ዕቡህ ብዕር
Статистикаበ ዕቡህ ብዕራችን የሁሉንም ደጃፍ እያንኳኳን ስሜቶቻቸውን እንዳስሳለን. ብዕራችን ያቀለመውን በግጥም እያዋዛን ለእናንተ እናደርሳለን. ✍️ እንኳን ደህና መጣቹ ለማንኛውም ሀሳብ ፣ አስተያየት እና ጥያቄ @Tirrubel @ediwub @poempen ልታናግሩን ትችላላቹ🖋️
- Последний пост
- 7 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 504
- 1/48двое суток
- 577
- 1/72трое суток
- 622
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ይህችን ጥዑም ግጥም ተጋበዙልኝ🥰 ✍ዔደን ታደሰ @ediwub @topazionnn @topazionnn
ብታጭ ለምስራች ታበስረኝ ብትመጣ ስለ አለማመኔ እንደ ዘካርያስ ዲዳነት ነው የኔ ዕጣ ይኩነኒ አላልኩም እንደ እመአምላክ ከአምላክ ፊት የሚቆም ቢላክልኝ መልዓክ ታንኳ ተሰዶልኝ ማህበሉን ማለፊያ እኔን ሚያሳስበኝ ወጀቡን መቅዘፊያ ገብርኤል ገብርኤል መልዓከ ራማ ለደረቀ ልቤ ቃሉን ለተጠማ ላላመነ ነፍሴ ገድሉን እየሰማ ድረስለት ፈጥነህ! እርዳው አለማመኔን ለውጥልኝ ስሜን ! [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
#አቡነ_ሐራ_ድንግል #third_life_lesson_አቡነሐራ @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
#አቡነ_ሐራ_ድንግል #second_life_lesson_አቡነሐራ @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
#አቡነ_ሐራ_ድንግል_ተመልሻለሁ 😊 #First_life_lesson_አቡነሐራ @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
የ self development መፅሀፍ ይፈልጋሉ እንግዲያውስ ይቀላቀሉ https://t.me/Amharic_Books_storee
ሰው ሲሞት ብቻ ሳይሆን በቁሙም አበባ ይሰጠዋል 🌹 እዘዙ 😊 t.me/milkoret
✍ @Ediwub @topazionnn @topazionnn
#ስጠኝ_ስትሰጥ_አይቻለሁ የእናቴ የሁልጊዜ ጸሎት ነች ።አንድ ቀን እንዲህ ብዬ ጠየኳት? “የሽዬ ይችን ጸሎት ትወጃታለሽ ለምንድን ነው የምትደጋግሚያት?” “አይ ልጄ ይስጠኝ ሲሰጥ.... አይቸዋለሁ” “አምላክን ነው ?” “እና አባትህን ነው ?” ስቄ ዝም አልኩ .....ከትንሽ ቆይታ በኋላ እንዲህ ተረከችልኝ “ድሮ ነው ያኔ በደጉ ዘመን አንድ ድሃ ገበሬ ነበር። ጫካ ገብቶ እንጨት ሰብሮ ተሸክሞ ከተማ አምጥቶ ሸጦ ቤተሰቡን የሚያስተዳድር .... አንዴ ታዲያ እንደተለመደው እንጨቱን ሰብሮ ተሸክሞ ወደ ቤቱ ሊሄድ ሲል ይደክመውና አንዱ ዛፍ ስር ደገፍ ይላል ። ከቆይታዎች በኋላ ሙዳ ስጋ የያዘ ትልቅዬ አሞራ ሰውዬው ከተቀመጠበት ዛፍ ፊት ለፊት ካለ ዛፍ ያርፍና በማንቁርቱ ሊበላ ሲጣደፍ ድንገት ስጋው ይወድቃል ይሄኔ እጥፍጥፍ ብሎ ተኝቶ የነበረ አንድ ከሲታ ውሻ አይኖቹን ባለማመን ሙዳ ስጋ ው ላይ ዘሎ ይከመርና እየተጣደፈ መብላት ሲጀምር ያ ምስኪን ሰው ይመለከታል ወደ ሰማይ አንጋጦም እንዲህ ይላል። . “አይ እግዛብሄር አንተኮ ታላቅ ነህ .....