tgindex
ትዝብተ-በርናባስ🔎✍️

ትዝብተ-በርናባስ🔎✍️

Статистика

ምድር እጅግ ሰፊ ናት፤ እኔ ወንድማችሁ በርናባስ ደግሞ ያሉኝ ሁለት ዐይኖች ብቻ! አባካችሁን ኑ...ና አጋጭተን (ዐይኖች አዋጥተን) እንይ!✍️ አሳብ አስተያየት ቢኖራችሁ፦ @barnica የግላችሁ ነው።

Последний пост
9 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 401
−3 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
600
20 постов
Вовлечённость
42,8%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
414
1/48двое суток
474
1/72трое суток
511

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ቤተ ክርስቲያንን ስታስቡ ጥንቅቅ ያለ ፕሮግራም ተካፍሎ ስለመመለስ፣ ከዐውድ ያላፈነገጠ ትምህርትና ስብከት ተካፍሎ ስለመምጣት አስባችሁ ከሆነ የነገረ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረታችሁ ችግር ገጥሞታል። ቤተ ክርስቲያን ፕሮግራም ተካፍሎ ለመመለስ የሚኬድበት ቦታ ሳይሆን ሕይወት ለመካፈል (ለመቀበልና ለመስጠት) የሚኬድበት ሕያው የሆነ የወንድሞች ኅብረት ነው። ሕያውነቱ አንዱ ሰው በሌላው ውስጥ በመኖሩ…

  • 9 авг.20321из metsihafuyinager

    ቤተ ክርስቲያንን ስታስቡ ጥንቅቅ ያለ ፕሮግራም ተካፍሎ ስለመመለስ፣ ከዐውድ ያላፈነገጠ ትምህርትና ስብከት ተካፍሎ ስለመምጣት አስባችሁ ከሆነ የነገረ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረታችሁ ችግር ገጥሞታል። ቤተ ክርስቲያን ፕሮግራም ተካፍሎ ለመመለስ የሚኬድበት ቦታ ሳይሆን ሕይወት ለመካፈል (ለመቀበልና ለመስጠት) የሚኬድበት ሕያው የሆነ የወንድሞች ኅብረት ነው። ሕያውነቱ አንዱ ሰው በሌላው ውስጥ በመኖሩ የሚረጋገጥ ነው። ወደ ቅዱሳን ጉባኤ ኺዱ፤ በፍጹም አትቅሩ። ዛሬ ጠዋት በኼዳችሁበት ጉባኤ በስንት ወንድምና እህቶች ልብ ውስጥ በቋሚነት አላችሁ? ስንት ሰዎች actively በሕይወያችሁ ውስጥ መብትና ኃላፊነት አላቸው? እንደርሱ ካልሆነ የኼዳችሁት ወደ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ወደ አንድ ቆንጆ ማኅበራዊ ክለብ ነው። ------------ Join Us! & Share!!! @metsihafuyinager @metsihafuyinager ------------ ወደ ውስጥ፦ @adfontess

