tgindex
ብዕረኛው

ብዕረኛው

Статистика

መረጃ ብቻ መስጠት

Последний пост
16 июн.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
1 192
+4 за 3 дн.
Сутки
+4
+0,34%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 380
19 постов
Вовлечённость
115,8%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የሸኔ ጥቃት‼️ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በዛሬው እለት ለሊት የሸኔ ታጣቂዎች በጉንደ መስቀል ጎለልቻ ገብተው አባት ከነ ልጁ ገድለዋል። 8 ሰው አቁስለው ሆስፒታል ገብተዋል፣ብዙዎች ታግተዋል የጠፉም መኖራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል። በርካታ የቀንድ ከብቶች በጥይት ተመተው ሞተዋል የተረፉትን ወስደዋቸዋል። ሰኔ 6/2018 በዚሁ ወረዳ ከአባዶ ወደ ጉንደ መስቀል ሲጓዝ የነበረ አንድ የህዝብ መኪና ሙሉ ተሳፋሪው ከነ ሹፌሩ ታግተዋል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

  • አገዛዙ “ህወሓት በፌዴራል መንግሥቱ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ወስኗል” ሲሉ፣ ህወሓትም በተመሳሳይ ትግራይ ላይ ጦርነት ሊከፈት ነው ሲል ተናገረ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የፌደራል መንግስት ገዢ ፓርቲ ብልፅግና፣ የሚያራምደው ሥርዓት በትግራይ ሕዝብ ላይ ድጋሚ ጦርነት ለመክፈት የሚያደርገውን ዝግጅት “በማታለልና በማጭበርበር ለመደበቅ እየሞከረ ነው” በማለት ኮንኖታል። ህወሓት በትናንትላው ዕለት ባወጣው መግለጫ ገዥው ፓርቲ ልዩነቶችን በኃይል ለመፍታት በማመን ቀደም ሲል በትግራይ ህዝብ ላይ ፈጽሞታል ያለውን “የጅምላ ግድያ” በሁለተኛ ዙር ለመፈፀም አሁንም የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ይገኛል ብሏል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን በኃይል የተቆጣጠረው፣ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ህጋዊ ሰውነቱ የተሰረዘው ህወሓት፣ ገዥው ፓርቲን በጦርነት ዝግጅት እና በሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ከስሷል፤ በመግለጫው፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት፣ በህወሓት ላይ ሰፊ ትችቶችን በመሰንዘር የጋራ ጽሁፋቸውን ያስነበቡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ አማካሪ ሚኒስትር እና የቀድሞው የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር  የነበሩት ጌታቸው ረዳ እና የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተሩ ሬድዋን ሁሴን “ህወሓት በፌዴራል መንግሥቱ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ወስኗል” ሲሉ መክሰሳቸው ይታወሳል። አክለዉም ​በትግራይ ክልል የፕሪቶሪያውን የዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነት የሚቃወመው የህወሓት ስብስብ፣ ስምምነቱን በይፋ በመሻር ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር ለቀጥታ ወታደራዊ ግጭት እየተዘጋጀ መሆኑን አጽዕኖት ሰጥተው ነበር፡፡ ከዚህ በተቸማሪም “ጽምዶ” የተሰኘው ጥምረት በአስመራ፣ በመቀሌ እንዲሁም በሱዳን ተደጋጋሚ ስብሰባ እያደረጉ መሆኑን በመጥቀስ ህወሓት በፌዴራል መንግሥቱ ላይ ጥቃት ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ መሆኑ መገለጹ አይዘነጋም፡፡ ይሁን እንጂ ህወሓት ሰሞነኛ በሚል ባወጣው መግለጫ፣ ይፋ ባደረገው ክስ ከፌደራል መንግስት በኩል በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉ የድሮን ድብደባዎች እና ከጫፍ እስከ ጫፍ እየተደረጉ ያሉ የወታደርና የጦር መሣሪያዎችን በማዝመት “ፉከራ ላይ ነው” በማለት ይህንንም ለጦርነት ትንኮሳው ዋነኛ ማሳያዎች ብሎ አቅርቧል። ድርጅቱ አክሎም ከዚህም በተጨማሪ በትግራይ ሕዝብ ላይ በተጣለው ከበባና ክልከላ ምክንያት በአሁኑ ወቅት የሕክምና ቁሳቁስና መሠረታዊ ሸቀጦች እጥረት መከሰቱን ገልጿል። በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ከመመለስ ይልቅ፣ ላለፉት ሦስት ወራት ይሰጣቸው የነበረው እርዳታ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን አንስቷል። በዚህ ጉዳይ ላይ ከፌደራል መንግስት በተደጋጋሚ የሚነሳ ነገር ያለ ሲሆን ይህም ህወሓት ለሰብዓዊ ረድኤት የሚላኩ ምግቦችን ለወታደራዊ ፍጆታ እየተጠቀመ ነው የሚል ነበር፡፡ “እስከ አሁን ወደ ግልጽ ጦርነት ያልተገባበት ብቸኛው ምክንያት በትግራይ በኩል ባለው ከፍተኛ ትዕግሥት በመሆኑ ነው” ያለው ድርጅቱ “ሊበሏት የፈለጓትን አሞራ ጅግራ ነሽ ይሏታል” የሚለውን አባባል በመጠቀም፣ ብልጽግና የትግራይን ህዝብ በጠብ ጫሪነት በመወንጀል ክስ ላይ ተጠምዷል ብሏል። በምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅናውን የተነፈገው ፓርቲው አክሎም በትግራይ ሕዝብ፣ በመንግሥት እና በህወሓት በኩል ያለው ጽኑ አቋም የትግራይ ሕዝብ ጥያቄዎች እና ማናቸውም ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚል ቢሆንም የብልጽግና ሥርዓት ግን ይህንን ትዕግሥት እንደ ድክመት ቆጥሮታል ብሏል። ህወሓት አሁን ላይ ወጣቶችን በማፈስ ወደ ወታደራዊ ካምፕ እንዲገቡ እያደረገ ነው በሚል የተለያዩ ተቋማትና እና መገናኛ ብዙኃን ዘገባዎች የሚያመላክቱ ሲሆን ወጣቶችም ለስደት እየተዳረጉ መሆኑ ተደጋግሞ ተዘግቧል። ለዚህ ክስ በቀጥታ ምላሽ ያልሰጠው የትናንቱ የህወሓት መግለጫ የትግራይ ሕዝብ በህልውናው ላይ ለሚሰነዘርበት ማንኛውም ጥቃት ራሱን የመከላከል ተፈጥሯዊ መብቱን በመጠቀም ህልውናውን ለማረጋገጥ ዛሬም እንደ ትናንቱ በጽናት እንደሚመክት በመግለፅ ሕዝቡ ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪ አቅርቧል። ድርጅቱ አክሎም “ዛሬም እንደ ትናንቱ የሕዝቡን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት” ለማረጋገጥ በሚደረገው ትግል ግንባር ቀደም ሆኖ በመሰለፍ “ትግሉን በድል ማጠናቀቅ” አለብን በማለት አሳስቧል ።

  • በፖለቲካዊ ሳይንስ እና በሰብአዊ መብቶች ጥናቶች ውስጥ፣ በግጭት ወይም በከፍተኛ አምባገነንነት ውስጥ የሚካሄዱ ምርጫዎች የይስሙላ ወይም የህዝብን ሞት ያወጁ ምርጫዎች ይባላሉ። ​በአንድ ሀገር ውስጥ ግጭት፣ ጭፍጨፋ ወይም ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ የሚካሄድ ምርጫን በተመለከተ የሚነሱ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦ ​የህጋዊነት ማስከበሪያ ሙከራ (Legitimization): ገዥ አካላት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ሆነ በሀገር ውስጥ ያለባቸውን የቅቡልነት (legitimacy) ጥያቄ ለመመለስ ምርጫን እንደ ሽፋን ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ይህም "የይስሙላ ምርጫ" (Sham election) በመባል ይታወቃል። ​የተቃውሞ ድምፆችን ማፈን: በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ነፃና ገለልተኛ የሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት እና ነፃ ሚዲያዎች ስለሚታገዱ ወይም ስለሚፈሩ ምርጫው ትክክለኛውን የህዝብ ፍላጎት ሊያንጸባርቅ አይችልም። ​ትርጉም ያለው ለውጥ ማጣት: ምርጫው የዴሞክራሲያዊ ሂደቶች መገለጫ ሳይሆን፣ ሥልጣን ላይ ያለው አካል የያዘውን መዋቅርና ሥልጣን ይበልጥ ለማጠናከርና ነባሩን ሁኔታ (Status quo) ለማስቀጠል የሚያደርገው ስልታዊ አካሄድ ሊሆን ይችላል። በአጠቃላይ በመንግስት ሴራ ጭፍጨፋን ለማስቀጠል የሚደረገው የይስሙላ ምርጫ ከመቼውም በላይ የአምባገነን መንግስታት ትልቁ መገለጫ ነው

  • አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር 31ኛ ክፍለጦር  ዳውንት ወረዳ ውስጥ ባሉ የአባት አርበኞች ስርዓት ወለድ ሽፍታ ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዷል! ግንቦት 20/2018 ዓ/ም በዳውንት ወረዳ የብልፅግና  ሎሌዎች ከወለጋ አምጥተው  በወረዳዋ ህዝብ ላይ ግፍን ይፈፅም የነበረ ስርዓት ወለድ ሽፍታ ላይ በአባት አርበኞች የድምሰሳ እርምጃ ተወስዷል። ስርዓት ወለዱ ሽፍታ ወለጋ ተወልዶ ያደገ ከመሆኑ አንፃር በፋኖ እርምጃ ለመውሰድ እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ ቢቆይም፤ በመጨረሻም በአባት አርበኞች እርምጃ ተወስዶበታል።በአንደኛው ግብረአበሩ ላይ እግሩን ተመቶ ተማርኳል!! የዳውንት ወረዳ የብልፅግና ሎሌዎች ይሄንን ግለሰብ ከወለጋ ያመጡት ሲሆን፤ወለጋ ሁለት አማራዎችን ከብልፅግና ተልኮ ተቀብሎ የፋኖ ስሜት አላችሁ በማለት ገሎ ወደ ዳውንት ወረዳ በብልፅግና አመራሮች በድብቅ አቀባበል ተደርጎለት የወረዳውን ህዝብ በፋኖ ስም እንዲያሰቃይ ተልዕኮ ተሰጥቶት ወደ ፀረ-ህዝብ አላማው ተሰማርቶ ከአራት የማያሱ ግብረአበሮቹን አስከትሎ በወረዳው ህዝብ ላይ፦ 1. ከአራት ግለሰብችን ገሏል! 2. ከአምስት ግለሰቦ ላይ የአካል ጉዳት አድርሷል 3. የዳውንት ወረዳ የገርሳ ጤና ጣቢያን ሁለት ጊዜ ዘረፋ ፈፅሞ ሙሉ የጤና ጣቢያ ባለሙያዎችን መሳሪያ ግባራቸው ላይ በመደቀን ስልልካቸውን ዘረፏል! 4. በወረዳው ውስጥ ከመቶ በላይ የግለሰቦችን ስልክ ነጥቆል 5. የግለሰቦችን መሳሪያ ከ17 በላይ ጨለማን ተገን አድርጎ ዘርፏል! 6. አንድ ወፍጮ በቦብ አውድሟል 7. ግለሰቦችን ከመኖሪያ ቤታቸው አፈናቅሎ ለስደት ዳርጓል! 8. የአባዋራዎችን ሚስቶችን ጋሻአግሬዎችን በመጠቀም ደፍሯል! 9. የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ስልክና ብር ዘረፋ ፈፅሟል 10. አንድ የጤና ፅፈት ቤት ሀላፊን ከስራው አፈናቅሎ አባሯል! 11. የገርሳ ትምህርት ቤት የአንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ መምህራኖች  ስልክ  በጠቅላላ ዘርፏል። በድምሩ  ከ130 በላይ ስልኮችን ዘርፏል! መዳረሻውን ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የሕልውና ተጋድሎ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 20/2016 ዓ/ም!!

