዳ።       * * * * ከሰፊሮስና ከእንቁ ተንከራ እኩል ተንጠባርራ አንድ ዲናር ንራ ትርምስ  ባደለች ፣           በዚህች በውድ ዓለም ሶስት መቶ ዲናርን          መስበር ልክ አይደለም!።              .              .      እውነት አለው አይደል?              .              .              . ልክ ነው ይሁዳ፣                 ግሩም ነው ሐሳቡ ምጡቅ ነው አዕምሮው፣                ይህን መሰብሰቡ። ቸብ ! ለይሁዳ ሰው መርዳት ለዳዳ።                     * * * * ለምን?..እንዴት?... ከተባለ አንድ ሚስጥር አለ። እግር ሽቶ ሲርስ፣ ያ ብልቃጥ ሲሰበር ይሁዳ ቤት ክርስቶስ፣ ዋጋው ስንት ነበር               ?               ?               ? አምላኩን ሊሸምት፣ እድሉን ሲታደል እርሱ ቤት ክርስቶስ፣ 30 ብር አይደል?             * * * * እናም እውነት አለው፣         የ 300 ሽቶ ስለምን ይደፋል 30 ነው ጌታው፣      ሁለት ከሰባ ብር እቤቱ ይተርፋል።              .              .              . አንተ ቤትስ ታዲያ፣          ክርስቶስ ይሸጣል? አዎ! ካልከኝ ደርሰ         ጌታህ ስንት ያወጣል?          እኛ ቤትስ?        by ሰምረ የሽዋስ @getem @getem @paappii

  • 5 авг.6 85718473

    ውሰደን እንዳንል ቅጣትህ አስፈራን፥ አኑረን እንዳንል ኖረን ምን አፈራን፥ ፀሎቱ ጠፍቶናል በፈለከው ምራን። By andina @getem @getem @paappii

  • 4 авг.8 028156100

    ‎አንዴ ብቻ ልርሳሽ ‎አንዴ ብቻ ላስብ ‎ለግማሽ ደቂቃ ‎ራሴን ልሰብስብ ‎ ‎ህይወትን ያላንቺ፣ ይጣፍጠኝ ልሙቀው ‎አንዲት ስንዝር ብቻ፣ ጥላሽን ልራቀው ‎እንዴት እንደማመልጥ፣ እኔ ነኝ የማውቀው። ‎ ‎by: yoseph workineh @getem @getem @paappii

  • 4 авг.8 3607552

    ውደሴ -------------------------- ባንቺ የተነሳ በእጥፍ ጨመረ የውበት ሚዛኑ፣ የፈኩት አበቦች አፍረው ተሸፈኑ፣ ዕንቡጦች ከምንጩ ደንግጠው መከኑ ድሮስ! ይሄ ሁሉ ውበት! ለጨረቃ ሰግዶ ፣ ፀሃይን ተማፅኖ ለምኖ ሚፈካ፣ ብምን ጉልበቱ ነው ካንቺ የሚለካካ? እኮ በምን ጥበብ እኮ በምን ዘዴ እንኳን የአበቦቹ፣ የፀሃይቱ ምንጭ አንቺ አይደለሽ እንዴ? By Bereket belayneh @getem @getem @paappii

  • 4 авг.7 7743310

    ∞∞  ∞∞  ∞∞  ∞∞  ∞∞ ታምርህን ሰምቶ እንዳላመነህ፣ አብርሖትህን እንዳልለመነህ፣ ከጅህ በረከት እንዳልጠገበ፣ ባንተ ሲጎበኝ፧ ቤትና 'ደጁ እንዳልጠበበ፣ ° በክንድህ ስንቱን እንዳላለፈ፣ ጽልም እና ሞቱን እንዳልገፈፈ፣ ሃይልህን አይቶ እንዳልሰከነ፣ ከግሮችህ ትቢያ እንዳልመነነ፤ ° እንደተረሳ እንደማይጠቅም፣ ድንገት አብርቶ በሚጠፋ አቅም፤ ዘብ እንደሌለው እንደባይተዋር፣ አውታሩ ጎድሎ እንዳለ ክራር፥ ° በኑሮ ቅኝት እያቀለለህ፣ ሸርተት እያለ የተላቀቀህ፣ እንዲህ ያለ ሰው አይተ ታውቃለህ?! #እንደኔ_ያለ! @mypoems396 @getem @getem @getem

  • 4 авг.7 4185114

    አብ ሆይ! በዛለ ሰውነት: በደከመ ገላ ከቦን የሞት ጥላ .. አንጋጠን ወደ ላይ ኤሎሄ ኤሎሄ : ሰርክ ብንጣራ እንባችንን ማታይ : ሀዘን 'ማትጋራ : በዘመን ሽግግር : ሌላ ዕዳ ሊከፈል እኛም እንደ እየሱስ : ተሰቅለናል መሰል¡ ✍️ ቃኤል @getem @getem

  • 3 авг.7 89013198

    እንኳን እንዲህ አድጌ ልጅም ሆኜ ድሮ እጠላ ነበረ ሰው መያዝ አባሮ መምጣትህ ለማይቀር በውድም በግድም ጥሪኝ አትበለኝ መጯጯህ አልወድም                      by ምልዕቲ.ኪ @getem @getem @paappii

  • 3 авг.7 4484118

    ይድረስ ለእግዚያር) ከበሬ ደጅ ብትጠና፣               አንኳክተህ ልቤን ብትመታው አልከፍትም አትድከም ከንቱ፣               እኔ እንደው ቃሌን አልፈታው ብትለምን ዘመን ብትፈጅም               ልትገባ በሽህ ቃል ብትጥር ተዘግቷል ቁርጥህን እወቅ                እሾህ ነው የልቤ አጥር።                  ; እያልኩኝ ደጄን ሳስጠናህ፣                 ከአሪያም እንዳትመለስ ከገነት እሳት አጥሩ፣              አሻግረኝ ለህይወት በለስ በሃይልህ ልቤን አብጀው፣               ዝናህም በአይሁድ ይክበር ትንሳኤ በሰጠህ አካል፣                ግባብኝ በሐዋሪያት በር።                     (በተዘጋው በር) by ሰምረ የሽዋስ @getem @getem @paappii

  • 3 авг.6 6163410

    አፈር እንብላ!! እስከ መቼ በመንጌጠጥ፣ እስከመቼስ በመማጠጥ፣ በልበ ጉልጥምት አንንጠቁለል፣ በግራር ቅርፍት እንጠቅለል፣ ወይ በባህርዛፍ እንሸብለል፣ ለሰሚው ትንግርት እንደስ ትቢያ እንሁን በመኖር ቃዳ፣ የቅልጥም እዣችን ይጉረፍ በጥቁር በርሜል ይቀዳ፣ በኛው ልክ ይገጠም ሳጥን፣ ለፉንጋላ ገላ እንዲመጥን፣ ልጣችን ይራስ በእቁር ውሃ፣ እንዲያከትም እህል ውሃ፣ ቋቋታም ኑሮ ከመኖር ነገደ ነቀዝ የጎረጎረው፣ የምቀን ዱንቲ ከተላብን ጥመት ፍቅርን ካጎረው፣ እናት አባት ሳይቀሩ ትንሽ ትልቅ ሳይተው፣ ልዥና አዋቂው ሳይተርፍ ባንድነት የጎመተተው፣ እንደ ነጯ ዘሃ፣ እንደሚውጣት አዞሃ፣ ከሟች ጋር እንዳጣበቋት ለአውራ ጣት ማሰሪያ ተብላ፣ እንደዚያ የኔ ዘመዶች ተያይዘን አፈር እንብላ። ግጥም ገ/መድህን አየነው @getem @getem

  • 2 авг.6 34112270

    “ናልኝ” ቢሉህ ÷ ትመጣለህ “ስጠኝ” ቢሉህ ÷ ትሰጣለህ ቸር አይደለህ ! ​.... ​እኔስ ግን... ምን ብዬ ልጠይቅ ? ሕይወቴን ÷ ምን ላድርገው ? እወቅልኝ እስቲ ምንድነው ጌታዬ ÷ እኔ የምፈልገው ? By HEnock Bekele @getem @getem @paappii

  • 2 авг.7 06212173

    ፀበል ጠምቆት የማይወጣ፣ ‎ካህን ዳብሶት ማይላወስ ‎በፆም ፀሎት ማይፈወስ… ‎አለኝ ሰይጣን፣ ‎አለኝ ልምሻ። ‎ሰው አምናለሁ… እንደውሻ! ‎ By ዮሴፍ ወ. @getem @getem @paappii

ግጥም ብቻ 📘 — tgindex