THE VOICE
Статистика- Последний пост
- 24 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 84
- 1/48двое суток
- 96
- 1/72трое суток
- 103
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የመጨረሻ ቃላት ከእስር ቤት ለወጣቱ አገልጋይ “ቃሉን ስበክ፥ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፥ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ፥ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም። ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ። እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፥ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ። አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም።” 2ጢሞ 4:2-5
አንድ ክርስቲያን ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ያለውን ግንኙነት ሲያርቅ ዲያብሎስ ፈገግ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ሲያቆም ዲያብሎስ ይስቃል። ጸሎት ሲያቆም ዲያቢሎስ በደስታ ይጮኻል። ~ Corrie Ten Boom “በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና።” መዝ133:3
“እምነቴ እንደ መርከብ ተሰብሮብኝ ከእግዚአብሔር እርቃለሁ ብዬ በምጨነቅበት ጊዜ፣ አለማመንን ‘በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ክርስቶስ ቀን ድረስ ይፈጽመዋል’ በሚለው የተስፋ ቃል እዋጋዋለሁ።” — ጆን ፓይፐር
. እግ/ር ተረት አይደለም ዮሐንስ ግርማ እና ዘፀአት ኳይር NEW SONG 🕐-10:35Min || 💾-8.8MB
✍️የእግዚአብሔር ልጆች የሆንነው ተገብቶን አይደለም። ✍️የእግዚአብሔር ልጆች የሆንነው በእግዚአብሔር ፍቅር ነው። ✍️ኢየሱስ ክርስቶስን በድንግዝግዝ ከምናይበት ወጥተን ፊት ለፊት እናየዋለን።(ታላቁ አስደሳች ነገር) ✍️ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ በርሱ ያለውን ባህሪ በኛም ውስጥ እናያለን። ✍️ጥሩ ስንሰራ እና ወደፊት ሳይሆን ዛሬ አሁን በዚህ ሰአት የእግዚአብሔር ልጆች ነን። HALLELUJAH !! 1 ዮሓንስ 3:1-10
የአውሮፕላን ክንፎች የእያንዳንዱን አማኝ ሕይወት ይወክላሉ። አንዱ ክንፍ የመንፈስ ቅዱስን አካል እና አገልግሎትን ይወክላል። ሌላው ክንፍ የእግዚአብሔርን ቃል ያመለክታል። አውሮፕላን ያለ ሁለቱ ክንፎች መብረር እንደማይችል ሁሉ፣ የክርስቶስ አማኝ እንዲሁ ‘መብረር’ አይችልም።” - ቢል ብራይት((CCC)የGreat commission)መስራች
መጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ሰው ያደርግሃል “የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ ያልሆነ ጠቃሚ ክርስቲያን አይቼ አላውቅም” - ዲ.ኤል. ሙዲ
👉ሰውን የሚለውጠው የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። 👉አህያ(የምድር ስኬት) ጠያቂና ፈላጊውን ትንቢት(የሰማይን ሀሳብ) የሚያናግር እግዚአብሔር ነው። 👉ለእግዚአብሔር የሚያሰደስተውን ሕይወት እንዲኖረን የሚያደርገው የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። “የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ይወርድብሃል፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰውም ሆነህ ትለወጣለህ።” 1ሳሙ 10:6 ተባርካችኋል!
“እነሆ ከሰማይ እንጀራን አዘንብላችኋለሁ፤ ሕዝቡም ወጥተው ለዕለት ለዕለት የሚበቃቸውን ይልቀሙ።”ዘፀ16:4 ያለ ጸሎት ያለ ቀን መንፈስ ቅዱስን ‘ዛሬ እገዛህ አያስፈልገኝም ማለት ነው። ያለ ጸሎት አንድ ሳምንት ለመንፈስ ቅዱስ እንዲህ ማለት ነው፡- ‘በዚህ ሳምንት የአንተ እርዳታህ አያስፈልገኝም። ጸሎት የሌለበት ሕይወት መንፈስ ቅዱስን እንዲህ ማለት ነው፡- ‘በራሴ ጥንካሬ መኖር እችላለሁ። በራሴ ሃይል ማድረግ እችላለሁ። A day without prayer is to say to the Holy Spirit, 'I don't need Your help today. ' A week without prayer is to say to the Holy Spirit, 'I don't need Your assistance this week. ' A life without prayer is to say to the Holy Spirit, 'I can live in my own strength. I can do it by my own power Anonymous
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።” ዮሓ 12:24 👉መሞት የማፍራት መርህ ነው። 👉ሕይወት ያለችው በውስጠኛው የማንነታችን ክፍል ነው። 👉ከላይ ያለው ቅርፊት( ego, ትእቢት፣ አውቃለው ባይነት፣ ትሁት አለመሆን) እስኪሰበር በውስጥ ያለው ሕይወት መውጫ የለውም። 👉ቅርፊቱ ሲሰበር መከራዎች ሁሉ ለዘሩ ቅንጣቲት ፍሬያማነት ግብአት ነው።
"ከሌሎች ትከሻ ላይ በመቆሜ ነው ሩቅ ማየት የቻልኩት።" "If I have seen further, it is by standing on the shoulders of giants." Isaac Newton
без подписи
የተቀባን ነን “እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።” 2:20 የተቀባውን ስናምን መንፈስ ቅዱስን በመቀበል የተቀባን ሆንን። መንፈስ ቅዱስ እውነት ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ ይመራናል። ከስህተት ይጠብቀናል። እውነትና ሀሰትን መለየት የምንችልበት መንፈስ ተቀብለናል።
በሃይማኖት ያይደለ ፍቅሩ ይዟት አለም ሁሉ እንዳስጠላት ድንግል ሴት፤ ቤ/ን በክርስቶስ ፍቅር አብዳ አለምንና ራሷን የካደች ሁለንተናዋን ለጌታዋ በመስጠት ጥዋት እና ማታ በናፍቆት በሩን እያየች ስለባሏ ውበት ፣ሕይወትና ተስፋ እያወራች መምጣቱን የምትጠባበቅ ሚስት ናት። ቤ/ን
እስኪ በጸሎትህና በጾምህ አትታለል። ሌሎችን እንዴት እንደምታስተናግድ ተመልከት። ያ ነው የነፍስህ እውነተኛ መስተዋት። · ሩሚ - ሩሚ እዚህ ላይ ትኩረትን ከሥርዓተ አምልኮ ወደ ባሕርይ ያዞራል—ጸሎትና ጾም ልማድ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን ለሌላ ሰው ያለህ አመለካከት ነፍስህን ያጋልጣል። ✍️abreham https://t.me/abrehamvoiceofthekingdom
የጸሎት ህይወታችንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችንን የሚያቀጣጥሉና ግዜያችንን ሳናባክን እንድንጠቀምበት የሚያነቃቁን ወዳጆችን እግዚአብሔር ያብዛልን:: J.C.Ryle መልካም ዕለተ-ዕሁድ 🤌🥰
45min አንተን ፈልጌ ነው |ይስሐቅ ሰዲቅ አይመጥኑህም | ሳሙኤል ገ/መስቀል
ይህ ነው ፀሎቴ የማይቀየረው ምንም ቢሰጠኝ እጄ ማይለቀው ጠብቄ የያዝኩት እንደ ቀሪ ሀብት ራሴን ማገኘው ሁሌም በአንተ ፊት
እድሜ ማስተዋልን ይሰጣል። ሆኖም የእግዚአብሔር ቃል የሚሰጠው ማስተዋል ሽምግልና እና ልማድ ከሚሰጠው ይበልጣል። “ምስክርህ ትዝታዬ ነውና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ። ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ።” መዝ 119:99-100 ✍️abreham https://t.me/abrehamvoiceofthekingdom
без подписи