tgindex
ሚሽን ሞብላይዜሽን ኢትዮጵያ - Mission Mobilization Ethiopia

ሚሽን ሞብላይዜሽን ኢትዮጵያ - Mission Mobilization Ethiopia

Статистика

ሚሽን ሞቢላይዜሽን ኢትዮጵያ የተስተማበረች (ማስተማር፣ ማስተባበር እና ማሰማራት) የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በሀገር ውስጥ እና ባሻገር ያሉ ያልተደረሱ የሕዝብ ክፍሎችን ስትደርስ ለማየት ካለ ትልቅ ናፍቆት እና ረሃብ ውስጥ የተወለደ አገልግሎት ነው፡፡

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
16
Всего постов
31
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 532
+5 за 5 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
244
29 постов
Вовлечённость
15,9%
к подписчикам
Постов в день
2,3
всего 31
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
202
1/48двое суток
231
1/72трое суток
249

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የጸሎት ፕሮግራማችን ተጀምሯል ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉን። https://t.me/MobilizationEthiopia?videochat=3020c43956d7b8623a

  • በእግዚአብሔር ቸርነት ሶስት አመታት እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም። ኦሪት ዘዳግም 32፡12 አገልግሎታችን ሚሽን ሞቢላይዜሽን ኢትዮጵያ አገልግሎት ነሐሴ 2015 ዓ.ም እንደ አገልግሎት ከተመሰረተ ጀምሮ ሶስት አመታት ሞላን፤ የረዳን እግዚአብሔር የተመሰገነው ይሁን። በዚህም ወቅት አብራችሁን እንድትሰለፉ ጥሪን እናቀርባለን፤ ይህም ሚሲዮናዊያን የማስቀጠል ጥሪ ነው ! በአገልግሎታችን ሚሲዮናዊያንን የማሰማራት እና የቤተክርስቲያን ተከላ ስራ የጀመርነው ታህሳስ 2017 ዓ.ም ነው፤ በእግዚአብሔር እርዳታ ብዙዎችን በማስተበባር እና ከቤተእምነቶችና አጥቢያዎች ጋር አጋር በመሆን አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ስምንት በወንጌል ባልተደረሱ እና በጥቂቱ በተደረሱ የሕዝብ ክፍሎች መካከል 30 ሚሲዮናዊያን ማሰማራት ችለናል። ባለፉት ባለፉት 18 ወራት 36,000 (ከሰላሳ ስድስት ሺህ) ባላይ ሰዎች የምስራቹን ወንጌል ሰምተው 1490 ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተጨምረዋል፤ 23 ቤተክርስቲያኖች ተተክለዋል። ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን! አሁንም እነዚህን ሚሲዮናዊያን ለሚቀጥሉት 12 ወራት ወይም አንድ አመት እንደሚገባ ለማገዝ፣ በመስኩ ላይ ወንጌሉን እየሰበኩ ብዙዎችን መድረስ እንዲችሉ ፤ማስቀጠል ከ2.1 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልገናል ለዚህም በገንዘብ እና በጸሎት በመደገፍ አብረውን የሚሰለፉ 200 ቅዱሳንን እንፈልጋለን። እርሶም • በየወሩ 500.00 (አምስት መቶ) ብር ወይም በዓመት አንድ ግዜ 6000 (ስድስት ሺህ) ብር የሚደግፉ • በየወሩ 1000.00 (አንድ ሺህ) ብር ወይም በዓመት አንድ ግዜ 12,000 (አስራ ሁለት ሺህ) ብር የሚደግፉ • በየወሩ 2000.00 (ሁለት ሺህ)ብር ወይም በዓመት አንድ ግዜ 24,000 (ሃያ አራት ሺህ) ብር እና ከዛም በላይ በፈለጉት መጠን በመደገፍ አጋር እንዲሆኑን እንጠይቃለን። የወንጌል ተልእኮ የጥቂቶች እሩጫ ብቻ ሳይሆን የብዙዎች አብሮ መሰለፍ ነው፤ እግዚአብሔር በረዳቹሁ መጠን ላይ ዛሬ በዚህ የወንጌል ስራ በመሰለፍ በምድራችን በተለያዩ የሕዝብ ክፍሎች መካከል ወንጌል እንዲሰበክ አብራችሁን ቁሙ። አጋር መሆን የምትፈልጉ ከታች ባሉት የቴሌግራም አድራሻዎች ወይም ከታች ባሉት ስልኮች በመደወል እንዲያገኙን እንጠይቃለን። እግዚአብሔር ይባርካችሁ! ቴሌግራም ፦ https://t.me/Amangeze / ፦ https://t.me/nardossol ፦ https://t.me/Redietbelay ስልክ፦ +251920293652 +25192213 7771 +25190065 6795

