tgindex
መሠረተ ህይወት ሰ/ት/ቤት ❤️

መሠረተ ህይወት ሰ/ት/ቤት ❤️

Статистика

"ይህ በደብረ መድሐኒት መድኃኔዓለም እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የመሰረተ ህይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ቻናል ነው። በዚህ ቻናል በመንፈሳዊ ሕይወትዎ የሚበረቱባቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች ባሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ። መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካለዎት @ahunadvert @Yidna

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
940
+2 за 2 дн.
Сутки
−1
−0,11%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
289
21 постов
Вовлечённость
30,7%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 23
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
164
1/48двое суток
187
1/72трое суток
202

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • …….. “ትቤሎ ሐና ለኢያቄም ብእሲሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ” ትርጉም ትቤሎ ሐና ለኢያቄም …ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ”… የራእይ ምስጢር፡- ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትኾን፤ ነጭነቷ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፤ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ ወደ ዦሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየኊ ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በዦሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን መኾኗን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ነሐሴ 7 ፅንሰታ ለማርያም “እንኳን አደረሳችሁ” መሠረተ ሕይወት ሚዲያ

  • «ጾምሰ ይእቲ መሠረተ ኩሉ ሠናያት፤ ወአምሳለ ኩሉ በረከታት፤ ወመጽሔተ ኩሉ መንፈሳዊት ኃይል፤ ወመፍትሔ ሰማያት።» «ጾም የመልካም ነገሮች ሁሉ መሠረት፤ የበረከቶች ሁሉ አምሳል፤ የመንፈሳዊ ኃይል ሁሉ መነጸር (መስታወት) እና የሰማያት መክፈቻ ቁልፍ ናት።» መጽሐፈ ምሥጢር መሠረተ ሕይወት ሚዲያ

  • ✝️ የፍልሠታ ጾም የጸሎት መርሐ ግብር ለሚያገለግል ሰው ከፍጹምነት የምታደርስ የተወደደች የተመረጠች ተልእኮ ጸሎት ናት ። በዚህ የፍልሠታ ጾም ሳምንት የጸሎት መርሐ ግብሩን የሚያስተባብሩ ክፍሎች፦ ━━━━━━━━━━━━━━ 📅 ሰኞ | 04/12/2018 🔹 ራብዓይ ክፍል 📅 ማክሰኞ | 05/12/2018 🔹 ኃምሳይ ክፍል 📅 ረቡዕ | 06/12/2018 🔹 ትምህርት ክፍል 📅 ሐሙስ | 07/12/2018 🔹 መዝሙር ክፍል 📅 ዓርብ | 08/12/2018 🔹 ሕፃናትና አዳጊያን ክፍል 📅 ቅዳሜ | 09/12/2018 🔹 ኪነ-ጥበብ ክፍል 📅 እሁድ | 10/12/2018 🔹 የአባላት ክትትል ክፍል ━━━━━━━━━━━━━━ እግዚአብሔር ጾማችንንና ጸሎታችንን ይቀበልልን። አሜን! መሠረተ ሕይወት ሚዲያ

  • ስንክሳር እረፍቱ ለአባ ስምዖን ዘዓምድ እረፍታ ለቅድስት ሶፍያ ምንባባት ተሰሎ ፩ ም· ፫ ቍ.፩ ፍ፡ም፡ ጴጥ ፩ ም· ፫ ቍ. ፲-፲፭ ግብ፡ ሐዋ፡ ም· ፲፬ ቍ· ፳ – ፍ፡ም፡ ምስባክ መዝ ፵፬ ቍ. ፲፪ - ፲፫ ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ። ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር። የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል። የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ። ለሐሴቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፤ ወንጌል ሉቃስ ም· ፲፰ ቍ ፱ – ፲፰ ቅዳሴ ዘእግዝእትነ ። (ጐሥዓ) እናስቀድስ መሠረተ ሕይወት ሚድያ

