tgindex
ሰመመን

እያረሩ መሳቅ እና የተለያዩ ወጎች ግጥሞች እና የመፅሐፍት ጥቆማ

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
142
+2 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
686
20 постов
Вовлечённость
483,1%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 20
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
39
1/48двое суток
44
1/72трое суток
48

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 12 авг.452из getem

    ውሰደን እንዳንል ቅጣትህ አስፈራን፥ አኑረን እንዳንል ኖረን ምን አፈራን፥ ፀሎቱ ጠፍቶናል በፈለከው ምራን። By andina @getem @getem @paappii

  • ሰላም ውዶቼ ስለትግስታቹ አመሰግናለሁ በአንዳንድ ምክንያት ፖስት ማረግ አልቻልኩም ለሰው ማጋራት ምትፈልጉትን ታሪክ በውስጥ ንገሩኝ በአሪፍ መልክ ማጋራው ይሆናል እወዳቹዋለው @zecutegirl0

  • እግር የማይረግጠው ሰው የማይደርስበት ዝምብሎ ለጌጥ ከተፈለፈለ የማይረባ አለት ውጪ አይታየኝም ሰው የሚያሰነብት ከሰማይ ጠቀስ ፎቅ ባዶነት ከሞላው ባይጠቅስ ይቅር ልክ እንደኋላው(እንደባቢሎን) ከተሽቆጠቆጠው ከአስፓልቱ ጀርባ ብዙ ጨካኝ አለ ህዝብን የሚያስነባ አይገርመኝም የተዋበ አይደላኝም የተጌጠ የስንቱ ደም ስንቱን እምባ ከመጠጠ ያማረቤት ወና እኮነው ያለ እናት ባዶ እኮ ነው ያለ አባት በተራበ ሆድ ባልጠገበ ሆድ ልብስ እንደመደረብ ካለብርድ ፍሬ

  • ቅኝ ገዢወች የአንድን አገር ማዕድን ሌላም ቁሳዊ ሐብት ዘርፈው መሄዳቸው የታወቀ ነው፤ ደቡብ አፍሪካዊያንን ግን ጭንቅላታቸውን ነቅለው ነው የወሰዱባቸው። ነፃነት ካለጭንቅላት ጋጠወጥነት ነው!! ነውረኞች! በነገራችን ላይ ሌሎችም አገራት ዛሬ ላይ ሰላም ነው ብላችሁ ሐብት የምታፈሩ ኢትዮጵያዊያን ምንጊዜም ይሄን አስታውሱ "እንቁላላችሁን አንድ ቅርጫት ውስጥ አታስቀምጡ" በተለይ አፍሪካ አገራት ውስጥ።

  • ሰው የፈለገ ቢሳሳት የመቃብር ሐውልት ላይ ፊደል ይሳሳታል? (አሌክስ አብርሃም) አሜሪካ ውስጥ በአገሩ ዘግናኝ ወንጀል  የፈፀመ፣ ወይም ቢሊየን ብሮች የዘረፈ ወንጀለኛ ተሰዶ ይኖራል። አሁን እንደምነግራችሁ አይነት ሚስኪን ሰው ደግሞ አለ፣ በአንዲት ፊደል ምክንያት ለስደት  የተዳረገ። በአንዲት ፊደል ብቻ! ባለፈው  ወደሆነ ቦታ በኡበር  ታክሲ እየሄድኩ ነበር። ሹፌሩ ከማሌዢያ የመጣ ትልቅ ሰው ነው። እያወራኝ "ሀገሬ ላይ በጣም አሪፍ ቢዝነስ ነበረኝ። የመቃብር ላይ ጽሑፍ እጽፍ ነበር፤ ተንደላቅቄ ነበር የምኖረው" አለኝ። ባዘነ ድምፅ። ​ "እና ታዲያ ለምን ወደዚህ መጣህ?" ​ "የተሰደድኩት የአንድ የተረገመ ባለስልጣን ሚስት የመቃብር እምነበረድ ላይ አንዲት ፊደል ተሳስቼ በመጻፌ፣ ሊገድለኝ ስለፈለገ ነበር" አለኝ። ​"እውነትህን ነው? ለአንዲት ፊደል?!" ​"አዎ ጌታዬ! አየህ፣ የምንጠቀመው ማላይኛ (ባሃሳ ማሌዢያ ይሉታል) በላቲን ፊደላት ነው የሚጻፈው። አንዲት ፊደል የምትፈጥረው ስህተት ቀላል እንዳይመስልህ። በእኛ ቋንቋ 'Kota' ማለት 'ከተማ' ማለት ነው። እኔም ሐውልቱ ላይ (('ባልሽ ብቻ ሳይሆን ቸርነትሽን የቀመሰው ሙሉ ከተማው አንቺን ይናፍቃል)) ብዬ አሳምሬ ጻፍኩ። ነገር ግን የሐውልቱ ምርቃት ቀን፣ ድፍን የከተማው ባለስልጣናትና ሀብታሞች በተሰበሰቡበት የተሸፈነበት ጨርቅ ሲነሳ... 'Kota' የሚለው ቃል ላይ ተሳስቼ 'a'ን በ 'e' ተክቻት ነበር። የተረገመች 'e'!" አለና መሪውን  በቡጢ ነረተው። ​ "እና 'e' ስትጨምርበት ምን ሆነ?" አልኩት። ​"Kote ሆነ!" ​"እኮ 'Kote' ምንድን ነው?" ​"የወንድ ብልት!" አሌክስ አብርሀም

