ናይናን - Naynan
Статистикаየእግዚአብሔር ቃል ትምህርት የጸሎት የማማከር አገልግሎትን ያገኛሉ። እንዲሁም አጫጭር መንፈሣዊ የድምጽ መልዕክቶችም በዚህ ቻናል ይለቀቃሉ። የyoutube ቻናላችንንም ይከታተሉ። 👇👇👇👇👇 https://www.youtube.com/@bereketkebede3418 @ናይናን
- Последний пост
- 27 янв.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ኢየሱስ በጥፋተኞች እናዝንባቸዋለን ፤ ጌታ ግን ያዝንላቸዋል።ስለጎዱን እናለቅሳለን ፤ ኢየሱስ ግን በጥፋታቸው ስለሚጎዱ ያለቅስላቸዋል።ሰላም ስላሳጡን እናባርራቸዋለን ፤ እርሱ ግን ሰላም ሆኖ ይሰበስባቸዋል።ስለጣሉን እናዝንባቸዋለን ፤ እኛን በመጣል ስለወደቁ ያዝንላቸዋል።መልኩ እዝነት ነው።ኃጢአተኛውን አይገፋም።ሁሌም ደጁ ክፍት ነው።ርኅራኄው አልቆ አያውቅም።ለወደቁት ይራራል።በየማለዳው የምህረቱ ብዛት ምድርን ይሸፍናል።በቸርነቱ ያቆማል።ይደግፋል።ያጸናል።ዳግመኛም ያበረታል።ብርታት የሌላቸው በእርሱ ይበረታሉ።ደካሞችም ይጸናሉ።እጁ ሁሉን ትረዳለች።ክንዱም ታጸናለች።ከወንድም በላይ ይጠጋጋል።ከእስትንፋስ ይልቅም ቅርብ ነው።የተረሱትን ያስታውሳል።ለተጠቁት ሁሉ ያዝናል።ለአጥቂዎች ልቡ ይደማል።ቀኑን ሙሉ ወደማይፈልጉት ህዝቦች እጁን ይዘረጋል።የምህረቱንም ኃይል ያሳያቸዋል።ለእነርሱ እንደሞተ ያስታውሳቸዋል።ብዙ ሺሆችን ወደ መንግሥቱ ያፈልሳል።ኃጢአተኞችን ያጸድቃል።የማይለካ ፍቅር ፣ የማይብራራ ምህረት ያለው ባለጠጋ ነው። ክብር ለኢየሱስ!
በሮች ሁሉን ክፍት እንዳልሆኑ መረዳት ያስፈልጋል።ዝግ በሮች መዓት ሲሆኑ ለምን እኔን ከማለት መቀበልን መምረጥ ይገባል።አስቂኙ እና የሞኝ የህይወት መርህ በሮች ሁሉ ክፍት ሆነው እንደሚጠብቁን ማሰብ ነው።ይህ ግን ላይሆን ይችላል።እግዚአብሔርም ሁሉን በሮች ከፍቶ የሚሰጥ ሳይሆን የሚያስፈልገንን ብቻ የሚሰጥ ነው።አንዳንዶች የምትለምኑትን አታውቁም ተብለዋልና።ምን እንደምንለምን አለማወቅ በመልሱ መቅረት እንድናዝን ያደርገናል።በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ስንሆን ግን ሁሉም በር ዝግ ሁሉምም በር ክፍት አይደለም።ተስፋ ስናደርግም በእውቀት ቢሆን ይመረጣል።አምላክ እውነተኛውን መንገድ ሲመራን የተዘጉ በሮችን ቢከፍትም አንዳንዴ ላይሆንም ይችላል።እምነት በነገሮች መቀየር ላይ መቆም ሳይሆን በእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ላይ መደገፍ ነው።
ዮሐንስ 14:12 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።
የመጨረሻው ድንቅ መገለጥ ኢየሱስ ነው።በዘፍጥረት አንድ ላይ የተፈጠሩት ድንቅ አይደሉም ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ግን እሱ ድንቅ ነው።
ትልቁ የህይወት ሕግ በከባድ ጉዳዮች ላይ ከብዶ መገኘት ነው።የክብደት መንገዱን ከኢየሱስ የጀመረ ደግሞ ከብዶ ጀምሯልና መቅለል አይቻለውም።
