tgindex
ASTUECSF official

ASTUECSF official

Статистика

ዓመታዊ መሪ ቃል: እግዚአብሔርን መፈለግ  በመመለስ  I በፅድቅ ኑሮ  I በመታመን Adama Science & Technology University Evangelical Christian Students Fellowship Official  Telegram channel contact us: @ASTUECSF_inbox CBE:1000696321179 Bethelhem & Lidiya &or Aklilu Telebirr:0950267178

Последний пост
06:15
Последнее чтение
06:58
Постов за неделю
6
Всего постов
265
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Образование
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 789
+2 за 4 дн.
Сутки
−1
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
894
40 постов
Вовлечённость
32,1%
к подписчикам
Постов в день
0,9
всего 265
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
368
1/48двое суток
421
1/72трое суток
454

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ✨ሰላም ሰላም የጌታ ውዶች እንዴት አላችሁ፤ ይሄን ሳምንት " እኛ ያመንን" በሚል ርዕስ የዲጂታል ሳምንት እንዳዘጋጀንላችሁ ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።🎉🎉 📌 እኛ ያመንን፡ ሃሳቡ እኛ ያመንን እንዴት መመላልስ እንዳለብን ከፊልጵስዩስ መጽሐፍ ውስጥ በተመረጡ 5 ሃሳቦች ላይ ተምስርተን ለማሳሰብ ነው። 'ከክርስቶስ ጋራ ካላችሁ አንድነት የተነሣ የትኛውም መበረታታት፣ ከፍቅር የሆነ መጽናናት፣ የመንፈስ ኅብረት፣ ምሕረትና ርኅራኄ ካላችሁ፣ ' ፊል 2:1 - እንግዲህ ከላይ ያለው ክፍል እንደሚለን ከክርስቶስ ጋር ካለን ሕብረት የተንሳ እነዚህ ነገሮች ካሉን ፣ እነዚህን ነገሮች በክርስቶስ እንዳገኘ ሰው እንዴት መመላለስ እንዳለብን ጳውሎስ ያሳስበናል ፤ እኛም እነዚህን ነገሮች እንደ ሕብረት በነዚህ 5 ቀናት ውስጥ አብረን እንድናይ ስንል ይህን ይዘት አዘጋጅተንላቹሃል። 🎊 እናንተም በዙሪያችሁ ላሉ አማኞች እንድታጋሩ እና ንቁ ሕብረታዊ ተሳትፎ እንድታደርጉ በጌታ ፍቅር እናሳስባቹሃለን 😊 ተባረኩ! OUR SOCIALS: INSTAGRAM | YOUTUBE | TIKTOK #እኛ_ያመንን #digital_week #digital_strategy #astu_ecsf

  • ለከረዮ ኦሮሞ ሕዝብ ክፍል 💥 የአብዛኛው ከረዩ ኦሮሞ ሕዝብ የጎሳ እምነት ውስጥ ሚገኝ ነው፡፡ እስልምናን የሚከተሉም በብዙ ቁጥር ይገኛሉ ነገር ግን የጎሳ እምነት ልምምድን ከእስልምና ጋር ዋና የሚያደርጉ አሁንም አሉ። 🙏እንጸልይ 🙏 👉ዛሬን ከእውነተኛው አምላክ እንዳያመልኩ ያገዷቸው፣ ያራቋቸው አምልኮተ ስርዓትቶችን እንዲጥሉ የሚያረገውን የኢየሱስ ታላቅ ስም እንዲሰሙ እንዲድኑበትም እንጸልይ! 👉 የከረዩ ህዝብ የእግዚአብሔር ቃል በቋንቋቸው የተተረጎመላቸው እድለኛ ህዝቦች መካከል ናቸው፣ እግዚአብሔርን  በቅዱስ ቃሉ በኩል ለማወቅ ፍላጎት እንዲቀሰቀስባቸው እንጸልይ! 👉 በከረዩ ማህበረሰብ መካከል  የእግዚአብሄር መንግስት (አገዛዙ፣ ፍርዱ፣ አመራሩ) እንድትገለጥ እንጸልይ! '“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና። ዮሐንስ 3:16

