የመናፍቃን ጥያቄዎችና መልሶቻቸው!!
Статистика☞ በዚህ ቻናላችን የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን በቤተክርስቲያናችን ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን መልስ የምንሰጥ ይሆናል #join & #share ለቻናል 👉 @kidestaresema ለማንኛውም ጥያቄ 👉 @tiotokos_bot
- Последний пост
- 29 мая
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
እመብርሃን👱♂️
ግንቦት ፩ /1/ በዚችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኀነት የሆነባት ናት ። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቅበሉም ነበርና ። እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር ። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ ክቡር እያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔርየታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኀነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው ። በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔርመልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔርአገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች ። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው ። በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
"የወደድኩህ በጣም ዘግይቼ ነው። ቀዳማዊ ብትሆንም ምን ጊዜም አዲስ ነህ። የወደድኩህ በጣም ዘግይቼ ነው አንተ በእኔ ውስጥ እያለህ እኔ በውጪ እፈልግህ ነበር። አንተ በፈጠርከውና ባሳመርከው ውስጥ ሁሉ ያለማስተዋል እባዝን ነበር። በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን አንተ ከእኔ ጋር ነበርክ እኔ ግን ከአንተ ጋር አልነበርኩም።" ሊቀ ጳጳስ አውግስጢኖስ
የጠዋት ቁርስ ተጋበዙ የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም!! ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹሕ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደ ተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ቃላቶችህ የተመጠኑና ጤናማዎች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡ የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው። ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደ ወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡ ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ፡፡ ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡ እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው? የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡
✨በትሕትናው ልዕልናን ላገኘ፣ ለፍጥረታት ባለው ርኅራኄ የአምላክ እናትን ለሚመስል፣ የተቸገሩትን ፈጥኖ መርዳት ልማዱ ላደረገው፣ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ፣ ደግ እና ሰውን ወዳጅ ለሆነው መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን።✨ "ስድብ ኃጢአት ባይሆን ኖሮ መሰደብ የሚገባው ዲያቢሎስ ነው:: ፍጥረት ሁሉ ስድብ ቢያዋጣ ለዲያቢሎስ የሚመጥን አይሆንም:: የክፋት ምንጭ ለሆነ ለእርሱ ሁሉም ክፉ ቃል መገለጫው ነው:: ይሁንና ቅዱስ ሚካኤል ይህንን ክፉ ጠላት ደፍሮ አልሰደበውም:: "እግዚአብሔር ይገሥጽህ!" አለው:: (ይሁ 1:9) እንደ ሚካኤል ንጹሕ በእኛ ዘመን ማን አለ? እንደ ዲያቢሎስስ ክፉ በእኛ ዘንድ ማን አለ? መልእክቱ ግልጽ ነው:: አንሆንም እንጂ እንደ ሚካኤል ንጹሕ ብንሆን እንኳን እንደ ሰይጣን የከፋን ሰው እንኳን መሳደብ አንችልም:: የመላእክት አለቃ ሚካኤል ከሥልጣኑ የወረደውን የቀድሞውን የመላእክት አለቃ ዲያቢሎስን አንድም ክፉ ቃል አልተናገረውም:: አንዱ ከሥልጣኑ ወድቆ ሌላው ሲሾም አዲሱ ተሿሚ ስለወደቀው ምን እንደሚል እናውቃለን:: አንደበቱ ስድብ በመናገር ያልረከሰው ቅዱስ ሚካኤል ግን ወድቆ በማያርፈው ዲያቢሎስ ላይ የስድብን ቃል አልተናገረም::" (ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ) ✨ቅዱስ ሚካኤል ይጠብቀን
"አርእይኒ ገጸ ዚአኪ ማርያም ምእረ፤ ዘኢይሰምዖ ካልዕ እንግርኪ ነገረ" "ማርያም ሆይ፣ ለሌላው የማልነግረውን ነገር እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ፊትሽን አሳይኝ" መልክአ ማርያም እንኳን ለበዓለ ደብረ ምጥማቅ በሰላም አደረሳችሁ!
