Zebidar Media (ዘቢዳር ሚዲያ)
Статистика# ይህ የዘቢዳር ቻናል የሀገራችን ብሎም የጉራጌ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካ፣ ኪነ ጥበብ፣ ታሪክ፣ ርዕዮት እና ሁለንተናዊ መልክ የሚዳሰስበት የመገናኛ የመወያያ እና የመጦመርያ አውድ ነው!
- Последний пост
- 31 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 979
- 1/48двое суток
- 1 121
- 1/72трое суток
- 1 210
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በአዲስ አበባ-ወልቂጤ መስመር ከባድ ዝርፊያ የፈጸሙ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ ወልቂጤ | ዘቢዳር ሚዲያ (ሐምሌ 24 ቀን 2018) ከአዲስ አበባ ወደ ወልቂጤ በመጓዝ ላይ በነበረ የተሽከርካሪ እና ጭነት ላይ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ከባድ የዝርፊያ ወንጀል የፈጸሙ ተጠራጣሪዎች በፖሊስ እና በጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። እንደቀረቡት መረጃዎች ገለጻ የሰሌዳ ቁጥሩ ማ/ኢ ኮድ 3 - 03175 የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ከኦሮሚያ ጎሮ ወረዳ ወደ ፌንጭር በሚወስደው መንገድ ላይ በመጓዝ ላይ እያለ የፖሊስ የደንብ ልብስ (Uniform) የለበሱና ታጣቂ የሆኑ አካላት ተሽከርካሪውን አስቁመዋል። ተጠራጣሪዎቹ አሽከርካሪውን እና ረዳቱን በጫካ ውስጥ በገመድ ካሰሩ በኋላ ተሽከርካሪውን ይዘው ለመሰወር ሙከራ ማድረጋቸው ተመልክቷል። በወቅቱ ተሽከርካሪው ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው ልዩ ልዩ ውድ ዕቃዎችን ጭኖ የነበረ ሲሆን ዘራፊዎቹ የተጫኑትን ዕቃዎች በከፊል በቀቤና ልዩ ወረዳ ወሸርቤ በኩል ካራገፉ በኋላ የቀሩትን ይዘው ወደ ወልቂጤ ከተማ ሲገቡ መያዛቸው ተገልጻል። የጎሮ ወረዳ ፖሊስ፣ የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ እና የጸጥታ የጋራ ግብረ-ኃይል ከህብረተሰብ በተገኘ መረጃ መሰረት ባደረጉት ከፍተኛ ክትትል ተሽከርካሪውን እና ተጠርጣሪዎቹን ከነታጠቁት ትጥቅ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። ከተያዙት ተጠራጣሪዎች መካከል አንደኛው አብዲ መኪ (በቅጽል ስሙ "ስሪሲክስ") የተባለ አሽከርካሪ እንደሚገኝበት ተጠቅሷል። በጉራጌ ዞን እና በወልቂጤ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጸሙ የዝርፊያና የጸጥታ መዛባት ድርጊቶች የዜጎችን የመንቀሳቀስና የንግድ እንቅስቃሴ አደጋ ላይ እየጣሉ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ህብረተሰቡ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እና መሰል ህገ-ወጥ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ አካላት ላይ የሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት የማጋለጥ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ አጥብቀው ጠይቀዋል። በተጨማሪም ወንጀለኞችን አሳልፈው በመስጠትና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ ረገድ ድጋፍ ላደረጉ ህብረተሰቦች እና የጸጥታ አካላት ምስጋና የቀረበ ሲሆን፣ መሰል የቅንጅት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ ዘቢዳር ሚዲያ ጉዳዩን አስመልክቶ ከዞኑና ከተማው ፖሊስ መምሪያ ተጨማሪ ይፋዊ መግለጫዎችን በመከታተል ለተከታታዮቿ የምታደርስ ይሆናል። ዘቢዳር ሚዲያ፦ እውነትን ለትውልድ! #SecurityNews #Wolkite #GurageZone #CrimeReport #ZebidarMedia #ወልቂጤ #የጸጥታ_ዜና #ወንጀል #ዘቢዳር_ሚዲያ #ህግ_ማስከበር
የስራ ቅጥር ማስታወቂያ ለጸጉርና ውበት ስራ ባለሙያዎች https://vt.tiktok.com/ZSQ4m2Nfm/
видео или голосовое, без подписи
ለወጣቶች የብድር አቅርቦት ለልማት ወይስ ለተጨማሪ ዕዳ? Johns Hopkins University Community service as a pathway to work በተባለ ሀገር በቀል ያልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት አማካኝነት በግብርና ዘርፍ:- በንብ ማነብ ፣ በዶሮ እርባታ እና በፍየልና በግ ማደለብ ሁለት ሺ ዘጠኝ መቶ ወጣቶች ብድር ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ የጉራጌ ዞን መንግስት አሳውቋል። ለወጣቶች ከ6 ወር እስከ 1 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚመለስ በመታወቂያ ዋስትና ብቻ በነፍስ ወከፍ ከ42,000 - 85,000 ብር የብድር አቅርቦት ተመቻችቶ ማሰራጨቱን ገልጿል። መንግስት ለወጣቱ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያደርገው ጥረት የሚበረታታ ቢሆንም፣ የብድሩ አሰጣጥ ሂደትና መጠኑ ግን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በርካታ ጥያቄዎችን ያስነሳል። 1. የገንዘቡ መጠንና የገበያው ሁኔታ በአሁኑ ሰዓት ባለው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትና የሸቀጦች መወደድ፣ 100 ሺህ ብር እንኳን ያልሞላ ብድር አንድን ወጣት ራሱን ችሎ ወደ ሥራ እንዲገባ ለማድረግ በቂ ነውን? ይህ መጠን ለታለመለት የሥራ መስክ መነሻ መሆን ካልቻለ፣ ወጣቱ ገንዘቡን ለእለታዊ ክዋኔው እንዲያውለውና ለተጨማሪ ዕዳ እንዲጋለጥ በር የሚከፍት ነው። 2. የአጭር ጊዜ የመመለሻ ገደብ የ85 ሺህ ብር ብድሩ በ6 ወራት የ42 ሺህ ብር ብድሩ ደግሞ በ1 ዓመት ውስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ ይኖርበታል። ገና ሥራ ላልጀመረ ወይም ገቢ ማመንጨት ላልጀመረ ወጣት ስድስት ወር እጅግ አጭር ጊዜ ነው። ይህ የጊዜ ገደብ ወጣቱ በሥራው ላይ ትኩረት አድርጎ ውጤታማ ከመሆን ይልቅ፣ "ብድሩን እንዴት እመልሳለሁ?" በሚል ስጋት እንዲወጠር ያደርገዋል። 3. ከፖለቲካ ፍጆታ ይልቅ ዘላቂ መፍትሄ ብድሩ ለሁሉም ወጣት ያለ ምንም መስፈርትና ስታንዳርድ በጅምላ ከማከፋፈሉ ይልቅ የተሻለ የሥራ ዕቅድ (Proposal) ላቀረቡና የመስራት ፍላጎቱ ለታየባቸው ውስን ወጣቶች ቢሰጥ የተሻለ ውጤት ያስመዘግባል። "ለወጣቱ ብድር አመቻቸን" የሚለው የይስሙላ ሪፖርትና የምርጫ ሰሞን የፖለቲካ ፍጆታ፣ ከወጣቱ ህይወት መለወጥና ከሀገር እድገት ሊበልጥ አይገባም። ለውጥ የማያመጣና አዋጭነቱ ያልተጠና ብድር ለወጣቱ መስጠት ወጣቱን የዕዳ እስረኛ ማድረግ ነው። በመሆኑም የሚመለከተው አካል የብድሩ መጠን፣ የመመለሻ ጊዜውና ተጠቃሚ የሚሆኑ ወጣቶች የሚመረጡበት መስፈርት ላይ በድጋሚ ቢመክርበት መልካም ነው። ዓላማችን ወጣቱን የሥራ ባለቤት ማድረግ እንጂ የዕዳ ተሸካሚ ማድረግ መሆን የለበትም! ዘቢዳር ሚዲያ - እውነትን ለትውልድ!
