- Последний пост
- 9 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 216
- 1/48двое суток
- 247
- 1/72трое суток
- 266
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
እግዚአብሔር ያልመለሰው ጸሎት (በይዲድያ ብሬ) የእግዚአብሔር ርኅራኄ የጀመረው ሰዎች ስለ ጸሎት ምንነት አውቀው መጸለይ ከጀመሩ በኋላ አይደለም ። ቸርነቱ ከፍጹማን አካላቱና ከዘላለማዊው ባሕርዩ ጋር ጸንቶ የኖረ ነው ። ጸሎታችን የእግዚአብሔር ቸርነት መገለጫ እንጂ እርሱን ቸር ማድረጊያ አይደለም ። አንዳንዶች የአባት ፍቅር የመጣላቸው ከወለዱ በኋላ ነው ። መውለድ የለወጠላቸው ጭካኔና ግዴለሽነት ፣ ራስ ወዳድነትና ሞልቃቃነት አለ ። እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ቸር ነው ። ጸሎት በእኛ ፍላጎትና በጌታ ቸርነት የሚፈጸም ነው ። ጸሎት በአብዛኛው የነፍሳችንን ጉዳይ የሚመለከት ነው ። ፀሐይ ባናምንም ባንጸልይም ትወጣለች ። ሥጋዊ ነገሮች ላላመኑና ላልተመለሱ ሰዎች ሲደረጉ እናያለን ። ጸሎት በዋናነት የነፍሳችንን ጥያቄ የሚፈጽም ነው ። እውነተኛውን ጸሎት መጸለይ የሚችሉት ከእግዚአብሔር የተወለዱ ናቸውና ። አባት ብሎ እግዚአብሔርን ለመጥራት መወለድ ያስፈልጋል ። እግዚአብሔር ሁሉንም ጸሎታችንን ይሰማል ፣ ሁሉንም ግን አይሰጠንም ። አልተሰጠንም ማለት አልሰማንም ማለት አይደለም ። ባለመስጠት የሚሰማቸው ሰዎች አሉ ። እግዚአብሔር ጸሎትን በተለያየ መንገድ ይመልሳል ። እነዚህም መንገዶች አራት ናቸው ። 1- እሺ እሰጥሃለሁ ✅ 2- ጠብቅ ታገኛለህ ✅ 3- አይሆንም አይሰጥህም ✅ 4- በሌላ መንገድ እከፍልሃለሁ ✅ ጸሎታችን በእነዚህ አራት መንገዶች ተመልሰዋል ። እኛ አንድ ነገርን ብቻ ስለምንጠብቅ ያልተመለሰ ይመስለናል እንጂ እርሱ ልመናን የሚመልሰው በተለያየ መንገድ ነው ። ➡️ እሺ እሰጥሃለሁ እግዚአብሔር የብዙ ሰዎችን ጸሎት መልሶአል ። የጸሎት ደብተር ስለሌለንና ስለምንረሳ ያልተመለሰ ይመስለናል እንጂ ከለመነው ውስጥ የሚበዛው መልስ አግኝቷል ። እግዚአብሔር ጸሎታችንን የሚመልሰው ራሱ ጸልዩ ብሎ ስላዘዘና አዛኝ ስለሆነ ነው ። ሰዎች ለሰዎች ደግ ነገርን ለማድረግ ፈቃድና አቅም አንድ ጊዜ አይሟሉላቸውም ። ፈቃዱ ሲኖራቸው አቅም የላቸውም ፣ አቅሙ ሲኖራቸው ፈቃዱ የላቸውም ። በዕለታዊ ኑሮአችን የምንሰቃየው በዚህ ምክንያት ነው ። ምንም ባልነበረን ጊዜ ለሰዎች ቤት ሠርተን ለመስጠት ፣ ድሆችን ከገበታችን ለማብላት ፣ አሥራት በኵራታችንን በእጥፍ ለማውጣት እንመኝ ነበር ። አቅሙ ሲመጣ ግን ዳተኛ ሆነናል ። በብር አሥራት ያወጡ የነበሩ በዶላር ማግኘት ሲጀምሩ ለማውጣት ይሰስታሉ ። አቅሙ ሲኖር ፈቃድ ይከዳል ፣ ፈቃዱ ባለበት ዘመን ደግሞ አቅም ዘግይቷል ። እግዚአብሔር ግን የልጆቹን ልመና ለመስማት ፈቃድም አቅምም አለው ። ሰው ሊከውን የማይችለውን ለብዙዎች በማድረግ ታላቅነቱን ገልጧል ። እግዚአብሔር መኖሩን ከሚያስመሰክርበት ነገር አንዱ ሳንለምነው በሚሰጠን ሌሊትና ቀን ክረምትና በጋ እንዲሁም ለምነነው በሚቸረን ብዙ ጸጋ ነው ። ➡️ ጠብቅ ታገኛለህ እግዚአብሔር በትዕግሥት ውስጥ እየተዘጋጀ ሳይሆን እኛን እያዘጋጀ ነው ። ለሚሰጠን በረከት ብቁና ስምም እንድንሆን የትዕግሥትን ዋጋ ያስከፍላል ። የሰው ልጆች በቀላሉ ያገኙትን ነገር በቀላሉ ሊጥሉት ይችላሉ ። እግዚአብሔር እንድናከብረው የሚፈልገውን ጸጋ የትዕግሥት ደጅ ጥናትን ያውጅበታል ። አብርሃም ዕለቱን ለምኖ ያገኘ አይደለም ። 25 ዓመታት እግዚአብሔርን በትዕግሥት ጠብቋል ። በዚህ መሐል ብዙ መውደቅና መነሣት አለ ። እርሱም የትምህርቱ አካል ነው ። ጉዳዩ ከመለወጡ በፊት እኛ ብንለወጥ ይሻላል ። የምንመኘው ነገር አንድ ክፍተታችንን የሚሞላ ነው ፣ ትዕግሥት ግን ለሕይወት ዘመናችን ስንቅ ፣ የተዘጉ በሮችን መክፈቻ ቁልፍ ነው ። አብርሃም ስለ ልጅ ልቡ ሞቶ ነበር ፣ በ75 ዓመቱ የተኛውን ልቡን ቀስቅሶ ልጅ እሰጥሃለሁ ያለው ራሱ እግዚአብሔር ነው ። ለአብርሃም ጸሎቱንም መልሱንም የሰጠ እግዚአብሔር ነው ። የያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ ሕልሙ እስኪፈጸም ብዙ መከራ ተቀብሏል ፣ 13 ዓመታት በስደትና በእስር ተጎድቷል ። ነገሥታትና ካህናት የሚለብሱትን ወጥ ቀሚስ አስቀድሞ በአባቱ ተሸለመ ፣ የአለቅነት ልብስ ከለበሰ በኋላ ዮሴፍ በወንድሞቹ ተቀጥቅጦ ጉድጓድ ተጣለ ፣ በሃያ ብር ተሽጦ ግብጽ ወረደ ። እግዚአብሔር ያለውን ይፈጽማል ፣ የትኛውም የጠላት መንጋ ሊያስቆመው አይችልም ። ዳዊት የ15 ዓመት ብላቴና ሳለ ተቀባ ። ከተቀባ በኋላ ግን የንጉሥ ጠላት መጣበት ፣ በሕመሙ ያጽናናውና የፈወሰው ሳኦል ጠላት ሁኖ ተነሣበት ። 15 ዓመታት ተንገላቶ የተቀባበትን መንበር ጨበጠ ። እግዚአብሔር በበጎች ጥበቃ መሪነትን አሰለጠነው ፣ ለሳኦል በገና በመደርደር ደግሞ የቤተ መንግሥቱን መግቢያና መውጫ አስለመደው ። በ15 ዓመታት ስደት የዓለምን መልክ አሳየው ። በይሁዳ አንግሦ ሰባት ዓመት አሰለጠነው ። ከሰባት ዓመት በኋላ በመላው እስራኤል ላይ አንግሦ ታላቅ ንጉሥ አደረገው ። በትዕግሥት ውስጥ መሠራት አለ ። በእነዚህ ዓመታት በመታገሡ ዳዊት እስካሁን ወደር ያልተገኘለት ንጉሥ ሆነ ። ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ አይሁድ የሚጠቀሙት የተደራረበ ሦስት ማዕዘን ያለው ባለ ስድስት ጫፍ ምልክት “የዳዊት ኮከብ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል ። በግምት ከ15 ሚሊየን ሕዝብ በላይ “ዳዊት” በሚል ስም አሁን እየተጠራ ነው ። የእስራኤል የመከላከያ ሥርዓት “የዳዊት ወንጭፍ- David`s Sling” በመባል የሚጠራ ነው ። እስራኤል ሦስት ዋና ዋና የመከላከያ ሥርቶች አሏት ። የዳዊት ወንጭፍ የሚባለው ግን ከባድ ሮኬቶችን የአጭርና የመካከለኛ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችንና ክሩዝ ሚሳኤሎችን እንዲሁም የአየር ስጋቶችን ለመጥለፍ የሚያስችል ነው ። የዳዊት ወንጭፍ ጎልያድን እንደ ጣለች እንዲሁም ይህ የመከላከያ ሥርዓት በእስራኤል ሰማይ ላይ የሚታዩ አጥቂዎችን የሚጥል ነው ። ዳዊት መዝሙሩ በመላው ቤተ አይሁድና ቤተ ክርስቲያን ቀንና ሌሊት ላለፉት 3 ሺህ ዓመታት ይዘመራል ። የመጠበቅ ዋጋ ከሞት በኋላም ደማቅ ኮከብ ያደርጋል ። ከሁሉ በላይ ክርስቶስ ከዳዊት ዘር መወለዱ አምላክ በትዕግሥተኞች ቤት ለማደሩ ምልክት ነው ። ይቀጥላል... #እነሆ_እኔን_ላከኝ #ተሐድሶ_ይሆናል #ክርስቶስ_ለሕዝብ_ሁሉ
የእግዚአብሔር ዓላማ (ክፍል-2) 3. የሚወዱን እኛ በራሳችን ላይ ዓላማ ይኖረናል፡፡ የሚወዱንም በእኛ ላይ ዓላማ አላቸው፡፡ ከሁሉ የሚልቀው ግን እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለው ዓላማ ነው፡፡ እኛ ይህችን ሕይወት በአደራ ተቀብለናታል እንጂ በባለቤትነት የያዝናት አይደለችም፡፡ ባለቤቱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለገዛ ሰውነታችን የሚጠይቀን ሰውነታችንን በአደራ ስለ ሰጠን ነው፡፡ እኛ የእግዚአብሔር ነን፡፡ እኛ የራሳችን አለመሆናችንን ብናውቅ ኖሮ በራሳችን ላይ ለማዘዝ አንፈቅድም ነበር፤ ሰዎችም እንዲያዙበት ክፍት አናደርገውም ነበር፡፡ በእኛ ላይ ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከራሳችን ይልቅ ለራሳችን የሚቀርበው አምላክ ነው፡፡ የሚወዱን እንድንሆንላቸው የሚፈልጉት ነገር አለ፡፡ ይህ በእኛ ላይ ያላቸው የወዳጆቻችን ዓላማ ነው፡፡ ነገር ግን ቀድሞ የሚያውቀን እግዚአብሔር በእኛ ላይ ዓላማ አለው፡፡ በራሳችን ላይ ባለ ዓላማ የሆነው ምናልባት ራሳችንን ካወቅንበት ጊዜ ጀምሮ አሊያም ለአካለ መጠን ስንደርስ ሊሆን ይችላል፡፡ ዓላማ የምንለውም ነገር ዓላማነቱ በጣም መፈተሽ ያለበት መሆኑን አንረሳም፡፡ የሚወዱንም በእኛ ላይ ዓላማ አላቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ወላጆቻችን በእኛ ላይ ዓላማ አላቸው፡፡ ገና በማኅፀን ሳለን፣ ወይም ተወልደን ባዩን ጊዜ አሊያም ብልህነታችን የማረካቸው ወቅት ሊሆን ይችላል፡፡ እነርሱ ዓላማ ያደረጉት ደም መላሽ እንድንሆን፣ ከድህነት እንድናወጣቸው፣ ስማቸውን እንድናስጠራ፣ ዘመድ እንድንሆናቸው፣ እንድናኰራቸው ሊሆን ይችላል፡፡ በእግዚአብሔር ሚዛን ግን ይህ ሁሉ ዓላማ አይደለም፡፡ ዓላማችንን በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ ካላገኘነው እውነተኛ አይደለም፣ ዓላማ ተብሎም አይጠራም፡፡ እኛ በራሳችን ላይ ዓላማ አለኝ ካልንበት ዘመን የወላጆቻችን ዓላማ ይቀድማል፡፡ ከወላጆቻችን ደግሞ የእግዚአብሔር ዓላማ ቀዳሚ ነው፡፡ ወላጆቻችን ዓላማቸው የጀመረው ገና በማኅፀን ሳለን ቢሆን እንኳ እግዚአብሔር ግን ዓላማ ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር፣ ከጊዜና ከቦታ በፊት በእኛ ላይ ዓላማ ነበረው፡፡ ዓለም ሳይፈጠር በዓላማ አየን፣ በመፍጠር ገለጠን፣ ትእዛዝ በመስጠት መራን፡፡ 4. ሰይጣን ሰይጣን በራሳችን፣ በወላጆቻችን ዓላማ ውስጥ የራሱን ዓላማ ያሳርፋል፡፡ የሰይጣን ዋነኛ ዓላማው የእርሱን ዓላማ ተግባራዊ እንድናደርግ ሳይሆን ለራሳችንም ሆነ ለሚወዱን ሰዎች ዓላማ ስንኖር ከእግዚአብሔር ዓላማ እንድንፈናቀል ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ዓላማ በሙሉነት አለመፈጸም ለሰይጣን ትልቅ እርካታና መግቢያ ነው፡፡ የሰይጣን ዋነኛ ዓላማው ባለጠጋ እንዳንሆን፣ ዝናን እንድናጣ አይደለም፡፡ እንደውም እነዚህን ነገሮች ሰይጣን ሊሰጠን የሚፈልጋቸው ነገሮች ናቸው፡፡ የሰይጣን ዋነኛ ዓላማ ለገንዘብ፣ ለትዳር ስንባዝን ዘመናችን በቶሎ አልቆ ለዘላለም የእርሱ እንድንሆን ነው፡፡ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ጋር የሚፎካከር በመሆኑ እግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ እንዳለው እርሱም ዘላለማዊ የክፋት ዕቅድ አለው፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማ የእግዚአብሔር ዓላማ ቅዱስ፣ ከፍ ያለ፣ ፍጻሜው ያማረ፣ ገዢ፣ ፀንቶ የሚኖር፣ የእኛን ዓላማ የሚጠቀልል ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማ በሕይወታችን ተግባራዊ ሲሆን ከኃጢአት እንርቃለን፣ ከፍ ባለ የሞራል ደረጃ እንራመዳለን፣ ፍጻሜአችን ያማረ ይሆናል፡፡ ዓላማችንን ዓላማው፣ ፈቃዳችንን ፈቃዱ እንዲገዛ ከሁሉ በላይ፡- ጌታዬ ሆይ በእኔ ላይ ያለህ ዓላማ ይፈጸም፣ ሁን እንዳልከኝ ኖሮ ማለፍ ይሁንልኝ ብለን መጸለይ ያስፈልገናል፡፡ የእኛ ዓላማ ባይፈጸም በእግዚአብሔር ዓላማ ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ደግሞም ፍጡር መሆናችንን እንገነዘባለን፡፡ እንኳን እኛ የነገሡ ሰዎችም ተመኝተው ያልሆነላቸው ብዙ ነገር አለ፡፡ ሰው ማለት አቅሙ የተወሰነ ፍጡር ማለት ነው፡፡ እስከዚህች ቀን የደረስነው እንዲሁ አይደለም፡፡ በብዙ ትግልና ውጣ ውረድ ውስጥ አልፈን ነው፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ሁሉ ከፍታና ዝቅታ ውስጥ አልተለየንም፡፡ ስንታመም ፈውሶናል፣ ስንራብ መግቦናል፣ ስንገፋ ደግፎናል፣ ስንረሳ አስታውሶናል፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ የደከመብን ሊጥለን አይደለም፡፡ የሚጥለውን ዋጋ የሚከፍልበት ማንም የለም፡፡ እኛም ለማንፈልገው ነገር ዋጋ አንከፍልም፡፡ እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር በእኛ ላይ ዓላማ አለው፡፡ ያየነውን ሳይሆን ያየልንን ለመውረስ ፈቃደኛ መሆን አለብን፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማ በሕይወታችን ተግባራዊ በማድረግ ደስተኛ ኑሮ እንድንኖር፡- 1.ዓላማ ያለው ሕይወት እንደሚያስፈልገን ማመን 2.ከእኛ ከወዳጆቻችንም ይልቅ የእግዚአብሔር ዓላማ ክቡር መሆኑን መረዳት 3.እግዚአብሔርን በማስከተል የኖርንበትን ኑሮ ትተን እርሱን በማስቀደም መመላለስ 4.በጸሎት ምሪቱን መጠየቅ ይገባናል፡፡ ብሩካን ናችሁ! #እነሆ_እኔን_ላከኝ #ተሐድሶ_ይሆናል #ክርስቶስ_ለሕዝብ_ሁሉ
የእግዚአብሔር ዓላማ (በይዲድያ ብሬ) ከረጅም ጊዜ መጥፋት በኋላ ዳግም ወደ ጽሑፍ አገልግሎት የተመለስኩበት ርዕስ የእግዚአብሔር ዓላማ መሆኑ ደስ አሰኝቶኛል። ብዙ የጠየቃችሁኝ መጥፋቴ ለምን ያስባላችሁ በጸሎታችሁ ያሰባችሁኝ ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ እያልኩ ወደ መልዕክቴ አልፋለሁ። ➡️ የእግዚአብሔር ዓላማ ዓላማ ራሳችንን የምናይበት፣ እግዚአብሔር እኛን የሚያይበት መድረሻ ነው፡፡ በዚህች ሕይወታችን ላይ አራት ወገኖች ዓላማ አላቸው፡- 1. እግዚአብሔር 2. ራሳችን 3. የሚወዱን 4. ሰይጣን በሁለት ክፍል የተሰነደውን ጽሑፍ በጉጉት እንድታነቡት አደራ እላለሁ። 1. እግዚአብሔር እግዚአብሔር መነሻችንና መድረሻችን ነው፡፡ ዓላማ መነሻን የሚያሳውቅ፣ መኖርን ምክንያታዊ የሚያደርግ፣ ፍጻሜን የሚለካ ነው፡፡ የሰው ልጅ ኑሮውንና ፍጻሜውን ለመወሰን መነሻውን ማወቅ አለበት፡፡ መነሻውን ያላወቀ መድረሻውም ይጠፋዋል፡፡ “የመጣህበትን አትርሳ፣ የምትሄድበት እንዳይጠፋህ” የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ የሰው ልጅ መነሻ እግዚአብሔር ነው፡፡ በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ የተካተተች ሕይወት ተቀብለናል፡፡ የተፈጠርንበት ዓላማና የምንኖርበት ዓላማ ፍጹም አንድነት አለው፡፡ የምንኖረው ለተፈጠርንበት ዓላማ ነው፡፡ በመፈጠራችን ላይ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ባለ ዓላማው እግዚአብሔር ነው፡፡ የአንድ ሥሪት ዓላማ ያለው ሥራው ውስጥ ሳይሆን የሠሪው ልብ ውስጥ ነው፡፡ እኛም ፍጡር መሆናችንን ካመንን የእኛ ዓላማ ያለው እኛ ጋ ሳይሆን የሠራን ጌታ ጋ ነው፡፡ ስለዚህ ዓላማ የምንለው አይደለም ዓላማችን፡፡ እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለው ዓላማ እርሱ ዓላማችን ነው፡፡ ዓላማ ኑሮን ይመራል፡፡ ፍጻሜን ያሳውቃል፡፡ ዓላማ ደስታ ይሰጣል፣ እግርን ተራማጅ ያደርጋል፡፡ ዓላማውን ያገኘ ሰው የመንገዱን ካርታ የጨበጠ በመሆኑ ያለ እንግልት በጊዜው ይደርሳል፡፡ 2. ራሳችን የአንድ ትልቅ መጽሐፍ አርእስትን አስቡ፡፡ ከመጽሐፉ የምዕራፍ ክፍሎች በአንዱ ውስጥ ያለውን ንዑስ ርእስ ደግሞ ለማሰብ ሞክሩ፡፡ የእግዚአብሔር ዓላማ የሕይወት ርእስ ነው፡፡ የሕይወት ራስ የሚለውን ቃል የሕይወት ርእስ ማለት እንችላለን፡፡ በትልቁ የሕይወት መጽሐፍ ውስጥ የእኛ ዓላማ ንዑስ ርእስ ነው፡፡ ሕይወትን በአንድ ትልቅ መጽሐፍ መመሰል መልካም ነው፡፡ ደራሲው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ በዚህ ዓለም የምናሳልፈው 70 ና 80 ዓመት አንድ አንቀጽ የማይሞላ ወይም ከመቅድም የማይዘል ነው፡፡ ስለዚህ የዚህ ዓለም ኑሮአችን የዓይን ጥቅሻ፣ የእሳት ብልጭታ የሚያህል ነው፡፡ ሰፊው ኑሮአችን ያለው በሰማይ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ሺህ ዓመት እንደ አንድ ቀን ነው ከተባለ ሰባና ሰማንያ ዓመት በእግዚአብሔር ዘንድ የ2 ሰዓት 30 ቆይታ ነው፡፡ በርግጥ በዚህ ዓለም ላይ የምናሳልፈው ቆይታ በጣም አጭር ነው፡፡ ዘላለማዊ ሕይወታችን ላይ ባለ ዓላማ የሆነው እግዚአብሔር ይህችን ትንሽ ቆይታ መምራት የሚሳነው አይደለም፡፡ የተለያዩ ዓላማዎች ሊኖሩን ይችላሉ፡፡ ገንዘብ መጨበጥ፣ ሥልጣን ላይ መቆናጠጥ፣ ትዳር መመሥረት፣ ልጆች መውለድ … ዓላማችን ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ግን ንዑሳን ዓላማዎች ናቸው፡፡ ዋነኛ የተፈጠርንበት ዓላማ ግን አባቶች እንደ ነገሩን ስሙን ለመቀደስ ክብሩን ለመውረስ ነው፡፡ ይህ በአጭር ቃል የተነገረው ትልቅ ፍቺ ያለው ነው፡፡ በዚህ ዓለም ስሙን እንቀድሳለን፣ እግዚአብሔርን የሚያስከብር ኑሮ እንኖራለን፡፡ በወዲያኛው ዓለም ደግሞ ክብሩን እንወርሳለን፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ገንዘብ የወረሱ ደስ ሊላቸው፣ ዕድለኞች ሊባሉ ይችላሉ፡፡ ክብር ግን የሚወረሰው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ስሙን ለሚቀድሱ ክብሩን ያወርሳቸዋል፡፡ ይቀጥላል... #እነሆ_እኔን_ላከኝ #ተሐድሶ_ይሆናል #ክርስቶስ_ለሕዝብ_ሁሉ
ከ80ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በደቡብ አፍሪካ ከባድ ጭንቀት ውስጥ ናቸው። ዛሬ june 30 በመጤ ጠሎች ከሀገራችን ለቃችሁ ውጡ የተባለበት የመጨረሻው ቀን ነው። የወገኖቻችን ደም በክፉ ሰዎች ምክንያት እንዳይፈስ ማንም ሰው የልጁን ፣ የወንድም እህቱን ፣ የወላጁን... የሞት መርዶ ከሰው ሀገር በዚህ ምክንያት እንዳይሰማ እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባና የሐማ ምክር እንዲፈርስ ወገኖቻችን ሰላም እንዲበዛላቸው በያለንበት በጸሎት እንድናስባቸው በእግዚአብሔር ፍቅር እጠይቃችኋለሁ። #እነሆ_እኔን_ላከኝ #ተሐድሶ_ይሆናል #ክርስቶስ_ለሕዝብ_ሁሉ
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን በግፍና በአሰቃቂ መንገድ በተገደሉት ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ምክንያት ልባችን እጅግ ተሰብሯል። ቢያንስ 13 ወገኖቻችን ሕይወታቸው ተቀጥፏል፤ ከሁለት መቶ በላይ ምእመናን ተፈናቅለዋል፤ ቤተ ክርስቲያናቸውም በእሳት ተቃጥሏል። ይህ እኩይ ድርጊት ሰውን በገዛ አምሳሉ በፈጠረው በእግዚአብሔር ላይ የተሰነዘረ ዐመፅ ነው። የርኅራኄ አባትና የመጽናናት ሁሉ አምላክ የሆንኸው እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ሐዘንተኞችን አጽናና፤ በተመሳሳይ የሞት ጥላ ውስጥ ላሉትም ወገኖቻችን እውነተኛ እረኛና ከለላ ሁን። "ሰውን በመልካችንና በአምሳላችን እንፍጠር" ብለህ በቅዱስ ሥላሴ መለኮታዊ ምክር ሰውን ያበጀህ አምላክ ሆይ፤ እባክህ ራራልን፤ ምድራችንን ከዚህ ከጭፍን ጥላቻ፣ ከጥፋትና ከጅምላዊ መወጋገድ ታደጋት። አምላክ ሆይ፤ እባክህን ወደ እኛ ተመልከት፤ ልቅሶአችንን ስማ፤ በጽድቅህና በእውነትህም ፍረድ። በዐመፅ ዑደት ልባችን እጅግ ዝሏል፤ ዐይኖቻችንም ወደ አንተ ብቻ ናቸው። አቤቱ ሁሉን ቻይ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤ በታላቅ ምሕረትህና በማያልቀው ርኅራኄህ መጠን ጐብኘን፤ የቈሰለውን ልባችንን ጠግን፤ ምድራችንንም በሰላምህ አሳርፋት። አሜን!
ቤተክርስቲያን ውስጥ ስብከት ላይ ወጣቶችን ቴክስት መደራረግን የማያስቆም መልእክት ከሌለኝ፣ ቴክስት መደራረግ ይቀጥሉ። መልዕክታችን እየተሰበከ እንኳን ኢንተርቴይመንት ሊያምረን፣ ሰዓት ጠብቀን የምንወስደውን መድኃኒት የሚያስረሳ መሆን አለበት። አሁን እኮ ስብከታችን ይዘት የለውም፤ እኛም የምናወራው ዝም ብሎ ተደጋጋሚ ቃላት ብቻ ነው። ወላጆች ወጣት ልጆቻቸውን አስገድደው ቸርች እንዲመጡ ያደርጓቸዋል። ልጆቻቸው ወይ ግቢ ውስጥ ይጫወታሉ ወይ በግድ ይቀመጣሉ። ዛሬ ማስተካከል ካልቻልን ከስረናል ማለት ነው። ለትውልዱ መልእክት አጥተናል ማለት ነው። ይዘት ያለው መልዕክት ይፈልጋሉ። ካልተዘጋጀን ትውልዱ በጣም ያመልጠናል። ፍጥነቱ በጣም ከፍተኛ ነው። እኛ ካልሰጠነው ዓለም የምሰጠው በጣም ብዙ አለ። እኔ መልእክቴን ስዘጋጅ የሚያስጨንቀኝ አንዱ ነገር ይሄ ነው። እኔ ካልሰጠሁት፣ እኔ ካላጎረስኩት፣ ይህ ትውልድ አየር ላይ ተንጠልጥሎ አይኖርም። የሚያጎርሰው አለ። መንገዱ አማራጭ በአማራጭ ነው። ኢንተርኔት ላይ ቢገባ፣ ጎግል ቢያደርግ ብዙ የሚጠቅም ነገር ያገኛል። የኔን የማይጠቅም ነገር ለመስማት ለምን ቁጭ ይላል? ድሮ አማራጭ ስለሌለ ነው። ዛሬ ምንም የሚዘገይ ነገር የለም፤ ድሮ ጋዜጣ እንኳን በደንብ በሌለበት አገር ነበር። አሁን መዓት ነገር አለ። ሁሉን የሚያስጥል! እኛ የፈለግነውን ነገር እያደረግን ወጣቱ በጠብታ እያለቀቀው ነው። አሁን ቸርች ውስጥ ረሃብ በጣም አለ። በጣም! አንዳንድ ወጣቶች ያስታውቃሉ። ዓለም ነች የምትመግባቸው። እኛ ስላልመገብናቸው ረሃብ ዝም ብሎ አይኖርም። እውነተኛ ምግብ ካላገኘህ ቆሻሻ ያስበላሃል። መንፈሳዊ ረሃብ በጣም ስላላቸው በዚህ ይሞክሩታል፣ በዚያ ይሞክሩታል። እና ዓለም የምትሰጣቸው ጃንክ ሆኖባቸዋል፣ ሰልችቷቸዋል፤ ቸርች ደግሞ የምትሰጣቸው ብዙ ሚረባ ነገር የለም።...
“እንደ ተናገረ ተነሥቶአል” ማቴ 28፥6 ዛሬ የድል ቀን ነው። ሞት ተሸንፏል፤ ሕይወት አሸንፏል። ትንሣኤው የአዲስ ሕይወት መጀመሪያ ነው። አዲሱ ሕይወት ማለት ክርስቶስ በእኛ የሚኖረው ሕይወት ማለት ነው። አዲሱን ሕይወት በየዕለቱ በመኖር የተባረካችሁ ሁኑ። ኢየሱስ ተነስቷል! መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ!
