tgindex
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)

ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)

Статистика

ይህ የጳውሎስ ፈቃዱ አገልግሎት ሲሆን፣ አብያተ ክርስቲያናትና ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕውቀት እንዲጎለብቱ መትጋትን በዓላማነት አንግቧል። youtube.com/PaulosFekadu fb.com/PaulsPulpit/

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Видео
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
7 598
+5 за 5 дн.
Сутки
+4
+0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
4 565
21 постов
Вовлечённость
60,1%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 21
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
749
1/48двое суток
858
1/72трое суток
925

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • 8 авг.2 428538

    የወደድሁትና የተማርሁበት ውይይት። https://youtu.be/g0Jzf0Ijs-I?is=vmC1FaHw2-s65BvH

  • 2 авг.3 7659228

    የአዲስ ኪዳን ምሁር በሆነችው ሶፋኒት ታመነ (ዶ/ር) የተቋቋመ የነገረ መለኮት በኣንላየን መቶ በመቶ ትምህርቱ በኣንላየን ነው። በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ! ለበለጠ መረጃ ቴሌግራሙን ይቀላቀሉ:- https://t.me/TyrannusCentreforTheology

  • 28 июл.4 49910835

    ካለፈው የቀጠለ ጌታ ኢየሱስ እንዴት የአዳም ኀጢአት ሳይተላለፍበት ቀረ? ጌታ ኢየሱስ ከእናቱ ከቅድስት ማርያም የሰውነትን ባሕርይ ተካፍሏል፤ የቱም ልጅ ከእናቱ የሚወስደውን ሁሉ እርሱም ከእናቱ ወስዷል። ከሰዎች ጋራ ሥጋና ደምን ተካፍሏል፤ በእናቱ በኩል ተዛምዶናል። ስለዚህም በሰውነቱ ከሰውነት ባሕርይ አንዳችም ያልጎደለው ምሉእ ሰው ነው። (ከመለኮትነት አንዳችም ያልጎደለው ምሉእ አምላክ መሆኑ እንደ ተጠበቀ ሆኖ።) በበርካታ ጥንታውያን ጽሑፎች ውስጥ ከድንግል ማርያም ሥጋና ነፍስ መንሣቱ የተጠቀሰው ይህንኑ ለማለት ነው። ከሥጋዋ ሥጋ ብቻ ሳይሆን፣ ከነፍሷ ነፍስ መንሣቱ የሚነገርበትን ዐውድ እዚህ ላይ ማንሣቱ ጠቃሚ ነው። የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ከተጋፈጠቻቸው ኑፋቄዎች መካከል አንዱ አቡሊናርዮሳስ (Applonarius) የተባለ ሰው ሲያቀነቅነው የነበረና ጌታ ኢየሱስ መለኮታዊ ነፍስ/መንፈስ እንጂ የሰው ነፍስ/መንፈስ እንደሌለው የሚናገር ነው። እንደ አቡሊናርዮሳዊነት ከሆነ፣ ጌታ አየሱስ የሰው hardware እና የአምላክ software ነው ያለው። የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን፣ ጌታ ኢየሱስ በእናቱ በኩል የሰዎችን ሥጋና ደም ብቻ ሳይሆን ሁለንተናም መውሰዱን ለማስረገጥ ስትል፣ ሥጋና ነፍስ መንሣቱን ደጋግማ ታትት ነበር። ጌታ ኢየሱስ ከእናቱ ከማርያም ሥጋንና ነፍስን ነሥቷል የሚለውን አሳብ በቅጡ መረዳት ግን ያስፈልጋል። እርሱ የሰው ነፍስ ያለው መሆኑንን ማስረዳት ነው የተፈለገው። የቱም ፅንስ የእናቱን ሥጋም ሆነ ነፍስ ቆርሶ እንደማይወስድ ሁሉ የጌታ ኢየሱስም ጉዳይ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። የቱም ሕፃን ከእናቱ የሚወስደውን ሁሉ እርሱም ከእናቱ ወስዷል። ከዚህም የተነሣ፣ በገጽታው ወይም በመልኩ ማንን ይመስላል? ቢባል፣ እናቱንን ወይም የእናቱን ዘመዶች ይመስላል ቢባል ስህተት አይደለም። ጌታ ኢየሱስ በገጽታው የዛሬ 2ሺህ ዓመት በይሁዳና በገሊላ የሚኖሩ ሰዎችን ይመስላል ማለት ነው። ስለዚህ ነጭ ወይም ጥቁር አልነበረም። ጌታ ኢየሱስ የሰውነትን ባሕርይ ከእናቱ ከወሰደ (ወይም በሥጋና በደም ከወንድሞቹ ጋራ ከተካፈለ) ኀጢአት እንዴት ላይተላለፍበት ቻለ? መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው፣ በአዳም ኀጢአት ምክንያት ክፋት ወደ ዓለም ገብቷል። ሰዎችም የተበላሸ ባሕርይ (nature) ይዘው ስለሚወለዱ ወደ ኀጢአት የሚያዘነብሉ ናቸው። የኀጢአት ውጤት የሆነውን ሞትም ተሸክመው ነው የሚወለዱት። ከነዚህ ነገሮች የተነሣ ሰዎች ሁሉ ኀጢአትን ይሠራሉ፤ ኀጢአተኛም ይሆናሉ። የአዳም ኀጢአት ከእርሱ በኋላ የመጡትን ሰዎች ሁሉ ኀጢአት አድራጊዎች ስላደረጋቸው ሰዎች ሁሉ ኀጢአትን ያደርጋሉ። በመሆኑም በመጨረሻው ፍርድ ላይ ሁሉም በየራሱ ኀጢአት ተጠያቂ ይሆናል፤ በራሱም ኀጢአት ይፈረድበታል እንጂ በአዳም ኀጢአት ተጠያቂ የሚሆን አንድም ሰው የለም። እናም ኀጢአተኛነት ሳይሆን ኀጢአት ይወረሳል ወይም ይተላለፋል ማለት የተሻለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አገላለጽ ነው። (ዝርዝሩን ለጊዜው እንተወው።) በዚህ አግባብ ኀጢአት ከወላጅ ወደ ልጅ የሚተላለፍ ከሆነ፣ ኢየሱስ ኀጢአት እንዴት ሳይተላለፍበት ቀረ? ምርጫ 1፤ ጌታ ኢየሱስ ከአዳም ጀምሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የነበረው ኀጢአት ያልተላለፈበት እናቱ ኀጢአት ስላልነበረባት ነው። ቅድስት ማርያም በአዳም ኀጢአት ምክንያት የተፈጠረው ምስቅልቅል አንዳችም አልተላለፈባትም፤ ከፅንሰቷ ጀምሮ። Immaculate Conception ተብሎ የሚታወቀው ይህ አስተምህሮ የካቶሊክ ቤ/ክ ይፋዊ አቋም ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግን አይደለም። ምርጫ 2፤ ጌታ ኢየሱስ ኀጢአት ያልተላለፈበት ያለ ወንድ ፈቃድ (ዘር) በመፀነሱ ነው። ይህ ትንታኔ፣ ኀጢአት የሚተላለፈው በወንድ አባለ ዘር በኩል መሆኑን ታሳቢ ያደርጋል። ጌታ ኢየሱስ ደግሞ በወንድና በሴት ሩካቤ ሳይሆን፣ በተአምር የተፀነስ የሴቲቱ ዘር በመሆኑ የአዳም ኀጢአት አልተላለፈበትም። ምርጫ 3፤ ጌታ ኢየሱስ ኀጢአት ያልተላለፈበት ከድንግል ማርያም የነሣውን (የወሰደውን) ነገር መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ ስላነፃው ነው። የምሥራቅ ኦርቶዶክሳውያን እና ኦርየንታል ኦርቶዶክሳውያን (ለምሳሌ የግብፅ እና የሶርያ አብያተ ክርስቲያናት) ከማርያም የነሣውን “ሥጋና ደም” መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ የቀደሰው መሆኑን ያስረዳሉ። አንዳንዶቹ እናቲቱን አስቀድሞ ከኀጢአት እንዳነጻት ሲናገሩ፣ አንዳንዶች ደግሞ ለኢየሱስ መፀነስ አስፈላጊ የሆነውን ነገር ቀድሶ እንደ ወሰደው ይናገራሉ። (ዝርዝሮችንና ልዩነቶችን ለጊዜው እንተዋቸው።) ከዚህ ጋራ የተያያዙ አሳቦችን ለመረዳት ከፈለግን፣ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ድንግል ማርያም ኢየሱስን እንደምትፀንስ ሲያበስራት፣ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑልም ኀይል ይጸልልሻል” በማለት የተናገረውን ልብ ማለት ያስፈልገናል (ሉቃ. 1፥34-35)። ወንጌላዊ ሉቃስ በዚህ ስፍራ የተጠቀመው የግሪኩ ቃል “ኤፒስኪያሴ” (ἐπισκιάσει) የሚል ሲሆን፣ ሥሩ “ኤፒስኪያዞ” (ἐπισκιάζω) ነው። ይህ ቃል ሁለት ትርጕሞች አሉት። የመጀመሪያው መጋረድንና መሸፈንን ሲጠቍም፣ ይህም በተለይ ሰዎችን በብሩህ ደመና ወይም ብርሃን ዙሪያቸውን መክበብና መጠቅለልን ያሳያል። ድርጊቱ መለኮታዊ ተግባር አለው። በዚህም የእግዚአብሔርን ሀልዎት ያመለክታል። ጌታ ኢየሱስ በተራራ ላይ ለደቀ መዛሙርቱ በተገለጠላቸው ጊዜ ብሩህ ደመና እንደ ጋረዳቸው ወንጌላቱ ሲነግሩን ይህንኑ ቃል ተጠቅመዋል (ማቴ. 17፥5፤ ሉቃ. 9፥34፤ ማር. 9፥7)። ሁለተኛው ትርጕም ደግሞ በአንድ ነገር ላይ ጥላ ማሳረፍን ያሳያል። ሐዋርያው ጴጥሮስ በሚያልፍበት መንገድ ላይ ሕመምተኞችን የሚያስቀምጡ ሰዎች ነበሩ። ይህንም የሚያደርጉት የእርሱ ጥላ እንዲያርፍባቸው ሲሆን፣ ይህም የተዘገበው በዚሁ ቃል ነው (የሐዋ. 5፥15)። የማደሪያው ድንኳን የእግዚአብሔርን በዚያ ስፍራ መገኘት በሚገልጠው የክብሩ ዳመና (“ሸኺና”) መሞላቱን በሚያመለክት መልኩ የግሪክኛው ብሉይ ኪዳን (ሰብዓ ሊቃናት) ይህን ቃል በዘፀ. 40፥35 ላይ ተጠቅሞታል። የአማርኛ ትርጉሞች የተጠቀሙት “ጸለለ” የሚለው ቃል ከግዕዝ የተወሰደ ሲሆን፣ “በላይ ሁኖ ማጥላት፣ ጥላ መሆን፣ ማልበስ፣ መክደን፣ መሸፈን፣ መከለል፣ መጋረድ፣ ማጨለም” የሚል ትርጕም አለው። ድንግል ማርያም ኢየሱስን ትፀንስ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንደ ጋረዳት ከዚህ በመነሣት መረዳት ይቻላል። በዚህ ጊዜ የተሠራ ተአምር መኖሩ ግልጽ ነው። እናም በዚህ የፅንሰት ሂደት ውስጥ ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፈው ኀጢአት ነክ ነገር እንዳይተላለፍ፣ እግዚአብሔር በኀይሉ ጋርዶ ወይም ከልሎ እንዳስቀረ መረዳት የሚቻል ይመስለኛል። ምርጫ 4፤ ጌታ ኢየሱስ ኀጢአት ያልተላለፈበትን ምክንያት አናውቀውም። እኛ መረዳት በማንችለው መንገድ እግዚአብሔር ኢየሱስ ኀጢአት ሳይተላለፍበት እንዲፀነስ አድርጎታል። በዚህም ሆነ በዚያ ግን፣ ጌታ ኢየሱስ ከኀጢአት ነጻ መሆኑን ለማስረዳት ሲባል ከድንግል ማርያም የሰው-ነትን ባሕርይ እንዳልወሰደ መናገር ሙልጭ ያለ ስሕተት ነው። የቅዱስ መጽሐፍም፣ የቅዱስ ትውፊትም፣ የአመክንዮም ድጋፍ የለውም። “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፣ እርሱ ደግሞ … በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። … የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም። ስለዚህ የሕዝብን ኀጢአት ለማስተስረይ፣ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፣ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።” (2፥14፡17)

  • 27 июл.3 345215

    የቅዱሳት መጻሕፍት ግብ የቱ ነው? 1) ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት እንደሚቆም ማስረዳት? ወይስ 2) እግዚአብሔር በፍጥረቱ መካከል እንዴት እንደሚኖር ማስረዳት? https://www.facebook.com/PaulsPulpit/posts/pfbid0gukcWzsZrXXTdPPa3oScQaUAGBiCe6Wo87moLcZ87cvJU8kNgYLX5BBoFw2j9Vdql

  • 23 июл.4 88210432

    ተሳስቼ አውቃለሁ። ጉዳዩ 20 ዓመታት ዐልፈዉታል። በMaxwell Whyte የተጻፈ “The Power of the Blood” የሚል መጽሐፍ ድሮ አንብቤ ነበር። የመጀመሪያው ምዕራፍ ጌታ ኢየሱስ ደሙን ከእናቱ እንዳላገኘው እና ከሰማይ ያመጣው መሆኑን የሚናገር እንደ ነበር አስታውሳለሁ። አዲስ ነገር ይማርካል አይደል? በዚህም ላይ ትምህርተ ድነትንም የተማርሁት ኢየሱስ ሥጋና ደም ከማርያም እንዳልነሣ በሚያስረዳ መልኩ ነበር። ስለዚህ ያን ምዕራፍ ወደ አማርኛ አመጣሁትና የአዲስ አበባ ሙሉ ወንጌል ልሳን በሆነው “ቀንዲል” የተሰኘ መጽሔት ላይ እንዲታተም ሰጠሁ። “ደም - የሕይወት ሕይወት” የሚል ርዕስ ተሰጥቶት ታተመ። ከብዙ ዓመታት በኋላ “ያልተንኳኩ በሮች”ን ላሳትም ስንቀሳቀስ በሰበስብኳቸው ጽሑፎች ውስጥ ያን ጽሑፍ አካትቼው ነበር። ረቂቁን አስቀድሜ ከሰጠኋቸው ሰዎች መካከል የቀንዲል መጽሔት አዘጋጅ የነበረው ወንድም አንዱ ነበር። በመካከል በነበሩት ዓመታት ውስጥ ጥቂት የነገረ መለኮት ትምህርት ቀስሞ ስለ ነበር ጽሑፉ ትክክል ላይሆን እንደሚችል ነገረኝ። መጋቢ በቀለ ወ/ኪዳን እና ዘማሪ ገዛኸኝ ሙሴም አስቀድመው ረቂቁን ሲያነብቡ ያንኑ አጸኑልኝ። ያን ጽሑፍ ነጥዬ አወጣሁና ለተስፋዬ ሮበሌ እና ለተስፋሁን ኀጢያ ሰጠኋቸው። የሁሉም አቋም አንድ ነበር። እናም ጽሑፉን በመጽሐፌ ሳላካትተው ሳላካትተው ቀረሁ። (የታተመው በ2000 ዓ.ም. ነው።) ከዚያማ እኔም የነገረ ክርስቶስ መጻሕፍት ንባብ ውስጥ ገባሁ። የነገረ መለኮት ሥልጠናም ጀመርሁ። የቤተ ክርስቲያንን ታሪክም አጠናሁ። እነዚህም ወደ ርቱዕ አስተምህሮ አመጡኝ። በዚያ ብቻ ግን አላበቃሁም። የድነት ትምህርት ያስተማረኝን ሰው በብዙ ውይይት አቋሙን አስቀየርሁት። የነገረ መለኮት ጽሑፎችን ማዘጋጀት ገና ሳልጀምር በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማንሣት አገልጋዮች በልከኛ የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜና በልከኛ ትውፊት መሠረት አቋማቸውን ዳግም እንዲያጤኑ የማድረግ ጥቂት የማይባሉ ዕድሎችን አግኝቻለሁ። ይህን ስል ግን ወንጌላውያን ክርስቲያኖች በሙሉ ጌታ ኢየሱስ የሰውነትን ባሕርይ ከእናቱ እንዳላገኘ ወይም የትኛውም ጽንስ ከእናቱ የሚወስደውን ነገር ጌታችን ከእናቱ እንዳልወሰደ ያስባሉ ማለት አይደለም። ይህ ጨርሶ ከእውነት የራቀ ነው። ቀላል ማስረጃ ላቅርብ። ታምራት ኀይሌ ቁጥር 7 የመዝሙር ሰንዱቁን ያወጣው መቼ ነበር? በዚያ ሰንዱቅ ውስጥ “ታሪኬ የጀመረው” የሚል መዝሙር አለ። እዚያ ውስጥ፣ “ከወህኒ ከፍርድ እኔኑ ሊያወጣ፣ ከድንግል ማርያም ሥጋ ነስቶ መጣ” የሚሉ ስንኞችን ይዟል። (ያን ጊዜ ዶክትሪን እንዘምር ነበር፤ አይገርምም?) በሌላ በኩል ግን ይህ ጉዳይ በቀላሉ የማይዋጥላቸው ወንጌላውያን ክርስቲያኖች እንደ ነበሩ መናገር እችላለሁ። ለምን? የወንጌላውያኑ አብዛኛው ተዋስኦ ከኦርቶዶክሳውያን ጋራ እንደ ሆነ ይታወቃል። “ማርያም ታማልዳለች ወይስ አታማልድም?” የሚል ዕውቅ ሙግት ለዚህ ዐይነተኛ ማሳያ መሆን ይችላል። እናም በዚህ ውይይት ወይም ንትርክ መካከል “በመስቀል ላይ የተሰቀለው የማርያም ሥጋ፣ የፈሰሰውም የእርሷ ደም ነው” የሚል ንግግር በተወሰኑ ኦርቶዶክሳውያን እንደሚዘወተር መናገር ይቻላል። ስለዚህ፣ ጭራሹኑ ከእናቱ ምንም አልወሰደም ብሎ በርን ጥርቅም አድርጎ መዝጋት ለዚህ በመፍትሔነት የተመረጠ ይመስላል። ሁለቱም አሳቦች ግን የቅዱሳት መጻሕፍትም፣ የትውፊትም፣ የአመክንዮም ድጋፍ የላቸውም። የእኔ ሥጋ፣ የእኔ እንጂ የእናቴ አይደለም፤ የእኔም ደም፣ የእኔ እንጂ የእናቴ አይደለም። የኢየሱስም ደም የእርሱ እንጂ የእናቱ አይደለም። እንደዚያ ከሆነ፣ የእርሷም ሥጋና ደም የእናቷ እንጂ የእርሷ አይሆንም። የእናቷም ... እያልን አዳምና ሔዋን ዘንድ መድረሳችን ነው። እናም የጌታችን ሥጋና ደም የእርሱ እንጂ የማንም አይደለም። ቅዱሳት መጻሕፍትም ትውፊትም ይህን ትምህርት ያጸናሉ። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ጌታ ኢየሱስ ከሰው-ነት አንዳችም ነገር ያልጎደለው ምሉዕ ሰው ነው። የቱም ሕፃን ከእናቱ የሚያገኘውን ነገር ሁሉ እርሱም ከእናቱ ወስዷል። የሰው-ነትን ባሕርይ ከእርሷ ተካፍሏል። የተዛመደንም በእርሷ በኩል ነው። ከዚህ በቀር ጌታ ኢየሱስ ከሰማይ ያመጣው ሥጋና ደም የለውም፤ እንዲያ ከሆነ ግን እርሱ ሰው አይደለም። ምናልባትም በሰማይ ያሉ ሌሎች ፍጡራንን እንጂ እኛን የአዳም ልጆችን ሊወክለን አይችልም። እኛን ወክሎ ጽድቅን ሊፈጽምም ሊሞትልንም አይችልም። ስለዚህም በእርሱ ማንነትና ሥራ ድነትን አናገኝም። በሌላ በኩል ደግሞ ወንጌላውያንን ከላይ ያነሣነው አሳብ ቀልባቸውን የሚወስደው ኀጢአት በሥጋና በደም እንደሚተላለፍ የማሰብ ዝንባሌ በመኖሩ ነው። ይህን ደግሞ ምናልባት ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን። https://www.facebook.com/PaulsPulpit/posts/pfbid0SkGjtMZKTfu1FKerd3DPTLPihrpjFZ2r7kwbN4t184KDF6Ve1Ai6DoQYtVQHkdGol

  • 18 июл.4 5324315

    አሁንም፤ ከባለፈው የቀጠለ ነው። የእግዚአብሔር ትልቁ ዓላማ ፍጥረቱን ሁሉ በመሲሑ በኩል መዋጀት ሲሆን፣ ለዚህ ክቡር ዓላማው የመረጣቸው ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች ምን ዐይነት ሰዎች እንደሚሆኑ ከመወለዳቸውም በፊት ያውቃል። የት ድረስ እንደሚጸኑ፣ የት ድረስ እንደሚወድቁ ያውቃል። እግዚአብሔር ሲመርጣቸው ቅድመ ዕውቀቱን ተጠቅሟል? ወይስ አልተጠቀመም ብሎ መሟገት ግን ይቻላል። (በዚህ ቦታ የምናነሣው ምርጫ ከድነት ጋራ የሚያያዝ አይደለም።) እግዚአብሔር ለዚህ ክቡርና ታላቅ ዓላማው ሰዎችን ሲመርጥ፣ ስለ ሰዎቹ ያለውን ዕውቀት ከግምት ሳያስገባ በዘፈቀደ እንደ መረጣቸው የሚያስቡ ሰዎች አሉ። በተቃራኒው ደግሞ፣ እግዚአብሔር ስለሚመርጣቸው ሰዎች ቅድመ ዕውቀቱን ተጠቅሟል የሚሉ አሉ። ክቡሩን ዓላማውን ለመሸከም ያልመረጣቸው ሰዎች አሉ፤ ዓላማውን እንዲሸከሙ የመረጣቸውም አሉ። ለመረጣቸው ግን ጸጋውን ይሰጣቸዋል። ያዕቆብና ኤሳው ለዚህ ምሳሌ መሆን ይችላሉ። እግዚአብሔር ሆን ብሎ አስቦና አቅዶ ነው የመረጣቸው። ውድቀታቸውንም፣ ብርታታቸውንም ለዓላማው ይጠቀምበታል በማለት ማሰብም ይቻላል። እኔም ይህን እያልሁ ነው። ስለ ምርጫ ሲነሣ፣ ብዙዎች ምርጫ ሁሉ ለድነት እንደሚመስላቸው እየታዘብሁ ነው። ይህን ያልተቀበለ ሰውም ከስም ልጠፋ (labling) አያመልጥም። ምን ማለት ይቻላል? እግዚአብሔር ለመሲሑ መምጣት መንገድ ሲያበጃጅ ከመረጣቸው ሰዎች አንዱ ቂሮስ ነበር። “እግዚአብሔር ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል። በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፥ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ፤ በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ። ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፥ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ በቍልምጫ ስምህ ጠራሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም።” (ኢሳ. 45፥1-4) ቂሮስ በእግዚአብሔር የተመረጠው፣ የተቀባው፣ የተጠራው ለድነት ስለ መሆኑ ምንባቡ አይናገርም። እንዲያውም “አንተ ግን አላወቅኸኝም” ነው የሚለው። “ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፥ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ ጠርቼሃለሁ” በማለት ቂሮስ ለምን እንደ ተመረጠ እግዚአብሔር በግልጽ አስቀምጧል። እስራኤል ደግሞ ለመሲሑ መምጫ እግዚአብሔር ያሰባትና የተጠቀመባት መሆኗ ያስማማናል። እግዚአብሔር በመጀመሪያ መጨረሻውን ያውቃል። የሚያውቀውንም ለዓላማውና ለሥራው ይጠቀምበታል። ለመረጣቸው ሰዎች ጸጋውንም ይሰጣል። ይህም ሆኖ ግን የተመረጡት ሰዎች ሊወድቁ ይችላሉ። ሳዖል የእግዚአብሔር ምርጫ ነው፤ ወድቋል። ሳዖል የራሱ ብርታትም ድክመትም ያለው ሰው ነበር። የእርሱ መውደቅ ግን ለእግዚአብሔር ያልታሰበና ያልታወቀ ጉዳይ አልነበረም። አስቀድሞም ያውቀዋል። ለዓላማው (ዳዊትን ለማሠልጠን) ተጠቅሞበታል። እግዚአብሔር የታሪክ ባለቤት ነውና በዓለም ላይ የሚካሄዱትን ነገሮች አስቀድሞ ያውቃል፤ ለዓላማውም ይጠቀምባቸዋል። የሆነ ነገር ሲከሠት፣ ድንገተኛ ነገር ሆኖበት ለማስተካከል መፍትሔ ፍለጋ የሚንቀሳቀስ አምላክ አይደለም። ቢበቃኝ የሚሻል ይመስለኛል። https://www.facebook.com/PaulsPulpit/posts/pfbid0eSaCSUjpgs8M45qpcAoKdK3WhvMU4qwBMSV7YRXrBKSm9CZiHXQDdSjEERRHxqZ5l

  • 16 июл.4 2034517

    ካለፈው የቀጠለ ... እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው። እያንዳንዳችን ምን ዐይነት ሰው እንደምንሆን ለማወቅ እስክንወለድና ሥራችንን እስክንከውን መቆየት አያስፈልገውም። እግዚአብሔር አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን ... መርጧል። እስማኤልንና ኤሳውን ግን አልመረጠም። በሁለቱም ጎራ ያሉ ሰዎች ምን ዐይነት ሰዎች እንደሚሆኑ ግን አስቀድሞም ያውቅ ነበር። እግዚአብሔር መሲሑን ልኮ ፍጥረቱን የመቤዠት ዓላማው ዓለም ሳይፈጠርም የነበረ ነው። ለአዳምና ለሔዋንም ይህን ቃል ገብቶላቸዋል። ስለዚህ መሲሑ ለእግዚአብሔር “2ኛ ዕቅድ” (Plan B) አይደለም። እስራኤል እንደማትወድቅ ገምቶ፣ ስትወድቅበት መሲሑን ወደ ማምጣት አልሄደም። እስራኤል የት ድረስ እንደምትጓዝ አስቀድሞም ያውቃል። አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ ... በሚል የጀመረው ጉዞ እስራኤልን ቢያስገኝም እንኳ እስራኤል እንደምትወድቅ እግዚአብሔር አስቀድሞም ያውቃል። እግዚአብሔር መሲሁን የማምጣት ዕቅዱን እንዲሁ በዘፈቀደ ያካሄደው አይደለም። የተመረጡትም ሰዎች በአጋጣሚ የተገኙ አልነበሩም። ሆን ብሎ ነው የመረጣቸው። እግዚአብሔር አስቦ፣ አቅዶ፣ አውቆ ነው ሰዎችን ለዓላማውና ለክቡር ኀላፊነት የሚመርጠው። የሚመርጣቸው ሰዎች የት ድረስ ኀላፊነቱን እንደሚሸከሙና ዓላማውን እንደሚፈጽሙ፣ የቱጋ ደግሞ እንደሚደናቀፉና እንደሚወድቁ ያውቃል። ያንም ለዓላማው ይጠቀምበታል። ይህም ሆኖ ግን እግዚአብሔር በማንም ችሎታና ብቃት ላይ አይታመንም። ለመረጣቸው ሰዎች ሁሉ ጸጋውን ሰጥቷቸዋል፤ በጸጋው ደግፏቸዋል፤ በጸጋው አስችሏቸዋል። እንዲህም ሆኖ ግን የተመረጡቱ ሊወድቁ ይችላሉ። ጸጋ ስለጎደላቸው ሳይሆን፣ ጸጋውን መግፋት ስለሚችሉ። ሳኦል በእግዚአብሔር የተመረጠ ንጉሥ ነበር፤ ነገር ግን ወድቋል። እስራኤል በእግዚአብሔር የተመረጠች ናት፤ ሆኖም ወድቃለች። ማሳሰቢያ፤ ይህ ጉዳይ ድነትን የሚመለከት አይደለም። ለመሲሑ መመጣት እግዚአብሔር የሠራበትን መንገድ የሚመለከት ብቻ እንጂ! https://www.facebook.com/PaulsPulpit/posts/pfbid029inkBVb59yFcUq4MB56TYBD4TVaqQy5iDXWgFbydDrkLNY49Fiw3f5ihvXqJs4s5l

  • 11 июл.5 3065613

    ያዕቆብና ኤሳው ገና ሳይወለዱ፣ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ እግዚአብሔር ከሁለቱ አንዱን ለትልቅ ዓላማና ኀላፊነት መምረጡ ምን ይደንቃል? ያዕቆብ ወይም ዔሳው ምን ዐይነት ሰዎች እንደ ሆኑ፣ ለተመረጡበት ግብና ተልዕኮ ኀላፊነት ብቁ ይሁኑ አይሁኑ እግዚአብሔር ማወቅ የሚችለው ከተወለዱ በኋላ ነውን? ኀላፊነት ለመሸከም መቻላቸውን ለማወቅ በጎ ወይም ክፉ ሲያደርጉ ማየት ያስፈልገዋልን? ሰዎቹ ሲወለዱና ሲያድጉ ምን ምን ዐይነት ሰዎች እንደሚሆኑ እግዚአብሔር አስቀድሞም ያውቅ ነበር። ወገኖች፤ ይህ አሳብ ስለ ድነት አይደለም https://www.facebook.com/PaulsPulpit/posts/pfbid0DvmBMbSwrDha8ujD3WQ9nkTAyZKPbxT2WqZ7KSRjMc2WFMLsKLoBGryBZ7KaRQR4l

  • 9 июл.5 159182

    https://www.youtube.com/watch?v=xjsM81lIEg0

  • 5 июл.5 795113

    https://www.missuniversegb.co.uk/finalists

  • 5 июл.5 664131

    без подписи

  • 5 июл.5 026131

    без подписи

  • 5 июл.4 686412

    без подписи

  • 5 июл.3 529101

    ይህች ክርስቲያን እኅታችን ሐኪም ለመሆን ሕልም ያላት ወጣት ናት። አሁን ግን አንድ ውድድር ላይ ናት፤ ሚስ ዩኒቨርስ። ሊያግዟት፣ ሊደግፏት የሚሹ ሁሉ ድምፅ እንዲሰጧት ትፈልጋለች። እናም የዩናይትድ ኪንግደም ነዋሪ ከሆናችሁ እባካችሁ ደግፏት።