  • ቁ.12-15 ጳውሎስ በስጋ ደዌ እንደሚሰቃይ በ2ቆሮ 12፥7-9 መመልከት እንችላለን። ታዲያ በብዙ ድካም ውስጥ ሆኖ የገላትያ ሰዎችን ወንጌል በሰበከላቸው ጊዜ ድካሙን ሳይፀየፉ በፍቅር ተቀብለውት ነበር። - "እንደ መልአክ አዎን እንደ ክርስቶስ እየሱስ ተቀበላችሁኝ" ሲል ብዙ ድካም ቢኖረኝም ምንም እንከን እንደሌለበት አድርጋቹ ተቀበላችሁኝ ማለቱ ነው።  ቁ.16-20 የሐሰት አስተማሪዎች በብርቱ የፈለግዋቸው ሳይሆን በውጪ ሊያስቀርዋቸው እንደሆነ ያስጠነቅቃቸዋል። -ክርስቶስ ዳግመኛ በእነርሱ ላይ እንዲሳል እጅግ እንደሚመኝ ይነግራቸዋል። 4:21-31 አጋር እና ሳራ ምሳሌ መሆናቸው  -በዚህ ክፍል ጳውሎስ አብርሃም ከባሪያይቱ አጋር እና ከሚስቱ ሳራ የወለዳቸውን ሁለቱን ልጆች እስማኤል እና ይስሐቅ የሕግና የተስፋው ቃል ምሳሌ አድርጎ ይጠቀማል።  ቁ.21-23 አብርሃም ከባሪያይቱ አጋር የወለደው እስማኤል እንደ ስጋ ፈቃድ የተወለደ ሲሆን፣ ከሚስቱ ከሳራ የወለደው ይስሐቅ የተስፋው ቃል ፍፃሜ ሆኖ ተወልዷል።  ቁ.24-26 ሁለቱ ሴቶች አጋር እና ሳራ ሁለቱን ኪዳኖች ይወክላሉ።  - ከሲና ተራራ የሆነችው ባሪያይቱ አጋር በዘፀአት 20 በሲና ተራራ የተሰጠውን ሕግ ትወክላለች። እርሷም ምድራዊውን እየሩሳሌሜ ትመስላለች። ጨዋይቱ ሳራ ግን እግዚኣብሔር የሚገኝበትን ላይኛውን እየሩሳሌም ትወክላለች።  ቁ.27 ከኢሳያስ 54፥1 የሚጠቅስ ሲሆን ይህ ቃል በቀጥታ ስለሳራ የተነገረ ባይሆንም መካን የሆነችውን ሳራ(ዘፍ 11፥30) ስለሚገልጽ ጳውሎስ ተጠቅሞታል።  ቁ.28-31 እንደ ስጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን ማሳደዱ በዘፍ 21፥9-10 እስማኤል በይስሐቅ ላይ መሳቁንና ማሾፉን የሚገልጽ ሲሆን ይህን የተመለከትችው ሳራ የባሪያይቱ ልጅ ከልጄ ጋር አይወርስም በማለት አጋርንና ልጇን አባራለች።ይህም የሕግ ጠባቂዎች ከተስፋው ቃል ልጆች ጋር አብረው እንደማይወርሱ ማሳያ ነው። - እኛም እንደ ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጆች ነን። INSTAGRAM | YOUTUBE | TIKTOK #summer_bs #galatians #astu_ecsf #digital_strategy

