tgindex
Daily Injera

A Christian ministry which delivers a verse from The Holy Bible everyday in partnership with @ethbiblica. www.dailyinjera.org Follow us on FB • IG • Twitter • Viber • YT - @dailyinjera

Последний пост
06:00
Последнее чтение
13:54
Постов за неделю
7
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
7 858
−1 за 3 дн.
Сутки
−3
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 050
22 постов
Вовлечённость
13,4%
к подписчикам
Постов в день
1,0
всего 23
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
679
1/48двое суток
778
1/72трое суток
839

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 06:0025891

    የዘላለሙ አምላክ በጊዜ ውስጥ የሚገባ ብቻ ሳይሆን የሚሠራም ነው። ለሰዎች ልጆችም በዘመን ሽግግርና በዘመን መካከል ድንቅ ሥራውን ይሠራ። ልጆቹ በየትኛውም ሁኔታ ቢሆኑ (በመከራ፣ ምርኮ፣ ሌላም) የዘላለም ዕቅዱ የከበረ፣ የጊዜ አምራሩም ድንቅ ነው። የሚያምኑት ቢጠሩት ይሰማል፤ ቢታመኑት ይታመናል፤ ቢፈልጉትም ይገኛል። Jeremiah 29:11-13 'For I know the plans I have for you,' declares the Lord, 'plans to prosper you and not to harm you, plans to give you hope and a future. Then you will call on me and come and pray to me, and I will listen to you. You will seek me and find me when you seek me with all your heart.' @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • #ArtSaturdays ጊዜ አስፈላጊ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ሁነኛ ጊዜም እንዲሁ ወሳኝ ነው። ሁነኛ ጊዜ ማለት አንድ ነገር ሊጀመር ወይም ሊሠራ የሚገባበት ሰዓት ወይም ቅጽበት ነው፤ ጳውሎስ ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ፣ ጸጋውን ለሕይወትና ለአገልግሎት ፍሬ—ተግባር—የተቀበልን እንደ ሆነ እያሳሰበ ከብሉይ ኪዳን ጠቀሰ፤ "እርሱ፣ 'በትክክለኛው ሰዓት ሰማሁህ፤ በመዳንም ቀን ረዳሁህ' ይላልና። እነሆ፤ ትክክለኛው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳንም ቀን አሁን ነው" (2ቆሮ 6፥2)። እግዚአብሔር ሊሠራ በሚነሣበት ጊዜና ሰዓት ዝግጁ መሆን ጥሩ ነው፤ እርሱ የዘላለም አምላክ ቢሆንም በጊዜና ቦታ ለተወሰነው ፍጥረቱ ገዢ፣ እረኛና መጋቢ ነው። ሰዎችም ወደ ክብሩ እንዲቀርቡ፣ የመንግሥቱ ተካፋይም እንዲሆኑ ይፈልጋል፤ ይሠራልም። የቀረቡም እንዲሁ እንዲጸኑና እንዲያድጉ ይፈልጋል። ለዚህ ጥሪ በትክክለኛው ጊዜ ምላሽ መስጠት፣ በጊዜውም አለጊዜውም (ቢመችም ባይመችም) ቍርጠኛ መሆን ይገባል። ያም ብዙ ደስታና ዕረፍት አለው። 2 Corinthians 6:2 For he says, 'In the time of my favor I heard you, and in the day of salvation I helped you.' I tell you, now is the time of God’s favor, now is the day of salvation. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • ነገርን ሁሉ "እንደ ፈቃዱ ምክር" የሚሠራው አምላክ "በዘመን ፍጻሜ ይሆን ዘንድ ያለው ሐሳቡ በሰማይም በምድርም ያሉትን ነገሮች ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ሥር ለመጠቅለል ነው" (ኤፌ 1፥10 አመት)። ሁሉ ከእርሱ (ከጌታ) እና ለእርሱ ነው። ፍጥረት በእርሱ እንደ ተገኘ፣ ትድግናም (ማዳን) በእርሱ በኩል ነው የሆነው። ዘመን እየተጠቀለለ ሲሄድም፣ ጊዜ የያዘውን ሁሉ እየጠቀለለ የጌታ ያደርጋል። ጊዜ ተቀብሎ ያስተናገደውን ሁሉ ለጌታ ያስረክባል። በዘመን መካከል አምላካቸውን የሚያከብሩም፣ የዘመን ዕረፍት ብቻ ሳይሆን የዘላለም ክብር ይጠብቃቸዋል። Ephesians 1:10 to be put into effect when the times reach their fulfillment—to bring unity to all things in heaven and on earth under Christ. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • የመክብብ ጸሐፊ—ጠቢቡ ሰባኪ—ዋነኛ ትኩረቱ ከፀሓይ በታች ስለሚሆኑ ነገሮች ነው። "ከንቱ" የሚለው ጭብጥ (ዋነኛ ሐሳብ) የሚጎላበት ይህ መጽሐፍም፣ ስለ ዘመን በጥልቀት ይዘረዝራል። ምዕራፍ 3፣ "ለሁሉም ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው" ብሎ ይጀምራል። ከዚያም በንጽጽር፣ ሁሉ ባለ ተራ እንደ ሆነ ያትታል። ለመወለድ ጊዜ እንዳለው ሁሉ ለመሞትም ጊዜ እንዳለው ይናገራል፤ "ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው" (ቍ. 8) ይላል። ምክንያት ሆንን አልሆንን የማይለወጡ ነገሮች አሉ። ከፀሓይ በታች ሁሉ "ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ" ከሆነ፣ የምንፈልጋቸው ብቻ ሳይሆን፣ የማንፈልጋቸው ነገሮችም ብዙ ናቸው። ዋናው ነገር ግን ከፀሓይ በላይ ያለውን አምላክ በዘመናችን መካከል ማሳተፍ—"ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን"—ነው። እንደ እግዚአብሔር ምርጦችም ለክፉውም ሆነ ለደጉ ጊዜ የሚጠበቅብንን እያደረግን፣ በነገር ሁሉ በእርሱ እየታመንንና ዕረፍታችንን እያጸናን ልናድግ፣ ልናፈራም ይገባል። Ecclesiastes 3:8 ... a time for war and a time for peace. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • እግዚአብሔር የዘላለም አምላክና ሁልጊዜ ሙሉ ነው። ስለዚህም አይለወጥም። ዘመን ከሥሩ እንጂ በእርሱ ላይ አይለወጥም፤ እርሱ ከጊዜ ውጪ ነውና። የሰዎች ልጆች ግን በጊዜ ውስጥ በለውጥ ያልፋሉ። አንዳንዶቹ በጊዜ መካከል ታሪክ ይሠራሉ፤ ሌሎች ደግሞ በሚሠራ ታሪክ ውስጥ ተመልካች ወይንም ተሳታፊ ብቻ ይሆናሉ። ጌታ አምላክ ደግሞ በታሪክ ላይ የበላይ ሆኖ ይቀጥላል። በጊዜ ውስጥ የሚሆኑ ነገሮች እርሱን አይነቀንቁትም፤ ሲፈቅድ ጣልቃ ይገባል፤ ሲጠየቅ በሰዎች ልጆች ጕዳይ ተገኝቶ ያግዛል፤ ይረዳል ይመራል፤ በራሱ ደግሞ ሉዓላዊ ፈቃዱን ያለ ማንም ከልካይ ይፈጽማል። ዘማሪው፣ "አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም" አለ (102፥27)። እግዚአብሔር የማይረድፍበት፣ በየትኛውም ጊዜ የሚሠራና ምንም—አቅርቦት—የማይጎድልበት ብርቱ አምላክ ነው። በዘላለም ውስጥ በክብር ከፍ ያለ ስለሆነም ባሕርይው አይለወጥም፤ ግርማውም ፈጽሞ አይደበዝዝም። Psalms 102:27 But you remain the same, and your years will never end. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • የሙሴ ጸሎት እንደ ሆነ የሚታመነው መዝሙር 90 ስለ ዘመን ይናገራል። እግዚአብሔር የዘላለምና ከዘላለም እንደ ሆነ ያትታል። ሰው ኀላፊ (ሣር፣ ዐፈር)፣ ጊዜ ደግሞ ለፈቃዱ የሚያጥር ወይም የሚገዛ እንደ ሆነ ይናገራል። ዘመናችንም የተሰፈረ ከሆነ የምንመዘንበትም ስለሆነ፣ ልናስበው፣ ልንፈትሸው፣ ምን ያህል እንደ ቀረንም እንድንጠይቅ ይነግረናል፤ "ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን" (ቍ. 12)። የእስካሁኑን (የኖሩትን) በደንብ የሚያስቡና የሚያሰላስሉ፣ ስለ ቀሪው ይጠይቃሉ፣ ያቅዳሉም። በጊዜ ውሰጥ ጌታን የሚያስቡም እንደ ዘማሪው ይጸልያሉ፤ "በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ፣ ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን" (ቁ 14)። ያኔም፣ እግዚአብሔር ምሕረቱንና ጸጋውን በዘመናችን መካከል ያትረፈርፈዋል። Psalms 90:12 Teach us to number our days, that we may gain a heart of wisdom. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • በእግዚአብሔር መታመን የዘመን ሁሉ (የሁልጊዜ) ተግባር ነው። እግዚአብሔርን የሚያውቁም በእርሱ ሊታመኑ ይገባል። ሰዎች ግን፣ በእግዚአብሔር መታመን ማለት ምን ማለት ነው? የሚል ጥያቄ ሊያነሡ ይችላሉ። በእግዚአብሔር መታመን ለእግዚአብሔር መሆን—መጽናት—ብቻ አይደለም፤ በእርሱ መጽናትንም ይይዛል። ዳዊት እንዲህ አለ፤ "እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ፤ 'አንተ አምላኬ ነህ' እልሃለሁም። ዘመኔ ያለው በእጅህ ነው" (31፥14-15)። ዘመን—ጊዜ—በእግዚአብሔር እጅ ከሆነ፣ በዘመን መካከል ስለሚፈጸሙ፣ ሊጎድሉ ወይም ሊሞሉ ስለሚችሉ ነገሮች ሁሉ በእግዚአብሔር መታመን ያስፈልጋል። ዘመን ደግም ክፉም ነገር ይዞ ይመጣል፤ የተሻለው እንዲቆይ፣ እንዲለመልምም፣ የባሰው ደግሞ እንዲገታ ወይም እንዲቆም እርሱን ማመን ይገባል። ስናምነው እንጠራዋለን፤ በዘመናችንም ላይ ጌታ እንዲሆን እንሾመዋለን። ያን ጊዜ ዘመኑን እኛ የምንሸከመው አይሆንም። Psalms 31:14-15 But I trust in you, Lord; I say, 'You are my God.' My times are in your hands; deliver me from the hands of my enemies, from those who pursue me. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 9 авг.936213

    በበዓለ አምሳ ዕለቱ የጴጥሮስ የድነት ስብከት፣ ትኩረቱ ጌታ ኢየሱስና የማዳን ሥራው ነበር። ንግግሩንም ዳዊት ስለ መሢሁ በተናገረው ሐሳብ አጸና፤ “እርሱ በቀኜ ነውና ከቶ አልታወክም ብሎም፣ ስለ “ሕይወት መንገድ” ገለጸ። የሕይወት መንገድ የሆነው ክርስቶስ ጌታ መዳንን የሚሰጥ፣ በሐሤትም የሚሞላ ነው። መንገዱ ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል፤ ከተደለደለ በኋላ ግን የሚጓዙበት (የሚያምኑበት) ቀለለላቸው። በዚያ ሕይወትና ደስታ ስላለ፣ የጕዞው ሂደት በተስፋ፣ በሐሤትና በበረከት ይሸፈናል። Acts 2:28 You have made known to me the paths of life; you will fill me with joy in your presence. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 8 авг.1 021235

    #ArtSaturdays የእግዚአብሔርን መንገድ ከሙሴ እስከ ዳዊት፣ ከኢሳይያስ እስከ ሚክያስ ሲጠይቁ፣ ሲያመለክቱም ኖሩ። እግዚአብሔርንም መንገድህን አስተምረን ብለው ተማጸኑ። እርሱም ዐውቀው ይከተሉት ዘንድ፣ እየተከተሉትም ያውቁት ዘንድ በመንገዱ መራቸው፤ ተጠነቀቀላቸውም። በዘመኑ መጨረሻም—በመጨረሻው መጀመሪያ—መንገዱን በመካከላቸው አኖረው፤ ጌታ ኢየሱስ መንገድ ሆኖ በሰዎች መካከል አደረ። ይህንኑም (እራሱ) ገለጠው፤ "መንገዱ እኔ ነኝ...በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም" (ዮሐ 14፥6)። አንድ ጌታ እንዳለ ሁሉ፣ መንገዱም አንድ ነው። ያ መንገድ የዐመጻ ዋጋ የተከፈለበት፣ የኅጢአት ይቅርታ የተገኘበት፣ ጸጋ የቀረበበትና ሕይወት የተሰጠበት ነው። እነዚህ ሁሉ ትሩፋቶች (ጥቅሞች) እና በረከቶች ሌሎች 'መንገዶች' ላይ የሉም። ይህ መንገድም የሚኬድበት ብቻ ሳይሆን፣ የሚታረፍበትም ነው። John 14:6 Jesus answered, “I am the way and the truth and the life. No one comes to the Father except through me. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 7 авг.1 003224

    ጥበብ መንገደኛ ነች። ፈላጊ ነች። ብዙዎች እንዳላቀፏት፣ እንዳላተረፉባትና፣ እንዳልተሻገሩ ባት ስላወቀች ጉዞዋንና ፍለጋዋን አታቋርጥም። መንገዷም የጽድቅ መንገድ ነው። በሰውኛ የተመሰለችው ጥበብ ይህንኑ እውነት በምሳሌ 8 ገልጣለች። ጥበብ ተጉዛለች፤ ፈልጋለች፤ ተጣርታለች፤ አስተምራለች። መንገደኝነቷንም እንዲህ በማለት አስረግጣለች፤ "እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፤ በፍትሕም ጐዳና እጓዛለሁ" (ቁ. 20)። ጥበብ ልታገኛቸው የምትፈልጋቸው ብዙ ቢሆኑም፣ መንገዷ ግን አንድ ነው፣ የጽድቅ ብቻ፤ ፍትሕና ርትዕም ያለበት። እርሷን ያገኙም፣ ከእርሷ ጋር በጽድቅና ፍትሕ መንገድ ላይ ይጓዛሉ። Proverbs 8:20 I walk in the way of righteousness, along the paths of justice @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 6 авг.1 093238

    እግዚአብሔር አምላክ ራሱን ለጥቂቶች ካስተዋወቀ በኋላ፣ በመገለጥ ሂደት ለብዙዎች—ለሕዝቦች—ማንነቱን እየገለጠ መጣ። ራሱን ባቀረበ መጠንም ሕዝቦች እየቀረቡት፣ እየተጠጉት እንዲመጡ ይጠበቃል፤ በበራቸው ቆሞ—ጌታ በሎዶቅያ እንዳንኳኳ—ካንኳኳ፣ 'ለምን ራሱ (በኅይሉ) ገፍቶ አይገባም?' አይባልም። በኢሳይያስ 2 ላይ፣ ምላሽ ስለ ሰጡ ሕዝቦች እናነባለን፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጐዳናውም እንሄዳለን" (ቍ. 3)። መውጣት ለማወቅ፣ መጠጋት ለመማር፣ መቅረብ አብሮ ለመጓዝ መሆኑ ነው። የእግዚአብሔርን መንገድ የተማሩ፣ ትምህርታቸው ትጋትም፣ ዕረፍትም ይሆናቸዋል። የእርሱ መንገድ ከመታወቅ በላይ ስለሆነም፣ አካሄድን ለማሳመር አደራረጉንም ለመረዳት ሁልጊዜ አብሮ መጓዝ ይጠይቃል። ከእርሱ የተማሩም በሌሎች 'መንገዶች' ግራ የሚጋቡ አይደሉም። Isaiah 2:3 Many peoples will come and say, 'Come, let us go up to the mountain of the Lord, to the temple of the God of Jacob. He will teach us his ways, so that we may walk in his paths.' @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 5 авг.1 180258

    መንገድና እውነት ሲስማሙ—ሲጣጣሙ—መድረሻ ይቀርባል። የእግዚአብሔር መንገድም የእግዚአብሔር እውነት ያለበት ነው፤ በእርሱ መንገድ እየተጓዝን ነው ብሎ እውነትን ማቅጠን ወይም መቀላቀል አይገባም። ዳዊት እንደ ጸለየውም፣ "መንገድህን አስተምረኝ፤ በእውነትህም እሄዳለሁ" (86፥11) ለማለት ቁርጠኝነት ያስፈልገናል። በዚያው መንገድ ለመጓዝ የወሰኑም እንደ ዘማሪው፣ "ስምህን እፈራ ዘንድ፣ ያልተከፋፈለ ልብ ስጠኝ" ሊሉ ይገባል። በሁለት ልብ ፍርሀት የለም፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ልባቸው—ትኩረታቸው—እርሱ ላይ ብቻ ሊሆን ይገባል፤ ያን ጊዜም መንገዱ መንታ አይሆንም። እውነት አንድ ስለሆነች፣ አንድ መንገድ ላይ ነው የምትገኘው። ፍላጎት ያላቸውም ይጸኑባታል። Psalms 86:11 Teach me your way, Lord, that I may rely on your faithfulness; give me an undivided heart, that I may fear your name. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 4 авг.1 122213

    መንገድ ጠያቂዎች አለማወቃቸው ብቻ ሳይሆን ማወቅ መፈለጋቸውንም ይገልጻሉ። እግዚአብሔርን የሚታመኑ ሰዎች ጸሎት፣ መንገዱን ለማወቅ መፈለጋቸውን (በጸሎቱ) ይገልጻሉ። ዳዊት ነፍሱን ወደ እግዚአብሔር እንደሚያነሣ ከገለጸ በኋላ፣ "አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም" አለ፤ ጭንቀቱን ተናግሮም፣ "እግዚአብሔር ሆይ፤ አካሄድህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ" ይላል (25፥4)። እየታመኑ መንገዱን መጠየቅ፣ በመንገዱ እየሄዱም በእርሱ መታመን ይገባል። እግዚአብሔርን ፈጽመው የተከተሉ አካሄዱን (አደራረጉን) የተረዱ ናቸው። መንገዱም ለታመኑበትና አቅም ለሚቀበሉበት በቀላሉ የሚሄዱበት ሲሆን፣ ፍጻሜውም ያማረ ነው። Psalms 25:4 Show me your ways, Lord, teach me your paths. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 3 авг.1 175264

    ሰማያዊ ተልዕኮ በሰማያዊ ክብር ካልታጀበ ለምድር አይከብድም—ታች ካለው ተግዳሮት በላይ አይሆንም፤ ሙሴ ይህንን ስለተረዳ የእግዚአብሔርን ክብርና ሞገስ ጠየቀ። የሚመራው ሕዝብ ከባድ፣ የሚሄድበት መንገድ አስቸጋሪ፣ በመንገዱ የሚገጥመው ፈተና አታካች፣ ከፊት ለፊቱ የሚጠብቀውም ሕዝብ ብርቱ ነበር። እግዚአብሔር የመንገዱ ባለቤትና መሪ፣ በመንገዱም ላይ ጠባቂና አጋዥ ካልሆነ ከግቡ ለመድረስ ከባድ እንደሚሆንም ተረድቷል። ስለዚህም፣ ይህንን ጸሎት ጸለየ፤ "በእኔ ደስ ተሰኝተህ ከሆነ፣ አንተን ዐውቅህና ያለ ማቋረጥ በፊትህ ሞገስ አገኝ ዘንድ መንገድህን አስተምረኝ" (ዘፀ 33፥13)። ከኋላው፣ አሥሩ መቅሰፍቶችና የባህሩ መከፈል ቢኖርም የአምላክ መንገድ የማይለመድ እንደ ሆነ ገብቶታል። የእግዚአብሔር መንገድ ወጥና ቀጥ ያለ፣ እውነትና በጎነት ያለበት ነው። በሰዎች መካከል በምድር ላይ ስለሚዘረጋም ይማሩታል፣ ይከተሉታል፣ ይጸኑበታልም። መንገዱን የሚማሩም፣ አምላካቸውን ያወቁ፣ ይበልጥ ለማወቅም የሚጓጉ ናቸው። Exodus 33:13 If you are pleased with me, teach me your ways so I may know you and continue to find favor with you. Remember that this nation is your people. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 2 авг.1 204224

    የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ተዘጋጀለት ማደሪያ ከገባ በኋላ ዳዊት አምላኩን በሕዝቡ ፊት ከፍ ከፍ አደረገ። ጥሪው የአምላኩን ማንነት ያገናዘበ፣ ለስሙ ክብር የሰጠና በእርሱ የሚገኘውን ትሩፋት (ጥቅም) የገለጸና ያስተጋባ ነው። ሥራውን ንገሩ ካለ በኋላም፣ "ዘምሩለት፤ ውዳሴም አቅርቡለት፤ ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ" (1ዜና 16፥9-10) ይላል። እርሱ፣ እያወደስነው የምናከብረው፣ እየቀረብነውም ደስ የምንሰኝበት አምላክ ነው። ስሙም መኩሪያችን ነው። እግዚአብሔርን የሚያወድስ ሕዝብም ሁልጊዜ ራሱን ሕልውናው ውስጥ ያገኛል። 1 Chronicles 16:9-10 Sing to him, sing praise to him; tell of all his wonderful acts. Glory in his holy name; let the hearts of those who seek the Lord rejoice. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 1 авг.1 333275

    #ArtSaturdays መላእክት ለእግዚአብሔር ልጅ ለኢየሱስ “በግንባራቸው ተደፍተው” ክብርን ሰጡ፤ ምስጋና አቀረቡ፤ ውዳሴን አስገቡ። የክርስቶስ ማንነት፣ ግርማና ሥራ በሰማይ አካላት ዘንድ ፈጽሞ የታወቀ ስለሆነ፣ ለእርሱ የሚገባው ክብርና ውዳሴ ሳይጓደል ይቀርብለታል። መላእክቱ፣ “ለአምላካችን” ብለው ለመለኮት የሚገባውን ክብር በብዙ ትሕትና ካቀረቡና በግንባራቸው ከተደፉለት፣ የኅጢአት ይቅርታ ያስገኘላቸውና ያዳናቸው ሰዎች ምን ያህል ሊያከብሩትና ሊገዙለት ይገባቸው! ውለታን የሚያውቅ ሕዝብ ውዳሴ አያጓድልም። Revelation 7:12 saying: 'Amen! Praise and glory and wisdom and thanks and honor and power and strength be to our God for ever and ever. Amen!' @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 31 июл.1 346216

    በክርስቲያኖች ላይ የሚመጡ ነገሮች ሁሉ—ምንጫቸው ጌታ ባይሆንም—በእግዚአብሔር የሚፈተሹ፣ ጎጂነታቸው የሚመዘንና ለተሻለ ማንነትና ሕይወት የሚመነዘሩ (ጥቅም ላይ የሚውሉ) ናቸው። ይህ እውነት በአዲስ ኪዳን ተደጋግሞ ተስተጋብቷል። ጴጥሮስም ከእምነታቸው የተነሣ በየስፍራው ተበትነው ላሉ ክርስቲያኖች የሚያሳስባቸው ይህንኑ ነው፤ ". . .በእሳት ተፈትኖ ቢጠራም፣ ጠፊ ከሆነው ወርቅ ይልቅ እጅግ የከበረው እምነታችሁ እውነተኛ መሆኑ እንዲረጋገጠና ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፣ ክብርንና ውዳሴን እንዲያስገኝላችሁ ነው" (1፥7)። እንግዲህ፣ የመከራ እሳት እምነትን ያጠራል፤ የእምነት ግንኙነትንም ከፍ ያደርጋል። ለአዳነን ጌታም ብዙ ክብር፣ ምስጋናና ውዳሴ እንዲቀርብ ያደርጋል። በመከራ ተፈትነው የሚጸኑ ባለ ብዙ አውታር የሆነው አምልኳቸው ስለማይቋረጥ፣ ለጌታ ብዙ ክብርን የሚያመጡ፣ ውዳሴንም የሚያበዙ ናቸው። 1 Peter 1:7 These have come so that the proven genuineness of your faith—of greater worth than gold, which perishes even though refined by fire—may result in praise, glory and honor when Jesus Christ is revealed. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 30 июл.1 209231

    የነቢዩ ኢሳይያስ ውዳሴ በእግዚአብሔር ውለታ ላይ ያርፋል፤ "እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አወድሳለሁ፤ አስቀድሞ የታሰበውን፣ ድንቅ ነገር፣ በፍጹም ታማኝነት አድርገሃልና" (25፥1)። ስሙ ሥራውን ይቀድማል፤ ያስከትላልም። ድንቅን የሚያደርግ አምላክ፣ በሁሉ ቦታና በሁሉ ዘንድ ታማኝነቱን ይዞ የሚቀጥል አምላክ ስለሆነ፣ ሊከበር፣ ውዳሴ ሊቀርብለትም ይገባል። እግዚአብሔርን አወድሰው የሚቆጩ የሉም፤ ማንነቱ አይቀየርም፣ ኀይሉም አይደክምምና። Isaiah 25:1 Lord, you are my God; I will exalt you and praise your name, for in perfect faithfulness you have done wonderful things, things planned long ago. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 29 июл.1 297243

    ውዳሴ ውጤት ላይ ያርፋል። እግዚአብሔርም ስለ ሥራው የሚመሰገንና የሚወደስ አምላክ ነው። ሥራው እንከን የማይወጣለት፣ እርሱም ፈጽሞ የማይሳሳትና በእውቀተና በጥበብ የማይጎድል ስለሆነ፣ የሚሠራው ሁሉ ትክክል፣ ሙሉና ፍጹም ነው። የሥራው፣ ያም የፍጥረቱ፣ መዋጀቱ፣ ትድግናውና ጸጋው ተባባሪ—አጋዥ—ባንሆንም እንኳን፣ እውቅና እንሰጠዋለን፤ ለክብሩም አድናቆታችንን እንገልጣለን። የመዝሙር መጽሐፍ የመጨረሻው መዝሙርም የሥራው ብርታትና ታላቅነቱ ሊያስወድሰው እንደሚገባ ያውጃል፤ "ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት፤ እጅግ ታላቅ ነውና ወድሱት" (ቍ. 2)። የእግዚአብሔርን ሥራ—ከፍጥረት እስከ ማዳን—ያስተዋሉና ያሰላሰሉም ለማንነቱ የሚመጥን ምስጋናና ውዳሴ አቅርበው አይጨርሱም። Psalms 150:2 Praise him for his acts of power; praise him for his surpassing greatness. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

  • 28 июл.1 423224

    ለእግዚአብሔር እየሆኑ፣ ለእግዚአብሔር እየሰጡ፣ እርሱን ማወደስ ትልቅ ክብር ነው። የመጀመሪያውን ቤተ መቅደስ ለመሥራት ፈልጎ፣ ልጁ ሰሎሞን እንጂ እርሱ እንደማይሠራ በእግዚአብሔር የተነገረው ዳዊት፣ ለመቅደሱ ሥራ የሚሆን ብዙ ሐብት ሰጠ፤ ሌሎችም እንዲሁ አደረጉ። "ስጦታው በገዛ ፈቃድና በፍጹም ልብ የቀረበ" ስለ ነበር፣ ሕዝቡ ሁሉ ደስ ተሰኘ፤ ዳዊትም እግዚአብሔርን አከበረ፤ "ባለጠግነትና ክብር የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተም የሁሉ ገዥ ነህ፤ ከፍ ከፍ ለማድረግ፣ ለሁሉም ብርታትን ለመስጠት፣ ብርታትና ኀይል በእጅህ ነው። አምላካችን ሆይ፤ አሁንም እናመሰግንሃለን፤ ለከበረው ስምህም ውዳሴ እናቀርባለን (1ዜና 29፥12-13)። የራሱን ምስጋናና ውዳሴ ከጨረሰም በኋላ፣ ሕዝቡን፣ "አምላካችሁን እግዚአብሔርን ወድሱት" አላቸው። አምላካችንን ስናከብረው፣ ሌሎችም እንዲያከብሩት እንጓጓለን። 1 Chronicles 29:20 Then David said to the whole assembly, 'Praise the Lord your God.' So they all praised the Lord, the God of their fathers; they bowed down, prostrating themselves before the Lord and the king. @ethbiblica Telegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

Daily Injera — tgindex