  • без подписи

  • እንጸልይ ለአርሲ ኦሮሞ የሕዝብ ክፍል ! በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፡— መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት፡ አላቸው። ማቴዎስ 9፡ 37 - 38 ሰላም  የሚሽን ሞቢላይዜሽን ኢትዮጵያ ቤተሰቦች! ዛሬ አርብ ምሽት ከ3:30 ጀምሮ በቴልግራም ላይቭ ለአርሲ ኦሮሞ የሕዝብ ክፍል ! በህብረት የምንፀልይበት ጊዜ ይኖረናል ከታች ባለዉ የቴሌግራም ቻናል ሊንክ በመግባት አብራችሁን እንድትጸልዩ እንጋብዛችኋለን። https://t.me/MobilizationEthiopia

  • ተልእኳችን ማለዳ ነሀሴ 8 - 2018 ዓ.ም የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ — የዮሐንስ ወንጌል 4:1-26 ከሰማርያ አንዲት ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም። ውኃ አጠጪኝ አላት። ምስክርነት፦ እኔ? ወንጌላዊ? ብዙ ክርስቲያኖች የወንጌልን የምሥራች ለሌሎች ለማካፈል ዳተኝነት ወይም ፍርሃት ይሰማቸዋል። የተሳሳተ ነገር ተናግረን ሰዎችን ማሳዘን ወይም ማራቅ አንፈልግም። እኔም በአንድ ወቅት ከቤት ወደ ቤት እየዞርኩ ወንጌል ለመስበክ በሞከርኩበት ጊዜ ምን ያህል እፈራ እንደነበር አይረሳኝም። በታዳጊነት ዕድሜዬ በበጋ ወቅት ከሌሎች ወጣቶች ጋር በመሆን በአካባቢችን በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን በበጎ ፈቃደኝነት አገለግል ነበር። በአቅራቢያችን ለሚኖሩ ሕፃናት የበጋ ወቅት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንሰጥ የነበረ ሲሆን፣ በኋላ ላይ የሕፃናቱን ቤተሰቦች ለመጠየቅ ስንሄድ ፍርሃታችን በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ እምነታችንን እንዴት እንደምናካፍል ይቅርና የምናገለግልበትን ቤተ ክርስቲያን ስም እንኳን የምንረሳበት ጊዜ ነበር! ይህ ዓይነቱ የወንጌል መስበኪያ መንገድ በአሁኑ ጊዜ ያን ያህል ውጤታማ አይደለም። ይልቁንም ከሰዎች ጋር ዘላቂ ወዳጅነትን በመስረጽ እና እንደ ወዳጅ በመቅረብ ምስክርነትን መስጠት የበለጠ ፍሬያማ እንደሆነ ብዙዎች ተረድተዋል። የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 4 ኢየሱስ በጉድጓድ አጠገብ ከአንዲት ሴት ጋር እንዴት ጨዋታ እንደጀመረ ያሳየናል። ከማያውቋት ሴት ጋር ማውራት በዚያ ዘመን ከነበረው ባህል አንጻር ያልተለመደ ቢሆንም፣ እሷ ግን ለሕይወቷ ያለው ቅንነትና እርህራሔ ተሰማት። ኢየሱስ ደፋር ቢሆንም፣ አቀራረቡ ግን እጅግ ደግነት የተሞላበት ነበር። ከእርሱ ጋር ስትነጋገርም አሳቢ፣ ነገር ግን በሕይወቷ በተበላሹ ግንኙነቶች ምክንያት ልቧ የተሰበረ ሰው መሆኗ ተገለጠ። አብዛኛዎቹ የወንጌል ምስክርነት አጋጣሚዎች እንደዚህ ዓይነት ፈጣን ለውጥ አያመጡ ይሆናል። ነገር ግን የሰዎችን የሕይወት ታሪክ በትዕግሥት በመስማት፣ ሕመማቸውን በመጋራት፣ እንዲሁም ስለሚወዳቸው አምላክ በትሕትናና በእርጋታ በመናገር የኢየሱስን የርህራሔ መንገድ መከተል እንችላለን። ጸሎት ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ ከሌሎች ጋር ያለኝ ግንኙነት የበለጠ ትርጉም ያለው እንዲሆን ቅዱሱን መንፈስን ይበልጥ ሙላኝ። በምትሰጠኝ አጋጣሚዎች ሁሉ በሰዎች መካከል  ከአንተ በሆነ ርህራሔ እና ፍቅር ምላሽ እንድሰጥ እርዳኝ። አሜን። ከ https://todaydevotional.com/authors/kevin-deraaf ድህረ ገጽ ተወስዶ የተተረጎመ

  • без подписи

  • ቀን 4 እንጸልይ ለአርሲ ኦሮሞ የሕዝብ ክፍል ፍላጎቶቻቸው ምንድን ናቸው የአርሲ አካባቢዎች የበለፀገ ባህላዊ ውርስ ቢኖራቸውም፣ እንደማንኛውም የአፍሪካ ቀንድ ገጠራማ አካባቢዎች በርካታ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል። ዋና ዋና የመሠረተ ልማት ፍላጎቶቻቸው ንጹሕ የመጠጥ ውሃ፣ ዘመናዊ የጤና ተቋማት እና የክልሉን የትምህርት ልዩነት የሚያጠበቡ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ማስፋፊያ ናቸው። በኢኮኖሚው በኩል አነስተኛ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በአየር ንብረት ለውጥ፣ በመሬት መበላሸት እና በገበያ እጥረት ተፅዕኖ ሥር በመሆናቸው፤ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎች፣ የእንስሳት ሕክምና አገልግሎቶች እና ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ሥርዓት ያስፈልጋቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ታሪኮችን መጠበቅ፣ የገዳ ሥርዓት ውርሶችን በሰነድ ማስፈር፣ እና ለአካባቢው ወጣቶች የሥራ ዕድልና የሙያ ስልጠናዎችን በመፍጠር የረጅም ጊዜ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው። ምንጭ፦ Joshua Project & Ethnologue Records: Oromo, Arsi in Ethiopia demographic and cultural dataset profile. የጸⶀት ርዕሶች 🤲🏼 👉🏼 በእምነታቸው ምክንያት ከቤተሰብ፣ ከጎሣ ወይም ከአካባቢው ማኅበረሰብ ስደት፣ ማግለልና ጫና የሚደርስባቸው አዲስ አማኞች በክርስቶስ ፍቅርና ጽናት እንዲቆሙ፣ ተስፋ እንዳይቆርጡ  እንዲሁም ስደት የሚያደርሱባቸው ወገኖች ልብ በወንጌል እውነት እንዲሰበርና ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ እንጸልይ። 👉🏼 ስለ አርሲ ኦሮሞ ሕዝብ መዳን፣ ትውልድ መለወጥና መንፈሳዊ መነቃቃት ቀንና ሌሊት የሚጾሙና የሚጸልዩ የጸሎት ቡድኖች (Prayer Shield) በየቦታው እንዲቋቋሙ፤ የእግዚአብሔርም ታላቅ ጉብኝት በምድሪቱ ላይ እንዲሆን እንጸልይ። 👉🏼 ለአካባቢው ወጣቶች በቂ የሙያ ሥልጠናና የሥራ ዕድል እንዲፈጠር፤ የታሪክ ቅርሶች ተጠብቀው ለትውልድ ሲተላለፉ ወጣቱ ከአሉታዊ ተፅዕኖዎች ተጠብቆ ለምድሪቱ ሰላም፣ መረጋጋትና ልማት መሪ ሆኖ እንዲወጣ እንጸልይ።

  • без подписи

  • ሶስት አመታት በእግዚአብሔር ቸርነት! የምስጋና ሳምንት እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም። ኦሪት ዘዳግም 32፡12 ባለፉት 12 ወራት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተካሄዱ 79 የአገልግሎት ትምህርቶችና ሥልጠናዎች 5,705 አማኞችን በማንቃት ለእግዚአብሔር ዓለም አቀፍ ተልዕኮ እንዲዘጋጁ ማድረግ ተችሏል። በ2018 ዓ.ም  በኦንላይን የጸሎት መርሃ ግብሮች፣ በየሁለት ወሩ በሚካሄዱ በአካል የሚደረጉ የጸሎት ጉባኤዎች (Prayer Summits) እና በእሁድ አምልኮዎች በተጀመሩ የጸሎት ንቅናቄዎች አማካኝነት ባልተደረሱ ብሔረሰቦች ላይ ያተኮሩ የጸሎት ፕሮግራሞችን ማካሄድ ችለናል። በዓመቱ ውስጥ ላልተደረሱ ብሔረሰቦች የሚደረገውን ሳምንታዊ የጸሎት ንቅናቄ አጠናክረን የቀጠልን ሲሆን፣ በ48 ተከታታይ ሳምንታት ውስጥ ለ80 ለተለያዩ ብሔረሰቦች የሚያስብ ቋሚ ፕሮግራም አካሂደናል። በሺዎች የሚቆጠሩ አማኞች በእነዚህ የኦንላይን መርሃ ግብሮች ላይ ተሳታፊ ሆነዋል። የረዳን ያገዘን አምላካችን እግዚአብሔር ስሙ የተባረከ ይሁን! አብራችሁን ለምስጋና ቁሙ!

