tgindex
መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ✝

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ✝

Статистика

+ከተለያዩ ፅሁፎች የተገኙትን መንፈሳዊ ህይወትን የሚሰብኩ ፅሑፎችንና ትምህርቶችን እናካፍላችሁ፡፡ ''አንብበን እንለወጥ።'' +መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ https://t.me/menfesawe12+

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
11 430
−40 за 3 дн.
Сутки
−22
−0,19%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
716
24 постов
Вовлечённость
6,3%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 24
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
139
1/48двое суток
159
1/72трое суток
171

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ? ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ 🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

  • 13 авг.24удалён 13 авг.

    📕📚ምን አይነት ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፎችን ማግኘት ይፈልጋሉ⁉️⬇️⬇️⬇️ 📚1 መጽሐፍ ቅዱስ በግእዝ እና አማረኛ 📚2 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት 📚3 ሕማማት 📚4 እመጓ፣ዝጎራ፣መርበብት፣ሰበዝ 📚5 መጽሐፈ መነኮሳት 📚6 የመንፈስ ነጻነት በአቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ 📚7 የኤፍራጥስ ወንዝ 📚8 መዝሙረ ዳዊት ብራና 📚9 ሞታ የተነሳችው ሴት ምስክርነት 📚10 ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ 1-3 ✝️ ይ 🀄️ ላ 🀄️ ሉ ✝️

  • ፍርድ የእግዚአብሔር ነው፡፡ እኛ ግን ወንድሞቻችን ላይ በመጨከን ስንት ጊዜ በክርስቶስ የፍርዱ ዙፋን ላይ ተቀመጥን? የሰውን ድካም ሳንረዳ ፈጥነን በመፍረድ ስንት ጊዜ ራሳችንን በእግዚአብሔር ቦታ አስገባን? እስኪ ዮሴፍን እናስበው፡፡ ወደ ግብጽ ባሪያ አድርገው በግፍ የሸጡት ወንድሞቹ ከአባታቸው ሞት በኋላ እርሱ ወደ ተሾመበት ግብጽ መምጣት በፈለጉ ጊዜ፣ የክፋታችንን ብድራት ያስከፍለናል ብለው ስለፈሩ ‹‹በደላችንን ተውልን›› ሲሉ መልእክተኛ ልከውበት ነበር፡፡ የዋሁ ዮሴፍም ይህንን ሲሰማ እያለቀሰ እንዲህ አላቸው ‹‹አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?››፤ አይደለም ሳታውቀው ዐውቀኸው እንኳን በበደለህ ወገንህ ላይ ለመፍረድ ልብህ በከጀለህ ጊዜ ለራስህ የዮሴፍን ጥያቄ ጠይቀው፡፡ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?›› (ዘፍ 50፡19) ዲያቆን አቤል ካሣሁን https://t.me/menfesawe12

  • " ወንጌልን ለመጻፍ ለበረታው ክንድህና የአርያምን ኃይል ለተቀበለው ክርንህ ሰላም እላለው ዮሐንስ ሆይ ለከንቱው የዓለም እንጀራ ስሽቀዳደም መንፈሳዊውን መብል አላገኘሁምና የተሰውረውን መብልና የብርሃን መጽሐፍ ስጠኝ "               መልክአ ቅዱስ ዮሐንስ https://t.me/menfesawe12

  • ፍልሰታ ምን ማለት ነው? ፍልሰታ ማለት ‹ፈለሰ – ተሰደደ› ከሚለው ግሥ የወጣ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡›› 'ፍልሰታ ለማርያም' የሚለው የግእዝ ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡ ሐዋርያት ኹለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡›› ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት››  ብሎ ነገራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡ ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ። ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡ የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐሥራት አገር በመኾኗ እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡ ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው፤፡፡ ይቆየን ምንጭ፦ ማኅበረ ቅዱሳን https://t.me/menfesawe12

  • 5 авг.475410

    + አለመቁረብ ምን ያጎድላል? + የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ አዲስ አበባ መጥተው በቀደሱበት ጊዜ ሕዝቡ ጥቅጥቅ ብሎ ቅዳሴ መሳተፉን አይተው ተደስተው ሳያበቁ፥ የሚቆርበው ምዕመን ቁጥር እጅግ ትንሽ መሆኑን ተመልክተው በወቅቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ለነበሩት ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ “ሕዝቡን እየቀለዳችሁበት ነው፤ ሕዝቡም እናንተ ላይ እየቀለደባችሁ ነው” እንዳሏቸው ይነገራል። አቡኑ እውነታቸውን ነው። ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ መቁረብ ካለመፈለግ በላይ፥ ካህን ሆኖም አስተምሮ ካለማቁረብ በላይ ቀልድ ማግኘት ይከብዳል። በጥንት ዘመን አባቶች ሰላምታ ሲለዋወጡ ‘የጸሎት ሕይወትህ እንዴት ነው?’ ይባባሉ እንደነበረ ይነገራል። ከሰላምታው ጀርባ ያለው እሳቤ፥ አንድ ሰው የጸሎት ሕይወቱ ደህና ከሆነ፥ እርሱም ደህና እንደሆነ የሚያጠይቅ ነው። ይህ መለኪያ በአሁኑም ዘመን የሚሠራ ሆኖ ሳለ፥ የመንፈሳዊ ሕይወት ጤንነትን አመላካች ከሆኑ ነገሮች አንዱ የቅዱስ ቁርባን ሕይወታችን መሆኑን ማስታወስ መልካም ነው። ከቅዱስ ቁርባኑ የተለየ ክርስቲያን ከምን እንደጎደለ ለማወቅ፥ በአንጻሩ ቅዱስ ቁርባን የሚያስገኘውን ጥቅም ማስተዋል ጥሩ አማራጭ ነው። ቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ በጻፉት “አኮቴተ ቁርባን፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቅዳሴ መሠረት፥ ታሪካዊ እድገት እና ይዘት” በተሰኘ መጽሐፋቸው (ገጽ 42) ላይ እንዲህ በማለት ይዘረዝሩታል፦ ለኃጢአታችን ይቅርታ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበውን የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም በመቀበል የምንኖር ከሆነ፦ -    የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን አባልነታችን ይረጋገጣል። -    በተፈጠርንበት የእግዚአብሔር አርአያና አምሳል እናድጋለን። -    የጌታን ሕማምና ሞት እያሰብን በምናደርገው የቅዳሴ አገልግሎት ምክንያት የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን በዝቶ ይፈስልናል። (ሮሜ 5፡5) -     “ፈኑ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ - የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ላክልን” እያልን በቅዳሴው አገልግሎት ዘወትር ስንለምን፥ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በየጊዜው እንቀበላለን። -    በሥጋውና በደሙ የምንቀበለው መድኃኒታችን ክርስቶስ በውስጣችን ህልው ስለሚሆን፥ ወደተፈጠርንበት ዓላማ፥ ይኸውም ከእግዚአብሔር ጋር ሙሉ ኅብረት ወደ ማግኘት እናድጋለን። -    እንደ እና ቅዱስ ቁርባንን ከሚቀበሉ አማንያን ጋር ኅብረት ይኖረናል። -    በጥምቀት የተቀበልነውን የልጅነት ጸጋ ጠብቅን እንድንኖር ያደርገናል። -    ሥርየተ ኃጢአትን (የኃጢአት ይቅርታን) እናገኛለን (1 ዮሐ 1፡7)፤ እንዲሁም ለኃጢአት ሞተን ድል አድራጊ ሕይወትን እንጎናጸፋለን። (ሮሜ 6፡11) -    ክርስቶስን የመምሰል ወይም ክርስቶስን የተሸከምን (ጸዋርያነ ክርስቶስ) እንሆናለን። -    በክርስቶስ የተሰጠን ዘላለማዊ ሕይወት እውን ይሆንልናል። -    የመንፈሳዊ ሕይወታችን መገለጫ ይሆንልናል፤ ይህን ሰማያዊ ማዕድ ሳንቀበል በፍጹም መኖር አንችልም። ስለሆነም በቅዱስ ቁርባን የምንቀበለው መድኃኒታችን ክርስቶስ ሕይወታችን ይሆናል። ይህ በቅዱስ ቁርባን የከበረ ሕይወት መለኮታዊ ጸጋን አልብሶ፥ የእግዚአብሔርን አርአያ እና አምሳል በሕይወታችን ወደምናሳይበት መንፈሳዊ ደረጃ ያሳድገናል። ከቅዱስ ቁርባን ራስን ማግለል ማለት ከላይ የተጠቀሱትን ጥቅሞች ሁሉ በራስ እጅ መግፋት ማለት ነው። ከዚህ ሁሉ ጎድለን ክርስትናችንን እንዳናጣ፥ የመዳን ቀን ዛሬ መሆኑን በማስታወስ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ከሕይወት ማዕድ እንቀበል። 🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