  • 1 июл.5 241543из melkampodcast

    🎧 1ኛ ጴጥሮስ 2፥1-3 ላይ ጌታ መልካም መሆኑን የቀመሱ ሁሉ፣ እኩዩን በመተው እግዚአብሔርን ወደ መምሰል የሚያደርሰውን ፈለግ እንዲከተሉ ሐዋርያው ምክሩን ይሰጣል። 👉 “መልካም ፖድካስት” ስያሜውን የወሰደው ከዚሁ ቅዱስ ቃል መነሻነት ነው። የፖድካስት ዝግጅቱ፣ ተስፋን የሚሰጥ፣ እምነት እና ዕውቀትን የሚጨምር እንዲሆን የተቃኘ ነው። 🌟 ታሪካዊ እና ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጕዳዮች፣ ስለ እግዚአብሔር እና ሥራዎቹ፣ ስለ ትውልዱ እና ዘመኑ እንዲሁም የክርስትና ሕይወት መንገድን የሚመለከቱ ርእሰ ጕዳዮች የሚዳሰሱበት ሳምንታዊ ዝግጅት ነው። 🌟 እንግዶች ሆነው የሚቀርቡ ተጋባዦች፣ በየትኛውም የሙያ ዘርፍ እና የሕይወት ጐዳና ላይ ያሉ አማኞች ሲሆኑ፣ ክርስትናን በሕይወታቸው እንዴት እንደተረዱትና እንደሚኖሩት የሚያካፍሉበት፣ እግዚአብሔር በሕይወታቸው የሠራውን መልካሙን ሥራ የሚመሰክሩበት መድረክ ጭምር ነው። 🔖 የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ አገልግሎታችንን ይደግፉ፤ ለሌሎች ያጋሩ፤ የማኅበራዊ ድረ ገጾቻችንን ይከታተሉ። https://linktr.ee/melkampodcast እናመሰግናለን!🙏 #melkampodcast #new #comingsoon #መልካም #christianpodcast #discipleship

  • 22 июн.5 780556

    ሰላም ወገኖች፤ ጸዴ ፖድካስት እየመጣ ነው። ሰብስክራይብ እያደረግን ብንጠብቅስ? https://youtu.be/joB4VqBj9Wk?si=5QOPVBkRLGJH3bq8

  • 20 июн.5 389439

    https://youtu.be/JMUJKtUA3w0?is=3UB6c8BhfebEt7ks

  • 18 июн.5 2401027

    እግዚአብሔር እንደ ወደደ ጸጋን ይሰጣል፤ ቤተ ክርስቲያን ይህን ተከትላ ዕውቅናን ትሰጣለች። ይህን ጤናማ አሠራር ማየት የሆነ ደስ የሚል ስሜት አለው። አብሮ አደጌን እና የአባቴን የአገልግሎት ፍሬ ምሕረትን፣ እንዲሁም ኬሊን እዚህ ውስጥ በማየቴ እጅግ ደስ ብሎኛል። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!

  • 10 июн.5 9875210

    ከዚሁ የወንጌል ስብከት እና መንፈሳዊ አገልግሎት ጋራ በተያያዘ የተአምር ያህል የምቆጥረው ክስተት አለ፤ ለየት ያለና ያልተደገመ ስለሆነ ትላንት የሆነ ያህል ትዝ ይለኛል። አንዲት ወጣት ሴት በጣም ትታመማለች። አዘውትረን ከምናውቀው የተለየና እንደ አእምሮ መታወክ ያለ ሕመም ነው። ሁኔታዋ ልቤን ስለ ነካኝ ከፊቷ ተንበርክኬ ጥልቅ በሆነ ተመስጦ ለሰዓታት ጸለይሁላት። በወቅቱ የነበረኝ የልብ ንጽሕና፣ የዋሕነት እና ጽኑ መንፈሳዊነት ይሁን አላውቅም ጸሎቴ ተሰማ። ልጅቷ ለወራት ስትሠቃይ እንዳልነበር በዚያ ቀን ተፈወሰችና አእምሮዋ ተመለሰላት። ይህን ‘ተአምራዊ ፈውስ’ እንደ መጀመሪያ መንፈሳዊ ተግባሬ አድርጌ መውሰድ እችል እንደሆን እንጃ። በዚያ የልጅነት ጊዜዬ ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ውስጥ “በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር፤ [ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ...] ሁሉም በእርሱ ሆነ ...” ለሚለው ክፍል የተለየ ፍቅር ነበረኝ። ሌንጮ ለታ፤ ትግል ሕይወቱ፤ ገጽ 35። ከዚሁ የወንጌል ስብከት እና መንፈሳዊ አገልግሎት ጋራ... - ምስባከ ጳውሎስ - Paul's Pulpit | Facebook