ግጥም በ ኤዶምገነት
Статистикаግጥም ብቻ ቤተሰብ ይሁኑ። የቻናላችንን የመወያያ ግሩፕ ለማግኘት https://t.me/slegtmenawga tiktok.com/@edom_ge ኤዶምገነት @Edom_Ge
- Последний пост
- 2 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሰላም ኤዱ ዜድ እባላለሁ። ይቅርታ ካላስቸገርኩሽ ይቺን ታሪኬን ቻናልሽ ላይ እንድትፖስቺያት ነበረ። የሰዎች ምክር ያስፈልገኛል ብዬ ስላመንኩ ነው። በብዙ ምክንያት እኔ እና እህቴ አንድ ላይ ከቤተሰብ ርቀን ነው የምንኖረው። እኔ ታላቅ ወንድሟ ነኝ እሷ ገና 17 አመቷ ነው 11ኛ ክፍል ናት። ጎበዝ ተማሪ እና ስርአት ያላት ነበረች፤ ግን አሁን እርጉዝ ናት። ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፤ እኔ እህቴ በዚህ ልክ ትሳሳታለች ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ቤተሰቦቻችን ወደ እኔ ሲልኳት "ለእሷም (ከአንተ ጋር) ከተማ መማር ይሻላታል፤ አንተንም ታነጋግርሃለች፣ አደራ ጠብቃት" ብለውኝ ነበር። ግን እሷ በሙሉ ልብ ከማፈቅረው ሰው አርግዣለሁ፣ ከእሱ ጋር መኖር እፈልጋለሁ አለችኝ። በሰአቱ በጣም ተናድጄ "የራስሽ ጉዳይ" አልኳት፤ ግን ሀሳብ ሆናብኝ ሳያት የወደፊት ህይወቷ እያሰጋኝ ነው። ያስረገዛትን ሰው እንድታስተዋውቀኝ ጠየቅኳት እና አንድ እሷን የሚያክል የ11ኛ ክፍል ተማሪ አምጥታ አስተዋወቀችኝ። ከዛ በኋላ 18 አመቱ እንደሆነ እና የሀብታም ልጅ ስለሆነ ብቻቸውን መኖር እንደሚችሉ እና ከአንተም ወንድምነትህን እንጂ ብር ምናምን አልፈልግም ብላ ነገረችኝ። ሊሆን እንደማይችል ባስረዳትም አልሰማችኝም እና የእህቴ ጉዳይ በጣም አስጨንቆኛል። ለማንም ሰው አላወራሁም፤ ቤተሰብ ቢሰሙ ምን ይሉኛል? "ጠብቃት አደራ" ብለውኝ አሁን እንዲህ ሆነች ለማለት አልቻልኩም። ምን ላድርግ? እህቴንስ ምን ልበላት? በናታችሁ የሆነ ነገር በሉኝ።
*** ፍቅር አለ ማይረሳ ፣ ሳቅን የሚቀማ ሰላም የሚነሳ ፣ ጭስ የማይደብቀው ፣ መጠጥ የማይፍቀው ፣ . አይንን የሚጋርድ ጆሮን የሚደፍን ፣ አንችሆየ አምባሰል ትዝታን ሚዘፍን ፣ ሌላ ማያሰማ ምክር የማይደንቀው ፣ መልክ ገለመሌ ውበት የማይሞቀው ፣ . ፍቅር አለ አዝጋሚ መቼም የማይጠፋ ፣ ከመጠጥ ከጭስ ከሁሉ ሚከፋ ፣ . ፍቅር አለ ፡፡ #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
አዲስ ነገር የለም """""""""""""""""""""" ከሰማዩ በታች የለም አዲስ ነገር፣ ጊዜ የገዛትን ታሪካዊት ምድር ጠይቋት ትናገር፣ ካንዱጋር ዳንኪራ ከሌላጋር ሀዘን፣ አንዱ ሲረጋጋ አንደኛው መባዘን፣ መጪ ስንቀበል ሌላው ተሰናባች፣ ተወለደ ሲባል እዛጋ ደሞ ሟች፣ የለም አዲስ ነገር ሆኖ እንጂ ለየቅል፣ ጊዜ ንጉስ ሆኖ አውርዶ ሲሰቅል፣ እኛም ሆነንለት ተጎናባሽ አሽከር፣ እንከተላለን .... በመሬት ዙሪያላይ ይዞን ሲሽከረከር፤ በዚች በቆምኩባት ባለሁበት ምድር፣ የወለደ ሲሞት ያሳደገ ሲድር፣ ጥንዶች ሲጫዎቱ የፍቅር ጫዎታ፣ ያረገዘች ስትወልድ ያገባ ሲፈታ፣ አማኝ የገዳም ሰው ወይም በግልባጭ፣ ጠንባዛ ሰካራም አንቡላ አንጫላጭ፣ መፍትሄ ጠፍቶበት ኑሮ ያቀወሰው፣ አይቻለሁ ባይኔ .... ጨርቁን ጥሎ ሲያብድ ጤነኛ ያልኩት ሰው፤ አዲስ ነገር የለም ስጠይቅ እራሴን .... ለምን እንደሆነ አንዱ አለፈ ሲባል ሌላው የሚተካ፣ ሲገባኝ እውነቱ .... ክብ አለም መዞር ነው ሂዎት ማለት ለካ። ✍ኤዶምገነት ፃፈችው @arifgtmbcha @arifgtmbcha
#አንተን_መውደድ ፏፏቴ ዳር ቁጭ ብሎ ዋሽንትን እንደ ማድመጥ፣ ዜማውን ተከትሎ በደስታ እንደ መስመጥ፣ አይንን ከደን እንዳረጉ የለሆሳስ ውዝዋዜ፣ ቢደጋገም የማይሰለች የሚናፈቅ አይነት ጊዜ፣ ከተፈጥሮ ተዋህዶ ንጹህ ህይወት እንደመልመድ፣ ልክ እንደዛ ሰላም አለው ደስ ያሰኛል አንተን መውደድ፡፡ #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
#ይሂድ . ለመሄድ ቀጠሮ ይዞ እያንቀላፋ ያለን ሰው፥ አባብለህ አታስቀረዉም መሄጃዉ ሲደርስ ቀስቅሰው፡፡ #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል እንኳን አደረሰን🤍🥰
#ብቻ_ይሳቅ መውዜርም አትስጡት ጎራዴም አትስጡት አይጠቅመውም ለሱ፣ ለመግደል ለመግደል ለመቅጣት ከሆነ ይበቃዋል ጥርሱ፣ ጉልበት የማይጠይቅ ልዩነው ፈገግታው ላየው ቀልብ ይገፋል፣ ለጠላው አይደለም ለወዳጁም ሳይቀር ሳቁ ይጋረፋል! #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
#እሷና_እሱ እሷ ኩሩ ናት ቅምጥል፣ አንድ ጌዜ ለብሳ የምጥል፣ እሱ ሚስኪን ነው ቆጥቋጣ፣ እሷን አግብቶ ተቀጣ። . ለአመት የመደበው ብር በቀናት እየተፈጀ፣ አቅታው የገዛ ሚስቱ ያለድሜው በጊዜ አረጀ! #ኤዶምገነት_ፃፈች @arifgtmbcha
#አምላኬ . ሆነልኝ ደስታና ሀሴት ሞላልኝ የኔ ሸለቆ፣ እያልኩኝ ባንተ ውለታ ይህ እርጉም ልቤ ተደንቆ፣ ላመሰግንህ ቀናስል የደስታ ለቅሶ አልቅሼ፣ በሰጠኸኝ ልክ ያረኩት አስጎነበሰኝ ምላሼ። #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
#እዴሜዬ..? በአንተ እሩጫ በእኔ አረማመድ፣ እንዴት እንዝለቅ ይሄንን መንገድ..? #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
#የኔ_እናት_እንዲህ_ናት . የማጠልቅ ፀሀይ ፣ የማጠቁር ሰማይ፣ የማትደርቅ አበባ፣ የማትረግፍ ወለባ፣ . ሁልጊዜ ደስታ፣ ዘወትር ጫዎታ፣ አትታይ ተከፍታ፣ አትታወቅ ፈርታ፣ . አዛኝ ሰው አክባሪ፣ ላድማጯ መካሪ፣ የማትሰምጥ መርከብ፣ የማትጠፋ ኮከብ፣ የማትጠር ንጋት፣ እናቴ እንዲህ ናት። #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