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ...አሳስቢ አባቶቻችን እንዳስተማሩን ፆም የምንፆመው በመብል ብቻ እንዳልሆነ የሰውነት አካሎቻችንም እንዲፆሙ አይናችን በጎ በጎዎን መመልከት ጆሮአችን ቃለ እግዚአብሔር እንዲሰማ ማድረግ አፋችን ክፉ ከመናገር መቆጠብ ሌሎችንም እንደዚሁ በንሰሐ ታጥበን ልባችን እንዲታደስ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ቁርኝት ማጠንከር የበረከት ፆም እንደመሆኑ በረከትን ለመውሰድ ያድለን። ​ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ “የብርሃን አጽራር” እያለ እንዳመሰገናት፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጸሐፈ ሰዓታት እንዳሰማው፣ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሱሩግ በግጥም ሐመልማለ ጽጌ እያለ እንዳነጻጸራት፣ እንዲሁም አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው “እመቤታችን ሆይ፤ ከሰማያት በላይ የረቀቅሽ፣ ከኪሩቤል የከበርሽ አንቺ ነሽ” እያለ እንዳቀረበው ምስጋና፣ የዚህች እመቤት ጾም የሰማይና የምድር መገናኛ ድልድይ ነው። በቅዳሴው መበርታት በቅዱስ ያሬድ ዜማ ድምፅ የእመቤታችንን ውዳሴዋን የሊቃውንቱን ትርጓሜ መስማት ሐዘኗን አስበን በረከቷ እንዲደርሰን መፀለይ ተገቢ ነው። ፀሎታችንን ታሳርግልን ዘንድ በምልጃዋ የምንድንበት ፆም ያድርግልን። መሠረተ ሕይወት ሚዲያ

  • እናስታውስዎ !!    ጾመ ፍልሰታን በማስመልከት (ከነገ ጀምሮ) የተዘጋጀ የጸሎት መርሐ ግብር በሰንበት ት/ቤታችን  አዳራሽ ከምሽቱ 12 ፡00 ሰዓት ጀምሮ ስለሚደረግ ሁላችሁም የመርሐ ግብሩ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ። ለሚያገለግል ሰው ከፍጹምነት የምታደርስ የተወደደች የተመረጠች ተልእኮ ጸሎት ናት። የሰ/ት/ቤቱ አባላት ክትትል ክፍል መሠረተ ህይወት ሚዲያ