በማን ስም እንጠመቅ? (ክፍል 1) ስለ ጥምቀት በተነሣ ቁጥር በወንጌላዊያንና በሐዋርያት ቤተክርስቲያን አማኞች መካከል የሚደረገው ሙግት ጥምቀት በማን ስም መደረግ አለበት የሚለው ነው።ይህንንም መመርመር እውነተኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ለማወቅና ለመያዝ ይጠቅማል።በኢየሱስ ብቻ አማኞች እምነት ጥምቀትን በአብ፣በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ማድረግ የተሳሳተ አመለካከት ነው።መጽሐፍ ቅዱሳዊም አይደለም የሚል ሙግት ይቀርብበታል።ስለሆነም በእነርሱ እምነት ጥምቀት በኢየሱስ ስም ብቻ ነውና በሌላው ስም ከተደረገ ስህተት ነው ብለው ያምናሉ።እንደ ክርስቲያን ልንጠይቅ የሚገባው የመጽሐፍ ቅዱስን አስተማሪነት ስለሆነ ይህንን ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ መፈተሽ ያስፈልጋል። መጽሐፍ ቅዱስ በማቴ 28:19-20 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ፣በወልድና በመንፈስ ቅዱስ እያጠመቁ አህዛብን ደቀመዛሙርቱ እንዲያደርጉለት ተከታዮቹን አዝዟል።በሐዋ 2:38 እና በሌሎች የሐዋርያት ሥራ ክፍሎች ደግሞ ሐዋርያቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰዎችን አጥምቀዋል።ይህንን በመያዝ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን አማኞች ``ሰው መጠመቅ ያለበት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ብቻ ነው'' በማለት የማቴ 28:19-20 ያለውን ጥቅስ ሦስቱ ስም ለኢየሱስ የተሰጡ የክብር ስሞች እንጂ መጠሪያዎች አይደሉም እንዳልሆኑ ያስተምራሉ። እዚህ ስፍራ ላይ በተለያዩ መጻሕፍቶቻቸው የምናውቃቸው ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ ``ዐበይት መናፍቃን'' በተሰኘ ሥራቸው በገጽ 153-154 የጠቀሱትን እንመልከት። ``በሐዋርያት ሥራ በኢየሱስ ስም' የተጠመቁት ሰዎች በሥጋም ሆነ በሃይማኖት አይሁዳዊ የሆኑት ብቻ ናቸው።በዝርዝር ሲያስቀምጡትም፦ 1.ዕብራዊያን ወይም በትውልድ እስራኤላዊ የሆኑ(2:5 ፤ 2:38 ፤ 22:16) 2.ሳምራዊያን (እነዚህም በምርኮ ከአህዛብ ጋር የተቀላቀሉ አይሁዶች ናቸው)(ሐዋ 8:12/16) 3.በትውልድ አህዛብ ሆነው የይሁዲ ሃይማኖትን የተቀላቀሉ(ሐዋ 10፥12:22:48) 4.የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት (ሐዋ 19:1-5)(እነዚህም `አብርሃም አባት አለን'' የሚሉ አይሁዶች ነበሩ።ማቴ 3:5)'' በማለት ያስቀምጡታል።
የሕግን ባህሪይ ያልተረዳ የኃጢአትን ባህሪይ አያውቅም።የኃጢአትን ባህሪይ ያልተረዳ ደግሞ የአዳኙን ባህሪይ አይረዳም። ዮሐንስ ቡንያን
እግዚአብሔር የአዳምን እርቃን ለመሸፈን የገፈፈው ቆዳ ከሞተ እንስሳ እንደሆነው የተስፋው ሙላት ሲገለጥም የሞተው ኢየሱስም ለተቀበሉት ሁሉ እርቃናቸውን የሸፈነ ልብስ ሆኗል።
``የአካሉ ጥላዎች'' ስድሳ ስድስት መጻሕፍትን የያዘው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳን በተባሉ በሁለት ዐበይት ኪዳናት ይከፈላል።እነዚህ ኪዳናትም ሁለቱም ስለ ክርስቶስ ሲናገሩ የየራሳቸው የትረካ ዘይቤም አላቸው።ብሉይ ኪዳን ስለ ክርስቶስ ተስፋን ሲናገር አዲስ ኪዳን ደግሞ የተስፋውን መፈጸም ያበሥራል።በዚህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሆነው ይህንን ተስፋ በንግግራቸውም ሆነ በኑሯቸው የሚናገሩ ሰዎች ነበሩ።እነርሱም ለሚገለጠው አካል ጥላ የሆኑ የአካሉ ጥላዎች ናቸው።እነዚህም በኑሯቸውና በንግግራቸው ከክርስቶስ ጋር ያላቸው ግንኙነት የተስፋ ቃል ተናጋሪነታቸውን ያሳያል።ስለሆነም ``የአካሉ ጥላዎች'' በሚል ርዕስ ይህንን ርዕሰ ጉዳይ በተከታታይነት እንማራለን። ዘወትር ሰኞ ፣ ማክሰኞ እና ረቡዕ ምሽት 3 ሰዓት በተከታታይነት ይቀርባል። #ናይናን
#አንደኛ_ሳይሆን_ምርጫ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ደቀመዛሙርቱን ከወቀሰበት ምክንያቶች አንዱ #እምነት ነው።የእምነት እጦት የተሰጣቸውን እንዳያውቁና እንዳይጠቀሙበት አድርጓቸው ነበር።እምነት ቢኖራቸው ሊንዱት የሚችሉትን ትልቅ ተራራ እያሳያቸው እነርሱ ግን ሊያምኑት አልቻሉም ነበር።አለማመን ክርስቶስ እንዳይሠራ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ነው።አንዳንድ ጉዳዮች ያልተሳኩልን ምናልባትም ከእምነት ማጣታችን ሊሆን ይችላል።እግዚአብሔር ሲታመኑት የሚወድ አምላክ ነው።አንድ ወቅት ወደ ገደል እየተንሸራተተ ያለ አንድ ሰው አንዲት ቅርንጫፍ ይዞ ወደታችና ወደላይ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ይቆያል።ከዚያም እግዚአብሔር እንዲረዳው ይለምናል።እግዚአብሔርም መልዓኩን ላከለት።መልዓኩም መጥቶ #ቅርንጫፉን_ልቀቀው_እኔ ላድንህ_ተልኬአለሁና ቢለውም ሰውዬው ግን ቅርንጫፉን ከለቀቀ እንደሚሞት አስቦ እምቢ አለ።መልዓኩም ተለየው። ልክ እንዲሁ እኛም እግዚአብሔር እንዲረዳን ብንጮህም እምነታችንን ግን በሥራ አናሳይም።እግዚአብሔር #ያለኸኝ_አንተ_ብቻ_ነህ ስንለው እንጂ ከሌሎች ጋር አማራጭ ስናደርገው አይወድም።አለማመናችንን እንዲረዳው መጸለይ ይገባናል።ምክንያቱም አለማመን ቤቱን ሠርቶብን እንኳን ሥራውን የእርሱን መኖር ራሱ ሁኔታዎቻችን እያጠራጠሩን ይገኛሉ።አምንሃለሁ በሚል ፉከራ ሳይሆን #አለማመኔን_እርዳው በሚል ልመና በፊቱ መሆን ያሻናል።እግዚአብሔር ምን ያህል ልመንህ ብንለው የሚለን #አንደኛ_ሳይሆን_ብቸኛ_አድርጋችሁ_እመኑኝ ነው።አንደኛ ሳይሆን ብቸኛ አድርገን እንድናምንህ እርዳን። #ናይናን
እርካታ ማጣት እየታገላችሁ ያላችሁ ወገኖች ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ። ዓለም የምታሰቃየው በመጀመሪያ የሚወዳትን ነው ። ወዳጅን የሚያውቀውን ፣ ወዳጅነትን የሚያከብረውን እግዚአብሔርን ተጠጉ ። “ሰይጣን ለወዳጁ አይሆንም” ሲባል ትሰማላችሁ ። በሰዎች ፊት ለማልቀስ ትልቅነታችሁ እንቅፋት ሆኖባችኋል ። ሳይታዘብ ድካማችሁን ለሚሰማው ጌታ በእንባ አዋዩት ። የእርሱ ገበያ መልካም ነው ። የማይገኝበት በረከት የለም ። የሚገርመው በክፍያ ያጣችሁትን ሰላም ከእርሱ ዘንድ በጸጋ ትቀበላላችሁ ።
ሰላም ቅዱሳን በዚህ ቻናል ሲቀርቡ የነበሩ ትምህርቶች ተቋርጠው እንደቆዩ ይታወቃል።ከሰሞኑ የተቋረጡትንም ሆነ አዳዲስ ትምህርቶችን ማቅረብ እንጀምራለን። ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!
መስቀሉ ክርስቶስ ፍቅሩን የሰበከበት ምስባኩ ነው።የመስቀሉ ፍቅር ከመስቀሉ በፊት ያልነበረ ፥ ከመስቀሉ በኋላም ያልተደገመ ነው።በዓለም ታሪክ ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ፥ እረኛው በጎቹን ስለወደደ በግ ሆነ ፥ ለበጎቹ የተዘጋጀውንም ሞት በመስዋዕትነት ተቀብሎ ሌሎቹ በጎች እንዳይሞቱ እርሱ ሞተ።በግ የሚወድ ሰው የመጨረሻ ተግባሩ እረኛ መሆን ነው።ክርስቶስ ግን እረኛ ብቻ ሳይሆን በግ ሆነ።ፍቅርም ያኔ ትርጉሙን አገኘ።
መረቤን ተውኩልህ። ደስ አለህ? የተውኩት ያልተወኝ በየቀን ዕለቱ ይዤው የምታየው ተውኩልህ ምለውን ያንን መረቤን ነው። አላዋጣ ካልከኝ ባንተ ከከሰርኩኝ መረቤን ለማንሳት ደግሜ እያሰብኩኝ እከተልሃለሁ፤ ትርፍ ኪሳራዬን ባንተ ውስጥ እያየሁ። ጆሮ ቆረጥኩልህ። ደስ አለህ? ሊይዙህ ቢመጡ ሊገድሉህ በመሻት ተከላከልኩልህ ሰይፌን በማንሳት ደስታዬ ቅጥ አጣ አንተን በማትረፌ አዝነህ ተመለከትኩ ደስታዬን አቅፌ የማልኮስ ደም ለእኔ ለሰይፌ ሲገበር ፤ አንተ ምታስበው ተውኩት ብዬ ያልኩትን ግን ደሞ ያልተወኝን ያንን መረብ ነበር። ደስ አለህ? አይ አይመስለኝም!
በደለኛን የሚያጸድቅ መሲህ በዚህ አለ።ደም የነካው መቆሸሹ ታውቆት ቢታጠብም የነካውን ሁሉ የሚያነጻ የተረጨበትን ሁሉ የሚያጸድቅ ደም በዚህ አለ።የሟቹን ሞት ሳይፈቅድ ለሟቹ የሚሞት ወዳጅ በዚህ አለ።ራሱን ለሞት ሰጥቶ ወንበዴውን የሚታደግ አፍቃሪ በዚህ አለ።ለሰቃዩ የሚሞት ስቅል ክርስቶስ በዚህ አለ።ለመስቀል ሞት የታዘዘ ፣ በሸላቾቹ ፊትም ዝም ያለ የእግዚአብሔር በግ በዚህ አለ።እንደ ዮናስ በጥፋቱ አሳ አንባሪ ሆድ ውስጥ እንዳደረው ሳይሆን ለጥፋቴ በምድር ሆድ ውስጥ ያደረ ከዮናስ የሚበልጥ በዚህ አለ። መልካም የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ
እግዚአብሔር ሆይ ስለማይቀየረው ፍቅርህ ስለማይጠቁረው ፊትህ ስለማይሰለቸው መውደድህ ስለማይታክተው እገዛህ ስለማያልቀው ትዕግስትህ ስለማይጨረሰው ምህረትህ ስለማይርቀው ድምጽህ ስለማይደበዝዘው ገጽህ ስለማይቋረጠው ምክርህ ስለማይነጥፈው በረከትህ ስለማይቆመው ጥበቃህ አመሠግንሃለሁ!!
“ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።” — ዮሐንስ 6፥63
ልጅ ሳለሁ ሳምሶን የገደለዉን አንበሳን እፈራ ነበር ፤ ካደኩ በኋላ ግን አንበሳ ገዳዩን ሳምሶንን የገደለዉን መፍራት ጀምሬያለሁ !!
የደካማው ጩኸት እኔን ስትፈልግ የእኔን እየሰጠሁህ መኖሬ ኪሣራዬን አብዝቶታል።ያለ እኔ የሰጠሁሀህ መዝሙርና ጊዜ ፣ ስብከትና ሩጫዬ ሁሉ ከንቱ ነው።ጨዋታዋ በማይጥመው በዚህች ዓለም የጣፈጠ ኑሮን ፍለጋ መዳከሩ እኔነትን አጥፍቶ ተላላ ብቻ ያደርጋል።ያለ እኔ የምሰጥህም ትተህ እኔን ያዘኝ።የተንከራተተ ማንነት የሚፈልገውን እንኳ የማያውቅ በድቅድቅ ጨለማ የሚዳክር የህይወትም ዳገት ያጎበጠው ቁልቁለቱም ቢሆን ያለ ሐሳብ የሚያንደረድረው ነፋስ የበዛበት ህይወቴን ያዘው።ለመጮህ አቅም በማጣት ውስጥ ሆኜ እንኳ በፊት እጮሃለሁ።አቤቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን።ከረግረጉ ልታወጣኝ ከጨቀየሁበትም ልታነጻኝ ወደ እኔ ፍጠን።
እኛ ሰው ምንም መልካም ቢሆን የሚታየን ጥቂት ክፋቱ ነው።እግዚአብሔር ግን የእኔ ብሎ ሰውን ሲጠራ አያፍርበትም።ኃጢአተኛውንም በምሕረቱ ሲያጸድቅ ከልካይ የለበትም።