tgindex
ማዕደ ሰማይ/ Heavenly Meat

ማዕደ ሰማይ/ Heavenly Meat

Статистика

#በፀጋ ነው #ፀጋው ብቻ #የታደገን ከዓለም ጡጫ። #በፀጋ የዳነ #ያለፀጋ አይፅፍም #ያዳነው እያለ #የዳነው አይነግስም፤ #ባለፀጋው #ባይኖር #እኔም ችዬ አልኖርም። እንዳለው እንድኖር ጸጋ አለ የሚያኖር። ለአስተያየቶ በዚህ 👇 ይላኩልኝ። @Surtsega @Surafeltsegamets @heavenlymeatministry

Последний пост
24 июл.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
562
−1 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
754
22 постов
Вовлечённость
134,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 22
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
62
1/48двое суток
71
1/72трое суток
76

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • #ለእኔ_ዘውዴ የምወድሽ ተወዳጄ ምርጧ ዕንቁ ያለሽ ከእጄ የሰው ቅመም፥ ቤት አድማቂ እንደምወድሽ ብቻ እወቂ ❤️❤️❤️ ለቤን እናት ለእኔ ዘውዴ የገመድሽ መንገድሽን ከመንገዴ ለደሃ ደግ እናት ፥ የማትነፍግ ከተሰጣት፤ ትጓ ለፍቶ አዳሪ፥ ለመታተር የማይደክማት።   ስንፍናን ምትጠየፍ ግብሯም ስሟም የተኳለ እናት ዘውዴ ቃልኪዳኔ፤ ማን ነው እንደኔ የታደለ ❤️❤️ በደምነት ሳለሽ ለጋ፥ አጥንቶችሽ ሳይዋደዱ፤ ቀናቶሽ ፥ በልዑሉ በክርስቶስ ፊት ተወደዱ። ያለማወጣት ያለአንዳች አለኝ፤ ነፍስሽ ዳነች ሞቶ የመረጣትን ክርስቶስን ስላወቀች። ተመረጥሽ ለቀናው ወግ ለአምላክ ስራ ተጠመድን ከእኔ ጋራ ከመኸሩ እንድንሰራ መልካም ልደት ለቤን እናት ለእኔ ዘውዴ ባልተቤቴ ደስተኛ ነኝ ከአንቺ ጋራ መጠመዴ። ለቤን እናት ከቤን አባት ብቻ እወቂ   ጸሎት ተማፅኖዬ የእኔ ሀ - ሴት አንቺ ደልቶሽ እንድትስቂ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም

  • #መቅደም_የሚሻ ጉድጓድ አይምስም፥ ይቆያል ከአምላክ ትከሻ❗️ (ርዕሱ ነው🔬) በእጅና እግር እልፍ እየመተሩ፤ በእኔ ዓለም ስሌት ዘግጠው በእነሱ የከበሩ፤ ጉድጓድ በመማስ ሳይተኙ ያደሩ፤ እስካሁን እዚህ ነህ፤ እንዴት ነህ? የሚሉ፤ ምናለ ሰከን ቢሉ፥ ግራ ቀኝ ቢያጤኑ? በስሌተ ዓለም ልዩነት መጣል መገፋት፥ መንገስ መሆኑ መቅደምስ መቀደም እንደሆነ ምናለ ቢያስተውሉ! 🫅🤴 (🔑 በጓዳ የጣልናቸው፤ አደባባይ ላይ ነው ክብር ሚጠብቃቸው። 🔑 )             ━━━━⊱✿⊰━━━━━ @gtmmbetsega @elgraceministry          @surafeltsegamets            ━━━━⊱✿⊰━━━━━

  • без подписи

  • 25 мая20631из Guragignamezemur

    ‼️ዋንጫ በልተን ወድቀናል 😔 ✍መፅሐፍ ቅዱስ ይዞ ቤተክርስቲያን ለመሔድ የሚያፍር ግን የክለቡ ማለያ ቤተክርስቲያን ለብሶ ለመሔድ እንደ ጀግንነት የሚቆጥር ትውልድ መካከል በመሆናችን ወድቀናል:: ✍በሚሰራበት ባጃጅና መኪና ዝማሬ ለመክፈት የሚያፍር በዋንጫ ሰሞን ደግሞ የክለቡ ማለያ መኪናውን የሚያከናንብ ትውልድ መካከል በመሆናችን። ✍የፀሎት ምሽግ እና ሌሎች መንፈሳዊ ፕሮግራሞች በኳስ ሰበብ ቀርቶ ወይ ቀን አስቀይሮ ወደ ዲኤስ ቲቪው የሚያመራ ትውልድ መካከል በመሆናችን ወድቀናል እንደ ትውልድ መካከል በመሆናችን ወድቀናል ። ✍ ዋንጫ የመብላትና ያለመብላት ፕሪሚየር ሊግ ከመጀመሩ አንስቶ ብዙ ታሪክ የሚጠቅስ የተጫዋችም ብቃትና ድክመት ቤተሰብና ሀገር ሚስትና ልጆች ወዘተ... ለይቶ የሚያውቅ..ለተከራካሪው አፍ የሚያዘጋ... ስለመፅሐፍ ቅዱስ ስለፀሎት ሲነሳ ግን አፉንም ልቡንም የሚዘጋ ትውልድ መካከል በመሆናችን 😔ዋንጫ እየበላንም ወድቀናል.....እያሸነፍን ተሸንፈናል😒 🙏ከወዴት እንደወደቅን እናስብ በትራችንን ከጣልንበት እናንሳ ከባዘንበት ወደ ስፍራችን እንመለስ ቡትቶአችንን ጥለን ኢየሱስን እንልበስ ወደ ተልእኮአችን እንመለስ እንታደስ እግዚአብሔር ትጋታችንን ይመልስልን ስሙ በእኛ መካከል ይቀደስ አሜን 🙌🧎🧎🧎🧎‍♂🧎‍♂‍➡️🙏✝ 🔥መላው የአርሰናል ደጋፊ እንኳን ደስ አላችሁ አለን 😒😂🏆🏆 ✝️ኢየሱስን በትውልድ ልብላይ መሳል✝️ 🔵 @Guragignamezemur 🔵 🔵 @Guragignamezemur 🔵 🔵 @Guragignamezemur 🔵

  • 12 апр.1 91023

    ኤፌሶን 2:4-6 •••••••••••••••••••• ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።        •••••••••••••••••••••••••  እግዚአብሔር እርሱ የምህረት ባለጠጋ ሆኖ ሳለ ንፉግ እንዳይሆን በትልቅ ፍቅሩ (አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ) ወደደን። አንድያ ልጁን ስለእኛ አደቀቀው። (በምን ይብራራ ይሆን ግን?) አንዳች ምላሽ ለመስጠት እንኳን የማንበቃውን እኛን በትንሳዔ በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋራ አስቀመጠን። በቃ እግዚአብሔር በኢየሱስ ወደደን።  (ዛሬ መቃብር ባዶ የሆነበት፤ የቀበሩት ያስቀበሩትም የደነገጡበት ቀን ነው።) በትልቅ ፍቅሩ ተቤዠን ወደ እርሱ እንድንተጠጋ አየን ከሁሉ የሚበልጠውን የእግዚአብሔርን ጸጋ ✨✨ @elgraceministry ✨✨         ከወደደን ትልቅ ፍቅሩ የተነሳ                    ትንሳዔ 👉👉 @elgraceministry 👈👈

  • 💫💥💫 #የሚያስብህን_አስብ 💫💥💫 ውስጥህ ዝም ሲል፣ ነፍስያህ መፅናናትን እንቢ ስትል፣ የምታናግረው ሲጠፋ፣ የሚሰማህ የሌለ መስሎህ ነገሮችን ከግራ ከቀኝ ሲደራረቡብህ፣ የሚወድህን ከማይወድህ መለየት ሲከብድህ፣ ዘመኑም የመከራ ዘመን ሲመስልህ እመነኝ #ሳታቋርጥ እግዚአብሔርን አስብ።  ነፍስያህ በምላሹ ትፈዛለች።          አስብ አስብ አስብ አስብ!  ያሰብከው #እሱ_፩_ወዳጅህ ከእልፍ ወዳጆችህ ይበልጣል። እግዚአብሔርም በቃሉ ሲያወጋን " •• በመከራዬ ቀን እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ እጆቼ በሌሊት በፊቱ ናቸው፥ አላረፍሁምም፥ ነፍሴም መጽናናትን አልቻለችም። #እግዚአብሔርን_አሰብሁት ደስ አለኝም፤ ተናገርሁ፥ ነፍሴም ፈዘዘች። " መዝሙረ ዳዊት 77:2-3 ✨✨ @elgraceministry ✨✨            የቃሉ  ብርሃን ያግኘን! 👉👉 @elgraceministry 👈👈

  • ጥቂት ጊዜ አለፈ ከተናገርካቸው አብርሃምና ሳራን ተስፋ ፈጠናቸው ከዚህ የተነሳ እርምጃን ወሰዱ አንተንም ቀደሙ እስማኤልን ወለዱ ግን አንተ ጌታችን ስለተስፋህ ብለህ ይስሐቅን አምጥተህ ቃልህን ፈጸምህ (2x) አዝ፦  አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም፤ ቀስ እያልክ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም። ነገርን በሙሉ በጊዜው ውብ አድርገህ፤ በድንቅ በተዓምራት ታበጃጀዋለህ፤ ክብርህን ትገልጻልህ። ወንድሞቹ ሲሰግዱ ዮሴፍ ህልምን አየ ግን የኖረው ኑሮ ከዚህ የተለየ ቃልህ እስኪመጣለት እርሱም ተፈተነ በእርኩሰት በኃጢአት ላይ ሁሌ እየጨከነ የሚጐበኝበት የእግዚአብሔር ቀን መጣ ከእዛ ጉስቁልና ከመከራ ወጣ (2x) አዝ፦  አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም፤ ..... ሃና መካኗ ሴት ብዙ አለቀሰች በወገኖች ሳይቀር እየተነቀፈች እርሷም እንደሰው . (1) . ዘመኗ ደረሰ እምባዋ በአንተ ጸና ታሪኳም ታደሰ አቤት የእግዚአብሔር ስራው ያስደንቃል የምስኪኑን እንባ በጊዜው ያደርቃል (2x) አዝ፦  አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም፤ ..... በጣም የምትወደው አልዓዛር ታሟል የሚል ድምጽ ከሰማ አራት ቀን ሆኖታል። የሞተውን ሊያስነሳ እንባቸውን ሊያብስ በራሱ ጊዜ መጣ ጌታችን ኢየሱስ። ዛሬም ብንጠበው በመጠበቂያችን እግዚአብሔር ቅርብ ነው ክብሩን ሊገልጽልን፤ ክብሩን ሊገልጽልን። አዝ፦  አትቸኩልም አንተ ደግሞም አትዘገይም፤ ..... ✨✨ @elgraceministry ✨✨            የቃሉ  ብርሃን ያግኘን! 👉👉 @elgraceministry 👈👈

  • 7 февр.1 21111

    #የሚጋባ_ንቀት አባታችን አብርሃም፥ በምድር ድንኳንን በመስራት፤ የሰማይ ሀገሩን ጽዮንን ናፍቆ፤ ይችን ዓለም ናቃት። https://t.me/elgraceministry

  • 7 янв.2 15434

    💥💯 #መድኃኒት_ክርስቶስ_ጌታ 💯💥 መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ #ዛሬ በዳዊት ከተማ #መድኃኒት እርሱም #ክርስቶስ #ጌታ የሆነ #ተወልዶላችኋልና።                               ሉቃስ 2:10-11     ማሳሰብያ፥ የተወለደውን #መድኃኒትን ሳትወስዱ ቀናችሁ አይለፍ፤ የተላከውን #ክርስቶስ-መሱሁን ሳታምኑ ቀርታችሁ ቀኑ ከአብ ተጣልታችሁ አይለፍባችሁ፤ የዘላለም መታረቂያ ነውና። #ጌታ_የሆነውን "ድሮስ ወያላ ነው" ማን አለ? በማለት ቀልዳችሁ ቀን አይጨልምባችሁ፤ ጌታን አምናችሁ ጨለማው ውስጥ ቀን ሁኑ እንጂ። ኢየሱስ ተወለደልን፤ ለማን? ለእኛ/ ለሰው ሁሉ እንደምን እንደ መርዶ ወይስ እንደ ምስራች? እንደ ታላቅ የምስራች፤ ተወለደብን ሳይሆን ተወለደልን። ለምን?  መድኃኒት፣ ክርስቶስና ጌታ ሊሆንልን። #ዛሬ  #በዳዊት ከተማ ቅዱሳን ይህ ገና ለእኔና ለእናንተ አምላክ የነገረንን ትንቢትና የምንናፍቀውን የፍቃዱን ፍሬ #ጊዜውንና_አድራሻው የምንሰማበትና ያንንም የምናይበት ይሁንልን።  አሜን! 💥💯 #መልካም_የመድኃኒታችንና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ_ ልደት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ 💯💥 @ሱራፌል ወርቁ (ጸጋ)

  • #ልክ_እንደ_ኢየሱስ የሉቃስ ወንጌል 4:1 (NASV) •••••••••• ¹ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ እንደ ተመለሰ፣ መንፈስ ወደ በረሓ ወሰደው፤ የተሞላነውና የተቀበልነው መንፈስ የሚመራ፤ አቅጣጫን የሚያሳይ፤ በሚመራን ሁሉ ስፍራ የሚያበረታን እንጂ በእኛ #የሚመራ_አምላከ አይደለም። መንፈስ ቅዱስን ማድመጥ አልፎም ደግሞ ለእርሱም መገዛት እና መታዘዝ ይሁንልን፤ #ልክ_እንደ_ኢየሱስ። ሱራፌል ወርቁ (ጸጋ)

  • 28 окт.336из barnabasism

    የአቦ-ሰጥ ዘሪዎቹ ---▣--- ከበርናባስ በቀለ ከሰሞኑ ዘሪቱን በገፍ ዘርተው አገኘሁና ኋላ ማጨድ እንዳለ ሳያውቁ በአቦ-ሰጥ መዝራት ከዘራቸው ነው ብዬ ዝም አልኩኝ። ለአስተያየትዎ፦ @barnica Join ➘ & Share ➝      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊      ◊   @barnabasism  ◊

  • 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5:9-13 (AMH) •••••••••• ⁹ የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና። ¹⁰ በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል። ¹¹ እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው። ¹² ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። ¹³ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።                ━━━━⊱✿⊰━━━━━   @gtmmbetsega    @elgraceministry