  • ነገረ ቀልቀሎ --🔘--- ከበርናባስ በቀለ "አንተ ለምን ነገሮችን ሌጣቸውን አትረዳቸውም" ይሉኛል። ሌጣውን ያለ ነገር አለ? ያለ ዐውድ፣ ጊዜና ቦታ የሚነገር ድስኩር ኖሮ ያውቃል? ሲያልፍም የሰጡትን ብቻ የሚቀበል ቀልቀሎ ወይም ስልቻ ነው። ይህም የሆነው ቀልቀሎ ስለ ሰጡት ነገር reflect ለማድረግም ሆነ በሰጡት ነገር እሴት (value) መጨመር የሚያስችለው ስብዕና ስለሌለው ነው። ለሕላዌው የሚያስብለት ሌላ ነው። የሚገለገልበትም ሌላ አካል ነው። አያስብም፣ ማሰብ ስላለመቻሉም አይጨነቅም። አሳቢው ሌላ ነውና የሰጡትን ብቻ ይቀበላል። በእህል ጠቅጥቀው ያኖሩትና የሰጡትን በታማኝነት ሸክፎ ይይዛል። ይመቸው! እኔ ግን ስብዕና አለኝ። በአምሳለ ስላሴ የተሠራሁ እንደመሆኔ አሳቢና ተመራማሪ አዕምሮ የተጎናጸፍሁ ፍጡር ነኝ። ስለዚህ የሰጡኝን ብቻ የምቀበል አይደለሁም። "ትውፊት፣ ታሪክ፣ ወግና ትርክት ይህን ይላልና ተቀበል" ሲሉኝ ቆዩኝ እስቲ እቀበለው ዘንድ በደንብ ልረዳው እላለሁ። ታዲያ ትርክትና ትውፊት ጠል አይደለሁም ግና ጠያቂ አዕምሮ ያለኝ አማኝ ነኝ። እጠይቃለሁ፣ አሰላስላለሁ፣ ደግሞም በደረስሁበት መረዳት መሠረት ኃላፊነት ወስጄ እወስናለሁ። ምክንያቱም ስልቻና ቀልቀሎ አይደለሁም! ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • እስከ ምን ላስብ? --🔘--- ከበርናባስ በቀለ "ሰው የገዛ ሕይወቱ ሸማኔ ነው፣ መዘወሪያው ደግሞ ሃሳብ ነው።" ይላሉ የሃሳብ ኃይል አወዳሾቹ። እነዚሁ አስቦ አደሮች "ሃሳብህን ከተቆጣጠርህ የሕይወትህን ፍጻሜ ትቆጣጠራለህ" ብለውም ያምናሉ። አንዲት ጉዳይ ቢጤ እያሰብሁ ነውና እስከ ምን ድረስ ላስብ የሚለውን እያሰብኩኝ ነው። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • የ'ኔ ተራራ! ⛰️ --🔘-- ከበርናባስ በቀለ አንደኛ ለመሆን አልሠራም። ጎበዝ ለመባል አልፈጋም። ተጽዕኖ ለመፍጠርም አልባትልም። ምድሩን ለማስደመም ድንጋይ አልፈነቅልም። ትላንት በሳቁብኝ በተራዬ ልስቅባቸው ጠብ እርግፍ አልልም። ታዋቂ መሆንም አልፈልግም። ዘመናዊ ለመሆን አላንቧችርም። ከማን አንሼ በሚል ተምች ቢሂል ናላዬ አይዞርም። እጄ ላይ ያለው ነገር ወደ ሰዎች እንዲደርስ ብዬ አልሠራም። እግዚአብሔርንም ላገለግለው ብዬም ያላቅሜ ከመለኮት እሰጥ እገባ ውስጥ አልገባም። እኔ መሆን የምፈለገው "ራሴን"፤ ማሸነፍም የምሻው ራሴን። ለመግዛትም ጦሜ ምጸልየው ራሴን። ተጽዕኖ መፍጠሩንም የምፈልገው በራሴው። ይህ ራሴ አመጸኛ ዓለም ነውና ትግሌ ከርሱ ጋር ነው። መንገዱ የክርስቶስ መስቀል እንደሆነ መጽሐፉ ነግሮኛልና (መድኀኒትነቱም የተፈተነ ነውና) ተስፋ አለኝ። ራሴን ካሸነፍሁ ዓለምን ማሸነፌ የት ይቀራል? ዓለም ምስቅልቅል ውስጥ ያለችው በራሳቸው በተሸነፉ ግን ሌሎችን ለማሸነፍ በሚጋደሉ ሰዎች መሆኑን መች አጣሁት። በቃ ምን አለፋችሁ! የኔ ተራራ እኔው ራሴ ነኝ። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • ክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር እቅፍ ወጥቶ ለቤዝዖቱ ሥራ መጣ፣ ከክርስቶስ ኢየሱስ ማንነትና ሥራ የድነት ወንጌል ወጣ፣ ከወንጌሉ ውስጥ መሲሓዊቷ ማኅበር (ቤተ ክርስቲያን) ወጣች፣ ከቤተ ክርስቲያን (በኩል) ሕያውነት ወደ ዓለሙ ይወጣል። ------------ Join Us! & Share!!! @metsihafuyinager ------------ ወደ ውስጥ፦ @adfontess

  • 22 июл.4547из metsihafuyinager

    ክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር እቅፍ ወጥቶ ለቤዝዖቱ ሥራ መጣ፣ ከክርስቶስ ኢየሱስ ማንነትና ሥራ የድነት ወንጌል ወጣ፣ ከወንጌሉ ውስጥ መሲሓዊቷ ማኅበር (ቤተ ክርስቲያን) ወጣች፣ ከቤተ ክርስቲያን (በኩል) ሕያውነት ወደ ዓለሙ ይወጣል። ------------ Join Us! & Share!!! @metsihafuyinager ------------ ወደ ውስጥ፦ @adfontess

