tgindex
ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ | Unity Gebi Gubae

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ | Unity Gebi Gubae

Статистика

በኢ.ኦ.ተ.ቤ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የዩኒቲ ግቢ ጉባኤ ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው። በግቢ ጉባኤያችን የሚከናወኑ ተግባራት፣ መረጃዎችንና መልእክቶችን ለውድ አባላቶቹ ያደርሳል። Instagram: https://www.instagram.com/unitygebigubae TikTok: https://www.tiktok.com/@unitygebigubae

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
9
Всего постов
25
Тип
открытый
Язык
am
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 155
+3 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
617
24 постов
Вовлечённость
28,6%
к подписчикам
Постов в день
1,3
всего 25
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
340
1/48двое суток
389
1/72трое суток
420

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ✨ የሕይወት ቀን - '2 ቀናት' ብቻ ቀረው ✨ 📆 አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • ✨እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✨🤗 እግዚአብሔር ቢፈቅድ የፊታችን ቅዳሜ የበዓለ ደብረታቦር ልዩ መርኃግብር ይኖረናል። በዕለቱም ጸሎት፣  ትምህርተ ወንጌል ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ፣ የኅብረት ዝማሬ እንዲሁም ልዩ ልዩ መርኃግብራት  ስለሚኖሩ ሁላችንም ተጠራርተን በመምጣት በዓሉን አብረን በድምቀት እንድናከብር ግቢ ጉባኤያችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች! 📆 ቅዳሜ ነሐሴ 9 ፤ 2018 ዓ.ም 🕰 ከቀኑ 06:00 ጀምሮ አድራሻ ፦ ቦሌ ገርጂ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ለበለጠ መረጃ ፦ 0912947576 0970038830 ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • ✨ የሕይወት ቀን - '3 ቀናት' ብቻ ቀረው ✨ 📆 አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • ✨ የሕይወት ቀን - '4 ቀናት' ብቻ ቀረው ✨ 📆 አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • ✨ የሕይወት ቀን - '6 ቀናት' ብቻ ቀረው ✨ 📆 አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • ✨ የሕይወት ቀን - '7 ቀናት' ብቻ ቀረው ✨ 📆 አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • “መልዕክተ ቅዱስ ፓትርያርክ" በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን ! በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው! ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው! በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ ©EOTC TV

  • ✨ የሕይወት ቀን - '8 ቀናት' ብቻ ቀረው ✨ 📆 አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • 6 авг.732176

