ብርሃን ይኹን💡
Статистикаብርሃን ይኹን መጽሐፍ ቅዱስን በተለያዩ መንገዶች በማድረስ ሰዎችን ኹሉ ክርስቶስን ወደ መምሰል ሕይወት እንዲጠጉ የሚያግዝ ክርስቲያናዊ አገልግሎት ነው። Facebook page link https://www.facebook.com/berhanyihunofficial/ Instagram link https://www.instagram.com/berhan_yihun/
- Последний пост
- 30 июл.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 136
- 1/48двое суток
- 155
- 1/72трое суток
- 168
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
https://youtu.be/ZoMT2fqnQyM?si=zNJIH9UHbHqX4Y0K
https://youtu.be/N_laZMxbHMU?si=mSr04LJexTrSTmwL
https://youtu.be/m4CuRYHvkTI?si=c8cHe8u2HnKZW32J
The hole in our Holiness, Kevin D. Young
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየቸገረህ ያለው ብትሉኝ አቋም በሚፈልጉ ግልጽ ጉዳዮች ላይ ሆነ ብለው አቋም ላለመያዝ አቋም የያዙ ሰዎች! እጃቸውን ዘርግተው ማትጨብጧቸው Ghost የሆኑ፤ መስመር የሌላቸው ሰዎች አሉ። ከቅርብ ጊዜ የመጣው አዲሱ ስትራቴጂ፤ አቋም ሳይይዙ መንሳፈፍ ነው። ለምን? ሁሉም ቤት ጣሪያ ላይ ማረፍ ያስችላል። ለዛ አዋጭ ነው። A ም ነኝ ደግሞም Z ም ነኝ። ከዚህ ከ A ጋር ፀብ የለም ከ Z ም ጋር ፀብ የለም፤ የሁሉም ወዳጅ ሆናችሁ መሄድ ከፈለጋችሁ፤ መንገዱ ውስብስብ አይደለም፤ አቋም አይኑራችሁ። በሁሉም ቤት አባወራ ላይ ዘፍ የሚል አሞራ ነው ምትሆኑት። መንፈሳዊ ብስለት ወንድሞቼ እህቶቼ፤ ተንሳፋፊ አያደርግም። በዶክትሪን ግንባታ ውስጥ አልፎ ማደግ አቋም የለሽ አማኝ አያደርግም። ተፍገምጋሚ ተንገዋላይ አያደርግም። እንደዛ የሚያደርግም አስተምህሮአዊ ምክር ቅዱሳት መጻሕፍት የላቸውም። የእግዚአብሔር ቃል ምክር የሐዋርያት ትምህርት እርስ በእርስ ፈጽሞ የማይጣጣሙ የተቃረኑ ስድስት እና ሰባት አቋሞች ውስጥ እንዲሁ እየፈሰሳችሁ እንድትሄዱ የሚፈቅድ ምክር የላቸውም። ጤናማ ዶክትሪን እንደ መልህቅ ይይዛል። አንዴ ወደ ፊት አንዴ ወደ ኋላ አያስኬድም። ወዲያና ወዲህ አቅጣጫ የለም! ፖዚሽን የለም! ግራውንድ የለም! እንደሱ የሚያደርግ የአስተምህሮ አቀራረጽ የለም። ጤናማ ዶክትሪን እንደዚህ አያደርግም። በአስተምህሮ መሬት የረገጠ ሰው ጽኑ ነው። ሀሰት ከየትም ይምጣ ከየትም አያፍገመግመውም። ከሁሉም ጋር ጎረቤት አይደለም! ቢቻላችሁ ነው ከሰው ጋር በሰላም ኑሩ የተባለው ስለማይቻል ነው። ከቻላችሁ ጥሩ፤ ግን አይቻልም። ሐዋርያትን ወንጌል