ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት(ዘፈጬ ማርያም)
Статистикаይህ በፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን የጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤት ይፋዊ የTelegram ገጽ ነው።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 14
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 168
- 1/48двое суток
- 192
- 1/72трое суток
- 207
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ርዕስ:-የንስሐ ቀን - የልብ ደስታ! ⛪ ሰላም ውድ ተማሪዎቻችን እንዴት ናችሁ!👋 ያለፈው የንስሐ ጊዜያችን እንዴት ደስ ይል ነበር! አሁንም በድጋሜ ነፍሳችንን የምናድስበት፣ ከጌታችን ጋር የምንታረቅበት ልዩ ቀን ደርሷል። 〇.ከ1ኛ - 4ኛ ክፍል ያላችሁ ተማሪዎች፦ እሁድ ነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የንስሐ አባቶቻችሁ ዘንድ ቀርባችሁ ንስሐ ትገባላችሁ። ንስሐ ማለት እግዚአብሔርን "ይቅር በለኝ" ብለን የምንታረቅበት ስለሆነ በፍጹም አያስፈራም፤ ይልቁንም ልባችንን በደስታ ይሞላዋል። ስለዚህ ሁላችሁም ተዘጋጅታችሁ ኑ። 〇.ለኬጂ (KG) ተማሪዎች፦ የእኛ ትንሽዬ የኬጂ ተማሪዎቻችን እናንተ ገና ትንሽ ስለ ሆናችሁ ንስሐ መግባት አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን ቅዱስ ቁርባን መቀበል ትችላላችሁ። 🙋♂ መርሐ ግብር፦ ①.ቅዳሜ፦ ነገ ስለ ንስሐ ዝግጅት ሰፋ ያለ ትምህርት እንማራለን። ②.እሁድ፦ 5:30 ላይ ከ 1ኛ - 4ኛ ክፍል ያላችሁ ተማሪዎች ንስሐ ትገባላችሁ። ( ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ!) 🙏📖✨
видео или голосовое, без подписи
ርዕስ:ጸሎተ ፍትሐት✨⛪ ሰላም ውድ ተማሪዎቻችን እንዴት አደራችሁ!👋 ◉.ንስሐ:የገባችሁ ተማሪዎቻችን በሙሉ ነገ ቅዳሜ ጠዋት ጸሎተ ፍትሐት ስለ ሚደረግላችሁ ሁላችሁም ጠዋት 2:00 ሰዓት ላይ የሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳስባለን። ከጸሎተ ፍትሐት በኋላ ደግሞ የመድኃኔዓለምን ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙን ለመቀበል ተዘጋጁ። 😇 ①.ቀን: ቅዳሜ ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ②.ሰዓት: ጠዋት 2:00 ሰዓት ላይ ③.ቦታ: የሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ ④.ዓላማ: ጸሎተ ፍትሐት እና ለቅዱስ ቁርባን መዘጋጀት ⚠️ማሳሰቢያ:- አደራ ተማሪዎቻችን አታርፍዱ በሰዓት ተገኙ።
видео или голосовое, без подписи
