tgindex
የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ

Статистика

ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው ። በዚህ ቻናል ላይ ግቢ ጉባኤውን በተመለከተ መልእክቶች፣መንፈሳዊ ጽሑፎች ፣ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎች መሰል መልእክቶች ይተላለፉበታል ፡፡ ያሏችሁን ጥያቄዎችና አስተያየት በዚህ bot ይላኩልን👉 @CommGibiGubae_bot

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 389
+3 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,07%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
654
20 постов
Вовлечённость
47,1%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
164
1/48двое суток
187
1/72трое суток
202

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✨ ነሐሴ 7 ጽንሰታ ለእግዝእትነ ማርያም ✨ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! “ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ፣ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ።” ማርያም ሆይ፣ በኃጢአት ፍትወት የተፀነሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ። በዚህች ዕለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተጸነሰች። ወላጆቿ ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና ልጅ አጥተው በቤተ እግዚአብሔር ጸሎት ይለምኑ ነበር። ሐና ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ፦ “አቤቱ ጌታዬ፣ ለዚች እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ፣ ምነው ለእኔ ልጅ ነሳኸኝ?” ብላ አለቀሰች፤ ይህን ያየ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ለ40 ቀናት ሱባኤ ያዘ። በ40ኛው ቀንም ሁለቱም ሕልም አዩ። ኢያቄም ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ነጭ ወፍ በራሱ ላይ ሲቀመጥ እንዳየ ነገራት። ሐናም ነጭ ርግብ በራሷ ላይ ወርዳ በጆሮዋ ገብታ በማህጸኗ ስትተኛ እንዳየች ነገረችው። ይህንን ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው። በዚያን ዕለት በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እየጠበቁ እስከ ሰባት ቀን ለየብቻቸው ሰነበቱ። በ7ኛው ቀን (ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ወደ እነርሱ ወርዶ፦ “ዓለም የሚድንባት፣ የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ” ብሎ ተሠወራቸው። እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። በዚህች ቀንም እመ ብርሃን ተጸነሰች። በፈቃደ እግዚአብሔር እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች። ምልጃዋና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን! አሜን። የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ  Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ሰላም ውድ የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁን? በግቢ ጉባኤያችን የሚገኘው የባች እና መርሐግብራት ማስተባበርያ ክፍል ለሚዲያ ክፍል አዳዲስ አባል ስለሚያስፈልግ፤ ማገዝ የምንችል በአቅማችን ለማገዝ፤ ካልቻልን ደግሞ ለምናውቃቸው እህት ወንድሞቻችን እንድናደርስ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScxUvrV2MkCQW37RQ7_gG-2hfuj3blyv9aJZGk-Go0oVYggUA/viewform?usp=publish-editor የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ  Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሰን/አደረሳችሁ! “ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ” ድንግል ሆይ ከተወዳጅ ልጅሽ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ ወደ እኔ ነዪ እኛን ትባርኪ ዘንድ። ፍልሰታ ምን ማለት ነው? “ፍልሰታ” ፈለሰ /ተሰደደ ከሚለው ግስ የወጣ ነው። ‹ፍልሰታ  ለማርያም› እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው  ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት፤ ከሥጋዊው ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁምና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት «የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?» ብለው በጠየቁት ጊዜ «እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት» ብሎ ነገራቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ 1 ቀን በዕለተ ሰኞ 2 ሱባዔ ያዙ፡፡ በ14ኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን ዐርፋ ነሐሴ 14 ቀን ተቀብራለች፡፡ ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሳኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ብቻ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ 16 ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ፡፡ ሁላችንም በጾሙ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን እናገኝ ዘንድ የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን! የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ  Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube

  • 5 авг.430104

    ክፍል ፪ ፡ መጾም ያለው ጥቅሞች በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተገለጸው ጾም የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት፦ - የሥጋን ምኞት ያጠፋል - የነፍስ ቍስልን ያደርቃል - ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ ያስገዛል - መላእክትን መስሎ ለመኖር ያስችላል - ልዩ ልዩ መከራን ያቃልላል - አጋንንትን ያስወጣል - ሰማያዊ ክብር እና ጸጋን ያስገኛል - በመንግሥተ ሰማያት ለመኖር የሚያስችል ምግባርን ያሠራል - ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቅርታ እና ምሕረትን ለማግኘት ይረዳል - አጋንንትና ጠላትን ድል ለማድረግ ያግዛል - ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመፈጸም ይረዳል - ከእግዚአብሔር ቍጣ ለመዳን ያስችላል - የተደበቀ ምሥጢርን ይገልጣል - ጸጥታን እና ርጋታን ያስተምራል - ከቅዱሳን በረከት ያሳትፋል - ሕይወትን ያድሳል - መንፈሳዊ ኃይልን ያሰጣል - ጥበብን ይገልጣል - ክህደት ጥርጥርን በማጥፋት እምነትን ለማጠንከር ይረዳል - ዕድሜን ያረዝማል - ትዕግሥትን ያስተምራል - በመላእክት ጠባቂነት ለመኖር ያስችላል፡፡ በጥቅሉ ጾም፣ ቍስለ ነፍስን የምትፈውስ፣ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም፣ የበጎ ምግባራት ዅሉ መጀመሪያ፣ ጸጋ እግዚአብሔርን የምታሰጥ፣ ለጽሙዳን ክብራቸው፣ ለደናግል የንጽሕና ጌጣቸው፣ የጸሎት እናት፣ የዕንባ መገኛ ምንጭ፣ አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ሥራ ዅሉ የምታነቃቃ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት /ማር ይስሐቅ አንቀጽ 4 ምዕራፍ 6/፡፡ እንደዚሁም ጾም ዕድሜን ያረዝማል፡፡ በጾም በጸሎት ተወስነው፣ ረጅም ዕድሜ የኖሩ የበርካታ አባቶቻችን ሕይወትም ለዚህ ማስረጃ ነው፡፡ ምእመናንም ጾምን ስንጾም አምላካችን ዕድሜአችንን ለንስሐ ያረዝምልናል፡፡ በጾም ወቅት መጸለይ፣ መመጽወት፣ መስገድ በጾም የምናገኘውን ዋጋ ከፍ ያደርገዋል፡፡ ‹‹ስለ ኀጢአቱ እንደሚጾም፣ እንደሚጸልይ ሰው ኹኑ›› እንዳለ ቅዱስ ያሬድ፡፡ ሁላችንም ጾሙን በደስታና በፍቅር ጾመን፣ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን እናገኝ ዘንድ፣ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ተራዳዒነት አይለየን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ  Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። እንኳን ለጾመ ፍልሰታ ለማርያም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! ጾም ምን ማለት ነው? ጥቅሞቹስ? 👉ጾም ‹‹ጾመ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ትርጕሙም መተው፣ መጠበቅ፣ መከልከል ማለት ነው፡፡  ጾም ከምግብ መከልከል ብቻ ሳይኾን ከክፉ ተግባር ዅሉ መቆጠብ ጭምር ነው፡፡ ሠለስቱ ምዕት፡- ‹‹ጾምስ በታወቀው ሰዓት፣ በታወቀው ዕለት፣ ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው›› በማለት የጾምን ትርጕም ያስረዳሉ (ፍት ነገ አንቀጽ 15)፡፡ ጾም በብሉይ ኾነ በሐዲስ ኪዳን የታወቀ፣ በነቢያት የነበረ፣ በክርስቶስ የጸና፣ በሐዋርያት የተሰበከ እና የተረጋገጠ መንፈሳዊ ሕግ፤ ፈጣሪን መለመኛ መንፈሳዊ መሣሪያ ነው፡፡  ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሳይኾን ልዑል እግዚአብሔር እና ለሰው ልጅ የተሰጠ የመጀመሪያው ትእዛዝ ነው፡፡  ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እከብር አይል ክቡር፣ እነግሥ አይል ንጉሥ፣ እጸድቅ አይል ጽድቅ የባሕርዩ የኾነ አምላክ ነው፡፡ ለእኛ አርአያ ቤዛ ሊኾነን እናንተም ብትጾሙ ብትጸልዩ አጋንንትን ድል ትነሳላችሁ ሲለን ጾምን ለመባረክ ለመቀደስ፤ በመብል ምክንያት ስተን ስለ ነበር ስለ እኛ ኀጢአት እና በደል ሲል 40 ቀንና ሌሊት ጾሟል፡፡ በጾም ጊዜያት ከመብል ብቻ ሳይሆን ከሁሉም አሰቀድሞና አስበልጦ ከኃጢያት ተግባራት መከልከል ይገባል። ዓይን ይጹም ክፉ ከማየት፣ አፍ ይጹም ክፉ ከመናገርም፣ ጆሮ ይጹም ክፉ ከመስማት፣ ልብ ይጹም ከቂም ከበቀል፣ ከጠብ ከጥላቻ፤ ሕዋሳት ሁሉ ይጹሙ። መጾም ያለውን ጥቅሞች በክፍል ፪ እናያለን... የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ  Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube

  • | የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐግብር | #SavetheDate! ሐምሌ 25፣ 2019 ዓ.ም የ2018 ዓ.ም የኮሜርስ ጊቢ ጉባኤ ተመራቂ ተማሪዎችን እንኳን ወደ ጉባኤ ኮሜርስ ተመራቂ ተማሪዎች ኅብረት አባል ሆናችሁ በማለት የቅበላ መርሐግር እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ቅዳሜ ሐምሌ 25፣ 2018 ዓ.ም መዘጋጀቱን ለመግለጽ እንወዳለን። 🤗 ሁላችንም በዕለቱ ለመገኘት ከወዲሁ ኘሮግራማችንን እናስተካክል። 📍ቦታ: ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ 🗓 ቀን: ቅዳሜ ሐምሌ 25፣ 2018 ዓ.ም የጉባኤ ኮሜርስ ተመራቂ የተማሪዎች ኅብረት

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✨ዲፓርትመንት ምርጫ ገለጻ ✨ የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ  Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube

  • Live stream finished (3 hours)

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • Accounting

  • видео или голосовое, без подписи

  • Economics

  • Economics course mapping

  • 29 июл.1 18820

    https://t.me/commercegebi?livestream=368e6f36463a84c1b1 የዲፓርትመንት ገለጻው ተጀምሯል!!

  • Live stream started

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✨ዲፓርትመንት ምርጫ ገለጻ ✨ ለ1ኛ ዓመት ተማሪዎች፤ ቀጣይ ስለምትመርጡት ዲፓርትመንት ለመወሰን ያግዛችሁ ዘንድ  ዛሬ ማታ ማለትም ረቡዕ ሐምሌ 22፤ 2018  ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ በሲንየር ተማሪዎች እና በተመረቁ ተማሪዎች የonline ገለጻ ይሰጣል። በመርሐግብሩ ላይ በመገኘታችን ምን እናተርፋለን? 📌 ስለሁሉም ዲፓርትመንቶች የተብራራ ገለጻ 📌ምክር እና ጋይዳንስ ከባለሙያ 📌ያላችሁን ጥያቄዎች ለመጠየቅ አጋጣሚውን ታገኙበታላቹ 📆 ረቡዕ ሐምሌ 22፤ 2018 ⏰ ምሽት 2:00 📍የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ ቴሌግራም ቻናል የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ  Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube

  • 28 июл.1 565833

    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✨ዲፓርትመንት ምርጫ ገለጻ ✨ ለ1ኛ ዓመት ተማሪዎች፤ ቀጣይ ስለምትመርጡት ዲፓርትመንት ለመወሰን ያግዛችሁ ዘንድ  ረቡዕ ሐምሌ 22፤ 2018  ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ በሲንየር ተማሪዎች እና በተመረቁ ተማሪዎች የonline ገለጻ ይሰጣል። በመርሐግብሩ ላይ በመገኘታችን ምን እናተርፋለን? 📌 ስለሁሉም ዲፓርትመንቶች የተብራራ ገለጻ 📌ምክር እና ጋይዳንስ ከባለሙያ 📌ያላችሁን ጥያቄዎች ለመጠየቅ አጋጣሚውን ታገኙበታላቹ 📆 ረቡዕ ሐምሌ 22፤ 2018 ⏰ ምሽት 2:00 📍የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ ቴሌግራም ቻናል የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ  Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ  በዓል በሰላም አደረሰን! ሐምሌ 19 መልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስን እና እናቱን ቅድስት እየሉጣን በፈላ ውሃ መካከል በተአምራት ያዳናቸው የከበረ ዕለት ነው። ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕፃኑም ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ። መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱንም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ከዚህም በኋላ መኰንኑ በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ልጅዋንም ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው። መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው። ያን ጊዜም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው። በረከታቸው ይደርብን አሜን የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ  Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube

  • በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✨ዝክረ ቅዱስ እስጢፋኖስ✨         📆 ቅዳሜ ሐምሌ 18፤ 2018 ዓ.ም  ⏰ ከ6:00-7:00 ⛪️ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ በመርሐግብሩ ላይ ተገኝተን ከበረከቱ እንድንሳተፍ በእመቤታችን ስም እናሳስባለን። የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ  Telegram | Instagram | Tiktok | YouTube

የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ — tgindex