tgindex
ሃይማኖት አንድ ናት

ሃይማኖት አንድ ናት

Статистика

ኤፌሶን ፬ ፡፭አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።ይቀላቀሉ በዝክ ቻናል የአባቶች ምክርና ተግሳፅ ተለያዩ በሃይማኖት ዙሪያ ትምህርት አዘል ይለቀቃል ።

Последний пост
19 апр.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 682
−4 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 474
16 постов
Вовлечённость
55,0%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ◦ከትንሣኤ_እሁድ_በኋላ_ያሉ_ዕለታት_ስያሜ፡- ◦ሰኞ ማዕዶት_ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ◦ማክሰኞ ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 ◦ረቡዕ አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ ◦ሐሙስ አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ ◦አርብ ቅድስት_ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ ◦ቅዳሜ ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ ◦እሁድ ዳግም_ትንሣኤ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ የተሣተውን ✍️ ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት ✍️ ✔️ ❤️ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ❤️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ለመቀላቀል 👇       ┏━━° •❈• ° ━━┓        @haymanotanednat @haymanotanednat       ┗━━° •❈• ° ━━┛

  • 10 апр.8 27711

    ❖ #አርብ #ዘጠኝ #ሰዓት(ጊዜ ተስዓቱ ስዓት)ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በገዛ ስልጣኑ የለየበት ስዓት።  በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ። ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ?  ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? ማለት ነው፡፡ ነብስኑም በገዛ ፈቃዱ ሰጠ ✞ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስራ ሦስት ሕማማተ መስቀል ከተቀበለ በኋላ የሰው ልጅ ያጣውን ሕይወት በሞቱ ለመካስ መራራ ሞትን በፈቃዱ ተቀበለ፡፡ ነቢዩ ኢሳኢያስ ‹‹እግዚአብሔር የሁላችንን በደል በርሱ ላይ አኖረ ✞ ተጨነቀ፣ተሰቃየ፣አፉንም አልከፈተም ለመታረድም እንደሚነዳ ጠቦት በሸላቾች ፊት ዝም እንደሚል በግ እንዲሁ አፉን አልከፈተም ከኃያላን ጋር ምርኮን ይካፈላል ነፍሱንም ለሞት አሳልፎ ሰጥቷልና፡፡››ኢሳ52፤6-12/ (ማቴ.27፥50፣ ማር .15፥34፣ ዮሐ.19፥31) ❖ #አርብ #አስራ #አንድ #ሰዓት(ጊዜ ሠርክ)፡- የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ። ቅዱስ ሥጋው ከመሰቀል ወደ መቃብር የወረደበት ስዓት ✞ ከዓለት በወቀረው በአዲሱ መቃብርም አኖረው፥ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ። (ማቴ.27፥60) ☞ ሠርክ በሆነ ጊዜ ምዕመናን በአንድነት እግዚኦታውን በአንድ ላይ ከካህናት ጋር ካሉ በኋላ ወደቄሱ እየቀረቡ ስግደት እዲሰጣቸው ይጠይቃሉ፡፡ ቄሱም በወይራ ቅጠል እየጠበጠበ ቀን ሲሰግዱ ከዋሉት ሌላ ተጨማሪ ስግደት ይሰጣቸዋል፡፡ ጥብጣቤው የጌታችን መስቀሉ ነው፡፡ ወይራ መሆኑ ወይራ ጹኑ እንደሆነ የጌታችን መከራ መስቀሉ ከባድ መሆኑ ለማስታወስ ነው፡፡ በስተመጨረሻ ንሴብሆ ተብሎ በሊቃውንት የአርብ ስግደት ይፈጸማል፡፡ ✝️እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም✝️ ✝️አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ✝️   ✝️ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር✝️         ✝️በፍስሐ ወበሰላም:: አሜን፡፡✝️ የተሣተውን ✍️ ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት                               ✍️     ✔️ ❤️ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ❤️ ለመቀላቀል   👇       ┏━━° •❈• ° ━━┓    @haymanotanednat @haymanotanednat

  • Channel photo updated

  • 🕊                        💖                       🕊                     [     ላሐ ማርያም [  የማርያም ለቅሶ  ]      ════════════════ የእመቤታችን ለቅሶ ሰማይን ስቅጥጥ ፣ ስቅጥጥ  አደረገው፡፡ ምድርን አንቀጠቀጠ፡፡ ባሕሩን አነቃነቀ ፡፡ ሐዋርያትን ሦስት ቀን አስለቀሰ፡፡ የለቅሶውም ድምጽ ሰውነታቸውን እንደ ሰም አቀለጠ፡፡ ❝ ልጄ ፡ ሆይ ከዚህ ፡ ካገኘህ ፡ የሞት ፡ ፃዕር ፡ የተነሣ ፡ ግፌን የሚመለከትልኝ ፡ ሹም ፡ ወይም ፡ በሐዘን ፡ የተሰበረውን ፡ ልቤን ፡ አይቶ ፡ በማስተዋል ፡ የሚፈርድልኝ ፡ ዳኛ ፡ አላገኘሁም። ❞ ላሐ ማርያም [  የማርያም ለቅሶ  ]    ▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬                            †††                ✟𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y✟ @haymanotanednat @haymanotanednat