  • ከወድሞች አንዱ ወደ አረጋዊ መጣና " አባ ፣ ደካማ ነኝና ጸልዩልኝ " አለው፡፡ አረጋዊም እንዲህ አለው " በሸተኛን ይቀባ ዘንድ በእጁ ቅባት የሚይዝና ሌላውን የሚቀባ ሰው እርሱም ደኀና ሆኖ ይቀባል፡፡ እንዲሁም እኛም ለሌላው ስንጸልይ ለራሳችን መድኃኒትና ፍስሐ ይሆነናል፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ሆይ ፣ አንዳችን ለሌላችን ልንጸልይና እርስ በርሳችን በጸሎት ልንተሳሰብ ይገባናል፤ ሐዋርያው " ትድኑ ዘንድ ለወንድሞቻችሁ ጸልዩ " ብሎ እንዳዘዘን። ከበረሐዊያን ህይወት አንደበት https://t.me/menfesawe12

  • የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ተራዳቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ለቅዱስ ቂርቆስና ለቅድስት ኢየሉጣ ተረዳኢ የሆነበት ሐምሌ ፲፱ ቀን ታላቅ በዓል በመሆኑ ቅድስት ቤተ ከርስቲያናችንም  ታከብረዋለች፡፡ የእነዚህም ቅዱሳን ታሪክ በስንክሳር እንደተመዘገበው እንዲህ ይተረካል፡፡ ቅድስት ኢየሉጣ በሮም ግዛት በሚገኝ አንጌቤን በሚባል አገር በፈሪሃ እግዚአብሔር፣ በክርስትና ሃይማኖት እና በበጎ ምግባር ጸንታ ትኖር የነበረች ደግ ሴት ናት፡፡ በሥርዓት ያሳደገችው ቂርቆስ የሚባል ሕፃን ልጅም ነበራት፡፡ ይህቺ ቅድስት የዘመኑን አረማዊ መኰንን እለእስክንድሮስን በመፍራቷ ከልጇ ጋር ከሮም ወደ ጠርሴስ በተሰደደች ጊዜ መኰንኑ እነርሱ ከሚገኙበት አገር ገብቶ ክርስቲያኖችን እያሳደደ መግደል ጀመረ፡፡ የንጉሡ ወታደሮችም እግዚአብሔርን እንዲክዱ፤ ለጣዖት እንዲሰግዱ ቅድስት ኢየሉጣንና ቅዱስ ቂርቆስን አስፈራሯቸው፡፡ ቅዱሳኑ ግን ሃይማኖታቸውን ለመለወጥ ፈቃደኛ አልሆኑም ነበር፡፡ በዚህም መኰንኑ ተቈጥቶ በዓይንና በአፍንጫቸው ውስጥ ጨውና ሰናፍጭ በመጨመር፤ በጋሉ የብረት ችንካሮች በመቸንከርና መላ ሰውነታቸውን በመብሳት በብዙ ዓይነት መሣሪያ አሠቃያቸው፡፡ እግዚአብሔርም የጋሉ ብረቶችን እንደ ውኀ ያቀዘቅዝላቸው፤ ሥቃያቸውንም ያቀልላቸው ነበር፡፡ በሌላ ጊዜም በገመድ አሳሥሮ ንጉሡ ሲያስጨንቃቸው ከቆየ በኋላ ራሳቸውን ከቆዳቸው ጋር አስላጭቶ እሳት አነደደባቸው፡፡ ዳግመኛም ከትከሻቸው እስከ እግራቸው ድረስ በሚደርሱ ችንካሮች ቸነከራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ከሥቃያቸው አድኗቸዋል፡፡ አሁንም ቀኑን ሙሉ በልዩ ልዩ የሥቃይ መሣሪያዎች ቢያስጨንቃቸውም የእግዚአብሔር ኃይልና የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት አልተለያቸውም ነበርና ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም፡፡ እንደ ገናም በመጋዝ ሰንጥቀው በብረት ምጣድ በቆሏቸው ጊዜ ጌታችን ከሞት አነሣቸውና በመኰንኑ ፊት ድንቅ ተአምራትን አደረጉ፡፡ ከተአምራቱ መካከልም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ የመኰንኑን ጫማ በጸሎት ወደ በሬነት እንዲቀየር ማድረጉ ተጠቃሽ ሲሆን፣ መኰንኑ በተአምራቱ ተቈጥቶ የቅዱስ ቂርቆስን ምላስ አስቈርጦታል፤ ጌታችንም ምላሱን አድኖለታል፡፡ ዳግመኛም በፈላ የጋን ውኀ ውስጥ ቅዱሳን ቂርቆስና ኢየሉጣን ሊጨምሯቸው ሲሉ ቅድስት ኢየሉጣ በፈራች ጊዜ ቅዱስ ቂርቆስ ‹‹እናቴ ሆይ  አትፍሪ፤  አናንያ፣ ዓዛርያና  ሚሳኤልን  ከእሳት ነበልባል ያዳናቸው እግዚአብሔር እኛንም ከዚህ የፈላ ውኀ ያድነናል›› እያለ ያረጋጋት በተጋድሎዋ እንድትጸና ወደ እግዚአብሔር ይጸልይላት ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ተያይዘው ወደ ጋኑ ውስጥ ገቡ፡፡ ያ ውኀም እንደ ውርጭ ቀዘቀዘ፡፡ ደግሞም ወታደሮቹ መንኰራኵር ባለበት የብረት ምጣድ ውስጥ አስገብተው ሥጋቸው እስኪቈራረጥ ድረስ በጎተቷቸው ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል አድኗቸዋል፡፡ በመጨረሻም ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ተቀብለው በመንፈቀ ሌሊት አንገታቸውን ተቈርጠው በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ እስከ ሞት ድረስ በታመኑበት ተጋድሏቸውም ከእግዚአብሔር ዘንድ የሕይወትን አክሊል ተቀብለዋል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣ የዚህን ዓለም ጣዕም በመናቅ  ‹‹ሞት   ቢሆን፣  ሕይወትም  ቢሆን፣ መላእክትም ቢሆኑ፣  ግዛትም ቢሆን፣  ያለውም ቢሆን፣  የሚመጣውም  ቢሆን፣ ኃይላትም ቢሆኑ፣  ከፍታም ቢሆን፣  ዝቅታም ቢሆን፣  ልዩ ፍጥረትም  ቢሆን  በክርስቶስ  ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ›› በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን ቃል በተግባር በማሳየት ለክርስቶስ ፍቅር ሲሉ ራሳቸውን ለመከራና ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ ቅዱሳኑ ተጋድሏቸውን እስኪፈጽሙ ድረስም ቅዱስ ገብርኤል አልተለያቸውም፡፡ በቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት ቅድስት ኢየሉጣና ቅዱስ ቂርቆስ ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ምእመናንም ተጠቅመዋል፡፡ ስሙ በሚጠራባቸው ገዳማትና አድባራት መልአኩ የሚያደርጋቸው ድንቅ ድንቅ ተአምራት ለዚህ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ይህም ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔር ስም መከራ የሚቀበሉ ምእመናንን እንደሚጠብቁና ከልዩ ልዩ ደዌ እንደሚፈውሱ የሚያስረዳ ታሪክ ነው፡፡ (ሮሜ. ፰፥፴፰-፴፱) እኛም በሃይማኖታችን ምክንያት መከራ ባጋጠመን ጊዜ ቈራጥ ልብ ያለው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ‹‹እናቴ ሆይ አትፍሪ›› እያለ በእሳት ውስጥ ሊጣሉ ባሉበት ወቅት እናቱን እንድትጸናና ለሰማዕትነት እንድትበቃ እንዳደረጋት ሁሉ፣ ዘለዓለማዊውን የእግዚአብሔርን መንግሥት በአንድነት ለመውረስ እንድንችል ‹‹አይዞህ! አይዞሽ! አትፍራ! አትፍሪ›› በመባባል በዚህ ዓለም የሚገጥመንን መከራ ታግሠን፣ እስከ ሞት ድረስ በሃይማኖታችን ጸንተን መኖር ይገባናል፡፡ ክርስትና ለብቻ የሚጸደቅበት መንገድ ሳይሆን በጋራ ዋጋ የሚያገኙበት የድኅነት በር ነውና፡፡ ከዚሁ ሁሉ ጋርም ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን የተራዳው የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በአማላጅነቱ እንዲጠብቀን ‹‹በተአምኖ ንሴፎ ትንባሌ ዚአከ መዓልተ ወሌሊተ፤ በእግዚአብሔር ታምነን በቀንም በሌሊትም የአንተን ልመና ተስፋ እናደርጋለን›› እያልን ዘወትር ልንማጸነው ያስፈልጋል፡፡ እርሱ ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር በተሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት ከሚደርስብን ልዩ ልዩ መከራና ሥቃይ ያድነናልና፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር  መልአክ  በሚፈሩት  ሰዎች  ዙርያ  ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (መዝ. ፴፬፥፯)፡፡ ይህን እንድናደርግም የቅዱሳን ተራዳኢነት አይለየን፡፡ የቅዱስ ገብርኤል፣ ቅድስት ኢየሉጣ እና ቅዱስ ቂርቆስ ጸሎታቸው፣ ምልጃቸው ይጠብቀን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ፤ ስንክሳር ዘወርኃ ሐምሌ https://t.me/menfesawe12

