- Последний пост
- 13 июл.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 51
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
እግዚአብሔር እርሱ መሐሪ፣ ሞገስ ያለው፣ ታጋሽ፣ በቸርነትና በእውነት የተሞላ አምላክ ነው። ዛሬ በድክመት ምክንያት እግዚአብሔር ርቀህ ይሆን? እርሱ ለንስሐ የሚጠራ፣ የሚቀበል፣ የሚምር እና በፍቅሩ የሚያቆም አባት ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት ከውድቀትህ ይበልጣል፣ ምሕረቱም ከኃጢአትህ ይበልጣል። ወደ እርሱ ስትቀርብ በምህረት ይቀበልሃል። ዘጸአት 34:6 እግዚአብሔርም በፊቱ አልፎ፡— “እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥ #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
(#Singer Teddy Tedesse) sʜᴀʀᴇ 🎁ᴊᴏɪɴ 🎁 sʜᴀʀᴇ @protestant_worships @protestant_worships
ለ 12 ተፈታኞች ✅ የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ለምትቀመጡ ተማሪዎች በሙሉ መልካም የፈተና ጊዜ እመኛለሁ! አላማችሁ እንዲሳካ #እግዚአብሔር ይርዳችሁ።🤞🤞 Wishing all Grade 12 students the best of luck!🤞🤞 #natu_fk
(#Singer Yohannis Girma) sʜᴀʀᴇ 🎁ᴊᴏɪɴ 🎁 sʜᴀʀᴇ @protestant_worships @protestant_worships
በቅንነት መመላለስ፣ እግዚአብሔርን በሙሉ ልብ መውደድ፣ በቃሉ መመላለስ እና ፈቃዱን ለመፈጸም መኖር ማለት ነው። እንዲህ ያለ ሕይወት በእግዚአብሔር ሞገስና በረከት ውስጥ ያኖራል። በዚህ ዘመን ብልጠትና ማታለል ስኬት የሚያመጡ የሚመስሉ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ግን የቅን ሰውን መንገድ ይባርካል። የእርሱ በረከት የሚያመጣው እውነተኛ እርካታ ነው። ዛሬ በእግዚአብሔር ላይ ታመን፤ በቅንነትም ተመላለስ። እርሱ ሞገሱን ይሰጥሃል፣ በረከቱንም ያበዛልሃል፤ ከመልካም ነገርም አያሳጣህም። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
(#Singer Tekeste Getnet) sʜᴀʀᴇ 🎁ᴊᴏɪɴ 🎁 sʜᴀʀᴇ @protestant_worships @protestant_worships
ዳዊት በዘመኑ ሁሉ የእግዚአብሔርን ታማኝነት እንዳየ መስክሯል። ጻድቅ ሲጣል ወይም ዘሩ እህል ሲለምን አላየሁም የሚለውም፣ እግዚአብሔር ለሚታመኑበት ሰዎች ታማኝ አቅራቢ እንደሆነ እየመሰከረ ነው። ዛሬ በሕይወት ጉዞህ እየታገልክ ከሆነ፤ እግዚአብሔር ያይሃል፣ አይጥልህም፣ ይደግፍሃል፣ አይተውህምም። እርሱ ከትውልድ እስከ ትውልድ ታማኝነቱን የሚገልጥ፣ እስከ እርጅና ድረስ የሚሸከም ቸር አምላክ ነው። በእግዚአብሔር መንገድ ለሚሄዱ ለእነርሱም ሆነ ለዘሮቻቸው የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ የሚያሟላላቸው እግዚአብሔር ብቻ ነው። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
በብዙ ነገር ባለጠጋ የሚመስሉ ሰዎች እንኳ አንድ ቀን ጉድለት እና ማጣት ሊያጋጥማቸው ይችላሉ። የዓለም ነገር ሁሉ ዘላቂ አይደለም፤ እግዚአብሔር ብቻ የማያልቅ ታማኝ ምንጭ ነው። እግዚአብሔር ለልጆቹ የሚያደርገው ሁሉ መልካም ነው። የሚያስፈልግህን ሁሉ በጊዜው ያቀርብልሃል። ዛሬ ሁኔታዎች ቢከብዱም፣ ልብህን በእግዚአብሔር ላይ አድርግ። እርሱን በእውነተኛ ልብ ስትፈልገው፣ ከሚያስፈልግህ ነገር ሁሉ አትጎድልም። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
እግዚአብሔር ሁልጊዜም ልጆቹን በእውነተኛ መንገድ ይመራል፣ ይጠብቃል፣ ይንከባከባልም። እርሱ ሲመራ በትክክለኛው እና ጥፋት በሌለበት መንገድ ብቻ ነው። አንዳንድ ጊዜ የሚያስፈልግህን ነገር በማጣት ምክንያት ልትጨነቅ ትችላለህ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር እረኝነት ውስጥ እውነተኛ ሙሉነት እና ማረፍ አለ። እርሱ ሕይወትህን በሚያስፈልግህ ነገር ሁሉ ይሞላዋል። ዛሬ እግዚአብሔርን እንደ እረኛህ አምነኸው ተከተለው፤ በእርሱ ውስጥ ሙሉ እርካታ ታገኛለህ። እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙረ ዳዊት 23 : 1 #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
ብዙ ጊዜ በሕይወትቴ ምን ያስፈልገኛል? የሚለው ሀሳብ ልብህን ሊያስጨንቅህ ይችላል: ኢየሱስ ግን ቅድሚያህ ምን መሆን እንዳለበት በግልጽ ይነግርሀል። ከሁሉ አስቀድመህ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ስትፈልግ፣ ሕይወትህን ለእርሱ ፈቃድ ስታስገዛ እና ፈቃዱን ብቻ ስትከተል፣ እርሱ የሚያስፈልግህን ሁሉ ያሟላልሀል። እግዚአብሔር በሕይወትህ ቀዳሚ ሲሆን፣ ነገርን ሁሉ በጊዜው ያዘጋጃል። ማቴዎስ 6:33 ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
እግዚአብሔር ሁልጊዜም ልጆቹን በእውነተኛ መንገድ ይመራል፣ ይጠብቃል፣ ይንከባከባልም። እርሱ ሲመራ በትክክለኛው እና ጥፋት በሌለበት መንገድ ብቻ ነው። አንዳንድ ጊዜ የሚያስፈልግህን ነገር በማጣት ምክንያት ልትጨነቅ ትችላለህ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር እረኝነት ውስጥ እውነተኛ ሙሉነት እና ማረፍ አለ። እርሱ ሕይወትህን በሚያስፈልግህ ነገር ሁሉ ይሞላዋል። ዛሬ እግዚአብሔርን እንደ እረኛህ አምነኸው ተከተለው፤ በእርሱ ውስጥ ሙሉ እርካታ ታገኛለህ። እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙረ ዳዊት 23 : 1 #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
Tesfa event pinned a photo
እግዚአብሔር የልጆቹን ፍላጎት የሚያውቅ እና የሚያሟላ ቸር አባት ነው። የሰው ልጅ የሚያስፈልገው ነገር ሲጎድልበት ሊጨነቅ፣ ተስፋ ሊያጣ ይችላል: ነገር ግን ተስፋውን በሰዎች ወይም በሁኔታዎች ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ያደረገ ሰው እነዚህ ነገሮች እያሰጉትም። እግዚአብሔር ከማያልቀው ሀብቱ የሚያስፈልግህን ሁሉ ያሟላልሀል። እግዚአብሔር የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ሳይሆን፣ በሕይወትህ ለሚያስፈልግህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ሊያደርግልህ ታማኝ ነው። እርሱ ፈጽሞ አይተውህም፣ አያሳፍርህምም። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
ታስፈልገኛለህ.... ታስፈልገኛለህ..... (#sɪɴɢᴇʀ_ᴀᴅɪsᴀʟᴇᴍ_ᴀsᴇғᴀ) sʜᴀʀᴇ 🎁ᴊᴏɪɴ 🎁 sʜᴀʀᴇ ♻️@protestant_worships ♻️@protestant_worships
እየጠበኩት ጌታ ድንገት ይመጣ (#sɪɴɢᴇʀ_ᴀᴅɪsᴀʟᴇᴍ_ᴀsᴇғᴀ) sʜᴀʀᴇ 🎁ᴊᴏɪɴ 🎁 sʜᴀʀᴇ ♻️@protestant_worships ♻️@protestant_worships
(#illasha_Fekadu) sʜᴀʀᴇ 🎁ᴊᴏɪɴ 🎁 sʜᴀʀᴇ ♻️@protestant_worships ♻️@protestant_worships
ከሰው ድካም የእግዚአብሔር ምሕረት እጅግ ያይላል። አንዳንድ ጊዜ በድካምህ ምክንያት ወድቀህ ልትቀር፣ በኃጢአትም እንደተሸነፍክ እና እጅ እንደሰጠህ ሊሰማህ ይችላል ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋ ከድካምህ ይበልጣል። ነገር ግን ኃጢአት ሊያሸንፍህ ቢሞክርም፣ ወደ እግዚአብሔር በንስሐ ብትመጣ እርሱ ይቅር ይልሀል፣ ያነጻሀል፣ እንደገናም በምህረት ያቆምሀል። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
