tgindex
ወልድ ዋሕድ የአብነት ትምህርት

ወልድ ዋሕድ የአብነት ትምህርት

Статистика
Последний пост
10 февр. 2023 г.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
19
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
180
мало замеров
Замеров пока мало
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
862
19 постов
Вовлечённость
478,9%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 19
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 10 февр. 2023 г.1 260из weldwahid

    ☘እንዴት አረፈዳችሁ🍀 📍#ስለ ቤተክርስቲያን ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤታችን ወልድ ዋሕድ  💚💛❤️ #ዛሬ_አርብ  #ከ12:00 - 1:30  💚💛❤️ ልዩ የጸሎት  መርሃግብር አዘጋጅታለች ⛪️ ኑ ሁላችንም አንድ ላይ  ስለቤተክርስቲያን አባታችን ሆይ እንበለው🙏🙏🙏 መቼ ❓🤔 🪧 #ዛሬ_አርብ_ ስንት ሰዓት ❓🤔 🪧 #12:00 የት❓🤔 🪧 #ወልድ_ዋሕድ_ሰ/ት/ት ቤት ✝ #አንድ_ሲኖዶስ ✝ #አንድ_መንበር ✝ #አንድ_ፓትርያርክ #ወልድ_ዋሕድ @Weldwahid

  • 12 янв. 2022 г.1 470из weldwahid

    ይሄ ከታች የምትመለከቱት Link የወልድ ዋሕድ የቤተ መጻሕፍት ቻናል ነው ሁላችሁም ተቀላቀሉት ድንቅ ድንቅ መጻሕፍትን በpdf ያገኛሉ ተቀላቀሉት 👇🙏👇🙏👇🙏👇🙏👇🙏 ይህን ይጫኑት 👉https://t.me/Abaiyesuslib ☝️🙏👆🙏👆🙏👆🙏👆🙏👆 ተቀላቀሉት #share #እናጋራ #share #እናጋራ

  • без подписи

  • 2 нояб. 2021 г.1 340из weldwahid

    👏👏👏እነሆ 1⃣ ዓመት 👏👏👏 ✨✨የረቡዕ ጉባኤ አንድ ዓመት ሞላው✨✨ 😱 🌸" ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ፤ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። "🌸 🌸(ትንቢተ ኤርምያስ 15:16)🌸 ዓመታዊ በዓሉን በማስመልከት ጥቅምት 24 ረቡዕ ከ11:30 ጀምሮ 📍ቃለ እግዚአብሔር በታላላቅ መምህራን 📍የዝማሬ መርሃ ግብር በምንወዳቸው ዘማርያን 📍 ድንቅ የኪነ ጥበብ መርሃ ግብር 📍እንዲሁም ሌሎችም ድንቅ መርሃግብራት እጥር ምጥን ባለ መልኩ ተዘጋጅተው እርሶን ይጠብቃሉ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ስለዚህ🙌 ✝ጥቅምት 24 11:30 🕦 ላይ በወልድ ዋሕድ ሰንበት ትምሀርት ቤት አዳራሽ ከሚወዱት አንድም ሁለትም ሦስትም..... ሰው ጋር ይገኙልን 🎊💙ጥቅምት 24 11:30 💙🎊 ❗️🙏❗️#አደራ! #ጠሪ_አክባሪ_ቀሪ......... ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @mels_asteyayet 👈 ላይ ይላኩልን 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 @weldwahid #ወልድ_ዋሕድ

  • ⛪️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!⛪️ ከትምህርት ❺ የቀጠለ👆 ፯) ጸብኀ ➳ ወጥ ሠራ ◦ጸብኅ ➳ወጥ ◦መጽብኅ➳የወጥ ዕቃ፣ድስት #ጸብሐ (ጠብቆ ሲነበብ)➳ግብር ገበረ ◦ጸባሒ ➳የሚገብር፥ገባሪ ◦መጸብሕ➳የሚያስገብር፥አስገባሪ ◦ምጽባሕ➳መገበሪያ፥ማስገበሪያ #ጸብሐ(ላልቶ ሲነበብ)➳ነጋ፥ጠባ ◦ጽባሕ➳ንጋት፥ጥባት ◦ውስተ ጽባሕ ነጽሩ ▪▪▪▪▪ ፰) ዋሐደ እና ውኅደ #ዋሐደ ➺ አንድ ኾነ፣ተባበረ ◦ዋሕድ➛አንድ የኾነ ◦ውሕደት ➺አንድነት፣መተባበር ◦ተዋሕዶ➺አንድ መኾን፣አንድነት፥ መዋሐድ ◦ዋሕድ ለአቡሁ #ውኅደ ➺ጎደለ፣አነሰ፣ቀነሰ ◦ውኅደት➺መጉደል ፣ማነስ ▪▪▪▪▪ ፱) ሰረየ ➳ፈታ፣ለቀቀ፣አነጻ(ከኀጢአት)፣ተወ ◦አስተሰርየ➳ይቅር አሰኘ፣አማለደ ◦ስርየት➳ዕርቅ፣ፍቅር፣ይቅርታ ◦መስተሰርይ➳ይቅር ባይ፥በደልን የሚተው ◦ስርየተ ኀጢአት #ሠረየ(ጠብቆ) ➳ሤራ ሠራ፣ተንኮል አሰበ ◦ሥርየት➳ተንኮል፥ምትሀት፣ሤራ ◦መሠርይ➳ተንኮለኛ፣ምትሀተኛ፥ጠንቋይ ◦ሲሞን መሠርይ በተጨማሪም ◦ሠረየ (ላልቶ ሲነበብ) ➳ፈተለ፣አሾረ (ለእንዝርት) ◦ሣሬት ➳ ሸረሪት፣ ፈታይ ▪አንዳንድ ግሶች ሲጠብቁና ሲላሉ የተለያየ ትርጕም ያላቸው አሉ። ▪▪▪▪▪ ፲) አሰረ➳ በቁሙ አሰረ፥ተበተበ ◦አሰሮ ለሰይጣን➳ሰይጣንን አሰረው ◦እም ማእሰረ ኀጢአት.... ➛ከኀጢአት ማሰሪያ ◦ አሠረ ➳ ተከተለ ◦ አሠር ➳ መንገድ ፍኖት ◦ አሠረ ፍኖት ➳ መንገድን መከተል #ዐሠረ ➳ ዐሥር(፲) አደረገ ◦ዐሥር ➳ ከዘጠኝ ቀጥሎ ያለ ቁጥር ◦ዐሥራት ➳ ከዐሥር አንድ ◦ዐሥራት ማውጣት ➳ ከዐሥር አንድ ማውጣት ▪▪▪▪▪ ብናውቃቸው የሚጠቅሙን፦ 📌 ኀደረ ➺አደረ ◦ማኅደር ➺ማደሪያ ◦ኅዳር ➺ጠባቂዎች ዱር የሚያድሩበት ወር ◦ኅደረት ➺ማደር ፣መኖር 📌ሠለሰ ➛ሦስት አደረገ ◦ሥሉስ➛ሦስት የኾነ ◦ሥላሴ➛ሦስትነት፣ሦስት መኾን ◦ትሥልስት➛ሦስት ዕጥፍ 📌ኀተመ➛አተመ ◦ኅትመት➛ማተም፥መታተም ◦ማኅተም ➛ማተሚያ፥መታተሚያ 📌ድኅነ ➵ዳነ ◦ድኅነት➵መዳን፣መፈወስ ◦ድህነት ➵ድኻ መኾን፣ማጣት 📌ኀሠሠ ➛ፈለገ ◦ኀሠሣ ➛ፍለጋ ◦ታኅሣሥ ➛ፍላጎት፣የወር ስም ◦ኅሥሥት ➛ዕሥሥት(የእንሻላሊት ዘር) 📌የሚከተሉት ቃሎች በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የምንጠቀምባቸው ናቸው። በትክክለኛ ፊደላት የተጻፉ በመኾናቸው ብትዩዟቸው ይጠቅሟችኋል። መንግሥት፣ማኅበር፣ ኅብረት፥ሆሳዕና ማኅተም፣ ጽሕፈት፣ ማዕበል፣ ማእከል ንጉሥ፣ ንጉሤ፣ሥዕል፣ሕፃን፣ቊጥር፥ኀላፊ፣ ደኅና ፣ ባህል፣ ዐይን፣ዐላማ፣ ፅንስ፣ሐኪም፣ ሕመም፣ ሒሳብ፣ ሐሰት፣ ሐሜት፣ ርእስ፣ ሰብእ ኀይል፣ ሥጋ ፣ሥራ ፣ዕዳ ፣ጾታ፣ጾም። #ማጠቃለያ የግእዝ ፊደላት የራሳቸው የኾነ ቅርጽ ፥ስያሜ፣ ድምፅ አላቸው። ከዚህ በተጨማሪ ምስጢር ያዘሉ ናቸው። እውነት ነው አሁን ላይ ድምፀታቸው ጠፍቶ ቅርጻቸው ቀርቷል። እኛም የጠፋውን ድምፀታ ቸውን ከሊቃውንት ጠይቀን መረዳት ይኖርብናል። #የትምህርት ጥቅም ያለንን ነገር ለመቀነስ ሳይኾን በአለን ላይተጨማሪ ዕውቀት ለመገብየት በመኾኑም የጠፋውን የፊደላትን ድምፅ እንደገና በመመለስ እና ከሥር መሠረቱ ጀምሮ የግእዝ ፊደላቱን በመማርና ማስተማር አባቶቻቸን ያቆዩን ዕንቁ ሀብታችንን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ከምሁራኑ አልፎ ተርፎም ከእኛ ይጠበቃል። እነዚህን ኹሉ ምሳሌዎች የቀረቡት የግእዝ ፊደላትን አይደለም መቀነስ ተቀያይረው ቢጻፉ የሚያመጡትን የትርጕም መፋለስ ለአብነት ያህል ለማሳየት ነው። ስለዚህ ወገኔ እንንቃ! ይቀነስ የሚሉት እንግዲህ በትንሹ ካየናቸው ምሳሌዎች እንኳን ቃሎችን፣ ትርጕም አልባ፣ እኛንም ታሪክ አልባ የሚያደርግ የቆየ የሚቆይ ማንነታችንን የሚያጠፋ ነውና እንንቃ። ምዕራፍ አንድ ላይ ስለ ፊደላት ከብዙ በጥቂቱ ከውቅያኖሱ በጠብታው ይህንን ይመስል ነበረ። ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየታችሁ @mels_asteyayet @mels_asteyayet እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ #ምዕራፍ_ኹለትን በቀጣይ እንጀምራለን። 🌷🌷🌷 ትምህርት ❻ 🌷🌷🌷