  • ምዕራፍ 4  4:1-7 የእግዚኣብሔር ልጆች  ቁ.1-2 በጳውሎስ ዘመን በሮም ሕግ እና ስርዓት መሰረት አንድ ልጅ የወራሽነት መብት የሚያገኘው ዕድሜው ለወራሽነት ሲደርስ ብቻ ነው። አባቱ የቀጠረለት ቀን እስኪደርስ ድረስ የወራሽነት የሌለውና ከባሪያ የማይለይ ነበር። ጳውሎስ ይህን ምሳሌ ከሕግ በታች ያሉትን ለመግለፅ ተጠቅሟል። ቁ.3-5 እንዱሁ እኛ አስቀድመን ከአለም መጀመርያ ትምህርት በታች ተገዝተን ነበር። ነገር ግን እግዚኣብሔር አብ ለወልድ በቀጠረለት ቀን ከሴት ተወልዶ እኛን ልጆቹ አድርጎን ከሕግ ዋጅቶናል። - "መዋጀት" (ቁጥር 5) የሚለው ቃል ከሕግ በታች ባሪያ የነበርነውን በክርስቶስ ሞት ነፃ መውጣታችንን ያሳያል። - በምሳሌው ልጁ አባቱ በቀጠረለት ቀን የወራሽነት መብት እንደሚያገኝ እግዚኣብሔር አብ ለወልድ በቀጠረለት ቀን ልጁን ልኮ ልጆቹ አድርጎ የወራሽነት መብትን ሰጥቶናል። - አስቀድመን ልጆች ያልነበርነውን ወደ እግዚኣብሔር ቤተሰብ አስገብቶናል(adopted into the family of God)። ቁ.6-7 ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጆች ነን እንጂ ባሪያዎች አይደለንም። ልጆች ከሆንን ደግሞ በክርስቶስ የእግዚኣብሔር  ወራሽ ነን። ልጅ በመሆናችንም እግዚኣብሔር አብ አባት ብለን የምንጠራበትን የልጁን መንፈስ በውስጣችን አኖረ። - መንፈስ ቅዱስ የርስታችን መያዣ እና ልጅ የመሆናችን ማረጋገጫ ሆኖተሰጥትናል። ኤፌ 1፥13-14, ገላ 4፥7  4:8-20  ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች ማሰቡ  ቁ.8-11 ከዚህ መልካም ሕይወት ከተካፈሉ በኃላ ወደቀድውሞ ትምህርት በመመለሳቸው ምናልባትም ስለእነሱ በከንቱ ደክሞ እንደሆነ እንደፈራ ይነግራቸዋል።

  • 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣 Out now! https://youtu.be/5RSCi3dD70w?si=5ah981qevGdM7FgC INSTAGRAM | YOUTUBE | TIKTOK #astu_ecsf #digital_strategy

  • 👋👋 ሰላም ሰላም ቤተሰቦቻችን እንዴት ናችሁልን ፣ ክረምት አሪፍ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን ፤ ይህን ተከታታይ ትምህርት ነገ እና ቀጣዩንም ክፍል ቀጣይ ሳምንት ረቡዕ ላይ እንለቅላቹሃለን እንደገና በደንብ እንድትሰሙት እናበረታታለን። https://youtu.be/5RSCi3dD70w?si=bPgN4EA4TYepsGgy 📌 ተባረኩ! #astu_ecsf #digital_strategy

  • 3:26-29  የእግዚኣብሔር ልጆች    ቁ.26-29 የእግዚኣብሔር ልጅ ለመሆን አይሁዳዊ መሆን ወይም መገረዝ አያስፈልግም። በእምነት በኩል ሁላችን በክርስቶስ እየሱስ የእግዚኣብሔር ልጆች ነን። - በእግዚኣብሔር መንግስት ውስጥ አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፣ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፣ ወንድ ወይም ሴት የለም፤ ሁላችንም በክርስቶስ እየሱስ አንድ ሰው ነን። ኤፌ 2፥13-18 INSTAGRAM | YOUTUBE | TIKTOK #summer_bs #galatians #astu_ecsf #digital_strategy

  • 3:15-25  የኦሪት ሕግ እና የተስፋው ቃል    ቁ.15-18 እግዚኣብሔር በዘፍ 15፥13-21 ለአብርሃም በተስፋው ቃል ለብዙ እንደሚናገር ለዘሮችህ ሳይሆን "ለዘርህ" ብሎ ተናገረው፤ እርሱም ከአብርሃም ዘር የሆነው ክርስቶስ ነው። - ሕጉ ለአብርሃም ከተሰጠው ከተስፋው ቃል ከ430 ዓመት በኃላ ነው የተሰጠው። ይህ ሕግ የተስፋውን ቃል ሊሽር ወይም ሊያፈርስ አይችልም።   - የእግዚኣብሔር ልጆች በመሆናችን የምንቀበለውን ርስት የምናገኘው በሕጉ በኩል ሳይሆን የተስፋውን ቃል በሰጠው  በእግዚኣብሔር ላይ ባለን እምነት ነው።   ቁ.19-25 ሕጉ የተሰጠው በመላእክት እጅ መካከለኛ በሆነው በሙሴ በኩል ነው።/ዘዳ 33፥2, ሐዋ 7፥38,53/   • ሕጉ ለምን ተሰጠ?  • ሰው ሕጉን ሙሉ ለሙሉ ሊፈፅም ይችላል?  • ሕጉ የተሰጠው ሕጉን ሙሉ ለሙሉ ፈፅመን እንድንጸድቅ ነው? - የእግዚኣብሔር ቃል የእግዚኣብሔር ሕግ ፍፁም፣ ቅዱስ፣ በጎ እና ቅን እንደሆነ ይነግረናል። ሮሜ 7፥12, መዝ 19፥7-11 - የእግዚኣብሔር ሕግ ፍፁም፣ በጎም በመሆኑ ከተስፋው ጋር የሚቃወም ወይም የሚጋጭ አይደለም። - ሕጉ ምንም ፍፁም ቢሆን ሰውን ፍፁም ሊያደርግ አይችልም። ጽድቅ በሕጉ ቢሆን ኖሮ የክርስቶስም መሞት ባላስፈለገ ነበር። - ሕግ ሀጥያትን ይገልጥ ዘንድ፣ የሰው ልጅ ሀጥያተኝነቱን ያውቅ ዘንድ ተሰጠ። ሮሜ 7፥7, 3፥20-21 - ሕጉ የእኛን ሀጥያተኝነት ብቻ ሳይሆን የእግዚኣብሔርን ቅድስና ያሳየናል። - ሕጉ የተሰጠበት ሌላኛው ምክንያት ፀጋው እስኪገለጥ ሊመራን፣ የእግዚኣብሔርን መንገድ ሊያሳየን፣ ሞግዚት ሆኖ ተሰጥኖል። ቁጥር 24 - አሁን ግን ፀጋው ስለተገለጠ ከሞግዚት በታች አይደለንም።

  • 4 авг.714104

    የሶማሊ ህዝብ ክፍል 💥ሶማሌዎች አንድ ቋንቋ ይጋራሉ፣ ነጠላ እምነትን ይከተላሉ፣ የዘላን አኗኗር ስርዓትን ይከተላሉ። አንድ ሰው ባሉት ግመሎች ብዛት ቁጥር ክብሩን ይጨምራል የሚል አመለካከት አላቸው። በጎሳ የተከፋፈሉ ህዝቦች ናቸው። እምነታቸው ምንድነው? ምንም እንኳን ሶማሌዎች ከሞላ ጎደል ሁሉም የሻፊዒት ሙስሊሞች ቢሆኑም፣ ብዙ እምነቶች እና ወጎች ከእስልምና ልማዶቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል። መደበኛ የእስልምና ጸሎቶች ብዙውን ጊዜ ይከበራሉ። ሶማሌዎች ደጋግመው ወደ ሼሁ(የሀይማኖት አስተማሪ) በመሄድ በረከቶችን ይቀበላሉ። 👉በሶማሌ ሕዝቦች መካከል ያለ መንፈሳዊ መታወር እንዲፈርስ የሚማልዱ የጸሎት ቡድኖችን እንዲያነሳ እግዚአብሔርን እየለመንን እንጸልይ! 👉 በሞት ፍርሃት በጠላት እስረኛ ካረጋቸው  ሀይል ነጻ ወጥተው ወንጌልን  እንዲሰሙ እግዚአብሔር ስራተኞችን እንዲልክ እና እንዲያመልጡ እንጸልይ። 👉ሶማሌዎች ኢየሱስን በማወቅና በማመን እንዲሞሉ፤ እግዚአብሔር በሃይሉ በድንቅ እና በተዓምራት መንፈስ እንዲጎበኛቸው እንጸልይ