видео или голосовое, без подписи
በኢንሴኖ ከተማ አምስት ንፁኃን በግፍ ተገደሉ፤ ጎጎት ፓርቲ ጥቃቱን በማውገዝ የመንግስትን ፈጣን እርምጃ ጠየቀ ኢንሴኖ | ዘቢዳር ሚዲያ (ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ል) በምስራቅ ጉራጌ ዞን፣ ምስራቅ መስቃን ወረዳ ኢንሴኖ ከተማ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ል ከለሊቱ 9:00 ሰዓት ገደማ በተፈፀመ ጥቃት አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ አምስት ንፁኃን ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ። የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ወገኖች ጎጎት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአሰቃቂው ግድያ ህይወታቸው ያለፈው ወገኖች ዝርዝር የሚከተለው ነው:- ዘምዘም ተመስገን (ዕድሜ 46፣ ሴት - እናት) ለይላ ሙባረክ (ዕድሜ 19፣ ሴት - ልጅ) ፍርዶስ ሙባረክ (ዕድሜ 5፣ ሴት - ልጅ) ፉአድ ሙባረክ (ዕድሜ 3፣ ወንድ - ልጅ) ሮዛ ሰባሁዲን (ዕድሜ 5፣ ሴት - ጎረቤት) የፓርቲው ጥሪ እና የአቋም መግለጫ ጎጎት ፓርቲ በግድያው የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ፣ ለሟቾች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል። ፓርቲው በጉራጌ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን "የተጠና እና በመዋቅር የተደገፈ" ሲል የገለጸውን ተከታታይ ግድያ መንግስት በአስቸኳይ እንዲያስቆም ዳግም ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም ፓርቲው፡ => ሃገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ => የዜና ማሰራጫ ተቋማት (ሚዲያዎች)፣ እና => መላው ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያን በንፁኃን ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግድያ እንዲያወግዙ እና ለተጎጂዎች ድምፅ እንዲሆኑ በአክብሮት ጠይቋል። ዘቢዳር ሚዲያ የኢንሴኖን የጸጥታ ሁኔታ በቅርበት የምትከታተል ሲሆን፣ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የሚሰጡ ማብራሪያዎችንም ለእናንተ የምታደርስ ይሆናል። ዘቢዳር ሚዲያ፦ እውነትን ለትውልድ! #Enseno #GurageZone #Ethiopia #SecurityCrisis #HumanRights #ZebidarMedia #ጎጎት #ኢንሴኖ #ሰበር_ዜና #ዘቢዳር_ሚዲያ #ፍትህ
ጎጎት ፓርቲ በወልቂጤ ከተማ የዕጩዎች እና የማኒፌስቶ ማስተዋወቂያ መድረክ ሊያካሂድ ነው ወልቂጤ | ዘቢዳር ሚዲያ (ሚያዝያ 8/2018 ዓ.ል) ጎጎት ፓርቲ የፊታችን እሁድ ሚያዝያ 11 ቀን 2018 ዓ.ል በወልቂጤ ከተማ ከደጋፊዎቹ እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር የሚመክርበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱን አስታወቀ። ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ በገለፀው መሰረት፣ በመድረኩ ላይ የፓርቲው ዕጩዎች ለህዝብ የሚተዋወቁ ሲሆን፣ የፓርቲው መርሃ-ግብር ወይም ማኒፌስቶ ላይም ሰፊ ማብራሪያ ይሰጣል። በተጨማሪም በአካባቢው ወቅታዊ የሰላም፣ የአንድነት እና የልማት ጉዳዮች ላይ ከነዋሪው ጋር ግልጽ ውይይት ለማድረግ አቅዷል። የመወያያ መድረኩ እሁድ ሚያዝያ 11 ቀን ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በወልቂጤ ከተማ በሚገኘው የጆካ (ሁለገብ) አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን፣ ፓርቲው ለአባላቱ፣ ለደጋፊዎቹ እና ለውጥ ፈላጊ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ ጥሪ አቅርቧል። ይህ መድረክ የፓርቲውን የወደፊት ራዕይ በቅርበት ለመረዳት እና ለፍትህ እንዲሁም ለእኩልነት በጋራ ለመቆም የሚያስችል መሆኑን የጠቀሰው ጎጎት ፓርቲ ማንኛውም ፍላጎት ያለው የከተማው እና የአከባቢው ነዋሪ ተገኝቶ ሀሳቡን እንዲያጋራ ጋብዟል። ዘቢዳር ሚዲያ የመድረኩን ሂደት ተከታትላ ለእናንተ የምታደርስ ይሆናል። ዘቢዳር ሚዲያ፦ እውነትን ለትውልድ! Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
видео или голосовое, без подписи
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ "የደንጣ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ" በሃድያ ዞን "የኮንቶማ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በቡታጀራ ከተማ ሊያደርጉት የነበረውን የመስራች ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያደርጉ መከልከሉን ተቃውሞ መግለጫ አወጣ። የመግለጫው ሙሉ ክፍል ከታች ባሉት 2 ገጾች ያገኙታል Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
видео или голосовое, без подписи
የወልቂጤ ዩኒቨሪስቲ ድንቅ ስራ። የሚሰማ እስካለ መናገራችንን እንቀጥላለን! የወልቂጤ ዩኒቨሪስቲ በጉራጌ ዞኖች እንደ የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት ያሉትን ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶችን እንዝለላቸው ከተባለ ብቸኛው የፌደራል ተቋማት ነው ማለት ይቻላል። ይህ ተቋም ለጉራጌ ውክልና የተሰጠ እንደመሆኑ መጠን ከዛሬ ሁለት አመት በፊት ከመግቢያ ዋና በሩ (Main gate) ጀምሮ ጉራጌአዊ መልክና ቁመና ሊኖረው ይገባል የሚል ትችት አቅርበን ነበር። በወቅቱ በርካታ የድጋፍ ሃሳቦችን ብናስተናግድም ጥቂት እማይባሉ ደግሞ በዘረኝነት ሲከሱን ነበር። የዩኒቨሪስቲው ቦርድ ቀድሞ በያዘው ውጥን ይሁን የማህበረሰቡን ፍላጎት መሰረት አድርጎ በወሰደው እርማት በአሁን ሰዓት የማህበረሰቡን ድንቅ የምህንድስና ጥበብ ሊያሳይ የሚችል እጅግ ውብ የሆነ የጉራጌ ጎጆ ቤት ንድፍ (design) በዋና መግቢያ በሩ ላይ ገንብቶ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል። እኛም እንደ ሚዲያ ለማህበረሰቡ ይበጃሉ ያልናቸውን ሃሳቦች በማጋራት፤ የሰሩ እጆችን በማወደስ፤ የተዘነጉ ተግባራትን በመጠቆም፤ የተበላሹ አሰራሮችን በመተቸት፤ የተገቡ ቃሎችንና የተረሱ ስራዎችን በማስታወስ እንቀጥላለን። ከጉራጌ ህዝብ ጥቅም ውጪ የምናጨበጭብለትም ይሁን የምንጮህበት ግለሰብም ሆነ የቡድን የለንም። መለኪያችን የህዝባችን ተጠቃሚነት ብቻ እና ብቻ ነው!። የወልቂጤ ዩኒቨሪስቲ የሰራው ስራ ይበል የሚያሰኝ ነውና አድናቆታችንን ልንቸረው እንወዳለን!። እናመሰግናለን! ሐምሌ 9,2015 ዓ.ል በዘቢዳር ያጋራነው እና የአስተያየት ሰጪዎች ሃሳብ ይህን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ። https://www.facebook.com/share/p/1BagrhA266/ Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