  • 15 окт. 2021 г.805из weldwahid

    ☘🍀☘🍀☘🍀☘🍀🍀☘🍀☘🍀🍀 #የነገ የቤተክርስቲያን ተረካቢዎች በወልድ ዋሕድ ❤️👏👏 ❤️❤️የአብነት ተማሪዎቻችን በትምህርት ላይ ❤️❤️ @weldwahid

  • ⛪️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ⛪️ 🌾 አንድን ቃል በትክክለኛው ፊደል መጻፍ እንዴት እንችላለን? ➳መልስ ፩) የቃሉን ሥርወ ግስ (መነሻ ግስ) ማወቅ ግስ ምንድን ነው? ግስ የቃል ክፍል ሲኾን የራሱ የኾነ መለያ ባሕርያት ያሉት ቢኾንም ዋናው መለያው በግእዝ ፊደል መጨረሱ እና እሱ በሚለው መራሒ መቀመጡ ነው። ( ምዕራፍ ሦስት ላይ በዝርዝር እንማረዋለን። ) በመኾኑም ከግሱ የሚገኙ ማናቸውም ስሞች፣ ቅጽሎች የሚጻፉት ዋናው ግስ በተጻፈበት ነው። ለምሳሌ ▪ #ቀደሰ ግስ ሲኾን ትርጕሙ #አመሰገነ ማለት ነው።በመኾኑም ቅዳሴ፣ ቅዱስ፣ ቅድስት፣ መቅደስ፣ ቀዳሲ የሚሉት ቃላት ግሱን መስለው በመነሻ ግሱ መሠረት ይጻፋሉ እንጂ ቅዳሤ፣ ቅዱሥ ፣ ቅድሥት፣ መቅደሥ፣ቀዳሢ ተብሎ አይጻፍም ▪ #ጸሐፈ ግስ ሲኾን ትርጕሙ ጻፈ ማለት ነው።በመኾኑም መጽሐፍ፣ ጽሑፍ፣ጸሓፊ፣ጽሕፈት ተብሎ ይጻፋል እንጅ መፅሀፍ፣ መጽሀፍ፣ ፅህፈት፣ ፅሕፈት ፅሁፍ፣ፅሑፍ ፣ፀሃፊ ተብሎ ሊጻፍ አይገባም። ምክንያቱም ስሞች መጻፍ ያለባቸው በሥርወ ግሱ ( በዋና ግሱ ) ፊደል ስለኾነ ነው። ስለዚህ አንድን ቃል በትክክለኛ ፊደል መጻፍ የምንችለው #ግስ ስናውቅ ነው። ምዕራፍ ሦስት መጀመሪያ ላይ ይህንኑ በተመለከተ በሰፊው እንማማራለን። ፪) ልምምድ ለጊዜው እስከ አሁን በምሳሌም ኾነ ለትምህርት የተጠቀምንባቸውን #ቃሎች በደንብ ተረድቶ ወደፊት በማንኛውም ኹኔታ ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል። ልዩነታቸውን እንድታስተውሉበት ( ፊደሎቹ ቢቀያየሩ ሊያመጡ የሚችሉትን የትርጕም መፋለስ በደንብ እንድታስተውሉ እንመክራለን። ፩) ሠነየ እና ሰነየ #ሠነየ➛አማረ፥ ተዋበ፣ ጥሩ ኾነ ◦ሠናይ➛መልካም፣የሚያምር፣ውብ ◦ሠናይት➛የምታምር፣ውብ ◦ሠኔ ➛የወር ስም ◦ሥን ➛ደም ግባት፣ መልካምነት ◦ሥነ ፍጥረት➛የፍጥረት ደም ግባት፥ አፈጣጠር፥ ሥርዐት ◦ሥነ ሕዝብ ➵የሕዝብ አኗኗር፣ ስለ ሕዝብ የሚያጠና.... ◦ ሥነ ሥዕል ➵የሥዕል አሣሣል፣... #ሰነየ ➛ኹለት አደረገ ◦ሰኑይ➛ሰኞ (ኹለተኛ ቀንለፍጥረት) ◦ሰነነ➛ጥርስ አወጣ ◦ስን ➛ጥርስ ▪▪▪▪▪ ፪) ዐበየ እና አበየ #ዐበየ ➛ታላቅ፣ገናና ኾነ ◦ዐቢይ➛ታላቅ፣ገናና፣ብርቱ ◦ዐበይት ነቢያት ➛ታላላቅ ነቢያት ◦ትዕቢት➛ትቢተኛነት፣ኩራት፣ ከእኔ በላይ ታላቅ የለም ማለት #አበየ➳እንቢ አለ፣ እንቢተኛ ኾነ ◦አብዮት➳እንቢ ማለት፣አሻፈረኝ ማለት ◦አቢይ ➳እንቢተኛ፣ ዕሺ በጎ የማይል ◦አብዮቱ ሲፈነዳ➳??? ▪▪▪▪▪ ፫) ተሐተ(ተትሕተ) እና ለዐለ(ተልዕለ) #ተሐተ ☞ ዝቅ ዝቅ አለ ◦ትሑት➛የተዋረደ፣የተናቀ፣ታዛዥ ◦ትሕትና➛ትሑትነት፣ዝቅታ ◦መትሕተ ፈጣሪ➛ከፈጣሪ በታች ◦ትህትና✖️፣ ትኅትና✖️ #ለዐለ ➳ ከፍ ከፍ አለ ◦ልዑል➳ከፍ ያለ፣የበለጠ ◦ልዕልና➳ታላቅነት፣ምጥቀት ◦መልዕልተ ፍጡራን➳ከፍጡራን በላይ ◦ልእልና✖️፤ ልኡል ✖️ ▪▪▪▪▪ ፬) ጸበለ እና ጠበለ #ጸበለ➳ሐመድ፣ትቢያ ኾነ ◦ጸበል➳ብናኝ፣ትቢያ፣ዐቧራ #ጠበለ➳ተነከረ፣ተዘፈቀ፣ተጠመቀ ◦ጠበል➳የተባረከ፣የተጸለየበት፥ከደዌ የሚያድን፥የሚፈውስ የጥምቀት ውሃ ▪▪▪▪▪ ፭) ተጸነሰ እና ተፀንሰ #ተጸነሰ➳አጣ፣ተቸገረ፣ ደኸየ ◦ተጽናስ ➳ችግር፣ማጣት ◦አልቦ ተጽናስ ➳ችግር የለም #ተፀንሰ➳ተረገዘ፣ተፀነሰ ◦ፅንስ➳በቁሙ፥ የማሕፀን ፍሬ ◦ፅንሰት➳እርጉዝነት፥ መፀነስ ▪▪▪▪▪ ፮) ሰብአ እና ሰብዐ #ሰብአ➳አብዝቶ ማግኘት፣ፈጽሞ መጥገብ ◦ሰብእ➳ሰው(ባሕርያዊ ስም) ◦ተሰብአ➳ሰው ኾነ፣ሥጋ ለበሰ፣ተዋሐደ ◦ትስብእት➳ፍጹም የሰው ባሕርይ #ሰብዐ➳ሰባት አደረገ ◦ተሰብዐ➳ሰባት ኾነ፣ለሰባት ተከፈለ ◦ሱባዔ➳ሰባት ቀናት ◦ሰብዓ ➳ሰባ(70) ◦ትስብዕት ➳ሰባትነት፣ሰባት ዕጥፍ @weldwahidabinet ⛪️⛪️⛪️ትምህርት ❺ ⛪️⛪️⛪️

  • በዓለ 'ሲመት' ወይስ በዓለ 'ሢመት'? ሢመት #➳ ሤመ፣ሠመየ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ሰየመ፣ ሾመ ማለት ሲሆን 'ሲመት' ማለት ደግሞ ድመት ማለት ነው። ቤተ - ክርስቲያን ለቅዱሳን ፓትርያርኮቿ የምትጠቀምበትን 'በዓለ ሢመት' (የሹመት በዓል) የሚለውን ቃል ወስደው ለሌላ የሰጡ ሰዎችን ታዝበናል። ስለዚኽ ፥ 'በዓለ ሲመት' እያሉ ሲጽፉ 'የድመት በዓል' ማለት ነው😁😁😁

  • ⛪️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ⛪️ የመልመጃ ፩ ማብራሪያ ፩. ዓመት ሲጻፍ በ ዐ ይጻፋል፡፡ ዓመት#➳ዘመን አዲስ ዓመት ➳ አዲስ ዘመን አመት #➳ባርያ ፣ገብር፣ አገልጋይ፣ሎሌ አመተ ሥላሴ ➳የሥላሴ አገልጋይ ፪. #አደመ➳ አማረ፥ተዋበ አዳም ➳የሚያምር፣ደስ የሚያሰኝ ፣ውብ ፣ መልከ መልካም ማለት ነው። ዐደመ➳ሤራ አዘጋጀ ዐድማ➳ሤራ፥ተንኮል፥ወጥመድ ዐደመ ➳ጊዜ ቀጠረ፣ ቀን ወሰነ(ሌላ ትርጕሙ) ተዐዳሚ➳ታዳሚ (ለሰርግ፣ ለጉባኤ፣ለስብሰባ) ዕድሜ ➳ ቀጠሮ፣ የተወሰነ ጊዜ፣ዘመን ፫. ሰላም በ "ሰ" ይጻፋል! #ሰላም ሰላም ለኩልክሙ ➳ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ፬. #ሰረቀ➳የራሱ ያልሆነን ወሰደ ምስራቅ➳የሌቦች መገኛ፥መስረቂያ #ሠረቀ ➳ወጣ ለፀሓይ ምሥራቅ ➳የፀሓይ መውጫ ▣ ሴት ልጁን ቆንጆ፣ ዐይናማ፣ መልከ መልካም ማለት ፈልጎ #ምሥራቅ አላት እንበል። ምን ችግር አለው በ #ሰ ቢጻፍ ብሎ አንድ ሰው #ምስራቅ እገሌ ብሎ ቢጽፍ ሰደበው እንደ ማለት ነው። ምስራቅ የሌቦች መገኛ እንደ ማለት ስለኾነ። ስለዚህ ሌባ ለማለት ሰራቂ እንጂ ሠራቂ አንልም፡፡ ሰረቀ ብርሃን? ሠረቀ ብርሃን➙ብርሃን ወጣ ፭. #ሰረገ ግስ ሲኾን ትርጕሙ #ደገሰ ማለት ነው። #ሰርግ ደግሞ ስም ነው ትርጕሙ ድግስ፥ የጋብቻ በዓል ። #ሠረገ ግስ ሲኾን ትርጉሙ ወደ ውስጥ ገባ ማለት ነው። #ሠርግ የሚለው ደግሞ ከሠረገ ይወጣል። ስለዚህ #ሠርግ ማለት መስኖ፥የመስኖ ውሃ (ቦዩ) ነው። "ሠርጎ ገብ" ሲባል ሰምታችኋል? አደራ ያላገባችሁ ስታገቡ መጥሪያው ላይ #ሠርግ ብላችሁ እንዳታጽፉ። እንዲህ ከኾነ ግእዝ ለሚያውቅ ሰው ድግስ ሊያበሉኝ ሳይኾን ቦይ ሊያስቆፍሩኝ ነው ብሎ አይታደምላችሁምና!😁😁😁 ፮. Medhane alem የሚጻፈው በብዙኀኑ ኀ እና በዐይኑ ዐ #መድኃኔዓለም ተብሎ ነው ፡፡ ምክንያቱም መነሻ ግሱ #ድኅነ ➙ዳነ በመኾኑ። አንዳንድ መጽሐፍ መድኀኔዓለም ብለው በግእዙ ይጽፉታል። ሌሎቹ ደግሞ መድኃኔዓለም ብለው ይጽፉታል።እንደጀማሪ በተለመደው መድኃኔዓለም የሚለውን እንያዝ። ▪ ድኅነት ፣መድኀኒት፥ዳኅና፣ ፯. #መሀረ➳ አስተማረ ማለት ሲኾን ከትምህርት ጋር ተያያዥነት ያለው ቃል በሃሌታው "ሀ" ይጻፋል። #መሐረ ➳ ይቅር አለ ማለት ሲኾን ከምሕረት ጋር ተያያዥነት ያለው ቃል ኹሉ በሐመሩ "ሐ" ይጻፋል። ስለዚህ ፦ #ኪዳነ ምሕረት☞የምሕረት፥የይቅርታ ኪዳን ውል ማለት ሲኾን በሐመሩ ሐ ሲጻፍ ብቻ ነው ትርጕሙ ከይቅርታ ጋር የሚያያዘው፡፡ በሌሎች ከተጻፈ ትርጕሙ ይለወጣል፡፡ ▪ መምህር፣ ትምህርት፣ ምሁር ▪ መሐረነ አብ ፣መሓራ ፥ዓመተ ምሕረት ፰. #ሀይመነ ➙አመነ፣ታመነ ሃይማኖት ➙ማመን ፣መታመን #ሃይማኖተ አበው ➙የአባቶች ማመን መታመን ማለት ነው። መሀይምን ➳ምእመን፣ያመነ፣የታመነ ፱) #ሥን ➳ደም ግባት፣መልክ፣ ሥነ ፍጥረት ➳የፍጥረት ውበት፣ ስለ ፍጥረት የሚያጠና.... #ሰነነ ➳ጥርስ አወጣ ከሚለው ግስ ስን ➳ጥርስ ስነ ፍጥረት ➳የፍጥረት ጥርስ ስነ ሕዝብ ➳የሕዝብ ጥርስ ፲) . እግዚእ ➳ ጌታ አብ➳ አባት ሔር➳ ቅዱስ ጌታ፣አባት፣ቅዱስ መንፈስ➳አብ ወልድ መንፈስቅዱስ # እግዚአብሔር #ማጠቃለያ፦ ከላይ ፊደላት አንዱ በአንዱ ሲቀያየሩ ምን ያህል የትርጕም ልዩነት እንደሚያመጡ በምሳሌዎች አይተናል። የኾነ ኾነና እኛ የግእዝ ቃላትን በትክክለኛው ፊደል ለመጻፍ ምን ማድረግ አለብን የሚለውን በቀጣይ ትምህርት የምናይ ይሆናል! በስተ መጨረሻም ለመልመጃ ፩ በርካታ መልሶች የተላኩ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ሁሉንም መልሶች በትክክል ያገኙ እና ቀድመው ለላኩ ሦስት ተሳታፊዎች የ "ሜጋ ባይት" ሽልማታቸውን ወስደዋል። በዚህ መሠረት አሸናፊዎች 🏅"Rumeran"( በቀጣይ ሙሉ ስም በአግባቡ ይጻፍ!) 🏅 ቤተልሔም አያሌው 🏅ይመስረት ጎሳ ናቸው። በቀጣይም ሁላችሁም ጠንክራችሁ ተሳተፉ ! "ሠናይ ጊዜ!" @weldwahidabinet ⛪️⛪️⛪️ትምህርት❹ ⛪️⛪️⛪️

  • ⛪️⛪️⛪️መልስ መስጫ⛪️⛪️⛪️ #የተማሪው_ስም_________ #ስልክ ቁጥር___________ ፩.________ ፪.________ ፫.________ ፬.________ ፭.________ ፮.________ ፯.________ ፰.________ ፱.________ ፲.________ @mels_asteyayet ⛪️⛪️⛪️ ምልማድ፩⛪️⛪️⛪️

  • 🇪🇹🇪🇹ምልማድ( መልመጃ )፩🇪🇹🇪🇹 ⛪️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !⛪️ ️#መልመጃ_፩ በቅድሚያ ባለፉት ጊዜያት ትምህርቶችን ለመልቀቅ ባለመቻላችን ይቅርታ እየጠየቅን ዛሬ የምንሰጣችሁ መልመጃ ከዚህ በፊት በፊደላቱ ዙሪያ ያላችሁን ዕውቀት ለመገምገም ያህል ብቻ ነው። ቀድመው ትክክለኛ መልስ ለሚመልሱ ሦስት ተሳታፊዎች 'የሜጋ ባይት' ሽልማት ተዘጋጅቷል። ስለዚህ መጽሐፍ ሳታዩ፣ሰውም ሳትጠይቁ ይኾናል ብላችሁ የምታስቡትን ወይንም ከዚህ በፊት በምታውቁት ብቻ ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ መልሳችሁን በ @mels_asteyayet እንድትልኩልኝ በአክብሮት እንጠይቃለን። @mels_asteyayet ለአብነት እና ግእዝኛ ተማሪዎች መልስ አስተያየት ጥያቄ መልመጃ/ለፈተና መልስ መቀበያ የተዘጋጀ የቴሌግራም አድራሻ ነው። @mels_asteyayet በመጫን በዚሁ #ብቻ በመጠቀም መልመጃውን ላኩልን። 🌷መልስ ሠርታችሁ የምትልኩልን ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በፈለጋችኹት ሰዓት እስከ ነገ #ረቡዕ_ማታ_12_ሰዓት ድረስ #ብቻ ይኾናል። ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ መላክ እንዳለመላክ ይቆጠራል። (መልመጃውን ሠርቶ ለመላክ 36 ሰዓታት ተሰጥቷችኋል ማለት ነው።) #ረቡዕ ማታ 12:00 ሰዓት ላይ ትክክለኛውን መልስ እልክላችኋለሁ። እስከዚያው የመለማመጃው ገጽ ዝግ ኾኖ ይቆያል። ስትልኩ እስከ ትምህርቱ መጨረሻ የምትጠቀሙበትን ስማችሁን እና ስልክ የቁጥራችሁን ላኩልን። መልመጃ ፩ #የተማሪው_ስም_________ #ስልክ ቁጥር___________ ትክክለኛ መልስ የያዘ ነው ብላችሁ የምታስቡትን ፊደል ምረጡ። ፩. አዲስ __! አ) አመት በ) ዐመት ፪. Adam የሚለው ሲጻፍ አ) ዐዳም በ) አዳም ፫.ѕєℓαм አ) ሰላም በ) ሠላም ፬. የፀሓይ መውጫን የሚያመለክተው፦ አ) ምስራቅ በ) ምሥራቅ ፭. የጋብቻ ሥነ ሥርዐት ለመግለጽ ፦ አ) ሰርግ በ) ሠርግ ፮. Medhanealem ለማለት፦ አ) መድሀኔአለም በ) መድኀኔዓለም ገ) መድሐኔዓለም ደ) መድሐኔአለም ፯. Kidane Mihret ለማለት፦ አ)ኪዳነ ምኅረት በ)ኪዳነ ምህረት ገ)ኪዳነ ምሕረት ደ)ኪዳነ ምኽረት ፰. haimanot የሚለው ሲጻፍ አ) ሃይማኖት በ) ሐይማኖት ገ) ኀይማኖት ደ) ሓይማኖት ፱. Sine ፍጥረት አ) ሥነ ፍጥረት በ) ስነ ፍጥረት ፲. EGZIABHER አ) እግዚአብሄር በ)አግዚአብኄር ገ) እግዚአብሔር ደ) እግዚያቤር ⛪️⛪️ምልማድ፩⛪️⛪️⛪️