  • - እንዲሁ አብርሃም በእግዚኣብሔር እንዳመነ በእግዚአብሔር የሚያምኑ የአብርሃም ልጆች ናቸው(ሮሜ4፥12)።የአብርሃም ልጅ መሆን በዘር ሳይሆን በእግዚኣብሔር በማመን ነው። ቁ.10-14 በሕግ ስር ያለ ሰው ሁሉ ከእርግማን በታች ነው(ዘዳ 27፥26, 28፥58)፣ በሕጉ የተጻፉትን ሁሉ የማያደርግ የተረገመ ነው ተብሎ ስለተጻፈ። - በዘዳግም 21፥23 እንደተጻፈው በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው። ክርስቶስ ስለእኛ በመስቀል ሲሰቀል ስለእኛ እርግማን ሆነ። ክርስቶስ ስለእኛ እርግማን የሆነው እኛን ከሕግ እርግማን ነፃ ሊያወጣን ነው። ስለዚህ መልሰን ከሕግ ባርነት ስር መሆን የመስቀሉን ስራ ዋጋ ማሳጣት ነው። INSTAGRAM | YOUTUBE | TIKTOK #summer_bs #galatians #astu_ecsf #digital_strategy

  • ላለፉት 2 ሳምንታት በአንድ አንድ ምክንያቶች ተቋርጦ ስለነበር ከልብ የሆነ ይቅርታ እንጠይቃለን እናም ጥናታችን እንደገና መጀመራችንን ልናበስራችሁ እንወዳለን፤ተባረኩ። ምዕራፍ-3   3:1-14: እምነት ወይስ የኦሪትን ሕግ መጠበቅ ቁ.1-5 ጳውሎስ ከሰበከላቸው ወንጌል የገላትያ ሰዎች ወደኃላ በማለታቸው በጣም ተገርሞ ተከታታይ የሆኑ ጥያቄዎችን ይጠይቃቸዋል። - የክርስቶስ መሰቀል በጳውሎስ ጽሑፎች ወንጌልን የሚያመለክት ሲሆን(1ቆሮ 1፥23) ይህን የተሰበከውን እውነተኛ ወንጌል እንዳያስተውሉ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ ይጠይቃቸዋል። - አስቀድሞ በመጀመሪያ ጳውሎስ ወንጌልን ለገላትያ ሰዎች በሰበከ ጊዜ ከመስማት በሆነ እምነት አምነው የእግዚኣብሄርን መንፈስ ተቀብለው ነበር።ወደኃላ ወደዛ ጊዜ መልሶ የእግዚኣብሄርን መንፈስ በሕግ ስራ ወይስ በእምነት እንደተቀበሉ ይጠይቃል። ቁ.6-9 ታላቅ የእምነት አባት የሆነውን አብርሃምን ምሳሌ በማድረግ ይጠቀማል። - አብርሃም እግዚኣብሔር ለእርሱ በገባለት ተስፋ በእግዚኣብሔር በማመኑ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት(ዘፍ 15፥6)። - እግዚኣብሔር አህዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ "በአንተ አህዛብ ሁሉ ይባረካሉ"(ዘፍ 12፥3) ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም ሰበከ። ስለዚህ አህዛብን በእምነት ማጽደቅ አስቀድሞ በእግዚኣብሔር ዘንድ የነበረ ሀሳብ ነው።