  • ✝ ሞትህን እንናገራለን ✝ ( 1ቆሮ.11፡26 ) የማይታመም ታመመ፤ የማይያዝ ተሰቀለ፤ የማይሞተው ሞተ ፡፡ ፍቅር አስገድዶት! ወዮ! ሕማም የሌለበት የእርሱን ሕማሙን እንናገራለን፤ ሞት የሌለበትን የእርሱን ሞቱን እንናገራለን፡፡ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በተቀመጠበት በዚያች ሌሊት /ምሴተ ሐሙስ/ በአባቱ ፈቃድ በራሱም ፈቃድ የገዛ ራሱን ነፍስ ለሞት አሳልፎ ሰጠ፡፡ ሁሉንም የሚይዘውን ጌታ ያዙት፤ ሁሉንም ለሚገዛው ጌታ አሠሩት፤ ሕያዉ የእግዚአብሔርን ልጅ የኋሊት አሠሩት፡፡ እነርሱ በቁጣ ጐተቱት፤ እርሱ ግን በፍቅር ተከተላቸው፡፡ በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግም አፉን ሳይከፍት ተከተላቸው፡፡ ሊቃነ መላእክት በፍርሐትና በመንቀጥቀጥ በፊቱ የሚቆሙለትን እርሱን በፍርድ አደባባይ አቆሙት፤ ኃጢአትን ለሚያስተሠርይ እርሱን “ኃጢአተኛ ነህ” አሉት፤ በመኳንንቱ ላይ የሚፈርድ እርሱን “ይሙት በቃ” ብለው ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድን በሚደፋላቸው በእርሱ የእሾኽ አክሊል ደፉበት፤ ለኪሩቤል ግርማን ለሚያለብሳቸው ለእርሱ ለመዘበት ቀይ ግምጃን አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፋቸው ተሸፍነው ለሚሰወሩለት ለእርሱ ክፉ ባርያ እጁን አክርሮ ፊቱን በጥፊ መታው፤ ሠራዊተ መላእክት እየፈሩ በፊቱ ለሚሰግዱለት ለእርሱ እያፌዙ በፊቱ ተንበረከኩ:: እንዲህ ያለ ትሕትና እንደምን ያለ ትሕትና ነው? እንዲህ ያለ ትዕግሥት እንደምን ያለ ትዕግሥት ነው? ይህን ያህል አርምሞስ እንደምን ያለ አርምሞ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ይህን ያህል ሰውን መውደድስ እንደምን ያለ ፍቅር ነው ? ፍቅር ለወልድ ከመንበሩ ሳበው፤ እስከ ሞትም ድረስም አደረሰው፡፡ ኃጢአት የሌለበት ጌታን “ኃጢአተኛ ነህ” ብለው ሰቀሉት፡፡ ሕይወትን የሚሰጥ እርሱ ከወንበዴዎች ጋር ሰቀሉት፡፡ አቤት! አዳምን የፈጠሩ እጆች በችንካር ተቸነከሩ፡፡ በገነት የተመላለሱት እግሮች በሚስማር በመስቀል ላይ ተቸነከሩ፡፡ በአዳም ላይ የሕይወትን እስትንፋስ እፍ ያለች አፍ ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ ሆምጣጤ ጠጣች፡፡ አቤት! የጌታን መከራ ሊናገር የሚችል ምን አፍ ነው? ምንስ ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የተወደደውን የወልድ መከራ ሲነገር ልብ በሐዘን ይከፈላል፤ ናላ ይዞራል፤ ነፍስ ትርዳለች ትንቀጠቀትማለች፤ ሥጋም ትደክማለች፡፡ #ሞት_የማገባው_እርሱ_ሞተ! #ሞትን_ይሽረው_ዘንድ_ሞተ! #ሙታንን_ያድን_ዘንድ_ሞተ! ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE    @haymanotanednat @haymanotanednat

  • 7 апр.1 5537

    በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸ ሥርዓቶች 1, ስግደት :- በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል። 2, ጸሎት :- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው። በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ። 3, ጾም :- በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል። 4, አለመሳሳም :- አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29 5. አክፍሎት :- እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው። 6, ጉልባን :- ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው። 7, ጥብጠባ :- ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው። 8, ቄጠማ :- ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን። እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

