ኆኅተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት
Статистикаይህ የመካኒሳ ምዕራፈ ጻድቃን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካቴድራል ኆኅተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት #ትክክለኛና_የቴሌግራም_ገጽ_ነው። ሰንበት ትምህርት ቤታችን መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ ወቅታዊ ኹኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎችን እንዲኹም ማስታወቂያዎችን በዚኽ ገጽ ለአባላቶቻችን እና ለተከታታዮቹ ያስተላልፋል፡፡ ያላችሁን ሀሳብና አስተያየት @gediK21
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 76
- 1/48двое суток
- 87
- 1/72трое суток
- 93
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን። የመምህራችን ዲ/ን ጋሻው መኳንንት ባለቤት እናት ሥርዓተ ቀብራቸው በነገው ዕለት ማለትም 02/12/18ዓ.ም በቤተል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኑ 6:00 ሰዓት የሚፈጸም ይሆናል።
የኆኅተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት ማኅበራዊ ሚዲያን ይወዳጁ፡- 📌 ቴሌግራም https://t.me/HohiteTsdeki05 📌 ፌስቡክ https://www.facebook.com/hohetesedk/ 📌 ቲክቶክ hohit_05 📌ዩቲዩብ https://youtube.com/@user-jl9tq9ey5z?si=ydDF_LTcesz8KTfd
ዜና ሀዘን የሰንበት ት/ቤታችን የቀድሞ ሊቀ መንበር የሆነው የመምህራችን ዲ/ን ጋሻው መኳንንት የባለቤቱ እናት ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ለመምህራችን እና ለመላው ቤተሰቡ መጽናናትን እንመኛለን። ሥርዓተ ቀብራቸው መቼ? የት? እና ሰዓቱን መረጃው ሲደርሰን የምናሳውቃችሁ ይሆናል። ኆኅተ ጽድቅ ሰ/ት/ቤት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! «ድንግል ሆይ፤ ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ።» — አባ ሕርያቆስ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። የተወደዳችሁ የመካኒሳ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካቴድራል አገልጋዮች፦አባቶቻችን ካህናት፣ዲያቆናት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የኆኅተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት፣ ምእመናንና ምእመናት ✨ እንኳን ለፍልሰታ ጾም በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!* ✨ 📌 የጾመ ፍልሰታ መልእክት ጾመ ፍልሰታ በእመቤታችን ቅድስት ማርያም ምልጃ ወደ እግዚአብሔር በፆምና በጸሎት በንስሐና በስግደት ፣በምጽዋት፣ በቅዱሳት ምሥጢራት ተሳትፎ የምንቀርብበት፣ ለቤተ ክርስቲያናችን፣ ለሀገራችን፣ ለማኅበረሰባችንና ለራሳችን ምሕረትና ሰላምን የምንለምንበት የተቀደሰ የሱባኤ ወቅት ነው። ስለዚህ በዚህ የፆም ወቅት ሁላችንም በንስሐ እና በጸሎት እየተጋን፣ በእመቤታችን ረድኤትና ምልጃ የእግዚአብሔርን ምሕረትና በረከት እንድናገኝ መበርታት እንዳለብን እያሳሰብን፤ መልካም የሱባኤና የጾም ወቅት እንዲሆንልዎ እንመኛለን። አምላከ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዚህ የጾም ዘመን ሁላችንንም በጸጋው ያጽናን፤ በምሕረቱ ይጎብኘን፤ በእመቤታችን ቅድስት ማርያም ምልጃም ይባርከን። አሜን! ✨ መልካም የፍልሰታ ጾም! ✨ ✨ መልካም ሱባኤ! ✨ ስብሐት ለእግዚአብሔር «ጸልዩ በእንቲአነ» ኆኅተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት
እናስታውሰው !! ጾመ ፍልሰታን በማስመልከት የተዘጋጀ የጸሎት መርሐ ግብር በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ ከምሽቱ 12 ፡ 00 ሰዓት ጀምሮ ስለሚደረግ ሁላችሁም የመርሐ ግብሩ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ። 👉ለሚያገለግል ሰው ከፍጹምነት የምታደርስ የተወደደች የተመረጠች ተልእኮ ጸሎት ናት።
የኆኅተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት ማኅበራዊ ሚዲያን ይወዳጁ፡- 📌 ቴሌግራም https://t.me/HohiteTsdeki05 📌 ፌስቡክ https://www.facebook.com/hohetesedk/ 📌 ቲክቶክ hohit_05 📌ዩቲዩብ https://youtube.com/@user-jl9tq9ey5z?si=ydDF_LTcesz8KTfd
📣 የጸሎት መርሐግብር ማስታወሻ "ሳታቋርጡ ጸልዩ።" (1ኛ ተሰሎንቄ 5፥17) ዘወትር ማክሰኞ በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ ከምሽቱ 12፡30 ጀምሮ የሚካሄደውን የጸሎት መርሐ ግብር እናስታውሳችው። ጸሎት የክርስቲያን ትንፋሽ፣ የአገልግሎት መሠረት እና የመንፈሳዊ ጥንካሬ ምንጭ ነው። ስለዚህ በአንድ ልብና በአንድ ሀሳብ በመሰብሰብ ስለ አገልግሎታችን ስለቤተክርስቲያናችን ፈጣሪን እንለምነው፤ በጸሎትም እንበርታ። 👉ለሚያገለግል ሰው ከፍጹምነት የምታደርስ የተወደደች የተመረጠች ተልእኮ ጸሎት ናት።
የኆኅተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት ማኅበራዊ ሚዲያን ይወዳጁ፡- 📌 ቴሌግራም https://t.me/HohiteTsdeki05 📌 ፌስቡክ https://www.facebook.com/hohetesedk/ 📌 ቲክቶክ hohit_05 📌ዩቲዩብ https://youtube.com/@user-jl9tq9ey5z?si=ydDF_LTcesz8KTfd
የኆኅተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት ማኅበራዊ ሚዲያን ይወዳጁ፡- 📌 ቴሌግራም https://t.me/HohiteTsdeki05 📌 ፌስቡክ https://www.facebook.com/hohetesedk/ 📌 ቲክቶክ hohit_05 📌ዩቲዩብ https://youtube.com/@user-jl9tq9ey5z?si=ydDF_LTcesz8KTfd
እናስታውሳችው !! ዘወትር ማክሰኞ የጸሎት መርሐ ግብር በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ ከምሽቱ 12 ፡ 30 ሰዓት ጀምሮ ስለሚደረግ ሁላችሁም የመርሐ ግብሩ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ። 👉ለሚያገለግል ሰው ከፍጹምነት የምታደርስ የተወደደች የተመረጠች ተልእኮ ጸሎት ናት።
ዜና ሀዘን የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው ወንድማችን አዳነ ማሞ አባት ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው ነገ 18/11/2018ዓ.ም 6:00 ሰዓት በካቴድራላችን የሚፈጸም ይሆናል። ለወንድማችን እና ለመላው ቤተሰቡ መጽናናትን እንመኛለን። ኆኅተ ጽድቅ ሰ/ት/ቤት
ዜና ሀዘን የሰንበት ት/ቤታችን መስራች አባል የሆነው የወንድማችን ወንደሰን አያሌው ወንድም ሙሉጌታ አያሌው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ 8:30 ሰዓት በካቴድራላችን የሚፈጸም ሲሆን አባላት ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ ልብሰ ስብሐት ስለሚለበስ እንድትገኙ። ለወንድማችን እና ለመላው ቤተሰቡ መጽናናትን እንመኛለን። ኆኅተ ጽድቅ ሰ/ት/ቤት
የኆኅተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት አዲሱ መተዳደሪያ ደንብና መዋቅር በጠቅላላ ጉባኤ ጸደቀ «ሁሉም ነገር በአግባብና በሥርዓት ይሁን» 1ኛ ቆሮንቶስ 14፥40 የመካኒሳ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካቴድራል ኆኅተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት አዲስ ያዘጋጀው መተዳደሪያ ደንብና መዋቅር በጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ገለጻና ውይይት ከተደረገ በኋላ በሙሉ ድምፅ ጸድቋል። መተዳደሪያ ደንቡ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ የጸደቀ ሲሆን፣ መዋቅሩም በሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ከተብራራ በኋላ ጸድቋል። አዲሱ መተዳደሪያ ደንብና መዋቅር በአዲስ በተመረጠው የሥራ አመራር ጉባኤ፣ በሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ እና ለዚህ ሥራ በተዋቀሩ አባላት በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በበርካታ ውይይቶች፣ ግምገማዎችና የማሻሻያ ሂደቶች አልፎ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቧል። ሰንበት ትምሕርት ቤታችን ስትመራበት የቆየችው መተዳደሪያ ደንብና መዋቅር መሻሻል ያስፈለገባቸው ዋና ምክንያቶች ሰኔ 2016 ዓ.ም. የጸደቀው የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት መተዳደሪያ ደንብ ጋር ለማጣጣም፣ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ዓላማና ተልዕኮ ዘመኑን በዋጀ መልኩ እንዲፈጸም ለማስቻል፣ በነባሩ ደንብ ውስጥ የነበሩ አሠራራዊ ክፍተቶችን ለማስተካከል እና በክፍላት መካከል የሚፈጠር የሥራ መደበላለቅን በማስቀረት የአስተዳደር ተጠያቂነትና የአገልግሎት ቅንጅትን ለማጠናከር መሆኑ ተገልጿል። በጉባኤው እንደተገለጸው አዲሱ መተዳደሪያ ደንብና መዋቅር የሰንበት ትምህርት ቤቱን አስተዳደራዊ ሥርዓት በማጠናከር፣ የአገልግሎት ቅንጅትን በማሻሻል እና የተልዕኮ አፈጻጸምን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ አስፈላጊ መሠረት እንደሚሆን ነው። በመጨረሻም የሰንበት ትምህርት ቤታችን ለዚህ ታሪካዊ ሥራ አስተዋፅኦ ላደረጉ የሥራ አመራር ጉባኤ፣ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ፣ በመተዳደሪያ ደንብና በመዋቅር ሥራው ለተሳተፉ አባላት እንዲሁም በጠቅላላ ጉባኤ በመሳተፍ ለተከታተሉ ሃሳብ አስተያየት ለሰጡ አባላት ሁሉ ምስጋናዋን ታቀርባላች። አዲሱ መተዳደሪያ ደንብና መዋቅር የሰንበት ትምህርት ቤቱን አገልግሎት ይበልጥ የተደራጀ፣ ውጤታማና ተጠያቂ ለማድረግ ወሳኝ መሠረት እንደሚሆን ይጠበቃል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи