Natty's Perspectives
СтатистикаI am a Christian whose goal is to glorify God by serving others.
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 12:13
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 209
- 1/48двое суток
- 239
- 1/72трое суток
- 258
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የኖርኩትን ዘመን ስቃኝ ከዚህ ውጪ ምን እልሃለሁ:- "እግዚአብሔርን። አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም።" ~ መዝ 16:2 ~ "I say to the Lord, “You are my Lord; I have no good apart from you.” ~ Psalm 16:2 ESV ~ በእኔ ሕይወት ለተገኘውና ለሆነው በጎ ነገር ሁሉ ብቸኛው ማብራሪያ አንተ ነህና ተመስገን! @Romans148
ጌታ ሆይ፣ ደክሞናል፤ እባክህ ቶሎ ና! @Romans148
የዓለም ኀጢአተኞች እንኳን ደስ ያላችሁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቷል ሊድናችሁ፤ የዓለም ኀጢአተኞች እንደኔ ያላችሁ፣ ኢየሱስ ያድናል በእርሱ ተስፋ አላችሁ። ኢየሱስ ሠርቶል- በእርሱ ተስፋ አላችሁ፣ አየሱስ ሆኖታል- በእርሱ ተስፋ አላችሁ። ኢየሱስ ችሎታል - በእርሱ ተስፋ አላችሁ። ወዳጆቼ፣ ግድ የለም ኢየሱስ አለላችሁ። ተነሱ፤ ወደቤቱ ሂዱ፤ በተስፋውም ታደሱ። መልካም የጌታ ቀን! @Romans148
የዮሐንስ ወንጌሎ ጥናት ወዳጆች፣ ባለፈው ባሳወቅኳችሁ መሰረት የዮሐንስ ወንጌል የምናጠናበትን Group ከፍቻለሁ። ተሰጥታችሁ ለማጥናት ፈቃዳችሁን የገለጣችሁ ሰዎች ከታች ያለውን ሊንክ ተጭናችሁ join አድርጉ። ግሩፑ ለሚያጠኑ ሰዎች ብቻ የሚሆን private group ነው። በየሳምንቱ ለማጥናት የሚረዱን ጥያቄና ጽሑፎችን እዛ ላይ አጋራችኋለሁ። https://t.me/+8339PM6iuPswNGQ5
የሐዮንስ ወንጌል ጥናት ወዳጆች እንዴት አላችሁ? በትዕግስት ስለጠበቃችሁኝ እግዚአብሔር ያክብርልኝ። በቤተክርስቲያናችን የኤፌሶንን ጥናት ጨርሰን የዮሐነስ ወንጌልን በቤተክርስቲያን ጥናት እየጀመርን ነው። ጥናቱን ለማድረግ ያሰብኩት በunit/pericop ነው ማለትም ከተቻለ አንድን ሀሳብ በአንድ ክፍል ለመጨረስ። ለጥናቱ እንዲያግዝ ጥያቄዎችን በየክፍሉ አዘጋጅቼ አጋራለሁ። ጥናቱ roughly ወደ 2 ዓመታት…
ክርስቶስን ለብሼ ከኩነኔ ባላመልጥ ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር?! በምንስ ድፍረት ፊትህ እቀርብ ነበር?! "ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።" - ገላትያ 3፡27 - "እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።" - ሮሜ 8፡1 - @Romans148
የጌታን እራት እየወሰድን ሲዘመሩ እንባዬን ከሚያመጡ ዝማሬዎች አንዱ ነው። ተጋበዙልኝ። 1. O Living Bread from heaven, How well You feed Your guest! The gifts that You have given Have filled my heart with rest. Oh, wondrous food of blessing, Oh, cup that heals our woes! My heart, this gift possessing, With praises overflows. 2. My Lord, You here have led me To this most holy place And with Yourself have fed me The treasures of Your grace; For You have freely given What earth could never buy, The bread of life from heaven, That now I shall not die. 3. You gave me all I wanted; This food can death destroy. And You have freely granted The cup of endless joy. My Lord, I do not merit The favor You have shown, And all my soul and spirit Bow down before Your throne. 4. Lord, grant me then, thus strengthened With heav’nly food, while here My course on earth is lengthened, To serve with holy fear. And when You call my spirit To leave this world below, I enter, through Your merit, Where joys unmingled flow. @Romans148
፩፡ ኢየሱስ ሲጠራህ ወደ ሰማይ ቸኩል ወደርሱ ሳትዘገይ። መንገዱንም ያስተምርሃል ፍቅሩ ይታይሃል። ድንቅ ይሆናል ለሰማይ መናኝ ድኖ ካምላክ ጋራ ሲገናኝ ምን ያህል ደስታ አለው በላይ በቤቱ በሰማይ። ፪፡ ዛሬ በቃሉ ቀርቦልሃል ቸሩ እረኛ ፈልጎሃል። ሰምተሃል ድምፁን ወንድሜ ሆይ ልብህን ከፈትህ ወይ ድንቅ ይሆናል . . .። ፫፡ ሳታመነታ ክፈትለት ፈጥነህ ተቀበል ከርሱ ስርየት። ዛሬ ሲሰጥህ ያምላክ ጸጋ ልብህን አትዝጋ። ድንቅ ይሆናል . . .። @Romans148
አቤቱ አንተን ለመስማት ያዘነበለ ልብ ስጠኝ!! @Romans148
ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ናት "የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።" - 1 ቆሮ 3፡16-17 - ይህ ከላይ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ብዙዎቻችን ስናነብ ለግለሰብ እንደሆነ እያሰብን ነው። ግለኝነት የሚያጠቃው የክርስትና እይታችን "የእግዚአብሔር በተመቅደስ ናችሁ" ሲባል ፈጥኖ የሚያስበው ጌታ እንደግለሰብ በእርሱ ውስጥ እንደሚያድር ብቻ ነው። ሃሳቡ በራሱ መጽሐፍ ቁዱሳዊ በመሆኑ ችግር የለበትም። ነገር ግን ክፍሉን በአውዱ ስታነቡት ቅዱስ ጳውሎስ እየተናገረ ያለው ስለ አንድ አማኝ-ግለሰብ ሳይሆን ስለ ቅዱሳን ህብረት፣ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ነው። የእግዚአብሔርን ቤተከርስቲያን "እኔ የጳውሎስ፣ እኔ ደግሞ የአጵሎስ ነኝ" በሚል ክፍፍል እንዳያፈርሱ ነው የጳውሎስ ማስጠንቀቂያ። ክፍሉ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ህብረት ያለውን ግንዛቤ ጥሩ አድርጎ ያሳየናል። የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን እንዲሁ የሚሰበሰቡ የግለሰቦች ክምችት ሳትሆን ሕያው እግዚአብሔር የሚያድርባት ቤተመቅደሱ ናት። ስለዚህ ወገኖቼ ወደ ቅዱሳን ህብረት ስትሄዱ እንዲህ ባለ መረዳት ይሁን። የቅዱሳን ህብረት እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል የሚያድርበት፣ ህዝቡን የሚባርክበት፣ ድኅነትን የሚለግስበት ስብስብ ነው። ስለዚህ ደስ እያላችሁ ሂዱ። "ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።" - 1 ጢሞ 3፡15- መልካም የጌታ ቀን! @Romans148
The Love of God does not find, but creates, that which is pleasing to it. The love of man comes into being through that which is pleasing to it. The love of God which lives in man loves sinners, evil persons, fools, and weaklings in order to make them righteous…
የሐዮንስ ወንጌል ጥናት ወዳጆች እንዴት አላችሁ? በትዕግስት ስለጠበቃችሁኝ እግዚአብሔር ያክብርልኝ። በቤተክርስቲያናችን የኤፌሶንን ጥናት ጨርሰን የዮሐነስ ወንጌልን በቤተክርስቲያን ጥናት እየጀመርን ነው። ጥናቱን ለማድረግ ያሰብኩት በunit/pericop ነው ማለትም ከተቻለ አንድን ሀሳብ በአንድ ክፍል ለመጨረስ። ለጥናቱ እንዲያግዝ ጥያቄዎችን በየክፍሉ አዘጋጅቼ አጋራለሁ። ጥናቱ roughly ወደ 2 ዓመታት ይፈጃል በሳምንት አንድ ጊዜ ስለሚሆን። ይዘቱ ለማንኛውም አማኝ የሚሆን እንጂ እንዲሁ speculative ዓይሆንም። ግቡም፣ ወንጌሉን ሲጽፍ ዮሐንስ እንዳለመው ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ማወቅ ነው፣ የእግዚአብሔርንም ሕይወት መካፈል ነው። አብራችሁኝ ይህንን የዮሐንስን ወንጌል ጥናት በመሰጠት ለማጥናት የምታስቡ ሰዎች በኮሜንት section ብታሳውቁኝ ወይ ግሩፐ ከፍተን አስፈላጊ ከሆነም በzoom አድርገን በጋራ ማጥናት እንችላለን። ስናጠና ከእኔ ወደናንተ እንዲፈስ ብቻ ሳይሆን ራሳችሁ ከወንጌሉ ጋር engage እንድታደርጉ አስባለሁ። ጥያቄዎችን እየላኩላችሁ ሰርታችሁ ትመልሳላችሁ። ከእናንተም የሚነሱ ጥያቄዎችን በጋራ ለመመለስ እንሞክራለን። @Romans148
ወዳጆቼ ፣እስቲ ጥቂት ጊዜ ከዚህ አካባቢ አረፍ ብዬ እመለሳለሁ። ታግሳችሁ ስለምትጠብቁኝ አመሰግናለሁ። የያዛችሁን ኢየሱስ አጥብቃችሁ ያዙት። ክበሩልኝ! @Romans148
"በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ። በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።" ~መዝ 37፥3-4~ Pursue God with all your strength, with all your heart, and with all your mind, and leave the rest to Him. መልካም ቀን! @Romans148
ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችንን ይዘን፣ ያልገቡንን እንቆቅልሾች ታቅፈን፣ መስቀላችንን ተሸክመን፣ እንከተልሀለን። ብቻ በዚህ ሁሉ ውስጥ አንተን አንጣህ፣ ህልውናህ አይለየን፣ በድካማችን የሚያግዝ መንፈስህ ይብዛልን፣ ቀኛችንንም ያዘን። አንተን ማብራሪያ የግድ አንልህም፣ ሉዓላዊ አምላክ ነህ ሁሉን እንደፈቃድህ ምክር የምትፈጽም። አንተን አንጠረጥርህም፣ በልጅህ ሞት የፍቅርህን ታላቅነት ያሳየኸን አባት ስለሆንህ። እያነከስንም ቢሆን እንከተልሀለን። በዚህ ሁሉ ግን አንተ ብዛልን፣ ፍቅርህን በልባችንን እንደ ዥረት አፍስስልን፣ ወደ ልጅህም መልክ ሞርደን። አሜን! @Romans148
видео или голосовое, без подписи
ከጌታ ጋር ስለምናሳልፈው የማለዳ የጥሞና ጊዜ ቆንጆ መልክት ነው። አድምጡት። ፓይፐር በእግዚአብሔር ላይ ያለን ፍስሃ እንዲከርም ምን ማድረግ እንዳለብን ጥሩ ምክር ይሰጣል። https://www.desiringgod.org/interviews/why-is-my-delight-in-god-so-short-lived
ቤተክርስቲያን ሂዱ፤ የጌታንም ጸጋ ተካፈሉ። ከቅዱሳን ጋር የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ በርቱ፤ መንፈሱ ይሥራችሁ፣ ያሳድጋችሁም። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:22 በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3:14-15, 18-19 [14-15] ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ፤ [18-19] ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ። መልካም የጌታ ቀን! @Romans148
“Mary and Martha represent two approaches to the Christian life. Martha is actively serving Jesus, but she is missing Jesus. She is busy in the 'doing' of life. Her life, at this moment, is filled with 'shoulds' and 'have tos.' Her life is fragmented, pressured, and filled with distractions. Her duties have become disconnected from her love for Jesus. Martha’s problem goes beyond her busyness. Her life is uncentered and divided. I suspect that if Martha were to sit at the feet of Jesus, she would still be distracted with everything on her mind. Her inner person is touchy, irritable, and anxious. One of the surest signs of her life being out of order is that she even tells God what to do” Peter Scazzero, Emotionally Healthy Spirituality: It's Impossible to Be Spiritually Mature, While Remaining Emotionally Immature እግዚአብሔር መስከንን ያብዛልን! ከሰሞኑ ይህን መጽሐፍ ሳነብ ምን ያህል ሕይወቴ በሩጫ የተሞላ እንደሆነና መረጋጋት እንደሚጎድለው እያስተዋልኩ ነው። በእግዚአብሔር ሕልውና ውስጥ ሆኖ ከራስ ጋር የጸጥታ ጊዜ ማሳለፍ አስፈላጊ ነው። @Romans148
ጥቂት ፡ አንተን ፡ ቀምሶ ፡ እንደ ፡ ጠገበ ፡ ሰው መሆን ፡ የጤና ፡ አይደለም ፡ ረሃቤን ፡ ፈውሰው ዕለት ፡ ዕለት ፡ ባዶ ፡ ትሁንና ፡ ነፍሴ በመገኘትህ ፡ ውስጥ ፡ ይረስርስ ፡ መንፈሴ... ናና ፡ እስኪ ፡ አጠጣኝ ናና ፡ እስኪ ፡ አጉርሰኝ የእጅህን ፡ ሳይሆን ፡ ክብር ፡ መልክህን የምድሩን ፡ ሳይሆን ፡ ሕልውናህን ሌላውን ፡ ሳይሆን ፡ አንተው ፡ እራስህን @Romans148