tgindex
Journalist Netsanet Getachew

Journalist Netsanet Getachew

Статистика

ሰላም ለሁላችሁም በዚህ ቻናል የተለያዩ ዎቅታዊ እና እውነተኛ መረጃዎችን ታገኛላችሁ። We are here to deliver updated News, Exclusive programs, Interviews, Entertainment and more Reliable and Updated Information about Ethiopia

Последний пост
21:13
Последнее чтение
07:19
Постов за неделю
19
Всего постов
42
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Новости и СМИ
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
651
−1 за 5 дн.
Сутки
+2
+0,31%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
80
36 постов
Вовлечённость
12,3%
к подписчикам
Постов в день
2,7
всего 42
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
66
1/48двое суток
75
1/72трое суток
81

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ዛሬ ዕለተ ሰኞ ነሀሴ 11/12/2018 ዓ.ም በተሰጠ መደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫ ምክክር ጉባዔው በአብዛኛው ጉዳይ ላይ እየተስማማ ጨርሷል አሉ ምክትል ኮሚሽነሯ 📌 በእውነት በጣም ደስ ብሎናል የፈለግነውን መግባባት፣ የፈለግነውን ሰላም ያመጣል ብለን እንገምታለን " - ነው ያሉት ኮሚሽነር ሒሩት ገብረሥላሴ ለስምንቱ አጀንዳዎች ከቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ግብዓት መሰብሰቡንና ረቡዕ በ4 ሺሕ ጉባያተኞች እንደሚጸድቅ ኮሚሽኑ አስታወቀ። 500 ሰዎች ከያዙት እያንዳንዱ ስምንት የሥራ ቡድኖች በተመረጡ 15 ሰዎች የተዋቀረው 120 አባላት የያዘ ቡድን በሁሉም የሥራ ቡድኖች የተነሱ የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦችን በማዳመጥ "ወጥ" ምክረ ሀሳብ ማቅረብ የሚያስችል ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ኮሚሽኑ ምሽቱን አሳውቋል። የእያንዳንዱ የሥራ ቡድን ተወካዮችም የየቡድናቸውን የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች ድግግሞሽ በማስወገድ፣ ያልተቀናጁ ሀሳቦችን በማደራጀት "ወጥ የሆነ ሰነድ" አዘጋጅተው ዛሬ ከሰዓት በኋላ 500 አባላት ላሉት የሥራ ቡድን አቅርበዋል ብሏል። የተደራጁ አጀንዳዎች የቀረቡላቸው 8ቱ የሥራ ቡድኖች ሀሳብ፣ አስተያየት አክለው የመጨረሻው ሰነድ እንዲዘጋጅ ለአደራጅ ቡድኖቹ መመለሳቸውን አሳውቋል። ግብዓት የሰበሰቡ ምክረ ሀሃሳቦችን የሚያጣጥሙ ቡድኖችም የተሰጧቸውን ሃሳቦች ነገ ከሰዓት በፊት አካተው ከሰዓት ለየሥራ ቡድኖቻቸው በድጋሚ በማቅረብ እንደሚያጸድቁ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል። በተያያዘ፣ የምክክር ኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሒሩት ገብረሥላሴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ "ተጣጥሞ፣ ተስተካክሎ የሚቀርቡት ምክረ ሀሳቦች ለስምንቱም ቡድኖች ተመልሰው ይቀርባሉ" ብለዋል። 8ቱም ቡድኖች በሚቀርቡላቸው ምክረ ሀሳቦች ግብዓት ሰጥተው ረቡዕ እንደሚጸድቅ ገልጸዋል። 120 አባላት ባሉት ቡድን በተሰራው ሥራ ላይ ግብዓት ለመስጠት ዛሬ ከሰዓት ስምንቱም ቡድኖች መሰባሰባቸውን ገልጸው፣ "የሚሰባሰበው ግብዓት ላይ ነገ ተሰርቶ ረቡዕ እለት 4 ሺው ጉቢያተኞች ያጸድቁታል" ብለዋል። 500 ሰዎችን የያዙት 8ቱ የሥራ ቡድኖች ያዘጋጇቸው ምክረ ሀሳቦች 120 አባላት ላሉት ምክረ ሀሳብ አዘጋጅ ቡድን መቅረባቸው ይታወሳል። ኮሚሽነሯ እንዳሉት፣ "8ቱ ቡድኖች ራሳቸው ያዘጋጇቸውን ምክረ ሀሳቦች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ 8ቱ ቡድኖች ላይ፣ የተቀሩት ሰባት ቡድኖች ላይ የተሰሩትንም ይተዋወቃሉ፤ ይረዳሉ።" እያንዳንዱ ስምንቱ ቡድኖች አንድ፣ አንድ አጀንዳ ላይ ሲመክሩ የሰነበቱ ሲሆን ኮሚሽነሯ፣ "በሌሎቹ እነርሱ ባልተሳተፉባቸው ቡድኖች የተሰሩት ምክረ ሀሳቦች ላይ ግብዓት ይሰጣሉ፤ ግብዓቱ ተሰብስቦ የመጨረሻው ሰነድ ይዘጋጃል" ሲሉ ተናግረዋል። ኮሚሽነሯ፣ "8ቱም ቡድኖች ላይ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ተሳታፊዎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ ናቸው። ሁሉም ባለድርሻ አካላት 8ቱም ቡድኖች ላይ ይገኛሉ። ሁሉም የኢትዮጵያ ወረዳዎች በስምንቱም ቡድኖች ላይ ይገኛሉ። ተመሳሳይ ናቸው" ብለዋል። በተያያዘም፣ "የተጠናቀሩት ምክረ ሀሳቦች ጉባዔው የተስማማባቸው ጉዳዮች ናቸው" ሲሉ የተናገሩት ሒሩት፣ "በየትኛውም ዓለም የሚደረጉ ሀገራዊ ምክክሮች መቶ በመቶ በሁሉም ጉዳይ ላይ ይስማማሉ አይባልም" በማለትም በዛሬው መግለጫቸው ገልጸዋል። " ደስ የሚለው ነገር በሀገራችን በተካሄደው ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ በአብዛኛው ጉዳይ ላይ እየተስማማ ጨርሷል። ስለዚህ በእውነት በጣም ደስ ብሎናል። የፈለግነውን መግባባት፣ የፈለግነውን ሰላም ያመጣል ብለን እንገምታለን" ሲሉም አክለዋል። https://t.me/journalistnetsanetgetachew