  • ተልእኳችን ማለዳ ነሀሴ 7 - 2018 ዓ.ም የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ — የሐዋርያት ሥራ 8:1 በዚያን ቀንም በኢየሩሳሌም ባለች ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ሁሉም ከሐዋርያትም በቀር ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ አገሮች ተበተኑ። ባህል-ተሻጋሪ፦ ለዓለም ሁሉ በዚህ ሳምንት ሌላኛውን አስፈላጊ የሚሲዮን ጽንሰ-ሐሳብ እንቃኛለን፦ ባህል-ተሻጋሪነት (Intercultural)። ለኢየሱስ ባህል-ተሻጋሪ አገልጋዮች መሆን ማለት፣ እግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ ባለው ታላቅ ዓላማ ውስጥ ለመካፈል ከተለያዩ የሕዝብ ክፍሎች  ከተወጣጡ ሰዎች ጋር በጋራ መሥራት ማለት ነው። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የተመዘገበውን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በትኩረት ካስተዋልን፣ ይህን መርህ በተግባር ሲገለጥ እንመለከታለን። ኢየሱስ ከአገልግሎቱ ዘመን አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፈው በገዛ ወገኖቹ (በአይሁዳውያን) መካከል ቢሆንም፣ የንግሥናው የምሥራች ለሕዝቦች ሁሉ የተዘጋጀ መሆኑን የሚያሳዩ በርካታ ፍንጮችን ሰጥቷል። የሚሲዮን ሥራ መነሻው ኢየሩሳሌም ነበረች፤ ሆኖም በስደት ምክንያት አማኞች በተበተኑ ጊዜ፣ "በሄዱበት ሁሉ ቃሉን ይሰብኩ ነበር።"ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳ ሁሉ፣ በሰማርያ እንዲሁም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቹ እንደሚሆኑ ቃል ገብቶላቸው ነበር (የሐዋርያት ሥራ 1:8) ። በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍላችንም፣ የወንጌል ትምህርት ከኢየሩሳሌም አልፎ ወደ ይሁዳና ሰማርያ እንዴት እንደተስፋፋ በግልጽ እንመለከታለን። የኢየሱስ የምሥራች እየተስፋፋ ሲሄድ የብሔርና የባህል ድንበሮችን እያለፈ ተሻገረ። በጥቂት ዓመታት ውስጥም እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ ያሉ ወንጌላውያን የእግዚአብሔርን የማዳን ቃል በሮም ግዛትና ከዚያም ባሻገር አበሰሩ። ዛሬ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን በከፍተኛ ፍጥነት እያደገች የምትገኘው እንደ አፍሪካ፣ እስያ እና ማዕከላዊ አሜሪካ ባሉ አካባቢዎች ነው። የኢየሱስ ቃል ኪዳን ዛሬም ቢሆን በእኛ ዘመን እየተፈጸመ ይገኛል! ጸሎት ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ መልካሙ የምሥራችህ በማንኛውም ባህልና ብሔር ውስጥ ላሉ ሕዝቦች ሁሉ ስለሆነ እናመሰግንሃለን። በዓለም ዙሪያ ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያንህና በተለያዩ ባህሎች መካከል ለሚያገለግሉ ወንጌላውያን ሁሉ ተልእኮህን ይበልጥ ይዘው እንዲሰማሩ እንጸልያለን። አሜን። ከhttps://todaydevotional.com/authors/kevin-deraaf ድህረ ገጽ ተወስዶ የተተረጎመ

  • без подписи

  • ቀን 3 እንጸልይ ለአርሲ ኦሮሞ የሕዝብ ክፍል እምነታቸው ምንድን ነው? አብርሃማዊ እምነቶች በስፋት ከመሰራጨታቸው በፊት፣ አርሲዎች በዋቃ (በአንድ ፈጣሪ) የሚያምነውንና የዓለምን የተፈጥሮና የሞራል ሥርዓት (ዳኒ/ሴራ) የሚጠብቀውን የኦሮሞ ባህላዊ "ዋቄፈና" እምነት ይከተሉ ነበር። ከ16ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ባለው ጊዜ ውስጥ ከምሥራቃዊ የእስልምና አካባቢዎች ጋር በተፈጠረው የንግድ መስመር ትስስር እና በግዛት ማካተት ወቅት በነበረው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሁነቶች ምክንያት፣ አብዛኛው የአርሲ ሕዝብ ወደ ሱኒ እስልምና እምነት ተለወጠ። ዛሬ ላይ የሱኒ እስልምና በሕዝቡ ዘንድ ቀዳሚው እምነት ቢሆንም፣ እንደ ባሌው የሼክ ሁሴን መቅደስ መንፈሳዊ ጉብኝት ያሉ ባህላዊና አካባቢያዊ ልማዶች ከእስልምና እምነት ጋር ተዋህደው ይታያሉ። በተጨማሪም ጥቂት የማይባሉ የአርሲ ኦሮሞዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እና  የፕሮቴስታንት  ክርስቲያኖች ናቸው። ምንጭ፦ Abbas Gnamo (2014): Conquest and Resistance in the Ethiopian Empire, 1880–1974: The Case of the Arsi Oromo, Brill Academic Publishers. የጸሎት ርዕሶች 🤲🏼 👉🏼 በአርሲ ምድር መካከል ተተክለው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዲታደሱ፣ በፍቅርና በአንድነት እንዲመላለሱ እንዲሁም የወንጌል እይታቸው እንዲሰፋ። እርስ በእረሳቸው በመያያዝ እና በመደጋገፍ በፍቅር ወንጌል እንዲመላለኩ ለዚህ ሕዝብ በረከት እንዲሆኑ እንጸልይ። 👉🏼 ከአርሲ ኦሮሞ ተወላጆች መካከል በወንጌል እሳት የተሞሉ ፣ ሕዝባቸውን በቅድስናና በዕውቀት የሚመሩ አገር በቀል የቤተክርስቲያን መሪዎችና እረኞች እንዲወጡ እንጸልይ። 👉🏼 በአርሲ፣ ምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች በሚገኙ ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የሚያጋጥማቸው የአየር ንብረት ለውጥ፣ የመሬት መበላሸትና የገበያ እጥረት እንዲቃለል፤ አካባቢው በቂ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ፣ ዘመናዊ የጤና ተቋማትና የትምህርት ዕድሎችን አግኝቶ ሕዝቡ በኢኮኖሚና በጤና እንዲበለፅግ እንጸልይ።

  • без подписи

  • ሶስት አመታት በእግዚአብሔር ቸርነት! የምስጋና ሳምንት እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም። ኦሪት ዘዳግም 32፡12 በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በአጠቃላይ 14 አዳዲስ ሚሲዮናውያን የተሰማሩ ሲሆን፣ ይህም በአጠቃላይ የተሰማሩትን ሚሲዮናውያን ቁጥር ወደ 30 አድርሶታል። እነዚህ አገልጋዮች በአሁኑ ወቅት በ8 የሕዝብ ክፍሎችና በ25 በሚሽን ጣቢያዎች ውስጥ በማገልገል ላይ ይገኛሉ። በ2018 ዓ.ም ወንጌል ዝርጋታ እና ቤተክርስቲያን ተክሎ አገልግሎታችን እግዚአብሔር በብዙ ረድቶን 27,255 ሰዎች የወንጌል ምስክርነትን ሰምተዋል፤ ከእነዚህም መካከል 839 ሰዎች ኢየሱስን ለመከተል ሕይወታቸውን ሰጥተዋል። የዳኑ ሰዎች እና የቀድሞ እምነት ከኦርቶዶክስ እምነት: 403 ሰዎች ከእስልምና እምነት: 173 ሰዎች ከባህላዊ እምነቶች: 262 ሰዎች ከሃይማኖት የለሽ: 1 ሰው የረዳን ያገዘን አምላካችን እግዚአብሔር ስሙ የተባረከ ይሁን! አብራችሁን ለምስጋና ቁሙ!

  • ተልእኳችን ማለዳ ነሀሴ 6 - 2018 ዓ.ም የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ፦  የሐዋርያት ሥራ 2:22   የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤ የተዓምራት ምድር የአዲስ ኪዳን አማኞች ተዓምራቶችን ፍለጋ ወደ ተለያየ ስፍራ የሚያማትሩ ወይም በጥልቀት  የሚመራመሩ አልነበሩም። እነርሱ  የሚኖሩት የተዓምራት ምድር (ቅጥር)  ውስጥ ነበር። የሚኖሩት በእግዚአብሄር መንግስት በመሆኑ በእያንዳንዱ ሁኔታዎቻቸው ላይ የእግዚአብሔርን የተዓምራት እጅ ይመለከቱ ነበር። በእነርሱ ዘንድ የዕለት ተዕለት ክርስቲያናዊ ሕይወት በራሱ ሙሉ በሙሉ በኃይልና በተአምራት የተሞላ እንደሆነ ይታመን ነበር። ይህ ጭብጥ በሐዋርያው ጳውሎስ መልእክቶች ውስጥ በሰፊው የሚገኝ ነው።   ቤተክርስቲያን በተመሰረተችበት የመጀመሪያው ቀን ተዓምራት የተትረፈረፈ ነበር። የድነት ተዓምራት (በአጥቢያ ቤተክርስቲያናቹ በአንድ ቀን 3000 አዳዲስ አማኞች ከእናንተ ጋር ቢቀላቀሏቹ ምን ሊመስል እንደሚችል አስቡት ፣ የፈውስ ተዓምራቶች ፣ የህብረት ተዓምራቶች (ባሪያዎች እና ጌቶች  ያላቸውን ሁሉ በአንድ ላይ እኩል ሲካፈሉ ማየት ለሚመለከታቸው ምን አይነት የማይታመን ነገር ሊሆን እንደሚችል አስቡት) ፣  የበረከት (የፋይናንስ) ተአምራት እና የመሳሰሉት። በጊዜው ስለነበረው ተዓምራትን ለመመልከት የሃዋርያት መጽሃፍ የመጀመሪያዎቹን 5 ምዕራፎች ማንበብ ብቻ በቂ ነው።  እነዚህ ተዓምራቶች የገዢዎችን ትኩረት የሳቡ እና በመካከላቸው ስጋትን (ፍራቻን) የፈጠሩ ነበሩ። ምክንያቱም ደግሞ እነዚህን ተዓምራት እንዴት እንደከወኗቸው ሊረዱት ባለመቻላቸው ነበር። የታወቀ ምልክት በእነርሱ እጅ እንደ ተደረገ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ተገልጦአልና፥ እንሸሽገው ዘንድ አንችልም፤ ሐዋ 4፡16 ምንም እንኳን በነገሩ ባይደሰቱም ፣ ሐዋሪያቱን በተለያዩ መንገድ ቢያሳድዷቸውም ፣ ተዓምራቱን በጭፍን ቢክዱትም  የእግዚአብሄርን ሃይል ከመንቀሳቀስ ሊያግዱ ወይም የሐዋሪያቶቹን ወንጌል የመስበክ ድፍረት (ጀግንነት) ሊያግዱ አልተቻላቸውም። የሚያሳዝነው ሁኔታ በሐዋሪያቱ ዘመን በቀላሉ የሚሆነው ተዓምራት አሁን በዘመናችን ግን ቀላል አይደለም። አሁን ላይ ተዓምራቶችን ለማግኘት አዳዲስ ዘዴዎች ፍለጋ ላይ ትልቅ ትኩረት ስለሰጠነው ነገርየው አንዳች ሚስጢራዊ ነገር ተደርጎ ይታሰባል። እኔ ይህን እንደሚስጥር የሚታየውን ከባዱን ነገር አስወግጄ መጀመሪያ በክርስቶስ ወደ ነበረው ቀላልነት መመለስ እፈልጋለው። አብረን አንድ ተአምር እንመለከታለን፤ ከዚያም ከእርሱ የበለጠውን ነገር እናያለን! በመጨረሻም፣ እኔና አንተ በራሳችን ሕይወት ውስጥ ተአምራትን እንመልከት!    ከሪንሃርድ ቦንኬ “Daily Fire” የዕለት ተዕለት የማለዳ የጥሞና መጽሐፍ የተወሰደ www.Reinhard Bonnke.com

