tgindex
ጸጋ ሥላሴ || Tsegasilase

ጸጋ ሥላሴ || Tsegasilase

Статистика

ከማይደርቅ እውነተኛ ምንጭ የሚቀዳ 🛑 YouTube 🛑 https://youtube.com/@tsegasilase?si=aV9bMxo_NGQBImVp ለማንኛውም ዐሳብና አስተያየት 👇👇 @TsegasilaseBot

Последний пост
26 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
993
0 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
688
21 постов
Вовлечённость
69,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
416
1/48двое суток
476
1/72трое суток
514

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል https://youtu.be/1sUF5BiP6Ag?si=IlLJhsAmHFGp9zPe

  • በቤተ መቅደሱ መሠዊያ ፊት ቆመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለምእመናን የሚያቀብሉት ቀሲስ ሥልጣኑ ፣ ከቤተ መቅደስ መውጫ በስተጀርባ እጅግ ከባድ የኾነ የሕይወት መስቀል ተሸክመዋል። እርሳቸው ለቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምእመናን መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡ ፣ ለአምላካቸው ታማኝ አገልጋይ ቢኾኑም ፤ በውስጣዊ ሕይወታቸው ግን በከባድ ሕመም እና በድህነት እሳት ውስጥ ያልፋሉ። የመጀመሪያ ልጃቸው የኾነችው ሕፃን ዓለም ሥልጣኑ በከባድ የአእምሮና የአካል ሕመም ምክንያት መናገር ፣ መራመድ ፣ ሰዎችን መስማትም ሆነ ምግብ በራሷ መመገብ አትችልም። ዳይፐር የመግዛት አቅም ስለሌላቸው ሕፃኗ ለብርድና ለእንግልት ትዳረጋለች። የሕፃኗን ሁኔታ የሚያዩ አከራዮች «ልጃችሁን ይዛችሁ ውጡልን» እያሉ በየሳምንቱ ስለሚያባርሯቸው ፣ አባታችን ልጃቸውን አዝለው በየደጁ ለማልቀስና ቤት ለመቀየር ተገደዋል። ቀሲስ ሥልጣኑ በቤተ መቅደሱ ከመቀደስ አልፈው ፣ የቀን ደሞዛቸው ለልጃቸው ዳይፐርና ምግብ እንኳ ስለማይበቃ በየመንገዱ ሎተሪ ፣ ሽቶና ካልሲ እያዞሩ ይሸጣሉ። ከዚህ ሁሉ ልፋትና እንግልት የተነሣ እርሳቸውም ደም እየተፉ አገልግሎታቸውን ይቀጥላሉ። ቀሲስ ሥልጣኑ ከዚህ ሁሉ ሥቃይ ጋር ልጃቸውን እንደ ዓይናቸው ብሌን ይንከባከቧታል። በቅኔያቸውም እንደ ኢዮብ ይሄን ከባድ ፈተና ለመልካም እንዳመጣባቸው ገልጸው ፣ የልጃቸውን ሕመም በራሳቸው ላይ እንደደረሰ አድርገው ይገልጡታል። ዛሬ እኚህ አገልጋይ አባት የሚያስፈልጋቸው ነገር ቢኖር የሕፃኗን ሕክምና ማድረግ ፣ የተረጋጋ የመጠለያ ቦታ ማግኘት እና የዕለት ምግባቸውን ማሟላት ነው። «እነሆ በኢየሩሳሌም እና በኢያሪኮ መካከል ወድቀው ደም የሚተፉ የተጎዱ አባታችንን የምናይበት ጊዜ አሁን ነው!» እግዚአብሔር አምላክ ለሁላችንም ከሰጠን በረከትና ሀብት ላይ ጥቂት አካፍለን ፣ የእኚህን የእግዚአብሔር አገልጋይና የሕፃኗን ዕንባ እንድንጠርግ ፤ «እንደ ደጉ ሳምራዊ በመንገዳቸው አልፈን» የእርዳታ እጃችንን እንድንዘረጋላቸው የዛሬ ጥሪዬ ነው። እገዛ ለማድረግ👇 1000252386215 ቀሲስ ሥልጣኑ ዋስይኹን 0929244662 የዛሬ የፊልም ዳሰሳችንን በዚህ ተክተነዋል። በቀጣይ ሳምንት በሰላም ያድርሰንና Man of God የሚለውን ፊልም እንዳስሳለን። በማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ የተለቀቀውን ከላይ የጻፍኩትን ሀሳብ በሙሉ ቪዲዮ ለመመልከት ከታች የተያያዘውን Link ተጫኑ። https://youtu.be/ZGFOdAeTeqI?si=prb0LrAzxW0tzv0L