  • በሥራዬ ጉዳይ ወጥቼ ቦሌ Morning Star አካባቢ ያለ ካፌ ውስጥ ነኝ። አጠገቤ አንድ ቆፍጠን ያለ ወጣት አለና ይደወልለታል። ስልኩን አንስቶ ወዳጁን "እ.. እየጠበኩህ ነው አትመጣም?" ይለዋል። "እየመጣሁ ነው ግን አንተ መኪና ይዘሃል አይደል? የእኔን መኪና ትቼው ልምጣ?" ብሎ ይጠይቀዋል። አጠገቤ ያለው ጎረምሳ "የኔዋ መኪና ፓርኪንግ ውስጥ ናትና ያንተን ይዘህ ና እና ሮጥ ብለን እንመለሳለን" ይለዋል። ከዚያም ያኛው ወዳጁ "የእኔ መኪና ላንተ አትሆንም፣ እባክህን ያንተን አውጣ ይለዋል" ኋላም ይኸኛው (አጠገቤ ያለው) ሰው "አንተ ምን ሆነህ ነው? እኔ በሳይክልም መኼድ እችላለሁ እኮ፣ ደግሞ vits እኮ ትልቅ መኪና ነው!" ይለዋል፣ ያኛው እንደተሳቀቀ "እሺ" አለውና ይኸው እየጠበቀው ነው። አይ... ቦሌ የሆነ ተፋልሶማ አለ! ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • ካረጁ አይበጁ! ---🔘---- ከበርናባስ በቀለ ዓለም ዋንጫዋን አስረክባለች። ሌጀንዶቹን እነ ክርስቲያኖንና ሊዮኔል ሜሲን ሸኝታ ላሚን Yamalንና መሰሎቹን (አዲሱን ትውልድ) ማንቆለጳጰሱን ይዛዋለች። "እኔ የሚያስፈልገኝ አዲስ ትውልድና አሠራር ነው!" (ካረጁ ለእኔም አይበጁ!) የምትል ይመስላል። እርሷ እኮ ጎበዝ ናት ማንን መቼ መጠቀም እንዳለባት ጠንቅቃ ታውቃለች። "በእነ እንትና ዋጋ መክፈል የመጣ ለውጥ" እያለች ያለፈውን ዘመን legacy ስታሞካሽና ከበሮ ስትደልቅላቸው አዳዲሶቿን አትቀርብርም። "አዳዲሶች አሉኝ እኮ" እያለች ቡቃያዎቿን ወደ ምድሩ ፊት ገጽ ታወጣለች። የቀዳሚዎቹን አሠራርና legacy ለማስቀጠል አዲሱን ትውልድ የሚሰዋ ማኅበር፣ አዲስ ነገር የሚጨንቀውና የጥንቱ አሠራር ታማኝ እስረኛ የሆነ መዋቅር ሁሉ ከዓለሚቱ ይማር ዘንድ እመኛለሁ። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • እግዚአብሔር ቸሩ! ---🔘---- ከበርናባስ በቀለ አሁን በጨለማው ክምር ላይ ትንሽዬ የብርሃን ተስፋ እያቆጠቆጠች ነው። ቀጥሎ ያለውን ዐረፍተ ነገር ስጽፍ ደግሞ ጨለማው አድራሻውን ሊለቅ ይመስላል። ይኸው ብርሃን! ይኸው ወገግታ። ታዲያ ጎህ ሲቀድ ሊነጋ ሲያቅላላ የብርሃኑ ጮራ ሲፈነጥቅ ጨለማው ደግሞ ሲፈረጥጥ ያዩ ዓይኖቼ የእግዚአብሔርን በጎነት የሚተርክ ዘጋቢ ፊልም እያዩ ይመስል ትዕንግርት ውስጥ ናቸው። እግዚአብሔር ቸሩ! "ብርሃን ይሁን አለ፣ ብርሃንም ሆነ" የተባለለት እርሱ ዛሬም ለሊቶቼን የሚያነጋልኝ እውነተኛ ብርሃን ነው። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • 15 июл.581262из metsihafuyinager