  • ዘማሪ ባሮክ ክፍሌ (ወንድምዓለም) 🙏🙏🙏 #አምነዋለሁ 🙏🙏🙏 https://t.me/elgraceministry የትላንቱ እግዚአብሔር ዛሬም እግዚአብሔር ነው፤ ጊዜና ሁኔታ ምክንያት አይለውጠው። መንገድ አስጀምሮ ጥሎኝ ሸሽቶ አይሔድም፤ ይጋፈጣል እንጂ ወደኋሏ አይልም። አምነዋለሁ የኔን ጌታ አምነዋለሁ አምነዋለሁ ኢየሱሴን አምነዋለሁ (*2) በርሃብ ዘመን ጥጋብ ሆኖኝ ኃይሌ ሲርድ ተሸክሞኝ አንድም ቀንም ሳይሰለቸኝ  ይኸው አለው እርሶ አኑሮኝ ስለዚህ ነው የማመልከው ክብሬን ጥዬ የማከብረው(*2)። ማዕበል ከወደ ፊት ይዞ ሲያስጨንቀኝ እንደ ምትሃት ታይቶ ጥሎኝ አልፎ አይሄድም ድንገት ፈጥኖ መድረስ ለእኔስ አመሉ ነው፤ የክፉ ቀን ጓዴ ጌታዬ ኢየሱስ ነው። አምነዋለሁ የኔን ጌታ አምነዋለሁ አምነዋለሁ ኢየሱሴን አምነዋለሁ (*2) በርሃብ ዘመን ጥጋብ ሆኖኝ ኃይሌ ሲርድ ተሸክሞኝ አንድም ቀንም ሳይሰለቸኝ  ይኸው አለው እርሶ አኑሮኝ ስለዚህ ነው የማመልከው ክብሬን ጥዬ የማከብረው(*2)። ድንጋይ ተንተርሼ ወድቄ ሳለሁኝ፤ ተስፋዬ አልቆ ሳለ አይኖችህ ፈለጉኝ። ተነስቼ ልውጣ ወደ ቤተልሔም፤ መሰዊያዬን ልስራ አምላኬን ላመስግን። አምነዋለሁ የኔን ጌታ አምነዋለሁ አምነዋለሁ ኢየሱሴን አምነዋለሁ (*2) በርሃብ ዘመን ጥጋብ ሆኖኝ ኃይሌ ሲርድ ተሸክሞኝ አንድም ቀንም ሳይሰለቸኝ  ይኸው አለው እርሶ አኑሮኝ ስለዚህ ነው የማመልከው ክብሬን ጥዬ የማከብረው (*2)። https://t.me/elgraceministry

  • #ጤንነት ነው ወይ? ፍቅርህ ሲለካ ሲመዘን ነፍስ እስከ መስጠት ሚመዝን ፍቅርህ ሲመዘን ሲለካ እስከ መስቀል ሞት ነው ለካ . . . አይገርምም ወይ ባልወድህ ጤንነት ነው ባላመልክህ? https://t.me/elgraceministry ይሰማ ይደመጥ ሃምሌት በልጁን https://t.me/elgraceministry

  • ማዕበል ቢነሳም የሚያናውጥ ታንኳን የሚገፋ ሊገለብጥ ከቶ አንጠፋም ገብተን ባህር ከአፉ ቃል ወጥቷል ሊያሻግር ጌታ ካለ ማዕበል እያለ መንሳፈፍ አለ ባህር እያለ መሻገር አለ መሞት እያለ መሰንበት አለ ሁከት እያለ እፎይታ አለ ጠላት እያለ ደህንነት አለ ውጊያ እያለ መዘመር አለ። https://t.me/elgraceministry