  • Salam ychanale betsboch temlshalw🫴🫴

  • 17 апр.1 23685

    "ቪያ ዶሎሮሳ" የመከራ መንገድ ​(አሌክስ አብርሃም) ​ኢየሱስ ሊሰቀል መስቀሉን ተሸክሞ የሄደበት፣ ስድስት መቶ ሜትር ያህል የሚረዝም መንገድ "ቪያ ዶሎሮሳ" (የመከራ መንገድ) ይባላል። ይህም በኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ከሚገኘው፣ የሮማውያን ገዢ ከነበረው ከጰንጤናዊው ጲላጦስ የፍርድ አደባባይ ተነስቶ፣ ከከተማው ቅጥር ውጭ ወደሚገኘው ቀራኒዮ ድረስ ማለት ነው። ​በመሀል መንገድ ኢየሱስ ደከመ። ሲገረፍ ነው የዋለው፤ የእሾህ አክሊል ራሱ ላይ እየደፉ ሲዘባበቱበት ነው የዋሉት፤ ደክሟል። ያንን ትልቅ የመሰቀያ ግንድ መሸከም ከባድ ነው። ወታደሮቹ በወደቀበት እንዳይሞት ሰጉ። "ተሰቅሎ ይሙት እንጂ መንገድ ላይ ይሙት" አይደለም ትዕዛዙ። ኃጢአተኛ ነው፤ ከተማቸው ውስጥ ከሞተ ምድራቸውን ያረክስባቸዋል፤ እስከዚህ ድረስ ነበር የተጸየፉት። ዞር ብለው መስቀሉን በመሸከም የሚረዳ ሰው በዓይናቸው ፈለጉ። የሚበዙት እንባ የሚራጩ የኢየሩሳሌም እናቶች ናቸው። ​ያንን ሁሉ ዓሣና ዳቦ ከኢየሱስ እጅ በልቶ የጠገበው ሕዝብ የለም! በተዓምር ከሽባነት የተፈወሰው ሁሉ የለም! ዓይኑ የበራለት የለም! ከሞት የተነሳችው የለችም! አጋንንት የወጣለት የለም! ከሰላሳ ስምንት ዓመት ደዌ ተፈውሶ አልጋውን ተሸክሞ የሄደው የለም! ያ ሁሉ በመማል፣ በመገዘት "አንለይህም" ያሉ ደቀ መዛሙርት ዓይን ውስጥ አልገቡም። ወደ ቀራኒዮ ጉዞዋ ለብቻ ናት! ​ይሄ ነው የሚገርመኝ፤ አንድ ባላገር ጨው ሊገዛ ይምጣ ላምባ አይታወቅም፣ ብቻ ከተማ መጥቶ ግርግሩን እየተመለከተ ነበር። የቀሬናው ስምዖን ይባላል። ወታደሮቹ "ና" አሉና የኢየሱስን መስቀል አስገድደው አሸከሙት። ይሄ ሰውዬ ከየት እንደመጣ ታውቃላችሁ? ከአሁኗ ሊቢያ። ቀሬና ማለት ሊቢያ ውስጥ ነው የምትገኘው። በስደት ወደዚያ ከሄዱ አይሁዳውያን አንዱ ይሆናል። ብቻ ያ ሁሉ ድግስና ተዓምር ላይ ያልነበረ ሰው፣ መስቀሉ ላይና መከራው ላይ እግሩ ጣለው። ​በኋለኛ ዘመን ታሪኩ፣ ይህ ሰው በክርስትና ውስጥ እንዳለፈ የሚያትቱ ድርሳናት አሉ። የሆነ ሆኖ ተገደንም ይሁን ወደን፣ የማንን መከራ፣ የማንን መስቀል እንደተሸከምን አናውቅም ይሆናል። ደስታና ፍሥሐውን ያላየን እኛ፣ በመከራ መንገድ ላይ እግራችን ጥሎን ይሆናል፤ ግን ትንሣኤ አለ። የተሸከምነው መከራ "መከራ" ባይሆንስ? መላው የሰው ልጅ ይድንበት ዘንድ፣ እኛም በዘላለሙ መዝገብ ታሪካችን ይከተብ ዘንድ መፍትሔው ቢሆንስ? ​አስባችሁታል? በሰው ልጅ ታሪክ "አምላኩን የረዳ" የሚል ስያሜ ያለው ሌላ ሰው የለም። ይሄ ምስኪን ገጠሬ በሰውኛ ሲታይ ያደረገው ይሄንን ነው። በሁለት መስመር ጽሑፍ የዘላለም ታሪክ የሆነ ሰው! በራሴ ትንሽ ልበላቹ ፈጣሪ በምድር ስጋ ለብሶ ያደረጋቸው የኛ ህይወት ገፆች ናቸው አስተማሪያችንም ነው

