ግጥም_በጸጋ
Статистикаበጥበብ ጠቢቡን እናልቃለን። እሱ ሊልቅ እኛ ልናንስ ግድ ነውና። የሆንነውን ካልሆንነው እያበጠርን በሆንነው እና በሆነልን መሃል እንዳንጠፋፋ ብዠታዎችን ለማጥራት እንተጋለን። ሁሉም በሙሽራው መመለስ መልስ እስኪያገኝ .... እንተራረማለን። እንሳሳላለን። እንሞራረዳለን። #ቀን_ሳለ ካሉም #አሁን ነው። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ !!! (የብዕ'ሬን ቀለም ጨርሰው በመልኬ መልክህን ግለጠው።)
- Последний пост
- 4 янв. 2024 г.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 18
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
⛸⛸ #የነፍሴ_ደዋሪ ⛸⛸ ምራዊ ሳቃችን፥ ምታስፈነድቀን፤ ህያው ተስፋችን፥ የምትናፍቀን፤ በደሳሳ ጎጆ፥ ሙላተ ማድጋ፤ በነጠፈ ተስፋ፥ ብርቱ ባለጠጋ፤ የሻገተውን፥ ፈጽሞ አለምላሚ፤ የተቆረጠውን፥ እንደአዲስ ገጣሚ፤ ከጥንት ጥንትን መስራች፥ ከዘላለም ዘላለምን ሰሪ፤ የህይወትን ትርጉም፥ የህይወትን ፍቺ፥ ብቻውን ቀማሪ፤ የሰማይ ሰራዊት እና የምድር አራዊት ደዋሪ፤ እውነተኛው ፈገግታችን፤ ሀዘን የለሹ ደስታችን፤ ምራዊ ሳቃችን፥ ምታስፈነድቀን፤ ህያው ተስፋችን፥ የምትናፍቀን፤ መቼ ነው መምጣትህ? መቼ ነው ምጻትህ? መችም እንደጥንቱ በረት አትወርድም፤ ዳግም ለእኛው፥ በእኛው አትዋረድም፤ ሰማይ እያወጋህ፥ ምድርም ሸሽጋህ፥ ጠባብ ደረት፤ አጭር ቁምጣ አያመጣህም። ምራዊ ሳቃችን፥ ምታስፈነድቀን፤ ህያው ተስፋችን፥ የምትናፍቀን፤ ልክ እንደሙሽሪት፥ ተጠናቃ ሙሽራዋን እንደምትጠብቅ፤ በንጽህና፥ እንደምትናፍቅ፤ መቼ ነው፥ `ምትመጣው? መች አንተን፥ እንጠብቅ? ምራዊ ሳቃችን፤ ምታስፈነድቀን ህያው ተስፋችን፤ የምትናፍቀን አሜን እንደናፈቅንህ፤ አሜን እንደራብከን፤ ሳይቀዘቅዝ ለአንተ ያለን ንጡህ ፍቅር ታጥበን ነፅተን እስክትመጣ እንጠብቅህ። ━━━━⊱✿⊰━━━━━ @gtmmbetsega @elgraceministry @Elgracebot @surtsega @surafeltsegamets
🙏🙏 #ስለበዛ 🙏🙏 መልካሙን 👉 ዕድል እንምረጥ ከእግሮቹ ስር 👉 እንቀመጥ ፀጋው ለእኛ 👉 #ስለበዛ #አንባክን 👉 እዚም እዚያ። የሚያስፈልገው ማይወሰድ 👉 #ጥቂት 👉 #አንድ_ነገር ከአፉ ቃል እየሰሙ ከኢየሱስ ጋር 👉 #አብሮ_ውሎ 👉 #አብሮ_ማደር። 🧣🧣 @gtmmbetsega 🧣🧣 Let us be together for Grace 🧣🧣 @gtmmbetsega 🧣🧣