ተወዳጆች የእግዚአብሔር ሰላም ይብዛላችሁ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ። ጌታችን ኢየሱስ ትልቅ ምስጢር የሆነውን ቅዱስ ቍርባን ስርዓት የመሰረተው በፋሲካ በዓል ቀን ነው። አይሁድ ንጹሕ በግ አርደው በሚያከብሩት በዓል ላይ ንጹሕ የእግዚአብሔር በግ በመሆን ራሱን ስለእኔ እና እናንተ መስዕዋት አድርጎ ያቀረበው ኢየሱስ ነው። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷል ! ይህ ቀን ቀላል ቀን አይደለም። ኢየሱስ ስለ ኃጢአተኞች የታረደበት ቀን ነው። #ተባረኩ!
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ለወንጌል መልካም ልብ የነበራት እህታችን ምስጥረ መሐመድ በድንገተኛ አደጋ ምክንያት ወደ ጌታ መሄዷን ስሰማ እጅግ በጣም ደንግጫለሁ። ወደ ሰሜን ለወንጌል አገልግሎት በምሄድበት የመጀመሪያ ጊዜ ላይ ብዙ የመከረችኝ እህቴ እና በገጠር የወንጌል አገልግሎት አብሮ ሰራተኛ እህቴ ነበረች። ለአዲስ አበባ አማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን እና ለወዳጆቿ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጽናናት ይሁን።
Maranatha pinned «ሰበር :- እግዚአብሔር እየረዳችሁ ትቀጥላላችሁ እንጂ ምንም አትሆኑም !»
ሰበር :- እግዚአብሔር እየረዳችሁ ትቀጥላላችሁ እንጂ ምንም አትሆኑም !
ሰሞኑን በተለምዶ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን (only jesus) የሚባሉ የኑፋቄ ትምሕርት አራማጆች በዓመታዊ የዋራ ቤቴል ጉባዔ ላይ 12,296 ሰው ተቀላቅሎናል ብለው የጥምቀት ስርዓት ሲፈጽሙ ከርመዋል። ይህ ሁሉ ሰው የእውነት ሄዶ ከሆነ ራሱ በእርግጠኝነት አብዛኛው የሄደው ከወንጌል አማኞች ቤት ነው። እርስዎ ስለ ሐዋርያት ቤተክርስቲያን (only jesus) ምን ያህል ያውቃሉ? ዛሬ እነርሱን መጠየቅ የምፈልገውን 10 ጥያቄዎች ይዤ ቀርቤያለሁ እናንተም አብራችሁኝ ጠይቁ። 1. #አብና_ወልድ_ይዋደዳሉ ( ዮሃ 3፥35፤ 5፥20 እና 14፥31) አንድ አካል ራሱን እንዴት ሊወድ ይችላል? እኔና እኔ እንዋደዳለን ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲገባን እባካችሁ አስረዱን? 2. #አብና_ወልድ_ይተዋወቃሉ ( ዮሃ 7፥28-29፣ 8፥55፣ ማቴ 11፥27 እና ሉቃ 10፥20) አንድ አካል መልሶ ከራሱ ጋር እንተዋወቃለን ሊል ይችላል? እኔና እኔ እንተዋወቃለን የሚል ሃሳብ ትርጉም ይሰጣል? እንዴት? አስረዱን? 3. #አብና_ወልድ_ይነጋገራሉ ( ዮሃ 11፥41-42፣ ማቴ 26፥26፣ ሉቃ 24፥30) ሁለት አካላት እንጂ አንድ አካል ከራሱ ጋር እየተነጋገርኩ ነው ሊል የሚችለው እንዴት ባለ ሎጂክ ነው? አንዱ ሲጸልይ ሌላው ጸሎትን ሲመልስ እያየን በምን አይነት አስተሳሰብ ነው ሁለት አይደሉም አንድ ናቸው የምንለው? አንድ አካል ራሱ ጠይቆ ዞሮ ደግሞ ራሱ እየመለሰ አይነት ለመረዳት የሚያስቸግር ሆኖብናልና ይህን ታቃርኖአዊና ኢ-ምክንያታዊ አስተምህሮአችሁን እንዲገባን በሚያስችል መንገድ የሚያስረዳን ሰው ይኖራችሁ ይሆን? 4. #አብ_ወልድን_ልኮታል (ዮሃ 17፥18፣ 20፥21፣ 3፥16-17፣ ገላ 4፥4፣ 1 ዪሃ 4፥10) አንድ አካል ራሱን ይልካል ማለት ምን ማለት ነው፣ የሚልክ ካል የሚላክ አለ ሁለት አካላት ሳይኖሩ ላኪና ተላኪ ማለት እንዴት እንችላለን? 5. #አብና_ወልድ_ይከባበራሉ ( ዮሃ 17፥1፣ 8፥54 ዕብ 5፥5፣ ማቴ 6፥9፣ ሉቃ 11፥2) አንድ አካል ይከባበራሉ በሚል ሊገለጥ እንዴት ይችላ? “እኔና እኔ እንከባበራለን” ማለት ትርጉሙ ምንድነው? 6. #አብ_ለወልድ_ይመሰክራል ( ዮሃ 5፥31-32፣ 8፥16-18፣ 12፥49) አንድ አካል መልሶ ለራሱ አካል መስካሪ መሆን የሚችለው እንዴት ነው? ምስክርነት ቢያንስ ሁለት አካላት መሳተፍ የለባቸውምን? አንዴት አንድ አካል ለራሱ አካል መስካሪ ሆኖ እንደሚቀርብ ማስረዳት ብትችሉ? 7. #አብና_ወልድ_በጋራ_ኖረዋል ( ዮሃ 1፤1 ፣ 17፥5፣ 8፥58፣ 1ዮሃ 2:1) ሁለት አካልት አብረው ኖረዋል ብንል ስሜት ይሰጣል አንድ አካልና ራሱ ያው አካል አብረው ይኖሩ ነበር ስንል ግን በትክክል የሚያስብ አዕምሮ እንዴት ነው የሚታርቀለት? 8. #ወልድ_ነፍሱን_ለአብ_ዐደራ_ሰጥቷል ( ማቴ 15፥34፣ 23፥46፣ ሃዋ 7፥59) አንድ አካል ነፍሱን ለራሱ ሰጠ ማለት ምን ማለት ነው? አንድ አካል ነፍሱን ለሌላ አካል ሰጥቷል ትርጉም ያለው ንግግር ነው። አንድ አካል ለራሱ አካል መልሶ ነፍሱን አደራ ሰጠ ስንል ግን ለመረዳት አይቻልም። እባካችሁ አስረዱን 9. #አብና_ወልድ_የተለያየ_ፈቃድ_ነበራቸው ( ሉቃ 22:42፣ ማቴ 26፥39-42፣ ማር 14፥35፣ ዮሃ 18፥11፣ 5፥30) አብና ወልድ አንድ አካል ከሆኑ ሁለት ፈቃድ ሊኖራቸው እንዴት ቻለ? አባት ሆይ የኔ ሳይሆን ያንተ ፈቃድ ይሁን ማለት እንዴት ይቻላል? 10 #ጌታ_እኔ_ስሄድ_ሌላ_አጽናኝ_እልክላችኋለው ሲል ሌላ ብሎ ሲል አይ ሌላ የለም ራሱ ነው የምትሉት ራሱን ኢየሱስን ነው የምትቃወሙት ? ኢየሱስ ሌላ ካላ አይ ሌላ የለም እሱ ራሱ ነው የምትሉን በምን ምክንያት ነው? እነዚህን ጥያቄዎች በአጠገባችሁ የሚገኙ የሐዋርያት (only jesus) አማኞች እንዲመልሱን አብራችሁኝ ጠይቁ! #እነሆ_እኔን_ላከኝ #ተሐድሶ_ይሆናል #ክርስቶስ_ለሕዝብ_ሁሉ
ስለረመዷን ጾም የመጨረሻው ምንባብ ክርስቶስ ስለእኛ ሞቷልና የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ፦ ሮሜ 5 - 8 ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር በዚህ ያስረዳል። በዒድ አል-ፊጥር በዓል ወቅት ለሙስሊም ወዳጆች ወንጌልን ማካፈል ልዩ ጥበብንና ከልብ የመነጨ ፍቅርን ይጠይቃል። ይህ ዕለት የጾም መፈቻና የደስታ ቀን በመሆኑ፣ ምሥራቹን የምናበስረው በክርክር ሳይሆን በክርስቶስ ፍቅር በተሞላ መስተንግዶና ሰላምታ መሆን አለበት። ሐዋርያው ጳውሎስ በቆላስይስ 4:6 ላይ "ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው እንደ ተቀመመ በጸጋ ይሁን" እንደሚለው፣ ንግግራችን የሚስብና ለልብ የሚቀርብ ሊሆን ይገባል። በመጀመሪያ፣ የዒድ በዓል የቤተሰብና የርኅራኄ ቀን እንደመሆኑ መጠን፣ እውነተኛ ክርስቲያናዊ መስተንግዶን ማሳየት ትልቅ በር ይከፍታል። ሙስሊም ጎረቤቶቻችንን ወይም ጓደኞቻችንን ለምሳ በመጋበዝ ወይም አብሮ በማሳለፍ፣ በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር የወንጌልን ብርሃን ማሳየት እንችላለን። 1ኛ ጴጥሮስ 3:15 "በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን" እንደሚለው፣ የእኛ ደግነትና ትሕትና እነርሱ ስለ እምነታችን ጥያቄ እንዲጠይቁ ምክንያት ይሆናቸዋል። በውይይት ወቅት ትኩረታችንን በክርስቶስ በኩል በሚገኝ የኃጢአት ስርየትና የልብ ሰላም ላይ ማድረግ ይገባል። ሙስሊም ወዳጆቻችን አላህን ለማስደሰትና ጽድቅን ለማግኘት የሚጥሩ በመሆናቸው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ፋንታ የከፈለውን ፍጹም መሥዋዕትነትና የሚሰጠውን ዋስትና ማካፈል የልባቸውን ጥማት ሊያረካ ይችላል። በሮሜ 5:8 ላይ እንደተጻፈው "ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር በዚህ ያስረዳል።" ይህ መለኮታዊ ፍቅር ለበዓሉ እውነተኛ ትርጉም የሚሰጥ ታላቅ ስጦታ ነው። በመጨረሻም፣ ወንጌልን ማካፈል በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና በጸሎት የሚደገፍ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ከወዳጆቻችን ጋር ከመገናኘታችን በፊትና በኋላ፣ እግዚአብሔር የልባቸውን ዓይን እንዲከፍትና የሰሙት ቃል በውስጣቸው እንዲሰራ መጸለይ ይገባል። ጌታ ኢየሱስ በዮሐንስ 14:27 ላይ "ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም" እንዳለው፣ በበዓሉ ደስታ መካከል የማይጠፋውንና እውነተኛውን የክርስቶስ ሰላም እንዲያገኙ መመኘትና መጸለይ የወንጌል አገልግሎታችን ዋነኛ ክፍል ነው። ጸሎት፦ የሰላም አምላክ ሆይ፣ በዚህ በዓል ወቅት ለሙስሊም ወዳጆቼ ያንተን ፍቅር የማሳይበትን ጥበብና ትሕትና ስጠኝ። ንግግሬ በጸጋ የተቀመመና ወደ አንተ የሚመራ ይሁን። በልባቸው ውስጥ እውነተኛውን ሰላምህንና የድነትህን ብርሃን አብራ። አሜን። #እነሆ_እኔን_ላከኝ #ተሐድሶ_ይሆናል #ክርስቶስ_ለሕዝብ_ሁሉ
ረመዷን ጾም ቀን 30 ከሥርዓት ፍጻሜ ወደ ዘላለም ሕይወት የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ፦ ዩሐንስ ወንጌል 4፡14 እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት። ዩሐንስ ወንጌል 4፡14 በዚህ በረመዳን 30ኛው ቀን፣ ሙስሊም ወዳጆቻችን የአንድ ወር ጥብቅ ጾምና ጸሎታቸውን አጠናቀው ለታላቁ የኢድ በዓል ዋዜማ ላይ ይገኛሉ። በዚህ ዕለት ጸሎታቸው ሁሉ "ያለፈው ድካማችን ተቀባይነትን አግኝቶ ይሆን?" በሚል ጥልቅ ተስፋና ስጋት የታጀበ ነው። ብዙዎቹ ኃጢአታቸው እንዲሰረይላቸውና በቀጣዩ ዓመት በሰላም እንዲያደርሳቸው አምላካቸውን ይማጸናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ በዕብራውያን 10፥14 ላይ "በአንድ መሥዋዕት የሚቀደሱትን ለዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና" እንደሚለው፣ እኛ ክርስቲያኖች በየዓመቱ ከሚደገም ሥርዓት ይልቅ፣ በክርስቶስ አንድ ጊዜና ለሁልጊዜ በተደረገው ቤዛነት ያገኘነውን ፍጹም እርካታ ልናስብላቸው ይገባል። ሙስሊሞች በዚህ ቀን ጾሙን ሲያጠናቅቁ የሚሰማቸውን መንፈሳዊ ድካም፣ እኛ ደግሞ በክርስቶስ ስላገኘነው የጸጋ ስጦታ ለማካፈል እንደ መልካም አጋጣሚ ልንጠቀምበት እንችላለን። እነርሱ "በሥራ" ጽድቅን ለማግኘት ሲደክሙ፣ እኛ ግን በቲቶ 3፥5 ላይ ያለውን እውነት እናስታውሳቸዋለን፦ "እርሱ እንደ ምሕረቱ መጠን በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው ስለ ጽድቅ ሥራ አይደለም።" እውነተኛው መዳን ከእኛ ጥረት ሳይሆን ከእግዚአብሔር ምሕረት የሚመነጭ መሆኑን፣ ለሙስሊም ወዳጆቻችን በታላቅ ትሕትናና ፍቅር ልናበስራቸው ይገባል። በዛሬው ጸሎታችን ደግሞ፣ እግዚአብሔር በዚህ የመዝጊያ ቀን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ልብ ውስጥ አዲስ ጥማትን እንዲፈጥር እንለምናለን። ጾሙ ሲያልቅ የሚመጣው ደስታ ጊዜያዊ ሳይሆን፣ የነፍሳቸው ጥማት በዘላቂው በሕይወት ውኃ እንዲረካ እንጸልያለን። በዮሐንስ 4፥14 ላይ ጌታ ኢየሱስ "እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም" እንዳለው፣ የረመዳን ወር ፍለጋቸው ወደ እውነተኛው የሕይወት ምንጭ እንዲመራቸው ጽኑ ልመናችን ይሁን። በተለይ በዚህ ሰዓት ለሚፈልጉት "የምሕረት ዋስትና" መንፈስ ቅዱስ በልባቸው ውስጥ ስለ ክርስቶስ እንዲመሰክርላቸው እንማጸናለን። በመጨረሻም፣ ይህ ቀን ለእኛም ለአማኞች የፍቅር ተልእኳችንን የምናድስበት ይሁን። ሙስሊም ወዳጆቻችን ለበዓል ሲዘጋጁ፣ እኛም በደስታቸው አብረን በመሆንና ስጦታዎችን በመለዋወጥ የክርስቶስን ፍቅር በተግባር ልናሳያቸው ይገባል። በ1ኛ ጴጥሮስ 4፥8 ላይ "ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ" እንደሚለው፣ በጸሎታችንና በምስክርነታችን የክርስቶስን መዓዛ ለነርሱ የምናሳይበት ጸጋ እንዲበዛልን እየለመንን ቀኑን እንጀምር። ይህ ወር እግዚአብሔር ለሙስሊም ወገኖቻችን የእውነተኛ መንፈሳዊ ብርሃን በልባቸው ላይ እንዲያበራ ይህም በልጁ አምነው እንዲድኑ ወደ ክርስቶስ ኅብረት ድነው የሚጨመሩ ሙስሊሞች እንዲበዙ አጥብቀን የምይጸልይበት ወር ይሁን። #እነሆ_እኔን_ላከኝ #ተሐድሶ_ይሆናል #ክርስቶስ_ለሕዝብ_ሁሉ
