URIM | ኡሪም
Статистикаለሞተልን መኖር | ብርሀንን ማብራት | ለምፅአት መዘጋጀት 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:15 ¹⁵ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። ሁሉን ለወንጌል ብቻ በልባችን እርሱ ያስብ በአንደበታችን እርሱ ያውራ። Creator- @Kaleabkasaye
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 12
- Всего постов
- 26
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Instagram (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 107
- 1/48двое суток
- 122
- 1/72трое суток
- 132
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በፀጋው ትናንት አለፈ! በፀጋው ዛሬን እንኖራለን! በፀጋው ነገን ተስፋ እናደርጋለን። ከእኛ የሆነ የኛ የምንለው አንዳች የለንም። የፀጋው ባለቤት ይመስገን! @Urim7
#ካነበብኩት ትጋት የተስፋ ልጅ ናት። ተስፋ ደግሞ በእኛና በፈጣሪ መካከል የእምነት ድልድይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ነውና! ዛፍ ቢቆረጥ ደግሞ ያቆጠቁጥ ዘንድ ቅርንጫፉም እንዳያልቅ ተስፋ አለው እንዲል መፅሀፍ። በዚህ አለም ከላይ ስንደርስ ታች የነበርንበት ከንቱ ይሆናል የጨበጥነውን እንረግጣለን ክብር የሰጠነውን እናዋርዳለን ከዚህ በላይ የለም ያልነውን ተራ ነገር እናደርገዋለን! አለሙ እንደዚሁ ነው። ንፋስ እንደመከተል ነው የሚያረካ የሚያስደስት ምንም ነገር የለም። የምቾት ችግሩ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ መመለስን አለመፍቀዱ፣ ወደ ላይ እንጂ ወደ ታች መውረድን አለመፈለጉ ነው። ምቾት ጥሩ ቢሆንም ከደረጃ ላለመውረድ የሚያስከትለው ትግል በራሱ ጭንቀት ፈጥሮ ቆይቶ ምቾትን መልሶ መንሳቱ አይቀርም። በምቾት ውስጥ ምቾት የለም! ሰበዝ- ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ @Urim7
አምልኮ የሚገባው በዙፋኑ ላይ አለ ችዬ እንዴት ዝም እላለሁ እስትንፋሴ እያለ መዝሙሬ የሚገባው በዙፋኑ ላይ አለ ችዬ እንዴት ዝም እላለሁ እስትንፋሴ እያለ መወደድ የሚገባው በዙፋኑ ላይ አለ ችዬ እንዴት ዝም እላለሁ እስትንፋሴ እያለ @Urim7
#ከተማርኩት_ የብሉይ_ኪዳን_ዳሰሳ መግቢያ- ሜሶጶጦሚያ Messo + Potomey = Between two rivers- በሁለት ወንዞች መሀከል። አሁናዊ መገኛው- የፋርስ ባህረ ሰላጤ አከባቢ የሚጀምር( The pursian Gulf) አከባቢ ማለት ነው። እነዚህ ወንዞች #ጤግሮስ እና #ኤፍራጠስ ይሰኛሉ። ኤደን የምትባለዋ ቦታ- በጤግሮስ እና በኤፍራጠስ መሀከል የምትገኝ ቦታ ናት። ይህም የኤደን ገነት መገኛ በዚያ ስፍራ እንደነበር የመፅሀፍ ቅዱስ አጥኚዎች ይስማሙበታል። አብረሀምም በዘመኑ ከዑር ውጣ የተባለው ከዚህ አከባቢ ነው ከ ሜሰጶጦሚያ ከተባለ አከባቢ ማለት ነው። ከሰው ልጅ መፈጠር እንዲሁም ከኤደን ገነት መውጣት ቡሀላ የሰው ዘር የተሰበሰበበት ቦታ ይህ ስፍራ ነው። የባቢሎንም ግንብ የነበረው በዚህ ስፍራ ነው እንዲሁም እነ ዳንኤል በምርኮ የተወሰዱበት አለፍ ሲልም በነ አስቴር ዘመን መፅሀፍ ቅዱስ ፋርስ እያለ የሚነግረን ስፍራ ይህ ነው። ሁሉም ከላይ የጠቀስናቸው ሀገራት የሚገኙት በጤግሮስ እና በኤፍራጠስ መሀል ባለ ሜሶጶጦሚያ በሚባል ስፍራ ነው። የሰው ዘር ለረጅም ዘመናት የኖረው በጥንታዊ በሆኑ ኢራቅ፣ ሶርያ፣ ካታር አከባቢ ነው። በእርግጥ በጊዜው የነበሩ ዝርያዎች አይደሉም አሁንም በዚያ ያሉት። በሜሶጶጦሚያ ከነበሩ ስልጣኔዎች መሀከል የሚጠቀሱት #ሱሜራውያን #አኬዳዊያን #ሂታዊያን #ባቢሎናዊያን #አሶራዊያን ይገኙበታል። አስተውሎት: አብረሀም የኖረው በዚሁ ስፍራ በዚሁ ዘመን ሲሆን የስልጣኔ መጀመርያዎች የነበረበት ወቅት ነው። በዚህም የሱሜራዊያን ስልጣኔ እንደ ስእል፣ ጌጥ፣ መስኖ፣ ሸክላ፣ ሰረገላዎች፣ የእንጨት ጎማዎች፣ ሽመና ( የጨርቃ ጨርቅ ስራ ) ፣ የጡብ ግንቦች፣ የብረታ ብረት እቃዎች ፣ የሂሳብ ቀመር ( መደመር፣ መቀነስ) የመሳሰሉትን ስራዎች ይሰሩ ነበር። ይህ ሁሉ በ Archaeology የተረጋገጠ ነው። ባቢሎን ማለት ድብልቅልቅ ማለት ሲሆን የባቢሎን የመጀመርያው መስራች ናምሩድ ተብሎ ይታወቃል። ይህም ሰው እጅግ ግዙፍ እንደነበር ይታመናል። የመጀመርያው የባቢሎን ንጉስ ሀሙራቢ ተብሎ ይታወቃል። ይህ ንጉስ ህግ የቀረፀ የሀሙራቢ ህግ ተብሎ በታሪክ የሚነገርለት እጅግ ገናና ንጉስ ነበር። በ Video ማስረጃ ለማየት- LINK ከባቢሎን ጣኦታት መሀከል በጥቂቱ #ተሙዝ #ባኦል #አስታሮት የመሳሰሉት ይገኙበታል። በመፅሀፍ ቅዱሳችንም የእስራኤል ህዝብ የሚሸወድባቸው አማልክት እነዚህ ነበሩ። ተሳትፎአቹ ይታይና እንቀጥላለን😊 @Urim7
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
እውነቱን ለመናገር ብዙ ነገር ጀምሮ የመጨረስ ልማድ እያጣሁ ነው። ይህንን የብሉይ ኪዳን ዳሰሳ ለብዙ ጊዜ ቢያንስ ከ 5ት ጊዜ በላይ በተደጋጋሚ ጀምሬዋለው ግን አንዴም አልጨረስኩትም😯። በዚህኛው ዙር ግን ለመጨረስ ቆርጬ ተነስቻለው ፀጋው ይረዳኛል😊 እናም በተቻለኝ መጠን ደግሞ የተማርኩትን በዚህ ለማጋራት እጥራለው። #ከተማርኩት በተሰኘ ፅሁፍ በየጊዜው የተማርኩትን ብታውቁት የምለውን የማጋራቹ ይሆናል። ከቻላቹ አብራችሁኝ እንድትጀምሩ ከታች የ Youtube Link አስቀምጣለው። ካልሆነም በዚህ የምለቀውን ፅሁፍ መከታተል ትችላላቹ። መማር የምትፈልጉ በዚህ በኩል መማር ትችላላቹ- Asfaw Bekele በተረፈው ግን በተቻላቹ መጠን ለሌሎች በማጋራት ሌሎችንም ብንጠቅም ደስ ይለኛል ፀጋ ይብዛላቹ። @Urim7
видео или голосовое, без подписи