  • без подписи

  • ቀን 2 እንጸልይ ለአርሲ ኦሮሞ የሕዝብ ክፍል ሕይወታቸው ምን ይመስላል? በታሪክ አጋጣሚ ከአርብቶ አደርነትና ከፊል አርብቶ አደርነት ጋር የተያያዘ የኑሮ ዘይቤ የነበራቸው የአርሲ ኦሮሞዎች፣ ዕለታዊ ህይወታቸው በከብት እርባታ፣ በወገንተኝነት/የዘመድ አዝማድ ትስስር እና በግብርና ላይ ያተኮረ ነው። በደጋ እና ወይናደጋ አካባቢዎች የከብት እርባታ ጎን ለጎን ገብስ፣ ስንዴ፣ ጤፍ እና በቆሎ እርሻ የኢኮኖሚያቸው ዋና መሠረት ሲሆን፣ በቆላማ ቦታዎች ደግሞ አርብቶ አደርነት አሁንም በስፋት ይሠራበታል። የኅብረተሰቡ መዋቅር በባህላዊ ሕጎች (ሴራ) በሚመሩ የተያያዙ ቤተሰቦች እና በአባት በኩል በሚቆጠሩ የጎሣ መዋቅሮች (ጎሳ) ላይ የተመሠረተ ነው። ባህላዊ የማኅበራዊ ሕይወት ድርሻዎችና የሽግግር ሥርዓቶች የጋራ አንድነትን፣ ለታላቆች የሚሰጥን ክብርና ማኅበራዊ ሀላፊነትን ያጎላሉ። በተለይም ሴቶች የተከበረ ማኅበራዊና ባህላዊ ስፍራ አላቸው፤ ለዚህም ማሳያው ያገቡ ሴቶች ይዘውት የሚንቀሳቀሱት "ሲቄ" የተሰኘው ባህላዊ በትር ሲሆን፣ ይኸውም ታሪካዊ የማኅበራዊ መብታቸው፣ የሞራል ልዕልናቸው እና ከበደልና ጥቃት መከላከያ ምልክታቸው ነው። ምንጭ፦ Paul T. W. Baxter (1978/1996): Ethnographic and historical field studies on the Arsi Oromo, Gadaa governance, and social institutions. የጸሎት ርዕሶች 🤲🏼 👉🏼 የአርሲን ሕዝብ ባህልና ቋንቋ የሚረዱ፣ በፍቅርና በትዕግሥት የተሞሉ ይህን ሕዝብ በወንጌል ለመድረስ የቆረጡ ሚሲዮናውያንና ወንጌላውያን ወደ አርሲ ምድር እንዲሰማሩ (ማቴዎስ 9:38) እንጸልይ። 👉🏼 ለአርሲ ሕዝብ ተልዕኮ የሚሄዱ አገልጋዮችን በቋንቋ፣ በባህልና በወንጌል ሥልት አዘጋጅተው የሚያሰማሩ አገልግሎቶች፣ የሥልጠና ማዕከላትና አብያተ ክርስቲያናት እንዲበዙ እንጸልይ። 👉🏼 በማኅበረሰቡ ዘንድ ያሉ እንደ "ሲቄ" (የሴቶች መብትና ሞራል መጠበቂያ) እና "ገዳ" ያሉ መልካም ባህላዊ ሥርዓቶች፣ ማኅበራዊ ፍትሕንና አንድነትን ለማጠናከር በሚያደርጉት በጎ አስተዋጽኦ ላይ የእግዚአብሔር ፍቅርና እውነት ተጨምሮበት ይበልጥ እንዲጎለብት፤ ሴቶች፣ ሕፃናትና መላው ቤተሰብ ከማንኛውም በደል ተጠበቀው በፍቅር እንዲኖሩ እንጸልይ።

  • без подписи

  • ሶስት አመታት በእግዚአብሔር ቸርነት! የምስጋና ሳምንት እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም። ኦሪት ዘዳግም 32፡12 በ2018 ዓ.ም በዲጂታል ሚሽን ሞቢላይዜሽን ፕሮግራማችን እግዚአብሔር በብዙ እረድቶን ብዙ ሺዎችን በማህበራዊ ሚዲያ በኩል መድረስ ችለናል። በፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ኢንስታግራም እና ቴሌግራም ገጾቻችን ላይ በየዕለቱ ከፍተኛ የተጠቃሚዎች ቁጥር ማግኘት ችለናል። ጥራት ያላቸውን ይዘቶች በማዘጋጀትና በቋሚነት በማሰራጨት፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ማኅበረሰባችን በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ይገኛል። ከ1,000 በላይ ልዩ ልዩ ይዘቶች ተዘጋጅተው ተሰራጭተዋል። በሁሉም ማኅበራዊ ሚዲያዎች የተገኙ እይታዎች (Views) 8.6 ሚሊዮን ደርሰዋል፤ ይዘቶቻችንን ያዩ የተለያዩ ቁጥር ያላቸው ተጠቃሚዎች  889,900 ደርሰዋል፤ የይዘት ግብረመልሶች (ላይክ፣ ሼር፣ ኮመንት) ደግሞ 401,300 ደርሰዋል። የረዳን ያገዘን አምላካችን እግዚአብሔር ስሙ የተባረከ ይሁን! አብራችሁን ለምስጋና ቁሙ!

