tgindex
አባ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ - Abba Henok Archbishop

አባ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ - Abba Henok Archbishop

Статистика
@archbishophenokКнигианглийский

Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Archbishop of South and West Africa Diocese. Website - www.archbishophenok.org

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
07:25
Постов за неделю
1
Всего постов
26
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
970
+7 за 3 дн.
Сутки
+2
+0,21%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
526
26 постов
Вовлечённость
54,2%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 26
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
102
1/48двое суток
116
1/72трое суток
126

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን

  • видео или голосовое, без подписи

  • “ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው።” ራዕይ ፲፬፥፲፫ ከቀናት በፊት በደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም ገዳም በተከሰተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለጠበል ፣ ለሱባኤና ለመሳለም ከተለያዩ አካባቢዎች በተሰበሰቡ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችላ ላይ በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን በሀገረ ስብከታችንና በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ በሚገኙ ካህናትና ምእመናን ስም እንገልጻለን። በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጽናናትን እንዲሰጥ እየተመኘን ጉዳት ደርሶባቸው በሕክምና ላይ ለሚገኙትም አምላከ ቅዱሳን ፈውስን ይላክላቸው። ለብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ለተጎጂ ወገኖች እና ለመላው የአካባቢው ምእመናን ጽናትን ይስጥልን። ነፍሳተ ሙታንን ይማርልን ! እግዚአብሔር ያዘኑትን ያረጋጋ ! ሀገራችንንና ሕዝባችንን ይጠብቅ ! + አባ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ “Blessed are the dead who die in the Lord from now on.” Revelation 14:13 A few days ago, a sudden landslide occurred at Debre Mitmaq Tsadqane Kidist Mariam Monastery. We express our profound sorrow, on behalf of our Diocese and the clergy and faithful of South and West Africa, over the tragic accident that claimed the lives of children of the Holy Spirit who had gathered from various places for holy water, spiritual retreat (subae), and pilgrimage. As we pray that God the Holy Spirit may grant comfort to the families of those who lost their lives in this tragedy, we also pray that the God of the saints may send healing to those who were injured and are receiving medical treatment. May God grant strength to His Eminence Abune Qelemintos, Archbishop of the North Shewa Diocese, to the affected families, and to all the faithful in the surrounding area. May God have mercy on the souls of the departed. May God comfort those who mourn. May God protect our country and our people. + Abba Henok Archbishop of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church the Archdiocese of South and West Africa Diocese 6 August 2026 Johannesburg, South Africa

  • "እነሆ አምላክ መድኃኒቴ ነው ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና መድኃኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜ አልፈራም ትላለህ።" ኢሳይያስ 12:2

  • видео или голосовое, без подписи

  • "አብርሃም አቡክሙ ተመነየ ከመ ይርአይ ዕለትየ፡ ወርእየሂ ወተፈሥሐ፤አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ አየም ደስም አለው።” ዮሐ ፰፥፶፮ እንኳን ለአጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን፣ ደቡብና ምዕራብ አፍሪካን ይባርክ ! Your father Abraham rejoiced at the thought of seeing my day; he saw it and was glad.” Joh 8:56 Happy the Annual Feast of the Holy Trinity May God bless Ethiopia, South and West Africa