  • የሱሪ ህዝብ ክፍል 💥ሱርማ ወይም ሱሪ በመባል የሚታወቁት ሕዝቦች የሚኖሩት በኢትዮጵያ ደቡብ ምዕራብ ዳርቻ አካባቢ ነው። በእነዚህ ሕዝቦች መካከል የሚስዮን አገልግሎት የተጀመረው በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ነበር። ሆኖም ግን፣ በተለያዩ ውጫዊ ተጽዕኖዎች ምክንያት አገልግሎቱ ለጥቂት ዓመታት ብቻ ቆይቶ ሊቋረጥ ችሏል። የፀሎት ርዕሶች 👉የሱሪ ህዝብ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያውቁና በእርሱ ከዘላለም ጥፋት እንዲያመልጡ እንጸልይ! 👉ወደዛ አከባቢ የሚላኩ የወንጌል ሰራተኞች እግዚአብሄር እንዲያብዛ እንጸልይ! 👉በዛ አከባቢ ያሉት ጥቂት ደቀመዝሙራት ለሌሎች ይህን ብርሃን እንዲገልጡ እንፀልይ!

  • 23 июл.1 21475

    https://youtu.be/mHNfvZDlYE8?si=_7-R02m5xIQQJQMr Out now! #astu_ecsf #digital_strategy #lad

  • 22 июл.1 00020

    📣 Our final drop hits thursday, stay tuned! https://youtu.be/mHNfvZDlYE8?si=EGFd05caA9E5gVXw Who is excited, drop🔥 INSTAGRAM | YOUTUBE | TIKTOK #astu_ecsf #digital_strategy #LAD

  • 20 июл.1 059122

    ለቱርካና የሕዝብ ክፍል 💥የቱርካና ሕዝቦች የሚኖሩባቸውን ቤቶች የሚገነቡት ከእንጨት በተሠሩ የዶሜድ ቡቃያዎች (ፍሬሞች) ላይ  የዶም ፓልም ዛፍ ‘ሃይፋኔን ቴባይካ’፣ ቆዳ ወይም ሌጦ እና ሳር በማልበስ ነው። ቤቶቻቸው በአማካኝ ስድስት የቤተሰብ አባላትን ለማኖር በቂ እንዲሆኑ ተደርገው ይሰራሉ። ብዙውን ጊዜ በእርጥበት ወቅት ፍሬሞቹ ረዣዥም ይደረጉ እና በጭቃዎች ይሸፈናሉ። በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት አብዛኛው ቱርካና ማህበረሰብ ክፍሎች ከባህላዊ የከብት እርባታ ወደ ዘመናዊ አርብቶ አደርነት ለመቀየር ተገደዋል። የማህበረሰብ አለቃዎች ወይም ሽማግሌዎች የሏቸውም። የፖለቲካ ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉት እድሜ፣ ሀብት፣ ጥበብ እና የንግግር ችሎታ ያላቸው  ግለሰቦች እንደሆኡ ይነገራሉ። ጋብቻ ወይም ትዳር መመስረት  በቱርካና ሕዝብ ማካከል ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፤ ከግዜያት ወዲህ ግን ባልተለመደ መልኩ በጨመረው  ከፍተኛ የጥሎሽ ይዘት ምክንያት አንድ ወንድ አባቱ ሞቶ የእንስሳት እርባታውን እስኪወርስ ድረስ ማግባት ፈጽሞ የማይቻል ነገር እየሆነ መጥቷል።   የጸሎት ርዕሶች 👉በቱርካና ህዝብ መሃል ያሉ አንዳንድ እግዚአብሔር የማይከብርባቸው ባህሎች ከዚህ ሕዝብ ክፍል እንዲወገዱ አጥብቀን እንጸልይ! 👉ቱርካና ጎሳ መካከል ያሉ ጥቂት የኢየሱስ ተከታዮች ለጌታ እየዘመሩ እና እያዜሙ የተቀደሰ ህይወት እንዲኖሩ እንጸልይ! 👉ለቱርካና ህዝብ በመንፈስ የተሞሉ ብርቱ የወንጌል ሰራተኞች እንዲላኩ  እግዚአብሔርን እየለመንን እንጸልይ!