  • በትላንትናው እለት ቴዲ አልበም እንካችሁ ብሎናል እኔ ወድጄዋለሁ

  • 14 мар.69872из sebalwengelbitseat

    የኔ  ነው  ያልሽኝ ለት.....                የኔም ስለነበር     የኔ  ያሉት ሁሉ  የራስ ላይሆን ነገር    የኔ  ነው  አትበይ..ያልኩሽ ለዛ ነበር ✍ብፅእት ስዩም

  • 8 мар.6543из ebstvworldwide

    መልካም የሴቶች ቀን!

  • 7 мар.6434из getem

    ባንድ ጭንቅላት በጠባብ ደረት ስንቱን ስሸከም ስንቱን ስደርት ለመሀላንኳ ምሳሌ ሚሆን ህያው ምልክት አንድም ሳላስቀር በሁሉም ሳጌጥ አጣሁኝ የክት እግሬ በመራው በነዳው ሲሄድ ጢሻ ለጢሻ ልቤም እንደ ዘር የትም ሲበተን ባገኘው እርሻ ለፈጠረኝም ለገደለኝም ስቆም ላምልኮ ስንት ብሆን ነው?.... አንድ ሰው ብቻ አልመስልምኮ!! By Tadios Alemayehu @getem @getem @paappii

  • አንዳንድ ቀኖች አሉ ምን አልባት ለናንተ ይሮጣሉ ለኔ ግን የአመት ያክል ዝግታ ያላቸው

  • የሰራቹኝን ስራ ያፈረሳቹትን ቃል የተናገራቹትን ቅስም ሰባሪ ንግግር ዞር ስል እየሰማው ያወራቹትን ወሬ ለመርሳት እየሞከርኩ ነው

  • አታፍቅር እያልኩት ለራሱ ሳስቼ ተቃቅፎ አየሁት እኔው ተሳስቼ አጃኢብ ከዛ በማግስቱ ትምርት እየሄድን ነገረኝ ማዘኑን እንደሆነ በድን አናላቹ ድንገት ሲሳለም አየሁት የሻምሱን እንጨት ቤት ፍሬ✍✍✍ https://t.me/blackiy77 https://t.me/blackiy77 https://t.me/blackiy77 https://t.me/blackiy77

  • የረሳሁክ መስሎኝ ስራመድ መንገዴን ሳሰላስል ጊዜ ናፈኩት መውደዴን ሂድ ብዬ ያነሳሁት እግሬ ሊራመድ ተሳነው መሄድንም ፈራው ልቤም አለች ለኔ: የተገፋ መውደድ የያዘ አፍቃሪ ተመልሶ የለም ብዙ አታቀርቅሪ ፍቅር ቢመላለስ ከመለየት ልቆ ከለቀቁ አይመጣ መያዝ ነው አጥብቆ ፍሬ ✍

  • ለመሄድ ቢሆንም እግር የተሰጠው ለማሰብ እኮ ነው ጭንቅላት የኖረው

  • ጥር 8፤2018  -   ተወዳጁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት፣ በተዋናይነትና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ውስጥ ስመጥር እና ተወዳጅ ከሆኑ የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ህመም በድንገት ከዚህ ዓለም ተለይቷል፡፡ ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነበር። ፈጣሪ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ለእርሱ መንግስተ ሰማያትን እመኛለሁ

  • 10 янв.1 46258

    በፍቅር እንጂ በንዋይኽ ላትገዛኝ ጊዜም ገለህ ከነገ ላይ አታባክነኝ          ፍሬ የፃፈችው https://t.me/blackiy77 https://t.me/blackiy77 https://t.me/blackiy77 https://t.me/blackiy77

  • 10 янв.1 09036

    #ብትሰብረኝም ና.. ተመለስ እንዳሻህ ሁን እንታረቅ በማሪያም ጣት፣ ይሻለኛል መጎዳቱ ለኔ ሞትነው አንተን ማጣት!! #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha https://t.me/blackiy77https://t.me/blackiy77 https://t.me/blackiy77 https://t.me/blackiy77