  • የአዲስ አበባ ጉዳይ ለምን ያሳስበኛል? 👉🏾 የአዲስ አበባ ነዋሪ ስለሆንኩ፣ 👉🏾የአዲስ አበባን እንቆቅልሽ መፍታት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ችግር ከመሠረቱ ለመፍታት ቁልፍ በር ስለሚከፍት። አዲስ አበባ ተበድላለች? 👉🏾 አዲስ አበባ ታድላለችም፣ ተበድላለችም፦ የታደለችው የመላው ኢትዮጵያ ሀብት የሚፈስባት፣ የአገሪቱ ዕጣ ፈንታ የሚወሰንባት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማዕከል ስለሆነች እና ነዋሪዎቿ አገሪቱ ማቅረብ ለምትችለው የተሻለ ዕድልና ጥቅማጥቅም ቅርብ ተቋዳሾች መሆን ስለሚችሉ ነው። 👉🏾 የተበደለችው ግን፦ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ዕድሜ ያላት ብዝኃ ማኅበረሰብ ያቀፈች ከተማ ብትሆንም፣ ከ30 ዓመታት በፊት በብሔር መሥፈርት እንደተዋቀሩት ክልሎች ነዋሪዎቿ እውነተኛ የራስን በራስ የማስተዳደርና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት አልተጎናጸፉም። ይህም የሆነው ከተማዋ የድኅረ-ብሔር እና የብዝኃ-ማንነት መኖሪያ በመሆኗ ነው። አዲስ አበባ የማን ናት? 👉🏾 አዲስ አበባ ውስጥ ሁሉም ሰው መጤ፣ ሁሉም ሰው ባለቤት ነው፦ ታሪኳ እንደሚያመለክተው፣ የዛሬይቱን አዲስ አበባ ከብቦ የሚገኘው ሰፊው የሸዋ ግዛት ከ9ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በማክዙሚ (Makhzumi) ሡልጣኔት፣ በኋላም በኢፋት ሡልጣኔት ሥር የነበረ ግዛት ነበር። በ13ኛው ክፍለ ዘመን በዐፄ ይኩኖ አምላክ የሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት ካንሰራራ በኋላ፣ የሙስሊም ሡልጣኔቶቹ ተዳክመው ሥፍራው በመካከለኛው ዘመን የክርስቲያን ነገሥታት ማዕከል ሆነ (በተለይ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ የደብረ ብርሃንና የየካ/በርአራ ቤተ መንግሥት ይገኛል)። በ16ኛው ክፍለ ዘመን የአዳል ሡልጣኔት መሪው ኢማም አሕመድ ኢብን ኢብራሂም አል-ጋዚ (አሕመድ ግራኝ) ክርስቲያናዊውን ሥርወ መንግሥት ካዳከመ በኋላ፣ የኦሮሞ ሕዝብ መስፋፋት ተከተለ። በዚህም ወቅት ትውፊታዊውን የገዳ ሥርዓት የሚከተሉ የኦሮሞ ማኅበረሰቦች (በዋናነት የቱለማ ጎሳዎች) በሸዋና አካባቢው ሰፍረው ኖሩ። በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ፣ ዳግማዊ ምኒልክ መንግሥታቸውን ከአንኮበር ወደ እንጦጦ፣ በኋላም ፍልውሃ ወደሚገኝበት ፊንፊኔ በማውረድ አዲስ አበባን ቆረቆሩ። ከዚያ በኋላም ኢትዮጵያውያን ከሁሉም ማዕዘናት እየፈለሱ ከተማዋን የጋራ መኖሪያቸው አደረጓት። አዲስ አበባ ኦሮሞዎችን በድላለች? 👉🏾 አዲስ አበባ የዳግማዊ ምኒልክ መንግሥት መናገሻ ሆና በተቆረቆረችበት እና በፍጥነት በተስፋፋችበት ወቅት፣ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ የኦሮሞ አርሶ አደሮች ባሕላቸዊ እና ቋንቋዊ ትስስራቸው ተሸርሽሯል። ቀጥሎም ከተማዋ ይበልጥ እየሰፋች በመጣች ቁጥር በርካታ የኦሮሞ ገበሬዎች ያለ በቂ ካሳና ተለዋጭ መተዳደሪያ ተፈናቅለዋል። የዚህ ያልተገባ መስፋፋት አሉታዊ ተፅዕኖ ዛሬም ድረስ በአጎራባች አርሶ አደሮች ላይ ስጋት ያሳድራል። 👉🏾አዲስ አበባ የተቋቋመችበትን ጊዜ ስናስብ ብሔረሰቦችን በአሁን አረዳዳቸው መረዳት የለብንም፤ ይህ አሁን እንደሚስተዋለው የተሳሳተ አጥፊ እና ጠፊ ምስል ይሰጠናል። እነ ዳግማዊ ምኒልክ ብሔረሰባዊ ማንነታቸውን እንደ "ሸዌ" ወይም ግፋ ቢል "ሀበሻ" ነበር የሚያዩት። "አማራ" የሚለውን ቃል ሲጠቀሙ ክርስትና እምነታቸው ጋር ነበር የሚያያይዙት፤ በዚያን ወቅት የተጻፉ ጽሑፎችም "ሸዌ" እና "አማራ" የሚለውን እንደተለዋዋጭ ሳይሆን፣ እንደ ተለያየ ሕዝብ የሚጠቅሱበት ጊዜ ይበዛል። መንግሥታቸውም ውስጥ (በተለይ በሠራዊታቸው) በርካታ ኦሮሞዎች ነበሩበት፤ እርሳቸውም ኦሮምኛ ይናገሩ ነበር። መንግሥቱ ብሔረሰባዊ ሳይሆን እምነታዊ ቢባል ይሻላል። በወቅቱ ከጎጃም ይልቅ የሸዋ ኦሮሞ የቤተ መንግሥቱ ቤተኛ ነበር ማለት ይቻላል። ታሪካዊ ችግሮችን ለመዘከር እና ከታሪክ ለመማር ምን ይደረግ? 👉🏾 የነዋሪዎች መብት ለድርድር አይቀርብም፦ አዲስ አበባ ታሪካዊና መዋቅራዊ ዕዳዎች ቢኖሩባትም፣ የነዋሪዎቿ ዴሞክራሲያዊና ዜግነታዊ መብት ግን በምንም መሥፈርት ለድርድር ሊቀርብ አይችልም። 👉🏾 ታሪካዊ እውነታዎችን በቅንነት መቀበል፦ ከተማዋ ታሪካዊ አመጣጧን ሙሉ በሙሉ ዕውቅና መስጠት አለባት። የአዲስ አበባ ሙዚየም ከከተማዋ መቆርቆር በፊት የነበረውን የታሪክ ቅብብሎሽ እና የነባር ነዋሪዎችን ታሪክ በግልጽ አጉልቶ ማሳየት አለበት። 👉🏾 ታሪካዊ በደሎችን መካስና ማረቅ፦ በከተማዋ ፈጣን መስፋፋት የተፈናቀሉ ማኅበረሰቦች ታሪክ ሊዘከር፣ ፍትሐዊ ካሳ ሊያገኙ፣ እንዲሁም ወደፊት የሚደረጉ የልማት መስፋፋቶች ተፈናቃይ የማይፈጥሩ እንዲሆኑ መገታት አለበት። 👉🏾 ብዝኃነትን የሚያንጸባርቁ ተቋማትን መገንባት፦ የከተማዋ አደባባዮች፣ ሙዚየሞች፣ መንገዶችና ፓርኮች የሁሉም ኢትዮጵያዊ መናኸሪያነቷን እና የታሪክ ባለቤትነቷን በእኩልነት የሚያስመሰክሩ መሆን አለባቸው። 👉🏾 ከሸገር ከተማ ጋር የጋራ ዕድገት ፍኖተ ካርታ መዘርጋት፦ ከተማዋ ከጎረቤቶቿ ጋር በሰላምና በቅንጅት ትዘልቅ ዘንድ፣ በአንድና በሁለት ትውልድ ውስጥ ወደ ሙሉ የጋራ ተጠቃሚነት የሚያሸጋግር ግልጽና ሕጋዊ የጋራ ማዕቀፍ መዘርጋት አለባት። የአዲስ አበባ ሕጋዊ ሁኔታ ምን ይሁን? 👉🏾 አዲስ አበባ ራሷን የቻለች “የከተማ-ክልል” (City-State) መሆን አለባት። አሁን ያለችበት የፌዴራል መንግሥት መቀመጫ እና የኦሮሚያ ክልል መናገሻ የመሆን ድርብ ተጠሪነት ለጊዜው የፖለቲካ መሸሸጊያ ቢሆንም፣ በዘላቂነት ግን የከተማዋንም ሆነ የኦሮሚያ ክልልን ተቋማዊ ዕድገት የሚያቀጭጭ ነው። 👉🏾አዲስ አበባ ወደ ክልልነት ስትሸጋገር ኦሮምኛ እና አማርኛን እኩል የሥራ ቋንቋ በማድረግ በሁለት ትውልድ ውስጥ እንግሊዝኛን ጨምሮ ባለብዙ ቋንቋ (multilingual) እንድትሆን ፖሊሲ ቀርፆ መሥራት። በዚህም ከተማዋ ከአጎራባች የኦሮሞ ኅብረተሰብ ጋር አዎንታዊ ግንኙነት እንድታዳብር ማድረግ ይቻላል። 👉🏾 አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያለች ክልል መሆኗ ምንም ችግር አይስከትልም፤ ሐረሪ ክልልም በኦሮሚያ የተከበበች ነች። እንኳን ክልል አገርም በአገር ውስጥ ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ ሌሴቶ በደቡብ አፍሪካ ሙሉ ለሙሉ የተከበበች ሉዓላዊ አገር ነች። 👉🏾 የፌዴራል ከተማ መቀየር፦ አዲስ አበባ ፌዴራል ከተማ በመሆኗ የፖለቲካም የኢኮሚም ማዕከል የሆነች አውራ ከተማ ሆናለች። ይህንን የዕድገት ዕድል በፍትሓዊነት ለማሳደግ ለሦስቱ የፌዴራል መንግሥት ቅርንጫፎች አንድ አንድ ከተማ (ከሰሜን፣ ከደቡብ እና ከደቡብ ምስራቅ) በመምረጥ፣ እነዚህን ከተሞች የሚያስተሳስሩ ፈጣን የባቡር መንገዶችን በመገንባት እና ከተማዎቹ ባሕላዊ ማንነታቸውን ጠብቀው እንዲያድጉ መሥራትና የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ስበት ማዕከሉን በማደብዘዝ የመሐል፣ ዳር አገር ክፍፍል መቀነስ። 👉🏾የኦሮሚያ ዋና ከተማን መቀየር፦ ሌሎች ክልሎች ከተሞቻቸውን በአምሳላቸው ለመቅረፅ የተመቻቸው ቢሆንም፣ ኦሮሚያ አዲስ አበባ ላይ በገባችው የታሪክ እሰጥ አገባ ምክንያት መቀመጫ ብታደርጋትም፣ ከተማዋን ግን የኦሮሚያ ክልል ብዙኃንን አስመስላ መቅረፅ አልቻለችም። አትችልምም። ይህንን ለማድረግ ሌላ ከተማ በመምረጥ እንደገና ማልማት መጀመር ይኖርባታል። ኦሮሚያ አዲስ አበባ ላይ ላፈራቻቸው ሀብቶቿ ካሳ ከተማዋን መጠየቅ የምትችልበት ዕድል በሥምምነት ሊወሰን ይችላል። አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለኦሮሚያ ክልል ሆኖ የፌዴራሉ መቀመጫ ብትሆን ምን ችግር አለው?