  • без подписи

  • ⛪️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !⛪️ #ዘጠኙ_ሞክሼ_ፊደላት [ ሀ ፣ሐ ፣ኀ ፣ ዐ ፣አ ፣ ጸ ፣ፀ ፣ ሠ፣ሰ ] በርእሱ ላይ ሞክሼ የሚለውን ቃል የተጠቀ ምኩበት በለመድነው እንዲገባን ያክል እንጂ የግእዝ ቋንቋ ሞክሼ ፊደላት #የሉትም ። አንድን ሰው የማያውቀውን ነገር በሚያውቁት ነገር ቢያስረዱት ይረዳልና! ◍ ሀ፥ ኀ እና ሐ =ha ፤ ◍ አናዐ=Aa ፤ ◍ ጸ እና ፀ =tse ፤ ◍ ሠ እና ሰ =se ብለን በተለምዶ እንጥራቸው እንጂ ድምፀታቸው ግን አንድ አይደሉም። የቋንቋው ሊቃውንት ፥እንደሚናገሩት እያንዳንዱ ፊደላት ፩. በቅርጽ አይመሳሰሉም። ◍ ሀ ፥ ኀ ፥ ሐ ◍ አ እና ዐ ◍ ጸ እና ፀ ◍ ሠ እና ሰ ፪. በስያሜ አይመሳሰሉም። #ሀ➙ ሃሌታው ሀ ይባላል። #ኀ ➙ብዙኀኑ ኀ #ሐ ➙ ሐመሩ ሐ #ዐ ➙ዐይኑ ዐ #አ➙ አልፋው አ ይባላሉ። #ሠ ➻ንጉሡ ሠ #ሰ ➻እሳቱ ሰ #ጸ ➻ጸሎቱ ጸ #ፀ ➻ፀሐዩ ፀ በመባል ይታወቃሉ። ፫. በአካላችን ውስጥ የራሳቸው የሚነገሩበት ክፍል አላቸው። ◍ ሀ እና አ የጉረሮ ድምፅ ሲኾኑ ላልተው ይነበባሉ። ◍ ሐ እና ዐ የጉረሮ ድምፅ ሲኾኑ ጠብቀው ይነበባሉ። ◍ ኀ የማንቁርት ድምፅ ◍ ሰ እና ጸ በምላስ እና በጥርስ የሚነገሩ ◍ ሠ እና ፀ የትናጋ ናቸው። አንዱ ከአንዱ ጋር ድምፃቸው እንደማይመሳሰል ከላይ ባለው እናያለን። ልዩነታቸውን በተለይ ትግርኛ ቋንቋ የሚናገሩ ወንድሞች እና እህቶች በቀላሉ ይረዱታል። እውነት ለመናገር አሁን ላይ ለእኛ የደረሱን ፣የምናውቃቸውም የየራሳቸው ድምፅ ጠፍቶ ◍ ሀ፥ኀ እና ሐ=ha ፤ አ ና ዐ=Aa ጸ እና ፀ =tse ፤ ሠ እና ሰ =se እያልን እንጠራቸዋለን፡፡ ነገር ግን አንድ ልናውቀው የሚገባ ቁም ነገር እነዚህ ፊደላት በድምፅም ፣በቅርጽም በስያሜም የማይመሳሰሉ በመኾናቸው ሞክሼ ፊደላት አለመኾናቸውን ነው፡፡ ከዚያ ቀጥሎ የጠፋውን የጥንት ድምፃቸውን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን በመጠየቅ መረዳት ይገባናል። መ/ር ዘርአ ዳዊት አድሐና ልሳናተ ሴም በተሰኘው መጽሐፋቸው ገጽ 13 ላይ " በልሳነ ግእዝ ውስጥ ፊደል የሌለው ድምፅ፣ ድምፅ የሌለው ፊደል የለም። ወይም የተዳበለ ሞክሼ ፊደልና ድምፅ የለም። እያንዳንዱ ፊደለ ግእዝ የየራሱ ድምፅ አለው።" በማለት በአጽንዖት ይገልጻሉ። አብዛኛዎቻችን ድምፀታቸውን ለይተን ይህ እንዲህ ነው የሚነበበው ማለት ስለማንችል #ብቻ ሞክሼ ፊደላት በማለት እንጠራቸዋለን። ነገር ግን ይህ ትክክል አይደለም። 🌺 ፊደላቱ እያንዳንዳቸው የራሳቸው ድምፅ ፣ቅርጽ ፣ስያሜ አላቸውና አንዱን በአንዱ መተካት፣ መቀየር የቃሉን ትርጕም እንዲሁም ምስጢርን ያዛባል። 🌷አንድ ዓይነ ሥውር ፀሓይን ማየት ስለማይችል ፀሓይ የለችም እንደ ማይል ኹሉ እኛም ድምፀታቸውን ለይተን ስላላወቅናቸው አንድ ዓይነት ናቸው ይቀነሱ ማለት ተገቢ አይደለም። መፍትሔው ድምፀታቸውን በደንብ ለያይቶ ከሚያውቁ የሥነ ልሳን ምሁራን ቀርቦ መረዳቱ ነው። እውነት ለመናገር በዚህ ዙሪያ የግእዝ ሊቃውንት የፊደላቱን የቀደመ ድምፃቸውን ለትውልዱ በማስተማር ትውልዱን የፊደላትን ልዩነት ተረድቶ ሞክሼ ናቸው ይቀነሱ ፣ በዝተዋል ይቀነሱ ከሚለው አስተሳሰብ እንዲወጣ ከፍተኛ አበርክቶ ይጠበቅባቸዋል። ፊደላቱ ከመነሻ ሲፈጠሩ በየራሳቸው አስፈላጊ እና ልዩ ናቸውና ሊቀነሱ ቀርቶ ፊዳላት በፊደላት ቢቀያሩ እንኳን የሚያመጡትን የትርጕም ፥ የምስጢር መፋለስ ከበቂ ምሳሌዎች ጋር እናያቸዋልን፡፡ https://t.me/weldwahidabinet 🌷🌷🌷ትምህርት ❸ 🌷🌷🌷

  • ⛪️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !⛪️ #ዲቃላ(ሕጹጻን) ፊደላት ሐጸጸ ማለት ጎደለ ፣አነሰ ማለት ሲኾን ሕጹጽ የሚለው ሳድስ ቅጽል ሲኾን ትርጕሙ ያነሰ፣ የጎደለ ማለት ነው። ዲቃላ(ሕጹጻን) ፊደላት የሚባሉት ደግሞ ብዛታቸው ፬ ሲኾን እነዚህ ፊደላት ከመደበኛዎቹ የተዳቀሉ(የተገኙ) ስለኾኑ ዲቃላ ይባላሉ። አንዳንድ መምህራን #ዝርዋን_ፊደላት በማለትም ይጠሯቸዋል። ለምሳሌ፦ #ኰ የተደቀለው(የተገኘው) ከመደበኛው ፊደል ከ #ከ ነው። #ቈ የተገኘው ከ #ቀ ነው። #ጐ የተገኘው ከ #ገ ነው። #ኈ የተገኘው ከ #ኀ ነው። ሕጹጻን(ጎደሎዎች) የተባሉበት ምክንያት ደግሞ ልክ እንደ መደበኞቹ ወደ ጎን ፮(6) አዕጹቅ(የጎን ቅጥያ) ሳይኾን ፬(4) ብቻ ስላላቸው ነው። ይህም #ካዕብ እና #ሳብዕ ፊደላትየላቸውም ማለት ነው። ለምሳሌ፦ መደበኞቹ ራሳቸውን ጨምሮ ፯ ናቸው። ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ ➝ 7 ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ ➝ 7 ሕጹጻኑ ደግሞ ራሳቸውን ጨምሮ ፭ ብቻ አላቸው፦ ፩) ኰ➛ኲ➛ኳ➛ኴ➛ኵ ➡ 5 ፪) ጐ➛ጒ➛ጓ➛ጔ➛ጕ ➡ 5 ፫ )ኈ➛ኊ➛ኋ➛ኌ➛ኍ ➡ 5 ፬) ቈ➛ቊ➛ቋ➛ቌ➛ቍ ➡ 5 #ማስታወሻ ከዝርዋን ፊደላት መካከል አንዱ ጐ ትክክለኛው #ጐ ሳይኾን ይኸው ፊደል ኾኖ ከላይ | መስመር የሌለው እና ገ ኾኖ ጎኑ ላይ ቀለበት ያለው ነው። ገ◦ ▣ዲቃላ(ሕጹጻን) የሚባሉትምየግእዝ ፊደላት መኾናቸውንና በመጻሕፍት ላይ እንደሚገኙ አስተውሉ። ለምሳሌ ያህል፦ ◦ በኊበኈ➟በሰበሰ ፣ሸተተ ማለት ሲኾን "ኊ" እና "ኈ" ኹለቱ ፊደላት ዲቃላ የግእዝ ፊደላት ናቸው። ◦ #ኵሉ ሲል "ኵ" ዲቃላ እንጅ መደበኛ ፊደል አይደለም። ◦ ኰነነ➙ገዛ፥ፈረደ ማለት ነው። "ኰነነ " ከሚለው ግስ "ኰ" መደበኛ የግእዝ ፊደል ሳትኾን ከሕጹጻን ውስጥ ናት። ይኴንን ◦ Mekonnen ለማለት መኰንን ተብሎ በዲቃላ (ሕጹጻን) ፊደላቱ ይጻፋል። ◦ ቋንቋ በሚለው ቃል ውስጥም #ቋ ሕጹጽ (ዲቃላ ) ፊደል ነው። ◦ትርጕም ◦ ቊጥር የመሳሰሉት ይገኙበታል። #ማጠቃለያ ◍ የግእዝ ፊደላት መደበኛዎቹ 26 ከነ አዕጹቃቸው(ቅጥያቸው) 26x7 = 182 ◍ ሕጹጻኑ 4 ከነ አዕጹቃቸው (ቅጥያቸው) 4x5 =20 በድምሩ የግእዝ ፊደላት (መደበኛ + ዲቃላ) 30 ሲኾኑ ከነ አዕጹቃቸው(ቅጥያቸው) ደግሞ 202 ናቸው። #የአማርኛ_ፊደላት መደበኛ የአማርኛ ፊደላት በመባል የሚታወቁት ብዛታቸው ፴፫(33) ሲኾኑ 26ቱን ሙሉ በሙሉ ከግእዝ ቋንቋ ወስዶ 7 የራሱን ፊደላትን 7 ፊደላት አሉት። ስለዚህ የአማርኛ ቋንቋ #የራሱ ፊደላት የሚባሉት ሰባቱ ብቻ ሲኾኑ እነሱም ሸ፣ ጨ፣ ቸ፣ ኸ፣ ዠ፣ ጀ፣ እና ኘ ናቸው። እነዚህም ቢኾኑ ማለቴ 7ቱ ከመደበኛዎቹ ቅርጽ በመውሰድ የተገኙ ናቸው። ፩) #ሸ ቅርጹ የተገኘው ከ #ሰ ፪) #ቸ የተገኘው ከ #ተ ፫) #ጨ የተገኘው ከ #ጠ ፬) #ኘ የተገኘው ከ #ነ ፭) #ጀ የተገኘው ከ #ደ ፮) #ኸ የተገኘው ከ #ከ ፯) #ዠ የተገኘው ከ #ዘ ነው። እነዚህ ፊደላት ማለትም ሸ፥ ቸ፥ ጨ፥ ኘ፥ ጀ፥ ኸ፥ዠ የአማርኛ ቋንቋ ፊደላት በመኾናቸው በግእዝ ቋንቋ ውስጥ አይገኙም። @weldwahidabinet ⛪️⛪️⛪️ትምህርት ❷ ⛪️⛪️⛪️

  • 🌿በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !🌿 በጸሎት የተጀመረ መርሐ ግብር ፍጻሜው ያማረ ይኾናልና ዕለቱም የትምህርታችንም የጾማችንም መጀመሪያ ነውና እኔንም እናንተንም በቸርነቱ ጠብቆ፣ የተሰወረውን ገልጦ፣ አእምሮአችን ብሩህ አድርጎ ፣ በጥበብና በማስተዋል ትምህርታችንን በሰላም አስጀምሮ በሰላም እንዲያስፈጽመን እግዚአብሔር አምላካችንን በያለንበት #አባታችን_ሆይ ብለን ስሙን እናመስግነው። ምዕራፍ አንድ ፩.፩ ስለ ግእዝ እና ግዕዝ ቋንቋውን ለመግለጽ ግዕዝ ወይስ ግእዝ ? አንድን ቃል በተለምዶ ሞክሼ ፊደላት ከሚባሉት ውስጥ በየትኛው ፊደል ሲጻፍ ነው ትክክል የሚኾነው የሚለውን ለማወቅ ዋናው ነገር የቃሉን መነሻ ግስ ማወቅ ነው። አንዳንድ መምህራን ቋንቋውን ለመግለጽ የሚጻፈው በዐይኑ ዐ #ግዕዝ ተብሎ ነው ሲሉ አብዛኛዎቹ ደግሞ በ አልፋው አ #ግእዝ ተብሎ ነው ይላሉ። እስኪ የኹለቱንም ቃላት መነሻ ግሳቸውን እንይ። #ግዕዝ ግዕዝ የሚለው ቃል ገዐዘ (ግዕዘ)☞አዘነ፥ ተበሳጨ፥ ተቆጣ ከሚለው ግስ የተገኘ ዘመድ ዘር ሲኾን ግዕዝ ማለት ዓመል፥ ጠባይ፣ መበሳጨት፥ ማዘን ይኾናል። #ግእዝ ግእዝ የሚለው ቃል ደግሞ ገአዘ (ግእዘ) ☞መጀመሪያ ፥ አንደኛ፥ቀዳሚ ከሚለው ግስ የተገኘ ዘመድ ዘር ሲኾን ግእዝ ማለት የፊደል ስም አንድ ቅንጣት ብቻ ያለው ቅጥያ የሌለው ፣ አንደኛ፣ መጀመሪያ ማለት ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ግስ ወሰዋስው ወመዝገበ ቃላት በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 29ላይ እንዲህ በማለት ይገልጹታል። "ግእዝ የቋንቋና የፊደል ስም ሲኾን በአልፍ አ እንጂ በዐይን አይጣፍም። በዐይኑ ዐ ሲጣፍ ትርጓሜው ሌላ ነው።" ከላይ ባየነው በመነሻ ግሱ መሠረት ቋንቋውን ለመግለጽ በአልፋው አ #ግእዝ የሚለውን እንጠቀማለን። የተለያዩ መጻሕፍት ላይ ግዕዝ ወይንም ግእዝ ተጽፎ ልታገኙ ትችላላችሁ። አብዛኛው የሚጠቀመው ግእዝ የሚለውን ሲኾን፣ እኔም የማምንበት እና የምቀበለው ይህንኑ በመኾኑ በትምህርት ቆይታችን ቋንቋውን ለመግለጽ #ግእዝ የሚለውን እንጠቀማለን። #ልሳነ_ግእዝ #ለሰነ ግስ ሲኾን ተናገረ፥ ለፈለፈ ማለት ነው ። ልሳን ደግሞ በቀጥታ ምላስ ማለት ሲኾን በምላስ መሣሪያነት የሚነገር ቃልና ቋንቋም ከርሱ ስም ተነስቶ #ልሳን ይባላል። በዚህ መሠረት ልሳነ ግእዝ ማለት የግእዝ ቋንቋ ፣ ግእዝ የተባለ ቋንቋ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ 💢💢💢 ፩.፪ የግእዝ ቋንቋ ፊደላት የግእዝ ቋንቋ ፊደላት መደበኛ ፊደላት እና ዲቃላ(ሕጹጻን) ፊደላት በመባል በኹለት ይከፈላሉ። ⭕️ መደበኛ ፊደላት መደበኛ የግእዝ ቋንቋ ፊደላት የሚባሉት ብዛታቸው ፳፮ (26) ሲኾኑ አቀማመጣቸው ኹለት ዓይነት ነው፡፡ 📌የመጀመሪያ አቀማመጣቸው (ቀዳማዊ) [ አ በ ገ ደ .... ] #በአበገደ..ቅደም ተከተል ሲቀመጡ አ➛በ➛ገ➛ደ➛ሀ➛ወ➛ዘ ➛ሐ ➛ኀ➛ጠ➛የ➛ከ➛ለ➛መ ➛ነ➛ሠ➛ዐ➛ፈ➛ጸ➛ፀ ➛ቀ➛ረ➛ሰ➛ተ➛ ጰ➛ፐ = 26 📌 ኹለተኛው አቀማመጣቸው(ደኃራዊ) (አሁን ላይ በአብዛኛው የምንጠቀምበት ) [ሀ ለ ሐ መ....] ሀ➛ለ➛ሐ➛መ➛ሠ➛ረ➛ሰ➛ቀ ➛በ➛ተ➛ኀ➛ነ➛አ➛ከ➛ወ➛ዐ ➛ዘ➛የ➛ደ ➛ገ➛ጠ➛ጰ ➛ጸ➛ፀ➛ፈ➛ፐ = 26 #ማስታወሻ፦ የአቀማመጥ ዓይነታቸው በአበገደ...ኾነ ፤ በ ሀለሐመ... ፊደላቱ በኹለቱም ብዛታቸው ፳፮ (26) መኾኑን እና በኹሉቱም የአቀማመጥ ስልት የተቀመጡት የግእዝ ፊደላት መኾናቸውን ልብ ይሏል። በመኾኑም የግእዝ ተማሪ የኾነ ኹሉ ፊደላቱን በኹለቱም አቀማመጥ በቅደም ተከተል መያዝ ይጠበቅበታል https://t.me/weldwahidabinet 🏳️🏳️🏳️ ትምህርት❶ 🏳️🏳️🏳️

  • 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 #ይዘት- #አንድ 🌻 #ምዕራፍ_አንድ ( የግእዝ ፊደላት ) ◍ ስለ ግእዝ እና ግዕዝ ◍ የግእዝ ፊደላት የሚባሉት ማን ማን ናቸው? ◍የግእዝ ፊደላት አቀማመጥ ◍በተለምዶ ሞክሼ ፊደላት ስለሚባሉት ◍ ፊደላት ያለቦታቸው ሲገቡ የሚያመጡት የትርጕም መፋለስ ◍የተለያዩ መልመጃዎች እና ሌሎችንም በዝርዝር እናያለን። ▣ የሚፈጀው ጊዜ ከ (8-10) የትምህርት ቀናት 🌻 #ምዕራፍ_ኹለት (መራሕያን ) ◦የመራሕያን ትርጉም የመራሕያን ዓይነቶች ◦ሰብአዊ ተውላጠ አስማት ◦ለሰላምታ ልውውጥ የሚያግዙ የግእዝ ቃላቶች ክፍል አንድ ◦ተስሓቢያዊ ተውላጠ አስማት ◦መስተዋድዳዊ ተውላጠ አስማት ◦ለሰላምታ ልውውጥ የሚያግዙ የግእዝ ቃላቶች ክፍል ኹለት ◦ዓመል ያለባቸው ግሶች እርባታ ◦በግእዝ ዐረፍተ ነገር መሥራት ◦የመራሕያን አገልግሎት ◦የተለያዩ መልመጃዎች እና ፈተና እና ሌሎችንም በዝርዝር እናያለን። ▣ የሚፈጀው ጊዜ ከ (ከ30-35) የትምህርት ቀናት 🌻 #ምዕራፍ_ሦስት ፩) ግስ ◍ የግስ ትርጉም ◍ የመደበኛ ግስ ባሕርያት ◍ የግስ ጥናት ➧ስምና የስም ዓይነቶች ◍የአናቅጽ ዐይነቶች (ዘር እና ነባር ) ➧ዐበይት አናቅጽ - ኀላፊ አንቀጽ -ትንቢት አንቀጽ ▹ዘንድ አንቀጽ -ትእዛዛዝ አንቀጽ ◍ አርእስተ ግስ ◍የግስ አወራራድ (ግስ መግሰስ) ◍ አሥራወ ግስ ➧መልመጃዎች ➧ንኡሳን አናቅጽ ◍ አርእስት ◍ቅጽል እና ዐይነቶቹ -ሣልስ ቅጽል -ሳድስ ቅጽል ፫) አገባባት -መስተጻምራን ቃላት -መስተዋድዳን ቃላት እንዲሁም ሌሎች ንኡሳን ርእሶች ይኖራሉ። #ዋቢ_መጻሕፍት ለትምህርታችን ማጠቃሻ የሚኾኑ መጻሕፍትን እያንዳንዱን ምዕራፍ ተምረን ስንጨርስ የማሳውቃችኹ ሲኾን ለጊዜው የዕለቱን ትምህርት በንቃት መከታተል በቂ ነው። መልካም የትምህርት ጊዜ! መስከረም 1/2014