  • 🌻 #ዛሬ በእርግጥ #ዛሬ_ብቻ #አይደለም። 🌻 ትናንትና ያለፈ ዛሬ፤ ነገም ተስፋ የምናደርገው ዛሬ ነው።  ማለትም ዛሬን ሳይሆን ያለፈ ትናንትና ዛሬን ሳይሆን የምናየው ነገ የለም። ዛሬ የትላንትናውን የምንሞርድበት ሞረድ ፤ የነገውንም የምናንፅበት መሃንዲሳችን ነው። #ዛሬን_መኖር ማለት የነገውን ትናንትና ዛሬ በጊዜው ማሰናሰን፤ ማስተናገድ ማለት ነው። ዛሬ እንጂ ትናንትም፤ ነገም "#ማን_ነበርን?" አሊያም "#ማን_እንሆናለን?" ለሚለው እንጂ "#ማን_ነን?" ለሚለው የትርጉም ጥያቄ መልስ የላቸውም። #ዛሬን_መኖር ማለት ዛሬን በመስታወትም በመነጽርም እየተመለከቱ መጓዝ ማለት ነው። የነገው ህይወታችን የዛሬን መኖራችን ያህል ይከብዳል፤ አሊያም ይቀላል። በመስታወትና በመነጽሩ መሃል ልክክነት ይጠይቃል። ዛሬያችን፤ ነገ ዛሬ ሲሆን ትናንትና ሆኖ የሚወራ፤ ተረት ብቻ ሳይሆን #የብዙዎችን_ዛሬ የሚያበራ ኩራዝ ☀️ እንዲሆን ዛሬ #ዛሬ_ሳለ በዘይት የተሞላ እና ክሩ የረዘመ ላንባ ሆነን እናልፍ ዘንድ ኧረ የዛሬ ያለህ እያልኩኝ ለሚሰማኝ ሁሉ እጮሃለው፤ እመክራለኹ። የዛሬ  አያያዛችን የነገውን አቋቋማችንን ይወስነዋል። (ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።1ኛቆሮ 10:12 ) አየን? መቆምም መውደቅም መጠንቀቅም ዛሬ ላይ ነው ወገን።  ነገን የሚያስብ እና ታሪክ መስራት የወደደ ሰው ሁሉ በዛሬው ላይ የበረታውን እና ያልተቆጠበ እርምጃውን ይራመድ።  በተራመድነው ልክ የሚታየን እይታ ይቀየራል። (ልክ ሲትበር ሲመለከታት የነበረችን አይሮኘላን ትንሽና የእጁ መዳፍ ያልመሰለችውና ወደ ማረፊያው ደርሶ ከአይኑ የገዘፈችው የአይሮኘላኗ ምሳሌ) እይታችን የት እንዳለን ይናገራል።  ዛሬን መመልከቻ መስታወታችንን ሆነ መነፅራችንን እናጢነውና እናንጻ ከዚያም የዘለገ ዛሬያችንን እንታደግ። ነገን የምናየው ዛሬ ላይ ወደ ነገ ከተራመድን  ነው። #ነገ ወደ ዛሬ የሚመጣው #ዛሬ ያልነውን ወደ #ትናንት ሊሸኝም ነውና  ነገን ከመጥራታችን በፊት ዛሬን አበጥረን እንኑረው፤ ዛሬን ራዕቆቱን በነገ ተክተነው እንሸኘው፤ ወደ ነገ ባንሄድም ነገ ወደ እኛ ይመጣልና። ዛሬ ወደ ትላንት ከመሸኘታችን አስቀድመን ዛሬን ከልጆቻችን የተዋስነው ነገ፤ ከአባቶቻችን የተረከብነው ትላንት መሆኑን አጥብቀን በማወቅ ነቅተን የተዘራበትን እንደበላ ትውልድ የነገ ትውልድ  የሚበላውን ዛሬ እንዝራለት። #የዕለት እንጀራችንን #ዛሬ ስጠን።   ማቲ 6 ፡ 11 በዕለት ተዕለት ዕለታዊ ጉዞ የዘላለም መናችን ኢየሱስ ሆይ ሳንጠግብህ አሁንም በዚህ አመት የየዕለት እንጀራችን ትሆንልን ዘንዳ በአንተ ርሃብ ባርከን።    ከጨመርክልንማ ቀን፤ ከተሻገርንማ ማዕበል ዛሬን ለአንተ ለመኖር አድርግልን የናዝሪቱ ኢየሱስ፤ ክርስቶስ ጌታና መድኃኒታችን ሆይ ለራሳችን ከመኖር ቀማና ወደራስህ ሃሳብ ጎትተን።    በዘላለም አምላክ ለዘላለም አምላክ አጀንዳ የምንገኝበት ዓመት ይሁንልን። መልካም አዲስ አመት  🌻🌻2018🌻🌻 👉 ታናሹ 🌻 ወንድም ሱራፍ_ኤል (ፀጋ) ወርቁ 🌻 🌻@elgraceministry🌻@elgraceministry

  • ወንድማችን በረከትን እንረዳው አልፎም እንርዳው! "እስካልሞትን ድረስ የትኛውም ህመም መጨረሻ አይደለም።" በማለት የሚታወቀው ወንድማችን በረከት "እጅግ በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት የጀርባ አጥንት መገጣጠም (Spina Bifida) በሽታ ተጠቂ ነኝ፤ ሽንቴንም ካካዬንም መቆጣጠር አልችልም። ዳይፐር እጠቀማለሁ፤ ነገር ግን በዚህም አላፍርበትም፤ ወድጄ አላመጣሁትምና" ይላል። አክሎም ከቤት ውጪ በሚሄድበት ጊዜ ሁሉ ዳይፐር መጠቀም የግድ እንደሆነበትና የእለት ተዕለት እንቅስቃሴውን በእጅጉ እንደገደበው ተናግሯል። በረከት 'እንደኔ አይነት ልጆች እንዲወለዱ አይመከርም' ቢልም፤ እርሱ ግን ለ23 አመታት ከዚህ ህመም ጋራ ታግሏል። አንድ ዳይፐር እርሱ ጋራ ትልቅ ትርጉም አለው።  ዳይፐር ከሌለው ከቤት ውጪ መሄድ ስለማይችል አብዛኛውን ጊዜ ቤቱ ውስጥ ይውላል። በረከት 60% የመዳን ተስፋ እንዳለውና  የህክምና ሂደቱን ለመጀመር ብቻ በህንድ ሆስፒታል $25,000 (3.6 ሚሊዮን ብር ገደማ) እንደተጠየቀ ገልጿል። ሁላችንም የበኩላችንን ብንወጣ ይህ ወንድማችንን ሸክም ያቀለዋል። ከወንድማችን በረከት ጎን ለመቆምና የአንድ ዳይፐር መግዣ እንዃን ለማዋጣት እነሆኝ የወንድማችን አካውንት እና ስልክ፦ በረከት በቀለ (Bereket Bekele) የCBE Account፦ 1000460635571 ቴሌብር በስልክ ቁጥር: 0954480005 የወንድማችንን ጥሪ ሰምተን የበኩላችንን እንወጣ! ሼር ማድረግም መርዳት ነው። በረከትን በሁሉም ሶሻል ሚዲያዎች Kimbifida በሚል ታገኙታላችሁ። ━━━━⊱✿⊰━━━━━ @elgraceministry    @elgraceministry         @surtsega

  • #በተመረቅኹበት_ምርቃት_ልመርቃችሁ አምላኬ እንደ ኃይሉ መጠን ለሰልፍ ኃይልን ያስታጥቃችሁ፣ የጠላቶቻችሁ ጀርባ ይስጣችሁ፣ በላያችሁ የቆሙባችሁን በበታቻችሁ ያስገዛላችሁ፣ እንደ ክምር ሸክም የከበዷችሁ፤ እንደምድር ትቢያ ይፈጩ፤ እንደ አደባባይ ጭቃ ይረገጡ፣ ከህዝብ ክርክር ያድናችሁ፣ የማታውቁት ህዝብ ይገዛላችሁ፣ ጮኸታችሁ በአምላኬ በእግዚአብሔር ዘንድ ይሰማ፣ ድላችሁም ከአምላኬ ከእግዚአብሔር ጋራ ይደምደም። 2 ሳሙኤል 22:43-44 አሜን በሉ። ━━━━⊱✿⊰━━━━━ @gtmmbetsega    @elgraceministry

  • 3 авг. 2025 г.385из tsegachurche

    “እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ ለነገሥታትና ለባለ ሥልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤”   1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥1 (አዲሱ መ.ት) https://www.youtube.com/watch?v=XQiYf6tbEM0&list=RDXQiYf6tbEM0&start_radio=1

  • без подписи