  • "አንተ ራስህ ለገዛ ወንድምህ ጨካኝና ይቅር የማትል ኾነህ ሳለስ እግዚአብሔር እንዲራራልህና እንዲምርህ እንዴት መለመን ይቻልሃል? "ባልንጀራህ ምናልባት ንቆህ ሊኾን ይችላል፡፡ አዎ! አንተ ግን እግዚአብሔርን ኹልጊዜ እንደናቅኸው ነው፡፡ በባልንጀራና በእግዚአብሔር መካከልስ ምን ንጽጽር አለ? ባልንጀራህ ምናልባት ጉዳት ሲደርስበት ሰድቦህ ይኾናል፤ አንተም በዚህ ተበሳጭተህ ይኾናል፡፡ አንተ ግን ምንም ሳይጎዳህና በአንተ ላይ ክፉ ሳያስብ ይልቁንም ዕለት ዕለት በረከቱን እየተቀበልክ እያለ እግዚአብሔርን ሰድበኸዋል፡፡ እንግዲህ ተመልከት! ነቢዩ፡- “እመሰ ኃጢአተኑ ትትዐቀብ እግዚኦ መኑ ይቀውም - አቤቱ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ ማን ይቆማል?” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የምንፈጽመውን በደል ቢመረምር ኖሮ አንዲት ቀንስ እንኳን በሕይወት መቆየት አንችልም ነበር (መዝ.129፡3)፡፡ እያንዳንዱ በደለኛ ሰው ለራሱ የሚያውቀውንና ሌላ ሰው የማይመሰክርበትን እግዚአብሔር ብቻዉን ግን የሚያውቀውንስ ይቅርና የተገለጠውና ሰው ኹሉ የሚያውቀው ኃጢአታችንን እንኳን እግዚአብሔር ቢቈጣጠር ኖሮ ከእነዚህ ኃጢአቶች በኋላ የምንጠብቀው ምንድን ነው? እግዚአብሔር ንዝህላልነታችንንና ጸሎት ስናደርስ የምናሳየው ግድየለሽነታችንን፣ ሠራተኞች ለአሠሪዎቻቸው ወታደሮችም ለአለቆቻቸው ጓደኛሞች ለጓደኞቻቸው የሚያሳዩትን ፍርሐትና ክብር ያህልስ እንኳን ለጸሎትና ለልመና በፊቱ በቆምን ጊዜ አለማሳየታችንን ቢቈጣጠር ኖሮ ምን ነበር የምንኾነው? አንተ ከጓደኛህ ጋር ስትነጋገር ለምታደርገው ማንኛውም ነገር ትጠነቀቃለህ፡፡ ስለ በደሎችህ እግዚአብሔርን ስትጠብቀው፣ ለብዙ መተላለፎችህ ይቅርታን ስትጠይቀው፣ ሥርየትን ለማግኘት ስታሳስበው ግን [በፊቱ ላይ] ኹልጊዜ ግድየለሽ ትኾናለህ፡፡ ጉልበትህ በምድር ላይ ተንበርክኮ ሳለ ልቡናህ ግን እዚህም እዚያም፣ በገበያ ሥፍራም፣ በቤት ውስጥም ይዋልላል፤ ከንፈርህ በከንቱና እንዲሁ ያነበንባል፤ ይህን የምንፈጽመው ደግሞ አንዴ ወይም ኹለቴ ሳይኾን ኹልጊዜ ነው። እንግዲህ እግዚአብሔር ይህን ብቻ እንኳን ቢመረምር ይቅርታን ወይም ምሕረትን እንደምናገኝ ታስባለህን? በእውነት አይመስለኝም!" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ https://t.me/menfesawe12

  • “በእናንተ ዘንድ ግን ሁሉ በፍቅር ይሁን” 1 ቆሮ 16:-14

  • "ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታድርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጥል አይደለም፡፡ የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በእናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ https://t.me/menfesawe12

  • ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት አባታችን አብርሃም እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ድንኳን ሠርቶ እንግዶች እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ ይኖር ነበር፡፡ ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ ለተንኮል አያርፍምና ይህንን መልካም ግብሩን፣ ርኅራኄውን፣ ትሕትናውን አይቶ ሊፈትነው አሰበ፡፡ አስቦም አልቀረ የተጎዳ ሰው መስሎ፣ ራሱን ፈንክቶ፣ ከጎዳና ላይ ቆሞ አብርሃም ቤት ለሚመጡ እንግዶች “ወዴት ትሄዳላችሁ? እያለ ይጠይቃቸው ጀመር፡፡ እነርሱም ወደ አብርሃም ቤት እንደሚሄዱ በገለጹለት ጊዜ አብርሃም እንግዳ መቀበል እንደተወ፣ ልብሱን ገፎ እንደመለሰው ነገራቸው፡፡ እንግዶቹም እውነት መስሏቸው እያዘኑ ይመለሱ ነበር፡፡ በዚህ የተሣም እንግዳ ወደ አብርሃም ቤት መምጣት ቀረ፡፡ አብርሃምም ማዕደ እግዚአብሔር ያለ እንግዳ አይበላምና ሦስት ቀን ሳይመገብ ጾሙን አደረ፡፡ በሦስተኛው ቀንም ይህን ደግነቱ እግዚአብሔር ተመልክቶ በኦሪት ዘፍጥረት ፲፰፥፩-፲፱ ተጽፎ እንደምናገኘው አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በሦስት ሰዎች አምሳል በመምሬ አድባር ዛፍ ተገለጡለት፡፡ አብርሃምም ከድንኳን ደጃፍ ተነሥቶ ወደ እነርሱ ሰገደና “አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈው” አለ፡፡ እነርሱም “ስለ ደከመን አዝለህ ውሰደን” አሉት፡፡ አንዱን አዝሎ ከገባ በኋላ በአምላካዊ ግብር ሁለቱም ገብተው ተገኙ፡፡ አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሚስቱ ሣራ ፈጥኖ ገባና “ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ ለውሺ፤ እንጎቻም አድርጊ” አላት፡፡ አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፤ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴናው ሰጠው፤ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኮለ፡፡ እርጎና ማር፣ ያን ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፤ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም በፊታቸው ቆሞ ያሳልፍላቸው ነበር፤ እነርሱም በሉ። መብላታቸውም አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በሰው አምሳል ስለ ተገለጡና ለአብርሃምም የበሉ መስለው ስለታዩት ተመግበዋል ተባለ እንጂ ለሥላሴ መብል መጠጥ የሚስማማቸው ሆኖ አይደለም፡፡ ሥላሴ ምግብ በሉ ማለት ቅቤ ከእሳት ገብቶ አልቀለጠም እንደ ማለት ነው፡፡ ከዚያም የታረደው ጥጃ ተነሥቶ “ስብሐት ለአብ፣ ስብሐት ለወልድ፣ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ” ብሎ አምላክን አመስግኗል፡፡ ሊሄዱም ሲሉ ከሦስቱ አንዱ እግዚአብሔር ቃል “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ልጅ ታገኛለች” አለ፡፡ ለጊዜው ስለ ልጁ ይስሐቅ ሲሆን ፍጻሜው ግን እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆኖ እንደሚያድነው ሲነግረው ነው፡፡ ይህ ታሪክ የተፈጸመው ከ፳፻-፲፰፻፶ (2000-1850) ዓ.ዓ. አካባቢ ነው፡፡ ከዚህ ብዙ ትምህርት እንማራለን፡፡ ለምሳሌ ያህልም የሚከተሉትን እንጠቅሳለን፡፡ ሀ. የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት አንድነቱና ሦስትነቱ እንዴት ነው? ቢሉ በዘፍጥረት ፲፰፥፪-፭ ላይ ያለውን ኃይለ ቃል መመልከት አስፈላጊ ይሆናል፡፡ “ዓይኑንም ባነሣ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳን ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤ እንዲህም አለ፤ “አቤቱ በፊትህስ ባለሟልነትን አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈው፤ ውኃ ላምጣላችሁ እግራችሁንም ታጠቡ” የሚለው ኃይለ ቃል ሦስትነቱ “ሦስት ሰዎች… ሊቀበላቸው፣ ወደ እነርሱ” የሚሉት ሐረጋት ሦስተነቱን ሲገልጽ “በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባርያህን አትለፈኝ” የሚለው ዓረፍተ ነገር ደግሞ አንድነቱን ይገልጻል፡፡ እንዲሁም ሦስት መስፈሪያ የሦስትነት፣ እንጎቻው (ዳቦ) አንድ መሆኑ የአንድነቱ ምሳሌ ነው፡፡ ለ. እግዚአብሔር ለአብርሃም ልጅ እንደሚወልድ ያበሠረበት ቀን ነው፡፡ አባታችን ጻድቁ አብርሃም እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ አበ ብዙኀን (የብዙዎች አባት) እንደሚሆን ቢነግረውም ልጅ ግን አልነበረውም፡፡ በዚህ እንግዳ ተቀባይነቱና መልካም ሥራው እግዚአብሔር በእንግድነቱ ከቤቱ በገባ ጊዜ በእርጅናው ልጅ እንደሚወልድ (ልጅ እንደሚሰጠው) አበሠረው፡፡ እግዚአብሔር እንደ አብርሃም ቅን ልቡና ያላቸውና ለጋሾች ለሆኑ፣ ምጽዋት መስጠትና እንግዳ መቀበል የዘወትር ልማዳቸው አድርገው በሚኖሩ ሰዎች ቤት እንደሚገኝ እንዲሁም ሲገባም የተዘጋ ማኅፀን እንደሚከፍት፣ ቤትንም በበረከት እንደሚሞላ እንዲሁም የተሠወረ ምሥጢር እንደሚገልጽ እንረዳለን፡፡ ሐ. የአብርሃም ድንኳን አባቶቻችን ሊቃውንት እንደተረጎሙልን የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡ በአብርሃም ድንኳን አላፊ አግዳሚ ያርፍበት፣ ይመገብበት እንደነበር ሁሉ እመቤታችን የነፍስም የሥጋም መድኃኒት፣ የዘለዓለም ማረፊያ፣ እውነተኛ መብልና መጠጥ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች እርሷ ናትና በአብርሃም ድንኳን ትመሰላለች፡፡ ቀትር በሆነ ጊዜም በስድስት ሰዓት አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በአብርሃም ድንኳን እንደገቡ፣ በስድስተኛው ወርም ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እመቤታችን ተልኳልና፡፡ (ሉቃ.፩፥፳፮) በሐምሌ ሰባት (፯) ቀን እግዚአብሔር አምላክ በአብርሃም ቤት ተገኝቶ እንደባረከው ቅን ልቡና ያላቸውን፣ ለጋሾች ለሆኑ፣ ምጽዋትን ለሚያቀርቡ፣ እንግዳ መቀበል የዘወትር ልማዳቸው ላደረጉ ሰዎች በቤታቸው ይገባል፡፡ የተዘጋውንም ማኅፀን እንደከፈተ ቤቱንም እንደባረከ አይተናል፡፡ ዛሬም እኛም ለተራቡ በማብላት፣ ለተጠሙ በማጠጣት፣ ለታረዙ በማልበስ፣ በመመጽወትና በመሳሰለው ተግባር መኖር፣ በቀና አስተሳሰብ መጓዝ እንዳለብን መጽሐፍ ይነግረናል፡፡ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ቸርነታቸውና ምሕረታቸው አይለየን፤ አሜን!!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!!!

  • ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጠርሴስ ከተማ ለዘጠኝ ዓመታት ቆይቷል። ከኢየሩሳሌም ውጭ የአሕዛብ ከተማ በነበረችው በአንጾኪያ የክርስትና ሃይማኖት ተስፋፋ። ከኢየሩሳሌም የተሰደዱት ክርስቲያኖች የአንጾኪያን ሕዝብ ተግተው በማስተማራቸው ዝናው እስከ ኢየሩሳሌም ደረሰ። በዚህም ምክንያት በኢየሩሳሌም የነበሩት አበው በርናባስን ወደ አንጾኪያ ላኩት። በርናባስ የግሪክ ቋንቋ ችሎታ ያለውን፣ ከማንኛውም ሰው ጋር መግባብ የሚችለውን፣ ደግሞም እግዚአብሔር ለአሕዛብ ሐዋርያ እንዲሆን የመረጠውን ቅዱስ ጳውሎስን ከጠርሴስ በማምጣት በአንጾኪያ ሥራቸውን ጀመሩ። በገላትያ መልእክቱ ምዕራፍ ፪ ላይ ራሱ እንደገለጠው ከአሥራ አራት ዓመት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ከአንጾኪያ ክርስቲያኖች የሰበሰበውን ርዳታ ይዞ ወጣ። በዚህም በአይሁድና በአሕዛብ መካከል የነበረውን መለያየት ክርስትና አንድ እንዳደረገው አስመሰክሯል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመጀመሪያውን ጉዞ ያደረገው ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ከተመለሰ በኋላ በልዑል እግዚአብሔር ጥሪ በአሕዛብ ሀገር ወንጌልን ለመስበክ ከበርናባስ ነው። በዚህ ጉዞአቸው በጠቅላላ ወደ ፪፼ (ሁለት ሺህ) ኪሎ ሜትር የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዟል። ይህም ጉዞ የተከናወነው በ፵፮ ዓ.ም. አካባቢ ነው። ሁለተኛው ጉዞ የተከናወነው በ፶ ዓ.ም. ገደማ ነው። በመጀመሪያው ጉዞ ማርቆስ አብሮ ተጉዞ ነበር። ነገር ግን ጵንፍልያ ከተማ ሲደርስ እናቱ ስለናፈቀችው መመለስ በመፈለጉ በርናባስ ወደ ኢየሩሳሌም ይዞት መጣ። ስለዚህም በሁለተኛው ጉዞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲላስን ይዞ ወደ ኪልቂያ ሶርያ ሲጓዝ በርናባስ ደግሞ ማርቆስን አስከትሎ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። በዚህ ጉዞው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ግሪክ ደርሶአል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስን ያገኘው በዚሁ ጉዞው በልስጥራ ከተማ ነው። ሦስተኛው ጉዞ የተከናወነው በ፶፬ ዓ.ም. ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከልዩ ልዩ ሀገሮች ክርስቲያኖች የሰበሰበውን ዕርዳታ ለኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን በመያዝ ሦስተኛውን ጉዞ አጠናቅቆ ኢየሩሳሌም ገባ። ነገር ግን ኢየሩሳሌም የገባበት ጊዜ የፋሲካ በዓል ስለነበር ከልዩ ልዩ ሀገሮች የተሰበሰቡ አይሁድ በከተማዋ ነበሩ። እነዚህ በዝርወት የሚኖሩ አይሁድ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን በየሀገራቸው በትምህርቱ የተነሣ ሲቃወሙት የነበሩ ናቸው። እኒህ አይሁድ ቅዱስ ጳውሎስን በኢየሩሳሌም ሲያዩት ታላቅ ተቃውሞ አነሡበት። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ተቃውሞ አነሡበት። ሐዋርያው  ቅዱስ ጳውሎስም  ተቃውሞአቸውን ለመግታት እንደ አይሁድ  ሕግ በቤተ መቅደስ የመንጻት ሥርዓት መፈጸም ጀመረ። ነገር ግን ከኤፌሶን የተከተለውን ጥሮፊሞስን ወደ መቅደስ ያስገባው ስለመሰላቸው ተቃውሞአቸው በረታ። ከተማውንም አወኩት፤ ይህ ቅዱስ ጳውሎስን በ፶፰ ዓ.ም. ለሮም እሥር ዳረገው። ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ታስሮ ሮም ገባ። በዚያም በቁም እሥር ለሁለት ዓመታት ያህል ወንጌልን ሰበከ። የሁለቱን ዓመት የቁም እሥር እንደጨረሰ ወደ ኔሮን ፍርድ ቤት ቀረበ። ይህም በ፷ዎቹ ዓ.ም ነው። በፍርድ ቤቱ በተደረገው ምርመራ የሮሜን ሕግ የሚቃወም  ምንም ወንጀል ስላልተገኘበት በነፃ ተለቀቀ፤ ከዚህ በኋላ  ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አራተኛውንና የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ያልመዘገበውን ጉዞውን ያደረገው። ይህ ጉዞው በመታሠሩ አዝነው ተክዘው የነበሩ ክርስቲያኖችን ለማጽናናት የጀመራቸውን ሥራዎች ፍጻሜ ለማየት የተደረገ ጉዞ ነው። በመጨረሻ በ፷፬ ዓ.ም. ኔሮን በጥጋቡ የሮማ ከተማ ስትቃጠል ምን እንደምትመስል ማየት እፈልጋለሁ ብሎ አቃጠላት። የሮም ሕዝብ በከተማው መቃጠል በማዘኑና በማመፁ ነገሩን ሁሉ በክርስቲያኖች ላይ አሳበበ። በዚህም የተነሣ ክርስቲያን የተባለ ሁሉ መሰደድ፣ መሠየፍ፣ መታረድ እጣ ፈንታው ሆነ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በኒቆጵልዮን ከተማ ሲያስተምር በ፷፭ ዓ.ም. ተይዞ ወደ ወኅኒ ገባ። ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ፸፬ ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ አንገቱን ተሰይፎ በ፷፯ ዓ.ም. ሐምሌ ፭ ቀን በሰማዕትነት ዐረፈ። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ሁለት፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ዐስራ አራት መልእክታትን ጽፈዋል። የቅዱሳኑ ሐዋርያት ረድኤትና በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን። ምንጭ፦ ✔መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ሐምሌ ፭፤ ✔መጽሐፍ ቅዱስ-ሐዲስ ኪዳን፣ ✔ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ ቁጥር ፩፤ በማኅበረ ቅዱሳን

  • በቤተ  ክርስቲያን  ታሪክ  መሠረት  ቅዱስ  ጴጥሮስ  በፍልስጥኤም፣  በሶርያ፣  በጳንጦን፣  በገላትያ፣  በቀጰዶቅያ፣ በቢታንያ እና በሮሜ ሰብኳል። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በሮሜ አንድ ዓመት ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ካስተማረ በኋላ የሮሜ ክርስቲያኖች እየበዙ ከመምጣታቸውም በላይ የክርስትናው ጉዞ እስከ ሮማ ባለሥልጣናት ደረሰ። የኔሮን የቅርብ ባለሥልጣናት የሆኑት የአልቢኖስና የአግሪጳ ሚስቶች ወደ ክርስትናው ገቡ። በዚህን ጊዜ ኔሮን ንጉሠ ሮማ በቅንዓት ተነሣባቸው። ኔሮን በሮም የነገሠው በ፶፬ ዓ.ም. ነው። በመንግሥቱ መጀመሪያ ደግ ሰው ነበረ። ነገር ግን በነገሠ በዓመቱ የጨካኝነት ዐመሉ ብቅ ማለት ጀመረ እና የአባቱን ልጅ አስገደለ። በ፶፱ ዓ.ም. ደግሞ እናቱን በመርዝ ገደለ። በ፷፫ ዓ.ም. እያስተማረ ያሰደገውን መምህሩን ፣ በ፷፪ ዓ.ም. የልጅነት ሚስቱን አግታሺያን አስገደለ። ከእርስዋ በኋላ ያገባትን ሚስቱንም ፓፒያን በርግጫ ብሎ ገደላት። ኔሮን በ፷፬ ዓ.ም. እርሱ ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኘው ቤተ መንግሥቱ ተቀምጦ የሮማን ከተማ እሳት ለቀቀባት። የሮም ሕዝብ በደረሰው አደጋ እጅጉን ተቆጣ። ኔሮንም በክርስቲያኖች አመካኘ። በዚህም የተነሣ በሮማ ከተማ ሁለት ዓይነት ወሬ መናፈስ ጀመረ። የሮማ አማልክት በክርስቲያኖች ሃይማኖት ስለተቆጡ በከተማዋ እሳት አዘነቡባት የሚለው የመጀመሪያው ሲሆን ክርስቲያኖች ሆን ብለው ከተማዋን አቃጥለዋታል የሚለው ደግሞ ሁለተኛው ወሬ ነበር። የከተማው መጋየት ያበሳጨው የሮማ ሕዝብ፣ ክርስቲያን የሆነውን ሁሉ እያወጣ መግደሉን ተያያዘው። ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ሰዓት በእሥር ነበርና ተሠይፎ ዐረፈ። ይህን የሰሙት የአግቢኖስና የአግሪጳ ሚስቶች (የሮም ባለሟሎች ነበሩ) «ባይሆን አንተ ትረፍልን» ብለው በከተማዋ ግንብ በገመድ አሥረው በቅርጫት በማውረድ ቅፅረ ሮማን ለቅቆ እንዲወጣ አደረጉት። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በኦፒየም ጎዳና ጉዞውን ቀጠለ። ሮማን ለቀቀ። እያዘገመ በሸመገለ ጉልበቱ ሲጓዝ አንድ ቀይ ጐልማሳ ወደ እርሱ ሲመጣ አየ። እየቀረበ ሲመጣ ጌታችን መሆኑን ተረዳ። ወዲያው በፊቱ ተደፋና «ጌታዬ ወዴት እየተጓዝክ ነው?» አለና ጠየቀው። «ዳግም በሮም ልሰቀል» አለው። በዚህ ሰዓት ቅዱስ ጴጥሮስ አዘነና እንደገና ወደ ሮማ ተመለሰ። የኔሮን ወታደሮች እየፈለጉት ነበር። «እነሆኝ ስቀሉኝ» አለ ቅዱስ ጴጥሮስ። ያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስን ይዘው አሠሩት። ከጥቂት ቀናት በኋላም ሮማውያን የመስቀያውን እንጨት አቀረቡለት። ያን ጊዜ «እኔ እንደ ጌታዬ ልሰቀል አይገባኝም» በማለት ቁልቁል እንዲሰቅሉት ለመነ። ያለውንም አደረጉለት። ሐምሌ ፭ ቀን ፷፯ ዓ.ም. በሰማዕትነት ዐረፈ። ፪. ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ዘሩ ከዕብራዊያን፣ ከብንያም ነገድ ሲሆን የተወለደውም በጠርሴስ ከተማ ነው። ጠርሴስ በንግድዋ የታወቀች የኪልቂያ ዋና ከተማ ናት። በከተማዋ እስከ አምስት መቶ ሺህ የሚገመቱ ከየሀገሩ የተሰባሰቡ ሕዝቦች ነበሩባት። ሮማውያን በሥራቸው ለሚተዳደሩት ሕዝቦች ሮማዊ ዜግነትን ይሰጡ ስለነበር፥ የቅዱስ ጳውሎስ አባት በዜግነት ሮማዊ ነበር። ይህም ለቅዱስ ጳውሎስ ተላልፎለታል። ቅዱስ  ጳውሎስ  በ፲፭  ዓመት  ዕድሜው  ወደ  ትውልድ  ሀገሩ  በመመለስ  በኢየሩሳሌም  ከነበረው  የታወቀው የገማልያል ትምህርት ቤት ገባ። በዚያም የአይሁድን ሕግና ሥርዓት እየተማረ እስከ ፴ ዓመቱ ቆየ። ገማልያል ፈሪሳዊ ስለነበር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ተቀብሎታል። በ፴ ዓመቱ የአይሁድ ሸንጎ አካል ሆኖ ተቆጠረ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ዘመን ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ስለነበረ ሁኔታዎቹን ሁሉ ያውቃል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በአይሁድ ሸንጎ አባልነት ለሁለት ዓመታት በሠራበት ወቅት ለኦሪታዊ እምነቱ ቀናተኛ ፈሪሳዊ በመሆኑ  ክርስቲያኖችን በማናቸውም አጋጣሚ ይቃወም ነበር። እንዲያውም ሊቀዲያቆናት እስጢፋኖስን በማስተማሩ ምክንያት ተከሶ ለአይሁድ ሸንጎ በቀረበ ጊዜ የተከራከረው እርሱ ነበር። በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ሲያርፍም የወጋሪዎችን ልብስ ይጠብቅ የነበረው እርሱ ነው። በ፴፪ ዓመት እድሜው ከኢየሩሳሌም ፪፻፳፫ (ሁለት መቶ ሃያ ሦስት) ኪ.ሜ. ርቀት በስተሰሜን በኩል በምትገኘው የደማስቆ ከተማ ብዙ ክርስቲያኖች መኖራቸውን ሲሰማ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀርቦ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የሚያስችለውን የፈቃድ ደብዳቤ አገኘ። ከዚህም በኋላ ጭፍሮችን አስከትሎ ወደ ደማስቆ አመራ። ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ከተማዋ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው ነበር ከሰማይ የወረደው ብርሃን አካባቢውን ያለበሰውና «ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ?» የሚለውን ድምፅ የሰማው። ሐዋርያው ጳውሎስም «ጌታ ሆይ ማን ነህ?» ብሎ ጠየቀ። «አንተ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ። የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል» ሲል መድኃኒታችን ተናገረው። ያን ጊዜም በወደቀበት ሆኖ እየተንቀጠቀጠ «ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?» ሲል ጠየቀ። ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ወደ ደማስቆ እንዲገባ ተነገረው። (የሐዋ. ፱፥፩) የሐዋርያው ዓይኖች ለማየት አልቻሉም። እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ። ለሦስት ቀናት ያህልም እህል ሳይቀምስ ቆየ። በዚያች ዕለት እግዚአብሔር አምላክ በደማስቆ ለሚገኘው እና ሐናንያ ለተባለው አባት በራእይ ተገለጠለት። ቅዱስ ጳውሎስም  ያለበትን  አድራሻ  ነገረውና ሄዶ እንዲያጠምቀው  አዘዘው። ሐናንያ አስቀድሞ  የቅዱስ ጳውሎስን  ማንነት ያውቃል። አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት የቅዱስ ጳውሎስን ማንነት ያውቃል። አብዛኞቹ በደማስቆ የሚገኙት ክርስቲያኖች ከኢየሩሳሌም በስደት የመጡ ናቸው። ያን ስደት ያስነሣው ደግሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ የደረሰው መከራ ነው። በዚህ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ደግሞ ዋናው ተዋናይ ሐዋርያው ጳውሎስ ነበር። ይህን የሚያውቀው ሐናንያ በቅድሚያ ከእግዚአብሔር ጋር መከራከር ጀምሮ ነበር። እግዚአብሔር አያውቀው ይመስል ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ማስረዳት ጀመረ። በመጨረሻ ግን «ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእሥራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና» በማለት እግዚአብሔር ሐናንያን ላከው። ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረው በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዓረብ ሀገር መሄዱን ራሱ ተናግሮአል። (ገላ ፩፥፲፯) ለ፫ ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ። በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ። ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱና ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰበክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት። በዚህም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት። ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የገጠመው ሁለት ችግር ነበር። በቅድሚያ አይሁድ ጳውሎስን እንደሚያውቁት እና እንደለመዱት ሆኖ ስላላገኙት ሊገድሉት ተነሡ። በሌላ በኲል ደግሞ ክርስቲያኖች የቅዱስ ጳውሎስን መመለስ ሊያምኑ አልቻሉም። በመጨረሻ ግን በርናባስ ወደ ሐዋርያት ዘንድ ወስዶ የጳውሎስን መመለስ በመተረክ እንዲያምኑት አደረጋቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በድፍረት በማስተማሩ አይሁድ ስለተቃወሙት ከተማዋን ትቶ በቂሳርያ በኲል ወደ ትውልድ ሀገሩ ጠርሴስ ተመለሰ።

  • ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ: ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ የቅዱሳን ሐዋርያት ታሪክ ገድልና ሥራ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሙሉ አልሰፈረም። አርባዕቱ ወንጌላት ሐዋርያት እንዴት እንደተጠሩና እስከ ዕርገት ድረስ የነበራቸውን ሁኔታ ሲጽፉ፤ ወንጌላዊው ሉቃስ ደግሞ የሐዋርያትን ታሪክ እስከ ፷ዎቹ መጀመሪያ ያለውን ጽፏል። ከዚህ በመለስ ያለውን የሐዋርያት ታሪክ ለማወቅ ግን ዋናው ምንጩ የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት ናቸው። የሐዋርያት ደቀመዛሙርት እነ ፓፒያስ፣ ፖሊካርፐስ፣ አግናጥዮስ፣ ቀሌምንጦስ ዘሮም ወዘተ. የአባቶቻቸውን ታሪክ ጽፈው አቆይተውልናል። ከዚህ በኋላ ጊዜም  በ፪ኛውና በ፫ኛው መቶ ክፍለ  ዘመን  የተነሱት የቤተ ክርስቲያን  ታሪክ  ጸሐፍት እነ አውሳብዮስ፣ ሩፊኖስ፣ ጄሮም፣ ወዘተ. በትውፊት የተቀበሉትን መዝግበው አልፈዋል። ቅዱሳን ሐዋርያት ገድላቸው የተጻፈላቸው፣ በዓላቸው የተከበረላቸው የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ናቸው። በቤተ ክርስቲያናችን በሐምሌ ፭ ቀን በታላቅ ድምቀት በዓላቸው ከሚከበረው ሐዋርያት መካከል የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስና የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ ታሪክ እንደሚከተለው ነው። ፩. ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተሳይዳ ነው። የአባቱ ስም ዮና ይባላል። ከአምስት ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ሲሆን በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሳ ማሥገር ጀመረ። ለደቀመዛሙርነት ሲመረጥ ዕድሜው ፶፭ ዓመት እንደነበረ ይነገራ፤ ወደ ጌታችን ያመጣውም ወንድሙ እንድርያስ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ በርናባስና ወንጌላዊው ማርቆስ ቤተ ዘመድ ናቸው። የማርቆስ አባት አርስጦቡሎስና በርናባስ በእናት የሚገናኙ ወንድማማች ናቸው። ቅዱስ ጴጥሮስ ያገባው የበርናባስና የአርስጦቡሎስን እኅት ስለነበር በጋብቻ ይዛመዳሉ። ቅዱስ ጴጥሮስ ለሐዋርያነት ሲጠራ መተዳደሪያው የነበረውን መረቡንና ታንኳውን እንዲሁም አባቱን እርግፍ አድርጐ ትቶ ጌታውን የተከተለ ሐዋርያ ነው። የቅዱስ ጴጥሮስ በመጀመሪያ ስሙን ስምዖን ብላ እናቱ የጠራችው በነገዷ ስም እንደሆነ ይነገራል። በቂሳርያ ከተማ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ማን ትሉኛላችሁ?» ብሎ በጠየቀ ጊዜ «አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ» ብሎ ለአይሁድ ሊቃውንት የተሰወረውን ምሥጢረ ተዋሕዶ ገልጦ በመመስከሩ ጌታችን «አንተ ጴጥሮስ ነህ» ብሎታል ይህም በላቲን ቋንቋ ዐለት ማለት ነው፤ በአርማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል። ቅዱስ ጴጥሮስ ከአዕማድ ወይንም የምሥጢር ሐዋርያት ከእነ ዮሐንስ እና ያዕቆብ ጋር የሚቆጠር ነው። ከሐዋርያት ሁሉ ቀደም ቀደም የማለት ባሕርይ ነበረው። ጌታ በጥብርያዶስ ባሕር ላይ ሌሊት በእግሩ ሲመጣ ቢመለከት ወደ አንተ እመጣ ዘንድ እዘዘኝ በማለት ካስፈቀደ በኋላ ወደ ጌታ ለመምጣት መንገድ ጀምሮ በመሐል ቤት ጥርጣሬ ገባውና መስጠም ስለጀመረ ጌታችን «ያመንክ እንጂ ያላመንክ አትሁን» ብሎ ገስፆ ከመስጠም አድኖታል። (ማቴ ፲፬፥፳፪-፴፫) በቅፍርናሆም ጉባኤ ጌታን ምሥጢረ ቁርባንን ሲያስተምር፣ አይሁድ ስላልገባቸው ወደ ኋላ አፈገፈጉ። ከደቀ መዛሙርቱም «ብዙዎቹ ወደ ኋላ ተመለሱ» በዚህን ጊዜ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁ?» ብሎ ሐዋርያትን ጠየቃቸው። በዚህ ሰዓት «ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም የሕይወት ቃል አለህ። እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንክ እናምናለን» በማለት ሐዋርያትን ወክሎ የመለሰ እርሱ ነው። (ዮሐ ፮፥፷፮-፷፰) ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ይወድ ነበር። ፍቅሩ ግን ቅንዓት የተቀላቀለበት በመሆኑ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ የሞቱን ነገር ቀድሞ ሲነግራቸው አይሁንብህ በማለት ተከራክሯል። (ማቴ ፲፮፥፳፫) በኋላም «ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እኔ ከቶ አልሰናከልም» ብሎ በራሱ ቅንዓት ተማምኖ ተናግሮ ነበር። ጌታችን «ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ» እያለው እንኳን «ከአንተ ጋር መሞት እንኳን የሚያስፈልገኝ ቢሆን ከቶ አልክድህም» በማለት የተናገረ ሰው ነው። (ማቴ ፳፮፥፴፬) ቅዱስ ጴጥሮስ አስቀድሞ የተናገረውን ቃል ለመጠበቅ ሞክሮ ነበር። ጌታ ዛሬ «የሰው ልጅ አሳልፎ ይሰጣል» ብሎ አስተምሮአቸው ነበርና መከላከያ ይሆነኛል ብሎ ሠይፍ ደብቆ ይዞ ነበር። የሮም ጭፎሮችም ጌታን ለመያዝ ሲጠጉ የሊቀ ካህናቱን ባርያ (ማልኰስን) በሠይፍ ጆሮውን ቆረጠው። ጌታችን ግን ሞቱ በፍቃዱ ለድኅነተ ዓለም ነውና «ሠይፍህን ወደ ሰገባው» መልስ ሲል ገሠፀው። ቅዱስ ጴጥሮስ የሚታወቅበት ሌላው ትልቁ ነገር ንስሐው ነው። ጌታው የነገረው መድረሱን፣ ቃል የገባለትን አምላኩን መበደሉን እንዳወቀ ከግቢው ወጥቶ አለቀሰ። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዕድሜው ታላቅነት በሐዋርያት ዘንድ እንደ አባት ይታይ ስለነበር ጌታ በተለያቸው ጊዜ ሐዋርያቱን ሊመግብ ወደሚያውቀው ሙያ ዓሳ ወደ ማሥገሩ ተሠማራ። ጌታም አስቀድሞ የመረጠው እርሱ ነውና ቢክደው እንኳን  በንስሐ  በመመለሱ  ንስሐውን  መቀበሉን፤  ዛሬም  እንደሚወደው  ይገልጽለትም  ዘንድ  በጥብርያዶስ  ባሕር ተገለጠለት። (ዮሐ ፲፰፥፲) ሦስት ጊዜ ክዶት ነበርና ቀኖና ሰጠው። አሁን ቅዱስ ጴጥሮስ በራስ መተማመኑ እንዳላዋጣው ዐውቆአልና «ትወደኛለህን?» ተብሎ ሲጠየቅ «አንተ ታውቃለህ» ነበረ መልሱ። የራሱ ዕውቀት የት እንዳደረሰው ያውቃልና ጌታችንም ኅዳጌ በቀል (በቀልን የሚተው) ነውና ዛሬም እንደሚወደው፣ በንስሐ ተመልሶአልና ዛሬም ለእርሱ የሰጠውን ክብር እንደማያጐድልበት ሲነግረው ግልገሎቼን አሠማራ፣ ጠቦቶቼን ጠብቅ፣ በጐቼን አሠማራ» በማለት አደራውን አስረከበው። ከዚያም በሞቱ እንደምን አድርጐ እግዚአብሔርን አንደሚያከብረው ነግሮት ወደ ሰማያት ዐረገ። (ዮሐ ፳፩፥፲፭-፲፯) ቅዱስ ጴጥሮስ በአራቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ በተቀመጡት የሐዋርያት ዝርዝር ቀዳሚውን ሥፍራ ይዞ ይገኛል። ይህም፦ ፩. በሽምግልና አባትነቱ፣ ፪. ጌታ በቂሳርያ በሰጠው ቃል ኪዳን፣ ፫. የሐዋርያት አፈ ጉባዔ ሆኖ ይናገር ስለነበር፣ ፬. በጥብርያዶስ ባሕር በተሰጠው ቃል መሠረት ነው። በዚህም የተነሣ በይሁዳ ምትክ ሌላ ሐዋርያ እንዲመረጥ ሐሳብ ያቀረበ እርሱ ነበር። በበዓለ ሃምሳም ለደቀመዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸው ጊዜ ለተሰበሰቡት አይሁድ አፈ ጉባዔ ሆኖ ወንጌልን የሰበከ ፫፼ (ሦስት ሺህ) ምእመናንንም አሳምኖ የመጀመሪያዋን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በኢየሩሳሌም የመሠረተ እርሱ ነው። (የሐዋ. ፩፥፲፮-፳፫፣ ፪፥፲፬-፴) አስቀድሞ ፈሪ የነበረውና በሊቀ ካህናት ቀያፋ ግቢ ጌታውን የካደው ቅዱስ ጴጥሮስ፣ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ካገኘ በኋላ ግን በአይሁድ ሸንጐ ድውይ ፈወስክ ተብሎ በተከሰሰ ጊዜ በድፍረት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ መሰከረ። ቆርነሌዎስን በማጥመቅ ወንጌልን ለአሕዛብ አስቀድሞ የሰበከው ሐዋርያ ነው። ይህ ሐዋርያ ልዑል እግዚአብሔር ባደለው  ጸጋ ጥላው እንኳን ድውያንን ይፈውስ ነበር። የሐዋ ፭፥፲፭። በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፲፭ ላይ በ፶ ዓ.ም. አካባቢ በኢየሩሳሌም በተደረገው የሐዋርያት ሲኖዶስ ከአንጾኪያ ክርስቲያኖች ለቀረበው ጥያቄ የመጀመሪያውን መልስ የሰጠው እርሱ ነበር። ስለ ቅዱስ ጴጥሮስ መልክና ቁመና ጥንታዊያን መዛግብት እንደሚከተለው ያቀርቡታል። «ፊቱ ሰፋ ያለ ሲሆን ሪዛምና መካከለኛ ቁመት የነበረው ራሰ በራ ሰው ነው። በማናቸውም ነገር ፈጣንና ቀልጣፋ ነበር።»