✅✅ #ባይሆንማ_ኖሮ ✅✅ ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ ይህ #ባይሆንማ_ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው። ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም ከእኔ ጋር እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ። ዮሐንስ 14 (አዲሱ መ.ት) 2-3 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ መልካሙ እረኛ ኢየሱስ ፤ ክርስቶስ ና የወይን ግንዱ የሆነው ያልሆነውን አልያም የማያደርገውን የማይናገር እርሱ በአባቴ ቤት ያለውን ብዙ መኖሪያን ለእናንተ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ ብሎን ከመሄዱ ቀድሞ ባይሆን ኖሮ ምን አስወራኝ፤ የሚሆን ነውና እመኑኝ። ብሎናል። ለምን? ዳግም ከእርሱ ጋር ሊያኖረን በክብር ይመለሳል። ሲመጣ እስከመምጣቱ ድረስ ያላፈርንበትን፤ አምነን የዳንበትን እርሱ በአለበት በአባቱ መንግስት ካህናት ሊያደርገን፤ ከእርሱ ጋር ሊያኖረን ያሰበው አጀንዳውን ሁሉ ፈጽሞና ከውኖ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ የሚመጣው በስሙ አምነው ለሚጠብቁት ሲሆን ለተቀሩት ግን ይመጣባቸዋል። ሙሽራው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽሪትን በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀችውን ሊቀበል በቅርቡ ይመጣል። ቤትን ልትሰራልን ከመሄድህ በፊት ነፍስህን ለነፍሳችን አኑረህ ፍቅርህ አይተናልና በዳግም መምጣትህ ደግሞ ፊት ለፊት እስክናይህ ጓጉተናል። ''ባይሆንማ ባላልከን ነበረ።'' ━━━━⊱✿⊰━━━━━ @gtmmbetsega @elgraceministry @Elgracebot @surtsega @surafeltsegamets ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ #Share #comment and #add_value
🥇✈️ #አንድ_ቀን_እንደቀረው_ኑር ✈️🥇 "ምድር ላይ እያንዳንዱን ቀን እንደ መጨረሻ ቀንህ አድርገህ ኑር ፤ አንድ ቀን ትክክል ትሆናለህ" ቲ.ቢ .ጆሽዋ “ዲያብሎስ #ጥቂት_ዘመን #እንዳለው #አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።” — ራእይ 12፥12 ጊዜውን መያዝ መሄዱንም ማቆም ባይቻልም ጊዜውን አልያም ዘመኑን ግን አንድ ቀን እንዳለው ሰው መዋጀት ይቻላል። አንድ ቀን ዛሬ፤ ዛሬም አሁን፤ አሁን ደግሞ አሁኑኑ ነው። በቀረው ዘመናችን ቀን ሆነ ሌታችን ኢየሱስ ይሁን ኑሮና ወጋችን። @gtmmbetsega @elgraceministry @Elgracebot @surtsega @surafeltsegamets
