tgindex
Tesfa

አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን?

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
390
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
6 166
+2 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 489
40 постов
Вовлечённость
24,1%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всего 390
Упоминаний
4
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
630
1/48двое суток
721
1/72трое суток
778

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የእግዚአብሔር ምሕረት ዛሬ ብቻ የሚያኖርህ አይደለም፤ ለዘላለም የሚፀና ምሕረት ነው። እስቲ ወደ ኋላ ተመልከት፤ ከየት እንዳወጣህ፣ ከስንት ነገር እንደጠበቀህና ዛሬ እዚህ እንዳደረሰህ አስብ። የትናንቱ ምሕረት ዛሬም አለ፤ ነገም ምህረቱ አያልቅም። ስለዚህ ዛሬ በምህረቱ ሀሴት አድርግ፤ በምስጋና የእግዚአብሔርን ታማኝነት ለትውልድ ንገር! መዝሙር 89:1 አቤቱ፥ ምሕረትህን ለዘላለም እዘምራለሁ፥ እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • የእግዚአብሔር ምሕረት ወሰን የለውም። ሰው ሊለካው የማይችለው ያህል ሰፊ፣ የማያልቅ ነው። ምሕረቱ በሰማይ ነው፣ የእግዚአብሔር ቸርነት ከምትገምተው በላይ ሰፊ ነው። ዛሬ ያለህበት ሁኔታ ምንም ይሁን፣ የእግዚአብሔር ምሕረት አይቀንስም። በድካምህ ይደግፍሃል፣ በውድቀትህ ያነሳሃል፣ በመከራህም ያጽናናሃል። ሁኔታዎች ቢለዋወጡም እርሱ ግን ታማኝ ነው። ምሕረቱ ከአንተ ጋር ነው። ስለዚህ በሁኔታህ ሳይሆን በእርሱ ታማኝነት ታመን። ዛሬም በእግዚአብሔር ምሕረት እረፍ፤ እርሱ አይተውህም። አቤቱ፥ ምሕረትህ በሰማይ ነው፥ እውነትህም ወደ ደመናት ትደርሳለች። መዝሙረ ዳዊት 36:5 #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • እግዚአብሔር የማይለወጥ ህያው አምላክ ነው። እርሱ ቃሉን የሚጠብቅ፣ ቃል ኪዳኑን የማይረሳ እና ምሕረቱን የማያቋርጥ ታማኝ አምላክ ነው። ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ነው። ሰው ቃሉን ሊረሳ ይችላል፤ እግዚአብሔር ግን የተናገረውን አይረሳም። ሰው ቃል ኪዳኑን ሊያፈርስ ይችላል፤ እርሱ ግን በቃሉ የፀና አምላክ። ምናልባት ዛሬ እግዚአብሔር የገባልህን ቃል እየጠበቅህ ይሆናል። ጸሎትህ መልስ ያላገኘ ሊመስልህ ይችላል፤ የምትጠብቀውም ነገር የዘገየ ሊመስልህ ይችላል። እግዚአብሔር የሚሰራበት ጊዜ አለው፤ ቃሉንም ደግሞ በጊዜው ይፈጽማል። እርሱ ትናንት ታማኝ እንደነበረ ዛሬም ታማኝ ነው፤ ነገም በታማኝነቱ ፀንቶ ይኖራል። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • ይህ ቃል ለዛሬም ታላቅ ተስፋ ነው። እግዚአብሔር የሚናገረውን አይረሳም፤ የሚሰጠውን ተስፋም አይተወውም። ሁኔታዎች ሊቀየሩ፣ መንገዱም ከጠበቅከው በላይ ሊረዝም ይችላል፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል አይለወጥም። ምናልባት ዛሬ እየጠበቅከው ያለ መልስ፣ እየጸለይክለት ያለ ጉዳይ ወይም እግዚአብሔር የሰጠህ ተስፋ ሊኖር ይችላል። እርሱ በጊዜው የሚያደርገውን ያውቃል። የጀመረውንም መልካም ሥራ እስከፍጻሜው ያደርሳል። እርሱ የተናገረው መልካም ነገር አንድም ሳይቀር ይፈጽማል። ኢያሱ 21:45 እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • እግዚአብሔር እንደ ሰው አይደለም። እርሱ ታማኝ ነው፤ ባሕርዩም አይለወጥም። ይህ ቃል በድካምህ መካከል ታላቅ መጽናናት ይሰጥሀል። እምነትህ ሊደክም ይችላል፤ ነገር ግን የአንተ ድካም የእግዚአብሔርን ታማኝነት አይለውጠውም። አንተ በእርሱ ላይ ልትደገፍ በማትችልበት ጊዜ እንኳን፣ እርሱ አንተን ለመደገፍ ታማኝ ነው። ምናልባት ዛሬ የምትጠብቀው መልስ ዘግይቶ ይሆናል፤ ወይም የምትጸልይለት ነገር እንደምትፈልገው መልስ እያገኘህበት አይደለም ይሆናል: እግዚአብሔር ግን አልተለወጠም። እርሱ በጊዜው የሚሠራ ታማኝ አምላክ ነው። ስለዚህ ዛሬ እምነትህ ቢደክምም፣ በእግዚአብሔር ታማኝነት ላይ ተደገፍ። ሁኔታውን ሳይሆን እርሱን ተመልከት። የተናገረውን አይረሳም፤ የጀመረውን አይተወውም፤ ራሱንም ሊክድ አይችልም። ዛሬ በዚህ እውነት እረፍ፣ እርሱ አይለወጥም። እርሱ ታማኝ ሆኖ ይኖራል። 2 ጢሞቴዎስ 2:13 ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።” #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 7 авг.1 1713110