  • видео или голосовое, без подписи

  • አምላክነሰ ኀይልነ ወጸወንነ፤ ወረዳኢነ ውእቱ በምንዳቤነ ዘረከበነ ፈድፋደ። ​አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።” (መዝሙር 46፥1) “ ሕዝቤ ሆይ፥ ና ወደ ቤትህም ግባ፥ ደጅህን በኋላህ ዝጋ ቍጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ” ኢሳ 26:20 ከቃሉ እንደምንመለከተው የቁጣ ጊዜ እንዳለ እርሱም እንደሚያልፍ እና እኛም ልናደርገው ስለሚገባን ቅድመ ሁኔታ ያስጠነቅቀናል ስለዚህ በአሁኑ ወቅት በደቡብ አፍሪካ በተለያዩ ከተሞች በስደት ሕይወት ውስጥ ለምትገኙ ወገኖቻችን፣ ከሀገራችን እንድትወጡልን ብለው በሚጠይቁ ሰልፎችና በተፈጠሩ ወቅታዊ ውጥረቶች ምክንያት በከፍተኛ ሥጋትና ሥነ-ልቦናዊ ጫና ውስጥ እንዳላችሁ እንረዳለን። በዚህ አስቸጋሪና ፈታኝ ወቅት፣ ከሁሉ አስቀድሞ ልባችሁ በፍርሃት እንዳይናወጥና ተስፋ እንዳይቆርጥ በእግዚአብሔር ቃል እንድትጽናኑ እንወደዳለን። የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያስታውሰን፣ የሰው ኃይልና ጥበብ በሚደክምበት፣ ዙሪያችንም በባዕድ ምድር ፈታኝ በሆነ ማዕበል በሚናወጥበት ጊዜ የማይናወጥ መጠጊያችን፣ ጉልበታችንና በታላቅ መከራ ውስጥ ፈጥኖ የሚደርስ ረዳታችን እግዚአብሔር ብቻ ነው። ፈተናው የበረታ ቢመስልም፣ ከእኛ ጋር ያለው አምላክ ግን ከችግሩ ሁሉ ይበልጣል። ምንም መፍትሔ አልባ በሚመስሉ መከራዎች ብንከበብም ችግሮቻችን ከአምላካችን እጅ በታች ናቸው ስለዚህ፣ በመንፈሳዊ ጥንካሬና በጸሎት ወደ እርሱ በመጠጋት ልባችሁን እንድታጸኑ አባታዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ተወዳጅ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ! በዚህ ወቅት ከፍተኛ የሆነ የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ የሁላችንም ቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ በአባታዊ ፍቅር አደራ ልላችሁ እወድዳለሁ። ይኸውም • ​ጥንቃቄ ይጠብቅሃል ማስተዋልም ይጋርድሃል እንዳለው ቃሉ ሰልፎችና ውጥረቶች በሚበራከቱባቸው አካባቢዎችና የንግድ ማዕከላት ያለ በቂ ምክንያት ከመንቀሳቀስ እንድትጠበቁና በተለይም በምሽት ሰዓት እንቅስቃሴን ከማድረግ እንድትቆጠቡ። • ​መረጃዎችን መከታተል፦ የአካባቢውን ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና ከኤምባሲም ሆነ ከማኅበረሰብ መሪዎች የሚወጡ ይፋዊ መግለጫዎችንና ማስጠንቀቂያዎችን በንቃት መከታተል። • ​አብሮነትና ግንኙነት ፦ ከሌሎች ወገኖቻችሁና ከቅርብ ጓደኞቻችሁ ጋር ያላችሁን የመረጃ ልውውጥና ግንኙነት ማጠናከር፤ ድንገተኛ አደጋ ቢከሰት እንኳ በፍጥነት የሚደርስ የሰንሰለት መረጃዎችን ብትዘረጉ። • ​ከአነቃቂ ሁኔታዎች መራቅ፦ በማኅበራዊ ሚዲያዎችም ሆነ በአካል ከሚደረጉ አላስፈላጊ ክርክሮችና ግጭትን ሊቀሰቅሱ ከሚችሉ ሁኔታዎች ራስን ሙሉ በሙሉ በማራቅ በትዕግሥት በመከራ ቀን መሸሸጊያ የሆነውን አምላካችንና ተስፋችን እግዘብሔርን በትዕግሥት እንድትጠብቁ ያስፈልጋል። እንደሚታወቀው ወቅቱ የዘመኑ ፍጻሜ በሆኑ ኩነቶች እንደተሞላ ከሚያሳዩን ትንቢቶች መካከል “ ምናሴ ኤፍሬምን ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤” ኢሳ 9:21 እንዳለ ወንድም ወንድሙን ለሞት አሳልፎ የሚሰጥበት የሚገድልበት ጊዜ ላይ በመድረሳችን ወቅቱን እንድንጠነቀቅ ያስረዳናል እግዚአብሔር በወንድሞቻቸው ደም የሚቆምሩትን ክፋት የሚፈጽሙትን የክፋት ምክራቸውን እንደ ጉም እንዲበትን ለእነርሱም ልቡና እንዲሰጣቸው እየፀለየን በቃሉ ላይ እንደሰፈረው ጌታ የሚታመኑበትን ያውቃቸዋል ያድናቸዋልም እንዳለ እንደ ዓይኑ ብሌን የሚጠነቀቅልን አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር መከራውን አሻግሮ የፀጥታና የማረፍ ጊዜ እንዲሰጠን እመንኛለን። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን፣ ደቡብ አፍሪካንና ምዕራብ አፍሪካን ይባርክ። + አባ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

  • видео или голосовое, без подписи

  • “በርግጥ እናንተ ክብራችንም ደስታችንም ናችሁ” ፩ ተሰሎንቄ ፪፥፳ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳት፣ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ ከሚገኘው Liberty University በEducational Leadership (Doctor of Education – EdD) በከፍተኛ ማዕረግ የዶክተሬት ዲግሪዎን በማጠናቀቃቅዎ በራሳችንና በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ስም የተሰማንን ደስታ እንገልጻለን። የብፁዕነትዎ ቡራኬ አይለየን !