#Advertisment እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! ✨✨ የሥነ መለኮት ትምህርት መማር ፈልገው በጊዜና በቦታ እጦት ለተገደቡ ሁሉ ታላቅ የምስራች! "ሰላም ለዓለም የሥነ-መለኮትና ሚሽን ኮሌጅ" ተደራሽነቱን በማስፋት ሙሉ በሙሉ በዲጂታል (ኦንላይን) መማር የሚያስችል አዲስ ምዝገባ ከፍቷል። ✅ የምንሰጣቸው ፕሮግራሞች፦ · ዲፕሎማ · ዲግሪ · ማስተርስ ✅ የዲፓርትመንት አማራጮች፦ · ስነ-መለኮት (Theology) · ሚሽን (Missiology) 📍 ለምን እኛን ይመርጣሉ? · ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውንስል እውቅና የተሰጠው። · በስልክ ወይም በኮምፒውተር 24/7 ማጥናት የሚቻልበት አመቺ ስርዓት። 📝 የምዝገባ ሂደት፦ የትምህርት ማስረጃዎን ፎቶ በማንሳት በቴሌግራም ይላኩልን፦ 📞 096 831 3305 | 0955263368 📩 @PFW_support ወይም @PFW57 ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ @peaceforthew
ምድር በኔ ዛቢያ አትዞርም። እኔ ባልኖርም ሁሉ ይቀጥላል እኔ ከሌለው ሁሉ እንደማይኖር ነገር እንደሚያበቃ ማሰብ ምንኛ ሞኝነት ነው? ስለራስ በራስ ጉዳይ ላይ ማተኮር መቻል ምንኛ መታደል ነው? ያኛውም ውስጥ ጥልቅ ይሄኛውም ውስጥ ጥልቅ ማለት ሰዋዊ ስነምግባር አይደለም። እንደ ሰው የራሳችን ፈላጭ ቆራጭ እንጂ የሰው ፈላጭ ቆራጭ አይደለንም ሁሉም የራሱን ኑሮ እንዲኖር መተው ከብዙ አላስፈላጊ እንግልት ይገላግለናል። ሁሉን መተው ነው ሁነኛ መፍትሄው ሁሉም የራሱን ኑሮ ይኑረው እኛም የራሳችንን እንኑር። እግዚአብሔር ለሁሉም እንዳሰበው እንደ ቸርነቱ መጠን ያድርግ። ለኔስ? ለኔም እንደ ፈቃዱ ያድርግልኝ። ከሌላው አጉድሎ ለኔ የሚሰጥ አምላክ አይደለም የማመልከው ሁሉ በሁሉ ነው ለሌላው ሲሰጥ ሳይቀንስበት ለኔም ሲያደርግ ሳይጎድልበት ነውና ቸሩን እማፀናለው። እንደዚህ ማሰብ ቢበዛልን😊 @Urim7
ፖርኖርሽን የፖርኖግራፊ መርዝ፣ መዘዝ እና መድሀኒት። ይህንን ድንቅ የሆነ መፅሀፍ መግዛት የምትፈልጉ በ @MinassieYirgu በኩል ማግኘት ትችላላቹ።
እግዚአብሔር አለቴ ነው፤ መጠጊያ አምባዬ ነው፤ የመማፀኛ ከተማዬም ነው፤ መሸሸጊያ ዋሻዬም ቢሆን እርሱ ነው። በከፍታም ቢሆን በዝቅታ የሚያረጋጋኝ ነገር ቢኖር የተደገፍኩት የፀና መሆኑ ብቻ ነው። ሌላውን ተውት በዚህች ምድር ፅኑ የሚባል ምን አለ? ሁሉ ተለዋዋጭ ነው። የማይለወጥ የማይቀየር የማያረጅ ብትደገፉት የማይከዳ እግዚአብሔር ብቻ ነው። በእርግጥ ይህ ቢበዛልን ጌታን ማለት ብንችል ሌሎች መታመኛዎቻችንን ጥለን ወደ እርሱ ብንሮጥ ከስንት እንተርፋለን መሰላቹ😊 @Urim7
እግዚአብሔር አለ! የነፍስን ጩኸት ማን ይመልሰዋል። የስጋን መጎትጎትስ ምን ሊገታው ይችላል። ለሚጨነቅ እንዴት ይሆናል ለሚል ምንስ ምላሽ ይገኝ ይሆን? ውጥርጥር ዝብርቅርቅ ላለ ነገር፤ ግራ ለሚያጋባ መፍትሄ ላጣ ጉዳይ፤ ቁጥርጥር እስርስር ብሎ ለተተበተበ እስር መፍትሄው አንድ እና አንድ ብቻ ነው። እግዚአብሔር አለ! በለሆሳስም ይሁን በጩኸት፤ በዝግታም ሆነ በጫጫታ እንዴትም ይሁን የእግዚአብሔርን መኖር ማስታወስ ፍቱን መድሀኒት ነው። ብወድቅስ? እግዚአብሔር አለ! ባልወድቅም እግዚአብሔር አለ። ነገ እንዴት ሊሆን ነው? እግዚአብሔር አለ! ለዛሬም ቢሆን እግዚአብሔር አለ። ከፀሀይ በታች መልስ አጥተን ለምንኳትንለት ነገር በሙሉ እግዚአብሔር አለ። ቀድሞውንስ ሰማይ የፀናው ምድርም የቀጠለው በመኖሩ መሆኑ መች ተዘንግቶ! የኛም ጉዳይ ነገራችንም በሙሉ በእጁ ነው። እኛም ለሰማነው ድምፅ ምላሽ እንሰጣለን በነገር ሁሉ እግዚአብሔር አለ። @Urim7
የዓለም ኀጢአተኞች እንኳን ደስ ያላችሁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቷል ሊድናችሁ፤ የዓለም ኀጢአተኞች እንደኔ ያላችሁ፣ ኢየሱስ ያድናል በእርሱ ተስፋ አላችሁ። ኢየሱስ ሠርቶል- በእርሱ ተስፋ አላችሁ፣ አየሱስ ሆኖታል- በእርሱ ተስፋ አላችሁ። ኢየሱስ ችሎታል - በእርሱ ተስፋ አላችሁ። ወዳጆቼ፣ ግድ የለም ኢየሱስ አለላችሁ። ተነሱ፤ ወደቤቱ ሂዱ፤ በተስፋውም ታደሱ። መልካም የጌታ ቀን! @Romans148
ወንጌል ያሕዌ የመላለሙ ላዕላይ ገዢ ነው። ኹሉን እንደ ፈቃዱ ምክር ያወጣል ያገባል። ከዘላለም ንጉስ ኾኖ የተሾመው ያሕዌ፥ ወኪል እንደ ራሴዎችን በመልኩ እንደምሳሌው ፈጠረ። በመንግስቱ ውስጥም ታማኝ ገዢ እንዲኾን ሾመው። ሰው ግን በፈጣሪው ላይ አመጸ። የጽድቅ አገዛዙንም ነቀፈ። ራስ ገዝ ለመኾንም ቋመጠ። ይኽን አለመታዘዝና ሸፍጥ ተከትሎ ስሙር የነበሩ ኅብረቶች ኹሉ መሻከር ጀመሩ። ኃጢያት ወደ ዓለም ገባ። ኃጢያትም ሞትን ወለደ። የእጁ ሥራ በኃጢያት ቅንበር ሲጎብጥ ማየት ያልሻተ ቸር አምላክ፤ ለበደለኛው ሰው መድኃኒት ሊያበጅለት ደነገገ። አብርሃምን በመጥራት ስብራቶችን መፈወስ ጀመረ። የኪዳን ሕዝብ አድርጎ በጠራው እስራኤልም፤ የጽድቅ መንግስቱ ቁመና ምን ሊመስል እንደተገባው አስታወቀ። ዳሩ ግን የያሕዌ በኲር የኾነው እስራኤል ጭምር ደጋግሞ በደለ። የንጉስ ካህናት መኾንም ቸግሮት ተገኘ። ፍጹም ፍቅርን የተሞላ አጽናፈ ዓለማዊ ንጉስ፤ ከዳዊት ዘር የኾነ፤ የልቡን መሻት ኹሉ የሚፈጽም መሲህ እንደሚወለድ አበሰረ። ዘመናትን ጠብቆ መሲሁ በዳዊት ከተማ ተወለደ። መላእክት የምስራቹን ለእረኞች ሰበኩ። የምስራቅ ጠቢባንም በጽድቅ ለሚገዛው የያሕዌ ንጉስ ለመስገድ ከሩቅ ተመሙ። መሲሁ በታላቅ መሰጠት የያሕዌን መንግስት እሴቶች አስተማረ። እስራኤል በወደቀበት ኹሉም ተፈትኖ በድል ዐለፈ። ፍጹም ኑሮን ከኖረ በኋላ በኃጢያት የጠለሸውን ኅብረት ለማደስ ደሙን ለስርየት አፈሰሰ። ያሕዌም በኲሩን ከሙታን ከማስነሳት የመሲሁን ምስክርነት አጸደቀ። ሥልጣንም በሰማይና በምድር የተሰጠው አጽናፈ ዓለማዊ ንጉስ ኾነ። በስሙ ለሚያምኑ ኹሉ የመንግስቱ ዜግነትን ሰጠ። በእኛም ውስጥ ይኽን የዕርቅ አገልግሎት አኖረ። በጸጋው የመንግስቱ ዜጎችና ወራሾች የኾንን እኛም ኑ ታረቁ ብለን እንማጸናችኋለን። ኑ ከዘላለም ንጉስ ታረቁ። ኑ ከክብር ንጉስ ጋር ኅብረት ጀምሩ። መሲሁ ይወድዳችኋል። ✍Ebsa @Urim7
ልብህ የሚጠማው ፍቅር አለ ወይ? ወዳጆቼ ልብህ ዛሬ ምን እያሰበ ነው? ለዘላለም የሚቆይ ፍቅር እየፈለገ ነው፤ በሶሻል ሚዲያ ፈለጋ ላይ ነው ! ያየውን ሁሉ እንደሚመኘው - በጓደኞች መፈለግን ስሜት እንዲሰማው እያደረግ ነው- ወይስ በፍቅረኛ መፈለገ ስሜትን እያሳደግ ነው። ወይስ ገንዘብን መፈለገ ላይ ነው ያለው። ልብህ ዬት ነው ? ምን እየፈለገ ነው? የሚገርመው ሁሉን ብታገኝ ልብህ ግን አይረካም! ምክንያቱም የተፈጠረው ለዘላለማዊ ፍቅር ነው! ፍለጋህን አስተካክል በሶሻል ሚዲያ ላይ ያየኸውን ሁሉ ፍጹም አይደለም! ደስተኛ የሚመስሉት ሁሉ እያለቀሱ ነው ሁሉም እንደ አንተ ይሰቃያሉ! ሁሉም እንደ አንተ ይፈልጋሉ! ግን አንድ ነገር አያውቁም፡— እውነተኛ ፍቅር ከሶሻል ሚዲያ አይመጣም ! እውነተኛ ፍቅር ከልብ ይመጣል! እውነተኛ ፍቅር ከፈጣሪ ይመጣል! እውነተኛ ፍቅር አንተ የምትፈልገው ፍቅር አለ! እርሱ በመስቀል ላይ አሳየው! እጆቹን ዘርግቶ "አንተን እወድሃለሁ! ያለ ጥፍሩን ሲወጉት "አንተን እፈልግሃለሁ!" ያለ! ሲሞት "ልጄ ነህ!" ያለ! ያ ዘላለማዊ ፍቅር ነው። ያ ፍቅር ዘላለማዊ ነው! ያ ፍቅር ፍጹም ነው! ያ ፍቅር የማይለወጥ ነው! ያ ፍቅር የማያልቅ ነው! "እግዚአብሔር ዓለምን እንዲያድን ልጁን ሰጠ!" (ዮሐንስ 3:16) ስለዚህ ልብህ ምን እያሰበ ነው። አንተስ ምን ትመልሳለህ? ልብህን ልትሰጠው ትፈልጋለህ? ዛሬ ጊዜው ነው! ዛሬ ውሳኔህን አድርግ! "እነሆ፥ በሩ ላይ ቆሜ አንኳኳለሁ!" (ራእይ 3:20) 📌 እውነተኛ ፍቅር አለ! አንተን ይጠብቃል! @Exodus5868 @Urim7
ጃዝሚን ትባላለች 23 ዓመቷ ነው። በስኪዞፍሪኒያ ህመም ትታገል ነበር። "ጠላት" በሚባል ምናባዊ ሰው ራስን ለማጥፋት ትበረታታ ነበር። ይሄም የሆነው ተደጋጋሚ በሰዎች የመጠላት ያለመፈልግ እና የዝቀተኝነት ስሜት ስለሚሰማት ነበር። በጥር 2023 ሽጉጥ ወስዳ አገጯ ላይ ተኩሳለች። ፊቷ ከባድ ጉዳት ደረሰባት። ለሁለት ሳምንት ኮማ ውስጥ ከቆየች በኋላ በእግዚአብሔር እርዳታ ተርፋለች። የሚገርመው አሁን ቁስሎቿን በመጋራት ሌሎችን ታበረታታለች፦እንዲህ ትላለች "ራስን ማጥፋት መፍትሄ አይደለም። ድጋፍ ፈልግ፣ ራስህን ውደድ!" ወዳጆቼ እንዲህስ ብላቹ አታውቁም ልቤ ዛሬ እንደ ደረቅ ምድር ነው። ዝናም የሚጠብቅ፣ነገር ግን ሳይመጣ የሚቀር። ልቤ ዛሬ እንደ ተሰበረ መርከብ ነው። ወደብ የሚፈልግ፣ነገር ግን መልህቅ የማያገኝ። ልቤ ዛሬ እንደ ጠፋ መንገደኛ ነው። መንገድ የሚፈልግ፣ነገር ግን አቅጣጫ የማያውቅ። ግን አንድ ነገር አውቃለሁ፡— ዝናም ይመጣል! መልህቅ ይገኛል! መንገድ ይታያል! ምክንያቱም እግዚአብሔር አለ! "እግዚአብሔር ለተሰበሩ ልቦች ቅርብ ነው!" (መዝሙር 34:18) 📌 አንተስ ልብህ እንዴት ነው? @Exodus5868 @Urim7
የኔው ብዙ ድካሞች እንዳሉ ሆነው አንዳንድ ነገሮችን ግን ሳስብ የቸኮለ ልብ ኖሮኝ ነው እንጂ በፍፁም የዘገየ አምላክ የለኝም። እና እግዚአብሔር አልዘገየም ጊዜውን ያውቃል ፤ በጊዜው ሁሉን...