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! የፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ✨ 🕊️ ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት 🕊️ ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🌿 ልዩ መንፈሳዊ ሥልጠና! ርዕስ:-ሰንበት ተማሪና አገልግሎት! “እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ።” 📖 ( ፩ኛ ጴጥ ፬፥፲ ) ሰንበት ተማሪ ማለት ተማሪ ብቻ ሳይሆን፣ የተማረውን በሕይወት የሚገልጥና እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋና መክሊት ሌሎችን የሚያገለግል የክርስቶስ አገልጋይ ነው። እግዚአብሔር የሰጠኝን መክሊት ምን እያደረግኩበት ነው? 🤔 📝 በሥልጠናው የሚዳሰሱ ነጥቦች: ①.አገልግሎት ምንድነው? የሰንበት ተማሪ ድርሻና ኃላፊነት። ②.መክሊታችንን ማወቅ የተሰጠንን ጸጋ ለቤተክርስቲያን ጥቅም ማዋል። ③.የአገልጋይ ስነ-ምግባር በትሕትና፣ በፍቅርና በታማኝነት ማገልገል። ④.አገልግሎትና ፈተናዎቹ በአገልግሎት የሚገጥሙንን መሰናክሎች ማሸነፍ። ⑤.ትምህርትና አገልግሎት ዓለማዊ ትምህርታችንንና አገልግሎታችንን በሚገባ ማመጣጠን። ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🙋♂ መርሐ ግብር፦ 🗓️ ቀን፦ ቅዳሜ ነሐሴ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ከቀኑ 10:00 ሰዓት 😇 ቦታ፦ የሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ 🗣️ አሰልጣኝ፦ ዲ/ን ቃለአብ ተካ 📢 ልዩ ጥሪ! ሁላችሁም ተጋብዛችኋል! 🙏 ▪︎ይህ ሥልጠና ለሁላችንም የሚጠቅም ስለሆነ፣ ማንም እንዳይቀር ሁላችሁም በሰዓቱ ተገኝታችሁ እንድትማሩ ማሳሰብ እንወዳለን።🕊️ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን።” 📖 ነህ ፪፥፳ 🙏 እንማር፣ እንዘጋጅ፣ እናገልግል! ( የሰንበት ት/ቤቱ ትምህርት ክፍል ) 📚
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
እርሱ ያውቃል! 😇 “የሚያስጨንቅህ ነገር እውነተኛ ሊሆን ይችላል፤ ስለዚህ ስለ መጨነቅህ ራስህን አትውቀስ። ነገር ግን ጭንቀትህን ብቻህን አትሸከም። የተቻለህን በትጋት አድርግ፤ የማትችለውን ግን በእምነት ለእግዚአብሔር አስረክብ። ሁሉን መቆጣጠር አይጠበቅብህም፤ በሁሉ ውስጥ እርሱን ማመን ነው የሚጠበቅብህ። ዛሬ የምትችለውን አድርግ፤ የነገን ግን ለእግዚአብሔር ተወው። እርሱ ከአንተ በፊት ነገን ያውቃል።” ( አባ ፓይሲዮስ ዘአቶስ )🙏📖✨ ▪︎ጭንቀታችንን ሁሉ ጌታ ላይ እንጣል!
ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፣ ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ያላችሁ ተማሪዎች አርብ 10:30 ላይ ጥናት ስለሚኖር በሰዓታችሁ እንድትገኙ። ለቡሄ አገልግሎት የሚሆናችሁን ልብስ ከወዲሁ እንድታዘጋጁ።
видео или голосовое, без подписи
ይህን ያህል ቀን ጾምኩ 🙎♂ ይህን ያህል ቀን ጾምኩ አትበሉኝ፡፡ ይህን አልበላሁም ወይም ያንን አልበላሁም፣ የወይን ጠጅ አልጠጣሁም አትበሉኝ። ይልቁንስ ከግልፍተኝነት ወደ ገርነት፣ ከጭካኔ ወደ ደግነት የተሸጋገርኽ እንደሆነ አሳየኝ፡፡ በአንተ ውስጥ ጥላቻና ቂም ቢኖሩ፣ በወይን ፋንታ ውኃ ብትጠጣ ምን ይጠቅማል? ጾም ብቻውን ሰማያዊ ምንዳ አያስገኝምና፤ ትርጉም በሌለው በባዶ የጾም ሥርዓት ራስህን አታስገዛ። ( ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ) 🙏📖✨ ▪︎ጌታ ሁላችንንም ይርዳን!