🫡አድዋ.... አሀዱ ጅማሬ ጥቁራን ሲነሱ፣ እንደ አሸን ፈልተው ሀገሬን ሲያለብሱ፣ ሞት ፅዋን ሲቀምሱ፣ ፍቅርን ሲዘምሩ ሲያነቡ ቀይ እንባ፣ ክተት በነጋሪት ዝመት በጥሩንባ፣ አድዋ.... ያንድነት ድል ዋልታ፣ ዘደብረ ሀበሻ ማተብ የማይፈታ፣ እምነተቢስ መቶ አረም እንዳይዘራ፣ ክብሩ ከሸፈበት በእነ ጣይቱ ጥበብ በእነ እምዬ ስራ፣ ከፋይ አከፋፋይ ሽንፈት የቀመሰ፣ በናቀው ምድር ላይ ደሙን አፈሰሰ፣ አድዋ.... የባላገር እልፍኝ የደመ ሙቅ ጓዳ፣ የቁርጥ ቀን ዎሰን ሰይፉን የከነዳ፣ ክብሩ የገነነ በነጭ የታፈረ፣ ሀቅ ያስመሰከረ.... በዝክረ ታቦቱ ውልደት የጀመረ፣ ያ ጥበብ ያ ቀለም ያ ስዕል አድዋ፣ በራቀው ሰማይ ስር ትውልድን የሰዋ፣ እልፎች ያለፉበት ታሪካዊ ዳና፣ ዛሬም ያኮራኛል ደማቸው ነኝ እና። ✍❤️✍❤️✍❤️ ኤዶምገነት ፃፈችው https://t.me/arifgtmbcha
#አንተ_ባለጊዜ . ገፋኝ ብሎ መውደቅ፣ ጊዜ ወስዶ ማድነቅ፣ ከአቻ ፋክክር፣ ከወዳጅ ምክክር፣ ለታክሲ መጋፋት፣ ለመናፈቅ መጥፋት፣ በትዝታ መዋጥ፣ አጥንት አዞ መጋጥ፤ . ለፓስታ እንኳ ሹካ፣ ቡና እስከ በረካ፣ ጠብቆ መጠጣት፣ ፊቱን ለመታጠብ በሳሙና መንጣት፣ ቆንጆ መርጦ ማግባት፣ ጫማ አውልቆ መግባት፣ ምኞት ለሆነበት ጌዜ ላልበቃው ሰው፣ ከሞላው ዘመንህ ምናል ብታውሰው፤ . ፓስታ እንዲበላ እንደሰው በሹካ፣ አንዲት ቆንጆ አግብቶ ዘሩን እንዲተካ፣ እሱም እንደ ሰው እስኪ ወግ ይድረሰው፣ ከጊዜህ ሽጥለት አለዚያም አውሰው። #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
#የባከነ _ሌሊት ወይ ሮንድ አላደርኩ ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ ወይ ሰአታት ቁሜ ቤተክስያን ስሜ ሰይጣን አላሳፈርሁ:: ሌቦች ደብድበውት አንዱን ምስኪን ላሥር ባምቢስ ድልድዩ ሥር ቆስሎ የወደቀ ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ "በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ ምስኪን አባወራ ብብት ሥር ገብቼ አፋፍሼ አንስቼ ተሸክሜ አድኜ ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ ወይ ምግባር አልሠራሁ ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ:: አንድ በትረ-ሙሴ ሁለት ስስ አሎሎ ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ ሲባክን ዝምብሎ " እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ" የምትል መለሎ ልቤን ሳትሰውረው አልጋየን ሳትሰብረው:: ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ " እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ:: አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት ሲገፉ ሲስቧት " እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን ልመናዋ ስቦኝ እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ ከሁዋላ ደርሼ ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን በማረግ ቃኝቼ ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ:: ድል ሳላስመዘግብ ውጥረት ሳለረግብ ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ:: By bewuketu seyoum @arifgtmbcha @arifgtmbcha
መልካም በዓል @arifgtmbcha @arifgtmbcha
አልፈልግም እኔ! ምን ያደርግልኛል የማላልፈው ድንበር ጥቅሙ አይታየኝም የማልገባበት በር እጅግ ቢያንገሸግሽ ኑሮዬ ከእሬት ምን ሊፈይድልኝ ሰው የሌለው መሬት አሳቻ ጠብቆ ሳያስቡ ድንገት በሚቆረጥበት የምስኪኖች አንገት የመንጋውን ውሀ እያደፈረሱ ቤት የሚገነቡት ሰው እያፈረሱ ኋላ ከምጎነጭ አይቀጡት ቅጣት በአፍንጫዬ ይውጣ ይሻለኛል ማጣት በብረት ብትፈልጡኝ በስለት ብትቆርጡኝ ይህ ደንዳና ልቤ ቁጣ አስደንግጦት መቼ ይርድና ይልቅ ጊዜ አትፍጁ ከዋሽቶ አደር ሰፈር የለኝም ዝምድና ከግብ ላያደርሰው የዛለን ሰው ጥማት አይገባኝም እኔ ህዝብ እየተናደ የከተማ ልማት ኢትዮጵያ ትቅደም! ✍️ ሚኪ https://t.me/blackiy77 join it @arifgtmbcha
ያያት ይመስላታል.. ለሱኮ አፍታ ናት፡ የሰከንድ ሽራፊ፣ ልብ ሳይላት ወታ፡ ወዲያው የምትጠልቅ፡ በውልብታ ጠፊ፣ እሱም ሙሉቀን ነው፡ እንደሙሉ ሌሊት፡ እንደሙሉ ንጋት፣ እና በምን በኩል፡ አንድ እሷን ለይቶ፡ ባይኑ ይፈልጋት ? #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
#እግርህ_ጠላቴ_ነው . በቃላት የልቤን ለመግለፅ አስቤ ፣ ወደድኩህ ለማለት ፃፍኩልህ ደብዳቤ ፣ ያለችኝን እውቀት አቅሜን አንጠፍጥፌ ፣ ምሁራን ጠይቄ ተጨንቄ ፅፌ ፣ መልስህን ለማወቅ እየጓጓሁ በጣም ፣ ላንተ ሚያደርስልኝ የሚሰጥህ ባጣም ፣ እንዲሁ በከንቱ ፅሁፌ እንዳይከስር ፣ ብታገኘውብዬ ጣልኩልህ በርህ ስር ። . በርህ ተከፈተ ከቤት እግርህ ወጣ ፣ ላፍታ ተጨነኩኝ ልቤ ምቱን አጣ ፣ አካሌ ደከመው ማየት ተደብቆ ፣ አይኔ ፈጦ ቀረ መልስህን ጠብቆ ፣ ግና አንድ ግዜ እድል ከኔርቆ ፣ ያ ያማረው ጫማህ ወሰደው ጨፍልቆ ፣ ታዲያ ከዚያ ወዲህ የምሻው ልነግርህ ፣ ቂም ይዤበታለሁ ጥላቴ ነው እግርህ። #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha
💐💐💐💐💐💐💐💐 ተፈፀመ ማህሌተ ፅጌ 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
* ይጠብቅህ የነበረው ትዕግስቴ አልቋል እና፣ . ቀን አትቁጠር ለመመለስ መፍጠን ከቻልክ አሁኑ ና! #ኤዶምገነት_ፃፈችው @arifgtmbcha