ለ10 ቀን ተሰጥቶ የነበረው የጊዜ ቀጠሮ ነገ ተሰብሮ እንዲታይ ተቀጥሯል። #ዘቢዳር_ሚዲያ:- ህዳር 10/2018 ዓ.ም ሃሙስ አመሻሽ ታስረው ሰኞ ከሰዓት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው የ10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸው የነበረው የጉራጌ ዞንና የወልቂጤ ከተማ አመራርሮችና የፖሊስ አዛዥ የቀጠሮ ቀኑ ተሰብሮ በነገው ዕለት መዝገባቸው እንደሚታይ የደረሰን መረጃ ያሳያል። ነገ ጠዋት በሆሳዕና ከተማ በሚሰየመው ችሎት የሚቀርቡት የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ነጋ አስፋው፤ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ሰለሞን መርሻ እና የወልቂጤ ከተማ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አስቻለው ገብሬ መሆናቸው ታውቋል። የዞንና የከተማ የጸጥታ መዋቅሩ አመራርሮች ለእስር ከተዳረጉ በኃላ ባሳለፍነው ቅዳሜ ከምሽቱ 4:30 አካባቢ የታጠቁ ኃይሎች የከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት ላይ ጥቃት ለመፈጸም ሙከራ አድርገው በጽ/ቤቱ ጠባቂዎች በተከፈተባቸው የአጸፋ ምላሽ ያሰቡትን ሳያሳኩ ለማፈግፈግ ተገደዋል። በወቅቱም የመናኸሪያ አካባቢ ቀበሌ ሊቀ-መንበር ተኩሰው በማቁሰላቸው ሊቀ-መንበሩ ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዱን ምንጮቻችን በዕለቱ ገልፀውልን ነበር። Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
በዞንና በከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ላይ ፍርድ ቤቱ የ10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጠ። #ዘቢዳር_ሚዲያ:- ህዳር 09/2018 ዓ.ል ያሳለፍነው ሳምንት ሃሙስ ለእስር የተዳረጉት የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ ኃላፊ አቶ ነጋ አስፋው፣ የከተማው ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስቻለው ገብሬና የጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሰለሞን መርሻ ትላንት ሰኞ ከሰዓት ፍርድ ቤት ቀርበው ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ የ10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶባቸዋል። Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
የወባ ወረርሽኝ በጉራጌ ዞን #ዘቢዳር_ሚዲያ :- ህዳር 08/2018 በጉራጌ ዞን ቆላማ አካባቢዎች ከፍተኛ የወባ ወረርሽኝ መከሰቱ ተሰምቷል። በርካታ ነዋሪዎች በተለያዩ ጤና ተቋማት ተኝተው እየታከሙ ሲሆን የጤና ተቋማት የመድሃኒት ችግር እንደገጠማቸው የዘቢዳር ምንጮች ገልፀዋል። በሽታው የሰው ህይወት እየቀጠፈ በመሆኑ መንግስትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ፈጣን እርምጃ ሊወስዱ ይገባል ሲሉ ለዘቢዳር ሚዲያ መረጃ ጥቆማ የሰጡ ተወላጆች ገልፀዋል። Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
የቀቤናና የሰባት ቤት ጉራጌ ግንኙነቶች:: ክፍል 1 ★ ቀቤኖች ከሲዳማ አካባቢ መጥተው በሰባት ቤት ጉራጌ አካባቢ ከሠፈሩበት ጊዜ ጀምሮ በልዩ ልዩ መንገድ ይገለጽ የነበሩ ግንኙነቶች በቀቤናና በሰባት ቤት ጉራጌ መካከል ተፈጥረው እንደነበር የሚታወቅ ነው:: ቀቤኖች በሕዝባዊ የፍለሳ እንቅስቃሴ ሲዘዋወሩ ከቆዩ በኋላ። በመጨረሻም ዘናበነርና በወልቂጤ አካባቢዎች በተደራጀና በተጠናከረ ሁኔታ ኑሮአቸውን መምራት የጀመሩ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ስላማዊ ኑር መመስረት ችለዋል ለማለት አያስደፍርም በመሆኑም በተለያዩ ጊዜያት ከአካባቢ የሰባት ቤት ጉራጌዎች ጋር ጦርነቶች ማድረጋቸውን የአካባቢው አፈታሪክ ያረጋግጣል:: በዚያን ጊዜ በአካባቢው የነበሩ የሰባት ቤት ጉራጌዎች የቀቤኖችን መምጣት በዝምታ አልተመለከቱም በተለያዩ ጊዜያትም ጉራጌዎች በቀቤኖች ላይ ባደረጉት ጥቃት የሰፈሩባቸውን ቀበሌዎች ለመልቀቅ ተገደው እንደነበር ይታወቃል:: በቀቤናና በሰባት ቤት ጉራጌዎች ስለተከሰተው አለመግባባትና ስለግንኙነታቸው መሻከር በሚመለከት በቀቤና የትውፊት መረጃ ውስጥ ይገኛል:: አፈታሪኩም እንደሚከተለው ያብራራዋል:: በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የተደረገው ጦርነት በአንድ የመስቀል በዓል ላይ በተጫረ ጠብ እንደነበር አፈታሪኩ ይገልጻል:: በዓሉን ለማድመቅ የቀቤናና የሰባት ቤት ጉራጌ ወጣቶች በምሽት ጭፈራ ላይ እያሉ የቀቤና ወጣቶች የጉራጌ ወጣቶችን በማጥቃታቸው ጠቡ እየሰፋ መጥቶ በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ለተከሰተው ጦርነት በምክንያትነት ይጠቀሳል :: በጦርነቱም ጉራጌዎች ቀቤኖችን ከይዞታቸው እንዳስለቀቁዋቸው ይነገራል:: በዚያን ጊዜ የቀቤኖች መሪ ኬሮ ማጋናሴ እንደነበር ይነገራል:: ይህም መሪ ቀቤኖችን ማፌድ ድረስ መርቶ የመጣ ነው:: ቀቤኖች በይዞተቸው ላይ ለመቆየት ሲሉ ልዩ ልዩ ዘዴዎችን ለመጠቀም ቢሞክሩም ጥረታቸው ባለመሳካቱ ክልላቸውን ለመልቀቅ ተገድደዋል:: በዚያን ወቅት የሰባት ቤት ጉራጌዎች ምሁርን፣ አክሊልንና ሶዶን ይዞ እስከ አይመለል ድረስ ያሉትን መሬቶች በይዞታቸው ሥር አድርገው ይኖሩ ነበር:: ቀቤኖች በይዞታቸው ሥር ያደረጉትን አካባቢ ከሰባት ቤት ጉራጌዎች በተደረገባቸው ግፊት ለቅቀው ከመሄዳቸው በፊት መሪያቸው አንድ ዕቅድ ወጥኖ እንደነበር አፈታሪኩ ያመለክታል:: ቀቤኖች አህዮቻቸውንና ዶሮዎቻቸውን ቤታቸው ውስጥ አስረው በሌሊት እንዲለቁ መሪያቸው ኬሮ መጋናሴ መመሪያ አስተላለፈ በተላለፈላቸው መመሪያ መሠረት ቀቤኖች አህዮቻቸውና ዶሮዎቻቸውን ቤታቸው ውስጥ አስረው ማፌድን በሌሊት ለቀቁ:: ሰባት ቤት ጉራጌዎች በቀቤኖች ላይ ጥቃት ለማድረስ በማለዳ ወደ ማፌድ ሲንቀሳቀሱ አንድም ሰው በመንደሩ ውስጥ ሊያገኙ አልቻሉም:: ያገኙት ነገር ቢኖር በየቤቱ ውስጥ የታሠሩትን አህዮችንና ዶሮዎችን ብቻ ነበር:: በመሆኑም ቀቤኖች ማፌድን መልቀቃቸውን ሲያረጋግጡ ወደ ክልላቸው ወደ ሰባት ቤት ጉራጌ ተመለሱ:: በአፈታሪኩ እንደተገለጸው ከሆነ ይህ ሁኔታ የተከሰተው ቀቤኖች ማፌድ ላይ ሠፍረው ኑሮአቸውን በሚገባ መመስረት ከጀመሩ በኋላ ነበር:: የሰባት ቤት ጉራጌዎች ወደ ክልላቸው ከተመለሱ በኋላ ኬሮ መገናሴ ዘናበነር ድረስ ሄዶ በአካባቢው ላይ ቅኝትና ስለላ ካከናወነ በኋላ ክልሉ ለሕዝቡ ኑሮና ለከብቶች አመቺነቱን አረጋገጠ:: በመጨረሻም ሕዝቡ ወደዚህ ሥፍራ ተንቀሳቅሶ እንዲሠፍርበት አደረገ ኬሮ መገናሴ ሕዝቡን መርቶ ዘናበነር ከመጣ ከጥቂት ዓመታት በኋላ እንደሞተ ይነገራል:: ይህ ፅሁፍ የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) 1988 ዓ.ል ወማ የቀቤና ብሔረሰብ ባህልና ታሪክ በሚል ካሳተመው መጽሃፍ የተወሰደ ነው። ገጽ 28-31 Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
የጫሙት ሽካ መጽሐፍ ትረካ በኤፍ.ኤም ሬዲዮ ሊቀርብ ነው። #ዘቢዳር_ሚዲያ:- ህዳር 05/2018 ከ60 ዓመታት ፊት በደራሲ አጋዝ ገብረኢየሱስ ኃ/ማርያም የተጻፈው የተፃፈው የጫሙት ሽካ የጉራግኛ መጽሐፍ ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ በወልቂጤ ኤፍ ኤም 89.2 ሬዲዮ መቅረብ እንደሚጀምር አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። በየሣምንቱ ሰኞ ከምሽቱ 3:20 እና በድጋሚ እሑድ ምሽት 2:30 በወልቂጤ ኤፍ ኤም እንደሚቀርብ ተገልጿል። የጫሙት ሽካ በሬዲዮ የቀረበ የመጀመሪያው የጉራግኛ ስራ ይሆናል። Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