🎚🎙 #በአጭሩ🎙🎚 እየኖሩ መብራት እየዘሩ ማፍራት በጨውነት መፍካት በመበስበስ መብዛት ደከመ ሲሉት እልፎቹን ማበርታት ስለወንጌል ሲሉ የዕሾህ አክሊል መድፋት ከእውነት ጋር ወግኖ በዚህ አለም መገፋት ከዉሃም ከመንፈስ መወለድ የራስን ባዶ አድርጎ በሰራው መጓደድ እርሱ ኢየሱስ ነው እርሱ ክርስቶስ ነው እርሱ ጌታና አምላክ ነው ብሎ በልብ አምኖ በአፍ መመስከር ቆርጦ መከተል እንደወታደር፤ በእግዚአብሔር ፍቅር፤ በድንቅ ስጦታው ከቶ አለማፈር። ነው ክርስትና በበጉ ደም ላይ ታትሞ የጸና። ________________________ join and share (ውጥን ሸራዬን) @gtmmbetsega @gtmmbetsega @gtmmbetsega @gtmmbetsega
😭😭#ለምን_ዝም_አለ? 😭😭 ለመታረድ እየሄደ ለመሸለት እንደሚሔድ ዝም ያለው መታረዱ ጠፍቶት ሳይሆን እኔን እና አንተን እኔን እና አንቺን አስቦ ነው። ለካ ፍቅር እንደሱ ነው። ━━━━⊱✿⊰━━━━━ 😘😘 @gtmmbetsega 😘😘 😘😘 @gtmmbetsega 😘😘 😘😘 @gtmmbetsega 😘😘
https://t.me/+0VG8PkcT3ZYwMWNk
በአለታላቅ ዙፋን ስፍራ እስክታጣ ተወለደኃል ኢየሱስ በታላቅ ዝቅታ። ለታመምነው መድህን ለጠፋን መገኛ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሰው ሆንክ ስለእኛ። አቤት ትህትና አቤት የዋህነት ንጉስ ቤት እያለ ማረፍ ከወደበረት አቤት ትህትና አቤት የዋህነት በደፈረሰው ዮርዳኖስ መጠመቅ። ሳትበድል መጠመቅህ ለዮሐንስ ዝቅ ማለትህ በእርግብ አምሳል መንፈስ ቅዱስ ወረዶብህ አብ ከላይ ልጄ ብሎ ሲመካብህ ምንም ሳትል ስትሳ ለሰው ስርዓት ስትገዛ አቤት የዋህነት አቤት ትህትና አልቆ መላቅ አስተምረሃልና። እኛን ትወክል ዘንዳ ሁሉን የሆንህ ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ የተፈተንህ መካከለኛችን የአብ ፍጹም ደስታ ጽድቃችን የሆንህ ንጉስ የለበስንህ ጌታ እስከ ሞት ታዘህ እኛን አዳንከን በአብ ቀኝ ሆነህ አብን አወረስከን ከሞት ጣር ነጥቀህ ህይወት ሸለምከን። አቤት የዋህነት አቤት ትህትና የፈጠርከው ሲተፋብህ ያኖርከው ሰው ሲያፌዝብህ ዝም ብለሃልና አቤት የዋህነት አቤት ትህትና "እኔ ነኝ" ስትል ደግመው ደግመው እንዳልወደቁ ብትያዝላቸው ስንቶች ሲሳለቁ? "እኔ ነኝ" አለማለትህ በዝምታህ እኔን ማየትህ አቤት የዋህነት አቤት ትህትና በዘላለም ስሌት ያንዕለት ዝም ብለሃልና አቤት የዋህነት አቤት ትህትና። 👑👑 @gtmmbetsega 👑👑 ትምህርቴ ኢየሱስ ነው 👑👑 @gtmmbetsega 👑👑