📣#በቤተክርስቲያን ውስጥ መደረግ የሌለባቸው #11 ወርቃማ ህጎች ቤተክርስቲያን #የእግዚአብሔር_ቅዱስ_ስፍራ_ነው፣ በቤቱ ስርአትና አክብሮት ሊኖር ይገባል! 1. #ፕሮግራም_አታርፍድ ⏰ እግዚአብሔር ለቀጠሮው አይዘገይም፤ አንተስ ለምን ታረፍዳለህ? በጊዜ መገኘት በረከትን ቀድሞ መቋደስ ነው። 📖 "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ" (መዝሙር 122:1) 2. #ድምፅህን_ጠብቅ፤ አታውራ 🗣️ በአምልኮና በትምህርት ሰዓት ወሬና ጨዋታ ለእግዚአብሔር ቤት አይመጥንም። ስፍራው የዝምታና የጸሎት ነው። 📖 "ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌሶን 4:29) 3.#ስልክህን_እረፍት_ስጠው 📱 በስብከት ወቅት ሶሻል ሚዲያ መጠቀምና ስልክ መነካካት መንፈሳዊ ትኩረትን ይሰርቃል። ስልክህ ሲደወልም አንስተህ አታውራ፤ ቅዱሱን ድባብ አታናጋ። 📖 "በላይ ያለውን አስቡ" (ቆላስይስ 3:2) 4. #አለባበስህ_ስርአት_ይኑረው 👗 ሰውነትን ገልጦ የሚያሳይና#ሌሎችን _ለፈተና የሚዳርግ አለባበስ ከቤተክርስቲያን ቅድስና ጋር አይሄድም። ይህ ወንዶችንም ይመለከታል። 📖 "ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን" (1 ቆሮንቶስ 14:40) 5. #አትተኛ፤ ንቃ! 😴 ቤተክርስቲያን የመንፈስ መታደሻ እንጂ መኝታ ቤት አይደለችም። ንቁ ሆነህ ቃሉን ተከታተል። 📖 "አንተ የምትተኛ ንቃ..." (ኤፌሶን 5:14) 6. #ተመልካች_ብቻ_አትሁን፤ በመንፈስ ተሳተፍ 👀🔥 ሌሎች ሲያመልኩና በረከት ሲቀበሉ አንተ ዝም ብለህ አትመልከት። ዘምር፣ አምልክ፣ ስገድ፤ በመንፈስና በእውነት ከፈጣሪህ ጋር ተገናኝ። 📖 "እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።" (ዮሐንስ 4:24) 7. #ቂም_ይዘህ_አትቆም_ቂም_ይዘህ አትጸልይ! ልብህ በቂምና በነገር ተሞልቶ አምልኮ የለም። አስቀድመህ ለበደሉህ ይቅርታ አድርግ፤ በንጹህ ልብም ፊትህ ቁም። 📖 "አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ" (ማቴዎስ 5:24) 8. #ተስፋ ሰንቀህ ቅረብ ከእግዚአብሔር እጅ አንድ ነገር እንደምትቀበል አምነህ ሂድ። የምትጠብቀው ነገር ከሌለ የምታገኘውም አይኖርም። 📖 "አፍህን በሰፊው ክፈት እኔም እሞላዋለሁ" (መዝሙር 81:10) 9. #አገልጋዮችን _አታቅልል 🙅♂️ ከአገልጋዮች ጋር ባለህ መቀራረብ የተነሳ ቅጥ የሌለው ድፍረት አታሳይ። የእግዚአብሔርን ቅቡዓን ማክበር ለራስህ ስኬት መቆለፊያ ነው። 📖 "የቀባሁትን አትንካ" (መዝሙር 105:15) 10.# ለዲያቆናትና ለአገልጋዮች ታዘዝ 🙏 ዲያቆናት የሚተጉት ስርአትን ለማስጠበቅና አንተን ለማገልገል ነው። ትህትናንና ትብብርን አሳያቸው። 📖 "ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ..." (1ኛ ጴጥሮስ 2:17) 11. #ፕሮግራም ሳያልቅ አትውጣ በጸሎትና በስብከት መሃል ጥሎ መውጣት ስርአተ አልበኝነትና ሌላውን መረበሽ ነው። እስከ መጨረሻው ታግሰህ በረከቱን ይዘህ ውጣ። 📖 "ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ" (መክብብ 5:1) sʜᴀʀᴇ 🎁ᴊᴏɪɴ 🎁 sʜᴀʀᴇ ♻️ @Truthofpath ♻️ @Truthofpath
እግዚአብሔር የልብን ጸሎት የሚሰማ የቅርብ አምላክ ነው። በምንም አይነት ሁኔታ ብትሆን እንኳን በቅን ልብ ወደ እርሱ ብትጮህ ይሰማሃል። ዛሬ ያለብህን ሸክም፣ ጭንቀት እና ሀዘን ሁሉ ለእግዚአብሔር ንገረው: እርሱ ጩኸትን የሚሰማ፣ ጸሎትንም የሚመልስ ታማኝ አምላክ ነው። አቤቱ፥ ጽድቄን ስማ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በተንኰለኛም ከንፈር ያልሆነውን ጸሎቴን አድምጥ። - መዝሙረ ዳዊት 17:1 #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads
የክርስቶስ ሰላም ችግር፣ ጭንቀት፣ ፍርሃት ወይም ግራ መጋባት ሲግጥምህ የሚመራህ እና የሚያሳርፍህ ነው። ዛሬ ልብህን የሚገዛው ፍርሃት ነው ወይስ የክርስቶስ ሰላም? እግዚአብሔር ወደ ሰላም፣ ወደ አንድነት እና ወደ ምስጋና ህይወት ጠርቶሀል። ሁኔታዎችህ ምንም ቢሆኑ፣ የክርስቶስ ሰላም ሁሉን አልፎ ልብህን በሰላሙ ይገዛዋል። ቆላስይስ 3:15 በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ። የምታመሰግኑም ሁኑ። #tesfa #hope Follow Tesfa on: Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads