tgindex
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

Статистика

ዜና ከምንጩ

Последний пост
15:12
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
53
Всего постов
80
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
32 751
+27 за 3 дн.
Сутки
+11
+0,03%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
3 287
40 постов
Вовлечённость
10,0%
к подписчикам
Постов в день
7,6
всего 80
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
по 5 постам
1/24сутки в ленте
3 735
1/48двое суток
4 280
1/72трое суток
4 616

Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.

Посты

  • 15:121 00571

    видео или голосовое, без подписи

  • 15:119871

    видео или голосовое, без подписи

  • 14 авг.3 61794

    ቦይንግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የመከስከስ አደጋ ጉዳት ለደረሰበት አየርላንዳዊው ተጎጂ ቤተሰብ 29 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተወሰነ ዓርብ፣ ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን መከሰክስ ሕይወቱን ላጣ የአየርላንድ ዜጋ ቤተሰቦች የአሜሪካ ፍርድ ቤት የ29 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፈላቸው ወሰነ። ከዚህ ቀደም የአንድ ኬንያዊ ተጎጂ ቤተሰብ ጋር የ3 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት አድርጎ ነበር። ይህም ጉዳይ አሁን ላይ እንደ አዲስ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየተዘገበ ይገኛል። አሜሪካዊው ደግሞ 49 ሚሊዮን ዶላር መከፈሉም ተዘግቧል። በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡት የአየርላንድ ዜጋ እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም መሐንዲስ የነበሩት የ39 ዓመቱ ማይክል ራያን ቤተሰቦች፣ ጉዳዩን ወደ አሜሪካ ፍርድ ቤት በመውሰዳቸው የ29 ሚሊዮን ዶላር ካሳ እንደተወሰነላቸው ተዘግቧል። ማይክል ራያን በላይቤሪያ የኤቦላ ወረርሽኝ ወቅት እና በኢትዮጵያ በሰብዓዊ ረድኤት ሥራዎች ላይ ያገለገሉ ባለሙያ ነበሩ። በሌላ በኩል በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡት 32 ኬንያውያን መካከል የአንዱ ተጎጂ ቤተሰብ፣ እ.አ.አ በ2020 ከፍርድ ቤት ውጭ በሚደረግ ስምምነት የ3 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ለማግኘት ተስማምቶ የነበረ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ ተጎጂዎች ከፍርድ ቤት ውጭ በምስጢር ስምምነት ማድረጋቸውን ዘገባዎች አስታውሰዋል። ባለፈው የግንቦት ወር ደግሞ የዚሁ አደጋ ተጎጂ የነበረችው አሜሪካዊቷ ሳምያ ስቱሞ ቤተሰቦች በሌላ የአሜሪካ ፍርድ ቤት የ49.5 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተወስኖላቸዋል። ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ናይሮቢ በመጓዝ ላይ ሳለ በቢሾፍቱ አቅራቢያ በተከሰከሰው በዚሁ በረራ ላይ የነበሩት 157 ሰዎች በሙሉ ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። በጉዳዩ ላይ የካሳ ክፍያ መጠን ልዩነት ሊኖር የቻለው አብዛኞቹ ተጎጂዎች ከኩባንያው ጋር ከፍርድ ቤት ውጭ በግል ስምምነት በመጨረሳቸው እና ጥቂቶች ደግሞ ጉዳያቸውን ወደ አሜሪካ ፍርድ ቤት በመውሰዳቸው ነው። አደጋውን ተከተሎ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በዓለም አቀፍ ደረጃ  ከበረራ የታገዱ ሲሆን፣ የቴክኒክና የሶፍትዌር ማሻሻያዎች ከተደረጉላቸው በኋላ  ወደ አገልግሎትም መመለሳቸው ይታወሳል።    ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲ t.ly/mxA

  • 14 авг.3 29312
  • 14 авг.3 228117

    በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግርና የሰላም ጉዳይ እልባት እስካላገኙ ድረስ ስደት ይቀጥላል ሲል አይ.ኦ.ኤም. አስጠነቀቀ  ዓርብ፣ ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) ከኢትዮጵያ  የምስራቁን  መስመርን  ተከትሎ  የሚደረገው ፍልሰት በዓመት  22 በመቶ ቀንሶ ወደ ሃምሳ ሺህ ስድስት መቶ  መድረሱን  ያስታወቀው ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅተ የኢኮኖሚ ችግር እና የሰላም ሁኔታ ካልተፈታ እንዲሁም ኢልኒኖ  ሊያደርሱት በሚችሉት ተጽዕኖ የፍልሰተኞች ቁጥር መጨመሩ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ፣ እ.አ.አ የ2026 የመጀመሪያ ሩብ ዓመትን አስመልክቶ  ባወጣው ሪፖርት ላይ እንደገለፀው ከሆነ ኢትዮጵያ የፍልሰተኞች ዋና የመነሻና የመመለሻ ማዕከል ሆና  ቀጥላለች፡፡   ይህ ሁኔታ የመንገድ መስተጓጎል ቀጥተኛ ውጤት ነው ያለ ሲሆን በየካቲት ወር የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በዋና ዋና የስደት መተላለፊያ በሆኑ መንገዶች ላይ ያሰማሯቸው ኃይሎች እና በጋላፊ–ዮቦኪ ድንበር አቅራቢያ የወታደሮች መኖር ሪፖርት መደረጉ  ፍልሰተኞች በሌሊት በደዌሌ-አሊ ሳይቤህ በኩል እንዲሻገሩ አስገድዷል ብሏል፡፡   ሪፖርቱ አክሎም፣ ከኢትዮጵያ የሚወጡ ፍልተሰኞች  ቁጥር ከ65,200 ወደ 50,600 ሲቀንስ፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 22 በመቶ  ዝቅ ማለቱንም አመልክቷል፡፡   በጅቡቲ ኦቦክ የባህር ዳርቻ በኩል የሚደረገው ጉዞ በ15 መቶ  ዝቅ ማለቱን የገለጸው አይ.ኦ.ኤም፣ይህ የሆነው ደግሞ ጅቡቲ በተያዘው የአውሮፓውያኑ ዓመት ባካሄደችው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ወቅት  የተጠናከሩ የጸጥታ እርምጃዎች በመወሰዳቸው እንደሆነ አንስቷል፡፡   የህገ-ወጥ የስደተኛ አስተላላፊ መስመሮች (ኔትዎርክ) የነበረውን ክፍተት ሞልተዋል የሚለው ሪፖርቱ፤ ቦራማ፣ ዋጃሌ፣ ሀርጌሳ፣ በርበራ፣ ቡራኦ እና ኤሪጋቮን ከቦሳሶ ጋር የሚያገናኙ ኔትወርኮች መስራታቸውን የቀጠሉና ተግባራቸውንም እንዳስፋፉ አስታውቋል።   ፍልሰተኞችን የመያዝና ወደ ሀገራቸዉ  የመመለስ  አደጋዎች ቢኖሩም ወደ ቦሳሶ  መጓዛቸውን  የሚስረዳው  ሪፖርቱ፣ ይህም  ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ለመጓዝ  ባለው መስመር ላይ ቅድመ-ሁኔታ የሌለው ፍላጎት አሳይቷል ብሏል። ፍልሰት ያለው የሰብአዊ ተጽዕኖው ከባድ ነው የሚለው ሪፖርቱ፣  በሶማሊያ ያሉ ስደተኞች ቁጥር  እ.አ.አ ከመጋቢት 2025 ላይ 2,649 የነበረ ሲሆን መጋቢት 2026 ደግሞ  7,760 ከፍ ብሏል።   ሪፖርቱ እንዳመለከተው፣ በቦሳሶ 2,200 ያህል  ሕፃናት በብዝበዛ፣ በጥቃትና እና በረዥም ጊዜ መሰናከል ላይ ከፍተኛ ተጋላጭነት ገጥሟቸዋል፡፡   ሪፖርቱ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት፣ ኤርትራ እ.አ.አ  በታህሳስ 2025 ከኢጋድ መውጣቷን ተከትሎ በሰሜን ኮሪደር ዙሪያ ላሉ የስደት ቦታዎች ያለውን ስጋት እንዲiጨምር እንዳደረገው ገልጿል። ሪፖርቱ በማጠቃለያው ኢኮኖሚያዊ  ምክንያቶች  እስካልተፈቱ  ድረስ ስደተኞች የትኛውንም መንገድ ቢመርጡ ወይም በመንገድ ላይ ምንም አይነት አደጋ ቢገጥማቸው የስደተኞች ቁጥር ከፍተኛ ሆኖ ይቆያል  ሲል ደመድሟል፡፡ ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲ t.ly/mxA

  • 14 авг.2 5623
  • 14 авг.2 92883

    በጃፓን ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ  የሰዎች ህይዎት ሲያልፍ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ትራንስፖርት ላይ እክል ፈጥሯል ተባለ ዓርብ፣ ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) በጃፓን ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ  አደጋ በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል በሚገኘው ቺባ  በተሰኘ ግዛት ቢያንስ ስድስት ሰዎችን ለሞት እና  አምስት ሰዎችን ለጉዳት የዳረገ ሲሆን የትራንስፖርት እና የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ላይ እክል ፈጥሯል ተባለ። ከ ዋና ከተማዋ ቶኪዮ አቅራቢያ በምትገኘው ቺባ የተከሰተው ከባድ ዝናብ በሰዓት ከ100 ሚሊሜትር በላይ መዝነቡን የአካባቢው ባለሥልጣናት የገለፁ ሲሆን ይህም በነሐሴ ወር ከሚጠበቀው አማካይ የዝናብ መጠን በሦስት እጥፍ የሚጠጋ ነው የተባለ ሲሆን  በጃፓን ከተመዘገቡ የዝናብ መጠኖች ከፍተኛው መሆኑ ተነግሯል። የጃፓን የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የዝናቡን ሁኔታ ሲያስረዱ “ከዚህ በፊት ያልታየ” በሚባል ደረጃ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ሞቃትና እርጥበት የበዛበት አየር ከላይ ካለው ቀዝቃዛ አየር ጋር በመገናኘቱ የከፋ የአየር ሁኔታ መፈጠሩን አስረድተዋል። ይህ  ዝናብ ከ20 ሺህ በላይ ቤቶች ኤሌክትሪክ አገልጎት ዉጭ ሲያደርግ በቶኪዮ ናሪታ አየር ማረፊያም ወደ 7 ሺህ የሚጠጉ ተጓዦች ሌሊቱን በአየር ማረፊያው እንዲያሳልፉ አስገድዷቸዋል ተብሏል ። በተጨማሪም በከባድ ዝናቡ ምክንያት የጎርፍና የመሬት መንሸራተት የተከሰተ ሲሆን ከ100 ሺህ በላይ አባወራዎች ቦታቸውን ለቀው ደህንነቱ  ወደተጠበቀ ስፍራ እንዲሄዱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። በርካታ የባቡር መስመሮችም አገልግሎታቸውን ሲያቋርጡ አንዳንድ ዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች ጭምር መዘጋታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ። ባለሥልጣናቱ እንደገለፁት ከሆነ በተለይም የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ሊከሰት በሚችልባቸው አካባቢዎች ላይ የአደጋ ስጋት መኖሩን በመግለጽ ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል። የቺባ ግዛት አስተዳዳሪ ቶሺሂቶ ኩማጋይ ሁኔታው በጃፓን የአየር ሁኔታ ታሪክ እንኳን እጅግ ያልተለመደ ክስተት ሲሉ ገልጸውታል። አክለዉም በቀደሙት በርካታ የአደጋ ጊዜያት ላይ ምላሽ ቢሰጡም እንደዚህ ያለ ሁኔታ ግን አጋጥሟቸው እንደማያውቅ ተናግረዋል። በጎርፍ በተሞላ መንገድ ውስጥ በመኪናዋ ተይዛ የሞተች ሴት ከሟቾቹ መካከል መኖሯን የገለፁት ባለስልጣናቱ ሌሎች ሁለት ሰዎችም በመንገድ ላይ ወድቀው ሕይወታቸውን እንዳጡ ገልፀዋል። በሌላ በኩል፣ በክልሉ የተከሰተው ከባድ የአየር ሁኔታ ከጃፓን ባሻገር በሌሎች የእስያ ሀገራትም ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑ ተገልጿል። በፊሊፒንስ በጎርፍ አደጋ ስጋት ምክንያት በሰሜናዊ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችና የመንግሥት ቢሮዎች በድጋሚ የተዘጉ ሲሆን  በዚህ ሳምንት ጃፓን፣ ፊሊፒንስና ቻይና በተከታታይ በተከሰቱ አውሎ ነፋሶች ከተጎዱ ሀገራት መካከል መሆናቸው ተመላክቷል ። ባለሥልጣናት የማዳን ሥራዎችን በማጠናከር በቅድሚያ የሰዎችን ሕይወት ለማዳን ትኩረት እንደሚሰጡ ገልጸዋል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲ t.ly/mxA

  • 14 авг.2 98374

    ማሊ 82 ወታደሮቿ ከ አማጺ ኃይሎች መለቀቃቸውን አስታወቀች ዓርብ፣ ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) በሰሜን ማሊ የሚገኙ ተገንጣዮች  በሚያዝያ ወር  በመንግስት ኃይሎች ላይ በተካሄደው ጥቃት ወቅት የተማረኩ  ወታደሮችን ጨምሮ 82 ወታደሮችን  መልቀቃቸዉን  የማሊ ጦርና የአማፂያን ቡድኑ ቃል አቀባይ አስታዉቀዋል፡፡ የማሊ ጦር ባወጣው መግለጫ “ነፃ የወጡት ወታደሮች አሁን ደህንነታቸው የተጠበቀ ሲሆን በሚመለከታቸው ባለሥልጣናት እንክብካቤ እየተደረገላቸው ነው” ነው በማለት አስታውቋል። የተገንጣዩ አዛዋድ ነፃነት ግንባር ቃል አቀባይ  ሙሀመድ ኤልማኡሉድ ራማዳን በኩሉ ወታደሮቹ መለቀቃቸውን አረጋግጠዋል። ማሊ ከአልቃይዳ ና ከእስላማዊ መንግስት ቡድን ጋር ትስስር ካላቸው ታጣቂዎች የእስልምና እና ሙስሊሞች ድጋፍ ቡድን (ጀኒም)  ጨምሮ  እንዲሁም በሰሜን በኩል ደግሞ በቱሬግ ከሚመራ ተገንጣይ አመፂ ሳቢያ ከአስር አመታት በላይ በደህንነት ስጋት ምክንያት ስትቸገር ቆይታለች፡፡ በጀኒም እና በቱሬግ ተገንጣዮች ጥምረት በመፍጠር በሚያዝያ  ወር በሀገሪቱን ዋና ከተማ ባማኮ የሚገኘውን አውሮፕላን ማረፊያ፣ በአቅራቢያ የሚገኘውን ካቲ የተሰኘ ጦር ሰፈር  እንዲሁም በ በርካታ የሰሜን እና መሃል ከተሞችን ዒላማ በማድረግ የተቀናጀ ጥቃት ሰንዝረዋል። ይህንንም  ተከትሎ የሚፈፀሙ ጥቃቶች  በቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሱ  ይገኛል፡፡   የተገንጣዩ  ቡድን ቃል አቀባይ እንዳሉት ከሆነ ወታደሮቹ የተለቀቁት በሰብዓዊ ምክንያት ሲሆን አንዳንዶቹ  ውታደሮች እ.አ.አ ከ2023 ጀምሮ እስረኞች ሆነው የቆዩ ናቸው። አክሎም  118 የሚሆኑ የማሊ ወታደሮች አሁንም በምርኮ ይገኛሉ ብለዋል። ማሊ በማዚያ ወር ላይ  የተፈጸሙባትን ጥቃቶችን ተከትሎ  አማፂያንን ለመዋጋት የምትከተለውን ስትራቴጂ ድክመት ያጋለጠ ነው የተባለ ሲሆን  እንደ ፈረንሳይ ካሉ የቀድሞ አጋሮቿ ጋር   ያላትን  ትብብር በማስወገድ  በወታደራዊ  መንግስት ከሚተዳደሩ ጎረቢቶቿ እና ሩሲያ  ጥገኛ በመሆን  ያላትን ትብብር እያጠናከረች ይገኛል ተብሏል።   የወታደሮቹ መለቀቅ የታወጀው የማሊ ፕሬዚዳንት የ20 ዓመት እስራት የተፈረደበትን ያን ቬዚሌር የተሰኘ ፈረንሳዊ  በይቅርታ  እንዲፈታ  ባደረጉበት  ዕለት ነው።   በማሊ ለፈረንሳይ ኤምባሲ ይሰራ የነበረው ያን  እ.አ.አ  በነሐሴ 2025 የታሰረው  ሀገሪቱን ለማተራመስ  በተደረገ ሴራ ውስጥ የስላላ ተግባር  አከናዉኗል በሚል ክስ ተመስርቶበት ነበር። የማሊ መንግስት ባወጣው መግለጫ ይቅርታው የፍርድ ቤቱን ውጤት የማይሽር እንደሆነ ና ግለሰቡ ወዲያውኑ ሀገሩቱን ለቆ መውጣት እንዳለበት  አስታውቋል።    ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲ t.ly/mxA

  • 14 авг.3 01553

    በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ሙስና ጉዳይ በተጠረጠሩ የስራ እና ክህሎት ሚኒስተር ባለሙያዎች ላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜን ፈቀደ ዓርብ፣ ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሥርዓትን በማጭበርበር፣ በጉቦና ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም የኤጀንሲዎችን እገዳ እንዲነሳ ማድረገን ጨምሮ በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለሙያዎችና “ግብረ አበሮቻቸው” ላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መፈቀዱ ተገለፀ ። ተጠርጣሪዎቹ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪዎቹ እገዳ የተጣለባቸውን የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች ፈቃዳቸው እንዲታደስ ወይም እገዳው እንዲነሳ በጉቦ እና ከባንክ የመጡ መስለው በተዘጋጁ ሐሰተኛ ሰነዶች ተጠቅመዋል ብሏል ። ከዚህ በተጨማሪም ሥልጠና ላልወሰዱ ዜጎች የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶችን በሐሰት በማዘጋጀት እና በመስጠት በከባድ የሙስና ወንጀል ተሳትፈዋል ብሏል። ፖሊስ ጉዳዩ በተደራጀ መንገድ የተፈጸመ እና ለመንግሥት ሊገኝ የሚገባውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ሊያሳጣ የሚችል ውስብስብ የሙስና ጉዳይ መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም ምስክሮችን ለመጠየቅ፣ ከተለያዩ ተቋማት ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ፣ የደረሰውን የጉዳት መጠን በኦዲት ለማረጋገጥ እና ከጉዳዩ ጋር ተያይዘው ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ 14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቋል። የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ፖሊስ ያቀረበው ጥርጣሬ በቂ እንዳልሆነና የእያንዳንዱ ተጠርጣሪ ተሳትፎና የተፈጠረው ጉዳት በግልጽ እንዳልተለየ ተከራክረዋል። አንዳንድ ተጠርጣሪዎችም ቋሚ ሠራተኞች ሳይሆኑ በፕሮጀክቱ ላይ በኮንትራት የተቀጠሩ መሆናቸውን በመጥቀስ የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ የሁለቱንም ወገኖች ክርክር ካዳመጠ በኋላ በፖሊስ የምርመራ መዝገብ በቂ ጥርጣሬ መኖሩን ገልጾ፣ የእያንዳንዱ ተጠርጣሪ ተሳትፎ በግልጽ ተለይቶ መቅረብ እንዳለበት አስገንዝቧል። በዚህም መሠረት በሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ 14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል። በሌሎች 8 ተጠርጣሪዎች ላይ ፖሊስ 14 ቀናት ቢጠይቅም፣ ችሎቱ ለአንዳንዶቹ 13 ቀናት እና ለሌሎች 12 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለነሐሴ 18 እና 19 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል። በቀሪዎቹ 3 ተጠርጣሪዎች ላይ የጊዜ ቀጠሮ ውሳኔ ለመስጠትም ለዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ቀጠሮ እንደተሠጠ አዲስ ማለዳ ከፌደራል የስነምግባር እና ፀረሙስና ኮሚሽን ያጋራው መረጃ ላይ ተመልክታለች ። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲ t.ly/mxA

  • 14 авг.2 7821
  • 14 авг.3 552125

    የፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሉ  በሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር ላይ የምትገኘውን ኩርሙክ ከተማ መቆጣጠሩን አስታወቀ ዓርብ፣ ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች(አር.ኤስ.ኤፍ.) ከሱዳን ጦር ጋር ባደረገው ከባድ ውጊያ በብሉ ናይል  ክልል የሚገኘውን እና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላትን እና ከኢትዮጵያ ጋር የድንበር ከተማ የሆነችውን ኩምሩክን በትናንትናው ዕለት ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታወቀ። የጦር ሰራዊቱ በበኩሉ ቦታውን ለቅቆ የወጣው በተከታታይ ለሶስት ቀናት ያህል ከኢትዮጵያ በድሮን እና በከባድ መሳሪያ ሰለተደበደብኩ ነው ብሏል፡፡ የቡድኑ ቃል አቀባይ ባወወጣው  መግለጫ ላይ የአር.ኤስ.ኤፍ.  ታጣቂዎች ከሱዳን  ጦር  ጋር ያደረጉትን ከባድ ውጊያ ተከተሎ ከተማዋን መቆጣጠራቸውን፣ በርካታ የጦር መሳሪያዎችንና ጥይቶችን መማረካቸውን ገልጿል ። የወታደራዊ ምንጮች እና የአካባቢው አስተዳደር እንደገለጹት ከሆነ ከሆነ ደግሞ የሱዳን ጦር ከተማዋን ለቅቆ ለመውጣት የተገደደው ከኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ለሦስት ቀናት ያህል በተከታታይ በተቃጡ የረጅም ርቀት ድሮኖች እና የከባድ መሳሪያ ድብደባዎች ምክንያት መሆኑን  ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል። ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይሉ የኩርሙክን ከተማ የተቆጣጠረው ከሁለት ቀናት በፊት በብሉ ናይል ክልል በከፈተው ሰፊ ጥቃት ሌላኛዋን ቁልፍ የድንበር ከተማ ቄሳን ከተቆጣጠረ በኋላ ነው። የሱዳን ጦር በቅርበ በዚሁ አካባቢ የተቃጣበትን ጥቃት መመከቱን ማስታወቁ አይዘነጋም። ከብሉ ናይል ክልል ዋና ከተማ ኤድ ዳማዚን በ136 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ኩርሙክ፣ ወደ ኢትዮጵያ የሚያስኬድ ትልቅ የድንበር ማቋረጫ እና የወታደራዊ አቅርቦት መስመር በመሆኗ በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ቦታ እንደሆነች እና ተፈላጊነቷም በዛው ልክ ነው መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡ ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲ t.ly/mxA

  • 14 авг.3 34311
  • 13 авг.4 033354

    አንድ ወር የፈጀው ምክክሩ አከራካሪ የነበረው የአዲስ አበባ ጉዳይን ጨምሮ በስምንቱም አጀንዳዎች ላይ ስምምነት ተደርሷል አለ ሐሙስ፣ ነሐሴ 07 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) ሐምሌ ስምንት የጀመረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በያዛቸው ስምንቱም አጀንዳዎች ተመካካሪዎች መስማማታቸውን አስታወቀ።   ስምምነት የተደረሰባቸው አጀንዳዎች ውስጥ በመንግስት አደረጃጀት እና በሌሎችም ላይ በልዩነት የተያዙ ምክረ ሀሳቦች መኖራቸውን አዲስ ማለዳ ከተሳታፊዎች ሰምታለች። ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየው ምክክሩ ከፌደራል ከተሞች ጉዳይ፣ ፓርላሜንታዊን ወይስ ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት፤ በሀገር ግንባታ ጉዳይ የሰንደቅ ዓላማ እና ታሪክ ጉዳዮች እና ሌሎችም ሰፊ ጊዜ የወሰዱ እና  የተለያዩ ሃሳቦች የቀረቡባቸው ናቸው። ኮሚሽኑ ይህ ስምምነት ተጠናቅቆ ሃሳቦችን ለሚያጣጥም እና የሚቃረኑ ነገሮች እንዳይኖሩ እንዲሁም የሃሳብ ድግግሞሽ እንዳይኖር የሚሰራ ቡድን ላይ ተሸጋግሯል ያለ ሲሆን በምክክር ጉባኤው  ወቅት አለመግባባቶችና ግጭቶች መኖራቸው የምክክሩን አስፈላጊነት ያሳየ እና ለዚህም ያደረሰ እንደሆነ አስታወቋል። የሀገራዊ  ምክክር ኮሚሽን  በምክክር ጉባኤው  የምክክር ሂደት ወቅት “አለመግባባቶችና ግጭቶች አልነበሩም አይባልም” ያለ ሲሆን እንዲህ መሰል ልዩነቶች ማጋጠማቸው ምክክሩ አስፈላጊ  መሆኑን ያረጋገጠ ነው ብሏል። ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ(ፕሮፌሰር) ከዚህ ቀደም አለመግባባቶች እና ግጭቶች ተጠባቂ እንደሆኑ ማንሳታቸው አይዘነጋም። በ500 ተሳታፊዎች ተዋቅረው ሲመካከሩ የቆዩት 8ቱ ቡድኖች በሂደቱ ያጋጠሟቸውን ግጭቶችና አለመግባባቶች በመደማመጥና በመነጋገር ተፈትተው ወደ አንድ የጋራ አማካይ ሃሳብ በመድረስ ላይም እንደሆኑ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጸዋል። ኮሚሽነሯ አክለውም አብዛኞቹ አጀንዳዎች ላይ ተመካካሪዎች በምክረ ሃሳቦቹ ላይ ፊርማቸውን በማስፈር  ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል። የፌደራል ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬድዋ  ጉዳይ አከራካሪ እና የሃሳብ ፍትጊያ እንዲሁም በስልታዊ ቡድን ወቅት አለመግባባት ከታየባቸው ጉዳዮች ውስጥ ነው። አዲስ ማለዳ ከተሳታፊዎች እንደ ሰማችው ከሆነ “አንዳንድ አጀንዳዎች ላይ በልዩነት የተያዙ እና ከአመራሮች በኩል ቀጥተኛ ያልሆነ ጫና እንደሚደርስ” አንስተዋል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ዋና ኮሚሽነሩ ከዚህ ቀደም ማንም ሊመካከር እንጂ ጫና ሊፈጥር እንዳልመጣ ማንሳታቸው ይታወሳል። የምክረ-ሃሳቦች  የሚያጠናክር ቡድን የተዋቀረ ሲሆን  ከስምንቱም እያንዳንዱ 15 ሰዎችን የያዘ 120 ተመካካሪዎች ተመርጠዋል። እነኚህ ከስምንቱም ቡድኖች የተመረጡ አባላት ያሉት ቡድን ሥራውን ጀምሯል የተባለ ሲሆን ተግባሩም የተዘጋጁትን ምክረ-ሃሳቦች ማጣጣም፣ ተቃራኒ ሃሳቦችን እንዳይኖሩ ማድረግ እና ድግግሞሾችን በማስቀረት የአንድ ወጥነት ባህሪ እንዲኖራቸው  በማድረግ እንደሚሰራ አስታውቋል። ኮሚሽኑ አክሎም ከግለሰቦች፣ ከቡድኖች እንዲሁም ከፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረቡ ቅሬታዎችን በኮሚሽኑ የቅሬታ አፈታት ሥነ-ስርዓት መሰረት የማጥናት፣ የመመርመርና ውሳኔ የመስጠት ስራ እየተከናወነ ይገኛል ያሉት ምክትል ኮሚሽነሯ ሒሩት ገብረ እግዚአብሔር ናቸው። እንደ አብን እና እናት ያሉ ፓርቲዎች በምክክር ሂደቱ ላይ የገለልተኝነት ጥያቄ ማንሳታቸው ይታወቃል። ኮሚሽነሯ አክለውም ምክክሩ የሦስት አራተኛ  ያህል ስራ መጠናቀቁ የገለፁ ሲሆን  የምክክሩን “ውጤታማነት” ለኢትዮጵያ ህዝብ “የማበሰር ስራ” ይከናወናል ብለዋል። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲ t.ly/mxA

  • 13 авг.3 7983

    በዛምቢያ ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው  ምርጫ ፕሬዝዳንት ሂቺሌማ ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን የማሸነፍ ዕድላቸው ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ ሐሙስ፣ ነሐሴ 07 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) ዛምቢያውያን ዛሬ ሐሙስ በተካሄደው ብሔራዊ ምርጫ ድምፃቸውን መስጠት የጀመሩ ሲሆን፣ በምርጫው አሁን በሥልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዞዳንት ሀካይንዴ ሂቺሌማ ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን የመመረጥ ሰፊ ዕድል እንዳላቸው ተገለጸ። ወደ 22 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያላት ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ዛምቢያ፣ ፕሬዚዳንታዊ፣ የፓርላማ እና የአካባቢ አስተዳደር ምርጫዎችን በአንድ ጊዜ እያካሄደች ትገኛለች። የምርጫ ጣቢያዎች ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ለድምጽ መስጠት የተከፈቱ ሲሆን፣ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ላይ እንደሚዘጉና የምርጫው ውጤትም በሚመጣው ሰኞ ዕለት ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል። በመዳብ ምርቷ የምትታወቀውን ዛምቢያን እ.አ.አ. ከ2021 ጀምሮ በመምራት ላይ የሚገኙት ሀካይንዴ ሂቺሌማ፣ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው ሀገሪቱን ከውጭ ዕዳ ቀውስ በማውጣትና የኢኮኖሚ ማገገሙን በማስቀጠል ላይ ትኩረት አድርገው የሠሩ ሲሆን፣ የዘንድሮውን የምርጫ ዘመቻቸውንም በዚህ የኢኮኖሚ አፈጻጸማቸው ላይ መሠረት ማድረጋቸው ተገልጻል። ዛምቢያ እ.ኤ.አ. በ2020 ዕዳዋን መክፈል አቁማ የነበረ ቢሆንም፣ ሂቺሌማ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የዕዳ መልሶ ማዋቀር እና የኢኮኖሚ ማገገሚያ ሂደቱን በብቃት መምራታቸው ይነገራል። የፕሬዚዳንት ሂቺሌማ ዋነኛ ተፎካካሪ ልምድ ያለው የፓርላማ አባል የሆኑት ብራያን ሙንዱቢሌ ሲሆኑ፣ ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ግን የዘንድሮው የመጀመሪያቸው ነው። ሮይተርስ እንደዘገበው ሙንዱቢሌ የቀድሞውን የዛምቢያ ፕሬዝዳንት ደጋፊዎች ያካተተ የተቃዋሚዎች ቅንጅትን በመምራት ላይ ይገኛሉ። ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲ t.ly/mxA

  • 13 авг.3 73743

    #ቃለምልልስ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ይፋዊ “የእርዳታ” ጥሪ አቅርበዋል። ዋነኛ ጥያቄያቸውም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደቡብ አፍሪካ በሄዱበት ወቅት የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ነው። አዲስ ማለዳ በደቡብ አፍሪካ የተባበሩት የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ማህበር ፕሬዝዳንት ዮሐንስ ሃቢቡ ጋር ባደረገችወሰ ቆይታ ከዚህ በተጨማሪ “አስፈሪ ነው” ከተባለው የህዳር ምርጫ አስቀድሞ ስላሉ አዳዲስ ጉዳዮች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። በተከታዩ ማስፈንጠሪያ እንድትከታተሉት ጋበዝን፦ https://youtu.be/TsoNzS22xWE?si=30AcdHiXleAShoZF

  • 13 авг.3 64794

    “ብሔራዊ ጥቅምን የሚጎዱ ሕገወጥ ሚዲያዎች እንዲሠሩ አይፈቀድም፤ በበይነ-መረብ ሚዲያዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል” ባለስልጣኑ ሐሙስ፣ ነሐሴ 07 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የማያስቀድሙ እና በሰላምና ደኅንነት ላይ ሥጋት በሚፈጥሩ ሕገወጥ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የገለጹት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ፤ ከዚህ በኋላም ከተቋማት ጋር በመቀናጀት እርምጃው እንደሚቀጥልና በተለይም በበይነ-መረብ (ኦንላይን) ሚዲያዎች ላይ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የአዋጅ ማሻሻያ እንደሚደረግ አስታወቁ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እስካሁን ሲያደርገው የነበረው የይዘት ክትትል ውጤታማነት በሚፈለገው ደረጃ አለመሆኑን በመግለጽ፣ ቁጥጥሩንና አቅሙን የሚያጠናክር የመግባቢያ ስምምነት ከተለያዩ ተቋማት ጋር ተፈራረሟል። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ እንደገለጹት፤ ተቋሙ የብሮድካስት፣ የህትመት፣ የበይነ-መረብ (ኦንላይን) እና የውጭ ሚዲያዎችን ፈቃድ የመስጠት፣ የማደስ፣ የማገድ እና የመሠረዝ ዋና ዋና የቁጥጥር ሥራዎችን የመሥራት ሕጋዊ ኃላፊነት አለበት። ነገር ግን እስካሁን የነበሩ የአሠራር ሂደቶች ሲፈተሹ፣ ባለሥልጣኑ የሚወስዳቸው ውሳኔዎች በአቅም ግንባታም ሆነ በቁጥጥር ረገድ የሚፈለገውን ያህል ውጤታማ መሆን አልቻሉም። ይህንን የቁጥጥርና የክትትል ሥራ ውጤታማ ለማድረግ ቅንጅታዊ አቅምን ማጠናከር አስፈላጊ በመሆኑ፣ ከ11 ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቶ መፈራረሙን ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። ባለሥልጣኑ ከዚህ ቀደም በሚዲያዎች ላይ ባደረገው ክትትል የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የማያስቀድሙ እና የሀገርን ሰላምና ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ ሲወስድ መቆየቱን ያስታወሱት ሃይማኖት፤ “ሕገወጥ ሚዲያ በሀገር ውስጥ እንዲሠራ አይፈቀድም፤ ከዚህ በኋላም ከተቋማት ጋር በመተሳሰር እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በተለይም ከብሔራዊ ጥቅም ጋር ተፃርረው የሚቆሙ አሠራሮች በበይነ-መረብ ሚዲያዎች ላይ በስፋት እየታዩ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በነዚህ ሚዲያዎች ላይ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና ሥርዓት ለማስያዝ የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።   ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲ t.ly/mxA

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ — tgindex