    ❣ጾመ ፍልሰታ/ጾመ ማርያም/        🌺ፍልሰታ ማለት ፈለሰ፤ ተሰደደ፤ ተጓዘ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች» በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡   🌺ጾመ ፍልሰታ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የዕረፍት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እመቤታችን በዚህ ዓለም ፷፬ ዓመታትን በሕይወተ ሥጋ ከቆየች በኋላ ጌታችን የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጂ ተድላ ሥጋዋን አይወድምና ጥር ፳፩ ቀን ፵፱ ዓመተ ምሕርት አረፈች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡   🌺ታሪኩ በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው አክብረው ወደጌቴሴማኒ መካነ መቃብር ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉም ነበርና ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩ ኖረዋል፤  እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና «ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው» ብለው በምቀኝነት ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡   🌺የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ ሥጋዋ ያለበትን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እነርሱ ባለማየታቸው እመቤታችን ባረፈች በ፮ኛው ወር ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ፲፬ ቀን ድረስ ከጾሙ በኋላ በ፲፬ኛው ቀን ሥጋዋን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በጌቴሴማኒ ባለው መቃብር ቀብረውታል፡፡   🌺ከዚህ በኋላ እንደ ልጇ በ፫ኛው ቀን ተነሥታ መላእክት እየዘመሩላት ወደሰማያት ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሰ ዕርገቷን በማየቱ መላእክት «እመቤትህ እርሷ ናት፤ስገድላት» አሉት፤ እርሱም «ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፤ከደመናው ሊወድቅ ወደደ» ምክንያቱም ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ፤ ዛሬ ደግሞ የእርሷን ትንሣኤ ለማየት ብሎ ነው፡፡ እመቤታችንም «ትንሣኤየን ያየህ አንተ ነህ ሌሎቹ አላዩም» ብላ ሐዋርያት ገንዘው የቀበሩበትን የሐር ግምጃ ሰጥታ አጽናንታ ሰደደችው፡፡   🌺ቅዱስ ቶማስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ ብሎ ጠየቃቸው፤እነርሱም አግኝተው እንደቀበሯት ነገሩት፤ እርሱም ያየውን ምሥጢር በልቡ ይዞ «ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ይህ እንዴት ይሆናል?»፤ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ «ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ እንዲሉ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ» ብለው ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ «አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ» ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸው፤ እነርሱም አምነው ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡   🌺በዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን ሐዋርያት በመንፈሰዊ ቅናት ተነሳስተው «ቶማስ ትንሣኤዋን አይቶ እኛ ሳናይ እንዴት ይቀርብናል» በማለት ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀምረው በ፲፮ኛው ቀን የሐዋርያትን ሱባኤ ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ፣ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዔ ዲያቆን አድርጉ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላም ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን  ጾመ ፍልሰታ ተብሎ ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ይጾመዋል፡፡ 💛የጾሙ እና የትንሣኤዋ በረከት ተካፋይ ያድረገን፤ አሜን💛 ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • ✨ የሕይወት ቀን - '9 ቀናት' ብቻ ቀረው ✨ 📆 አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • ቅዱስ ቁርባን «ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን እያስነሳዋለሁ።» (ዮሐ. 6፥54) የተወደዳችሁ የግቢ ጉባኤያችን አባላት፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሁላችንም በጋራ የምንካፈልበት የሕብረት ቅዱስ ቁርባን ቀን ይደርሳል። ቤተክርስቲያን ከምታከናውናቸው መንፈሳዊ ምስጢራት ሁሉ በላይ የሆነው፣ «የምስጢራት ሁሉ ማጽኛ ማኅተም» በመባል የሚታወቀው ምስጢረ ቁርባን የክርስትና ሕይወታችን ማዕከል እና ከእግዚአብሔር ጋር የምንዋሐድበት ታላቅ የጸጋ ድልድይ ነው። ወደዚህ አምላካዊ ማዕድ ከመቅረባችን በፊት ምስጢሩን ዘንድ የሚከተለውን ትምህርታዊ ማብራሪያ ተጋሩት፦ 1. የምስጢረ ቁርባን ትርጉምና አምላካዊ ጥበብ «ቁርባን» የሚለው ቃል የመጣው ከሱርስትና ከግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙ «መንፈሳዊ አምኃ (ስጦታ)፣ መባዕ፣ ወይም ለአምላክ የሚቀርብ መስዋዕት» ማለት ነው። ግብጻውያን ደግሞ «ዩክሪስት» ይሉታል፤ ይህም «የምስጋና መስዋዕት» ወይም «የጌታ እራት» ማለት ነው። በብሉይ ኪዳን ሰዎች ለአምላካቸው የበግ፣ የላምና የጊደር መስዋዕት ያቀርቡ ነበር። ለምሳሌ አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ለመሰዋት በወጣ ጊዜ ይስሐቅ «የመስዋዕቱ በግ ወዴት አለ?» ብሎ ሲጠይቅ፣ አብርሃም በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ «ልጄ ሆይ የመስዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል» ብሎ ነበር (ዘፍ. 22፥7-8)። በሐዲስ ኪዳን ግን እግዚአብሔር ያዘጋጀው እውነተኛው የመስዋዕት በግ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የብሉይ መስዋዕት፦ ጊዜያዊ፣ በተደጋጋሚ የሚቀርብና እንስሳዊ ነበር። የሐዲስ ኪዳን ቁርባን፦ ከሰው ለእግዚአብሔር የቀረበ ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር ለሰው ልጅ የተሰጠ አምላካዊ ስጦታ ነው። ክርስቶስ ራሱ መስዋዕት፣ መስዋዕት አቅራቢ፣ እና መስዋዕት ተቀባይም ሆኖ አንድ ጊዜ ስለ ዓለም ሁሉ ቤዛ ሆኖ ቀርቧል። አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም እንደተናገረው፡ «ይህ ማዕድ በበግና በላም ደም እንደነበረው እንደ ቀደሙት አባቶች መስዋዕት አይደለም፤ እሳት ነው እንጂ! ፈቃዱን ለሚያደርጉ የሚያድን እሳት፣ ለዓመፀኞች ግን የሚበላ እሳት ነው።» 2. ምስጢረ ቁርባን በማን እና እንዴት ተመሠረተ? ምስጢረ ቁርባን የሰው ልጅ ፈጠራ ሳይሆን በራሱ በጌታችንና መድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረተ አምላካዊ ሥርዓት ነው። ጌታችን ለሕማማትና ለሞት ከመሰጠቱ በፊት በሐሙስ ምሽት ከደቀመዛሙርቱ ጋር በነበረው እራት ላይ፦ «እንጀራውን አንስቶ ባረከ፤ ቆርሶም ለደቀመዛሙርቱ ሰጠና 'እንካችሁ ይህ ሥጋዬ ነው' አለ። ጽዋውንም አንስቶ አመስግኖ ሰጣቸው፤ 'ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ፤ ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው' አለ።» (ማቴ. 26፥26-28) አይሁድና ደቀመዛሙርቱ በመጀመሪያ «ሥጋውን ልንበላ ይሰጠን ዘንድ እንዴት ይቻላል?» ብለው ቢጨነቁም፣ መንፈስ ቅዱስ ከወረደ በኋላ ግን የዚህን ምስጢር ሕይወት ሰጪነት ተረድተው በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሲፈጽሙት ኖረዋል። 🔔 ጥሪ ለተቀደሰ ዝግጅት በንስሐ እንታጠብ፦ ወደ ንስሐ አባታችን በመሄድ የልባችንን በደል እንናዘዝ። ፍቅርን እንልበስ፦ ከወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ያለንን ቂም አስወግደን በይቅርታ እንታረቅ። ሕይወታችንን እንመርምር፦ የጌታን ሥጋና ደም ለመቀበል ልባችንን የማንኛውም አምላካዊ ጸጋ ማደሪያ አድርገን እንዘጋጅ። ከ10 ቀን በኋላ የሚጠብቀን የሕብረት ቁርባን ከጌታችን ጋር የምንዋሐድበት፣ የዘላለም ሕይወትን የምንወርስበትና መንፈሳዊ ማንነታችን የምናድስበት ልዩ ቀናችን ነው። አሁኑኑ ልባችንን በማዘጋጀት ለዚህ ታላቅ የጸጋ ማዕድ እንዘጋጅ! ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • ✨ የሕይወት ቀን - '10 ቀናት' ቀረው ✨ 📆 አርብ ነሐሴ 8፤ 2018 ዓ.ም የኛስ ዝግጅት ምን ያህል ነው የቀረው? ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • 31 июл.1 074105