ከሁሉም ሰው ጋር ሲያወዳጃቸው አናይም ። ዘመዳቸው ከቃሉ ጋር ዘመድ የሆነ ሰው ነው። ከቃሉ ጋር በግልጽ ጠብ የወጣን ሰው ጎረቤት የሚያደርግ አስተምህሮ ቀረጻ ብሎ ታሪክ የለም። ለምን የሰማይ ስባሪ አያክሉም። ከመላእክት ጋር ቡና እየጠጡ የሚወርዱ ሰዎች ለምን አይሆኑም! እሚፍገመገሙ ከሆነ ተንሳፋፊዎች ናቸው! ተጠበቋቸው። ጤናማውን አስተምህሮ፤ ከሀሰት ትምህርት ለይቶ ማወቅ የመንፈሳዊ ብስለት ምልክት ነው። በእግዚአብሔር ቃል ተኮትኩቶ የማደግ ምልክት ነው።ይሄ ሀሰት ነው! ይሄ እውነት ነው ማለት። ይሄ ጨለማ ነው ይሄ ብርሃን ነው ማለት። ሰኞን ሰኞ እንደምንል፤ ማክሰኞንም ማክሰኞ እንደምንል፤ አንዳንዱን ትምህርት አንዳንዱን እንቅስቃሴ አንዳንዱን ጎራ፤ አንዳንዱን ስብስብ ይሄ ከሰይጣን ነው፤ ይሄ ከክርስቶስ ነው ማለት ይጠበቅብናል። ስለዚህ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ከንግዲህ ህጻናት መሆን አይገባም። ይሄ የሐዋርያው የጳውሎስ ምክር፤ ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን ፤ ከዘመናት በኋላ የኤፌሶንን ቤተ ክርስቲያን ጠቅሟት ነው ያየነው። ሐዋርያት ሳይሆኑ ሐዋርያት ነን የሚሉትን መርምረህ ሐዋርያ እንዳልሆኑ ደርሰህባቸዋል። ይህንን አደንቅልሃለው ብሏቸዋል ጌታችን። ይሄ ሐዋርያዊ ትምህርት ተጽፎ ስለተሰጣቸው፤ እንዲህ ባለ አስደናቂ ምክር ተገርተው ስላደጉ፤ ሐዋርያ ያልሆነውን ሐዋርያ አይደለህም ብለው ዞር ያደርጉት ነበር። መንፈሳዊ መደባለቅ፤ ጎራ መደባለቅ በበዛበት የትምህርት አውራቂስ፤ የሀሰት ማዕበል፤ የብዙዎችን ታንኳ እየመታበት ባለበት በዚህ ዘመን ውስጥ፤ ሰዎችን ከእውነት መንገድ ዞር የሚያደርጉ፤ መጽሐፍ እንደሚል የአንዳንዶችን እምነት የሚገለብጡ፤ እምነት ገልባጮች እውነቱን ከላይ አሳይተው ሀሰትንና መርዝን ከታች አስርገው፤ አሽሉከው የሚያስገቡ በበዙበት በዚህ ዘመን፤ የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች gamblers በረቂቅ ተንኮል እንደወጣ ቁማርተኛ፤ በወንጌል ላይ ቁማር ለመስራት የወጡ ሰዎች የመድረክ ላይ አፈ ቀላጤነትና ጮሌነታቸውን ተጠቅመው ብዙ የዋሆችን በእግዚአብሔር ቃል ያላደጉትን የሚያስቱ ሰዎች፤ በጾታ በቀለም በበዙበት በዚህ ዘመን ውስጥ እንደ ህጻናት መሆን አያስፈልገንም። በአስተምህሮ ንፋስ ወዲያና ወዲህ መፍገምገም አያስፈልገንም። በማዕበል ወደ ፊት ወደ ኋላ መሄድ አያስፈልገንም። ከመንፈሳዊ ሕፃንነት መውጣት አለብን። በእግዚአብሔር ቃል በሐዋርያቱ ምክር በተቀበልነው በዚያ አንድ ሃይማኖት እስከመጨረሻ ጸንቶ የመቆም ቁርጠኝነት እያንዳንዳችን ይጠበቅብናል። እግዚአብሔር በሰማያዊ ስፍራ እግዚአብሔር በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ከባረካችሁ በፊቱ ቅዱሳንና አለ ነውር ትሆኑ ዘንድ አለም ሳይፈጠር በክርስቶስ ኢየሱስ በፍቅር ከመረጣችሁ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ከወሰነን በክርስቶስ ኢየሱስ ህያዋን ካደረገን በሐዋርያትና በነቢያት መሰረት ላይ የታነጽን ከሆንን እንደ አካል ደግሞ እየተገነባን ሙሉ ሰው እንድንሆንለት የአገልግሎት ስራም እንዲበዛልን መልእክተኞችን ነቢያትን እረኞችን አስተማሪዎችን ከሰጠን ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ከሰጠን እንደዚህ ያሉ ነገሮች ደግሞ የበዛላቸው አማኞች ከሆንን ከንግዲህ በማዕበል ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየተነዳን በልዩ ልዩ አይነት የትምህርት ንፋስ በሰዎችም ረቂቅ ተንኮልና ማታለል ወዲያና ወዲህ እየተንገዋለልን ህጻናት መሆን አይገባንም። ሳሚ ቱራ
https://www.instagram.com/reel/DXBJa4iiFkb/?igsh=bTVheWU0d3ozMjY2
መልካም የትንሣኤ ደስታ ለሁላችሁ ይሁን። እርሱ በኩር ሆኖ እንደተነሣ፣ እኛም እንዲሁ እንነሣለን።
без подписи
https://www.instagram.com/reel/DW7Y7zhAhL-/?igsh=MWV1ZmVuN3J3aHlvbw==
ሕማማቱ ሐሙስ በዚህ ኹኔታ እያሉ የቂጣ በዓል በመድረሱ፣ ጌታችን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የፋሲካን ራት እንዲመገብ ሁኔታዎች መቻቸት ነበረባቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስ የፋሲካው ጠቦት በሚታረድበት ቀንና ሰዓት እንደሚሞት ስለሚያውቅ፣ የቂጣ በዓል መጀመሪያ የሆነውን የፋሲካ ራት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ሳይመገብ አልቀረም፡፡ ፋሲካ መበላት ያለበት በኢየሩሳሌም ከተማ ሲሆን (ዘዳግም 16፡ 5-6)፣ ጌታ ኢየሱስ ብዙ ትኲረት የሚስብ ሆኖ በመገኘቱ፣ በተወሰነ መልኩ ሰወር በሚል (ምስጢሩን በጠበቀ) ሁኔታ የፋሲካን ራት ተመግበዋል፡፡ ስለዚህ ራቱን በሚመለከት ከሐዋርያቱ መካከል ጴጥሮስንና ዮሐንስን ምልክት ሰጥቶ ወደ ከተማ ላካቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ከቤቱ ባለቤት ጋር አስቀድሞ በመነጋገር ሁኔታውን ያመቻቸ ይመስላል፡፡ በዚያን ወቅት ብዙውን ጊዜ ውሃ ተሸክመው የሚሄዱት ሴቶች ስለሆኑ፣ በምልክት እንደ ተነገራቸው ውሃ ተሸክሞ የሚሄድን ወንድ ለይቶ ማወቅ ቀላል ነው፡፡ እነርሱም በተባሉት መሠረት ሄደው ቤቱን አሰናዱ፡፡ ይህ ደግሞ ሐሙስ ዕለት ነው፡፡ ከዚያም ጌታ ኢየሱስ የመጨረሻውን ራት (ፋሲካን) ከደቀ መማሙርቱ ጋር ተመገበ፡፡ እየተመገበ እያለም ከእነርሱ ጋር ይህን ለማድረግ ይናፍቅ እንደ ነበረ ነገራቸው (ሉቃስ 22፡15)፡፡ በእግዚአብሔር መንግሥት አብሮአቸው አስከሚመገብበት ጊዜ ድረስ ይህ የመጨረሻው ራት መሆኑንም አሳወቃቸው (ቊጥር 16 እና 18)፡፡ በዐሮጌው ኪዳን (አካሉ ከመከበሩ በፊት) ፋሲካን ከእነርሱ ጋር የሚመገበው ለመጨረሻ ጊዜ ነው፡፡ የዚህ ራት ፋይዳ የኢየሱስን ሞት ማዕከል ማድረጉ ነው፡፡ ስለዚህ የኢየሱስ ሞት የፋሲካውን በግ ተክቷል፡፡ በዚያም ወቅት ስለ እነርሱ የሚፈስሰውን ደሙን እና ስለ እነርሱ የሚቈረሰውን ሥጋውን የሚያመለክተውን የጌታን ራት ሥርዓት ሰጣቸው፡፡ (በመሥዋዕት ጊዜ ደሙ ከሥጋው የተለየ የራሱ ሚና እንደሚኖው ማስታወስ ተገቢ ነው)፡፡ በማቴዎስ ወንጌል እንደ ተነገረው፣ ጌታ ኢየሱስ ኅብስቱንና ጽዋውን በሚሰጣቸው ወቅት፣ ‘‘ስለ ብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የዐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው’’ ብሏቸዋል፡፡ ዘሌዋውያን 17፡11 እንደሚነግረን፣ በብሉይ ኪዳን የመሥዋዕቱ ደም ከስርየት ሥርዓት ጋር የተቈራኘ ነውና ደም ሳይፈስ ስርየት ወይም ይቅርታ የለም (ዕብራውያን 9፡22)፡፡ በዚህ መሠረት የኢየሱስ ደም ስርየት አለው፡፡ ከዚህ በፊት የኀጢአት ስርየት ሂደት የሚከወነው በቤተ መቅደሱ መሠዊያ ላይ ነበር፡፡ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ በሰጣቸው የመጨረሻው ራት ላይ ግን ይህን ሂደት ቀየረው፡፡ የቤተ መቅደሱን የመሥዋዕት ሥርዓት ወደ ራሱ አዞረው፡፡ ከዚህ በኋላ የኀጢአት ስርየት የሚገኘው በተቈረሰው ሥጋው እና በሚፈስሰው ደሙ በኩል ብቻ ነው፡፡ ከዚያም በኋላ ይህን ሥርዓት ለመታሰቢያው እንዲያደርጉትም አዘዛቸው፡፡ ይህ በርግጥም የፋሲካ ራት ነው፡፡ ነገር ግን ትርጓሜው ሥር ነቀል ለውጥ አለው፡፡ የየሰው አእምሮ 1500 ዓመት የኋሊት በሚመለከትበት ዕለት፣ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ወደ ፊት የሚመለከቱትን ነገር ሰጣቸው፤ በማግሥቱ የሚፈጸም ነገር፡፡ ሞቱን፡፡ ይህ ወደ ትናንት ብቻ ሳይሆን ወደፊት የሚያመለክት ፋሲካ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብፅ ባርነት ነጻ ለማውጣት የወሰደውን ርምጃ የኋሊት የሚያመለክት ሳይሆን፣ ሕዝቡን ከመጨረሻው ባርነት ማለትም ከሞት፣ ከኀጢአት እና ከሌሎችም ተያያዥ የክፋት ኀይላት በታላቅ መሥዋዕት ነጻ የሚያወጣበት ፋሲካ ነው፡፡ እውነተኛ ፀዐት (መውጣት) ይህ ነው! …. ጳውሎስ ፈቃዱ፣ የተሰቀለው፡ የጌታ ኢየሱስ የመስቀል ሞት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንተና (ዐዲስ አበባ፡ ርኆቦት ዐታሚዎች፣ 2018 ዓ.ም)፣ 91– 94 ይቀጥላል