  • ተልእኳችን ማለዳ ነሀሴ5 - 2018 ዓ.ም የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ፦  የዮሐንስ ራእይ 14:15 ሌላ መልአክም ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመ ጠው፡— የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፥ የምድሪቱ መከር ጠውልጓልና ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። የተረጋገጡ  ምልክቶች ክርስቲያኖች ስለ ክርስቶስ ዳግም ምፅዐት (ተመልሶ መምጣት) ይቃትታሉ። ይህም ጸሎት በማንኛውም ቀን እንደሚመለስ ነገ የመንጋቱን ያህል እርግጠኞች ነን። በዚህ ልክ ግን እንዴት እርግጠኞች መሆን ቻልን? ምክንያቱም መጽሃፍ ቅዱስ ስለነገረን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ በትንቢት በተናገረው መሠረት ክርስቶስ ለመጀመሪያ ጊዜ በትክክል መጥቷል፤ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ዳግመኛም በርግጥ ይመጣል! ከዚህም በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ አስቀድሞ በመተንበይና ትንቢቱም በትክክል በመፈጸሙ እውነተኛነቱን ያረጋገጠ ብቸኛው መጽሐፍ ነው። ጌታም፦ “እፈጽመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁና” በማለት ተናግሯል። (ኤር 1፡12)። የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት በክርስቶስ የመጀመሪያ አመጣጥ (ልደት) ወቅት ሙሉ በሙሉ ተፈጽሟል። ሰበአሰገል በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎችን ተጉዘው ኢየሱስን መጽሐፍ ቅዱስ የሚገኝበትን ቦታ አስቀድሞ በተናገረው መሠረት በቤተልሔም አግኝተውታል። የብሉይ ኪዳን ነቢያት እንዴት እንደሚወለድ፣ እንደሚኖርና እንደሚሞት አስቀድመው ተናግረው ነበር። ይህም እጆቹ እንደሚወጉ፣ በልብሶቹ ዕጣ እንደሚጣጣሉበት፣ መቃብሩም “ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፥ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።” የመሳሰሉትን ትንቢቶች ተናግረዋል። (ኢሳይያስ 53፥9) መጥምቁ ዩሃንስ ከመጻሕፍት መሲሁ ሊገለጥ እንደቀረበ የተረዳ ሰው ነበር። ኢየሱስ ወደ ሕዝባዊ አገልግሎቱ ከመግባቱ በፊት ዮሐንስ እንዲህ እንደሚል በመጀመሪያው እይታ መለየቱን ተናግሯል፦ « ከእኔ የሚበረታ ከእኔ በኋላ ይመጣል፤ እኔ ዝቅ ብዬ የጫማውን ማሰሪያ ልፈታ አይገባኝም። እኔ በውኃ አጠመቅኋችሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል» (ማርቆስ 1፥7–8)። እነዚህን ሁሉ ግልጽና የተረጋገጡ የመጀመሪያ አመጣጡን ምልክቶች በማየት፣ የተናገረውን ተስፋ በርግጥ እንደሚፈጽም ሙሉ በሙሉ በመተማመን የዳግም ምጽአቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምልክቶች መከታተል እንችላለን! የእኛ ድርሻ ደግሞ እርሱ እስኪመጣ ድረስ መከሩን መሰብሰባችንን መቀጠል ነው! ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።እናንተ፦ ገና አራት ወር ቀርቶአል መከርም ይመጣል ትሉ የለምን? እነሆ እላችኋለሁ፥ ዓይናችሁን አንሡ አዝመራውም አሁን እንደ ነጣ እርሻውን ተመልከቱ። የሚያጭድ ደመወዝን ይቀበላል፥ የሚዘራና የሚያጭድም አብረው ደስ እንዲላቸው ለዘላለም ሕይወት ፍሬን ይሰበስባል። ዩሐ 4፡34-36   ከሪንሃርድ ቦንኬ “Daily Fire” የዕለት ተዕለት የማለዳ የጥሞና መጽሐፍ የተወሰደ www.Reinhard Bonnke.com