    ሰማዩ ዝም ያለ ሲመስለንና ነገረ ዓለሙ ግራ ገብቶን ስንዋትት እግዚአብሔር የነፍሳችን ማረፊያ ነው። እርሱ ልባችንን በሕያውነቱ የሚያሞቅ የደህንነታችን ምንጭ ነው። የሞት ሸለቆ በሚመስል ዝቅታ እያለፍን ያለን ሲመስለን እርሱ የዘላለሙ ከፍታችን ነው። ስለ ነገያችን አስበን እርግጠኝነት ሲጎድለን ዓለማትን በመግቦቱ የያዘው እርሱ መድን ዋስትናችን ነው። ------- Join Us! @metsihafuyinager @metsihafuyinager ------- በውስጥ፦ @adfontess

  • የኢሉሚናቲ መንፈስ! ---🔘----- ከበርናባስ በቀለ ከሰሞኑ ሚስቴና ልጄ ለጋራ ተልዕኳችን ኼዴዋልና ሳምንቱን ላጤ ነኝ። ምግብ ሠርቼ መብላት እችላለሁ፣ ኧረ ማብላትም እችላለሁ። ግን እነርሱ ኼደው ብቻዬን ስበላ የከዳኋቸው ይመስለኝና አይዋጥልኝም። ላስበውም አልፈልግም። እናም ሚስቲቱ "ትክክል አይደለህም፣ እንደውም ስመለስ ሽምግልና መቀመጥ አለብን!" ብላኛለች። አንቺ ሰላም ተመለሺ እንጂ አያሳስብሽ ብዬአታለሁ። እሺ፣ እኔ ምን ላድርግ? እርሷ በሌለችበት ቤት ምግብ መብላት በታማኝነት ጉድለት የሚያስከስስ የሚመስለኝን ነገር ምን ላድርግ? ደግሞ እኮ ላለፉት 7 አመታት እንደ ትንሽ ልጅ እንዲሁ ነው ሳስቸግራት የኖርሁት (ለነገሩ ለእናቴ አሁንም ልጅ ነኝ፣ ኤታቤቱ!)። ትላንትም (እሑድ ከሰዓት) ወደ ነበረኝ መርሓ-ግብር ያቀናሁት ምሳዬን ሳልበላ ነበርና ጓደኛዬ ሰሎሞን አዝኖልኝ "መፍትሔ አግኝቼልሃለሁ" አለኝና ቀጥሎ "የኛ ቤቱን የምግብ policy ተከተሉ! እኛ ቤት ሁሉም ሰው በየራሱ ሳህን (Dish) ስለሚበላ በምግብ ጉዳይ ማንም ከማንም ጋር emotionally attached አይደለም! ስለዚህ Betty ስትመለስ ይህን ዘዴ ተከተሉ!" እኔም ከአፉ ቀበል አደረግሁና "ይህ የኢሊሙናቲ መንፈስ ነው! ሥራህ ይፍረስ!" አልኩት። በቃ Ema ስትመጣ በትክክል እበላለሁ። ዛሬም በሌላ ፕሮግራም ከከተማ ርቄ ስለነበር ይኸው አምሽቼ (4:35) ገባሁና ስለ ውሎዬ ምስጋናዬን ወደ ሰማዩ ካሳረግሁ በኋላ "ስለ ምግብ" የሕሊና ጸሎት በማደርግበት ሰዓት ነው ይህችን የጻፍሁት። እናንተ ምን አለባችሁ፣ ራታችሁን በልታችሁ የሰው ቤት ጉድ አንብቡ! እኔም ይንጋና ወጥቼ "ፏ" ያለ ቁርስ እበላለሁ። የመጣ ይመጣል እንጂ ግን Solን አልሰማውም። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • ሞትም ሰልጥኗል! ---🔘---- ከበርናባስ በቀለ የቅርብ ወዳጄ ናት። እጅግ ትጉህና የአቋም ሴት በመሆኗ በዙሪያዋ ባሉ ዘንድ ተከብራ የምትኖር እንስት እንደሆነች ስነግራችሁ እኔም ከተጽዕኖዋ ያልተረፍሁ መሆኔን ሳልሸሽጋችሁ ነው። ከምትኖርበት ከተማ ወደ ሌላኛው የክፍ'ላገር ከተማ በጉዳይ ተጉዛ ነበር (እርሱንም ከሳምንታት በፊት አሳውቃኛለች)፣ የዚያ ከተማ ተልዕኮዋን ጨርሳ ወደ እናት ከተማዋ ልትመለስ ሁለት ቀን ሲቀራት "ወንድምሽ አርፏልና ቶሎ ድረሺ" የሚል የስልክ ጥሪ ደረሳት። 