https://youtu.be/y8stHUXa1hI?si=6fczGSqCA8ErYZY2
ሕማማቱ ረቡዕ ዕለቱ ረቡዕ ነበር፡፡ ጌታ ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ሲያስተምር ቢይዙት ከባድ ችግር መፈጠሩ አይቀርም፤ በርካቶችም ከ5 ቀናት በፊት ሆሣዕና የዳዊት ልጅ በማለት በጩኸት እያዜሙ ተቀብለውታል (ማቴዎስ 21፡9)፡፡ በዚህ ኹኔታ የሚፈጠረው ሁከትበሮማውያን ላይ ወደ ማመፅ በቀላሉ ሊሻገር ይችላል፡፡ በተለይ ከግብፅ ነጻ የወጡበትን በዓል በሚያከብሩበት ወቅት የሕዝቡ አገራዊ ስሜትና ከሮማውያን ነጻ የመውጣት ፍላጎት እጅግ ስለሚጋጋል፣ ኢየሱስ ፖለቲካዊ ፍላጎት ባይኖረው እንኳ ኹኔታው አደገኛ ይሆናል፡፡ በተለይም የገሊላ ሰዎች ለእንዲህ ዐይነቱ ዐመፅ ይበልጥ የተጋለጡ ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ ገሊላውያን ደግሞ የኢየሱስ ደጋፊዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ የአይሁድና የሮሜ መሪዎች ለበዓሉ በሚሰበሰቡ ብዙኀኑ ዘንድ ድንገተኛ ረብሻና ሁከት እንዳይነሣ ይሠጋሉ፡፡ በሃይማኖትና በብሔራዊ ስሜት የጋለው ሕዝብ በቀላሉ ወደ አብዮት ተጋፋፍቶ ሊገባ ስለሚችል ሁልጊዜም በፋሲካ ሳምንት በርካታ ሰራዊት ይጨምራሉ፡፡ ከዚህም የተነሣ ኢየሱስን ከፋሲካ በፊት ማስወገድ ቢችሉ ጠቀሜታው ከፍ እንደሚል አስበዋል፡፡ የካህናት አለቆችና ጻፎች ጌታን ስለ መያaያ ለመነጋገር የተሰበሰቡት በሊቀ ካህናት በቀያፋ ግቢ ነው፡፡ ከተመካከሩም በኋላ ዕቅዳቸውን ለመፈጸም ምቹው ጊዜ የቂጣ በዓል ካለፈ በኋላ እንደ ሆነ መግባባት ላይ ደረሱ፡፡ ምክንያቱም ለክብረ በዓሉ ወደ ኢየሩሳሌም የተሰበሰቡት አማኞች በዓሉ ሲጠናቀቅ ወደየመጡበት ስፍራ ተመልሰው ስለሚሄዱ ግርግር አይኖርም፡፡ ስለዚህ ዕቅዳቸውን ያለ ምንም ኹከት ሊፈጽሙ አይቸገሩም፡፡ እንደ እነርሱ ሐሳብ ከሆነ፣ ሥልጣኑም ሆነ ኀይሉ በእጃቸው ነውና አመቺ ጊዜ ጠብቀው ቢራመዱ፣ የማታ ማታ ዕቅዳቸውን ማሳካታቸው አይቀርም፡፡ የአስቆርቱ ይሁዳ ወደ እነርሱ በመሄድ ሊተባበራቸው የተስማማው በዚህ ወቅት ነበር (ሉቃስ 22፡1-6፤ ማቴዎስ 26፡3-5፡ 14-16)፡፡
без подписи
ሕማማቱ ማክሰኞ በማግሥቱም ማለትም ፋሲካ 3 ቀናት ሲቀረው (ማክሰኞ)፣ ጌታ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለሰ በኋላ በየዕለቱ እንደሚያደርገው ሕዝቡን በቤተ መቅደስ ያስተምር ነበር፤ ሕሙማንንም ይፈውስ ነበር፡፡ በየቱም መንገድ ቢሆን ኢየሱስን ለማስወገድ ጥረት የጀመሩት አለቆች፣ ራሱን በራሱ ቃል ለማጥመድ ለሮማውያን ግብር የመክፈልና ያለ መክፈል ጥያቄ አቀረቡለት፡፡ ‘‘ግብር ይከፈል’’ የሚል ምላሽ ከሰጠ፣ ለቅኝ ገዢዎቻቸው ግብር እንዲከፈል ፈልጓልና ከገዛ ሕዝቡ ጋራ ይጣላል፡፡ ‘‘ግብር አይከፈል’’ ካለም፣ ከገዥዎቹ ሮማውያን ጋራ መጣላቱ ነው፡፡ ስለዚህ በቀላሉ እርሱን ለማስያዝና ለማስቀጣት የሚሆን ሰበብ ይገኛል፡፡ በእውነቱ እጅግ ፈታኝ ወጥመድ ነበር፡፡ የእርሱ ምላሽ ግን ለየቱም ወጥመድ አልተመቸም፡፡ በዚህ ሁሉ መካከል ጌታ ኢየሱስ ቀን ቀን በኢየሩሳሌም ሲያስተምር ይውልና ማታ ማታ ከከተማዪቱ እየወጣ ያድራል (ሉቃስ 21፡37)፡፡ ከዳግም ምፅአቱ ጋራ የተያያዙ ትምህርቶችን የሰጠው በዚህ የትምህርት ወቅት ነበር (ማቴዎስ 24 – 25፤ ማርቆስ 13፤ ሉቃስ 21)፡፡ የቤተ መቅደሱን መፈራረስ አይቀሬነትም ከዚህ ጋራ አያይዞ ገልጧል፡፡ ለፋሲካ ኹለት ቀናት እስኪቀሩት ድረስ ሁኔታው በዚህ መልኩ ቀጥሏል፡፡ ከዚያስ? ጳውሎስ ፈቃዱ፣ የተሰቀለው፡ የጌታ ኢየሱስ የመስቀል ሞት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንተና (ዐዲስ አበባ፡ ርኆቦት ዐታሚዎች፣ 2018 ዓ.ም)፣ 89– 90
ሕማማቱ ሰኞ ‘‘የትናንትናው የእሁድ ኵነቶች (የሆሳዕና ቀን) በየሰው አእምሮ ስለ ነበረ፣ ጌታ ኢየሱስ ከዚያ ቀጥሎ ምን እንደሚያደርግ ብዙዎች ይጠባበቁ ነበር፡፡ እርሱም ወደ ቤተ መቅደስ በመሄድ ማስተማሩን ቀጠለ፡፡ ቤተ መቅደሱ፣ ቃለ እግዚአብሔር እንደሚለው የአሕዛብ የጸሎት ቤት ከመሆን ይልቅ የወንበዴዎች ዋሻ መስሎ ነበር፤ አምልኮተ እግዚአብሔርን በማሳለጥ ስም ሃብታሞችና ጒልበታሞች ድኾችን የሚበዘብዙበት የወንበዴዎች ዋሻ፡፡ እናም ጌታ ኢየሱስ የገንዘብ መንዛሪዎችን ጠረጴዛና የርግብ ሻጮችን መቀመጫ እየገለባበጠ፣ ነጋዴዎቹን ከዚያ በማስወጣት ቤተ መቅደሱን አነጻ (ማቴዎስ 21፡12-13፤ ማርቆስ 11፡ 15-17፤ ሉቃስ፡ 45 - 46) ይህም የአይሁድን ባለ ሥልጣናት በቀጥታ የሚገዳደርና ሁከት እንዳይኖር የሚፈልጉትን ሮማውያን ምቾት የሚነሣ ድርጊት ነበር፡፡ በቤተ መቅደሱ ላይ ባለ ሥልጣናቱ እነርሱ ስለ ነበሩ የአይሁድ አለቆች፣ ‘‘እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ?’’ በማለት ጠይቀውታል፤ የሚያቀርብላቸው የቱም ምላሽ እንደማያረካቸው ግን ግልጽ ነበር (ማርቆስ 11፡28)፡፡ በርግጥም ምላሹን ሊቋቋሙት አልቻሉም፡፡ ይህም በሕዝቡ ዘንድ የተጋለጡ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ በወቅቱ በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች የካህናት አለቆች፣ ጻፎችና የሕዝቡ ታላላቆች ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፡፡ ሆኖም በሕዝቡ ተከብቦ ስለ ነበር ሐሳባቸውን የሚፈጽሙበት ክፍተት ሊያገኙ አልቻሉም (ማርቆስ 11፡18-19፤ ሉቃስ 19፡47)፡፡ በዚህም ዕለት ጌታ ኢየሱስ በኢየሩሳሌም አላደረም፤ በማግሥቱ ግን ተመልሶ መጥቷል (ማርቆስ 11፡19-20 ማቴዎስ 21፡ 17-18)፡፡’’ ጳውሎስ ፈቃዱ፣ የተሰቀለው፡ የጌታ ኢየሱስ የመስቀል ሞት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትንተና (ዐዲስ አበባ፡ ርኆቦት ዐታሚዎች፣ 2018 ዓ.ም)፣ 88 – 89
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ዓለምን ፈጥሮ ሲጨርስ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ። ይህም በዕብራይስጥ ቋንቋ "ዕረፍት" ማለት ሲሆን "ሰንበት" (ይበልጥ በትክክለኛው አጠራር "ሻባት") ይባላል። በብሉይ ኪዳን ሰንበት የእግዚአብሔር የፍጥረት ሥራ (ዘፀአት 20:11) ብቻ ሳይሆን የማዳን ሥራውም (ዘዳግም 5:15) ሳምንታዊ መታሰቢያ ነበር። ኦሪት ዘፍጥረት እና ኦሪት ዘፀአት በእያንዳንዱ ሰንበት ይታሰቡ ነበር። ፍጥረትም ሆነ ቤዛነት (ማዳን) በኢየሱስ ውስጥ ይገናኛሉ። ዓለምን የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ፣ የሰውን ልጅ አዲስ አድርጎ የመፍጠር ሥራውን አጠናቆ፣ በሰባተኛው ቀን በሞት መቃብር ውስጥ ዐረፈ። "ተፈጸመ" አለ። ሥራው ተፈጽሞ ነበር፤ ስለዚህ ዕረፍቱን ወሰደ። ይህም የእሱ ሰንበት ነበር። ይህ ደግሞ ማብቂያ የሌለው ሰንበት ነው። የእርሱ ትንሣኤ ፍጥረት ሁሉ ከዘፍጥረት ጀምሮ ሲጠባበቀው ወደነበረው ሰንበት ያሸጋግረናል። እኛ ደካሞችና ሸክም የከበደን ወደ ኢየሱስ እንመጣለን፣ እርሱም በእርሱ ውስጥ ሰንበትን (ዕረፍትን) ይሰጠናል። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" በእኔ ውስጥ ሰንበትን እሰጣችኋለሁ። ዛሬ በቅዳሜ ስዑር (Holy Saturday) ኢየሱስ በመቃብር ውስጥ ሰንበትን ያደርጋል። ከእርሱ ጋር አብረን የተሰቀልን እኛም የትንሣኤን ቀንና አብሮ መነሳታችንን እየጠበቅን በዚያ እናርፋለን። ቻድ በርድ
But He obeyed the will of the Father.
"ጌታ ኾይ፤ ይህ በኀጢአት የቆሸሸ እና ክፋት ያደበዘዘው ዓይኔን እኔ አልፈልገውም፣ አንተንም ደስ አያሰኝም። በላዩ ታትመው የቀሩ ብዙ የበደል አሻራዎችን ስለ ተሸከመ የማየው ሁሉ ጤነኛ አይደለም። በዓይኖቼ ነገረ መስቀልህ ተሥሎ አልቀረም። ዓይኔን ያዩ ኹሉ ተንኮል እና ምቀኝነት፣ ክፋትና ተቅበዝባዥነትን እንጂ ሌላ ምንም አያነቡም። እባክህ እንደ ሐዋርያህ በፍቅርህ ብርሃን እጠበኝ እና የምሕረትህን ማኅተም በዓይኖቼ አኑርብኝ? ሰው ኹሉ በብርሃንህ የበዘበዝካቸው ዓይኖቼን እያየ በአንተ ይቅር ባይነት ይደነቅ።" "ቅዱስ ጳውሎስ" ዲያቆን አቤል ካሣሁን ገጽ 100
"We cannot pray in love and live in hate and still think we are worshipping God." A. W. Tozer