  • 17 июл.1 17853

    ለህብረታችን ምሩቃን በሙሉ ... 📌 ሰላም የተወደዳችሁ የህብረታችን የምሩቃን የASTUECSF Graduates ቴሌግራም ግሩፕ join በማድረግ ከ ምሩቃን (graduates) ጋር በተያያዘ የሚለቀቁ መረጃዎችን ማግኘት ትችላላችሁ። https://t.me/astuecsf_graduates

  • 16 июл.1 23177

    ቁጥር 17-18. ጳውሎስ የሚሰብከው ከሕግ ነፃ የሆነ ወንጌል አንድ ጥያቄን ሊያስነሳ እንደሚችል በማወቅ አስቀድሞ መልስ ሰጥትበታል።ጥያቄውም: ወንጌል ከሕግ ባርነት ሰውን ነፃ የሚያወጣ ከሆነ ሰው ሀጥያትን እንዲያደርግ ፈቃድን አይሰጥም?፣ እኛስ በክርስቶስ የምናምን ሀጥያተኛ ሆነን ከተገኘን ክርስቶስ የሀጥያት አገልጋይ ነው? አይደለም።  ቁጥር 19-20. ጳውልስ እንዲህ በማለት መልስ ይሰጣል።ከክርስቶስ ጋር ተሰቂያለው፣እኔም አሁን ህያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፣አሁንም በስጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝ እና ስለእኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለእምነት የምኖረው ነው። ->ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለው ሲል አሮጌውን ማንነት፣የስጋን ሀሳብ እና ፈቃድ በመስቀል ገድያለው ማለቱ ሲሆን(ኤፌ 4:22) አሁን የምኖረው ሕይወት ደግሞ ስለወደደኝ እና ስለእኔ እራሱን በሰጠ በክርስቶስ ባለእምነት ነው በማለት ይመልሳል።  ቁጥር 21. ጽድቅ በሕግ በኩል ቢሆን የክርስቶስ መሞት ከንቱ ነበር ማለት ነው።ነገር ግን ጽድቅ የሚገኘው በክርስቶስ በኩል ብቻ ነው። #summer_bs #galatians #astu_ecsf #digital_strategy

  • 16 июл.1 09457

    ምዕራፍ 2:11-21 ጳውሎስ ጴጥሮስን ተቃወመ ቁጥር 11-12. አንጾኪያ በሶርያ ውስጥ የምትገኝ ከእየሩሳሌም 480KM ርቀት በስተ ሰሜን የምትገኝ ከተማ ናት።በአንጾኪያ ብዙ አህዛብ የሚገኙ ሲሆን ብዙ የወንጌል ሰባኪዎች ከአንጾኪያ ወደተለያዩ አህዛብ የሚገኙባቸው ስፍራዎች ይላኩ ነበር (ሐዋ 13:1-3)።   -> በሐዋርያት ስራ 10(10:28) እግዚኣብሔር ጴጥሮስን ከአህዛብ ጋር ሕብረት ማድረግን ካስተማረው በኃላ ጴጥሮስ ከአህዛብ ጋር ማዕድ ይቆርስ ነበር።ነገር ግን አይሁድ የሆኑ የሐዋርያው ያዕቆብ ተከታዮች ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ እነርሱን በመፍራት ከአህዛብ ጋር ለማዕድ አንድ ላይ መቀመጥ አቆመ።    • እግዚኣብሔር ለአይሁድ የሰጠው የአመጋገብ ሕግ (dietary laws) /ዘሌዋውያን 11/ ስላለ አህዛብ ደግሞ ይሄን ሕግ ይከተሉ ስላልነበር በአይሁዶች ዘንድ ከአህዛብ ጋር ለማዕድ መቀመጥ እንደ ሀጥያት ይቆጠር ነበር። ቁጥር 13. ይሄ የጴጥሮስ ድርጊት ብዙ አይሁዶችን በርናባስን ጨምሮ ወደ ስህተት መንገድ መርትዋል።  ቁጥር 14. ጳውሎስ ይሄን ድርጊታቸውን ባስተዋለ ጊዜ ጴጥሮስን በሁሉ ፊት ተቃወመ።  ቁጥር 15. በአይሁዶች ዘንድ በሕጉ ስር የማይኖር ማንኛውም ሰው ሀጥያተኛ ነው።አህዛብ የሕጉ ተቀባይ ባለመሆናቸው(በሕጉ ስለማይኖሩ) በአይሁድ ዘንድ እንደ ሀጥያተኛ ይታያሉ።  ቁጥር 16. ሰው በእግዚኣብሔር ፊት የሚጸድቀው በክርስቶስ በማመን ብቻ ነው።በሕግ ስራ በእግዚኣብሔር ፊት ጸድቆ ለመታየት መሞከር በራስ ስራ በእግዚኣብሔር ፊት ልክ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው።የእኛ ስራ የእኛን ሀጥያት እንጂ የእኛን ጽድቅ ሊያሳዩ አይችሉም።ይልቁኑ ሰው ሊጸድቅ የሚችለው እኛ በእግዚኣብሔር ፊት እንጸድቅ ዘንድ ስለ እኛ ሀጥያት በሆነው በክርስቶስ በማመን ነው(2ቆሮ 5:21)።

  • 13 июл.1 113111

    ወለኔ የሕዝብ ክፍል 💥የወላኔ ተወላጆች ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 160 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሰሜን ምስራቅ ጉራጌ ክልል ቀቤናን፣ ኦሮሞ እና ሙር ህዝቦች አቅራቢያ ይኖራሉ። አብዛኞች ግን አዲስ አበባ አከባቢ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው ይኖራሉ። አዲስ አበባ የሚኖሩት ወለኔዎች በመርካቶ ነጋዴ ሆነው ኑሯቸውን የሚመሩ ናቸው ። በጉራጌ ክልል የሚኖሩ ግን በግብርና እና አርብቶ አደሮች ናቸው። እንፀልይ 👉  የወለኔ ሕዝብ  በእግዚአብሔር ዘላለማዊ አጀንዳ እንደታሰቡ እንዲያውቁ እና ፍቅሩን ማየት ይችሉ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ፊት እያቀረብን   እንጸልይ። 👉 የወለኔን ማህበረሰብ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ቤተ-ክርስትያን ወይንም ሰራተኞች መኖራቸውን የሚጠቁም  ምንም አይነት መረጃ  የለም፣ በእግዚአብሔር ሓይል እና መንፈስ የተሞሉ፣ ብርቱ ሰራተኞችን እግዚአብሔር እንዲልክ እንጸልይ። 👉 የወለኔ ሕዝብን በመጨረሻው የሰማይ ጉባዬ ለታረደው በግ በቋንቋቸውና ባህላቸው ክብር ሲያመጡለት እናይ ዘንድ እንማልድ!

  • 10 июл.1 612197

    ⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️ This drama is out now, make sure to check it! 🔗here is the link: https://youtu.be/MbP3UDyjFVo?si=p4fkJ2VLLZHWxe6q #astu_ecsf #digital_strategy