ረመዷን ጾም ቀን 29 ከስንብት ወደ ዘላቂው ግንኙነት የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ፦ ዩሐንስ ወንጌል 7፡37 – 38 ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ። ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። ዩሐንስ ወንጌል 7፡ 37 - 38 በዚህ በረመዳን 29ኛው ቀን፣ ሙስሊም ወዳጆቻችን የጾሙን ወር በመጨረሻው ሰዓት ላይ ሆነው በታላቅ ስሜት ይሸኙታል። በዚህ ዕለት ጸሎታቸው ሁሉ "ያለፈው ወር ጾማችንና ጸሎታችን ተቀባይነት አግኝቶ ይሆን?" በሚል ጉጉትና ስጋት የታጀበ ነው። ብዙዎቹ ኃጢአታቸው እንዲሰረይላቸውና ከገሃነም እሳት ነጻ እንዲወጡ (ዒትቁን ሚነናር) አጥብቀው ይለምናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ በሮሜ 8፥1 ላይ "እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም" እንደሚለው፣ እኛ ክርስቲያኖች በሥራ ሳይሆን በክርስቶስ ደም ያገኘነውን ፍጹም የደህንነት ዋስትና በማሰብ ለነርሱም ይህ እውነት እንዲበራላቸው ልንማጸን ይገባል። ሙስሊሞች በዚህ ቀን ጾሙን ሲያጠናቅቁ የሚሰማቸውን የሥራ ድካምና የፍርሃት ስሜት፣ እኛ የክርስቶስን ወንጌል ለማካፈል እንደ መልካም አጋጣሚ ልንጠቀምበት እንችላለን። እነርሱ "ከአላህ ጋር ታረቅን ይሆን?" ብለው በሚጠይቁበት በዚህ ወቅት፣ እኛ ግን በ2ኛ ቆሮንቶስ 5፥19 ላይ ያለውን የምሥራች እናስታውሳቸዋለን፦ "እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና።" እርቅ የተፈጸመው በእኛ ጥረት ሳይሆን በእግዚአብሔር ፍቅር መሆኑን፣ ለሙስሊም ወዳጆቻችን በደግነትና በምሕረት በተሞላ ንግግር ልናሳያቸው ይገባል። በዛሬው ጸሎታችን ደግሞ፣ እግዚአብሔር በዚህ የመዝጊያ ቀን በሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል ታላቅ መንፈሳዊ መነቃቃትን እንዲያመጣ እንለምናለን። ብዙዎች በረመዳን ወር ውስጥ የጀመሩት አምላክን የመፈለግ ጉዞ ጾሙ ሲያልቅ አብሮ እንዳያበቃ፣ ይልቁንም ወደ እውነተኛው የሕይወት ምንጭ ወደ ኢየሱስ እንዲመራቸው እንጸልያለን። በዮሐንስ 7፥37 ላይ ጌታ ኢየሱስ "ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ" እንዳለው፣ የነፍሳቸው ጥማት በሃይማኖታዊ ሥርዓት ሳይሆን በሕያው ውኃ እንዲረካ ጽኑ ልመናችን ይሁን። በተለይ በዚህ ሰዓት ለሚፈልጉት "የምሕረት ማረጋገጫ" እውነተኛውን ምስክር መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጣቸው እንማጸናለን። በመጨረሻም፣ ይህ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች የፍቅር ተልእኳችንን የምናድስበት ይሁን። ሙስሊም ወዳጆቻችን ለኢድ በዓል (የጾም መፍቻ) ሲዘጋጁ፣ እኛም በደስታቸው አብረን በመሆን የክርስቶስን ፍቅር በተግባር ልናሳያቸው ይገባል። በ1ኛ ጴጥሮስ 3፥15 ላይ "በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን በገርነትና በፍርሃት ይሁን" እንደሚለው፣ በትሕትና ተሞልተን የምስክርነት ሕይወታችንን እናቅርብ። ዛሬ ቀኑን ስንጀምር፣ ጌታ ኢየሱስ በንግግራችንና በባሕርያችን ታይቶ ለብዙዎች የሕይወት በር እንዲሆንላቸው እየጸለይን እንሰማራ። ይህ ወር እግዚአብሔር ለሙስሊም ወገኖቻችን የእውነተኛ መንፈሳዊ ብርሃን በልባቸው ላይ እንዲያበራ ይህም በልጁ አምነው እንዲድኑ ወደ ክርስቶስ ኅብረት ድነው የሚጨመሩ ሙስሊሞች እንዲበዙ አጥብቀን የምይጸልይበት ወር ይሁን። #እነሆ_እኔን_ላከኝ #ተሐድሶ_ይሆናል #ክርስቶስ_ለሕዝብ_ሁሉ
ረመዷን ጾም ቀን 28 ከድካም ወደ እውነተኛው ዕረፍት የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ፦ ዩሐንስ ወንጌል 17፡3 እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። ዩሐንስ ወንጌል 17፡3 በዚህ በረመዳን 28ኛው ቀን፣ ሙስሊም ወዳጆቻችን የጾሙን ወር ሊያጠናቅቁ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዋቸዋል። በዚህ ወቅት ብዙዎቹ በከፍተኛ ድካም ውስጥ ቢሆኑም፣ የቀሩትን ጥቂት ቀናት በጸሎትና በልመና በመትጋት "ተቀባይነትን" ለማግኘት ይጥራሉ። ትኩረታቸውም ያለፉትን ቀናት ጉድለት ለመሙላትና የእግዚአብሔርን ምሕረት ለማረጋገጥ መማጸን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በማቴዎስ 11፥28 ላይ "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ" እንደሚለው፣ የሰው ልጅ በሃይማኖታዊ ሥርዓትና በሥራ ሊያገኘው የማይችለውን እውነተኛ ዕረፍት የሚሰጠው ክርስቶስ ብቻ መሆኑን እናስባለን። ሙስሊሞች በዚህ ቀን "ተቀባይነት አገኘሁ ይሆን?" በሚል ጥርጣሬና ተስፋ መካከል ሆነው ሲጸልዩ፣ እኛ ክርስቲያኖች ደግሞ በክርስቶስ ስላገኘነው ፍጹም እርግጠኝነት ልናበስራቸው ይገባል። በሮሜ 5፥1 ላይ "እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ" ተብሎ እንደተጻፈው፣ ሰላም የሚገኘው በገዛ ሥራችን ሳይሆን በክርስቶስ በተከናወነው ሥራ መሆኑን ማሳየት አለብን። ይህን የምሥራች ስናካፍል፣ በፍርሃት ሳይሆን በፍቅርና በልጅነት መንፈስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንደሚቻል በሚያሳይ ትሕትና ሊሆን ይገባል። በዛሬው ጸሎታችን ደግሞ፣ እግዚአብሔር ለሙስሊም ወገኖቻችን የልባቸውን አይን እንዲከፍትላቸው እንማጸናለን። በጾም ወራት የፈለጉት አምላክ ራሱን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንዲገልጥላቸው እንለምናለን። በዮሐንስ 17፥3 ላይ "እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት" ተብሎ እንደተገለጠው፣ እውነተኛው እውቀትና ሕይወት ወደ እነርሱ እንዲመጣ ጽኑ ልመናችን ይሁን። በተለይ በዚህ የድካም ወቅት፣ የመንፈስ ቅዱስ መጽናናትና ብርሃን በቤቶቻቸው ውስጥ እንዲበራ እንጸልያለን። በመጨረሻም፣ ይህ ቀን ለእኛም ለአማኞች በጸጋው ለመመላለስ ታላቅ መነቃቂያ ይሁን። ጾሙ ሊያልቅ ሲል ሙስሊሞች የሚያሳዩት ትጋት፣ እኛም ወንጌልን ለጠፉት ለማድረስ ያለብንን አጣዳፊነት ሊያሳስበን ይገባል። በ2ኛ ቆሮንቶስ 5፥20 ላይ "ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን" እንደሚለው፣ የእግዚአብሔር አምባሳደሮች መሆናችንን አስበን በዙሪያችን ላሉት ሙስሊሞች የምሕረትና የፍቅር ድምፅ እንሁን። ዛሬ ቀኑን ስንጀምር፣ ጌታ ኢየሱስ በሕይወታችን ታይቶ ብዙዎችን ወደ እርሱ የሚስብበት ጸጋ እንዲበዛልን እየለመንን ወደ ተግባር እንሰማራ። ይህ ወር እግዚአብሔር ለሙስሊም ወገኖቻችን የእውነተኛ መንፈሳዊ ብርሃን በልባቸው ላይ እንዲያበራ ይህም በልጁ አምነው እንዲድኑ ወደ ክርስቶስ ኅብረት ድነው የሚጨመሩ ሙስሊሞች እንዲበዙ አጥብቀን የምይጸልይበት ወር ይሁን። #እነሆ_እኔን_ላከኝ #ተሐድሶ_ይሆናል #ክርስቶስ_ለሕዝብ_ሁሉ
ረመዷን ጾም ቀን 27 ከሺህ ወራት የሚበልጠው እውነተኛ "ውሳኔ" የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ፦ ኤፌሶን 1፡4 ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን። ኤፌሶን 1፡4 በዚህ በረመዳን 27ኛው ቀን፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች "ለይለተል ቀድር" ወይም "የመወሰኛዋ ሌሊት" ብለው በሚጠሯት እጅግ የተቀደሰች ምሽት ላይ ይገኛሉ። በዚህ ዕለት ትኩረታቸው ሁሉ የቀጣዩ ዓመት እጣ ፈንታቸው እንዲባረክ፣ ኃጢአታቸው እንዲሰረይና ከአላህ ምሕረትን ለማግኘት ሌሊቱን ሙሉ በጸሎትና በልመና መትጋት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በኤፌሶን 1፥4 ላይ "ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳንና ያለ ነቀፋ በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን" እንደሚለው፣ የሰው ልጅ እጣ ፈንታና ውሳኔ አስቀድሞ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ፍቅር የተከናወነ መሆኑን እናውቃለን። ሙስሊም ወዳጆቻችን በዚህ ምሽት ለሚፈልጉት "የሕይወት መለወጫ" ውሳኔ፣ እኛ ክርስቲያኖች እውነተኛው የሕይወት ለውጥ የሚገኘው በክርስቶስ ቤዛነት መሆኑን ልንነግራቸው ይገባል። በዚህ ዕለት ሙስሊሞች "መላእክትና መንፈስ ወደ ምድር ይወርዳሉ" ብለው በሚያምኑበት ጊዜ፣ እኛ አማኞች ደግሞ እግዚአብሔር ራሱ በልጁ በኩል ወደ እኛ እንደወረደና ከእኛ ጋር መሆኑን ልናበስራቸው ይገባል። በዮሐንስ 1፥14 ላይ "ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ" ተብሎ እንደተጻፈው፣ እግዚአብሔርን ለማግኘት እኛ ወደ ሰማይ የምናደርገው ጥረት ሳይሆን እርሱ ወደ እኛ የመጣበት ፍቅር ትልቁ የምሥራች ነው። ሙስሊም ወዳጆቻችን በዚህ ምሽት ለሚደክሙበት የሥራ ትጋት፣ እኛ ግን በክርስቶስ የተገኘውን ፍጹም ዕረፍትና የጸጋ ወንጌል በሕይወታችን ልናሳያቸውና ልናካፍላቸው ይገባል። በጸሎታችን ደግሞ፣ በዚህ የፍለጋ ምሽት እግዚአብሔር ራሱን በታላቅ ብርሃን እንዲገልጥላቸው እንማጸናለን። ብዙዎች በጭንቀትና በተስፋ መካከል ሆነው ምሕረትን በሚፈልጉበት በዚህ ሰዓት፣ ጌታ ኢየሱስ በዮሐንስ 14፥6 ላይ "እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም" በማለት የተናገረው ቃል ልባቸውን እንዲነካው እንጸልያለን። የመዳን እርግጠኝነት በሌለበት ሃይማኖታዊ ትጋት ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን፣ መንፈስ ቅዱስ የልባቸውን መጋረጃ ገፎ በክርስቶስ ያለውን የዘላለም ሕይወት ዋስትና እንዲያሳያቸው ጽኑ ልመናችን ይሁን። በመጨረሻም፣ ይህ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ታላቅ የመነቃቂያ ጥሪ ነው። ሌሊቱን ሙሉ ለሚተጉት ሙስሊም ወዳጆቻችን ያለን ፍቅር በጸሎትና በምስክርነት እንዲገለጥ ጌታ ይርዳን። በሮሜ 10፥1 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ "የልቤ መሻትና ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጸሎቴ እንዲድኑ ነው" እንዳለው፣ የእኛም የጠዋት ጸሎትና መሻት ሙስሊሞች ከሃይማኖታዊ ቀንበር ወጥተው ወደ እግዚአብሔር ልጆች ነጻነት እንዲመጡ ይሁን። ዛሬ ቀኑን ስንጀምር፣ በንግግራችንና በሥራችን ሁሉ የክርስቶስን መዓዛ ለነርሱ የምናሳይበት ጸጋ እንዲበዛልን እየለመንን ወደ ተግባር እንሰማራ። ይህ ወር እግዚአብሔር ለሙስሊም ወገኖቻችን የእውነተኛ መንፈሳዊ ብርሃን በልባቸው ላይ እንዲያበራ ይህም በልጁ አምነው እንዲድኑ ወደ ክርስቶስ ኅብረት ድነው የሚጨመሩ ሙስሊሞች እንዲበዙ አጥብቀን የምይጸልይበት ወር ይሁን። #እነሆ_እኔን_ላከኝ #ተሐድሶ_ይሆናል #ክርስቶስ_ለሕዝብ_ሁሉ
видео или голосовое, без подписи