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 📌ስማችሁ ከዚህ በታች የተዘረዘረ አባላት በቅዳሴ ማስተባበር አገልግሎት የተመደባችሁ በመሆኑ፣ ሁላችሁም በተመደበላችሁ ቀን የማስተባበር አገልግሎቱን እንድትሰሩ እንዲሁም ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት ቀድማችሁ እንድትገኙ በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን። 👉ማክሰኞ 1 ኤፍራታ አዳነ 2 አዳም በጋሻው 3 ቃልኪዳን አብርሃ 4 ናሆም አንዶለም 5 ቃልኪዳን ተስፋሁን 6 ቃልአብ ሳሙኤል 👉ረቡዕ 1 እድላዊት ሙሉነህ 2 ምህረት አብታሪኩ 3 ቤተልሄም ተመስገን 4 አርሴማ ሺበሺ 5 በሱፍቃድ ኩሪባቸው 6 አቤኔዘር በላቸው 👉ሀሙስ 1 ሲፓራ ግዛቸው 2 አብርሃም ተረፈ 3 ፀደይ አንሙት 4 እድሜአለም አግዴ 5 አዶናዊት ጥላሁን 6 ተአምረ ማርያም ኤልያስ 👉አርብ 1 ዲያና ጀማል 2 ጌታባለው ኩራባቸው 3 የአብስራ ተረፈ 4 አዳም በጋሻው 5 አቤኔዘር በላቸው 6 ሳሮን በቀለ 👉ቅዳሜ 1 ሀና እንዳልካቸው 2 አፀደ ማርያም አገዘ 3 ቃልአብ ሳሙኤል 4 ናሆም አንዶለም 5 ያብስራ ተረፈ 6 አብርሃም ተረፈ 👉እሁድ 1 እየሩስ ደጀኔ 2 ታአምረማርያም ኤልያስ 3 ማልዳ እሸቱ 4 ምህረተአብ ታሪኩ 5 ዳግማዊ ግደይ 6 ማዕድ እሸቱ ✨የበረከትና የሰላም ጾም ይሁንልን✨ ሥርዓትና ግንኙነት ክፍል @sereat21
видео или голосовое, без подписи
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! የፈጬ ደብረ ገነት ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን ✨ 🕊️ ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት 🕊️ ርዕስ፦ የቅድስና ሕይወትና የሰንበት ተማሪው መንፈሳዊ ጉዞ — ልዩ የመንፈሳዊ ሥልጠና መርሐ ግብር በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ! "እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።" (፩ኛ ጴጥ ፩፥፲፮) ትላንትና ቅዳሜ ነሐሴ ፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም. በሰንበት ትምህርት ቤታችን አዳራሽ ለተማሪዎቻችን የተዘጋጀው ልዩ መንፈሳዊ ሥልጠና በመንፈሳዊ ድባብ ተከናውኗል። ይህ መርሐ ግብር በሰንበት ተማሪዎች የዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ "ቅድስና" እንዴት ሊገለጥ እንደሚገባ ለማሳየትና ለተማሪዎች አቅጣጫ ለመስጠት ያለመ ነበር። 〇.ከሥልጠናው የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ 📝 ①.ቅድስና ለሁላችን፦ ቅድስና ለጥቂት ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለእያንዳንዱ የሰንበት ተማሪ የተሰጠ ተግባራዊ የሕይወት ጥሪ መሆኑን መረዳት። ②.በዘመናዊው ዓለም የቅድስና ፈተናዎች፦ በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታና በቴክኖሎጂ መካከል ሆነን ክርስቲያናዊ ማንነታችንን ጠብቀን የመኖር ጥበብ። ③.የሕዋሳት ጥበቃ፦ ለቅድስና ሕይወት መቃወስ ምክንያት የሆኑትን ዐይንን፣ ጆሮንና ልብን የመቆጣጠር መንፈሳዊ ስልቶች። ④.ተግባራዊ የቅድስና ልምምዶች፦ በዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ የጸሎት፣ የጾም እና የቃለ እግዚአብሔር ንባብ ለቅድስና ያላቸው ድርሻ። ⑤.ጓደኝነትና የሰንበት ተማሪው ማንነት፦ በቅድስና ጉዞ ላይ እንቅፋት የሚሆኑ ወዳጅነቶችን መለየትና በመልካም ጓደኝነት የመታነጽ አስፈላጊነት። ⑥.የንስሐና የሥጋ ወደሙ ሕይወት፦ ለቅድስና ጉዞ የማይተኩትና ዋነኞቹ የኃይል ምንጮቻችን። 🙌 ልዩ ምስጋና፦ ✨ ይህን ወቅታዊና ለሕይወታችን ወሳኝ የሆነ ሥልጠና ለሰጡን ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ዋና ሰብሳቢ ለመ/ር ቴዎድሮስ ዮሴፍ ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረብ እንወዳለን። ቃለ ሕይወትን ያሰማልን! ✨ መርሐ ግብሩን በመምራት ለተሳተፉት ለሰንበት ት/ቤታችን ምክትል ሰብሳቢ መ/ር ኪሩቤል ጌታነህ እና የሰንበት ትምህርት ቤቱን ጥሪ አክብራችሁ ለተገኛችሁ ተማሪዎቻችን ላሳያችሁት ንቁ ተሳትፎ ምስጋናችን የላቀ ነው። በትምህርቱ ያገኘነውን መንፈሳዊ ስንቅ ወደ ተግባር በመቀየር በቅድስና ሕይወት እንድንመላለስ አምላከ ቅዱሳን ይርዳን። 😇 ምኞታችን፦ አምላካችን እግዚአብሔር ሁላችንንም በቅድስናው ጎዳና ይምራን፤ ለሰማያዊ ክብርም ያብቃን! ''የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን።'' ( ነህ ፪፥፳ ) ቀን፦ ፫/፲፩/፳፻፲፰ ዓ.ም ( የሰንበት ት/ቤቱ ትምህርት ክፍል ) 📚
видео или голосовое, без подписи
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! የፈጬ ደብረ ገነት ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን ✨ 🕊️ ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት 🕊️ ርዕስ፦የቅድስና ሕይወትና የሰንበት ተማሪው መንፈሳዊ ጉዞ! ✨ ውድ የሰንበት ትምህርት ቤታችን ተማሪዎች፤ በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ ከእውቀት በላይ "ሕይወት" ይቀድማል። "እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ" (1ጴጥ 1፥16) የሚለውን የአምላካችንን ጥሪ መሠረት በማድረግ፣ በተኩላዎች መካከል እንደ በግ በምንኖርባት በዚህ ዓለም ውስጥ እንዴት በቅድስና መመላለስ እንደምንችል የሚያስረዳ ልዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብር አዘጋጅተናል። 🗓️ ቀን፦ ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፦ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ 😇 ቦታ፦ የሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ 🗣️ አሰልጣኝ፦ መ/ር ቴዎድሮስ ዮሴፍ ◉.የሥልጠናው ዋና ዋና ትኩረቶች፦ 😇 ①.ቅድስና ለሁላችን፦ ቅድስና ለጥቂት ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለእያንዳንዱ ሰንበት ተማሪ የተሰጠ ተግባራዊ የሕይወት ጥሪ መሆኑን መረዳት። ②.በዘመናዊው ዓለም የቅድስና ፈተናዎች፦ በትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታና በቴክኖሎጂ መካከል ሆነን ማንነታችንን ጠብቀን የመኖር ጥበብ። ③.የሕዋሳት ጥበቃ፦ ለቅድስና ሕይወት መቃወስ ምክንያት የሆኑትን ዐይንን፣ ጆሮንና ልብን የመቆጣጠር መንፈሳዊ ስልቶች። ④.ተግባራዊ የቅድስና ልምምዶች፦ በዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ የጸሎት፣ የጾም እና የቃለ እግዚአብሔር ንባብ ለቅድስና ያላቸው ድርሻ። ⑤.ጓደኝነትና የሰንበት ተማሪው ማንነት፦ በቅድስና ጉዞ ላይ እንቅፋት የሚሆኑ ወዳጅነቶችን መለየትና በመልካም ጓደኝነት የመታነጽ አስፈላጊነት። ⑥.የንስሐና የሥጋ ወደሙ ሕይወት፦ ለቅድስና ጉዞ የማይተኩትና ዋነኞቹ የኃይል ምንጮቻችን። ይህ መርሐ ግብር በቤተክርስቲያን ቅጽር የምናገኘውን ሰላም ወደ ቤታችንና ወደ ኑሯችን እንድንወስደው ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥርልናል። የቅድስና ሕይወት የደስታ ሕይወት መሆኑን የምንረዳበት ልዩ ጊዜ ስለሚሆን ሁላችሁም ተማሪዎች ተጋብዛችኋል። ''ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።'' ( ዕብ 12÷14 ) ( የሰንበት ት/ቤቱ ትምህርት ክፍል ) 📚
видео или голосовое, без подписи
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ፩.ፍልሰታ ማለት ምን ማለት ነው❓ "ፍልሰታ" የሚለው ቃል "ፈለሰ" ከሚል ከግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም "መነሳት" ወይም "ማረግ" ማለት ነው። ስለዚህ "ጾመ ፍልሰታ" ማለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሞት ተነስታ ወደ ሰማይ ያረገችበትን ጊዜ የምናስታውስበት ጾም ማለት ነው። ይህ ጾም በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ካሉት ከሰባቱ አጽዋማት ውስጥ አንዱ ሲሆን በዓመት ውስጥ የመጨረሻው ጾም ነው። ፪.ጾመ ፍልሰታን ለምን እንጾማለን 🤔 ጾመ ፍልሰታ ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 15 ድረስ እንጾማለን። ቤተክርስቲያናችን እንደምታስተምረው እመቤታችን ጥር 21 ቀን አረፈች። ሐዋርያትም ሥጋዋን ሊቀብሩ ወደ ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁዶች "ልጇ ከሞት እንደተነሳ ሁሉ እሷም ልትነሳ ነው?" በማለት ሐዋርያትን አስቸገሯቸው። በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን ሥጋ ነጥቀው ወደ ገነት ወሰዱት። ቁልፍ ቃል: ①.ሐዋርያት: የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮችና ደቀ መዛሙርት ናቸው። ②.ሱባኤ: ወደ እግዚአብሔር መጸለይና ምሕረትን መጠየቅ ነው። ፫.የሐዋርያት ሱባኤ እና የእመቤታችን ትንሣኤ 🕊️ በነሐሴ ወር ሐዋርያት ከነሐሴ 1 እስከ 14 ሱባኤ ያዙ። እግዚአብሔርም የእመቤታችንን ሥጋ መልሶላቸው በክብር ቀበሯት። ቶማስ የሚባል ሐዋርያ በዚያን ጊዜ ለስብከት ወደ ሀገረ ስብከቱ ሄዶ ስለ ነበር ቀብሩ ላይ መገኘት አልቻለም። እመቤታችን ነሐሴ 14 ቀን ከተቀበረች በኋላ በዚያው ቀን ተነሳች። ቶማስም ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ እመቤታችንን አገኛት። ቶማስ የእመቤታችንን ትንሣኤ አይቶ ሌሎች ሐዋርያት አይተው እንደሆነ ጠየቃት። እመቤታችንም ለቶማስ "አንተ ብቻ ነህ ትንሣኤዬን ያየኸው" አለችው። ምልክት እንዲሆነውም ሰበኗን ወይም መግነዟን ሰጠችው። ቶማስም ወደ ሐዋርያት ሄዶ "ስለ እመቤታችን ምን ሰማችሁ?" ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም "ሱባኤ ይዘን ሥጋዋን ተቀብረናል" አሉት። ቶማስም "እንዴት ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ብሎ ጠየቃቸው?" ። ሐዋርያትም "አትጠራጠር! ጌታችን ሲነሳ እንዳላመንክ ታውቃለህ አሁንም እንደዚያ ልትሆን ነው?" አሉት። ከዚያም ቶማስ ሐዋርያትን ይዞ ወደ መቃብሩ ሄደ። መቃብሩ ባዶ ነበር! ቶማስም "እመቤታችን ዐርጋለች! ስመጣ አግኝታኛለች። ይኸውም ምልክቱ የቀበረቻችሁበት ሰበን ነው" አላቸው። ሐዋርያትም ሰበኑን ተከፋፍለው በረከትን ተቀበሉ። ምሳሌ: ①.