በርሃብ ሊሞት የነበረውን ውሻ እንዲህ በጥበብ ትመግበው ....ስራህ ግሩም ነው። እግዚአብሄር ሆይ እንግዲህ ስትሰጥ አይቼሃለሁና ለኔም ስጠኝ ....ስጠኝ ስትሰጥ አይቼሃለሁ” ብሎ ተናግሮ እንጨቱን ትቶ ባዶ እጁን ቤቱ ይደርሳል ባለቤቱም ያየችውን ባለማመን “አንተ ሰውየ ቤት ውስጥ የሚበላ ነገር እንደሌለ እያወክ እንዴት የሚሸጥ እንጨት ሳትይዝ ትመጣለህ?” “አይዞሽ አትፍሪ ይስጠኝ ሲሰጥ አይቸዋለሁ” ብሎ ጠፍር አልጋ ላይ ወጥቶ ተኛ:: ሚስት በቁጣ እየለፈለፈች ቀኑ መሸ:: ሊነጋጋ ሲል በአቆማዳ የሞላ ጠገራ ብር ሰርቆ ሲሮጥ የነበረ ሌባ አባራሪዎቹ እየደረሱበት እንደሆነ ሲያውቅ ከሰውዬው ጎጆ በራፍ ላይ አስደግፎት ይሮጣል። በማለዳ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ የምትወደው የምስኪኑ ገበሬ ሚስት የጎጆዋን በራፍ ስትከፍት በአቁማዳ የሞላው ጠገራ ብር ወደቤቷ ግልብጥ ብሎ ይደፋል። . ይሄኔ ሃይለኛ እንቅልፍ ላይ የነበረውን ባለቤቷን ጸሎትህን ሰምቶሃል ተነስ ብላ ቀሰቀሰችው ምስኪኑም ያየውን ባለማመን “እግዚአብሄር ሆይ አመሰግንሃለሁ .... አሁንም ስጠኝ ሰትሰጥ አይቸሃለሁ” አለ ይባላል ልጄ፡፡ ከ TikTok ገፅ ( Abeni 🥰 ) ሳነብ ካገኘውት @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
#ኪዳን ( የመጨረሻ ክፍል ) አጭር ኢ-ልቦለድ ታሪክ . በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ . #ለመመለስ_አልረፈደም ክርስቶስ ሲሰቀል ሐዋርያት የተባሉት ሳይሆኑ ኃጥዓን ተብለው የተገፉት ናቸው ከስሩ የተገኙት ! ፀሃፊ እና አንባቢ :- [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
ለምናልባት ቦታ......... 😌 ወላጅ እናትህ በድገት ብትከዳህ ያፀድቃል ያልከው ሲኦል ቢነዳህ ለፈውስ የዋልከው አጉል ቢጎዳህ የስካሁን ውሎ የስኮሁን ኑሮ ቅዠት ነው ቢባል አስበህዋል⁈ አለህ ወይ ትከሻ አለህ ወይ መሸሻ ህመም ማስታገሻ አለህ ወይ ምንአልባት ማረፍያ ምቶንህ በዛ ጭቅ ሰአት ? ሙሉ አለም አትስራ አበጅለት ክፍተት ልክ ሆነህ አትኑር አክልበት ስተት ነፍስህ ይደናበር ዝግ ልብህን ስበር አፍርስ ግርግዳውን ለመስኮትና በር ሂወት ፀጋ ስትችር ያኔ እድትቀበል። ቻናሉን ይቀላቀሉ፧።~👇👇👇👇👇 @love_words_qutes @love_words_qutes @love_words_qutes https://t.me/love_words_qutes
<< ስትሞት ቀድመህ ምታደርገው ምንድነው >> ስትል ጠየቀችኝ ! መጨረሻዬ ምንም ሆነ ምን ለአምላኬ የማቀርበው አንድ ተማፅኖ ይኖረኛል! << ምን የሚል ? >> በማርያም አንድ ጊዜ መታቀፍን ! በማርያም አንድ ጊዜ መነካትን ! በማርያም አንድ ጊዜ ልጄ መባልን ! በማርያም አንድ ጊዜ መዳሰስን ! ተማፅኖዬ ይሄ ነው ! << መንግሥትህን አውርሰኝ ትላለህ ብዬ ስጠብቅ ነበር ! >> አቅፋ ለገሃነም እንደማትሰጠኝ አውቃለሁ! በእሷ ተዳስሼ ሲዖልም ብገባ ጠረኗ ገነት ሆኖ ያቆየኛል! [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