    እግዚአብሔር በአንተ የጀመረውን ሥራ ይፈጽመዋል! መንፈሳዊ ጉዞህ የሚጀመረው በራስ ጥረት አይደለም። በአንተ ውስጥ መልካምን ሥራ የሚጀምረው እግዚአብሔር ነው። በእርሱ ስታምን፣ በየቀኑ ክርስቶስን እንድትመስል እየቀረጸህና እያሳደገህ ይመራሃል። ምናልባት ዛሬ በሕይወትህ እግዚአብሔር ሚሰራውን ሙሉ በሙሉ ማየት አትችል ይሆናል። እምነትህ ሊፈተን ይችላል: ነገር ግን ተስፋ አትቁረጥ፤ በአንቱ ስራን የጀመረው እግዚአብሔር እስከ ፍጻሜው ድረስ ታማኝ ነው።እግዚአብሔር በቃሉና በመንፈሱ እየመራህ፣ እያስተማረህ፣ እያሳደገህ እና ወደ እርሱ እያቀረበ ይመራሃል። በአንተ የጀመረውን መልካም ሥራ በታማኝነት ይፈጽመዋል። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 6 авг.1 228222

    ያለህበት ዓለም፣ ሁኔታዎች እና ሰዎች ሊለዋወጡ ይችላሉ። ዛሬ ያለው ነገ ላይኖር ይችላል፤ የምትመካባቸው ነገሮችም ሊቀየሩ ይችላሉ። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጽሞ አይለወጥም። ትናንት የነበረው ታማኝ ማንነቱ፣ ፍቅሩ፣ ጸጋው እና ኃይሉ ዛሬም ያው ነው፤ ነገም እንደዚያው ይኖራል፤ እስከ ለዘላለምም አይለወጥም። ይህ ለአንተ ታላቅ መጽናናት ነው። ስትጨነቅ፣ ስትፈራ፣ ወይም ስትደክም እንኳ፣ ታማኝ የሆነው ጌታ ኢየሱ አይለወጥም። ትናንት የረዳህ እርሱ ዛሬም ከአንተ ጋር ነው፤ ነገህንም በታማኝነቱ ይመራሀል። ትናንት ሕያው የነበረው ጌታ ዛሬም ሕያው ነው፤ ለዘላለምም ይኖራል። ስለዚህ ዛሬ ከሚለዋወጡ ሁኔታዎች ይልቅ በማይለወጠው ኢየሱስ ላይ ታመን። እርሱ የተስፋህ መሠረት፣ የኃይልህ ምንጭ እና የሕይወትህ ታማኝ ጌታ ነው። ዕብራውያን 13:8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 5 авг.1 311305

    እግዚአብሔር ሁልጊዜ ቸር ነው። የእርሱ ቸርነት በሁኔታዎቻችን አይለወጥም፤ በችግርም ሆነ በደስታም ሆነ በድካም እርሱ ያው ቸርና ታማኝ አምላክ ነው። ስለዚህ ምስጋናህ በምን አገኘሁ፣ በምንሆነልኝ ፣ ላይ ሳይሆን: እግዚአብሔርን ብቻ በመታመን ላይ የተመሠረተ ይሁን። እርሱ ቸር ነው፤ ምሕረቱም ለዘላለም ነው። ዛሬ የምትተነፍሰው እስትንፋስ፣ ያለህ ተስፋ፣ የተቀበልከው ምህረት እና በየቀኑ የምትለማመደው ቸርነቱ ሁሉ የእርሱ ስጦታ ነው። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 3 авг.1 517258

    አዲስ ሳምንት ስትጀምር፣ እንደ እቅድህ ላትውል ትችላለህ። እቅዶች ሊቀየሩ፣ ሁኔታዎች ሊለዋወጡ፣ ያልጠበቅኸውም ነገር ሊያጋጥምህ ይችላል። ነገር ግን ከሁሉ በላይ የማይለወጥ አንድ እውነት አለ! የእግዚአብሔር ቸርነት እና የሰላሙ ቃል ኪዳን ፈጽሞ አይለወጡም። እግዚአብሔር “ተራሮች ቢፈልሱ፣ ኮረብቶችም ቢወገዱ እንኳ፣ ቸርነቴ ከአንተ ዘንድ አይፈልስም፤ የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም” ይላል። ይህ የሚያስታውስህ ደግሞ: የሕይወት ሁኔታዎች ቢለዋወጡም እግዚአብሔር ግን ያው ታማኝ፣ ያው መሐሪ፣ ያው አፍቃሪ አባት መሆኑን ነው!። ስለዚህ ይህን ሳምንት በፍርሃት ሳይሆን በእምነት ጀምር። በሚለዋወጡ ሁኔታዎች ላይ ሳይሆን: በማይለወጠው አምላክ ላይ ተደገፍ። የእርሱ ቸርነት ይመራሃል፣ የሰላሙም ቃል ኪዳን ልብህን ያጸናል። የዚህን ሳምንት ሁሉን እቅድህን ለእርሱ አደራ ስጥ፤ እርሱ ታማኝ ነው። ኢሳይያስ 54:10 ተራሮች ይፈልሳሉ፥ ኮረብቶችም ይወገዳሉ፤ ቸርነቴ ግን ከአንቺ ዘንድ አይፈልስም የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም፥ ይላል መሐሪሽ እግዚአብሔር። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 30 июл.1 774277

    በሕይወትህ ውስጥ ጭንቅና መከራ የሚያጋጥም ቢሆንም፣ ከእነዚህ ሁሉ የሚበልጥ ግን የማይናወጥ ተስፋ አለ። ይህ ተስፋ በሁኔታዎች ወይም በሰዎች ላይ የተመሠረተ ሳይሆን፣ በመልካሙና በታማኙ አምላክ ላይ የተመሠረተ ነው። እግዚአብሔር በመከራ ወቅት የምትሸሽበት መሸሸጊያ፣ የምትደገፍበት አለት እና የማይፈርስ ምሽግ ነው። “በእርሱ የሚታመኑትን ያውቃል” የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ታላቅ ማጽናኛ ነው። እርሱ የልብህን ህመም፣ የምታልፍበትን ፈተና እና የምትፈራውን ሁሉ ያውቃል። ስለዚህ ዛሬ በማንኛውም ጭንቀት ውስጥ ብትሆን፣ ወደ እርሱ ቅረብ። እርሱ የማይሰበር መሸሸጊያህ፣ የማይናወጥ ተስፋህ እና የማይጥልህ አምላክ ነው። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 29 июл.1 675182

    እግዚአብሔር የምሕረት ምንጭ ነው። እርሱ መሓሪ፣ ይቅር ባይ እና በፍቅር የተሞላ አባት ነው። በቅን ልብ የሚጠሩትን ፈጽሞ አይጥላቸውም፤ በፍቅር ይቀበላቸዋል፣ በምሕረቱም ይቅር ይላቸዋል። የእግዚአብሔር ይቅርታ በኃጢአትህ ብዛት አይለካም፤ በማይለወጥ ቸርነቱና በታላቅ ምህረቱ እንጂ። እግዚአብሔር ወደ እርሱ የሚመለስን ልብ ሁልጊዜ ይቅር ይላል። በንስሐና በቅን ልብ ወደ እርሱ ስትመጣ አይጥልህም፤ ይቀበልሃል፣ ያነጻሃል፣ አዲስ ተስፋም ይሰጥሃል። ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ፤ ምሕረቱን ፈልገህ ወደ እርሱ መሮጥ ያስፈልግሃል። እርሱ የተሰበረን ልብ አይንቅም፤ የሚጠሩትንም በምሕረቱ ይመልሳል። መዝሙር 86:5 አቤቱ፥ አንተ መሓሪና ይቅር ባይ ነህና፥ ምሕረትህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 28 июл.1 701283

    የእግዚአብሔር ምሕረት በሕይወት የምትቆምበት መሠረት ነው። ዛሬ በህይወት ያለኸው፣ አዲስ ቀን ማየትህ በእርሱ የማያልቅ ርኅራኄ እንጂ በራስህ ብቃት አይደለም። በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቅርና ምሕረት አዲስ ሕይወት እና ዘላለማዊ ተስፋ ይሰጥሃል። ሰቆ ኤርምያስ 3:22 ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 23 июл.1 998277

    የእግዚአብሔር ቸርነት ለሰው ሁሉ የተዘረጋ ነው። እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ምሕረቱም በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ነው። ፀሐይን በጻድቃንና በኃጢአተኞች ላይ እንደሚያበራ፣ ዝናቡንም በሁሉ ላይ እንደሚያዘንብ፣ ቸርነቱም በየቀኑ በሕይወትህ ይገለጣል። ከሁሉ የሚበልጠው የእግዚአብሔር ቸርነት ደግሞ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጧል። በእርሱ ኃጢአትህን ይቅር አለህ፣ አዲስ ሕይወትንም ሰጠህ፣ ከእርሱ ጋርም ዘላለማዊ ተስፋ ሰጥቶሀል። ዛሬም የእግዚአብሔር ቸርነት ከአንተ አልራቀም። በእርሱ ታመን፣ እርሱ ቸር ነው፤ ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው። መዝሙር 145:9 እግዚአብሔር ለሚታገሡት ቸር ነው። ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 21 июл.1 956275

    የምስጋና ትልቁ ምክንያት እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ማወቅ ላይ ነው። እርሱ ቸር ነውና! እግዚአብሔር ዛሬም ቸር ነው:ነገም ቸር ነው: ለዘላለምም ቸር ነው። ምሕረቱ በውድቀትህ አያበቃም፣ ፍቅሩም በድካምህ ወቅት አይቀንስም። በየቀኑ በጸጋው ይደግፍሀል፣ በታማኝነቱም ይመራሀል። የእግዚአብሔር ቸርነት ከሁኔታዎችህ በላይ ነው። ቸርነቱ አያልቅም፣ ምሕረቱም ለዘላለም ይኖራል። ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ። መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 16 : 34 #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 20 июл.1 809196

    የእግዚአብሔር ቸርነት ጊዜያዊ አይደለም፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ከአንተ ጋር የሚዘልቅ የማይቋረጥ በረከት ነው። ዳዊት “ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል” ሲል የተናገረው፣ በሁሉም ወቅት: በደስታም ሆነ በመከራ እግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ እንደሚጠብቀው በመተማመን ነው። የዚህ ተስፋ ፍጻሜም ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ዘላለማዊ ኅብረት ነው። “በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ” የሚለው ቃል፣ የእርሱ ቸርነት እስከ ዘላለም የሚዘልቅ መሆኑን ያስረዳሀል። ይህ ተስፋ እና ይህ ሕይወት የሚገኘው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። እርሱን የሕይወትህ ጌታና አዳኝ አድርገህ ስትቀበለው፣ የአሁኑንም ሆነ የዘላለም ሕይወትህን ይለውጣል። ዛሬ ይህን ውሳኔ ብትወስን፣ በእግዚአብሔር ቤት ለዘላለም ትኖራለህ። መዝሙር 23:6 ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 16 июл.2 109248

    የእግዚአብሔርን ቸርነት መረዳት የምትችለው እርሱን በማወቅ፣ ወደ እርሱ በመቅረብ እና ፍቅሩን በሕይወትህ በመለማመድ ነው። ይሄን የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕይወትህ ልትቀምሰው ይገባል። ለዚህም ህይወት ደግሞ እግዚአብሔር እንድትቀርበው፣ በእርሱ ብቻ እንድትታመን እና ቸርነቱን በየቀኑ እንድትለማመድ ይፈልጋል። እግዚአብሔርን የሚታመኑ ሰዎች ቸርነቱን በየቀኑ ያያሉ፣ በድካማቸው ኃይልን፣ በጭንቀታቸው ሰላምን፣ በችግራቸው መፍትሔን ያገኛሉ። አንተም በሁሉም ሁኔታ ታማኝ በሆነው እግዚአብሔር መታመን ዛሬ ጀምር፤ ቸርነቱን በሕይወትህ ትቀምሰዋለህ፣ ከእርሱ ጋር ያለውንም ድንቅ ሕይወት ትለማመዳልህ። መዝሙር 34:8 እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 15 июл.1 892295

    የእግዚአብሔር ላንተ ያለው ፍቅር ቅድመ ሁኔታ የሌለው፣ ዘላለማዊ እና ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን እስከ መስጠት የደረሰ ፍቅር ነው። ይህን ፍቅር በመልካምነትህ ወይም በሥራህ አላገኘኸውም፤ በእግዚአብሔር ጸጋ በነፃ የተሰጠህ ስጦታ ነው። ፍቅር አንተ እርሱን እንደወደድከው አይደለም፤ እርሱ አስቀድሞ እንደወደድህ ነው። አንተ ገና ኃጢአተኛ ሳለህ፣ ክርስቶስ ስለ አንተ ሞቶ የእግዚአብሔርን ፍቅር ገልጦልሀል። እግዚአብሔር አስቀድሞ ወዶሃል። ፍቅሩ አይለወጥም፣ አያልቅም፣ ዘላለማዊ ነው። ይህን ያለ ምክንያት የተሰጠህን ፍቅር ስትረዳ፤ ሰዎችንም በዚያው ፍቅር መውደድ ትችላለህ። ዛሬ ለዚህ ድንቅ ፍቅር ምላሽ ትሰጣለህ? እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:19 #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 14 июл.2 106285

    የሰው ልጅ እውቀት እና ግንዛቤው ውስን በመሆኑን በራስህ መደገፍ የለብህም:: ለዚህም ነው እግዚአብሔርን መታመን እርሱ ፍጹም በሆነ እቅድ እንደሚመራህ በማወቅ እርግጠኛ መሆን የምትችለው። በዚህ አድካሚ የህይወት ጉዞ ዝለሃል? እንግድያውስ ለዚህ ሁሉ መፍትሄ የሚሆነውን ልንገርህ፤ የራስህን ውስን የሆነ ማስተዋል መተው!በእግዚአብሔር መታመን፤ ጥቂት በሆነው በገዛ ማስተዋል መባዘኑን ትተህ፤ ፍጹም በሆነው በእግዚአብሔር ማስተዋል ላይ ተደገፍ። እርሱ ያሳርፍሀል:: በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤” — ምሳሌ 3፥5 #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 13 июл.1 864215

    እግዚአብሔር እርሱ መሐሪ፣ ሞገስ ያለው፣ ታጋሽ፣ በቸርነትና በእውነት የተሞላ አምላክ ነው። ዛሬ በድክመት ምክንያት እግዚአብሔር ርቀህ ይሆን? እርሱ ለንስሐ የሚጠራ፣ የሚቀበል፣ የሚምር እና በፍቅሩ የሚያቆም አባት ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት ከውድቀትህ ይበልጣል፣ ምሕረቱም ከኃጢአትህ ይበልጣል። ወደ እርሱ ስትቀርብ በምህረት ይቀበልሃል። ዘጸአት 34:6 እግዚአብሔርም በፊቱ አልፎ፡— “እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥ #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads

  • 9 июл.2 084352

    የእግዚአብሔር ባሕርይ ፈጽሞ አይለወጥም። እርሱ ሁልጊዜ ቸር፣ ምሕረቱ የማያልቅ፣ በቃሉም የታመነ አምላክ ነው። ሰዎች ሊለወጡ ይችላሉ፤ ሁኔታዎችም ሊቀየሩ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን በቸርነቱና በታማኝነቱ ፈጽሞ አይለወጥም። ምሕረቱ ለዘላለም ይኖራል። እውነቱና ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይቀጥላል። ከጥንት ጀምሮ ታማኝ የነበረው አምላክ ዛሬም በአንተ በሕይወትህ ታማኝ ነው። እግዚአብሔር ቸር፥ ምሕረቱም ለዘላለም፥ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና። - መዝሙረ ዳዊት 100:5 #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads