ቢብሊካ ኢትዮጵያ (Biblica Ethiopia)
Статистика- Последний пост
- 09:04
- Последнее чтение
- 09:52
- Постов за неделю
- 12
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 324
- 1/48двое суток
- 371
- 1/72трое суток
- 400
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
መልእክተ ሰንበት የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚያከብሩ እርሱን ያወቁ ናቸው። ይህ ዕውቀት ደግሞ መቅረብን ያቀርባል፣ በፊቱም ንጹሕ ድፍረትም ይሆናል። እነርሱም ከዮሐንስ ጋራ እንዲህ ማለት ይችላሉ፤ "ትእዛዞቹንም ስለምንጠብቅና በፊቱም ደስ የሚያሠኘውን ስለምናደርግ የምንለምነውን ሁሉ ከርሱ እንቀበላለን" (1ዮሐ 3፥22)። መታዘዛቸው ልመናቸውን ያስውባል፤ ጥያቄያቸውም አቅርቦቱን ይገናኛል።
መልእክተ ቅዳሜ ባርነት መገዛትን ብቻ ይጠይቃል። ነጻነት ደግሞ መታዘዝን። በክርስቶስ ለሆኑ ደግሞ የተሰጠው ሕግ (ትእዛዝ) አርነትን የሚያጎናጽፍ ነው፤ "ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ ተመልክቶ የሚጸና፣ የሰማውን የሚያደርግና የማይረሳ ሰው በሥራው ብሩክ ይሆናል" (ያዕ 1፥25)። ቃሉ ከሸክም ወደ ዕረፍት ያመጣል። ይህ ዕረፍት ደግሞ ጠቃሚና ውጤታማ የሚያደርግ እንጂ ለሌላ ባርነት የሚዳርግ አይደለም፤ አንዳንዶች ዕፎይታቸውን ወደ ባሰ እስራት እንደሚለውጡበት። በሰሙት የሚጸኑ ግን ብሩካን ይሆናሉ። ነጻነታቸውም የብዙ ፍሬ ምክንያት ይሆናቸዋል።
የዕለቱ ሐሳብ ክርስቶስ ጌታ የመታዘዝ ምሳሌ ነው፤ በአምላክነት ላይ ሰውነትን ለመጨመር ታዘዘ። ትሕትናን ተላብሶ ወረደ፤ "ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ። ስለዚህ እግዚአብሔር እጅግ ከፍ አደረገው፤ ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው" (ፊል 2፥8-9)። በዚህ መታዘዝ እኛን ሁሉ የራሱ አደረገ። ትቶት የወረደውንም ከፍታ በመታዘዙ—በብዙ የነፍስ ምርኮ—ተጎናጸፈው። በመታዘዙም ወደው የሚገዙለትን የራሱ አደረገ። አብ አባቱም፣ ሰው ሲሆን የወሰደውንም የአዳኝነት ስም—ኢየሱስ—እስካሁን ከተጠሩትም ሆነ ወደፊት ከሚጠሩት ስሞች በላይ ከፍ ከፍ አደረገው።
የዕለቱ ቃል "ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ። ስለዚህ እግዚአብሔር እጅግ ከፍ አደረገው፤ ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው፤" (ፊል 2፥8-9 አመት)
የዕለቱ ሐሳብ በምድር ላይ የሚወድቅ ዘር ያበቃቀል ሥርዓት እንዳለው ሁሉ፣ የሰዎችም ዕድገት እንዲሁ ነው። ጌታችን በወይን ተክል በተመሰለበት የዮሐንስ 15ቱ ምሳሌ እንዲህ አለ፤ "በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ፤ ይሰጣችኋልም" (ቁ. 7)። ቅርንጫፍ የራሱ ሕይወት የለውም። አቅርቦቱን ሁሉ ከተክሉ ያገኛል። ከላይ የሚወርደው ዝናብ ቢያረጥበውም እንኳን ሕይወት አይሆነውም። ለልምላሜ የሚሆነውን የሚያገኘው በግንዱ በኩል ነው። እኛም የሚያስፈልገንንና የምንፈልገውን የምናገኘው በርሱ በመኖር ነው። ቃሎቹንም ስንኖር በፈቃዱ ክልል ያቆዩናል። የሚሰጠንን ሁሉ እንድንለምንም ያበቁናል።
የዕለቱ ቃል "በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ፤ ይሰጣችኋልም።" (ዮሐ 15፥7 አመት)
የዕለቱ ሐሳብ የሚያምኑትንና የሚወድዱትን መታዘዝ ቀላል ነው። ከእግዚአብሔር በላይ ለዚህ ብቁ የሚሆንስ የት ይገኛል?የሚጠበቀውም መስማማት ብቻ ነው፤ አቅም ከርሱ ዘንድ ይመጣልና። ቃሉ እንዲህ ይላል፤ "ዕሺ ብትሉ፣ ብትታዘዙም የምድርን በረከት ትበላላችሁ" (ኢሳ 1፥19)። የዚህ ግልባጩ ደግሞ ለአጥፊው አልፎ መሰጠት ነው። እግዚአብሔርን ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ 'ዕሺ' አይሉትም፤ ሁልጊዜ እንጂ! እርሱ ለተወሰኑ ጉዳዮችና ለተለዩ ሁኔታዎች ብቻ የሚፈለግ አይደለም፤ ለሁለመናና ለሁልጊዜ እንጂ።
የዕለቱ ቃል "ዕሺ ብትሉ፣ ብትታዘዙም የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤" (ኢሳ 1፥19 አመት)
የዕለቱ ሐሳብ ጽድቅና ዓመፅ በሚነጻጸሩበት ብቻ ሳይሆን አንዱ ሌላውን በሚቃረንበት ጊዜ፣ ሕያው አምላክንና የርሱን ብቻ ይዞ መጽናት የባሕርይ ልቀት ነው። እርሱ ዘመኑን ጠንቅቆ እንደሚያውቅ ሰዎችንም እንዲሁ ይለያል፤ "እግዚአብሔር የንጹሓንን የሕይወት ዘመን ያውቃል፤ ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል" (መዝ 37፥18)። ዕውቀቱ በአቅርቦቱ ይታጀባል፤ በሚሰጠው ተስፋም ያብባል።እርሱን በመስማትና በመታዘዝ ልዩነትን ለሚያሳዩም መዝገቡ ሙሉ ነው።
የዕለቱ ቃል "እግዚአብሔር የንጹሓንን የሕይወት ዘመን ያውቃል፤ ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል።" (መዝ 37፥18 አመት)
የዕለቱ ሐሳብ መታዘዝ አቅርቦትን ይቀድማል። ኤልያስ የእግዘብሔርን ቃል ሰማ፤ አምኖም ታዘዘ። የመጣለት ቃልም መራው፤ "ስለዚህ እግዚአብሔር ያዘዘውን ፈጸመ፤ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ወዳለው ወደ ኮራት ወንዝ ሄዶ በዚያ ተቀመጠ። ቍራዎችም ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ውሃም ከወንዙ ይጠጣ ነበር" (1ነገ 17፥5-6)። ቍራ ብልኀ ወፍ ቢሆንም በቀላሉ የሚገራ ግን አይደለም--የኖህን ገጠመኝ ልብ ይሏል። እግዚአብሔር ሲያዝዘው ግን መልእክቱንም ሆነ ጊዜውን አላዛነፈም። ጌታ ቃሉን ለሚታዘዙ ሁሉ ሌላውንም ያስገዛላቸዋል።
የዕለቱ ቃል "ስለዚህ እግዚአብሔር ያዘዘውን ፈጸመ፤ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ወዳለው ወደ ኮራት ወንዝ ሄዶ በዚያ ተቀመጠ። ቍራዎችም ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር፤ ውሃም ከወንዙ ይጠጣ ነበር።" (1ነገ 17፥5-6 አመት)
መልእክተ ሰንበት በጌታ ፍቅር ውስጥ አቅም አለ። ጥሪውም አስቻይ ነው፤ “በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እርሱን በማወቅ ለሕይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገንን ሁሉ የመለኮቱ ኀይል ሰጥቶናል” (2ጴጥ 1፥3)። የተቀበልነውን ሕይወት የምንኖርበትን አቅም ከመለኮቱ ሙላት ተቀብለናል። በዚያም ከእውነት የጎደለ መንፈሳዊነት የለም።
መልእክተ ቅዳሜ ክርስቶስ ጌታ አይለወጥም። የማንነት መዋዠቅ፣ የባሕርይ ሽግሽግ፣ ወይም የአቅም መቀነስ በርሱ ዘንድ አይታሰብም። የዕብራውያን ጸሐፊ እንደ ገለጠው፣ "ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬም ለዘላለምም ያው ነው" (13፥8)። በመለኮት ሙላት እስከ ዘላለም ይኖራል። አቅሙ ሙሉ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ፍቅሩም ሙሉ ነው። ሳይለወጥ ይለውጣል፤ ሳይጎድል፣ የጎደሉትን ይሞላል።
የዕለቱ ሐሳብ የጌታ ሰውነት ሞቶ የተነሣ ብቻ ሳይሆን የመለኮት ሙላትና የክብር ነጸብራቅን የያዘ ነው፤ "እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዟል። የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ" (ዕብ 1፥3)። ሁሉ በርሱ ተገኝቷል፤ እርሱም የሁሉ ወራሽ ነው። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የመለኮትን ክብር ከምሕረት ጋራ አቀረበልን። ኀያል ቃሉም ሕይወታችንንና ነጋችንን አጽንቶ ይዟል።
የዕለቱ ቃል "እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዟል። የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።" (ዕብ 1፥3 አመት)
የዕለቱ ሐሳብ ቃል ሥጋ ሲሆን መለኮት አልቀነሰም፤ ይልቁንም ለሰው ልጆች ቀረበ፤ "የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በርሱ ይኖራልና" (ቈላ 2፥9) ተብሎ እንደ ተጻፈ። ጌታችን ሊቀ ካህናት ሲሆንልን መለኮትነቱን ይዞ ነው። በሰውነቱ መሥዋዕትነቱን ፈጸመ፡፡ በአምላክነቱም ድነትን አጸና። በዚህ ክብሩ በአብ ቀኝ እንድሚታይልን፣ ስሙን በምንጠራበት ነገር ሁሉ በማንነቱ ይገለጣል። ድነትና ትምክህታችን ማንነቱና 'ሙላቱ' ነው።
የዕለቱ ቃል "የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በርሱ ይኖራልና፤" (ቈላ 2፥9 አመት)
የዕለቱ ሐሳብ ጌታ ፍጥረቱን ያስገኘ ብቻ ሳይሆን የሚቆጣጠርና የሚገዛም ነው፤ "ሁሉ ነገር በርሱ ተፈጥሯል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በርሱና ለርሱ ተፈጥሯል።" (ቈላ 1፥16)። ሁሉ በርሱ እንደ ተፈጠረ፣ ለርሱ ተፈጥሯል፤ ገዦችና ባለሥልጣናት ከርሱ እይታና ቍጥጥር አይወጡም። ኅይሉና ማንነቱም ሁሉን ሞልቷል። ጌታ በሁሉ አለ። የርሱ ለመሆን የሚፈቅዱም፣ ከርሱ የተነሣ ከሁሉ በላይ ከፍ ይላሉ—በሰማያዊ ስፍራ በርሱ እንደ ተባረኩ። በምድር ከፍ ያሉትን ሁሉ ከላይ እንደማየት ያለ ዕድል የለም!
የዕለቱ ቃል "ሁሉ ነገር በርሱ ተፈጥሯል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በርሱና ለርሱ ተፈጥሯል።" (ቈላ 1፥16 አመት)