  • Journalist Netsanet Getachew pinned a photo

  • 20:375522

    በጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው የሚቀርቡ እውነተኛ ሚዛናዊ በሙያዊ ስነምግባር የሚቀርቡ መረጃዎችን በየቀኑ ያግኙ ለሌሎች አዳዲስ አባላቶችን ይጋብዙ። በዚህ ሳምንት 1 ሰው ቢያንስ 10 አዲስ አባሎችን በመቀላቀል የቤተሰባችንን ቁጥር እናብዛ ተደራሽነትን እንጨምር ለናንተ ለውድ ቤተሰቦቸ የማቀርበው የአክብሮት ጥሪ ነው🙏🕴 https://t.me/journalistnetsanetgetachew

  • https://youtube.com/shorts/CWiDdJtroLE?si=P7InhmoMPuoTRIbT

  • ተይዘዋል! አዲስ አበባ፤ነሐሴ 11 ቀን 2018ዓ/ም(አዲስ ፖሊስ)፦ፈርዶስ መሃመድ ፣ ኤደን ዳዊት እና ሃኒ ሁሴን የተባሉ ታዳጊ ተማሪዎች በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አለም ባንክ አካባቢ ጓደኛቸውን ሲደበድቧት የሚያሳይ አሳዛኝ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱን ተከትሎ ድርጊቱን የፈፀሙት ግለሰቦች በህግ እንዲጠየቁ ህብረተሰቡ አስተያየት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ድርጊቱ ጥቅምት 14 ቀን 2018 መፈፀሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቆ ቪዲዮው በማህበራዊ ሚዲያ ከመሰራጨቱ ከወራት በፊት ወንጀሉን የፈፀሙትን ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ ማጣራቱን ፖሊስ ገልጿል፡፡ በወንጀሉ የተጠረጠሩት ሦስት ተማሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበው በጊዜ ቀጠሮ ታስረው ፖሊስ አስፈላጊውን ማስረጃ በማሰባሰብ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ መዝገቡን ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ልጅቷ ስትደበደብ የሚያሳየው ቪዲዩ መለቀቁ በልጅቷም ሆነ በቤተሰቧ ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ ቪዲዮውን የለቀቀውን አካል ለማረጋገጥ ፖሊስ ሦስቱን ተጠርጣሪዎች በድጋሚ በቁጥጥር ስር አውሎ ተጨማሪ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል፡፡ ህብረተሰቡ ድርጊቱን በማውገዝ ወንጀሉን የፈፀሙ ሰዎች በህግ መጠየቅ እንዳለባቸው ያሳየውን መቆርቆር የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አድንቋል፡፡ https://t.me/journalistnetsanetgetachew

  • የሀሰት መረጃዎችና እገታዎች ለጸጥታ ስራው ፈተና መሆናቸውን ፖሊስ ገለጸ በአዲስ አበባ ከተማ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎችና በተደራጀ መልኩ የሚፈጸሙ ‹‹የሀሰት እገታ›› ድርጊቶች በፖሊስ ስራ ላይ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታዉቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኘነት ሀላፊ ኮማንደር ቶማስ ጌታቸው፤አንዳንድ ግለሰቦች ለገንዘብ ጥቅም ሲሉ ‹‹ታግተናል›› በማለት ለቤተሰቦቻቸውና ለፖሊስ የሀሰት መረጃ በመስጠት ትልቅ የጸጥታ ስጋት ሲፈጥሩ ተስተውሏል ብለዋል። በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ የሀሰት መረጃዎች ህዝቡን ለማሸበርና በፖሊስ ላይ ያለውን እምነት ለመቀነስ ሆን ተብለው የሚዘጋጁ በመሆናቸው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል። ለገንዘብ ጥቅም ሲባል የሚፈጸሙ የሀሰት እገታ ድርጊቶችን ፖሊስ በቴክኖሎጂ የታገዘ ምርመራ በማድረግ እውነታውን እያጋለጠና በፈጻሚዎቹ ላይ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ብለዋል፡፡ ስለሆነም ህብረተሰቡ መረጃዎችን ከተረጋገጡ የፖሊስና የመንግስት የመረጃ ምንጮች ብቻ እንዲያገኝ አሳስቧል። በመጨረሻም ፖሊስ በቀጣይ የሚከበሩትን የመስቀልና የኢሬቻ በዓላትን በሰላም ለማክበር ከወዲሁ ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ወደ ስራ መግባቱንና ህዝቡ እንደተለመደው ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል። https://t.me/journalistnetsanetgetachew

  • የሚዲያ ባለሙያዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ያልተረጋገጡና ጫፍ ያልደረሱ መረጃዎችን በማሰራጨት ብዥታ ከመፍጠር እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በጥብቅ አሳሰበ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አንድ ወር መሙላቱን አስመልከቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን ወቅታዊ መልዕክት ዛሬ ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም ማምሻውን አስተላልፏል ። ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ፤ ላለፉት ሰላሳ ቀናት የተካሄደው የምክክር ሂደት ስኬታማና አዲስ የምክክር ባህል እንዲዳብር መሰረት የጣለ እንደነበር ገልጿል። ይሁን እንጂ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ አልጋ በአልጋ እንዳልነበረና ተፈጥሯዊ የሆኑ አለመግባባቶች ማጋጠማቸውን ጠቁሟል። በተለይም ሂደቱ አሁን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በስም ያልጠቀሳቸው ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላትና አንዳንዶች ሲል የገለጻቸው የተዛቡና ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝብን ለማደናገር እየሞከሩ ነው ብሏል። ስለሆነም ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑና በስፍራው ከሚገኙ ህጋዊ መገናኛ ብዙኃን ከሚወጡ መረጃዎች ውጪ ያሉ ሀሰተኛወሬዎችንእንዳይከታተል፣የሚዲያ ባለሙያዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ደግሞ ያልተረጋገጡና ጫፍ ያልደረሱ መረጃዎችን በማሰራጨት ብዥታ ከመፍጠር እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስቧል። በመጨረሻም ኮሚሽኑ ሙያዊና ሥነ-ምግባራዊ ጥሰት በሚፈፅሙ የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎች ላይ ተጠያቂ የማድረግ እርምጃ እየወሰደ መሆኑንና ይህ ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። https://t.me/journalistnetsanetgetachew

  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ (CEO) አቶ መስፍን ጣሰው ለተጨማሪ አንድ ዓመት በሥራቸው ላይ እንደሚቆዩ ማረጋገጣቸውን 'አዲስ ፎርቹን' ዘገበ። የአየር መንገዱ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ሰብሳቢነት የአቶ መስፍን ጣሰውን የሥራ ዘመን ማራዘሙ ተገልጿል። አቶ መስፍን በቅርብ በሰጡት መግለጫ፣ ጡረታ መውጣት የነበረባቸው ከ3 ዓመት በፊት የነበረ ቢሆንም በመንግሥት ፍላጎት መጀመሪያ ለ2 ዓመት ከዚያ ለ1 ዓመት የስራ ውላቸው መራዘሙን ተናግረው ነበር። አሁንም ለተጨማሪ አንድ ዓመት ኃላፊነታቸው መራዘሙን 'አዲስ ፎርቹን' ከእሳቸው ማረጋገጡን ገልጿል።

  • አንድ ወር የፈጀው ምክክሩ አከራካሪ የነበረው የአዲስ አበባ ጉዳይን ጨምሮ በስምንቱም አጀንዳዎች ላይ ስምምነት ተደርሷል አለ ሐምሌ ስምንት የጀመረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በያዛቸው ስምንቱም አጀንዳዎች ተመካካሪዎች መስማማታቸውን አስታወቀ።   ስምምነት የተደረሰባቸው አጀንዳዎች ውስጥ በመንግስት አደረጃጀት እና በሌሎችም ላይ በልዩነት የተያዙ ምክረ ሀሳቦች መኖራቸውን አዲስ ማለዳ ከተሳታፊዎች ሰምታለች። ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየው ምክክሩ ከፌደራል ከተሞች ጉዳይ፣ ፓርላሜንታዊን ወይስ ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት፤ በሀገር ግንባታ ጉዳይ የሰንደቅ ዓላማ እና ታሪክ ጉዳዮች እና ሌሎችም ሰፊ ጊዜ የወሰዱ እና  የተለያዩ ሃሳቦች የቀረቡባቸው ናቸው። ኮሚሽኑ ይህ ስምምነት ተጠናቅቆ ሃሳቦችን ለሚያጣጥም እና የሚቃረኑ ነገሮች እንዳይኖሩ እንዲሁም የሃሳብ ድግግሞሽ እንዳይኖር የሚሰራ ቡድን ላይ ተሸጋግሯል ያለ ሲሆን በምክክር ጉባኤው  ወቅት አለመግባባቶችና ግጭቶች መኖራቸው የምክክሩን አስፈላጊነት ያሳየ እና ለዚህም ያደረሰ እንደሆነ አስታወቋል። የሀገራዊ  ምክክር ኮሚሽን  በምክክር ጉባኤው  የምክክር ሂደት ወቅት “አለመግባባቶችና ግጭቶች አልነበሩም አይባልም” ያለ ሲሆን እንዲህ መሰል ልዩነቶች ማጋጠማቸው ምክክሩ አስፈላጊ  መሆኑን ያረጋገጠ ነው ብሏል። ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ(ፕሮፌሰር) ከዚህ ቀደም አለመግባባቶች እና ግጭቶች ተጠባቂ እንደሆኑ ማንሳታቸው አይዘነጋም። በ500 ተሳታፊዎች ተዋቅረው ሲመካከሩ የቆዩት 8ቱ ቡድኖች በሂደቱ ያጋጠሟቸውን ግጭቶችና አለመግባባቶች በመደማመጥና በመነጋገር ተፈትተው ወደ አንድ የጋራ አማካይ ሃሳብ በመድረስ ላይም እንደሆኑ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጸዋል። ኮሚሽነሯ አክለውም አብዛኞቹ አጀንዳዎች ላይ ተመካካሪዎች በምክረ ሃሳቦቹ ላይ ፊርማቸውን በማስፈር  ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል። የፌደራል ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬድዋ  ጉዳይ አከራካሪ እና የሃሳብ ፍትጊያ እንዲሁም በስልታዊ ቡድን ወቅት አለመግባባት ከታየባቸው ጉዳዮች ውስጥ ነው። አዲስ ማለዳ ከተሳታፊዎች እንደ ሰማችው ከሆነ “አንዳንድ አጀንዳዎች ላይ በልዩነት የተያዙ እና ከአመራሮች በኩል ቀጥተኛ ያልሆነ ጫና እንደሚደርስ” አንስተዋል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ዋና ኮሚሽነሩ ከዚህ ቀደም ማንም ሊመካከር እንጂ ጫና ሊፈጥር እንዳልመጣ ማንሳታቸው ይታወሳል። የምክረ-ሃሳቦች  የሚያጠናክር ቡድን የተዋቀረ ሲሆን  ከስምንቱም እያንዳንዱ 15 ሰዎችን የያዘ 120 ተመካካሪዎች ተመርጠዋል። እነኚህ ከስምንቱም ቡድኖች የተመረጡ አባላት ያሉት ቡድን ሥራውን ጀምሯል የተባለ ሲሆን ተግባሩም የተዘጋጁትን ምክረ-ሃሳቦች ማጣጣም፣ ተቃራኒ ሃሳቦችን እንዳይኖሩ ማድረግ እና ድግግሞሾችን በማስቀረት የአንድ ወጥነት ባህሪ እንዲኖራቸው  በማድረግ እንደሚሰራ አስታውቋል። ኮሚሽኑ አክሎም ከግለሰቦች፣ ከቡድኖች እንዲሁም ከፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ ቅሬታዎችን በኮሚሽኑ የቅሬታ አፈታት ሥነ-ስርዓት መሰረት የማጥናት፣ የመመርመርና ውሳኔ የመስጠት ስራ እየተከናወነ ይገኛል ያሉት ምክትል ኮሚሽነሯ ሒሩት ገብረ እግዚአብሔር ናቸው። እንደ አብን እና እናት ያሉ ፓርቲዎች በምክክር ሂደቱ ላይ የገለልተኝነት ጥያቄ ማንሳታቸው ይታወቃል። ኮሚሽነሯ አክለውም ምክክሩ የሦስት አራተኛ  ያህል ስራ መጠናቀቁ የገለፁ ሲሆን  የምክክሩን “ውጤታማነት” ለኢትዮጵያ ህዝብ “የማበሰር ስራ” ይከናወናል ብለዋል።