  • 6 апр.1 45112

    ✨✨✨🌿✨🌿✨🌿 በሰሙነ ሕማማት ይህንን አድርጉ በሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ ሰሙነ ሕማማት አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ቤዛ ሆኖ ተላልፎ መሰጠቱን የምናስታውስበት ሳምንት ነው። ይህንን ምክንያት በማድረግ የሥርዓት ለውጥ ሲደረግ ሲመለከቱ ግራ የሚጋቡና ሥርዓተ አምልኮውን በሚገባ ከመከታተል ይልቅ ሥርዓት የጣሱ እየመሰላቸው የሚጨነቁ ስላሉ ልናደርገው የሚገባንን እጽፍላችኋለሁ። 1. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ ፊትንና መላ ሰውነትን በትዕምርተ መስቀል {በመስቀል ምልክት} ማማተብ አይከለከልም። ከካህን እጅ ቡራኬ አንቀበልም በካህኑ እጅ ያለውን መስቀል አንሳለምምና ማማተብም የለብንም በሚል ፍልስፍና ካልሆነ ማማተብ ክልክል ነው ተብሎ የተጻፈበት ቦታ የለምና። 2. የሚከለከል ጸሎት የሌለ መሆኑን አውቃችሁ ያስለመዳችሁትን ጸሎት በትጋት ጸልዩ። መሥዋዕት ካለመሠዋታችን ቅዳሴ ካለመቀደሳችን በቀር በዚህ ሳምንት ከብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ጀምሮ እስከ ሊቃውንት ድርሳናት ድረስ በቤተ ክርስቲያን የማይጸለይ ጸሎት የለምና። 3. ሰላምታ መስጠት ከጸሎተ ሐሙስ ዕለት በቀር አልተከለከለም፤ እሱም ቢሆን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በይሁዳ ሰላምታ ተላልፎ መሰጠቱን ለማስተዎስ እንጅ ሌላ የተለየ ምክንያት ስለሌለው በመርሳት ወይም በሌላ ከድፍረት በተለየ ምክንያት ሰላምታ ያቀረበላችሁን ሰው ልታስደነግጡና ትልቅ ኃጢአት እንደሠራ አድርጋችሁ ልታስጨንቁት አይገባም። 4. “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ” ብሎ መጻሕፍትን ማንበብ ወይም ሌላ ሥራን መጀመር ይቻላል። ስመ እግዚአብሔር መጥራት የምንከለከልበት ጊዜ መቸም የለምና። 5. የጌታችንን ሕማሙንና ሞቱን የሚያስታውሱ መጻሕፍትን በማንበብና በመስማት ጊዜአችንን መወሰን ይገባናል። 6. በዚህ ሳምንት ተድላ ደስታን ሲያደርጉ መገኘት ከአይሁድ ጋር እንደ መተባበር የሚያስቆጥር ስለሆነ አብዝቶ በመብላትና በመጠጣት፣ ያማረውንና ጌጠኛውን ልብስ በመልበስ፣ ባልና ሚስት በምንጣፍ በመገናኘት እንዲሁም በልዩ ልዩ ምክንያት ከምናደርጋቸው ተድላ ደስታዎች መራቅ ይገባናል። ቅዱሳን በዘመናቸው ሁሉ ባሰቡት ጊዜ የሚያስጨንቃቸውን የክርስቶስን መከራ እያሰብን ለጥቂት ጊዜም እንኳን ቢሆን የክርስቶስን መከራ በሰውነታችን ማሰብ ይገባናል። የተቻለው እንደ ጴጥሮስ የራሱን ኃጢአት እያሰበ እንደ ማርያም መግደላዊት የክርስቶስን ሞት እያዘከረ ሊያለቅስ ይገባዋል። በወዲያኛው ዓለም ከማልቀስ የሚያድነን ዛሬ የራሳችንን ኃጢአት አስበን የክርስቶስን ሞት አዘክረን የምናለቅሰው ለቅሶ ነው እንጅ ዛሬ ከተደሰትን ደስታችንን በዚህ ዓለም ማድረጋችን አይደለምን? 7. በተቻለን መጠን በቤተ ክርስቲያን መዋል ይገባናል፤ ሕማማተ መስቀልን የሚያስታውሱ መጻሕፍት የሚነበቡበት ሳምንት ስለሆነ ነው። ነገር ግን በልዩ ልዩ ምክንያት በቤተ ክርስቲያን መዋል እንኳን ባይቻላችሁ ባላችሁበት ቦታ ሁናችሁ እየዋሻችሁ በሐሰት የከሰሱትን፣ እየቀማችሁ ልብሱን የገፈፉትን፣ ሰው እየደበደባችሁ በጅራፍ የገረፉትን፣ በወንድሞቻችሁና በእኅቶቻችሁ ላይ እየፈረዳችሁ በክርስቶስ ላይ የፈረዱበትን፣ በሰዎች ላይ እየተዘባበታችሁ የተዘባበቱበትን፣ በሳቅና በሽንገላ ሰውን እየሸነገላችሁ ሽንገላ በተሞላበት ሰላምታ ጌታውንና መምህሩን አሳልፎ የሰጠ ይሁዳን ልትመስሉ አይገባም። ይልቁንም በአይሁድ እጅ ተላልፎ ቢሰጥም ንጹሓ ባሕርይ መሆኑን በማመን እስከ ቀራንዮ የተከተሉትን ደቀመዛሙርት ልትመስሉ ይገባል። እግራችሁ በመቅደሱ ውስጥ ባይቆምም ልባችሁን ከመቅደስ ልታወጡት አይገባም። እያዘናችሁ ባላችሁበት ቦታ ዋሉ። 8. በቤታችሁም ሆነ በቤተ ክርስቲያን አብዝታችሁ ስገዱ። ስለሁላችንም ቤዛ የሚሆን ክርስቶስ በፊታችን መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ እያያችሁት ትቆማላችሁን? አይሁድ ገፍተውት አንድ ጊዜ ወደ ምድር በወደቀ ጊዜ ለወደቀው መውደቅ ዘመናችንን ሙሉ ብንወድቅ ብንነሣ ውለታ መክፈል እንችል ይመስላችኋል? ቅዱሳን ሳያቋርጡ ሲሰግዱ የሚኖሩት ክርስቶስ በፊታቸው በአይሁድ እጅ እየተገፋ መስቀሉን እንደተሸከመ ሲወድቅ በዓይነ ሕሊናቸው ስለሚያዩት ነው። በስንክሳር ተጽፎ የምናገኘው ዜና ሞታቸው እየሰገዱ ሳሉ ሞት ነፍሳቸውን ከሥጋቸው ለይቶ እንደሚወስዳትና ለስገደት ታጥቀው እንደተንበረከኩ እንደሚገኙ ይነግረናል። የተሰቀለውን ክርስቶስን የሚያስብ ሰው ለሰውነቱ ዕረፍትን አይሻም። 9. ከሁሉም ሰው ጋር ፍቅርን አድርጉ። ሰውን ለመውደድ ምክንያት አታብጁ። ክርስቶስ አሳልፎ የሰጠውን ይሁዳን “ወዳጄ” ብሎ ሲጠራው አትሰሙትም? እግዚአብሔርን አንተን ያለ ምክንያት እንደ ወደደህ አንተም ያለ ምክንያት ሰውን መውደድ ልመድ። ክርስቶስ አንተን ጠላቱ ሆነህ ሳለ ፍቅርን ካላጎደለብህ ለጠላትህ ፍቅርን አታጉድልበት። ክርስቶስ ይሁዳን ‘’ወዳጀ’’ ብሎ ከጠራው አንተም ይሁዳዎችህን ወዳጀ ብለህ ጥራቸው። አውቃለሁ ጠላትን መውደድ መራራ ሐሞትን ከመጠጣት በላይ መራራ ነው። ነገር ግን እኔም ለይሁዳዎቻችን ፍቅርን እንስጥ ማለቴ መራራ ሐሞት የጠጣ ክርስቶስን እንድንመስለው ነው። 10. ለሁሉም መስጠት በምትችሉት መጠን ስጡ እንጅ አትቀበሉ። ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነውና በመስጠታችሁ ብፁዓን ተብለው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገቡት ትቆጠራላችሁ። ምናልባትም የምትሰጡት ገንዘብ ባይኖራችሁ ዕዳ ይሆንባችሁም ቢሆንም ገንዘብ ለሰጧችሁ ባለጠጎች የምትሰጡት ጸሎት ሊኖራችሁ ይገባል። ከምንጊዜውም የበለጠውን ስጦታ የተቀበልንበት ሳምንት መሆኑን እያሰባችሁ አንዳች የምጸጡት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ስጦታ የሌላችሁ ባዶዎች እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። ✨✨🌿 ከሁሉ በላይ የሆነውን ስጦታ የጌታን ሥጋና ደም እነሆ ተቀብለናል። ክርስቶስ መድኃኒነ መጽአ ወሐመ በእንቲአነ ወበሕማማቲሁ ቤዘወነ‼ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሊቃውንት ጉባዔ ሰብሳቢ የዐራቱ ጉባዔያት ምስክር መምህር ✨✨✨🌿✨🌿✨🌿

  • ‟ ሕማማት"... "ሕማማት" የሚለው ቃል የግዕዝ ቃል ሲሆን፣ ትርጉሙም "መከራ"፣ "ሥቃይ" ወይም "ሕመም" ማለት ነው። በተለይም በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ "ሰሙነ ሕማማት" ተብሎ የሚጠራው፣ ከሆሳዕና ማግስት (ሰኞ) ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ዋዜማ (ቅዳሜ) ያለውን የአንድ ሳምንት ጊዜ ነው። ይህ ሳምንት የሚከተሉት ዋና ዋና ትርጉሞች አሉት፦...... 👉የመከራ መታሰቢያ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል የተቀበላቸው ልዩ ልዩ መከራዎች (ግርፋት፣ መገፋት፣ እስከ መስቀል ሞት ድረስ) የሚታሰቡበት ነው። 👉የጾምና የጸሎት ጊዜ፦ አማኞች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በከፍተኛ ጾም፣ በስግደት እና በጸሎት የሚያሳልፉት፣ የክርስቶስን መከራ በኅሊናቸው የሚያሳስቡበት ወቅት ነው። 👉የሥርዓተ አምልኮ ጊዜ፦ በዚህ ሳምንት በቤተክርስቲያን ልዩ የሆኑ የጸሎት መጻሕፍት (ለምሳሌ ግብረ ሕማማት) ይነበባሉ፤ ካህናትና ምዕመናን ጥቁር ልብስ በመልበስ ሐዘናቸውንና መከራውን ያስባሉ። በአጭሩ "ሕማማት" ሲባል የሰው ልጅ ከኃጢአት ነጻ እንዲወጣ የተከፈለውን መከራና ዋጋ የሚያመለክት መንፈሳዊ ቃል ነው።

  • Channel photo updated

  • 🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼🌼       🌼🌼HAPPY NEW YEAR🌼🌼

  • ድንግል ሆይ ነይ በሱባኤ (በእንተ ጾመ ፍልሰታ) . . . ምድሩ ለምለሙን ለብሶ  - ውበቱ እንደደመቀ ፏፏቴው ጉልበት አግኝቶ - ሞገሱን እንደታጠቀ አበቦች ሊፈኩ ቋምጠው - ክረምቱን እያቻኮሉ ያችን  የ’አበባዮሽ’ን ቀን - በተስፋ ነይ እያሉ ሊጣሩ ባሰቡ  ጊዜ - አፋቸው ቅያሱን ሰራ “ነይ!”  ድምጹን ከፍ አርጎ - ድንግል ማርያምን ጠራ፡፡ ድንግል ሆይ ነይ በሱባኤ - ገበሬው ተስፋው  ባረገሽ መምጫሽን  ለሚጠባበቅ - እረኛው ሽቅብ እያየሽ የኃምሌው ነጎድጓድ አልፎ - የክተት መለከት ነፊ የንግስቲቷን መምጫ - ከደመና ላይ ሆኖ - አዋጁን ለህዝብ ለፋፊ ክተቱ እንደ ተሰማ - ለምክንያተ ክልኤ ድንግል ሆይ ነይ በሱባኤ፡፡ እዪአት ኢትዮጵያ ቤትሽን - ያለች ስትጠባበቅ ትመጪሽን አስባ - ክረምቱን ለምትናፍቅ ተመልከች ቤተመቅደሱን - ቅጽሩ በህዝብ ተሞልቶ የጎረፈው ሊያይሽ - ያንን ክተቱን ሰምቶ የሚጠቡት ህጻናት - ወተቱን ካንቺ ይሻሉ የሚሯሯጡ ልጆች - “ድንግል”  “ድንግል” ይላሉ የዛለች የአዛውንት ጉልበት -  ባንቺ ልታደስ ብላ ሌቱን ደጅሽ ታድራለች- ቀኑን በደጅሽ ውላ የርህራሄ እናት - ወትረ ድንግል በክልኤ እንዲህ ለሚማጸኑሽ - ድንግል ሆይ ነይ በሱባኤ፡፡ ሁሉም ከቤቱ ወጥቶ - አንቺን ፍለጋ ሲሸሽ በገዳም ተጠግቶሽ - እየተጣራሽ ሲያመሽ አፉን ጥፍጥና ይዞት - ቃሉን በደጋገመ ከምስጢር ባህር ገብቶ - ተደንቆ ባረመመ መናኙ ልጅሽ በልቡ - በሕሊናው እንደ ሳለሽ በማህሌቱ ዜማ - በብርሃን ዓምድ እያየሽ አይቶም እንዳለቀሰ - ሐሴት  ተሞልታ ነፍሱ በመሻት የተግባር ጉዞው- በቶማስ መግነዝ ውርሱ ከውዳሴሽ ባህር ውስጥ - ገብቶ እንደሚዋኘው ከምስጢር ከፍታ በላይ - ከፍ ብሎ እንደሚቀኘው እንደሚደነቅ ሕይወት - እንደ ቅዱሳን ጉባኤ ድንግል ሆይ ነይ በሱባኤ፡፡ @haymanotanednat @haymanotanednat