🤔 #ኧረ_ከግርግም_እንውጣ 🤔 " በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው። " ሉቃ 2 ፥ 6-7 ✅ በእርግጥ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከብቶች በረት በግርግም ተጠቅልሎ ተቀምጧል ይሁን እንጂ በግርግም አልያም በበረት ውስጥ አልተወለደም። አልተጠቀሰም ተብሎ መታለፍ ሲችል ያልተጻፈ ለምን እንዘባርቃለን? በተጨማሪም ማብራርያ ቢደገፍም እንኳን በረት እንዳልሆነ ግን በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ✅ ሰባሰገሉ (የሩቅ ምስራቅ ጠቢባን) ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን መስዋት (ከርቤ፣ ወርቅና ዕንቁ) የሰውለት በበረት አልያም በግርግም ተጠቅልሎ ሳለ አይደለም። ኧረ በህግ! በተወለደ ጊዜ ያዩት ኮከብ መርቶ ወደ ንጉስ እስኪያደርሳቸው ወደ 2 አመት የሚጠጋን ጊዜ ወስዷል። ለዛም ነው ሔሮድስ ከ 2 አመት ያነሱትን ህጻናትን ያስገደለው። "እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር። ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው። ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።" ማቲ 2፥9-11 🌐 ኧረ መላው የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የውልደት ታሪክን ከበረት አንስፋው እንጂ ‼️ በስምንተኛው ቀን እንኳን ስርዓቱን ሊፈጽም ከቤተመቅደስ ነበረ። 🔔🔔 ♻️♻️ @gtmmbetsega ♻️♻️ ይ🀄️ላ🀄️ሉን ♻️♻️ @gtmmbetsega ♻️♻️
#ለገዳዩ_ሟች #ረቡኒ የራስ ቅል ከምለው ቀራንዮ ጎልጎታ ራሴን ፈትቼ አንተን የሰቀልኩህ ዕለታ ከአንተ የተካለልኩበት ድንበሬ ፈረሰ የተበተበኝ መጋረጃዬ ላይሽር ተቀደደ። ተጠማሁ ስትለኝ ለጥምህ ማብረጃ ሆምጣጤ ለህመምህ የሰጠሁህ ዕለታ ቤተ-መቅደስ ያልኩት ግንብ እየፈረሰ ለአንተ ማደሪያነት ልቤ ተቀደሰ። በጥፊ ስመታህ በተመታህልኝ እጅህን ለችንካር በዘረጋህልኝ ጎንህን በጦር በተወጋህልኝ ''''''''' "አፍታ" ነውር አልባ ደምህን ያፈሰስኩት ዕለታ ትግስት ፍቅርህን በሚገልጥ ዝምታ የማትሞተው ስትሞት በድኩም ስትረታ ዘላለም ላይሻር ታሪኬ ተፃፈ ከሞት ፍርሃት ቀንበር ህይወቴ ተረፈ በአንተ የፃድቅ ሞት የእኔ ሞት አለፈ አብ ረካብህ ልቤ በአንተ አረፈ። ላብህ እስኪሆን ደም ለአብ ፍቃድ ለእኔ መዳን ከሞት ጋራ ስትፋለም ይለፍ ያለከው ሳያልፍ ሲቀር የሞት ፅዋህ ከሬት ሲመር በጨለማ ሳንገላታህ እንደወንበዴ ጥፍር ሳስርስህ ምራቅ ስድቤን ስተፋብህ ጊዜው ሲሆን በእኔው ለእኔው ልትቀጣ በእኔው ለእኔው እንደ ሸላቾች በግ ስትነዳ በዛው ዕለት በዛው ማታ የተቀጣህ የታረድክ ዕለታ አብ እኔን አየ ተከፈለ ዕዳዬ #ብርሃን #አዲስ_ኪዳን #ህያው #አዲስ_ፍጥረት ሆነ መጠሪያዬ። በንጹህ በክቡር ደምህ ዘላለሜ በራ #መሰማት ሆነልኝ በስምህ ስጣራ። አባ አባ ስትል ሞትን ስታታጥር አላስችልም ሲልህ ለእኔ ያለህ ፍቅር ነፍስህን አሳልፈህ ተፈጸመ ያልክ ዕለት ካኖርኩህ መስቀያዬ ላይ በተንጠለጠልክበት ቀን ሳለ ጨለመ ፍጥረት በእኔ አደመ ፀሐይም ብርሃንዋን ከለከለች ምድርም ሙታኖቿን ተፋች ዓለም ብርሃን አጣች በዛች ዕለት እርቃንህን ሆነህ እርቃኔን ሸፈንከው የዕዳ ጽህፈቴን በአንዴ ደመሰስከው ተከፍሏል እያልክ ስንቱን መለስክልኝ የበደሌ ዋጋ ሆነህ እየታየህልኝ። ከቀበርኩህ ስፍራ ከበረታው አለት ብርቱው ድንጋይ ተንከባሎ የተነሳህ ዕለት አብሬህ ሞቼ አብሬህ ተነሳሁ እኔው እየሰቀልኩህ እኔው በሰቀልኩህ በአሳደፍኩህ ነጻው። በቁስልህ ተፈወስኩ በደምህም ነጻው፤ አንተ በሞትከው ሞት ዘላለሊሜን ረታው። በዛው ዕለት በዛው ማታ የተቀጣህ የታረድክ ዕለታ አብ እኔን አየ ተከፈለ ዕዳዬ #ብርሃን #አዲስ_ኪዳን #ህያው #አዲስ_ፍጥረት ሆነ መጠሪያዬ። ለገዳዩ ሟች የፍቅር ረቡኒ በዝምታ ነጎድጓድ ምህረትን አብሳሪ ተፈጸመ ብለህ ነፍስህ ስትሰጥ ላሰቀለችህ ነፍስ ወደመሞት ስትወርድ ያኔ ተረታች ያሰቀለችህ ነፍስ እየበደለችህ ስለእርሷ ስታለቅስ ገዳይህ ሳለው ልጅህ ተብያለው እስከሞት ታምነህልኛል እና ዘላለም አርፋለው ፤ እኖርልሃለው። @gtmmbetsega @gtmmbetsega @gtmmbetsega @gtmmbetsega
━━━━⊱ #አንድ_ርዕሴ ⊰━━━━━ ትናንት አንተን ብዬ ጽፌአለሁኝ ግጥም መሸ ነጋ ብዬ ዛሬ ርዕስ አልለውጥም አንተው ነህ ግጥሜ አንተው ነህ ዜማዬ አንተን ነው የምቀኘው የማልጨርስህን ልቀኝ ምጀምረው። አንተው ነህ ያው አንተ ሁሉንም ያበጀ ዘላለምን አሸምግሎ በዘላለም ያላረጀ። የፍጥረታት ሁሉ ዘዋሪ ጅማሬ የሌለው ጀማሪ አንተው ነህ ያው አንተ ከእቅፍህ የወጣው ልጅህ የተረከህ ለዘመንህ ቁጥር አልባ አመታቶችህ የማያልቁ ታላቅ የለሽ አንድ ትልቁ። አላየሁም ፊትህ ቀርቦ ልጅህን ብሎ ያልጸደቀ ተማምኖብህ ተመርኩዞህ በአጥፊው ወጥመድ የወደቀ። ━━━━⊱✿⊰━━━━━ 👉👉 @gtmmbetsega 👈👈 👉👉 @gtmmbetsega 👈👈
Channel photo updated
😂😂 #ያለማወቅ_ጥግሽ 😂😂 አንቺ ህሙም አለም መዳሐኒት ያጣሽው ደዌዬ ነው ብለሽ መድሐኒትሽን ነው #መስቀል_ላይ_የሰቀልሽው። አሁንም❓ #ተነስቶም❓ ባዶ መቃብሩንም አይተሽ❓ ሰላምሽን የገፋሽው፤ የዘላለምን መድህን ጥሪን ነው ጆሮ ዳባ ያልሽው። የማወቅሽ ጥራዝ ነው ያለማወቅ ጥግጋትሽ መጠበብሽ ዳር ነው ሚታይ ሞኝነትሽ። እውነት ህይወት መንገድ ኢየሱስን ንቀሽ ክርስቶስን ጥለሽ ጌታን አጣጥለሽ ደጅሽ ሰላም የለም በብርቱ የጸና መድሃኒትን ሽሮ መዳን የለምና። #በመልኬ_መልኩ_እስኪሳል! 💡━━━━⊱✿⊰━━━━━ 💡 @gtmmbetsega @gtmmbetsega 💡━━━━⊱✿⊰━━━━━ 💡