  • видео или голосовое, без подписи

  • ፍቅር ሲመነምን ውጤቱ የበዙ ጥፋቶችን ማስከተል ይሆናል!! የፍቅር እጦት ቂም እና ጥላቻን ይፈጥራል። ይህ ደግሞ በኃጢአት ሐሴት ማድረግን ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ በመሰናከሉም ልብህ ሐሴት አያድርግ" ምሳ 24፥17 ሌላው የፍቅር እጦት ውጤት ቁጣ እና ክፋት ነው። እንዲህ ያለው ሁኔታ ስድብን፣ ጠብን፣ ግድያን፣ ነቀፋን፣ ማዋረድንና ስም ማጥፋት ማስፋፋትን ያስከትላል። ከዚህ በተጨማሪ የፍቅር እጦት ወይም ጉድለት ወደ ቅንዓት፣ ወደ አላዋቂነት፣ ወደ ኩራት፣ ወደ ጽናትን ማጣትና ወደ ጭካኔ ይመራል። ለእግዚአብሔር የሚሆን ፍቅርን ማጣት በብዙ ጉዳዮች ውስጥ ሊገለጥ ይችላል፤ ከእርሱም መካከል ጸሎትን፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ቤተ ክርስቲያንን መርሳት ጥቂቶቹ ናቸው። በእግዚአብሔር ፊት መቆምን ማጣት እና በእግዚአብሔር መንግሥት ፈጽሞ ሐሴት አለማድረግ ሌሎቹ ጉድለቶች ናቸው። ብጹዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ https://t.me/menfesawe12

  • 28 июн.1 1474

    "ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሣኤ የተጽናናችው፡፡ የተዋረደች ስትሆን በድንግልናሽ ቡቃያ መውጣት ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች፡፡ በዕለተ ዓርብ ከልጅሽ ቀኝ በፈሰሰው ውኃ ተጠምቃ የውግታቱን ደም ተቀብታ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሰግንሻለች። የልዑል እግዚአብሔር በግ የተባለ ልጅሽ አማኑኤል የተሞሸረባት መርዓዊ ሰማያዊ የተባለባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ https://t.me/menfesawe12

  • 24 июн.1 283115

    ቤትህ ውስጥ ከፍተህ የረሳኸው ባንቧ ቢኖርና ድንገት ሌሊት ከእንቅልፍህ ስትነቃ መሬቱ እንዳለ በውኃ ተጥለቅልቆ ብታገኝ በቅድሚያ ምን ታደርጋለህ? የፈሰሰውን ውኃ ለመጥረግ ወይስ የሚፈሰውን ቧንቧ ለመዝጋት ነው የምትቸኩለው? ቧንቧውን ሳትዘጋ መሬት ላይ ያለውን ውኃ ለማፈስ ብትሞክር ትርፉ ድካም ነው። ቀኑን ሙሉ ስትዝቅ ብትውል ቤትህ የሞላውን ውኃ አታጎድልም። እናስ? ቧንቧውን ዝጋዋ! በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ መፍትሔ በማታገኝበት ነገር ላይ ጊዜህን አታባክን። ለዚህ የሚዳርገኝ መነሻው ምክንያት ምንድን ነው? ብለህ ራስህን ጠይቅ። አእምሮህ ውስጥ የሞሉትን ክፋቶች ከመቁጠር በላይ እነዚያ ክፋቶች የገቡበትን አንድ ቀዳዳ ወይም ሽንቁር ለማወቅ ጣር። እርሱን ያወቅኸው ቀን ለችግርህ ትልቁን መፍትሔ አብረህ ታገኛለህ። ያን ቀዳዳ ከዘጋህ ወይም ምንጩን ካደረቅኸው የቀረው ቀስ እያለ ተኖ መጥፋቱ አይቀርም። ከመውደቅህ በላይ የውድቀትህ ምክንያት ያስጨንቅህ። ዲያቆን አቤል ካሳሁን https://t.me/menfesawe12

  • 21 июн.1 12253

    ቅዱስ ሚካኤል - መልአከ ምክሩ *** በቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔር ከቅዱሳን ጋር ስለሚያደርገው የምክር ጉባኤ ተጽፏል። ይህ መለኮታዊ ምክር ( the devine council) እግዚአብሔር ስለሚያደርገው እና ስለፍርዱ ከተመረጡ ቅዱሳን ጋር የሚያደርገው ነው። ይህን የሚያደርገውም ከቅዱሳንም መርጦ ላከበራቸው ያለውን ክብር ያሳይ ዘንድ ከሥልጣኑ በጸጋ እያሳተፋቸው እንጂ ከእግዚአብሔር ፍርድ እና ምክር የሚጎድል ኖሮ እነርሱ ሊሞሉለት አይደለም። የመጀመሪያው ይህን የተመረጡ ቅዱሳን ምክር የሚያሳይ ጥቅስ መዝ. 81/82 ነው፦ “እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።" ሌላኛው ደግሞ "እግዚአብሔርን በሰማይ የሚተካከለው ማን ነው? ከአማልክትስ ልጆች እግዚአብሔርን ማን ይመስለዋል? በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው፤ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው፤" የሚለው ነው። (መዝ. 89፥6-7) *** ቅዱስ ሚካኤል መልአከ ምክሩ የሚባል የመላእክት አለቃ ሆኖ የዚህ መለኮታዊ ምክር አካል ስለሆነ ነው። 'ተሾመ' የሚለው ቃል ይህን መመረጥ ይገልጣል። ከሌሎች መላእክት በተለየ በዙፋን ላይ ተቀምጦ መሳሉም ለዚሁ ነው። ድንግል ማርያምም የዚህ ማኅበር አካል ነች። ቀድሞ የክርስቶስ ምሳሌ የሆነው ሰሎሞን ለእናቱ ያለውን ክብር ይገልጥ በጎኑ ዙፋን አስቀምጦ ያማክራት ነበር። (1ኛ ነገ. 2፥19) ዳዊትም "ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" ብሎ ተናግሮላታል። (መዝ. 44/45፥9) ሐዋርያትም እንዲሁ ናቸው፤ ጌታ በ12ቱ የእሥራኤል ነገዶች ላይ ሲፈርዱ በዙፋን እንደሚቀመጡ መናገሩ የመለኮታዊው ምክር አካላት እንዳደረጋቸው ያሳያልና። (ማቴ. 19፥28) ይህንም ነቢዩ ዳንኤል ቀድሞ ተናግሮታል፦ “ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ፥ የራሱም ጠጕር እንደ ጥሩ ጥጥ ነበረ፤ ዙፋኑም የእሳት ነበልባል ነበረ፥ መንኰራኵሮቹም የሚነድድ እሳት ነበሩ።” (ዳን. 7፥9) ነቢዩ 'ዙፋኖች' ያለው እግዚአብሔር ብዙ ዙፋኖች ኑረውት ሳይሆን የተመረጡ ቅዱሳን የሚሳተፉበትን ከእግዚአብሔር ፍርድ ሲወጣ ቀድመው የሚያውቁ እና በባለሟልነት የሚማልዱ የቅዱሳን ጉባኤ ክብራቸውን ለማመልከት ነው። *** በዚህ ሁሉ ታላቁ መልአክ ሚካኤል አለ! ኦ ሚካኤል ኦ ሚካኤል! ከእግዚአብሔር የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው። ለጎስቋሎች ባሮችህ ለምንልን። አሜን።

መንፈሳዊ ህይወት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ✝ — tgindex