  • "ገንዘብ እንፈልጋለን ፤ የገንዘብን ባለቤት ግን ትተነዋል። ጤና እንፈልጋለን ፤ የጤናን ባለቤት እግዚአብሔርን ትተነዋል። ሰላም እንፈልጋለን ፤ የሰላምን ባለቤት ርቀነዋል። ከእሱ ርቀን ምንስ ሊገኝ ይችላል? እግዚአብሔር ባለበት ግን ሁሉ አለ። እግዚአብሔር ያለበት ሁሉ ገንዘብም ነው ፣ ሰላምም ነው። እግዚአብሔር የሌለበት ደግሞ፦ 🔸ምቾት እንኳን ቢሆን . . . ስቃይ ነው! 🔹ነፃነት ቢሆን እንኳን . . . እስራት ነው! 🔸ክብር ቢሆን እንኳን . . . ውርደት ነው! 🔹ባለጸግነት እንኳን ቢሆን . . . ድህነት ነው!" ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

  • 🎬 “አሁን ሰዓቱ ስንት ነው?” የቅዱሱ አባት የአባ ዮስጦስ (ዝምተኛው መነኩሴ) አስደናቂ ታሪክ “እግዚአብሔር አባ ዮስጦስን በ20ኛው ክፍለ ዘመን ያመጣቸው፣ በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ ቅዱሳንን የቅድስና ሕይወት በዓይናችን እንድናይ ለማድረግ ነው” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ከእግዚአብሔር ውጪ ለዚህ ምድር ነገር ሁሉ ጀርባቸውን የሰጡት ፣ በጸሎትና በታላቅ ተጋድሎ የኖሩትና “ዝምተኛው መነኩሴ” እየተባሉ የሚጠሩት የጻድቁ አባ ዮስጦስ ታሪክ በሁለት ክፍሎች ተከፍሎ በመንፈሳዊ ፊልም መልክ ቀርቧል። 📌 ክፍል አንድ፦ ከተደነቀው ዝምታ በስተጀርባ . . . ታሪኩ የሚጀምረው በታላቁ የግብፅ ገዳም (በአባ እንጦንስ ገዳም) ውስጥ ነው ፤ አባ ዮስጦስ በገዳሙ ውስጥ ለብዙ ዘመናት ፍጹም ዝምታን መርጠው በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ኖረዋል። ከተደነቀውና ድንበር ከሌለው ዝምታቸው ባሻገር ግን ፣ በገዳሙ መነኮሳትንና ሰዎችን በድንገት ሲያገኙ የሚጠይቋት አንዲት እንግዳ ጥያቄ ነበረቻቸው፦ 👉 “አሁን ሰዓቱ ስንት ነው?” ይህችን ጥያቄ ለምን ይጠይቃሉ? ከዚህስ ጥያቄ ጀርባ ምን ዓይነት ጥልቅ መንፈሳዊ ምስጢር ተሸሽጓል? ይህ በክፍል አንድ ላይ በስፋት ይተረካል . . . 