  • видео или голосовое, без подписи

  • “.. ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል” ሐዋ.ሥ ፩፥፲፩ እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ ! “This Jesus, who was taken up from you into heaven, will come in the same way as you saw him go into heaven." Act 1:11 Happy Feast of Ascension

  • видео или голосовое, без подписи

  • "አሠርገዋ ለኢትዮጵያ በስብሐት ወበሃሌ ሉያ ያሬድ ካህን ፀሐያ፤ ኢትዮጵያን በምስጋና ያስጌጣት (የሸለማት) የብርሃን ፀሐይ የሆነው ካህኑ ያሬድ ነው።” እንኳን ለኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ ! የቅዱስ ያሬድ ሕይወት በርካታ ችግሮች ውስጥ ለምትገኘው ዓለም እንዲሁም ለሰው ልጆች ሁሉ እጅግ አስደናቂ ትምህርትን የምናገኝበት ነው። ከብዙ መጎዳትና ከሀሳቦቻችን አለመሳካት ጋር ተያይዞ በእግዚአብሔር አምላካችን ላይ የጸና እምነትን ይዘን የምንሻገርበትን ድልድይ የምናይበት ዐይን የዚህ ሊቅ ሕይወቱ ነው። ሐዋርያው "የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።" (ዕብራውያን 10:36) እንዳለ የእግዚአብሔር ይቅርታውና መግቦቱ የሚገኘው በተስፋው ቃል በመጽናት ስለሆነ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ የሚኖረን የመጽናት መጠን የፍላጎቶቻችን ውጤቶች ላይ የራሳቸው አስተዋጽኦ አላቸው እና ይህን ማስተዋል ያስፈልጋል። ተወዳጆች ሆይ ! "ናሁ ናስተበጽዖሙ ለእለ ተዓገሡ፤ እነሆ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን" (ያዕ 5፥11) ያለው የሐዋርያው ቃል ከመጽናት የተነሳ ስለምንደርስበት የክብር ሥፍራ የሚነግረን ሲሆን ቅዱስ ያሬድም ከመጽናቱ እና በታጋሽነት የሚጠበቅበትን ከማድረጉ የተነሳ እንዴት ብሎ ወደ ብርሃናዊው የዕውቀት መንገድ እንደደረሰ ስንመለከት ዛሬ ላይ ብንወድቅ የምንነሳው፣ መንገዱ ቢጠፋን ወደ ትክክለኛው ጎዳና የሚመራን፣ ብንሰናከል የሚጠብቀን፣ ብንራቆት የሚያለብሰን፣ ዝቅ ብንል ወደ ከፍታ የሚያወጣን አምላካችን እነዚህን መታገሶቻችንን ተመልክቶ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል (ማር 13፥13)። በአጠቃላይ ከኃጢአት ቁራኝነት ለመላቀቅ ያልቻልን፣ በንስሐ ለመመላለስ የኃጢአት መሠናክል ሕይወታችንን ዳገት ያደረገብንና በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንዳንሮጥ እንቅፋት የሆነብንን ጉዳይ ሁሉ የሊቁን ሕይወት አብነት አድርገን፤ ፈተናው የክብር ሽልማት አይቀሬ መሄጃው መንገድ መሆኑን በመረዳት፣ ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ የጠቢብ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ መሆኑን አብዝተን በመገንዘብ (ምሳሌ 13:14) በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ቅዱሱን በመምሰል መኖር ጌታ እግዚአብሔርን ያስደስታል ፍጻሜያችንንም ታላቅ ያደርገዋል። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም የቅዱስ ያሬድ አማላጅነት ይጠብቀን አሜን። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን፣ ደቡብና ምዕራብ አፍሪካን ይባርክ !

  • видео или голосовое, без подписи

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ቅዱስ ተክለሃይማኖት እንኳን ለ፳፻፲፰ ዓ.ም የጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላምና በጤና አደረስዎ ቅዱስነትዎ ለረጅም ዘመናት በሰላም እና በጤና በመንበርዎ እንዲቆዩ ምኞታችን ነው። የቅዱስነትዎ ቡራኬ አይለየን ! His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of Ethiopia Archbishop of Axum and Echege of the See of Saint Teklehaimanot Happy Easter for the year 2026. May the Feast of the Resurrection of our Lord, and Savior Jesus Christ reach Your Holiness in peace and good health. Your Holiness, it is our wish that you remain on your throne for many years in peace and good health. May the blessing of Your Holiness be with us all!

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи