- Последний пост
- 6 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 96
- 1/48двое суток
- 110
- 1/72трое суток
- 118
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በክፍሉ ውስጥ ያለው እውነተኛው ብልህ ሰው ማን ነው? 🧠💡 በአንድ ክፍል ውስጥ ያለ እውነተኛው ብልህ ሰው «ብዙ የሚያውቀው» ሰው አይደለም፤ ይልቁንም «ምን እንደሚያስፈልግና ዋናው ነገር ምን እንደሆነ የሚረዳው» ሰው ነው! እውቀት (Knowledge) ማለት ዝም ብሎ መረጃዎችንና እውነታዎችን መሰብሰብ ነው—ልክ የምግብ አሰራር መመሪያን በቃል እንደመሸምደድ። ጥበብ (Wisdom) ማለት ግን «ጨው መቼ መጨመር እንዳለብህ» ማወቅ ነው! እውቀት አእምሮህን በዝርዝር መረጃዎች ሲሞላው፣ ጥበብ ግን ህይወትህንና አኗኗርህን ይቀርጻል፤ የትኞቹ ጥያቄዎች መጠየቅ እንዳለባቸው የሚያሳይህም እሱ ነው። ስለዚህ መረጃዎችን በከንቱ መሰብሰብ አቁም! በምትወስዳቸው ውሳኔዎችና ምርጫዎች ህይወትህን መፍጠር ጀምር። 🧠 የስነ-ልቦና እውነታው፡ በስነ-ልቦና ትምህርት ውስጥ ሜታኮግኒሽን (Metacognition፡ ስለ አስተሳሰብ ማሰብና መረዳት) የሚባል ከፍተኛ የእውቀት ደረጃ አለ። በአሁኑ የቴክኖሎጂ ዘመን መረጃ በየቦታው ይገኛል። አእምሮን ባልተፈለገ መረጃ መሙላት (Information Overload) ለጭንቀትና ለውሳኔ ማጣት (Decision Fatigue) ይዳርጋል። እውነተኛ ብልህነት መረጃን ማከማቸት ሳይሆን፣ አላስፈላጊውን አስወግዶ ጠቃሚውን መለየት (Filter ማድረግ) እና በጥቅም ላይ ማዋል ነው! ዋናው መልእክት፡ የእውቀትህ ልክ በሚያውቁት መረጃ ብዛት ሳይሆን በህይወትህ በምታሳየው ጥበብና ውሳኔ ይመዘናል.
Admas pinned «Alex Abreham #ከገቢው_ይልቅ_መግቢያው_በር_የከበረባቸው_ተቋሞች! (አሌክስ አብርሃም) በዚህ ሰዓት ዩኒቨርስቲ ከመግባት ይልቅ የዩኒቨርስቲ መግቢያ በሮችን መጎብኘት የተሻለ ደስታ ሳይሰጥ አይቀርም ! ታዝባችኋል ግን …ከዩኒቨርስቲዎቻችን የቀረን ብቸኛ የሚያምር ነገር የመግቢያ በሮቻቸው ውበት ብቻ ሁኗልኮ! ሁላችንም ተረባርበን ይሄን አስነዋሪ ድርጊትና አልቂት ባጭሩ ካልተገታ እነዚህ የወጣትነታችን…»
Admas pinned «Alex Abreham አይኔን በሌላ ሰው አይን ሳየው! (አሌክስ አብርሃም) #ፍቅረኛየ_በየቀኑ_እንዲህ_ትለኛለች “ አብርሽ ‹የ› ” በቃ ‹ የ› ከጨመረች ጥያቄዋ ምን እንደሆነ አውቀዋለሁ …ቢሆንም እንደአዲስ ነገር ለመስማት “ወይየ” እላለሁ “በናትህ ልጅ እንውለድ ” የሄው አላልኳችሁም ..አቤት ልጅ ስትወድ ! “የኔ ማር ልጅ ምን ይሰራልሻል ?” “ልጅ እኮ በቃ…ምን ልበልህ …በቃ …..” ቃል ያጥራታል…»
Admas pinned «Alex Abreham #ባንዲራ_ብትለብስም_አንድ_ዜጋ_እንጅ_ሀገር_አትሆንም !! (አሌክስ አብርሃም) አሁን ባለው ሁኔታ ያስቸገረን ነገር የአገርም ይሁን የክልል ባንዲራ ለብሶ የፈለገውን ሲሰራና ሲናገር ሲያጋጭና ሲያባላ ይውልና ነካ ሲደረግ ‹‹ኡኡ አገር ተነካ›› የሚሉት ነገር ! ባንዲራ መልበስ ከማንኛውም አይነት የህግ ተጠያቂነት አያድንም !! እንኳን መልበስ ቆዳህ ጋር አብረህ ብታሰፋው አንድ ዜጋ እንጅ…»
Admas pinned «Alex Abreham #ማንበብ_ሙሉ_ወሬኛ_ደርጋል? (አሌክስ አብርሃም) ከአገራችን ‹‹አንባቢዎች›› የተረዳሁት ነገር ቢኖር ለራሳቸው የሰጡት ‹‹አንባቢ›› የሚል ማዕረግ አናታቸው ላይ ወጥ ቶ በባዶ ጉራ እና በብዙ ባዶ ተረት እንደወጠራቸው ነው …! ይሄ ጉራ ካልተነፈሰ ወደፊት የሚመጣው ትውልድ እንኳን ሊያነብ መፅሃፍ ማየት እንኳን የሚያስጠላው ትውልድ እንደሚሆን አትጠራጠሩ ! ማንኛውም ውብ ትርክት የሚፈጠረው…»
Admas pinned «Alex Abreham ይሄ ነገር በሳምንት ሆነ እንዴ አመጣጡ ? #ለሴቶች_ብቻ!!! (አሌክስ አብርሃም) መቸም ይችን አገር የወረሯት ደም የሚያፈሉ ማስታወቂያዎች ብዛት ተቆጥሮ አያልቅም !! እንደውም ብዙሃኑ ኢትዮጲያዊ በማስታወቂያና በዜና ደሙ ከመፍላቱ ብዛት ውስጡ ቢከፈት ልብ ሳይሆን ራዲያተር ሳይገኝ አይቀርም፡) እና አንዴ ‹‹ራዲያተር ብላችሁ አድምጡኝ›› (ልብ ብላችሁ አድምጡኝ እንደማለት…»
💡የፊፋ (FIFA) የማርኬቲንግ ስትራቴጂ እግር ኳስን ከተራ ስፖርትነት ባለፈ "የዓለም አቀፍ ስሜት እና የቢሊዮን ዶላር ንግድ" ያደረገ እጅግ ግዙፍ ስትራቴጂ ነው። 🛡ፊፋ ራሱን የሚያስተዋውቀውና ገቢ የሚያመነጨው በእነዚህ 5 ዋና ዋና ስልቶች ነው፦ ⚽️ 1. ስሜትንና ብሔራዊ ኩራትን መሸጥ (Selling National Pride) ፊፋ የሚሸጠው 90 ደቂቃ ጨዋታ ብቻ ሳይሆን የአገራትን ኩራትና ፍቅር ነው። የዓለም ዋንጫን በየአራት ዓመቱ በማድረግ የጉጉት ስሜት ይፈጥራል። የስፖርቱን ስሜታዊነት በመጠቀም ዓለም አቀፍ ትኩረትን ሙሉ በሙሉ ወደራሱ ይስባል። ⚽️ 2. ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖንሰርሺፕ ጥቅሎች (Tiered Sponsorship) ፊፋ የስፖንሰርሺፕ መብቶችን በደረጃ ከፋፍሎ በውድ ዋጋ ይሸጣል፦ ⛳️ የፊፋ አጋሮች (FIFA Partners)፦ እንደ ኮካ ኮላ እና አዲዳስ ያሉ ዓመቱን ሙሉ ከፊፋ ጋር የሚሰሩና ሁሉንም መብቶች የሚቆጣጠሩ ግዙፍ ኩባንያዎች ናቸው። ⛳️ የዓለም ዋንጫ ስፖንሰሮች (World Cup Sponsors)፦ ለዋንጫው ውድድር ብቻ ከፍተኛ ክፍያ የሚከፍሉ ናቸው። ⛳️ የቀጣናው ደጋፊዎች (Regional Supporters)፦ በተወሰኑ አህጉራት ብቻ የማስተዋወቅ መብት የሚሰጣቸው ናቸው። ⚽️ 3. የብሮድካስት መብት የበላይነት (Broadcasting Monopoly) የፊፋ ትልቁ የገቢ ምንጭ (ከ45% በላይ) የጨዋታዎችን በቀጥታ የማስተላለፍ መብት ለቴሌቪዥንና ለዲጂታል ሚዲያዎች መሸጥ ነው። ይህንን መብት ለማግኘት የዓለም ትላልቅ የሚዲያ ተቋማት በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ። ⚽️ 4. ጥብቅ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ (Ambush Marketing Protection) ፊፋ የእሱን ስም፣ አርማ፣ አልፎ ተርፎም "World Cup" የሚሉ ቃላትን ያለፈቃድ መጠቀምን በጥብቅ ይከለክላል። ይህ ጥበቃ ስፖንሰር ላደረጉት ኩባንያዎች ብቻ ልዩ የበላይነት (Exclusivity) ስለሚሰጥ፣ ኩባንያዎቹ ለስፖንሰርሺፕ የሚያወጡትን ዋጋ እጅግ ከፍ ያደርገዋል። ⚽️ 5. አሳታፊ የደጋፊዎች ቀጠና (Fan Zones & Experiential Marketing) በአካል ወደ ስታዲየም መግባት ለማይችሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደጋፊዎች "Fan Festival" የተባሉ ትላልቅ የስክሪን መመልከቻ ቦታዎችን ከተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ጋር ያዘጋጃል። ይህም ደጋፊዎች ከብራንዶቹ ጋር በቀጥታ እንዲገናኙና የውድድሩ አካል እንዲሆኑ ያደርጋል። #FIFA © ሳይንስኛ
ከራሴ የማልወደው አንድ ነገር ቢኖር አስራ ስድስት አመት ዘግይቼ መፈጠሬን ነው። በቻልኩት አቅም ላስተካክለው እሞክራለሁ። ጂንስ አልለብስም። ካኪ ሱሪ በወፍራም ሹራብ ለብሼ ጥግ ላይ እቀመጣለሁ። የዘወትር ፀሎቴ ሌላ አይደለም። "እባክህ ጌታዬ እኩያዋ አርገኝና አግብቻት ከዚህ መርዛማ ህዝብ ነጥቄ ወደ ሸዋ ልውሰዳት!!" ነው። በዚህ አመት ነው ከባለቤቷ እና ከሁለት ልጆቿ ጋር እኛ ወደምንኖርበት አከባቢ የመጡት። መልኳ፣ ፀባዩዋ እና አለባበሷ አንድ አይነት የሆነላት ሴት የማውቀው እሷን ነው። እንዲሁ ቀልብን የሚሰልብ ርግት ያለ ድባብ አላት። መንገድ ላይ ስታልፍ አባውራው ሁላ ምናምኑን በጋቢው እየሸፈነ ነው የሚያያት። ራሷን ልታጠፋ ሞክራ ከተረፈች ቡኃላ ግን ሁሉም አገለላት። እነማዬም እሷን ቡና መጥራት አቆሙ። ባሏም "ራሷን ብታጠፋ የለሁበትም" ለማለት ነው መሰል እየዞረ ስላለባት ችግር ሲያወራ ነው የሚውለው። «ምንድን ነው እንዲህ አይነት ቅብጠት? ማንም ሴት ትዳሯ በምትፈልገው መንገድ ላይሔድላት ይችላል! ራስን ለማጥፋት መሞከር ግን ትኩረት ፈላጊነት ነው።» ትላለች እማዬ ስለሷ ሲነሳ። እንዳለ ቡና ጠጭው በስምምነት ራሱን ይነቀንቃል። እኔጋ ስለምንቀራረብ እንድታብራራልኝ የማላደርገው ጥረት የለም። «ለምንድን ነው ግን ሁሉም የሚጠሉሽ?» «ምንድን ነው እንዲህ ያስከፋሽ?» እላታለሁ። የሷ መልስ ሁሌም አንድ ነው። «ወፍ ረግማኝ!» ትለኛለች እየሳቀች። መመለስ እንዳልፈለገች ይገባኝና እተወዋለሁ። የመጣች ሰሞን ከሷ የያዘኝ የአይን ፍቅር በሽተኛ አድርጎኝ ነበር። አልበላም፣ አልጠጣም፣ አልተኛም። ትክክለኛ የዘፈን ግጥሞች ላይ ያለው ፍቅር ነበር የያዘኝ። ፍቅር አያስበላ አያስጠጣ የሚለው ያፈቀርከውን ሰው ማግኘት እንደማትችል እያወቅክ ስታፈቅረው ሳይሆን አይቀርም። በመጨረሻ ግን ተሸነፍኩ። ቀጥ ብዬ ቤቷ ገባሁ። በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ለወፎች ጥሬ እየመገበች ነበር። ደንግጣ ዙራ አየችኝ። ተጠግቼ ሰላም እንኳን ሳልላት «ዘርዬ እወድሻለሁ» አልኳት። ቀልዴን መስሏት ነበር። እንባዬን ስታይ ከሳቋ ላይ ግርምት ጨመረችበት። «ና እስኪ ተቀመጥ የኔ ቆንጆ!» አለችኝ! እንባዬን እየጠረግኩ ተቀመጥኩ። «ስንት አመትህ ነው?» «አስራ ስድስት» «ታውቃለሀ? እኔ ራሱኮ በጣም ነው የምወድህ!» «እውነት?» «የምሬን ነው። ይሔ ልጅ ልጄ በሆነ ብዬ እመኝ ነበር።» ኧረ ቅስሜን! «ትምህርት እንደወጣህ የቤት ስራ ምናምን ካለብህ እኔጋ እየመጣህ ስራ እሺ! ጓደኛ ትሆነኛለህ።» ከዛ ጊዜ ጀምሮ ጓደኞቼን ዞር ብዬ አይቻቸው አላውቅም። የነሱ ጭንቀት "የምወዳት ልጅ እንደወንድሜ ነው የማይህ" አለችኝ ነው። የኔ ጭንቀት "የምወዳት ልጅ እንደልጄ ነው የማይህ" አለችኝ...እኩያቸውን ይፈልጉ። ትምህርት ቤት ራሱ የምሔደው የቤት ስራ ለመቀበል ነው። እንደመጣሁ እነማዬ ሳያዩኝ ተደብቄ ዘሪቱጋ እሔዳለሁ። ስራ ጨርሳ ወደ በረንዳው ስትመጣ ከአጠገቧ ሂጄ እቀመጣለሁ። ባሏ እንደልጅ ነው የሚያዬኝ መሰለኝ ሲያዘኝ ራሱ ሰላም ሳይለኝ ነው። እኔም ለነገሩ ለሱ ሰላምታ ግድ ኑሮኝ አያውቅም። «እንዴት ግን ይሔን ሰው አገባሽው?» አልኳት የሆነ ቀን። ምንም ብጠይቃት አትደነግጥም። ርጋታዋ ሳይናድ ትመልስልኛለች። «የህልም ሽንት ታውቃለህ?» አለችኝ። በቃ እኔ ለሷ ሁሌም ህፃን ነኝ። «ኧረ አላውቅም» አልኩ አልጋ ላይ ሸንቼ ማወቄን እንዳታውቅብኝ። «ሽንት ቤት ሂደህ በስነስርዓት ልብስህን አውልቀህ ትሸናለህ...ስትነቃ ግን አልጋህ ላይ ነው የሸናኸው።» «እእእእ» አልኩ! «እንደዛ ነው የኔ ፍቅር። በኔ ቤት ሁሉን ነገር በጥንቃቄ መርጨ ጨርሻለሁ። ስባንን ያልሆነ ቦታ ላይ ነው ልቤን የጣልኩት» አሁን አሁን በአጠገቤ ሲያልፍ በሆዴ "አንተ የህልም ሽንት" እለውና ለራሴ እስቃለሁ። ዘርዬ እንደነገረችኝ ከሆነ አዲሳባ እያሉ ለመፅሔቶች አንዳንድ ፅሁፎችን ትሰራ ነበር። ሰው መስሏት ይሔን የባንክ ሰራተኛ አገባችው። ከተራ የደንበኛ አስተናጋጅነት አንስተው ማናጀር አደረጉትና ወደዚህ አዛወሩት። የሱ ኑሮ ቀጠለ። የሷ እንደነገሩ ሁኖ ቀረ። እናት መሆን አቃታት። ሚስት መሆን አጎበጣት። እነማዬ ሌላ ህልም ኑሯቸው አያውቅምና ፍላጎቷን እንደቅንጦት ቢያዩት አይገርመኝም። አንድ ቀን ማታ ዘርዬ ባልተዘጋጀሁበት ስለዛች ወፍ ታወራኝ ጀመር። «ከአስራ ስድስት አመት በፊት ባንተ እድሜ እያለሁ ይመስለኛል።» አለች በድንገት። ነቃ አልኩ። «እንዲሁ በጨዋታ ዲንጋይ ስወረውር ያንደኛዋን ወፍ ክንፍ ሰበርኩት። በኢላማዬ ደስ ብሎኝ የወደቀችውን ሒጄ ሳያት መብረር አትችልም። አሳዘነችኝ። ቤት ወሰድኳት። ዶሮዎቼ ጋር ቀላቅዬ ጥሬ እያበላሁ እስክትሞት ድረስ አኖርኳት።» «ታዲያ ምን አጠፋሽና ትረግምሻለች? የተሳሳትሽውን አስተካክለሻልኮ!» አልኩ በጭንቀት። «ሁለት ጊዜ ነው የገደልኳት። ክንፏን መስበሬ ሳያንስ የክንፏን መሰበር እንደ ችግር በማያዩ ዶሮዎች መሀል እንድትኖር አደረኳት። ሲመስለኝ እሷ ወፍ ረግማኛለች።» ከጃኬቷ ኪስ ወረቀት አውጥታ ሰጠችኝ። ላነበው ስል «ነገ ማታ እንድታነበው ነው የምፈልገው» አለችኝ። ነገ ተነስታ ልትሰወር ነው ብዬ አልጠረጠርኩም። እኔ በተኛሁበት የኔ ወፍ ዘርዬ ሰባራ ክንፏን እየጎተተች ርቃ ሔደች። ጧት ወደ ትምህርት ቤት ስሔድ የግቢያቸው በር ተከፍቶ ፊትለፊት ባዶ ቤታቸው ከመንገድ ላይ ይታያል። ተንደርድሬ ስገባ ሁለት ሰዎች እየዞሩ እያዩ ነው። ለቀው መሔዳቸውን አረዱኝ። መከዳት ተሰማኝ። ትምህርት ቀርቼ ሳለቅስ ዋልኩ። በሶስት ቀን ውስጥ አንድ ሰሞን ወደነበርኩበት በሽታ ተመለስኩ። አልበላም፣ አልጠጣም፣ አልተኛም። ከመሔዷ በፊት ወረቀት ሰጥታኝ እንደነበር ያስታወስኩት ራሱ መምሬ ሶስት ቀን በፀበል ካጠመቁኝ ቡኃላ ነው። መሔዷን እያሰብኩ ያልረሳሁት ምን አለ? አልጠበኩም ነበር! ገልጨ ሳነበው ከህመሜ ተፈወስኩ። መምሬ በመዳኔ እማዬ ስታመሰግናቸው «ሶስት ቀን መቆዬቱ ራሱ ገርሞኛል» ሲሉ ጉራቸውን ነፉ። ዛሬ በዘሪቱ እድሜ ሁኜም ያ ደብዳቤ ከኪሴ አይጠፋም። የስሜት መዋዠቅ ሲገጥመኝ አውጥቼ አነበዋለሁ። «ቻው ያላልኩህ አንተን ቻው ማለት ስለከበደኝ ነው። ደስ ትለኛለህኮ። በአንተ ውስጥ ራሴን አያለሁ። አስራ አምስት አመት ፈጥኜ ባልወለድ የማገባው አንተን ነበር። አምላኬን የምጠይቀው አንድ ነገር እኔ ያጣሁትን ሁሉ ላንተ እንዲሰጥህ ነው። ያልኖርኩትን ኑርልኝ። ስለሁሉም አመሰግንሀለሁ። ያላንተ አላልፈውም ነበር ይሔን ጊዜ።» ይላል። ዛሬ ላይ የመፅሔት አዘጋጅ ነኝ። ደስተኛ ሰው ነኝ። ጓደኞቼ «ለምንድን ነው ሰው ሁሉ ያለ ምክኒያት የሚወድህ?» «ለምንድን ነው የነካኸው ሁሉ የሚሳካልህ?» ይሉኛል። የኔ መልስ ሁሌም አንድ ነው። «ወፍ መርቃኝ!» እላቸዋለሁ እየሳቅኩ። ማብራራት እንዳልፈለኩ ይሰማቸውና ይተውኛል። ፨፨፨ (March 2022) Mickel azmeraw
ጭንቀት እነዚህን ነገሮች በ አንድ ላይ ማድረግ ነው ®አሁን መደረግ ያለበት ®መዘግየት የሚችል ®ለሌላ ሰው መስጠት የሚቻል ®ከነ መተው
Admas pinned «የወንዶች ጉዳይን ከሳቅ በዘለለ መረዳት የሚፈልግ አንድም ጤነኛ ሰው ያለ አይመስለኝም። እኔ ግን ጤና ስለሚጎለኝ የወደድኩትን ነገር እስክጠላው ድረስ መጎርጎሬን አላቆምም። የመጀመሪያው ጥያቄዬ "ደራሲው የዋና ገፀባሕሪዎቹን ስም አዕምሮ እና ሕሊና ያለው ባጋጣሚ ነው?" የሚለው ነበር። በርግጥ ይሕ ጥያቄ ብቻውን ወደ ሌላ አለም ይወስደኛል ብዬ አላሰብኩትም። ምክኒያቱም ሌሎች ደራሲዎች እንዲህ አይነት ነገር…»
видео или голосовое, без подписи
የሆነው ሁሉ ሁኖ መጨረሻ ላይ ሕሊና አዕምሮን ፈልጋ ስትሔድ በሩን ዘግተው ሊያስቆሟት የሚሞክሩት እኒያው ደባል ሱሶቹ ነበሩ። የዚያኔ ግን ድክመቷን ብቻ ሳይሆን ድክመቶቹንም ጠንቅቃ ስለተረዳች ማናቸውም ሊያስቆሟት አልቻሉም። የወይን አበባዬ 📯 የወይን 🎶 Mickel Azmeraw
የወንዶች ጉዳይን ከሳቅ በዘለለ መረዳት የሚፈልግ አንድም ጤነኛ ሰው ያለ አይመስለኝም። እኔ ግን ጤና ስለሚጎለኝ የወደድኩትን ነገር እስክጠላው ድረስ መጎርጎሬን አላቆምም። የመጀመሪያው ጥያቄዬ "ደራሲው የዋና ገፀባሕሪዎቹን ስም አዕምሮ እና ሕሊና ያለው ባጋጣሚ ነው?" የሚለው ነበር። በርግጥ ይሕ ጥያቄ ብቻውን ወደ ሌላ አለም ይወስደኛል ብዬ አላሰብኩትም። ምክኒያቱም ሌሎች ደራሲዎች እንዲህ አይነት ነገር የሚያደርጉት ከላይ ሲታይ ደስ ስላላቸው ብቻ ነው የሚሆነው። አድማሱ ግን የደበቀውን ታሪክ እንድናገኝበት ያስቀመጠልን ካርታ ነበር። ፊትለፊታችን ሁኖ የተሰወረው ስቶሪ ባጭሩ ይሕ ነው። አዕምሮ ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት ሲል ሕሊናውን እየዋሻት ነው። እንዲዋሻት የሚተባበሩት ደግሞ ስድስት ደባል ሱሶች አሉበት😃 ላይሆን ይችላል...ይሕ ቲዎሪ ብቻ ነው። እስከሚያስኬደን ድረስ እንሒድበት🙂 ወዳጆቹ...እስከጥግ የሚገዙለት አንድ ነገር አላቸው። አንደኛው ያገኘውን የሚያገበሰብስ ሆዳም ነው። አንደኛው አላፊ አግዳሚውን የሚያስረግዝ ዘማዊ ነው። አንደኛው ሰርግ ቤት ሳይቀር ከመለኮስ የማይመለስ አጫሽ ነው። አንደኛው ከሰከንድ በፊት ያገኛትን ሴት ቂጧን ካልጨበጥኩ የሚል ሴሰኛ ነው። አንደኛው እቁብ ሲወጣለት ልብስ ልግዛ ሶፋ ልቀይር ሳይሆን "ዛሬ ይጠጣል!" የሚል ጠጃም ነው። አንዳቸውም በሰውነታቸው ላይ ሀይል የላቸውም። ህይወታቸው በሱሳቸው ዙሪያ ነው የሚያጠነጥነው። ሱሰኛ ብቻ ሳይሆን ሱስ ራሱ ናቸው። ግን አትጠሏቸውም። በጣም ነው የሚያዝናኑት። ሲጫወቱ ለምናያቸው ለኛ "ጓደኞቼ በሆኑ!" የሚያስብሉ ናቸው። ያው ሱስ ሱስን ይወዳልና አንድ ላይ ሰብሰብ ብለው የመሰረቱት ማሕበርም አላቸው። የዚህ ማሕበር አስተባባሪ እና ዋና ፀሀፊ ቀጮ ነች። ቀጮ እንደሌሎቹ ሱስን አትወክልም። "ታዲያ ሱስ ካልሆነች ሱሶችን የምትሰበስባቸው እሷ ማነች?" ልትሉ ትችላላችሁ። ቀጮ ማለት ሴት ሁና ሳለ ራሷን እንደ ሴት የማታይ ሰው ነች። "ሴቶች" እየተባለ ሲወራ እንኳን እኔን ይመለከተኛል ብላ አትሰማም። ለዛም ነው ወንዶች ሴቶች ላይ ለሚፈፅሙት ተንኮል ተባባሪ ሁና የምትገኘው። ያ ማለት ግን ሴቶችን ትንቃለች ማለት አይደለም። የምትንቀው ራሷን ነው። አዕምሮን ስትመርቅ እንኳን "ቀጠን ያለችዋን፤ እንደ እንዝርት ተሽከርካሪዋን፤ እንደ ዳር ተወርዋሪዋን ያጋጥምህ!" ነው የምትለው። የሷ ምርጥ ሴት...እሷን የማትመስል ነች። ስለዚህ የነዚህ ሱሶች ሰብሳቢ የወረደ በራስ መተማመን ያላት እና ከተቃራኒ ወገን ተሰልፋ የምትዋጋ ፍጡር መሆኗ ስሜት ይሰጣል። ሱሶችን የሚጠራቸው ይሔ አይነቱ ራስ ጠልነት ነው'ና! (ቀጮ Insecurity ነች እያልኩ ነው ምዕመናን😭) አዕምሮም ወደነሱ የተሳበው በዚችው ጎኑ ነው። ማሕበራቸውን እንዲቀላቀል ያላደርጉት ጥረት አልነበረም። አንዱም አልሰራም። የሚወዳት ፍቅረኛው ከውጭ ለመጣ ሰው ጥላው መሔዷም ለሽንፈት አላበቃውም። ከዛ በፊትም ብዙ ሴት ጋ ተለያይቷል። ብርቁ አይደለም ፍቅሩን ማጣት። ለሽንፈት ያጋለጠው ከመሔዷ በፊት የጣለችበት ንግግር ነው። "አንተን ብዬ መቼም ከምመኛት አሜሪካ መቅረት አልችልም!!!" 😃 ይሕ ንግግር ጥላቻም የለውም። ርሕራሔም የለውም። ምርር ያለ እውነት ብቻ ነው። ይሔንን እውነት ለመዋጥ አዕምሮን Pride ያንቀዋል። ያጥወለውለዋል። ስራ ትቶ መኝታ ላይ ይውላል። የዚያኔ ማሕበርተኞቹ ደም እንዳሸተተ ሻርክ ተቀላቀለንና ከሀዘንህ እናድንህ እያሉ ይዞሩታል። የደረሰበትን ሽንፈት እምደሚያስረሱት ደጋግመው ቃል ይገቡለታል። መፍትሔው ያለው በነሱ እጅ እንደሆነ ጨቅጭቀው ያሳምኑታል ልክ ሁነውም ይገኛሉ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ከወደቀበት ተነስቶ መሳቅ መጫወት ይጀምራል። ሕሊናውን ከመዋሸት ቢሆንም ደስታው የተገኘው ከነበረበት መጥፎ ስሜት አንፃር ይሔ አስር እጥፍ የሚሻል መንገድ ይሆንለታል። "አሁንማ እንከባከብሀለን ቅድም እኮ ቅጥል ነው ስታደርገን የነበረው!" እያሉ የበለጠ ሰምጦ እንዲገባ ያበረታቱታል። ውሸቱ እንዲሰራ መንገዱን ያሳልጡለታል። ፅዋ ያነሱለታል። እጃቸውን ጭነው ይመርቁታል። ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ይሆናል። ችግሩ ይሔንን ስሜት ለማስቀጠል ሁሌም ጧት ተነስቶ አንድ አዲስ ውሸት መዋሸት አለበት። ዛሬ አለቃውን አታልሎ ከስራ የቀረ እንደሆነ ነገ ደግሞ የእህቱን ሽቶ ሰርቆ ቤቱን መበጥበጥ ይኖርበታል። ደባል ሱሶቹ ለሚሰጡት ደስታ በምላሹ ከሱ የሚጠይቁት ሕሊናን እንዲተኛት፤ በውሸት አለም ውስጥ እንዲያባክናት...ባጭሩ Corrupt እንዲያደርጋት ነው። እንደመጀመሪያዎቹ ጊዜያትም ቶሎ ቶሎ አይስቁለትም። በሆነ ባልሆነው ነው የሚነጫነጩበት። "ታዲያ አዕምሮ ይሔ ሁሉ ውሸት ውስጥ ሲዋኝ ሕሊና እንዴት መጠርጠር ይሳናታል?" የሚለው ሁለተኛው ጥያቄዬ ነበር። እንግዲህ አዕምሮ የምናዬው የምንዳስሰው የማሰቢያ ማሽን ነው። ይሕን ማሽን የሚጠልፉትም የምናያቸው የምንዳስሳቸው አደንዛዥ ዕፆች ናቸው። ሕሊና ግን የማናያት፤ 'ማንዳስሳት...አዕምሯችንን እየወቀሰች በትክክለኛው መንገድ እንዲሔድ የምታስገድደው ስውር አለቃችን ነች። ህሊናን ሱስ አያሸንፋትም። እሷን ሚጠልፋት እንደሷ ለማዬት ለመዳሰስ የሚከብደው ዲያቢሎስ አልያም እርኩስ መንፈስ ነው። ሸዊት የምትጫወታት ገፀባህርይ (ማርታ) የምትወክለው ይቺን ከሕሊናችን ጆሮ ላይ የማትጠፋውን አንሾካሿኪ ድምፅ ነው🙂 ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለአዕምሮ ውሸቶች የምትማልለው እሷ ነች እንጂ ሕሊና አልነበረችም። በፍቅሩ ተይዛለች። "ሶፋ ብናስቀይረው፤ ወርቅ ብናስገዛው" እያለቻት ነው ጆሮዋ ላይ ቁማ። ሐሳቧን ውድቅ እንዳታደርግባት ደግሞ ለቤተሰባችን ስንል ነው እያለች ታግባባታለች። ቤት የጋበዘችው ቀን ሶፋቸው መበላሸቱን ነግራ ልታስገዛው ስትሞክር አዕምሮ "እሰራዋለሁ!" ብሎ መዶሻ ነገር ፍለጋ ይገባል። ማርቲ አመዷ ቡን ብሎ "ምንም ነገር የለንም...ጎረቤትም የላቸውም!" ስትለው ሕሊና ተነስታ ከጠረንጴዛው ስር የተቀመጠውን ዘነዘና ትሰጠዋለች። የአዕምሮ እውነተኛ ማንነነቶች ፈንቅለውት በሚወጡበት ቅፅበቶች ሁሉ ሕሊናን ይማርካታል። በተቃራኒው ማርታን ያቅለሸልሻታል። ሁለቱ ያለ ሶስተኛ ወገን ብቻቸውን ሲገናኙ የሆነ ደስ የሚል ነገር አላቸው። አንዳቸው ላንዳቸው ነው የተፈጠሩት ያስብላሉ። መዋደዳቸውም ያስቀናል። ነገር ግን መሰረቱ ወሸት ላይ ነው'ና ሒሳቡ ሳይወራረድ ግኑኝነቱ ሊፀና አይችልም። አዕምሮ መቼም መቼም መቼም ቢሆን ከገባበት ክብ መውጣት አይችልም። ከገባበት ክብ ልታወጣው የምትችለው ሕሊናው ብቻ ነች። እሷ ደግሞ እሱን ማውጣት እንድትችል በቅድሚያ ጆሮዋ ላይ ያለችውን መንፈስ ጠንቅቃ መረዳት ይኖርባታል። መረዳት ብቻ ሳይሆን ንቃ መተው መቻልም አለባት። ያን ማድረግ እንድትችል መንፈሳዊ እገዛ ትፈልጋለች። ለዛ ነው የቤተክርስቲያኑ ትዕይንት ትክክለኛ ቦታ ላይ ገብቷል የምለው። አዕምሮ እንደልማዱ "ጌታዬ ውሸቴን የማስቀጥልበት ገንዘብ ስጠኝ!" አይነት ፀሎት ይፀልያል። እሷ ግን እውነቱን መኖር እንዲጀምሩ ነው የምትማፀነው። ጌታም የሕሊናን ልመና ሰምቶ የጠዬቀችውን ብርታት ይሰጣታል። ማርታ ያስጀመረቻትን ድራማ ትታ ሀቁን በማፍረጥረጥ አዕምሮን ከገባበት ስካር ታባንነዋለች። ነፍሱ ስትያዝ ይናዘዛል። መክፈል ያለበትን የንስሀ ዋጋ ይከፍላል። እውነቱን ማውራት ሲጀምር እሷም እንዳዲስ እየወደደችው ትመጣለች።
ደላላነት ስራ ብቻ አይመስለኝም የሆነ ሱስ ነገር ነው። አንድ እሳት የላሰ የሰፈራችን ደላላ ጌታን ተቀብሎ ከድለላው ጎን ለጎን ሰባኪ ሆነ። እና የዛን ሰሞን ቤት ያገኘላት አንዲት የክለብ ዘፋኝ አምሽታ ስለምትገባ ቤት ፈልጊ ተብላ አዝና እየነገረችው ነው። "ስራየ ከሰው አላኗኗረኝም ፣ ዘፈን መረረኝ ከአሁን በኋላ የሆነ ሐይማኖት ተከታይ ሆኘ ማረፍ ነው የምፈልገው" ትላለች በምሬት። ደላላው ፈጠን ብሎ "አታስቢ እጀ ላይ ምን የመሰለ ጌታ አለ" 😁
የሆነ ጊዜ ጧት የስራ ባልደረባየ ጋር ታክሲ ውስጥ በአጋጣሚ ተገናኝተን ወደቢሯችን አብረን እየሄድን ነበር። ልክ ስንደርስ ክንዴን ያዝ አድርጎኝ ሰዓቱን ተመለከተና... "ልክ በሰዓቱ ደረስን፣ ትንሽ እናርፍድ" አለኝ። "እ? ለምን?" "በሰዓቱ ከገባን አለቃችን ይለምዳል"😁 ትቸው ገባሁ እርሱ አርፍዶ መጣ። ሌላ ቀን አርፍጀ ስገባ አለቃየ ተነጫነጨ፣ በማርፈዴ ድርጅቱ ሊደርስበት የሚችለውን የመሬት መንቀጥቀጥ አስረዳኝ። ይቅርታ ጠይቄ ገባሁ። ከእኔ በኋላ ብዙ ቆይቶ ያ እናርፍድ ያለኝ ጓድ ሲደርስ "በቃ አይሞላልህም አንተ " ምናምን ብሎ በሞቀ ሰላምታ ተላለፉ። በየቢሮው ስንት ስትራቴጂስት አለ እናንተ?
видео или голосовое, без подписи
የRed Car Theory ወይም «የቀይ መኪና ቲዎሪ» በህይወታችን ውስጥ ስለሚኖሩ ዕድሎች እና በትኩረታችን (Focus) ኃይል ላይ የሚያጠነጥን በጣም ድንቅ የስነ-ልቦናዊ ምሳሌ (Metaphor) ነው። ይህንን ሜታፎር በቀላሉ ለመረዳት የሚከተለውን ጥያቄ እናስብ፡ “ዛሬ ወደ ስራ ወይም ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ ስንት ቀይ መኪናዎችን አየህ?” አብዛኛውን ጊዜ መልሱ “አላውቅም” ወይም “ትኩረት አልሰጠሁትም” የሚል ነው። ቀይ መኪናዎች በየመንገዱ ነበሩ፤ ነገር ግን አንተ እነሱን ለመፈለግ ስላልተዘጋጀህ አእምሮህ እንደ አላስፈላጊ መረጃ (Noise) ቆጥሮ አሳለፋቸው። አሁን ግን እራስህን እንዲህ ብለህ እዘዘው፡ “ነገ መንገድ ላይ ለሚያጋጥመኝ ለእያንዳንዱ ቀይ መኪና 1,000 ብር እሸለማለሁ።” በማግስቱ ወደ ውጭ ስትወጣ ምን የሚፈጠር ይመስልሃል? በየደቂቃው ቀይ መኪናዎችን ማየት ትጀምራለህ። እንዲያውም «በየመንገዱ ይሄን ያህል ቀይ መኪና የት ነበረ?» ብለህ ትገረማለህ። መኪናዎቹ በድንገት ከሰማይ አልረገፉም፤ ሁልጊዜም እዚያው ነበሩ። ልዩነቱ አንተ እነሱን መፈለግ መጀመርህ ብቻ ነው። የሬድ ካር ቴዎሪ ዋና መልዕክቶች (The Core Lessons) ይህ ሜታፎር በዕለት ተዕለት ህይወታችን፣ በንግድም ሆነ በግል ስኬታችን ላይ ትልቅ ትምህርት ይሰጠናል፦ ዕድሎች ሁልጊዜም አጠገባችን አሉ። ልክ እንደ ቀይ መኪናዎቹ ሁሉ፣ አዳዲስ የንግድ ሀሳቦች፣ የስራ ዕድሎች፣ ጠቃሚ ግንኙነቶች እና መፍትሄዎች ሁልጊዜም በዙሪያችን አሉ። ነገር ግን ዝግጁ ካልሆንንና ትኩረታችንን ካላስተካከልን ልናያቸው አንችልም። የአእምሮአችን ማጣሪያ (The RAS Filter)፤ በስነ-ልቦና ውስጥ Reticular Activating System (RAS) የሚባል የአእምሮአችን ክፍል አለ። ይህ ክፍል በየቀኑ ከሚመጡብን በቢሊዮን የሚቆጠሩ መረጃዎች መካከል እኛ «ትኩረት የሰጠናቸውን» ብቻ አጥሮ ያሳየናል። ስለ ውድቀት የምታስብ ከሆነ አእምሮህ የውድቀት ምክንያቶችን ብቻ ያሳየሃል። ስለ ስኬትና ዕድሎች የምታስብ ከሆነ ደግሞ መፍትሄዎችን ማሳየት ይጀምራል። ዕድል የዕድለኛነት ጉዳይ አይደለም፣ የዝግጁነት ነው። ብዙ ሰዎች «እሱ እኮ ዕድለኛ ነው» ይላሉ። ነገር ግን ስኬታማ ሰዎች ዕድለኛ የሆኑት በዙሪያቸው ያሉትን «ቀይ መኪናዎች» (ዕድሎች) ነቅተው ለመመልከት እራሳቸውን ስላዘጋጁ ነው። ይህንን በህይወትህ እንዴት ትተገብረዋለህ? የምትፈልገውን ነገር በግልፅ እወቅ፦ ምን ማሳካት ትፈልጋለህ? ምን ዓይነት ዕድል ነው የምትፈልገው? ይህንን በግልፅ ስታውቅ አእምሮህ ያንን ነገር «መፈለጊያ ራዳር» ያበራል። አእምሮህን አሰልጥን፦ በየቀኑ ጠዋት ስትነሳ «ዛሬ አዳዲስ ዕድሎችን አገኛለሁ» ብለህ እራስህን አሳምን። በንቃት ተከታተል፦ በአካባቢህ የሚፈጠሩ ችግሮችን ተመልከት፤ ምክንያቱም እያንዳንዱ ችግር ጀርባውን የዞረ «ቀይ መኪና» (ትልቅ የንግድ ወይም የስኬት ዕድል) ሊሆን ይችላል። ባጭሩ፦ ዓለም በዕድሎች የተሞላች ናት። ጥያቄው “ዕድሎች አሉ ወይ?” ሳይሆን “የአንተ አእምሮ ቀይ መኪናዎችን ለመፈለግ ዝግጁ ነው ወይ?” የሚለው ነው። Psych addis
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
አሜሪካ ሄጀ ወያላ ልሁን የሚል ኮሜንት እንዳትሰጡ! (አሌክስ አብርሃም) ባለፈው አንድ መኪና ከፊቴ ቆመና የ "STOP" ምልክቱን ዘረጋ። ሁላችንም ከኋላ ተደርድረን ቆምን። ልክ እንደስኩል ባስ አይነት ግን ትንሽ ቫን ነገር ነው። እና በሩ ተከፍቶ አንድ ውሻ ሮጦ ወጣና ቁማ ወደምትጠብቀው ሴት ጋር ሄዶ በደስታ ይቦርቅ ጀመር። አቅፋ ሳመችው። ውሾች ልክ እንደትምህርት ቤት ውለው ሲመለሱ የሚመላለሱበት የውሻ ሰርቪስ ነው። Doggy Daycare Bus” ወይም “Puppy School Bus” እየተባለ ይጠራል። ውሾቹ የት ነው የሚውሉት? ብየ ጎግል ሳደርግ እነዚህ ውሾች የሚሄዱት ባለቤቶቻቸው ስራ ሲሄዱ "Doggy Daycare" ወደሚባሉ ቦታዎች ነው። እዚያ ቀኑን ሙሉ ብቻቸውን ቤት ውስጥ ከመቀመጥ ይልቅ እንደልጆች ጧት ከየቤታቸው በሰርቪስ ሄደው ከሌሎች ውሾች ጋር ይጫወታሉ፣ ዋና ይዋኛሉ፣ እንቅልፍ ይተኛሉ፣ እንዲሁም አንዳንድ የስነ ምግባር ስልጠናዎችን ያገኛሉ። ባለቤቶች ጠዋት ወደ ስራ ከመሄዳቸው በፊት ውሻቸውን ማቆያ ቦታ ድረስ መውሰድ ስለሚደክማቸው፣ ይህ የባስ አገልግሎት ትልቅ እፎይታ ሆኖላቸዋል። አስባችሁታል "ውሻሽ የት ነው የሚማረው?" ምናምን ሲባባሉ! ወደቲክቶክ ስመለስ አንዲት መንግስት ቤት 20 ዓመት የሰራች ሴትዮ ከኮየ ፈጨ በሰልፊ ቪዲዮ ቅሬታዋን እያቀረበች ነው። "ለሚመለከተው አድርሱልኝ... 56 ቁጥር ባስ ቀረችብኝ ይሄው ሕዝቡ ተሰልፎ እየጠበቀ ... ከስራ አረፈድን " እያለች።