😥 "ባርኒ ወንድሜን አጣሁት እኮ" ብላ text አደረገችልኝ። መደወል ፈራሁ! ስልኬን አስሬ እያነሳሁ መለስሁ። እንደምንም ግን ደወልኩላት። መቼ? እንዴት ምን ሆኖ? ብቻ ብዙ ጥያቄዎችን አከታትዬ ጠየቅኋት። "ባርኒ እንዴት የሚለውን እኔም አላውቅም" ይኸው ቀብረነው ቁጭ ብለናል። እኔም ማለት? ምንም ሳይታመም? ያለ ምንም አደጋ? ብዬ እንደ ደነገጥሁ ግራ መጋባቴን ነገርኋት። እሺ፣ ቆይ ምን ይባላል? ስለ ብዙዎች ኃላፊነት በመውሰድ የሚታወቅ ጀግና ወንድም ሲሠራ ውሎ ባለበት ወደቀ ሞተ፣ የሚለውን እንዴት እንመን? ህመም ቀርቷል ማለት ነው? ሞትም ሰልጥኖ በሌላ version እየመጣ መሆኑ ነው? ወይስ እኛ ያልገባን ሌላ ነገር አለ? ወንድማችን ሳይማቅቅ ሳይሰቃይ ወደተሻለችው ከተማ ኼዷል፣ ወዳጄ (ሀረግዬ) ከጥቂት ቀናት በኋላ ደህና ትሆናለች አውቃለሁ፣ እኛም አለንላት። ግን ለምን? እና እንዴት የሚለው ጥያቄ አዕምሮዬን ሰቅዞ ይዞታል። ቤተሰቦቼ ሞት ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ራሱን አዘምኖ ወደኛ ቀርቧልና አጠገባችሁ ያለውን ሰው ቼክ ማድረጋችሁን አትዘንጉ። በርግጥ ሞትን የምፈራ አይደለሁም፣ እርሱም ይህን ጠንቅቆ ያውቃል። ሞቼ አላየሁትም እንጂ የምወዳቸውን ስቀብራቸው ኖሬአለሁ። ተስፋዬም ከሞት ባሻገር ያለው ሕይወት ስለሆነ ወደዚያ ለመሻገር ከሚናፍቁ መካከል ነኝ። የኼደ አንዴ ኼዷልና እርሱ አይጨነቅም፣ ግን እዚህ ለቀረን ግዙፍና በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጥያቄ ትቶልን ይኼዳል። ስለ ወዳጄ እጸልያለሁ፣ እናንተም በጸሎታችሁ ታግዟታላችሁ። ግን አጠገባችሁ ላለ ሰው መልካምነት ልታሳዩ አስባችሁ እንደሆነ ቀን አትቅጠሩ። አዝናችሁበት እንደሆነ ለነገ አትበሉ። ትወዱትም እንደሆነ ፍቅራችሁን ለመግለጥ ዘግይታችሁ ጠሃይቱ አትግባ። ነገ አታገኙትምና ዛሬ ድረሱለት። ቀጣይ አመት አብሯችሁ ላይሆን ይችላልና ልባችሁ ከብዶበትም ከሆነ ዛሬውኑ ጊዜ ሰጥታችሁ ንገሩት። ይቅር ተባባሉ! ስልክ ቁጥሩ እጃችሁ ስላለ ሰውዬው ሁሌ ይኖራል ማለት አይደለምና (አንድ ቀን ስልኩ እስከወዲያኛው ሊዘጋ ይችላልና) ዛሬውኑ ደውላችሁ ምህረትን አውርዱ። በንፁህ ፈገግታችሁ ቀን የምትጨምሩላቸው አጠገባችሁ አይጠፉምና ግራ ቀኛችሁን ቼክ ማድረጋችሁን አትርሱ። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • 7 июл.678152