#በውበት_አትለካ ከማትገምቱት ሰው ጋር Collab አድርገናል ✨✍️ ተጋበዙልን ፀሐፊ :- [ ጥሩቤል ] አንባቢ :- @Mcole ( ሚኪ ✍️ ) X [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
#Special_Life_Lesson ይኼን Life Lesson የሰማ ብዙ ያተርፈበታል ከሁሉም Life Lesson Special የሆነ ነው የምር አድምጡት ብዙ ታተርፉበታላቹ [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
#ኪዳን ( ክፍል - 2 ) አጭር ኢ-ልቦለድ ታሪክ . በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ . ፀሃፊ እና አንባቢ :- [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
#ኪዳን አጭር ኢ-ልቦለድ ታሪክ . በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ . የመጀመሪያ አጭር ድርሰቴ ነው ሀሳባቹን አሳውቁኝ ✨ ፀሃፊ እና አንባቢ :- [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
✍ @Ediwub @topazionnn @topazionnn
አጀብ ዘንድሮ ሰይጣንም ጭምር ነው ስራ የፈታው.....የዘመኑ ሰው ለመንፈስም አልመች ብሏል። ቀጣዩ የተቃውሞ ሰልፍ ከሲዖል Broadcast መደረጉ አይቀሬ ነው ። [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
#አድነኝ_ሚካኤል በአርባ ቀኔ መዓዛ ደቂቅ ሰውነቴ በእናቴ ዕቅፍ ተይዛ ከመቅደስህ ገባው ላጠልቅ ማህተቤን ክንፈ ሚካኤል አሉት ስሜን ንፁህ ፀዳል ነፍሴ ተዳበሰ በእጅህ አንተ አባት ሆንከኝ እኔም ሆንኩኝ ልጅህ ልጅ ሳለሁ ከዕልፍኜ ጠረንክን ዘግኜ . . ጥርሴ ሲፍለቀለቅ እያጫወተው ነው አባቱ በክንፉ ወትሮም የመልአክ ልጅ ደስታ እኮ ነው ትርፉ ተብዬ አድጌ ተብዬ ጎልምሼ ማንነቴን ሳውቀው ተገኘው አንሼ ገፄ ሲሸመግል ጠፍቶኛል ወዜ ገና እንጭጭ ነው ነፍሴ ገላዬ አርባ ዓመት ነፍሴ አርባ ቀኑ ሁለቱም በጋራ ወደ ቅጥር አቀኑ አንዱ ታበየ ፊትህ ለማጎንበስ አንደኛው ዘለለ ከመቅደስህ ሲደርስ እንደምን ላሸብሽብ ታጠፈ መዳፌ ድንገት ተጠልፌ ኦ ሚካኤል ኦ መተንብል አላማረልኝም መዳፍህ ብጥል [ ጥሩቤል ] @ebuhbhr @ebuhbhr @tirrubel
መች ኖረን ነው የሚበቃን? እያወጋን በመንገድ ላይ ተያይዘን መች አለፍን መች አንድ ላይ ሳንሳቀቅ በነፃነት ተቃቀፍን መች በክረምት ለእግረ መንገድ በደመና አብረን ወጣን የሚያስፈራ የዶፍ ዝናብ በቆምንበት መቼ መታን በጭለማ አብረን ሆነን በጨረቃ መች ሰየምከኝ ሳላስበው ሳልገምተው መች በድንገት ጉንጬን ሳምከኝ በእቅፍክ ተከልዬ ከውጪ ዓለም መቼ ራቅን የብቻችን አየር ስበን ለብቻችን መቼ ሳቅን ባልተኖረ ትንሽ ክፍል ባልኖርንበት ትንሽ ቦታ የሚወራ ታሪክ ሳንፅፍ ቀን ሳናደምቅ ለትዝታ ይብቃን አልከኝ? ቤተ -ስኪያን ዳር ሕዝብ ቆሞ ሳናበራ የፍቅርን ጧፍ በሄድንበት ሳንታማ ሳንገባ ከሰዎች አፍ ሰማይ ምድር ሳይመሰክር ፍቅራችንን ሳያወራ በስማችን ምንዘክረው ሽራፊ ቀን ሳንጋራ መኖር አንተን ሳይሸልመኝ ሳንጣላ የረባ ጥል እንዲህ ይብቃን ፣እንዲህ እንጨርስ፣እንዲህ እንቅር በእንጥልጥል ✍#mercy @M_mercy27