ሰዎች ፈተና/ችግር ሲገጥማቸው ወይም እርዳታ ሲፈልጉ ሱባኤ ይዘው ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ይችላሉ። ፬.የጾሙ ቀጣይነት በቤተክርስቲያን ⛪ በዓመቱ ሐዋርያት ተሰብስበው "ቶማስ ትንሣኤሽን አይቶ እኛ እንዴት እንቀራለን?" አሉ። ስለዚህ ከነሐሴ አንድ ጀምረው ሱባኤ ያዙ። ነሐሴ 16 ቀን የእመቤታችንን ትንሣኤ አዩ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያትን ምሳሌ በመከተል ጾሙን እንድንጾም ታስተምረናለች። 🔔 ማጠቃለያ 🔔 ①.ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችንን ትንሣኤ የምናስታውስበት ጾም ነው። ②.ሐዋርያትም ጾመው የእመቤታችንን በረከት ተቀብለዋል። ③.ሁላችንም ይህን ጾም በመጾም የእመቤታችንን በረከት እንድንቀበል ቤተክርስቲያን ታስተምረናለች። የእመቤታችን ረድኤትና በረከት ከሁላችንም ጋር ይሁን!
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! የፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን! 🕊️ ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት 🕊️ ርዕስ፦ የሀገር አቀፍና የሀገረ ስብከት የማጠቃለያ ምዘና በታላቅ ስኬት ተጠናቀቀ! ትላንትና ሐምሌ ፳፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም በሰንበት ትምህርት ቤታችን ሁለት ታላላቅ የምዘና መርሐ ግብሮች በስኬት ተከናውነዋል። የዕለቱ መርሐ ግብር ከመጀመሩ በፊት በአባታችን ጸሎትና ቡራኬ ተጀምሮ በሰላም ተጠናቋል። ①.ሀገር አቀፍ ምዘና፦ በሰንበት ትምህርት ቤታችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አምና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሀገር አቀፍ ፈተና መውሰዳቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ትላንት ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ሌሎች ተማሪዎቻችን ይህንን ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ምዘና በስኬት አጠናቀዋል። ②.የሀገረ ስብከት ምዘና፦ በተመሳሳይ ዕለት በሀገረ ስብከት ደረጃ የተዘጋጀው የማጠቃለያ ምዘና የ4ኛ፣ የ8ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን በታላቅ ስኬት አጠናቀዋል። 〇.መልእክት፦📝 ✨ ለተፈታኝ ተማሪዎቻችን፦ ፈተናውን የወሰዳችሁ ተማሪዎቻችን! ላሳያችሁት ቁርጠኝነት እና ትጋት ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። በውጤታችሁም የደረጃ ተማሪዎች ሆናችሁ እኛንም ቤተክርስቲያናችንንም እንደምታኮሩን አንጠራጠርም። የድካማችሁን ፍሬ በውጤታችሁ እንደምታዩት ተስፋ እናደርጋለን። ✨ ለተከበራችሁ መምህራን፦ ተማሪዎቻችን ለዚህ ደረጃ እንዲበቁ፣ እውቀት እንዲገበዩና በጥሩ ዝግጅት እንዲቀርቡ ላደረጋችሁት ያልተቆጠበ ጥረት፣ ለሰጣችሁት ድጋፍና ለነበራችሁ ትጋት ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን። እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን ይባርክ! 🙏 😇 ምኞታችን፦ ለተፈታኝ ተማሪዎቻችን ሁሉ የድካማችሁን ፍሬ አግኝታችሁ ለብሩህና ለመልካም ውጤት እንዲያበቃችሁ ከልብ እንመኛለን! ''የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን።'' ( ነህ ፪፥፳ ) ▪︎ቀን፦ ፳፯/፲፩/፳፻፲፰ ዓ.ም ( የሰንበት ት/ቤቱ ትምህርት ክፍል ) 📚