    "የዓለም ዋንጫ!" ⚽ ----▣------ ከበርናባስ በቀለ ከሚከተሉት መካከል ስለ ዓለም ዋንጫ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው? (ታዲያ በፍጥነትና በትክክል የመለሱ የመጀመሪያዎቹ 5 ሰዎች ይሸለሙ ዘንድ ወስነናል)። ----------- ሀ) የእግር ኳስ ስፖርቱ ተወንጫፊ ከዋክብት በዓለሙ ገጽ ፊት እየተወረወሩ የሚያበሩበት የትዕይንት መድረክ። ለ) ዓለም የዋንጫ ጨዋታ አዘጋጅታ ልጆቿን እያጫወተች ነው፤ ልጅ ጨዋታ ይወድ የለ? ሐ) ዓለም ዋንጫ አላት፣ በብርቱ ለሮጠላት ትሰጠዋለች። መ) አንተ ደግሞ፣ እስቲ አታወዛግበን። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • ⚠️ ------ ከበርናባስ በቀለ ሩጫ በዝቶብኝ ጉልበቴ ዝሎ እና አዕምሮዬ ረጅም እረፍት የሚያስፈልገው አይነት አኳኻን ውስጥ ስሆን--- ከአካላዊ እረፍቱ በላይ ለምን በዚህ ልክ ተወጣጠርሁ? ጊዜዬን እየበሉት ያሉት ነገሮች ድንበር ዘለል፣ መርኾ ተኮርና እግዚአብሔር ለአጽናፈ ዓለሙ ካለው እቅድ ጋር የሚቆራኙ ናቸው? ለሚል ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ ማግኘቱ የበለጠ ያሳርፈኛል። ከዚያም ወደ physical & mental እረፍቴ አቀናለሁ። ባለፉት ጊዜያት ብዙውን ጊዜዬን የበላብኝ አፍርሶ መገንባት እንደሆነ ስላስተዋልሁ አሁን አዲስ ግንባታዎችን ሁሉ ማቆም አለብኝ። ባይሆን የተገነቡ ግኑኝነቶችንም ሆነ እንቅስቃሴዎቼን እየመረመርሁ በየቅድሚያቸው ማሰለፍ ይኖርብኛል። ትክክል የሆነ ነገር ሁሉ እውነተኛ ብሎም ዘላለማዊ አይደለምና እድሜዬን በtrial & error ⚠️ እንዳልጨርስ ከወዲሁ በተጠንቀቅ መቆም አለብኝ። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • በምድሩ ላይ ርገጥ! ----▣--- ከበርናባስ በቀለ ለተጨነቀች ነፍስ ማዳንህን ለምትሻ ለ"አዳኝ ያለህ!" ባይዋ ከክፉው ንክሻ በሰማያት ያለህ አንተ በምድሩ ላይ ርገጥ ምህረትህን አውርድ ክንድህንም ግለጥ። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • በቸርነትህ ብቻ የቆሙ ግን ማዳንህን የዘነጉ በየእለት ኑሯቸው ከእጅህ የሚበሉ ግን የፊትህ ነገር ግድ የማይሰጣቸው ሰዎች መካከል ራሴን ሳገኝ አንተ እግዚአብሔር የመልካም ነገር ሁሉ መገኛ ምንጭ ስለመሆንህ ቆፍጠን ብዬ እመሰክር ዘንድ ክንድህ ይደግፈኝ። አለዚያ እኔም ተደርቤ ለጠላቶችህ ሳማህ ልውል ነውና በፊትህ ብርሃን ጨለማዬን "ወግድ!" በልልኝ። ከበባውንም በትንልኝ፤ ኋላም ትኩረቴ ከእጅህ ወደ ፊትህ ይሁንልኝ። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • የMercy መስመር! ----▣---- ከበርናባስ በቀለ ጉዳይ ቢጤ ነበረኝና Mercy ጋር በጠዋት ስልክ መታሁ። ያቺ ሴትዮ "የደወሉላቸው ደንበኛ መስመር ስለተያዘ" ስትለኝ ብዙ ነገር አሰብሁ። ደግሞ "የደወሉላቸው ደንበኛ" ትላለች እንዴ? ደበኝነቷ ለእነርሱ አይደል እንዴ? ለእኔ እኮ ወዳጄ ናት። ለምን "የደወሉላቸው የቅርብ ወዳጅዎ አትለኝም?" ይህች ዓይን አውጣ ሴትዮ! እያልሁ አጉተመትማለሁ። ብዙ ነገር ማሰቤን ቀጠልሁ። እሺ፣ መስመሯ የተያዘው ለምንድነው? መስመር ያዢዎቹ ጠላፊዎች ቢሆኑስ? የመስመር ላይ ሌቦች ቢሆኑስ? እንዲሁ በቀላሉ መስመርን የመሰለ ነገር ማስያዝ!? ሆሆሆ! እያልሁ መንገዱ ላይ ብቻዬን አወራለሁ። መስመሯ በትክክለኛ ያዥ (በሕጋዊ መስመረኞች) ተይዞ መሆን አለበት። የሆነ ሆኖ ግን ደጋግሜ ስሞክር ስልኳ ተነሳልኝ። እኔም Mercye ደህና ነሽ? ሴትየዋ "መስመርሽ ተይዟል" ስትለኝ እኮ ደንግጫለሁ አልኋት። እርሷ እየሳቀች "ለምን ባርኒ?" አለችኝ። በልቤ ሰው ተጨንቆ እርሷ ትስቃለች እንዴ? እያልሁ መስመርሽ በመያዙ ነዋ! አልኋት። "ኦኦኦ ባርኒ፤ የስልኬ መስመር እኮ ነው።" አለችኝ። እኔም፦ ኡኡፍ! እንደርሱ በዪኛ ታዲያ አልኋት። እኔ የስልኳ መስመር ብቻ የተያዘ መሆኑን በምን አውቃለሁ? ሴትዮዋ እንደሆነች አታብራራ። "መስመር ስለተያዘ" ብቻ ነው የምትለው። ቀጥዬም ሌሎች መስመሮችሽ ደህና ናቸው? አልኋት። "አዎን! ሁሉም ጥሩ ነው!" አለችኝ። እሰይ! ብዬ ወደ ዋናው ጉዳዬ አመራሁ። እናተስ መስመራችሁ ደህና ነው? በመስመርማ ቀልድ የለም!!! ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • ደብረብርሃን አየሯ ብርዳማ ነው። በመግቢያዋ ያለች "ጠባሲ" የተሰኘች ከተማ ስሟን ያገኘችው ብርዷ የሚጠበስ ከመሆኑ እንደሆነ ነግረውናል። በርግጥ እኛ የመጣነው አየሩ ጥሩ በሆነበት ወቅት ስለመሆኑም አጫውተውናል። ትራንስፖርት ውስጥ ያገኙን አዳዲስ ከሆናችሁ "አረቄ ግድ ነው!" ይሉናል። "እኛ ቅዝቃዜውን የቻልነው በአረቄው ነው!" እያሉ ምርጥ የደብረብርሃን አረቄ ያለበት ቤት ይጠቁሙናል። እኛ ደግሞ ቡናችንን በሰዓቱ እናግኝ እንጂ አያሳስባችሁ (የኛ ቤት አረቄ ቡና ነው!) እንላቸዋለን። የሆነ ሆኖ ግን የልበ ቅኖች ከተማ ናት። ለመጣንበትም ተልዕኮ ቀና ምላሿን ሰጥታናለች። ከእንግዲህ ደብረብርሃን በሰሜን ሸዋ አንዷ የተልዕኳችን ማዕከል ሆና ልታገለግለን ቃል ገብታልናለች። አንኮበር፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻና መንዝ የቀጣይ ወር መዳረሻዎቻችን ናቸው። በእነዚህ አካባቢዎች ያላችሁ ወዳጆቼ ከዚህ ጉባዔ ወደ ኋላ ቀርታችሁ እንድታገኙኝ ይሁን!😊 ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • እንዳልቀባጥር! 🤲 ---▣---- ከበርናባስ በቀለ ለጣዕመ ቢስ ልሳኔዬ በድንቅ አደራረግህ ለዛ ሰጥተኸው ሌሎችን የሚያንጽ ነገር ማውራት ከቻልሁ ዘንዳ አንደበቴ የምህረትህ ባለ ዕዳ ነውና በጎነትህን ብቻ ያውራ። ክብርህን በሚሻማ መልኩ ለአፍታ እንዳልቀባጥር መንፈስህ ለከናፍርቴ ዘብ ይቁምልኝ። እንዳስለመድከኝ ሁሉ በዛሬውም ጉዞዬ (ከፊቴ ባለች ከተማ) ነገያቸውን ማየት ለተቸገሩ ከነገህ (from your future) እየጨለፍሁ የፍጻሜያቸውን ተስፋ እጠቁም ዘንድ ደካማውን ስብዕናዬን እንድትጠቀም ልመናዬን አቀርባለሁ። ምስክርህ ሆኜ በምቆምበት ሁሉ "እኔ አይደለሁም፣ እርሱ ነው!" እያልሁ አድንሆትህን አስተጋባ ዘንድ ቅዱሱ መንፈስህ እኔነቴን በአንተነትህ ይክደንልኝ። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