  • በአዲስ አበባ የትራፊክ ሕግ ጥሰት ከ1.5 ሚሊዮን ማለፉ ተገለጸ   በአዲስ አበባ ከተማ በተያዘው ዓመት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የትራፊክ ሕግ ጥሰቶች መመዝገባቸውን ዋና ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8  በሚተላለፈው ታዲያስ አዲስ የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። ከተመዘገቡት ጥሰቶች መካከል ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት የቀይ መብራት ጥሶ ማለፍ ሲሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ከ900 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች እንደሚንቀሳቀሱም ተመልክቷል። ዋና ኢንስፔክተሩ የትራፊክ ሕግን አለማክበር ለሕይወትና ንብረት መጥፋት ዋነኛ መንስኤ መሆኑን አሳስበው፤ የቁጥጥርና የቅጣት አፈጻጸሙ መጠናከሩ ግን አደጋዎችን በመቀነስ ረገድ አዎንታዊ ውጤት እያሳየ ይገኛል ብለዋል።   በዚሁ መሠረት በ2017 ዓ.ም 4መቶ11 የነበረው የሞት አደጋ በ2018 ዓ.ም ወደ 3መቶ82፤ የከባድ አደጋዎች ቁጥር ደግሞ ከ1 ሺህ9መቶ85 ወደ 1ሺህ8መቶ65 ዝቅ በማለት የ1መቶ20 አደጋዎች ቅናሽ አሳይቷል። በአንጻሩ ቀላል አደጋዎች ከ1መቶ15 ወደ 7መቶ35፣ የንብረት ጉዳቶች ደግሞ ከ34 ሺህ84 ወደ 34 ሺህ7መቶ2 ከፍ ብለዋል።   በመጨረሻም አሽከርካሪዎች በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ሕግን በማክበር ማሽከርከር እንዳለባቸው እና የሰው ሕይወትና ንብረትን ከውድመት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል።

  • ሲኤንኤን በቅርቡ ባወጣው ዘገባ በደቡብ ምዕራብ ሳዑዲ አረቢያ በሚገኘው የኸሚስ ሙሻይት እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን አስከፊ ሁኔታ ይፋ አድርጓል። ዘገባው በትግራይ ግጭት ወቅት ከሀገር ወጥቶ በየመን በኩል ወደ ሳዑዲ የገባውን እና “አማኑኤል” የተባለውን ወጣት የሕይወት ታሪክ ያሳያል። ወጣቱ እረኝነት ሲሰራ ከቆየ በኋላ የሳዑዲ ዜጎች መደበኛ ዕቃ እንደሆነ በመንገር የሰጡትን መኪና ሲነዳ ሀሺሽ ተገኝቶበት እንደተያዘ ይናገራል። በምርመራ ወቅት ድብደባ እንደተፈጸመበት፣ በማያውቀው የአረብኛ ቋንቋ በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ እንዲፈርም መደረጉን እና ተርጓሚ እንዲሁም የሕግ ድጋፍ ሳያገኝ በአጭር ጊዜ የሞት ቅጣት እንደተፈረደበት አስረድቷል። በአሁኑ ወቅት በኸሚስ ሙሻይት እስር ቤት ብቻ በዕፅ ተያያዥ ክስ የሞት ቅጣት ተፈርዶባቸው የምስቀያ ቀናቸውን የሚጠብቁ 60 ገደማ ኢትዮጵያውያን በአንድ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ። የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እንደሚሉት ሳዑዲ አረቢያ በየዓመቱ በዕፅ ወንጀል የተከሰሱ በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎችን የምትገድል ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያውያን ከፍተኛውን ቁጥር አላቸው። በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ለመታደግ በተደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት 1 ሺህ 971 ኢትዮጵያውያን የንጉሣዊ ምሕረት ተጠቃሚ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል። https://t.me/journalistnetsanetgetachew

  • без подписи

  • без подписи

  • በሳዑዲ የድንበር ጠባቂዎች ሀሺሽ እና ጫት የተገኘባቸው 8 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ዋሉ። በሳዑዲ አረቢያ የዓሲር እና የጃዛን ክልሎች የድንበር ጥበቃ ኃይሎች ጫት እና ሀሺሽ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሞከሩ ያሏቸውን 8 የኢትዮጵያ ዜጎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተነግሯል። በሳዑዲ አረቢያ ሕግ መሠረት እንደ ጫት እና ሀሺሽ ያሉ እፆችን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እጅግ ከባድ ወንጀል ሲሆን፣ ጥፋተኞች እስከ ሞት ቅጣት ወይም እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት፣ ከባድ የገንዘብ መቀጮ እና ከሀገር የመባረር እርምጃ ያስቀጣል። ለመሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለምን በተደጋጋሚ በዚህ መልኩ ይያዛሉ ? በየዓመቱ ከ100 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የምሥራቃዊውን የስደት መስመር በመከተል በጂቡቲ እና በየመን አቋርጠው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሲጓዙ፥ አብዛኞቹ ስደተኞች ከሀገር የሚወጡት በድህነት፣ በሥራ እጥረት እና በየአካባቢው በነበሩ ግጭቶች ምክንያት ነው። ታዲያ በጉዞ ወቅት በአዘዋዋሪዎች ታግተውና ተገደው ዕዳቸውን ለመክፈል ወይም ዕቃ እንዲያጓጉዙ በመደረግ ለአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ይዳረጋሉ። አንዳንዶቹም ጫት በኢትዮጵያ ሕጋዊ በመሆኑ በሳዑዲ አረቢያ ያለው ሕግ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ሳይረዱ ለከፍተኛ አደጋ ይጋለጣሉ። https://t.me/journalistnetsanetgetachew

  • ቅድመ ሁኔታውን አንቀበልም በማለት ለመፈረም ፈቃደኛ ካልሆኑት መካከል ፖለቲከኛ እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን ጨምሮ 30 ተከሳሾች ተጠቃሽ ናቸው። ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ያቀረበው ክስ፣ በአማራ ክልል ካለው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ በተፈፀሙ የሰዎች ግድያዎች፣ የአካል ጉዳት እና የንብረት ውድመት እንዲሁም በሌሎችም የሽብር ወንጀሎች ላይ ተሳትፎ እንዳላቸው የሚዘረዝር ነው። የይቅርታ መጠየቂያ ሰነዱ፣ በየክስ መዝገባቸው በሽብር የቀረበባቸውን ወንጀል አምነው ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚጠይቅ ይዘት ያለው ስለመሆኑ ቢቢሲ የተመለከተው እና ሰነዱን አንፈርምም ካሉት የሽብር ተከሳሾች መካከል ሠላሳዎቹ የፈረሙበት ደብዳቤ ያመለክታል። ፈርሙ የተባሉበት ሰነድ "በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ፣ በቀውሱ ለሞቱ እና ለቆሰሉ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች (በየክስ መዝገቡ ቁጥሩ ይለያያያል) ኃላፊነት ውሰዱ፤ በቢሊዮኖች የተገመተውን የንብረት ውድመት ፈፅመናል ብላችሁ እመኑ" የሚሉ ነጥቦችን ያካተተ እንደሆነ በደብዳቤያቸው ላይ ጠቅሰዋል። በተጨማሪም "አገሪቱ በአማራ ትውፊቶች እና እሳቤ መመራት አለባት" የሚል አቋም ማራመዳቸው ተጠቅሶ ይህም ወንጀል መሆኑን እንዲያምኑ ስለመጠየቃቸው አስፍረዋል። እንዲሁም "ያለ አግባብ የተወሰዱ የአማራ ርስቶች መመለስ አለባቸው" ስለማለታቸው እና ይህም ወንጀል መሆኑን እንዲያምኑ በሰነዱ መካተቱን ገልፀዋል። በሰነዱ ላይ "ጽንፈኛ ኃይሎች" ተብለው የተጠቀሱትን በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን እንዲያወግዙም ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን አመልክተዋል። ተከሳሾቹ የተጠቀሱትን ወንጀሎች ስለመፈፀማቸው አምነው፣ ዳግመኛ የእንደዚህ ዓይነት ድርጊት ውስጥ ላለመሳተፍ ቃል እንዲገቡ እና የሚሳተፉ ከሆነ ደግሞ መንግሥት "አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድባቸው" እንዲስማሙም ሰነዱ ይጠይቃል። ሆኖም፣ ይህን ቅድመ ሁኔታ ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በሰነዱ ላይ አለመፈረማቸውን በደብዳቤያቸው ላይ ጠቅሰዋል። "ወንጀለኛ ነን ብለን አንፈርምም። [ይህ] በሕግም፣ በሞራልም፣ በፖለቲካም ተቀባይነት የለውም" የሚሉት ሠላሳዎቹ ተከሳሾች "የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎችም ሕጋዊ ናቸው ብለን እናምናለን" ሲሉም አክለዋል። የተከሰሱበትን ክስ "አንቀበልም" ብለው በፍርድ ቤት እየተከራከሩ ባሉበት ሁኔታ፣ "ወንጀለኞች ነን" ብለው ለመፈረም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ስለመግለፃቸው ሦስት ጉዳዩን የሚከታተሉ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በመሆኑም፣ ከሦስት ዓመት በላይ ያለ ፍትሕ መቆየታቸውን እና "ቤተሰቦቻቸውም ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸውን የሚገልፁት እነዚህ ተከሳሾች፣ መንግሥት "ክሱን አቋርጦ በፖለቲካዊ መንገድ በምህረት ይፍታን" የሚል አቋም አላቸው። ተከሳሾቹን እና መንግሥትን አደራድሯል ከተባለው ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ስለ ጉዳዩ አስተያየት ጠይቀን ነበር። ሆኖም የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ በጉዳዩ ላይ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል። ቢሆንም ኮሚሽኑ እንደዚህ ባሉ ጉዳዮች ላይ በራሱ መንገድ ከሚሰጠው መግለጫ ውጭ መረጃ ለመስጠት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ከሌሎች የኮሚሽኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመሆን በታኅሣሥ ወር በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ቂሊንጦ የጊዜ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ጉብኝት አድርገው ነበር። በጉብኝታቸውም ከተከሳሾቹ ጋር በሰብዓዊ መብት አያያዝ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገው መመለሳቸው በወቅቱ ተገልጿል። ምንጮቻችን እንዳሉት፣ ዋና ኮሚሽነሩ ብርሃኑ አዴሎ ከሽብር ተከሳሾቹ ጋር ውይይት ካደረጉ ከስድስት ወራት በኋላ ነው በድጋሚ አግኝተዋቸው የማደራደር ተግባር የጀመሩት። ስለ ይቅርታው ጉዳይ ከተከሳሽ ጠበቆች በኩል አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ለጊዜው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አልተሳካም። ይሁንና ይቅርታ የመጠየቅ እና የመስጠት ሂደት ከሕግ አንፃር እንዴት እንደሚታይ የጠየቅናቸው አንድ የሕግ ባለሙያ፣ አንድ ተከሳሽ ወንጀለኛ ተብሎ ካልተፈረደበት በስተቀር በይቅርታ ሂደት ውስጥ ማለፍ እንደማይችል ተናግረዋል። በጥብቅና ሥራ ላይ የተሰማሩት የሕግ ባለሙያው አቶ ኤርሚያስ ጥላሁን፣ በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 229 መሠረት፣ ይቅርታ ለመስጠት "በግልፅ የተወሰነ የቅጣት ውሳኔ መኖር አለበት" ይላሉ። በተመሳሳይ ይቅርታ መጠየቅም የሚቻለው ውሳኔ ባገኘ ወይም ፍርድ በተሰጠው ጉዳይ ላይ መሆኑን አስረድተዋል። የይቅርታ አቀራረብ ድንጋጌዎችን የያዘው የይቅርታ አዋጅ 840/2006 በአንቀፅ 15 ላይ፣ በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የመጨረሻ ቅጣት የተወሰነበት ማንኛውም ሰው የይቅርታ ጥያቄውን ራሱ ወይም በቅርብ ዘመዱ ወይም በሚወክለው ጠበቃው አማካኝነት ማቅረብ እንደሚችል ይደነግጋል። በመሆኑም የፍርድ ውሳኔ ሳይሰጥ የይቅርታ ጉዳይን ማንሳት እንደማይቻል አቶ ኤርሚያስ አብራርተዋል። ምርጫ 97ን ተከትሎ በነበረው ሁኔታ ታስረው የነበሩት እነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን እና ብርትኳን ሚደቅሳን ጨምሮ ሌሎችም እስረኞች ከተፈረደባቸው በኋላ ጉዳያቸው በይቅርታ ታይቶ መፈታታቸውን፣ እንዲሁም በ2010 ከነበረው "የመንግሥት ለውጥ" በኋላ በተመሳሳይ መልኩ የተፈቱ ሰዎች መኖራቸውን በማሳያነት አንስተዋል። የሕግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ተፈርዶበት በይግባኝ ላይ የሚገኝ ተከሳሽ እንኳን ይቅርታ መጠየቅ አይችልም። በኢሰመኮ አደራዳሪነት ቅድመ ሁኔታዎችን ተቀብለው ይቅርታ እንዲጠይቁ የፊርማ ሰነድ የቀረበላቸው የሽብር ተከሳሾች፣ ገና ፍርድ ያላገኙ እና የክስ ሂደታቸው በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኝ ናቸው። በመሆኑም በሕጉ መሠረት ከእስር መለቀቅ የሚችሉት ክሳቸውን በማቋረጥ እና በምህረት እንደሆነ የሕግ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። መረጃው የቢቢሲ ነው። https://t.me/journalistnetsanetgetachew

  • በአማራ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ለተከሰሱት ከሦስት መቶ በላይ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ግለሰቦች በይቅርታ እንዲለቀቁ ሂደት ላይ ይገኛሉ። ለሽብር ተከሳሾች የቀረበው የይቅርታ ሰነድ በክልሉ ለተፈፀሙ ግድያዎች እና ጉዳቶች ተከሳሾቹ ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚጠይቅ መሆኑን ቢቢሲ የተመለከተው ሰነድ ያሳያል። የሕዝብ ተወካዮችን እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችን ጨምሮ በአማራ ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር በተገናኘ በተለያዩ መዝገቦች የሽብር ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች፣ ይቅርታ ጠይቀው ክሳቸው እንዲቋረጥ እና ከእስር እንዲለቀቁ በመንግሥት ለቀረበላቸው ጥያቄ የተለያየ ምላሽ መስጠታቸውን ቢቢሲ ከምንጮቹ አረጋግጧል። ሦስት ዓመት እና ከዚያም በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የሽብር ተከሳሾች፣ ይቅርታ ጠይቀው ከእስር እንዲለቀቁ የሚጠይቀው ሰነድ (ፎርም) የደረሳቸው በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አማካኝነት መሆኑን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል። የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ፣ ከሰኔ 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል በተከሳሾቹ እና በመንግሥት መካከል የማደራደር ተግባር ሲያከናውኑ ከቆዩ በኋላ ተከሳሾቹ ይቅርታ የሚጠይቁበት እና ቅድመ ሁኔታዎችን ያካተተበት ሰነድ ለየግላቸው እንደደረሳቸው ታውቋል። በአቶ ብርሃኑ አዴሎ መሪነት ተካሄደ ከተባለው ድርድር በኋላ ሰነዱ የቀረበላቸው የሽብር ተከሳሾች ቁጥር ከ300 በላይ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀዋል። በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ከሚገኙት ከእነዚህ ተከሳሾች መካከል አብዛኛው የቀረበላቸውን ሰነድ ሲፈርሙ ያልፈረሙም ስለመኖራቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

  • የመንግስት አደረጃጀት ፓርላሜንታዊ ወይስ ፕሬዚዳንታዊ ይሁን? የሚለው ጉዳይ ባለማስማማቱ በልዩነት ተይዞ ቀጣዩን ውሳኔ የሚጠባበቅ ሆነ። ከ8ቱ አጀንዳዎች አንዱ በሆነው የመንግስት አደረጃጀትና ቅርጽ አጀንዳ፣ የመንግስት አወቃቀር፥ ፓርላሜንታዊ ወይስ ፕሬዚዳንታዊ ይሁን? የሚለውና በ250 "ስልታዊ" ቡድን ሲያከራክር የቆየው ጉዳይ 500 ሰዎችን በያዘው "የሥራ ቡድን"ም አከራካሪነቱ ቀጥሎ ለአስማማሚ ኮሚቴ፣ ካልሆነ ለድምፅ አሰጣጥ ተሻገረ። የአጀንዳው ፀሐፊ አቶ ሰለሞን ገብሬ ለአንድ የሀገር ውስጥ ማህበራዊ ሚዲያ በሰጡት ቃል፣ 500 ሰዎችን በያዘው "የሥራ ቡድን"ም የመንግስት አወቃቀር፥ "'ፓርላሜንታዊ ሆኖ ፕሬዚዳንቱ ከፓርላማ ይመረጥና የፕሬዚዳንቱንም የጠቅላይ ሚኒስትሩንም ሥራ አንድ ላይ ይስራ'" እና "'ፕሬዚዳንታዊ ሆኖ ፕሬዚዳንቱ ከህዝብ ይመረጥ' የሚሉት ሁለት አማራጮች ቀርበው በሁለቱም የጋራ ውሳኔ ሳይሰጥ ወደ ቀጣይ ሂደት አልፈዋል" ብለዋል። የምክክር ኮሚሽኑ፣ 500 ሰዎችን የያዘው "የሥራ ቡድን"፣ ተመካካሪዎች "በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፤ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልና እና የምርጫ ስርአት" በተሰኘው አጀንዳ መግባባት ላይ ደርሰው "የቃለጉባኤ ሰነዶች ላይ በመፈረም አረጋግጠዋል" ሲል ዛሬ አሳውቋል። የአጀንዳው ፀሐፊ ደግሞ፣ በአጀንዳው ከቀረቡ 53 ሀሳቦች በ50ዎቹ ከስምምነት ቢደርሱም፣ በሦስት ጉዳዮች ግን ምክረ ሀሳቦች አከራካሪነታቸው በመቀጠሉ መግባባት ላይ የተደረሰው በአስማሚ ኮሚቴ፣ ካልሆነ በድምፅ ብልጫ እንዲታዩ መሆኑን ለሚዲያ ተናግረዋል። ለአስማሚ ኮሚቴ፣ ካልሆነ ለድምፅ ውሳኔ የሚሻገሩት በልዩነት የተያዙት የትኞቹ ጉዳዮች ናቸው ? የመንግስት አደረጃጀት ነገር፦ የመንግስት አወቃቀር ፓርላሜንታዊ ወይስ ፕሬዚዳንታዊ ይሁን? የሚለው ጉዳይ በተመካካሪዎች ምክረ ሀሳብ መሰረት ሁለት ጽንፍ መያዙን ሰለሞን ገልጸዋል። በአንድ በኩል፣ "ፓርላሜንታዊ ሆኖ ፕሬዚዳንቱ ከፓርላማ ይመረጥና አሁን ያለውን የፕሬዚዳንትና የጠቅላይ ሚኒስትርን ተግባር አንድ ላይ ይዞ ይሰራል። የጠቅላይ ሚኒስትሩም የፕሬዚዳንቱም ስራ በአንድ ላይ ሆኖ ለሀገረ መሪው/ፕሬዚዳንቱ ይሰጠዋል። ሀገረ መሪው ከፓርላማ ይመረጣል" የሚል ምክር መቅረቡን ተናግረዋል። በሌላ በኩል፣ "ፕሬዚዳንቱ ተወዳድሮ ቀጥታ ከህዝብ ይመረጥ። ያሸነፈው ሀገሪቱን ይምራ" የሚል መከራከሪያ ቀርቧል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውክልና ጉዳይ፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የብሔረሰቦች መወከያ መሆኑን፣ አሁን ባለው አሰራር ከእያንዳንዱ ብሔረሰብ አንድ ተወካይ እንደሚሰጥ፣ ለቀረው ደግሞ አንድ አንድ ሚሊዮን ህዝበ ተጨማሪ አንድ፣ አንድ ሰው እየሆነ እንደሚሰጥ የገለጹት አቶ ሰለሞን፣ ይህ ማለት "በህዝብ ቁጥር ይሆናል ማለት ነው" ሲሉ አስረድተዋል። "ሁሉም ማንነቶች በአንድ ይወከሉና ባላቸው በህዝብ ቁጥር ደግሞ በአንድ፣ አንድ ሚሊዮን አንድ፣ አንድ እየተጨመረ ይኬዳል" ሲሉ አክለው፣ በአንድ በኩል ይሄው አሰራር "ይቀጥል" የሚል አማራጭ ሀሳብ ከተመካካሪዎች መቅረቡን ገልጸዋል። በሌላ በኩል፥ "ሁሉም ብሔር ማንነቱ እኩል ነው፤ ትንሽ የሚባል ማንነት የለም። ስለዚህ ሁሉም ብሔረሰቦች እኩል ቁጥር፣ እኩል ተወካይ ይኑራቸው" የሚል መከራከሪያ ሀሳብ መቅረቡን ገልጸዋል። ለፌዴሬሽን ም/ቤት የብሔረሰብ ተወካዮች አመራረጥ ጉዳይ፦ ይህም ሌላው አከራካሪቱ የቀጠለ ጉዳይ ነው። ሕገ መንግስቱ፣ "የብሔረሰቦችን ተወካዮች የክልል ምክር ቤቶች ይልካሉ፤ ወይም ምርጫ ይደረጋል" የሚል ሲሆን፣ "ነገር ግን ተግባራዊ እየሆነ ያለው ክልሎች ናቸው እየላኩ ያሉት፤ እስካሁን ባለው አሰራር" ያሉት ሰለሞን፣ በአንድ በኩል ይሄው አሰራር እንዲቀጥል የሚል ሀሳብ መቅረቡን ነግረውናል። በአንፃሩ ደግሞ፣ "እንደዚህ ሳይሆን ራሱ የብሔረሰብ/የማንነት ውክልና ስለሆነ ብሔረሰቡ ራሱ ምርጫ ያድርግ" በሚል መከራከሪያ መቅረቡን አቶ ሰለሞን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። በእነዚህ ሦስት ጉዳዮች የቀረቡ ሁለት፣ ሁለት የተለያዩ ምክሮች በቀጣይ በአስማሚ ጉባዔና በሽማግሌዎች ታይተው ወደ ስምምነት ለማምጣት እንደሚሰራ፣ ካልሆነ ወደ ድምፅ ብልጫ የሚያልፉ ጉዳዮች ሆነው መያዛቸው ታውቋል። በኮሚሽኑ መመሪያ መሰረት፥ 75% ድምፅ ያገኘ ሀሳብ ይጸድቃል፤ ከዚህ በታች ድምፅ ያላገኘ እንደገና እንዲያገኝ ተደርጎ 70% ካገኘ ይያዛል። https://t.me/journalistnetsanetgetachew

  • በ4 የሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎች ላይ መግባባት ተደረሰ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ ምክክር፣ 4 የሥራ ቡድኖች በተመካከሩባቸው ምክረ ሃሳቦች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን አሳውቋል። እነዚህም አጀንዳዎች፦ • የሃይማኖት ጉዳዮች • የሰላም ግንባታ • የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ስርዓት • ሙስናና መልካም አስተዳደር .... ጉዳዮች ናቸው። እያንዳንዱ አጀንዳ 500 ተሳታፊዎች ባሉት የሥራ ቡድን ሲመከር ቆይቷል። ቡድኖቹ በተጠናቀሩ የጋራ ምክረ ሀሳቦቻቸው ላይ ተስማምተው በቃለ ጉባኤ ሰነዶች ላይ በመፈራረም መግባባቱን አረጋግጠዋል። በቀሪዎቹ አጀንዳዎችም በቀጣይ ቀናት ተመሳሳይ ምክክርና የመግባባት ሂደት እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ ገልጿል። https://t.me/journalistnetsanetgetachew

  • በኢትዮጵያ በውርስ ወይም በስጦታ በሚገኙ ገቢዎች ላይ አዲስ የታክስ ዓይነት ሊጣል መሆኑ ተገለጸ።   ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የውርስና የስጦታ ገቢዎች ለዚህ ታክስ እንደሚዳረጉ ተመልክቷል።   ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የአምስተኛውን ዙር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ተከተሎ ይፋ ባደረገው ባለ 132 ገጽ ሙሉ ሪፖርት እንደጠቆመው፣ የአገሪቱ የታክስ መሠረት በጣም ጠባብ በመሆኑ መንግሥት በየዓመቱ የአገር ውስጥ ገቢውን ለማሳደግ አዳዲስ የታክስ ዓይነቶችን ለመተግበር አቅዷል።   በዚሁ ሪፖርት መሠረት በውርስና ስጦታ  ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ ታክስ ይጣላል።   በሲጋራ፣ በአልኮልና በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚጣለው ታክስ እንደሚጨምር የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም አገራዊ ገቢን ከመጨመር ባለፈ ለጤና ፖሊሲዎች አተገባበር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመልክቷል።   የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ በሰጡት አስተያየት፣ እነዚህ አዳዲስ የታክስ እርምጃዎች በአጠቃላይ በአገሪቱ ኢኮኖሚና በህብረተሰቡ ላይ ተጨማሪ ጫና ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።   ሆኖም መንግሥት አገራዊ ገቢውን ለማሳደግ ሲል ውሳኔዎቹን በቁርጠኝነት እንደሚተገብራቸው ይጠበቃል ብለዋል። https://t.me/journalistnetsanetgetachew