ሚስት ስናጭ #ቤተክርስቲያን #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ #ethiopianorthodox #ርእሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረኪዳን https://youtube.com/watch?v=wkfTQmVsUSo&si=dHJ7sap8r_Mgq70J
የመናፍቃን ጥያቄዎችና መልሶቻቸው!! pinned «ክፉ ሐሳብን እንዴት ማሸነፍ እንችላለን?? አባ እንጦንስ በገዳም በነበረበት ጊዜ በሐልዮ(በሀሳብ) ሀጢያት ይጠቃ ነበር። በዚህ ጊዜ እንዲ ብሎ ይጸልያል "ጌታዬ ሆይ እኔ ልድን እወዳለኹ ይሁን እንጂ እነዚህ ክፉ ሀሳቦች ሊተውኝ እና ሊለቁኝ አልቻሉም በመከራ ውስጥ ስሆን ምን ላድርግ? እንዴትስ ልድን እችላለኹ?" በማለት ይፀልያል!! ከጥቂት ደቂቃዎች ቡኋላ ጸሎቱን ጨርሶ ከበዓቱ ሲወጣ የእግዚአብሔር…»
ክፉ ሐሳብን እንዴት ማሸነፍ እንችላለን?? አባ እንጦንስ በገዳም በነበረበት ጊዜ በሐልዮ(በሀሳብ) ሀጢያት ይጠቃ ነበር። በዚህ ጊዜ እንዲ ብሎ ይጸልያል "ጌታዬ ሆይ እኔ ልድን እወዳለኹ ይሁን እንጂ እነዚህ ክፉ ሀሳቦች ሊተውኝ እና ሊለቁኝ አልቻሉም በመከራ ውስጥ ስሆን ምን ላድርግ? እንዴትስ ልድን እችላለኹ?" በማለት ይፀልያል!! ከጥቂት ደቂቃዎች ቡኋላ ጸሎቱን ጨርሶ ከበዓቱ ሲወጣ የእግዚአብሔር መላእክ መነኩሴ መስሎ ቁጭ ብሎ ሥጋጃ ሲሰራ ይመለከታል። ያ መነኩሴ ጥቂት ሲሰራ ከቆየ ቡኋላ ስራውን አቋርጦ ይነሳና መጸለይ ይጀምራል። ጸሎቱን እንደጨረሰም መልሶ ወደ ወደ ስራው ሰሌን መታታቱን ይቀጥላል። በዚህ ጊዜ መልአኩ "እንዲህ ካደረክ ትድናለህ!" ብሎት ተሰወረ!! አባ እንጦንስም ከዚህ ቡኋላ ከዚህ ሀጢያት ሊድን ችሏል!!
“ብዙ እናቶች ስቃይ ካለበት የወሊድ ሰዓት በኋላ ልጆቻቸውን ሌሎች እንዲመግቡላቸው ለእንግዶች ይሰጣሉ። ክርስቶስ ግን እኛ ልጆቹን በብዙ መከራ እና ስቃይ በመስቀል ላይ ከወለደን በኋላ ሌሎች እስኪመገቡን ድረስ አይተወንም። በገዛ ሥጋ እና ደሙ እየመገበ ራሱ ያሳድገናል። በዚህ ሁሉ መንገድም ከራሱ ጋር አንድ ያደርገናል” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
без подписи
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ አገር እንዳይገቡ ተከለከሉ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል። ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል። ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው እንደሚገኙ ታውቋል።
አስተርዮ ማርያም በዘመነ አስተርዮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የሆነበትና የአምላካችን አንድነትና ሦስትነት የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን በጥር ፳፩ የከበረች እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍት ቀን በመሆኑ “አስተርዮ ማርያም” በማለት በዓልን አናደርጋለን፡፡ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባስገነዘባት መሠረት በክብር ዐርፋለች፡፡ የዚህን ዓለም መከራና ሥቃይ ለሰዎች ድኅነት የተቀበለችው ክብርት እናታችን በሥጋ ብትሞትም እንደ ልጇ ደግሞ በትንሣኤዋ ተነሥታለች፤ ይህም የሆነው በተቀደሰች ዕለት ነሐሴ ፲፮ ነው፡፡ እመ ብርሃን ከእናትና ከአባቷ ጋር ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት፣ ከተወዳጁ ልጅዋ ጋር ፴፫ ዓመት ከሦስት ወር፣ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ፲፭ ዓመት፣ በድምሩ ፷፬ ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓመተ ምሕረት በክብር ዐርፋለች፡፡ ክርስቲያኖች በሙሉ ይህንን በዓል ልናከብር ይገባልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትን ሠርታልናለች፡፡ “አስተርዮ ማርያም” በሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ የሚከበር በዓል በመሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉን የምናከብረውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፍ በማዘከር ብቻ ሳይሆን አማላጅነቷና ተረዳኢነቷን በማሰብና ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ ስለዚህም እመ ብዙኃን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዐሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን እንድታስባት፣ ለእኛም ለሕዝቦቿ ሰላምን፣ ፍቅርንና አንድነትን ታሰጠን እንዲሁም ለነፍሳችን ድኅነትን ትለምልን ዘንድ ዕረፍቷን መዘከር ይገባል፡፡
https://vm.tiktok.com/ZM6sSSYoy/
እኛ የምናገለግለውና የምንቀድሰው፣ ሥጋ ወደሙን የምንቀበለውና የምናቀብለው የምንዘምረውና የምንቀድሰው በቅተንና ንጹሕ ሆነን መስሏችሁ ነው? የለም የለም ጉዳዩ ስለገባን ነው ጉዳዩ የመዳን ጉዳይ ስለሆነና ሌላው ሌላው ነገር ስለማያዋጣ ነው። ምዕመናን እናንተም አትሞኙ ይሄ እኮ መንፈሳዊ ገብያ ነው ሁሉም እንደ አቅሙ ለሰማያዊ ጉዞው የሚያስፈልገውን ስንቅ እየሸመተና እየገዛ ነው እናንተም የሥላሴን ቸርነት እያሰባችሁ ንስሐ በመግባት ሥጋ ወደሙን ተቀበሉ እንጂ እግዚአብሔርን እንደ ጨካኝ እያሰባችሁ ወደ ኋላ አትበሉ። ነገረ ሥላሴን ማወቅና ሃይማኖት ይቀድማል ሌላው ነገር ጌጣጌጥ ነው ትምህርት ነው የሚጎድለን ስብከትማ ተሰብካችሁ አልቃችሁ የለ? ሁሉም እየተነሳ ይሰብካችኋል ይጮህባችኋል በቃ ተሰብካችሁ አልቃችሁ የለ! አሁን መማር ያለባችሁ ነገረ ሃይማኖት ነው በሱም ላይ መጽናት ነው። #ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በረከታቸው ይደርብን። @kidestaresema @kidestaresema6 @kidestaresema
ወጣት ነህን? ወጣት በመሆንህ ገና ብዘለ ዘመን አለኝ እድሜዬ ገና ነው ብለህ አትተማመን። ተለክቶ የታወቀ ቀሪ ጊዜ ያለህ አድርገህም አታስብ። "የጌታ ቀን ድንገት እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና" 1ኛ ተሰ 5፥2 ስለዚህ ምክንያት የዕድሜያችንን መጨረሻ አስቀድመን እንድናውቀው አደረገ ይህም ከዛሬዋ ዕለት ጀምሮ በትጋት ዝግጅታችንን እንጀምር ዘንድ ነው። በለጋ ዕድሜያቸው ሲቀጩ በየጊዜው አታይምን? ስለዚህም ሲራክ ሲመሰክር እንዲህ ብሏል:- "ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ አትዘገይ ከዛሬ ነገ እመለሳለው እያልክ ቀጠሮ አትቅጠር" ሲራ 5፥8 ዛሬ ነገ እመለሳለው ስትል አንድ ቀን ባቋራጭ እንዳትወሰድ!! ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
https://youtu.be/o7JN1b_XxKM?si=X2h8IdRxOknJDG5R
https://youtu.be/o7JN1b_XxKM?si=X2h8IdRxOknJDG5R
📖ከአፍ የሚወጣ እሳት "አፌ ይለፈልፋል እንጂ ውስጤ እኮ ንጹሕ ነው" አለች አባ ፊት ቀርባ - በክፉ ንግግርዋ ብዙ ሰው ያስቀየመች ሴት:: አባ መለሱላት :- ልክ ነሽ ልጄ እባብም እኮ መርዙን ከተፋ በኁዋላ ውስጡ ንጹሕ ነው! ምላስ አጥንት የለውም ነገር ግን አጥንት ይሰብራል:: እግዚአብሔር ምላስን እንደ ጆሮ ክፍት አላደረገም:: በከንፈርና በጥርስ ሸፍኖታል:: ትንሽ አሰብ አድርገን እንድናወራ ነው:: "ሰው ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን" የሚለው ቅዱስ ያዕቆብ ስለ አንደበት ሲናገር "ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል" እንዳለ የምላስ ኃይል እጅግ ከባድ ነው:: ከአፍ የሚወጣ እሳት ብዙ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል:: ሰው በዱላ ቢደበደብ ታክሞ ቁስሉ ያገግማል:: ክፉ ንግግር የሚያቆስለው ቁስል ግን በቀላሉ አይሽርም:: ዱላ የሚያርፈው ሥጋ ላይ ሲሆን መጥፎ ንግግር ግን ነፍስ ላይ ነው:: ክፉ ንግግሮች ሰውን ለጊዜው ብቻ ሳይሆን ለዘላለም ሊያመርሩት ይችላሉ:: (ሌላ ነገርዋን ትተነው) ሚሼል ኦባማ በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ በጣም ልብ የሚነካ ነገር ስትናገር ሰማሁ። ስለወረደባት ስድብ ስታስታውስ "አንዳንድ ክፉ ቃላት የነፍስን ቅርፅ ይቀይራሉ" ብላ ነበር:: እውነት ነው በመራር ቃላት የነፍሳቸው ቅርፅ ከተቀየረ ስንቶች ናቸው? የማይዘነጉት ንግግር እድሜ ልክ የሚያቆስላቸው : የአንድ ሰው ከባድ ስድብ በራስ መተማመናቸውን የነጠቃቸው : የአንድ ሰው "አትችልም" የሚል ድምፅ እጅና እግራቸውን ያሰራቸው እጅግ ብዙ ናቸው:: ሰው ለማሳቅ ተብለው የተሰነዘሩ "ትረባዎች"ና አጥንት ሰባሪ ቀልዶች ቂመኛ ያደረጉዋቸው ሰውን ሁሉ ያስጠሉአቸው ስንት ናቸው? በስድብ ብቻ የፈረሱ ቤቶች አሉ:: ስለተሰደቡ ብቻ በሕዝብ ላይ የሚፈርዱ ዘር እስከማጥፋት የተነሡ አሉ:: ተናጋሪው በጥፋታቸው ውስጥ ትልቅ ድርሻ እና ተጠያቂነት እንዳለው ግን ይዘነጋል:: እግዚአብሔርም "እንደ ዋዛ ለተናገራችሁት ቃል በፍርድ ቀን መልስ ትሠጡበታላችሁ" ብሎአልና ለሰዎች የምንሰነዝረው እያንዳንዱ ቃል ያስጠይቀናል::በተቃራኒው ለሰዎች ጥሩ ቃል መናገርን ብዙ ዋጋ አንሠጠውም:: ለስድብ የማናቅማማ ሰዎች ለምስጋና ሲሆን ግን እንሽኮረመማለን::ፊት ለፊት አሳምረን የምንሳደብ ሰዎች ለማመስገን ሲሆን "በፊትህ ማመስገን እንዳይሆንብኝ" እንላለን::ሆኖም ብናወጣው ሰዎች የሚነገራቸው ጥቂት በጎ ቃል ሰብእናቸውን ይገነባል:: ፈጣሪ "ብርሃን ይሁን" ብሎ በቃሉ እንዳበራው ማድረግ ባይቻልህ እንኩዋን በጥቂት በጎ ቃላት የአንድን ሰው ቀን ማብራት ትችላለህ:: ከምንም ሥጦታ በላይ መልካም የምስጋና ቃላት በሰው ልብ የሚቀር ውድ ሥጦታ ነው::ባል ለሚስቱ ከሚገዛው ሥጦታ በላይ "ባልዋም ያመሰግናታል" የሚለውን ቃል ቢፈጽምላት ደስታ ይሆንላታል:: ልጆች ከብዙ ሥጦታዎች በላይ ከወላጆቻቸው የሚሰሙት የፍቅር ቃል ይሠራቸዋል:: የእስክንድርያው ፊሎ ለልጅ አባትና እናቱ ከሀገሪቱ ንጉሥና ንግሥት በላይ ናቸው ይላል:: የንጉሥ ቃል የሹመት ቃል ነውና ልጆች በወላጆቻቸው የሚሰሙት "ጎሽ" የሚል ቃል ከፍ ያደርጋቸዋል:: "ልጅሽ ትምህርት የማይገባው ደደብ ስለሆነ ትምህርት ቤት አትላኪው" የሚልን ደብዳቤ "ልጅሽ በጣም ጎበዝ ስለሆነ እሱን ማስተማር ስለማንችል በቤት አስተምሪው" ብላ ያነበበች እናት ትልቅ ሳይንቲስት አፍርታለች:: ብርሃን ይሁን ! ምድር ታብቅል! ብሎ የፈጠረን አምላክ በአርኣያው ፈጥሮናልና በቃላችን የምናሳምም ሳይሆን የምንፈውስ እንሁን:: እናንተ ግን ንግግራችሁ በጨው እንደተቀመመ ይሁን። ✍ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ @kidestaresema @kidestaresema6 @kidestaresema
"ውስተ አፍላገ ባቢሎን ህየ ነበርነ ወበከይነ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ውስተ ኲሓቲሃ ሰቀልነ እንዚራቲነ" " በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ ጊዜ አለቀስን በአሓያ ዛፎቿ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን" መዝ 136፥1 @kidestaresema @kidestaresema @kidestaresema