    "ሥጋዬን፡የሚበላ፡ደሜንም፡የሚጠጣ፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡አለው፥እኔም፡በመጨረሻው፡ቀን፡ አስነሣዋለኹ።ሥጋዬ፡እውነተኛ፡መብል፡ደሜም፡እውነተኛ፡መጠጥ፡ነውና።ሥጋዬን፡የሚበላ፡ደሜንም፡የሚጠጣ፡በእኔ፡ይኖራል፡እኔም፡በርሱ፡እኖራለኹ።" የዮሐንስ ወንጌል 6፥ 54-56 3ኛው የሕይወት ቀን - በኅብረት ቅዱስ ቁርባን እንቀበል ነሐሴ ፰፤ ፳፻፲፰ (8/2018) ዓ.ም ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • 29 июл.1 01545

    "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ" ማቴ 26፥41 ወርኃዊ የመሐረነ አብ ጸሎት 🤲 የእግዚአብሔር  ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን በግቢ ጉባኤያችን በወሩ የመጨረሻ አርብ የመሐረነ አብ ጸሎት እንደምናደርስ ይታወቃል። ስለሆነም የፊታችን አርብ ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 - 11፡00 በመገኘት ስለ ሀገራችን ፣ ስለ ሃይማኖታችን ፣ ስለ ማኅበራችን በኅብረት እንጸልይ ስትል ግቢ ጉባዔያችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች። ለበለጠ መረጃ፦ 0912947576 0970038830 ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

  • 28 июл.1 006107

    ✨እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✨🤗 እግዚአብሔር ቢፈቅድ የፊታችን ቅዳሜ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልዩ የጽዋ መርኃግብር ይኖረናል። በዕለቱም ጸሎት፣  ትምህርተ ወንጌል ፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ፣ የኅብረት ዝማሬ እንዲሁም ልዩ ልዩ መርኃግብራት  ስለሚኖሩ ሁላችንም ተጠራርተን በመምጣት በዓሉን አብረን እንድናከብር ግቢ ጉባኤያችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች! 📆 ቅዳሜ ሐምሌ 25 ፤ 2018 ዓ.ም 🕰 ከቀኑ 06:00 ጀምሮ አድራሻ ፦ ቦሌ ገርጂ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ለበለጠ መረጃ ፦ 0912947576 0970038830 ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ

ዩኒቲ ግቢ ጉባኤ | Unity Gebi Gubae — tgindex