👉 [ ክፍል 1ን እዚህ ይጫኑና ይመልከቱ ] 📌 ክፍል ሁለት፦ የመጨረሻው ሰዓትና የተገለጠው ተአምር! በሁለተኛው ክፍል የጻድቁ አባት የአባ ዮስጦስ የመጨረሻ የዕረፍት ጊዜ (ሞት) ሲቃረብ የሚታዩትን እጅግ ልብ የሚነኩ መንፈሳዊ ክስተቶች ይመለከታሉ። ሁልጊዜ “አሁን ሰዓቱ ስንት ነው?” እያሉ የሚጠይቁበትን የሰዓቱን እውነተኛ ምስጢር ፤ ማለትም ሰው ወደ ዘላለማዊ ቤት ከመሄዱ በፊት ቀሪው ሰዓት ምን ያህል አጭር እንደሆነ ለእኛ ማስተማሪያ መሆኑን እንረዳለን። ጻድቁ አባ ዮስጦስ ሲያርፉ (ሲሞቱ) መላው ገዳምና ሰማይ በምን ዓይነት ሰማያዊ ምስጋናና ደስታ እንደተሞላ ፣ ያሳዩትስ የመጨረሻው አስገራሚ ተአምር ምን እንደነበረ ክፍል ሁለት ላይ ይመለከታሉ። ይህ ፊልም ልብን የሚነካ ፣ ከምድራዊ ኑዛዜ በላይ ሰውን ወደ ንስሐና ወደ መንፈሳዊ ሕይወት የሚጠራ እውነተኛ ታሪክ ነው። 👉 [ ክፍል 2ን እዚህ ይጫኑና ይመልከቱ ] ለዓለማዊ ሩጫችን ማቆሚያ መስታወት ነው! አባ ዮስጦስ “አሁን ሰዓቱ ስንት ነው?” እያሉ የጠየቁት እኛንም የንስሓ ጊዜያች ሳያልፍብን ነቅተን እንድንጠብቅ ያደርገናል። ለዘመናችን ቅርብ በኾነው በ20ኛው ክፍለ ዘመን በግብፅ በረሃ የነበረውን እውነተኛ ተጋድሎ በዓይናችን እንድንመለከት የሚያደርገንን ይህንን መንፈሳዊ ፊልም ያልተመለከታችሁ እንድትመለከቱት ግብዣችን ነው። በሳምንት አንድ መንፈሳዊ ፊልም እየተመለከትንንና እየተማማርንበት እንቀጥላለን። የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር በረድኤት አይለየን። @Tsegasilase ሐምሌ ፯/፳፻፲፰ የምሕረት ዓመት

  • ዛሬ ማክሰኞ አይደል? ቀጠሮ አለን ፊልሞቹን ተመልክተናል በሚል ተስፋ እንቀጥላለን

  • እንኳን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሳችኹ! የሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን! መልካም በዓል!!!

  • #ዘቀዳሚት ◈◈ “እ . . . ናት” ◈◈ ብዙዎችን "እናት ለእናንተ ምንድናት? እንዴት ትገለጻለች? እናትነት ምንድር ነው?" ብዬ ጠየኳቸው ፤ ብዙዎች የተለያየ ምላሽ ሰጡኝ ፤ ከመልሶች መካከል ይህንን ተመለከትኩ . . . "እናት ፈጣሪ የእርሱን ማንነት በሁሉም ቤት ለማሳየት የፈጠራትና የሚጠቀምባት ጥበብ ትመስለኛለች። ባለ ብዙ ስጦታ ናት። ሥላሴ በጸጋ ለሰው ልጅ የሰጡት ምሳሌያት በሙሉ እናት ለልጇ በምታደርጋቸው ነገሮች በግልጽ ይታያሉ ፍቅር ፣ ትዕግሥት ፣ መሥዋዕትነት ፣ ልግስና ሁሉም . . . እናት በምንም አትገለጽም ፤ በቃ ዝም ብለው እያዩአት መገረም ብቻ ነው እንደ ሠሪዋ። መገለጫዋ ሕመም ነው ፤ በልጇ ደስታም ኃዘንም ማልቀስ። ምናልባት ፍቅር መሥዋዕትነት ነው እንደሚባለው ይኹን እንጃ . . ."  አስገረመኝ! ብዙዎች ስለ እናት ለመግለጽ ሲቸገሩ ተመለከትኩ ፤ አንተ እናታችን አንተ አባታችን እያልን በቤቱ ስላደግነው ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ለመጻፍ ነበር ስለእናት መጠየቅ የፈለግሁት። ንፍገት የሌለበት ፤ ስስትን የማያውቅ ፤ ሁሉን በልግስና የሚሰጥ ፤ ጠይቀውት ቸል የማይል ፤ ቀጠሮ የማይዘነጋ ፤ ቢረሱት የማይረሳ ፤ ቢተዉት የማይተው ፤ ይህንን ታማኝ ወዳጅ "እናት" ከማለት ውጪ በምን ልግለጸው? መምህረ አሕዛብ የተባለ ይህ ታላቅ ሐዋርያ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች በጻፈው እውነተኛ መልእክቱ ላይ ፣ ለልጆቹ የነበረውን መንፈሳዊ ፍቅርና የልብ ትርታ በገዛ አንደበቱ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ “ነገር ግን ሞግዚት የገዛ ልጆቿን እንደምትከባከብ ፥ በመካከላችሁ የዋሆች ሆንን ፤ እንዲሁም እያፈቀርናችሁ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማካፈል ብቻ ሳይሆን የገዛ ነፍሳችንን ደግሞ ልናካፍላችሁ ደስተኞች ነበርን ፥ ለእኛ የተወደዳችሁ ሆናችሁ ነበርና።” (፩ኛ ተሰ. ፪፥፯-፰) አዎ! ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ብቻ ሳይሆን የገዛ ነፍሱን ፣ ደሙንና ዕድሜውን አፍስሶ የጠገነን ፣ ልክ እንደ እናት ማኅፀን በቃል ኪዳኑ ጥላ ሥር አሳድጎ ለክብር ያበቃን ሰማያዊ ሙሽራ ነው።  የዓለም ወዳጅነት ሁሉ በጥቅምና በጊዜያዊ ስሜት ሲለወጥ ፣ ይህ ሐዋርያዊ አባት ግን በፈተናና በስደት መካከል እንኳ ልጆቹን ጥሎ የማይኮበልል እውነተኛ የታማኝነት ማማ ነው። በሕይወትህ መገፋትና ብቸኝነት የተሰማህ ወንድሜ ፤ በሰዎች መካከል ኾነሽ ሰው የለኝም የሚል ጭንቀት የዋጠሽ እኅቴ “የሚሰማኝ ፣ የሚረዳኝና የቀጠሮ ዕለቴን የማይረሳ ታማኝ ወዳጅ ከወዴት አገኛለሁ?” የሚል ጥያቄ ውስጣችሁ ሲፈጠር 'በትምህርቱና በምልጃው ጥላ ሥር ስላሳደገን ስለዚሁ ታላቅ አባት ውለታ ቆም ብላችሁ አስቡ!' “የክርስቶስ እውነተኛ መልክ የሆንክ አባታችን ጳውሎስ ሆይ! እኛ በኃጢአትና በመዘናጋት ብንረሳህም ፣ አንተ ግን እንደ እናት አትተወን ፤ በልግስናህና በጸሎትህ ጥላ ሥር ጠብቀህ ለሰማያዊው መንግሥት አብቃን” እንበለው። ያኔ ያ የማይጠፋው ሐዋርያዊ ፍቅር ልባችንን ያክመዋል። ነገ ደርሰን ከበዓሉ በረከትን ለመቀበል ያብቃን። ከወዲሁ መልካም በዓል! @Tsegasilase ከቀናት በአንዷ ቅዳሜ ሐምሌ ፬/፳፻፲፰ የምሕረት ዓመት #ዘቀዳሚት_challenge

  • без подписи

  • 9 июл.690131

    እናት ለእናንተ ምንድናት? እንዴት ትገለጻለች? እናትነት ምንድር ነው?

  • 8 июл.767171

    ምሥጢረ ሥላሴ 101 ✍️ ዲ.ን ሚክያስ አስረስ (ማስያስ) እንደጻፈው - 2 - ".... እንጂ ..." * መልክእ ማለት በቁሙ ልዩ ልዩ ሕዋሳት (ዐይን፣ አፍንጫ፣ እጅ ... ) መላ ሕዋሳትን ለየብቻ መቁጠርና ማወቅ ነው። ለሥላሴ "መልክእ" ተብሎ ሲነገር "ረቂቃን ሕዋሳት" ማለት እንጂ እንደ ሰው ግዙፍና የሚወሰን ማለት አይደለም። "ረቂቃን ሕዋሳት" የተባለውም የእግዚአብሔርን የባሕርዩን መገለጫዎች ለማመልከት እንጂ "ረቂቃንም ሆነው ክፉላት" ለማለትም አይደለም። "ሕዋሳት" ተብለው የሚነገሩት ማየት፣ መስማት እና ማድረግን የሚያመለክቱ ናቸው እንጂ እንደ ሰው ሕዋሳት ያለ የተገጣጠሙና የተዋሐዱ (Composite) ማለት አይደለም። እዚህ ጋር ሥላሴን በባሕርይ አንድ ስንል "ዋሕደ ባሕርይ"፣ "ዕሩየ መለኮት (Homoousios)" ለማለት እንጂ "ከሁለት ወደ አንድ (በተዋሕዶ) የመጣ Composite" ማለታችን አይደለም። እርሱ "ተዋሕዶ" ለሥጋዌ እንጂ ለሥላሴ አይነገርም። የሥላሴ ባሕርይ የሚከፈል፣ የሚደመር የለውም። ስለዚህም ለእግዚአብሔር "ዐይን፣ አፍንጫ ... " እየተባለ ቢነገር እንደ ሰው መዋቅራዊ (Structural) ሳይሆን፡ ባሕርያዊ እና የባሕርይ መገለጫ መሆንን ያሳያል። የሰው ዐይን አይሰማም፤ የሰው ጆሮ አይዳስስም። ዐይን የማያደርገው (የማይችለው) አለ እያልን ነው። ይኸውም ክፍል እና ክፍልነት ስላለበት ነው። በሥላሴ ዘንድ እንዲህ ዐይነት መከፋፈል የለም። "ሕዋሳት" ለሥላሴ ሲነገሩ የባሕርይ መገለጫዎች ናቸው እንጂ የተደመሩ ክፍሎች አይደሉም። በሃይማኖተ አበውም "ለእግዚአብሔር ዐይኖች ጆሮዎች እንዳሉት መጻሕፍት የተናገሩት የቀሩትም እንዳሉት ስለ እግዚአብሔር የተነገረ ሁሉ የታመነ እውነተኛ እንደሆነ እናምናለን። ነገር ግን አይመረመርም፤ አይታሰብም" (ሕንጻ መነኮሳት 19:33) ተብሎ ቢጻፍ ከቀደሙት አበው ትምህርት የሚቃረን አይደለም። ትልቁ ጉዳይ ለእግዚአብሔር እኒህ ሕዋሳት ሲነገሩለት እንደሰው የአካል ክፍል ማለት አለመሆኑን መረዳት ነው" ገጽ በቁሙ ከአንገት በላይ ያለው ፊት፤ የአካል መገለጫ ማለት ነው። ገጽ የሥልጣን፣ የረድኤት .. መገለጫ ነው። "ገጹ ለእግዚአብሔር ኀበ እለ ይገብሩ እኩየ፤ የእግዚአብሔር ፊት ክፉ በሚያደርጉ ላይ ነው" (መዝ 33:16) ተብሎ ቢነገር "ገጸ መአቱ፤ የቁጣው ፊት ክፉ በሚያደርጉ ላይ ነው" ተብሎ ይተረጎማል። በሌላ ንባብ ለገጸ ምሕረቱም የተነገረ ይገኛል። የፈራጅነት ሥራውን መግለጫ ነው እያልን ነው። **** በሌላ ጉዳይ ጸሎተ ሃይማኖት ላይ "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ" የሚለው ንባብ በስህተት የአማርኛ ትርጉም "በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል" እየተባለ ይነገራል። ይህ ስህተት ነው። ሥላሴ "የሚተካከል/የሚበላለጥ" በአጠቃላይ "የሚወዳደር/የሚነጻጸር" መለኮት (ባሕርይ) የላቸውም። በረከታቸው ይደርብንና አቡነ ጎርጎርዮስ ሌሎችም ሊቃውንት "ዘዋሕድ ምስለ አብ በመለኮቱ" ብለው ወስደውታል። "በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ የሚሆን" ተብሎ በትክክል ሊነገር/ሊመሰከር ይገባል። ወደ ነገረ መለኮቱ ከሄድንም የአማርኛው የስህተት አባባል ከመንፈቀ አርዮሳውያን (Homoiousios ከሚሉ ጋር) ከሚሉት ጋር ያገናኛል እንጂ ከኦርቶዶክሳውያን ጋር አይደለም።

  • 7 июл.624194

    የምርጫችሁን ውጤት አይታችሁታል አይደል? በዚህ ሳምንት የምንመለከተው ዝምተኛው መነኩሴ የሚለውን ፊልም ይኾናል ፤ የፊታችን ሰኞ ደግሞ አጠር ያለች ዳሰሳ እንጽፍበታለን። እስከዚያው በተመቻችሁ ቀን ተመልከቱት ፤ ርእሶቹን ተጭናችሁ ሊንኩን ተከተሉ። ክፍል ፩ ክፍል ፪

  • የመምህራችን የዲ.ን ዮሐንስ ጌታቸው መጻሕፍትን እንድንመርቅ ተጋብዘናል የመጻሕፍቱ ምርቃት የፊታችን፦ ➡️ሐምሌ 4/2018 ዓ.ም 📍በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ 🕓 ከቀኑ 07:00 ሰዓት

  • 5 июл.662332

    🕊️ የማይለወጠው አባት — እግዚአብሔር ወረት የሌለው፣ ትናንት ደግፎ ዛሬ ቸል የማይል። በሌላ ፍቅር የማይወሰድ። ወዳጅ የማይለውጥ፣ ስንለወጥ የማይለወጥ አባት... እግዚአብሔር ነው። ደግሞ የማይደክመው ፣ ምሮ የማይሰለች ፣ ለሁሉም የሚበቃ አባት . . . እግዚአብሔር ነው። ርእሰ ሊቃውንት የኔ ገብረ ኪዳን መልካም ሰንበት

  • 4 июл.817335

    #ዘቀዳሚት ◈◈ እኔን አይሰማኝም ◈◈ በጉሊቱ መሐል እናት ልጇን ታሯሩጠዋለች ፤ ግፊያውና ወከባው ላይ ሌላ ግርግር ተጨምሯል። ልጅ አፍላነቱ ያላቆመው ዓመፅ ፊቱ ላይ እየተነበበ እናቱን ይገለምጣል ፤ ደም አቧራና ወዝ ተቀላቅሎበት ፊቱ አመጽ ተሞልቷል። የሆነ ትልቅ ጥፋት እንዳጠፋ ያስታውቃል ፤ እናትየው በምሬትና በእልህ ትገሥጻለች ፤ ሮጣ ባትደርስበትም በጩኸት ትናገራለች። ልጁ በትዕቢት ማግጠጡን አላቆመም። ተስፋ በቆረጠ ድምፅ እናት አጠገቧ ለቡና አጣጯ “እስኪ አንቺን ከሰማሽ ምከሪው . . . እኔንማ አይሰማኝም! ድብደባዬ ከመግደል መለስ ያለ ኾኖ እንኳን ወይ ፍንክች ፤ ጦስ ሊከተኝ ነው" በቁጭት ተናገረች። “እኔን አይሰማኝም!” የሚለው ያ ምራቅ የዋጠ ምሬት በጆሮዬ አልፎ ወደ ልቤ ዘለቀ። ውስጤን ታላቅ የጸጸት እሳት አቃጠለው። “ፈጣሪ እኔን አይሰማኝም” ያልኩባቸው ጊዜያት ጥቂት አይደሉም ፤ "ከሰው ሁሉ ለይቶ እኔን ምነው ተወኝ?" በማለት ያላማረርኩበት ጊዜ የለም። ላልሰማሁት አምላክ አልሰማኝም የሚል አቤቱታዬ ለራሴ አስገረመኝ። በአምላክ ፈቃድ መጓዝን ፈቃዱ ያላደረገ ፤ ትዕዛዙን ያፈረሰ ፤ አምላኩ የማይወደውን ድብቅ ኃጢአት ደጋግሞ የሠራ ፤ በቃሉ ሲመክረው እምቢ ያለ ፤ ለደግ አባቱ ያልታዘዘ ልጅ "አባቴ አልሰማኝም ማለት ይችላል?" አንዳንዴ እውነተኛው አባት መድኃኔዓለም “ብነግረውም፣ ብቀጣውም እኔን አይሰማኝም!” ብሎ ተስፋ የቆረጠብን እስኪመስለን ልባችን ይደነድን የለ? ታዲያ 'አይሰማንም' ለማለት ድፍረቱን ከየት ነው የምናመጣው? የመድኃኒታችንን ትእዛዝ ለመስማት ጆሮዎቻችን ካልተከፈቱ ለእኛ ጩኸትና ጥያቄ የእርሱን መስማት መጠበቅ ከንቱ ድካም አይኾንም? ጆሮዎቻችንና ልባችን ለእርሱ ሲከፈቱ እርሱም ይሰማናል። እኛ ግን የፈጣሪን ድምፅ ዘግተን፣ የእኛን ጩኸት ብቻ እንዲሰማን እንወተውታለን። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “እኔ በጠራሁ ጊዜ እነርሱ እንዳልሰሙኝ፥ እንዲሁ እነርሱ በሚጠሩበት ጊዜ እኔ አልሰማም” (ዘካ 7፥13) "አይሰማኝም" ከማለት በፊት "አልሰማሁትም" ማለት ይቀድማል ፤ ሰምተነው ቢኾን ያ ሁሉ መዳከር ባልነበር። ሰምተነው ቢኾን ዛሬ ስማኝ ብለን የምንጮኸው ጩኸት ሁሉ መልሱን እያገኘ ከእርሱ ጋር አብረን እንኖር ነበር። “እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኃጢአተኞችን እንዳይሰማ እናውቃለን።” እንዲል ቅዱስ ዮሐንስ (ዮሐ 9፥31) ስንት ጊዜ መድኃኔዓለምን "እኔን አይሰማኝም" አሰኝተነው ይኾን? መድኃኔዓለም ሆይ ቃልህን ባለመስማት ካደረብን ድንዛዜ አውጣን ፤ ለአንተ የምንታዘዝበትን የምሕረት ልብ ስጠኝ! @Tsegasilase ከቀናት በአንዷ ቅዳሜ ሠኔ ፳፯/፳፻፲፰ የምሕረት ዓመት #ዘቀዳሚት_challenge

  • 2 июл.646172

    ይህንን የኹለት መምህራን ወግ አንብቡትማ

  • без подписи

  • без подписи

  • ጥሩ የምትሉትን መንፈሳዊ ፊልም ወይም ዶክመንተሪ ጠቁሙን Comment | @TsegasilaseBot

  • без подписи

  • ሰኔ ፳፩ እንኳን አደረሳችኹ! **** ✍️ በቅድስት ማርያም ስም በፊልጵስዩስ  የመጀመሪያው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የተሠራችበት ቀን ✍️ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ ለሰው ልጆችም ይቅርታ የለመነችበት (የጸለየችበት) ቀን (ሰኔ ጎልጎታ .. ) ✍️ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መንበረ ፕትርክና ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበት ቀን ፤ የመጀመሪያው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ፓትርያርክ  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዩስ የተሾሙበት። (፲፱፻፶፩ ዓ.ም) መልካም በዓል!