  • 🌼 ዕንቍጣጣሽ 🌼 እንቋዕ እም ዘመነ ማቴዎስ ኀበ ዘመነ ማርቆስ በሰላም ወበጥዒና አዕደወክሙ የተከበራችሁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም በጤና አሸጋገራችሁ በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ለዛሬ ደርሰናል እነሆ ትምህርታችንን ልንጀምር ነው። 🌺 ትምህርቱ በሥርዐት የተደራጀ ፣ በዕቅድ የሚመራ እና ሕግና ደንብ ያለው፣ ጀማሪ የግእዝ ቀንቋ ተማሪን ታሳቢ ያደረገ ሲኾን የግእዝ ቋንቋን በቀላሉ ለመረዳት ያስችላል። 🌺 ትምህርቱ በሳምንት ሦስት ቀናት 👉በዕለተ ሠሉስ (ማግሰኞ) 👉በዕለተ ሐሙስ (ሐሙስ) 👉በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት (ቅዳሜ) እንደ ኢትዮጵያን ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 12:00 እስከ 3:00ድረስ በዚሁ የቴሌግራም ቻናል ይለቀቃል። 🌺 ትምህርቱን በትክክል የተከታተለ ተማሪ 👉 ስለ ግእዝ ፊደላት ጠንቅቆ ይረዳል። 👉 አንድን ቃል በትክክለኛ የግእዝ ፊደላት ይጽፋል። 👉 በግእዝ ቋንቋ መነጋገር፣ መጻፍ፣ አንብቦ መረዳት የሚያስችለውን ዕውቀት ይገበያል። 👉 ውዳሴ ማርያም በግእዝ ማንበብ 👉 መዝሙረ ዳዊት በግእዝ ማንበብ 👉በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚጸለዩ ማናቸውንም የግእዝ ጸሎቶች(ቅዳሴ) ለመስማት እና መረዳት፥ ገብቶትም ለመጸለይ የሚያስችል ትምህርትን ቢያንስ ያገኛል። 🌺 ትምህርቱን ለማገዝ የተለያዩ መልመጃዎች ምዘናዎች እና የተግባር ስራዎችን የሚሰጡ ሲሆን መልመጃዎቹን በአግባቡ መስራት በጣም ጠቃሚ ነው በተጨማሪም በሦስት መመዘኛዎች ጥሩ ውጤት ለሚያመጡ ተማሪዎች 🎉🎉🎉ሽልማት 🎉🎉🎉🎉 ተዘጋጅቷል። #ተግታችሁ ተማሩ። ከዚህ በተጨማሪ ያሉትን ወደፊት የምንነጋገርባቸው ይሆናል። ✅ትምህርቱን ለመጀመር በቂ ሰው አለ ነገር ግን ይህ ትምህርት ማንንም ሊያመልጥ አይገባም 👉 ጓደኞቻችሁ (ቢያንስ 3) 👉 ቤተሰቦቻችሁ 👉የስራ ባልደረቦቻችሁን 👉 ሰንበት ተማሪዎችን እንዲቀላቀሉ አሁኑኑ ጋብዟቸው!! ለመልሶች እና ለአስተያየት ከዚህ በታች ያለውን 'ሊንክ ' ይጠቀሙ!! @mels_asteyayet https://t.me/weldwahidabinet

  • 🌻🌻🌻 🌻🌻🌻 🌻🌻🌻 🌷በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !🌷 ዓርብ 21/12/13 ዓ.ም የተከበራችኹ የመ/ቅ/ኢያቄም ወሐና ቤተ ክርስቲያን ወልድ ዋህድ ሰ/ት/ቤት የአብነት እና የልሳነ ግእዝን ተማሪዎች እንኳን በደኅና መጣችሀ!! ይህ በመ/ቅ/ኢያቄም ወሐና ቤተ ክርስቲያን ወልድ ዋህድ ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል የአብነት ትምህርት ማስተባበሪያ አማካኝነት 🔴 የግእዝ ቋንቋንእና ⚪መሠረታዊ የአብነት ትምህርት መግቢያዎችን ለሰ/ት/ቤት ተማሪዎች፣ ለአብነት ተማሪዎች እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ና ምእመናን ከመጽሐፍት እና ከተለያዩ ምንጮች የምናገኛቸው አስተማሪና ጠቃሚ ትምህርቶች ለማስተማርም ታቅዶ የተዘጋጀ "ቻናል" ነው። 💐 እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ትምህርቶቹን #መስከረም 1 ቀን2014 ዓ.ም ለመጀመር አስበናል በመሆኑም ትምህርቱን እኩል ለመጀመር ያቀድን በመሆነኑበአንድም በሌላም ምክንያት ግእዝን መማር የሚፈልጉ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች ካሏችሁ እስከ ዓርብ 05/13/2013ዓ.ም ጊዜ ድረስ ከዚህ በታች ያለውን "ሊንክ" በመጫን እና በመቀላቀል ይመዝገቡ!! @weldwahidabinet በቀጣይ ስለ ትምህርቱ ሕግና ደንብ ፣ ስለምንማራቸው የትምህርት ርእሶች የምናሳውቃችሁ ሲኾን ትምህርቱ እስከ ሚጀመር ድረስ በየቀኑ እየገባችሁ መልእክቶችን እንድትከታተሉ በታላቅ ትሕትና እናሳስባለን ፡፡ #ማሳሰቢያ፦ ትምህርቱ እጅግ ቀላልና አጓጊ በመኾኑ በቻላችኹት አቅም ከቤተሰብ ጋር ኾናችኹ ብትማሩት እንመራለን። ቤተሰቦቻችኹ፣የሥራ ባልደረቦቻችኹ እና እናንተን የሚመስሏችኹን ኹሉ ብትጋብዙ በአንድ ድንጋይ ለቤታችኹ መሠረት ትጥላላችኹ፣ የግእዝ ተናጋሪ ቤተሰብን ታፈራላችኹና ፣እናንተ እግራችኹ ቀድሞ ገብቷልና እንደቤታችኹ ቆጥራችኹት ያልገቡትን ብትጋብዙ ትጠቀሙበታላችኹ። እኔ እንኳን አይገባኝም፣ እሱ እንኳን አይገባውም እሷ እንኳን አይገባትም አትበሉ። ትምህርቱ መጻፍና ማንበብ ለሚችል ሊረዳው በሚችል መልኩ የተዘጋጀ ነውና በዚህ በኩል ሐሳብ አይግባችኹ። ኑ ግቡ በጋራ ኾነን በአጭር ጊዜ ግእዝ ቋንቋችን እንማማር። 🌻🌻🌻 🌻🌻🌻 🌻🌻🌻

  • Channel created