  • ☑️ ቋሪት የማይነጣጠሉት መንትያ ብርጌዶች በርካታ ቁጥር ያለውን የዐቢይ ሠራዊት ደመሰሱ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት) ዐፋብኀ በጎጃም 5ኛ ክ/ጦር የማይነጣጠሉት ገረመው ወንዳውክና አረንዛው ዳሞት መንትያ ብርጌዶች ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የዐቢይ አሸባሪ ሠራዊት ደመስሰው ውለዋል። በቋሪት ወረዳ 5ኛ ቀኑን በያዘው ውጊያ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአሸባሪው ሠራዊት አባላት ሲሸኙ ብዙዎቹ ቆስለዋል። የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ዒላማውን የጠበቀ ሞርተር ወርውሮ በጠላት አባላትና አመራሮች እንዲሁም በተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ሲያደርስ፤ ባለታሪኩ አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ከገረመው ወንድውክ ጋር ባደረገው ተጋድሎ ሦስት መሣሪያዎችን መማረኩ ተረጋግጧል። ዛሬ ከተደመሰሱ የአገዛዙ ታጣቂዎች መካከል በስም ያልተለየ አንድ ባንዳም እንደተሸኘ ተሰምቷል። አሸባሪዉና መዝባሪው ዙፋን ጠባቂ ቡድን በበኩሉ የበቀል በትሩን በንፁሃን ሀብትና ንብረት እንዲሁም በእንስሳት ላይ አሳርፏል። አንድ በሬ፣ አንድ በግና አንድ የመኖሪያ ቤት በአገዛዙ ሠራዊት ጉዳት አስተናግደዋል። ይህ ጨፍጫፊ ሠራዊት በቤቱ የነበረን አንድ አርሶ አደር ተኩሶ አቁስሏል። ምንጊዜም የማይለያዩት ሁለቱ ወንድማማች ብርጌዶች  ጠላትን በመረጥው የቃብር ቦታ እየቀበሩት ነው። ዝርዝር የተደመሰሰ እና የምርኮ መረጃዎችን ውጊያ እንዳጠናቀቅን ይዘን እንመለሳለን። በመጨረሻም አንጋፋው ብርጌድ አረንዛው ዳሞት ከገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ጋር ተጣምሮ በቋሪት ወረዳ ላስመዘገበው ድል ከገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ምስጋና ተችሮታል።

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ✍️ሰሞኑን ከየክልሉ ወደ ጎጃም የገባው የአብይ አህመድ ገዳይ ቡድን በየአቅጣጫው መግባት እንጅ መውጣት አልቻለም‼️ በ2ኛ (ተፈራ ዳምጤ)ክ/ጦር ብቻ ከአምስት በላይ ክ/ጦር አሰማርቷል ። በደጋ ዳሞት ፣በሞጣ መብረቁ ተፈራ፣በጎንጅ ዮሐንስ አለማየሁ፣በድጎና በሰዴ በሁሉም አቅጣጫ የፋኖን ኃይል መቋቋም ሲከብደው በንፁሐንና በተቋማት  ንብረት ላይ እልኩን እየተወጣ ይገኛል ።    እንግዲህ ለህዝብ ሰላም ማስከበር ወጣሁ እያለ የሚዘምረው የብልፅግና መንግስት ከገባበት ቀን እስካሁን ያለ የሌለ ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍ ንፁሐንን፣ተቋማትን ፣እንስሳትን አየዘረፈና እያወደመ ይገኛል ።  አለሙ መለሰ ብርሐን የ2ኛ(ተፈራ ዳምጤ )ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት 25/10/2017 ዓ.ም

  • ጠቅላዩ 😃ማነው? ጠንቋዩ ነገ የ2017 ዓ.ም የመንግስት አፈፃፅምን አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ ይሰጣል....ሆሆ የትኛው ጥቁር ቀለም ነጭ ነው ተብሎ ይወራ ይሆን 😃😃 የሚጠበቅ ነው!!

  • በአዲስ መልክ በአዲስ አበባ ጅምላ ስር እና አፈናው ተጠናክሮ ቀጥሏል‼️ ለአማራውያን የምድር ሲኦል ሁና የቀጠለችው የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ የአማራ ተወላጆችን ዛሬም እንደትላንቱ ለአስፈሪው ዘንዶ እየቀለበች ትገኛለች። በጋራ እሴቶች ላይ የእኩል ተጠቃሚነት የማይታይባት ኢትዮጵያ ከሌሎች ብሔርብሔረሰቦች ጋር በጋራ በመሆን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ያላንዳች ልዩነት የሰራትን የአማራን ህዝብ ካገለለች ሰነባብታለች። ማግለልም ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ ውስጥ ሐሰተኛ ትርክትን መሠረት በማድረግ የአማራን ህዝብ በጠላትነት በመፈረጅ በተገኘበት እንዲገደል እንዲጨፈጨፍ ፣እንዲሁም እንዲታፈን እንዲታሰር የሚል አዋጅ ታውጆበት መተግበር ከጀመረ አመታትን አስቆጥሯል። በእርግጥ በሀገሪቱ ውስጥ መታፈን በጅምላ መታሰር አዲስ ባይሆን ከሰሞኑ በዓልን መሰረት በማድረግ በአዲስ ዙር በአዲስ አበባ ከተማ የአማራ ተወላጆች ላይ የሚደረገው አፈና በእጅጉ በአሰቃቂ ሁኔታ ቀጥሏል። በአዲስ አበባ የሚኖር ማንኛውም የአማራ ተወላጅ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልክታችን ነው። ጥላቻ ይውደም አማራነት ይለምልም!!

  • የውሻ ሞተ ወይስ የአርቲስት ግራ ያጋባል...ብቻ ውሻ ሙቷል🤣 ትላንት አንድን አሸባሪን ቡድን በመደገፍ የከነፍ ለሚናገረው ነገር ልከት ያጣ የተጨነገፈ ሰው ነበር። ህውሃት  የሚባል በጥላቻ የተገነባ ቡድን ከአማራ ጋር ሒሳብ አወራርዳለሁ ብሎ ሲነሳ የመጀሪያ መርህ ያደረገው ንፅሀን የአማራን ህዝብ መጨፍጨፍ ነበር ይህን አስነዋሪ ተግባር በቀዳሚነት በመደገፍ እራሱ ውሻ ሆኖ ሳለ የአማራን ህዝብ ውሻ ብሎ የተሳደበው  ዘፋኝ በኋላም በጥበብ አጠራር አርቲስት  ቀጥሎም አክቲቪስት የነበረው የውሾች ውሻ  ሰለሞን ተካልኝ የሲኦል በር ተከፍቶለት ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ጎበዝ <<ውሻ ወይስ አርቲስ ኧረ ግራ ያጋባል የሰለሞን ነገርስ>>!!🤣😂

  • የተሳካው ደም የማፍሰስ ዘመቻ!! ክቡርነትዎ ሰው በምን ሰዎችን ላስታርቅ ብሎ በሚጨነቅበት ሰዓት ምነው እርስዎ ሰውን በምን ላጣላ ፣ሀገርን በምን ላበጣበጥብ ብለው ሲጨነቁ ሲጠበቡ ይውላሉ። <<በራስ ጌጥ ይኮሩበት >> ይላሉ አበው ኢትዮጵያውያን ሲተርቱ እርስዎ ግን በአለም ላይ አምባ ገነን ከሚባሉት መሪዎች ጋር የራስዎን ማንንነት ቀይረው ከአለባብስ እስከ አረማምድ ሲያመሳስሉ ይታያሉ። ይህም አልበቃዎት ብሎ ዋሻ ውስጥ እንደተደበቀ የጣኦት ዘንዶ ማነህ ባለተራ--ማነህ ባለ ሳምንት እያሉ የሀገሬውን ህዝብ ደሙን ይጎነጫሉ። ክቡርነትዎ 2010 ዓ.ም የኢህአዴግን ካድሬዎች ሸውደው የብአዴን ነፈዞችን አፍዝዘው የአዞ እምባዎን እየረጩ ኢትዮጵያ ---ኢትዮጵያ ብለው ህዝቡንም አደንዝዘው ስልጣን ጨበጡ። ስልጣን ከያዙ በኋላ የመጀመሪያው ስራዎት የሆነው በአውሮፓም በአሜሪካም እየተዘዋወሩ ሳህን ማጠብና ሱስ ያደነዘዘውን ዲያስፖራ ተብዮውን የሰከረ ኢትዮጵያዊን በመሰብሰብ አጦዙት። ከዛም ኢህአዴግ የሚለውን የፓርቲ ስም ብልፅግና ወደሚል የሀይማኖት ይዘት ወዳለው ስም ቀየሩ። ቀጥለውም ህውሃትን ከአዲስ አበባ በማስወጣት መቀሌ እንዲመሽግ አደረጉት። በዚህም አላበቁም ለጦርነት የሚያነሳሱ ቃላትን በመጠቀም አንዱን ጨቋኝ ሌላኛውን ተጨቋኝ በማደረግ ከማቀሳሰረ በተጨማሪም እራስዎን እንደ ነፃ አውጪ አድርገው ማውራትም ሆነ ማስወራት ጀመሩ። በእርስዎ ምክንያት የተፈጠረውን የሰሜኑን ጦርነት ሰበር ዜና ብለው ኢትዮጵያውያንን በስሜት አነሳስተው የትግራይና የኢትዮጵያን ህዝብ ማባላት ከጀመሩ በኋላ ጦርነቱ ለ2ት አመታት በቆየበት ሰዓት የአማራ ሊህቃንን እንዴት ማጥፋትና ማሰር እንዳለብዎትም ካጤኑ በኋላ ማጥፋትም ማሰረም ቻሉ። አሁን ደግሞ ህውሃትን ከሁለት በመሰንጠቅ ጦርነት ለማካሄድ ዝግጅት ላይ ናቸው። አይ!?ክቡርነትዎ!

  • የአማራ ፋኖ በጎጃም የባሕርዳር ብርጌድ በዛሬው ዕለት ዝክር ሰማዕታትን አስቦ ዋለ የድርጅቱ ወታደራዊ አዛዥ አማካሪ ፋኖ ማንችሎት እሱባለው እና ሌሎች የክፍለጦሩና የብርጌዱ አመራሮች በተገኙበት መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በጭስ አባይና በባሕርዳር ዙሪያ መስዋትነት የከፈሉ ጀግኖችን ከሰማዕታት ቤተሰቦቻቸው ጋር አብረው አስበው ውለዋል።

  • Channel photo removed

  • መረጃ‼️ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ጌታቸዉ ረዳ ወደ ፌደራል ስልጣን ሊመጡ እንደሆነ ምንጮች አስታዉቀዋል ፡፡ የህውሃት አመራሮች በአቶ ጌታቸው ረዳ ምትክ ጀኔራል ታደሰ ወረደን ፕሬዝደንት አድርገው ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዲያፀድቁላቸው ነገ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተሰምቷል ፡፡ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ፕሬዝደንት የመሾም ኃላፊነት የጠቅላይ ሚንስትሩ ነው።

  • ለምንስ ግጭትን በየቀኑ እየፈጠሩ  አጀንዳ መሆን ተፈለገ....ኩብርነትዎ እስከመቼስ ወተትን ጥቁር ነው ይላሉ!! በብዙዎቹ አጠራራ የምስራቅ አፍሪካው የባህር ማዕበል ይሏቸዋል....የሀገራቸው መረጋጋት በተደጋጋሚ የሚያስጨነቃቸው የኢትዮጵያውያን ፍቅር የሚያበሳጫቸው ፖለቲካን ተንተርሰው በዘር በሀይማኖት ያናክሱታል...ማህበራዊ ህይወቱን ደግሞ መንደርና ሰፈር እንዲሁም ድንበር ለይተው ያለያዩታል። በኢትዮጵያውያን ላይ የክቡርነትዎ ግፍ በዚህም አያበቃም የከተማ የኮሊደር ልማት በሚል ሰበብ ቤቱን እያፈረሱ ያፈናቅሉታል ግማሹን ሜዳ ላይ በትነው ለአውሪ ሲዳርጉት ግማሹን ደግሞ በስደት የበረሀ ሲሳይ አድርገውታል። አይ! ክቡርነትዎ ደም ማፍሰስን ልክ  የውሀ ቧንን ከፍቶ ውሀ እንደማፍሰስያክል ለሳቸው ቀላል ነው። አደባባይ ላይ ወጥተው ነጩን ቀለም ጥቁር ነው ብለው ህዝብን የሚያሳምኑት ...ክቡርነትዎ ሳናጣራ አናስርም ይሉ ነበር..እንደግዛታቸው የማይቆጥሩትን የክልሎችን ጭፍጨፋና ጅምላ እስራትስ  በጣም ስለበዛ ትተነው የአዲስ አበባ ወጣት ያለአንዳች ጠያቂ በየማጎርያ ቤቱ ፣በየጨላማ እስር ቤቶች መታገታቸውስ ምን ?ይሆን ሚስጥሩ! የያኔው ሙሴ የአሁኑ የባህር ዘንዶ ምስራቅ አፍሪካንም የትርምስ ቀጠና ለማድረግ  ከሶማሌ ላንድ እስከ ሞቃዲሾ ከጅቡቲ እስከ ኤርትራ ድረስ ወላፈናቸውን በየቀኑ እየዘረጉ የማይፈፅሙቱን ጉራ እየረጩ ትኩረት መሆንን ተያይዘውታል አይ! ክቡርነትዎ መጨረሻዎት ምን ይሆን!?

  • የጦርነቱ ውጤት አሰከፊው ስደት‼️ ከአማራ ክልል ጦርነት ወደ አረብ ሃገራት የሚሰደደዉ ወጣት ቁጥር እየጨመረ ነው! በየዕለቱ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ አረብ ሀገራት ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ የሚጓዙ ወጣቶች በሠሜን ወሎ በርካቶች ናቸዉ ተብሏል። ምንም እንኳን በአካባቢዉ ወደ አረብ ሀገር በባህር መጓዝ ከዚህ በፊት የተለመደ ቢሆንም አሁን በአካባቢዉ ያለዉ ያልተረጋጋ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ወጣቶች ይህን መንገድ ምርጫ አድርገዋል። በህገወጥ መንገድ ተሰደው  ወደሀገራቸው ከሚመለሱት መካከል 95 በመቶው ከአማራ፣ ከትግራይ እና ከኦሮሚያ ክልል መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። ከዚህም ውስጥ ደግሞ 57 ሺህ የሚሆኑት ተመላሾች ከአማራ ክልል እንደሚሄዱ ሲሆኑ 42 ሺህ የሚጠጉት ደግሞ ከኦሮሚያ የተቀሩት 28 ሺህ ገደማው ደግሞ ከትግራይ ክልል የሄዱ መሆናቸው ተብሏል። ስደተኞቹ በሊቢያ በኩል ለመውጣት ጥረት ቢያደርጉም በህገወጥ ደላሎች ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ሲሆን ታግተው ገንዘብ የሚጠየቅባቸው በርካታ ስደተኞች መኖራቸው ታውቋል። ብዕረኛው

  • ጥብቅ መልዕክት ለባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች!! በባህር ዳር ከተማ በአማራ ፋኖ በጎጃም አንደኛ ክፍለጦር ስም በደብዳቤና በስልክ የሚጠየቁ የገንዘብ ድጋፎች እንዳሉ ክፍለጦሩ ተረድቷል። እነዚህን በዚህ ወቅት እየቀረቡ ያሉ የድጋፍ ጥያቄዎች ምናልባትም በአገዛዙ ወንበዴዎች የቀረበ ሊሆን እንደሚችልና ክፍለጦሩም የማያውቃቸው መሆኑን እየገለፀ፣ ይህንን በመረዳትም መሰል ጥያቄዎች ሲመጡ በየአካባቢው ካለው የፋኖ አደረጃጀት ማረጋገጥ እና መረጃም መስጠት እንደሚያስፈልግ ክፍለጦሩ አሳስቧል።