💡 #ክርስቶስን_ከአልሰበከ 💡 የነጠፈው ማህፀን ይስሃቅን አቀፈ ከአከተመ ጉልበት ዮሃንስ ተፀነሰ። የዘገየው መድረክዮስ ከፊት ተሰለፈ ታስራ ለነበረች ለአህያይቱ ጊደር ለውርጭላይቱ ዕልፉ ተነጠፈ። የተረሳው ዳዊት ታስቦ ተቀባ ያዕቆብ በስተርጅና በደስታ አነባ አርባውን ተጉዞ እስራኤል ህዝበ እግዚአብሔር ከከንዓኑ ገባ። ይህ ሁሉ ሲሆን ክርስቶስን እንጂ ሌላ ማንን ሰበከ? ከክርስቶስ በቀር ሌላ ማንንስ ሰነቀ? ክርስቶስን ላያበስር ኢየሱስን ላያወራ በርባን ለምን ተፈታ አልአዘር ለምን ተነሳ? ክርስቶስን ሸሽጋ ዓለም፤ ብትመስልም የደመቀች፣ ጩኸት ብቻ የማትበራ፤ የውሸት ትብታብ እንደከርሞ አሁን ዛሬም ጨለማ ነች። #በመልኬ_መልኩ_እስኪሳል! 💡━━━━⊱✿⊰━━━━━ 💡 @gtmmbetsega @gtmmbetsega @elgraceministry 💡━━━━⊱✿⊰━━━━━ 💡
👉👉 #ስለሩቁ_እናስለምድ ከፍ ያለውን ነገረ መመልከት የማይችል ሰው አሁን ላለው ጊዜያዊ ነገር ባሪያ ነው። የነፃነት ያህል ኃላፊነትን የሚጠይቅና #የአርነትን ያህል #የሚከብድ ነገር የለም። በዘመናት መካከል ራስን የመግዛት ያህል ሰውን የሚገራ ነገር የለም። ራሱን የገዛና በነጻነት መሃል ያልፈረካከሰው ሰው ራሱን ለምን እንዲያስለምድ ያውቃል። እንደልማዳችን ራሳችንን ወደ ክርስቶስ እናሳድግ። የነፃነትን ዋጋው የሚያውቀው ቂሊጦ ተከርችሞ ከእጅ እግር ጤና ጋር ተሳስሮ ሰንብቶ ነፃ ነህ ተብሎ የተፈታ ሰው ነው። 💡━━━━⊱✿⊰━━━━━ 💡 @gtmmbetsega @gtmmbetsega 💡━━━━⊱✿⊰━━━━━ 💡
ሙሽሪት ነን ግን? Realy❗️❗️ '''''''''''''''''''''''''°°°°°°°°°°'''''''''''''''''''''''''''''' ሙሽራውን የናፈቀች ሙሽሪትን እንምሰል እንጂ። ወዴት ወዴት ነው? ሙሽሪት ግን አዳፋሽን ያበዛሽ የምትጠብቂውን የዘነጋሽ አይመስልሽም? በይ በበጉ ደም ታጥበሽ ከዙፋኑ ፊት የማታፍርን ሙሽሪትን ሆነሽ ተሰሪ። አሁንም ጊዜ አለ ማለትም በአለቀም ሰዓት መዝለቅ ይቻላል። ብዙ ጊዜ እንዳላት ሆነሽ አትዘባለይ። ዳይ ወደዝግጅት ሙሽራው መምጫው ለሊት ደርሷል። ነቃ ነቃ❗️ ያፈዘዘሽ ይፍዘዝ። ስትጠብቂው ታድያ በተጠንቀቅ። እንደሚመጣ ብቻ ሳይሆን እንደምትሄጂም አትርሺ። ሲወስደሽ ያለአዳፋሽ ይሆን ዘንድ ሁልጊዜ ሁሉንም በማስተዋል አድርጊ። 💡━━━━⊱✿⊰━━━━━ 💡 @gtmmbetsega @gtmmbetsega 💡━━━━⊱✿⊰━━━━━ 💡
Channel photo updated
Channel created