  • 🕊 † እንኳን ለቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † †  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !  † †  🕊 ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም  🕊 † † ቸር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው:: ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ ጽድቅ መድረስ አይቻልም:: ይቅርና እኛ ክፉዎቹ የሰማይና የምድር ፈጣሪ: የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ጾምን ነው:: ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፯ [ 7 ] አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ: በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች:: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው:: "ፈለሠ" - ሔደ: ተጉዋዘ እንደ ማለት ሲሆን "ፍልሠታ" ማለት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው:: እመ ብርሃን በዚህ ዓለም ለ ፷፬ [64] ዓመታት ኑራ ካረፈች በሁዋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም:: ለጊዜው በዕጸ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና:: ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው:: ከ፯ [7] ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት:: ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል:: - የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ: ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ:: - ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን: በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን: በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ:: - የኔ ብጤ ደካማ ደግሞ ጠዋት ማታ ወደ ደጇ እየተመላለሰ "አደራሽን ድንግል" ይላታል:: † በእርሷ አምነን አፍረን አናውቅምና ነጋ መሸ ሳንል እንማጸናታለን:: † ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ልበለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን:: - ጾሙን የፍሬ: የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን:: †  🕊 ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ  🕊 † † እጅግ የተወደዱ: ሞገስ የሞላላቸውና ፈጣሪያቸውን በክብር ገንዘው የቀበሩ አባቶች ናቸው:: †  🕊  ቅዱስ ዮሴፍ ዘአርማትያስ  🕊 † † ቅዱሱ በእሥራኤል ምድር ተወልዶ ያደገ: ኦሪትን የተማረ ባለጠጋ ሰው ነው:: የተማረ ደግ ሰው ነውና የክርስቶስን መምጣት በተስፋ ይጠብቅ ነበር:: ባገኘውም ጊዜ በአዳኝነቱ [በመሲህነቱ] አምኖ በስውር ተከታዩ ነበር:: †  🕊   ቅዱስ ኒቆዲሞስ   🕊  † † ወንጌል እንደሚነግረን ይህ ሰው የአይሁድ አለቃ: መምሕር: ዳኛ እና ሃብታም ሰው ነበር:: እነዚህ ሁሉ ማነቆዎች ግን እርሱን ከፈጣሪው ሊያስቀሩት አልቻሉም:: ሌሊት እየመጣ ከጌታችን እግር ይማር ዘንድም አድሎታል:: በመካከልም ከአይሁድ ጋር ብዙ ተጋጭቷል:: ሁለቱ አባቶች መድኃኒታችን ስለ እኛ ሲል ሞቶ ባለበት ሰዓት ላይ በእርሱ የደረሰ ይደርስብናል ሳይሉ በድፍረት ሥጋውን ከዺላጦስ ተካሠው ለመኑ:: እንባቸው በፊታቸው እየወረደ ከመስቀል አውርደው በዮሴፍ በፍታና በኒቆዲሞስ ሽቱ ገነዙት:: እንዲህ እያሉ :- "ሙታንን የምታስነሳ ጌታ አንተ ሞትክን?! ደካሞችን የምታጸና ቸር አንተ ደከምክን?!" - በዚያች ሰዓት ጐልጐታ አካባቢ ዝማሬ መላእክትን እየሰሙ የክብር ባለቤትን ቀብረውታል:: ጌታችንም ከተነሳ በሁዋላ በንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: "እየሳማችሁ አክብራችሁ እንደ ገነዛችሁኝ እኔም በሰማይ በእንቁ ዙፋን ላይ አስቀምጣቹሃለሁ" ብሏቸዋል:: "አነ አብረክሙ ዲበ መንበረ ሶፎር" እንዲል:: ጻድቃን አበው ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በተረፈ ዘመናቸው ወንጌልን ሰብከው: ከአይሁድ መከራን ታግሰው: በበጐ ሽምግልና ዐርፈዋል:: †  🕊  ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት  🕊  † † ቅዱስ አቦሊ የሰማዕታቱ ቅዱስ ዮስጦስና  ቅድስት ታውክልያ ልጅ ሲሆን በ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን ያበራ የቤተ ክርስቲያን ዕንቁ ሰማዕት ነው:: የሚገርመኝ ሦስቱ የግማሹ ዓለም አስተዳዳሪዎች ነበሩ:: ዮስጦስ ንጉሥ: ታውክልያ ንግሥት: አቦሊ ደግሞ ልዑል ነው:: ነገር ግን ይህንን ክብራቸውን በክርስቶስ ፍቅር ጐን: ሚዛን ላይ ቢያኖሩት በጣም ቀሎ ታያቸው:: ፫ [3]ቱም ከዙፋናቸው ወርደው: ወገባቸውንም ታጥቀው: ባሮቻቸው በነበሩ ሰዎች ስለ ክርስቶስ ብዙ ተንገላቱ:: መራራ ሞትንም ታገሱ:: በተለይ ቅዱስ አቦሊ ከአንጾኪያ ወደ ግብጽ [ብስጣ] ይዘው አምጥተው ክርስትናውን እንዲተው ያላደረጉት የለም:: በቁሙ ቆዳውን ገፈው: በቆዳው አቅማዳ ሰፍተው: ያንንም አሸክመው: የተገፈፈ አካሉን ጨውና ኮምጣጤ እየቀቡ አዙረውታል:: እርሱ ግን ጌታ በላከለት ድንቅ መልአክ  ቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ሁሉን ችሎታል:: በዘመኑ ብዙ ተአምራትን የሠራ ሲሆን አንድ ጊዜ ቤት ተንዶ ፲፮ [16] ሰዎች ቢያልቁ የተገፈፈ ቆዳውን እየጣለባቸው ተነስተዋል:: በተአምራቱና በተጋድሎውም ብዙ ሺህ አሕዛብን ለክርስትና: ብሎም ለሰማዕትነት አብቅቷል:: እርሱም ከብዙ የመከራ ጊዜያት በሁዋላ በዚህች ቀን አንገቱን ተከልሏል:: ጌታችን "ዜናሕን የጻፈውን: ያነበበውንና የሰማውን ይቅር እለዋለሁ" ብሎ ቃል ኪዳንን ሰጥቶታል:: † ፈጣሪ ከጻድቃንና ሰማዕታት በረከትን አይለይብን:: ወርሐ ነሐሴንም ለበረከት ይቀድስልን:: [   † ነሐሴ ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ] ፩. በአተ ጾመ ፍልሠታ ፪. አበው ሐዋርያት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ፫. ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት ፬. ታላቁ ቅዱስ ዸላሞን ገዳማዊ ፭. ቅድስት ሐና [የእመ ብርሃን እናት] ፮. ቅድስት ሐና ነቢይት [ወለተ ፋኑኤል] ፯. ደናግል ቅዱሳት [የንግስት ሶፍያ ልጆች] [   †  ወርኀዊ በዓላት    ] ፩. ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ ፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ፫. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት ፬. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ ፭. ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር † " የጌታ ኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ዺላጦስን ለመነ:: ዺላጦስም ፈቀደለት:: ስለዚህም መጥቶ የጌታ ኢየሱስን ሥጋ ወሰደ:: ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ:: የጌታ ኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት::" † [ዮሐ.፲፱፥፴፰] (19:38) † " በጽዮን መለከትን ንፉ:: ጾምንም ቀድሱ:: ጉባዔውንም አውጁ:: ሕዝቡንም አከማቹ:: ማሕበሩንም ቀድሱ:: ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ:: ሕጻናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ:: ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ::" † [ኢዩ.፪፥፲፭] (2:15) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖

  • Channel photo updated

  • መንገዷን ሰውራ የምታስተውን (ግራ የምታጋባውን) መድኃኒት ልጇን ተወልዳ አይታ በደስታ አነባች፡፡ የፍጥረት እናትና አባት የሆኑ አዳምና ሔዋን ልጃቸውን እናታችን፣ ካሳችን፣ መድኃኒታችን፣ ሰማያችን ተወለደች እያሉ ሲደሰቱነ ሲያመሰግኑ ልጆቻቸውም ከእነርሱ ጋር የባሕርያችን መመኪያ የድኅነታችን ቀርን ዛሬ ተወለደች እያሉ ተደሰቱ፡፡ ከአንድ ከዲያብሎስ በቀር ሁሉም ደስ አላቸው፡፡ እርሷም  በኋላ እንኳን የቀደመው የኋላው ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል አለች፡፡ እንግዲያስ በእርሷ መወለድ እንደ ዲያብሎስ አይክፋን፤ ይልቁንም የፍጥረት ሁሉ አባትና እናት እንደሆኑት እንደ አባታችን አዳምና እንደ እናታችን ሔዋን፣ እንደ ነቢያትና አበው ሁሉ አብረን ደስ ይበለን፡፡ እንኳን ደስ አለን፤ ዛሬ የባሕርያችን መመኪያ፣ ሰማይ የደረሰችው መሰላል፣ እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር ሆኖ  አማኑኤል ተብሎ ከእኛም ጋር እንዲሆን ምክንያት የሆነችልን የእመቤታችን ልደት የእኛም የሁላችን ልደት ነውና፡፡ ሰማይ የደረስሽው መሰላል፣ ከምድር ባሕርያችን የተሠራሽ ሰማይ ሆነሽ የጽድቅ ፀሐይን ያወጣሽልን ሰማይ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ዛሬም የዲያብሎስ ግሣት የሆነውን ኮረና ዘረኝነትን፤ ኮረና መለያየትን እና ኮረና ርኩሰትን ለተግሣጽ ከተላከለን ለጊዜውም ቢሆን ካስደነገጠን ኮረና ቫይረስ ጋራ አንድ ላይ አስወግጅልን፡፡ የባሕርያችን መመኪያ ሆይ ለአጋንንትና ለመናፍቃን መሳለቂያ አታድረጊን፡፡ በእኛ ጉድለት ምክንያት ታመነውባት አፈሩ፣ ተማጽነውባት መልስ አጡ እያለ ዝንጉዎችን እንዳያጠራጥር ቸሪቱ አማላጂቱ ሆይ በልደትሽ ስላስደሰትሻቸው ከሐፍረትና ከውረደትም ስላዳንሻቸው እናትና አባትሽ ስለኢያቄምና ስለሐና ፣ ስለአዳምና ሔዋን ብለሽ ድረሽልን፡፡ በእሥራኤል ትውፊት እሥራኤል በተጨነቁ ቁጥር ራሔል ስትጮህ ይሰማቸው እንደነበረ ዛሬም አንቺ ከጮሕሽ ልጅሽ ይምራልና በእውነት ይቅር ይለን ዘንደ ለምኝልን፤ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡ በክርስትናው ለሚያምን ሁሉ እንኳን ደስ አለን፤ እንኳንም ለእናታችን ልደት ለሁላችንም የጋራ የልደት በዓል አደረሰን፡፡ © ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ

  • Kesis Getnet Aytenew: የፍጥረት ሁሉ ደስታ - ልደታ ለማርያም ግንቦት አንድ ቀን የእመቤታችን የንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት ስለሆነ የደስታችን ቀን ነው፡፡ የቀደሙ አባቶቻችን ሁሉ በፍጹም ደስታ ያሳለፉት ቀን ነው፡፡ የልደቷ ቀን የሐና የደስታ ዕለት ነበር፤ "አንች ያልወለድሽ መካን ሆይ ደስ ይበልሸ የሚለውን ቃል ሰምታበታለችና" /ኢሳ 54፤1/፡፡ የልደቷ  ቀን የኢያቄም የደስታ ዕለት ነበር፡፡ ከዕሴይ ግንደ በትር ይወጣል /ኢሳ 11፤1/ የሚለው ቃለ ነቢይ በውድ ልጁ ሲፈጸምና በበትሩ ሠራዊተ አጋንንትን ሲርቁ አይቷልና፡፡ በእርሷ ልደት ነቢያት ሁሉ ተደስተዋል፡፡  ትንቢታቸው ፍጻሜ ሲደርስ ፤ የንባባቸው መንፈሰ ሲገለጥ፣ ሕግ ለጸጋ፣ ኦሪት ለወንጌል ሊያስረክቡ፣ ነገደ ሌዊ ሊቀ ካህንነቱን ለነገደ ይሁዳ ሊያስረክብ ሲሰላለፉ አይተዋልና፡፡ የእርሷ ልደት የያዕቆብ ፍጹም ደስታ ነበረ፡፡ በሕልሙ ከመሬት እስከ ሰማይ ተዘርግታ ያያት መሰላል በእውን ከምድር ወደ ላይ በቅድስና  ስትደርስ ለማየት በቅቷልና፡፡ ራስዋ ላይ እግዚአብሔር የተቀመጠባት እውነተኛዋ መሰላላችን በርግጥም ድንግል ማርያም ናት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የሴት ሁሉ ራስ ወንድ ነው/1ኛ ቆሮ 11፤1/ አለ፡፡ የእርሷ ራስ ግን ያዕቆብ እንዳየው እግዚአብሔር ነው፡፡ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል ያለችው ቅዱስ ጳውሎስ የሴት ሁሉ ራሰ ያለው ወንድ በእርሷ ዘንድ ስላልነበረ ነውና፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ልዩ መሆኗን ስለሚያውቅ አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ የተባረክሽ ነሺ፤ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ጽንስሽም እንደ ሌሎቹ ሴቶች አይደለም እያለ ሲሰግድላትና ሲያመሰግናት እርሱን አልፋ ለእግዚአብሔር መቀመጫ ዙፋን ማደሪያ መቅደስ መሆኗን ያየው አባታችን ያዕቆብ በእውነት ደስ አለው፡፡ አብርሃም ልጁን ይስሐቅን የተቤዠለትን አማናዊ በግ ይዛለት የምትወርደውን ዕፀ ሳቤቅ ተወልዳ አይቶ ደስ አለው፡፡ እርሷ ስትወለድ ያች ያያት ቀን መድረሷን አውቆ ፍጹም ደስ አለው፡፡ ይስሐቅም ከታሰረበት ያስፈታችውን ስለእርሱ ፋንታ ቤዛውን ይዛለት ከች ያለችውን ስትወለድ አይቶ በደስታ ቃል ዘለለ፡፡ ከሲኦል እስራት የሚፈታበት ቀንም እንደ ደረሰ በእርሷ ልደት ደወሉን ሰምቷልና ፈነደቀ፡፡ ሙሴ በእርሷ ልደት በደስታ ብዛት ቦረቀ፡፡ ከሩቅ ያያት የማትቃጠል ቁጥቋጦ በሐና ጭን ቁጭ ብላ ሲያይ እንደገነና ወደ እርሷ ሊገሰግስ ወደደ፤ ያኔ ጫማህን አውልቅ ያለውን ድምጽ አቃጨለበትና ባለበት ቆሞ ያያት ጀመር፡፡ ሲያያት ሕብረ ብዙ ሆና አስደነቀችው፡፡ ኦሪትን በሥነ ፍጥረት ሲጀምር በሁለተኛው ቀን ሰኞ እግዚአብሔር ከውኃ ጠፈር ያለውን ሰማይ እንዳሳየው ዛሬ ደግሞ ከመሬት አዳም የተወለደችውን ድንግል አዲስ ሰማይ ሁለተኛ ሰማይ አድርጎ ሲያሳየው ተገረመ፡፡ ያኛው ሰማይ ለዚህ ዐለም ፀሐይ ሲዘጋጅ ወደ ኋላ እንዳየ አሁን ደግሞ የአማናዊው የጽድቅ ፀሐይ መውጫ ስትወለድ ፀሐዩን ሊሞቅ ጊዜው መድረሱን አይቶ ተደሰተ፡፡ እንደገና ሲያያት ደግሞ አሁንም ሕብሯን ለውጣ ታየችው፡፡ ምደር ከመረገሟ በፊት ያለ ዘር ዕፀዋት አዝርእትን ስታበቅል አይቶ የነገረን ሙሴ ከእናቱ ከሔዋን ልጆች ሆና መርገም ያላረፈባት ያለወንድ ዘር የሕይወት እንጀራ ሆኖ የሚሰጠውን ፍሬ የምታስገኘውን አማናዊት ገራኅተ ሠሉስ አይቶ እንደገና አደነቀ፡፡ ሙሴ ከተመስጦ አልተመለሰም፡፡ መንፈስ ቅዱስን እንደ ጣት አድርጎ በጽላት ላይ ቃሉን ጽፎ የሰጠው እርሱ አካላዊ ቃል ሰው ሆኖ የሚታይባትን ጽሌ ተወልዳ ሲያይ ተገረመ፡፡ ፊትህን አሳየኝ ሲለው ፊቴን ልታይ አትችልም ነገር ግን ጀርባዬን ታያለህ ያለው አምላክ የሚወልደባትን ተወልዳ ሲያይ የጌታን ጀርባ በደብረታቦር የሚያይበት ቀን መድረሱን አውቆ በደስታ ዘለለ፡፡ የመገናኛውን ድንኳን የተከለው ሙሴ ከድምፁ በቀር ያላገኘውን አምላክ የሚያገኝባት እውነተኛዋ የመገናኛው ድንኳን ተተክላ ባያት ጊዜ ደስ አለው፡፡ መቅረዝ ፣ ሙዳየ መና፣ ታቦትና የሥረየት መክደኛ ላይ ደም እየረጨ ሲያመልክ የነበረው ሙሴ አማናዊው ብርሃን የሚበራባት መቅረዝ፣ እውነተኛው መና የሚገኝባት ሙዳይ፣ እውነተኛው የሥረየት ደም የሚረጭባት ምሥዋዕ፤ አካላዊ ቃል የተቀረጸባት በሁለተናዋ ጽሩይ ወርቅ በተባለ ፍጹም ንጽሕና ተጊጣ ድንግሊቱን ባያት ጊዜ መደነቁን አበዛ፡፡ ድንኳኑን ሲያስብ እርሷ፣ ታቦቱንም ሲያስብ እርሷ፣ ጽላቱን ሲያስብ እርሷ፣ ሙዳየ መናውንም ሲያስብ እርሷ፣ መቅረዙንም ሲያስብ እርሷ፣ ማዕጠንተ ወርቁንም ሲያስብ እርሷ ስትሆንበት እንዴት አይደነቅ በእውነት፡፡ ሙሴ በዚህ አላበቃም፡፡ ሕግ የተቀበለበትን የጨሰውን ተራራ አስታወሰና ልጁን ዳዊትን ጠራው፡፡ ዳዊትም የአባቱን ሙሴን ጥሪ ሰምቶ ሲነሣ የረጋችው ተራራ ተወልዳ አያትና እርሱም በደስታ ዘለለ፡፡ አዎ "የእግዚአብሔር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው፤ የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ፤ እግዚአብሔር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው " /መዝ 68 ፤ 16/ ብሎ የተናገረላት ተራራ ስትወለድ አይቶ ደስ አለዉ፡፡ ሐላፊውን ብሉይ ኪዳን አባቱ ሙሲ ሲቀበል በነጓድጓድ ድምጽ በረዓድና በፍርሃት ነበረ፡፡ የማያልፈው ሐዲሱ ኪዳን ግን በጸና ተራራ እንደሚሰጥ የተናገረላት ያድርባት ዘንድ የወደደዳት አማናዊት የንጽሕና የቅድስና ተራራ ተወልዳ አይቶ ደስ እያለው መዝሙሮችን በአናት በአናት አከታተለ፡፡ ልጁ ሰሎሞንም  "ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው፤ ጠጕርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ እንደ ፍየል መንጋ ነው" /መኃ 4 ፤ 1/ እያለ በምስጋና ተከተለው።  ኢሳይያስም ንጹሕ ወረቀቱን አይቶ ደስ አለው፡፡ እንደ ታሸገች የተጻፈባት ሀዝብም አህዛብም ይህን ደብዳቤ ልናንብበው አንችልም ያሏት አካላዊ ቃል በድንግልና የሚጻፍባትን ንጹሕ ወረቀት /ኢሳ 29;11/ አይቶ ተደነቀ፡፡ ሕዝቅኤልም ሁለንተናዋ ዝግ ሆኖ እግዚአብሔር ብቻ ገብቶ የወጣባት መቅደሱን ተሠርታ አይቶ ደስ አለው፡፡ ተራ በተራ ሁሉም ነቢያት ትንቢቶቻቸውን ይዘው ስለእርሷ ያዩትን ራእይ፣ ምሳሌና ትንቢት ፍጻሜውን እያዩ ተደነቁ፡፡ መሐንዲስ የሕንጻውን ንድፍና የሚሠራውን ሕንጻ እንደሚያስተያይ እነርሱም በልደቷ ትንቢታቸውን ከፍጻሜው መጀመሪያ መሠረት ጋር እያስተያዩ ተደሰቱ፡፡ በመጨረሻም የፍትረት ሁሉ አባት አዳም ከልጆቹ ጋር ደስ አለው፡፡ አዳም ሆይ መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህ ያለው ጌታው ከጨለማ ሲኦል ሊያውጣው ልጁን ከመሬት ባሕርዩ አንሥቶ  እርሷን ሰማይ አድርጎ ሲያያት በእርሷም ላይ እርሱ ፀሐይ ሆኖ ሊወጣ ወገግታውን ሲያሳየው በደስታ አነባ፡፡ የሰጠኸኝ ሴት አሳተችኝ ብሎ የከሰሳት ሔዋንን ተክታ የሚያመሰግናት ሌላ ሔዋን ተወልዳ ሲያይ ደስስስ አለው፡፡ ምሳሌና የሚተካከላት እንደሌለም ሲያይ ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ "ለእኗቷ አንዲት ናት፣ ለወለደቻትም የተመረጠች ናት" የሚለውን ዘምር አለው፡፡ ልጆቹ ሁሉ ከመረገሙ በፊት ያለ ክብሩን ስላላዩ በተገቢው መጠን የማያደንቁለትን ከስሕተት በፊት የነበረ ክብሩንና ጸጋውን ይዛ ስትወለድ በደስታ ተንሰቀሰቀ፡፡ የአዳምን ለቅሶ ሰምታ ሔዋን እናቷ የመርገም ጨርቋን ጥላ ብድግ አለች፡፡ አንድ ልጇን እያየች በደስታ አለቀሰች፡፡ በልጆቿ ሳይቀር ምነው እባብን ሰማሽው የሚል ወቀሳ እየሰማች ስታዝን የኖረች ምስኪን እናት መርገሟን ወርውራ በቅድስና ከብራ መላአክትን በልጣ እንደ ጨረቃ ስታበራ ስታያት መካሷን አይታ ፈነደቀች፡፡ ያሳታትን ዲያብሎስ በቅድስና

  • видео или голосовое, без подписи

  • 💚@mzemur_orthodox💚 💛@mzemur_orthodox💛 ❤@mzemur_orthodox❤                 •➢ ሼር // SHARE         ✧┈┈•◦●◈◎❖◎◈    ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

  • እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በአብይ ኃይል ወስልጣን አሰርዎ ለሰይጣን አግዓዝዎ ለአዳም ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሰሀ ወሰላም👏 ❤አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15: 20) @haymanotanednat @haymanotanednat

  • Channel photo updated

  • ቀዳም ሥዑር "በማግሥቱም ከመዘጋጀት በኋላ በሚሆነው ቀን፥ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተሰበሰቡና። ጌታ ሆይ፥ ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ። ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን" /ማቴ. ፳፯፥፷፪-፷፫/ ከስቅለት ማግሥት የምትመጣው ቅዳሜ በሥጋው የሞተው ጌታችን በመቃብር ያረፈበት ዕለት ነው። ይህች ዕለት በተለያዩ ስያሜዎች ትጠራለች። 1. ቀዳም ሥዑር ይህች ዕለት ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ሥዑር /የተሻረች/ ተብላለች። ቅዳሜ ጠዋት፣ ምእመናኑና ካህናቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሰበሰባሉ፤ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም "በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ፤ ትንሣኤውን ገለጸ፤ የምሥራች" እየተባለ ይዘመራል። ካህናቱም የተባረከ ቀጤማ ለምዕመናን ያድላሉ። ቀጤማ የሚበቅለው በወንዝ ዳርና በረግረጋማ ቦታዎች ነው። ክረምት ሲሆን ውኃ ሲሞላ በውኃ ትዋጣለች ፣ የተፈጥሮ መልኳ ጠፍቶ ቢጫ ትሆናለች አልፎም ተርፎ ትበሰብሳለች ፤ ክረምት አልፎ ውኃ እየጎደለ ሲሔድ ደግሞ ትለመልማለች። ካህናትም ለምለም ቄጤማ ማደላቸው ክርስቶስ ስለ እኛ በመስቀል ተሰቅሎ በመሞቱ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመናት በሙሉ በሰው ልጅ ላይ የተፈረደበት መርገምና ሞት መወገዱ ፣ አንድም ቄጤማ በውኃ ሙላት ምክንያት የተነጠቀውን አረንጓዴነት ውኃ ሲጎድል መልሶ እንደሚያገኝ ሁሉ የሰው ልጅም በክርስቶስ መከራና ሞት ወደ ቀድሞው ክብሩ መመለሱን ለማብሠር ነው። 2, ለምለም ቅዳሜ ካህናትና ዲያቆናት ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ ለምለም ቅዳሜ ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል እየመቱ ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምዕመናንም ይህንን ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ያስሩታል። ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት ለማያስታውስ የሚደረግ ነው፡፡  በብሉይ ኪዳን ምድር በጥፋት ውሃ በተጥለቀለቀች ጊዜ የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ፣ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡ 3. ቅዱስ ቅዳሜ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችን የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል። ዕለቱ በሲዖል ለነበሩት ነፍሳት የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ በሰንበት ዕለት የግልም ሆነ የአዋጅ ጾም በፍጹም አይጾምም። ነገር ግን በዚህች ቅዳሜ ይህ ሥርዓት ይሻራል ይጾማልም። ስለዚህ የተሻረችው ቅዳሜ ተባለች። በዚህ ዕለት የሚጾምበት ምክንያት እናቱ እናታችን ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ሐዋርያት የጌታን ሞት አይተው እስከ ትንሳኤው ምግብን አልቀመሱም ነበር። ይህን መሠረት በማድረግ ሁላችን ከቻልን ከሐሙስ ምሽት ጀምሮ እናከፍላለን ይህ ከከበደን ደግሞ አርብ ማታ ተመግበን ቅዳሜን ቀኑን ሙሉ ውለን እስከ ሌሊቱ 9:00 ሰዓት እናከፍላለን እንጾማለን። ለተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE         @haymanotanednat @haymanotanednat

ሃይማኖት አንድ ናት — tgindex