  • የኅሊና ዳኛ እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ኅሊና ውስጥ፣ ኹል ጊዜ ንቁና ትጉ የኾነ ዳኛ ያስቀመጠው ስለ ምንድን ነው ብለኅ ብትጠይቀኝ፣ ከሰው ወገን ይኽን የ'ኅሊና ዳኛ'ን የመሰለ፣ እንቅልፍ የለሽ ዳኛ ስለሌለ ነው ብዬ እመልስልሃለኹ፤ ዳግመኛም፣ የውጪ ዳኞች በገንዘብ፣ በውሸት በመደለል፣ የሐሰት ፍርድ እንዲሰጡ በማስፈራራት፣ እንዲኹም በሌሎች መጠነ ብዙ ምክንያቶች፣ ርቱዕ የኾነ (ያልተዛባ) ውሳኔአቸውን ሊያጣምሙ ይችላሉ፤ የ'ኅሊና ዳኛ'ን ግን በእነዚኽ በገለጽናቸው ምክንያቶች በምንም መንገድ የሚደለል አይደለም፤ ጉቦ ብንሰጠው፣ ልንዋሸው ብንሞክር፣ ብናስፈራራው፣ ሌላ ሌላም ብናደርግ እንኳ፣ ይኽ የ'ኅሊና ዳኛ' ለምናስበውና ለምንሠራው ኀጢአት ምንም ሳይጠመዝዝ እውነተኛ ፍርድን ይሰጣል፤ ኀጢአት የሠራ ሰው፣ ሌላ ሰው ባይወቅሰውም እንኳ፣ ርሱ ራሱ ራሱን ይወቅሳል፤ አንዴ ወይም ኹለቴ ብቻ አይደለም፣ መላ ዘመኑን እየደጋገመ ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ኅጢአት የሠራነው ከረዥም ዘመናት በፊት ሊኾን ይችላል፤ የኅሊናችን ዳኛ ግን ያን የሠራነው ጥፋት ፈጽሞ አይረሳውም። የኅሊና ዳኛ ኀጢአት ከመሥራታችን በፊትም ይኹን በኋላ ምንም ሳይሸፋፍን በግልጽ ይወቅሰናል፡፡ በተለይ ደግሞ ከሠራነው በኋላ፡፡ ኀጢአት በምንሠራበት ሰዓት ግን ይኸን ዳኛ አጥርተን አንሰማውም፡፡ ይኸውም በምንሠራው ክፉ ሥራ ስለምንሰክር ነው፡፡ ኀጢአት መሥራታችንን ባቆምን ጊዜ ግን ወድያው የጸጸት ሽመሉን ይመዠልጣል፡፡ ይኽም በቀጥታ ምጥ ከያዛት ሴት ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ እርጉዝ ሴት ምጥ የያዛት ጊዜ እጅግ አስጨናቂ የኾነ ሕመም ይሰማታል፡፡ ከወለደች በኋላ ግን በቃላት ሊገለጽ የማይችል ዕረፍት ይሰማታል፡፡ በወለደችው ልጅ ታላቅ ሐሴት ይሰማታል፡፡ ኀጢአት ስንሠራ ግን ከዚኹ ተቃራኒ ነው፡፡ በሐሳብ የፀነስነውን ኀጢአት በግብር እስክንወልደው ድረስ “ደስታ" ይሰማናል፡፡ ከፉው ልጃችንን (ኀጢአታችንን) በግብር ከወለድነው በኋላ ግን በልጃችን ፊት ከፍተኛ ሐፍረት ይሰማናል፡፡ ምጥ ከያዛት ሴት በላይም ያሰቃየናል፡፡ ስለዚኽ ልጆቼ! ይኽን ከፉ መሻት ከመዠመርያ አንሥተን ከመቀበል እንከልከል፡፡ ከተቀበልነው እንኳ ገና ፍሬ ሳያፈራ ሳለ ከውስጣችን (በገቢር ሳንገልጥ) እንግደለው፡፡ ይኽን ማድረግ ሳንችል ቀርተን ልጃችንን በገቢር ከወለድነው ግን በንስሐና በዕንባ እንዲኹም ራሳችንን በመውቀስ እንግደለው፡፡ (ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 49-50) መሠረተ ህይወት ሚዲያ ሠናይ ቀን!

  • ብሒለ አበው ክርስቲያን በማንኛውም ምክንያትና በማንኛውም ሁኔታ ሊጨነቅ አይገባውም፤ የሕያው እግዚአብሔር ፈቃድና ጥበቃ በእጆቹ ላይ ይሸከመዋልና። የእኛ ብቸኛ ጭንቀት ሁልጊዜ ለጌታ ታማኝ ሆነን መኖር ብቻ መሆን አለበት። — ቅዱስ አግናጥዮስ ብሪያንቻኒኖቭ መሠረተ ሕይወት ሚዲያ

  • ስንክሳር እረፍቱ ለዮሴፍ ጻድቅ (የእመቤታችን ጠባቂ) እረፍቱ ለሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ጢሞቴዎስ እረፍቱ ለአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን የአባ ሮዲስና የሳሙኤል መታሰቢያ ምንባባት ቲቶ ም· ፫ ቍ· ፩ – ፍ፡ም፡ ጴጥ ፩ ም· ፬ ቍ· ፮ – ፲፪ ግብ፡ ሐዋ፡ ም· ፳፰ ቍ· ፩ – ፲፯ ምስባክ መዝ· ፻፴፬ ቍ· ፯ - ፰ ያዐርግ ደመናት ደመናተ እምአጽናፈ ምድር ። ወገብረ መብረቆ ለጊዜ ዝናም። ዘያወፅኦሙ ለነፋሳት እመዛግብቲሆሙ ። ከምድር ዳር ደመናትን ያወጣል፤ ለዝናም ጊዜም መብረቅን አደረገ፤ ነፋሳትንም ከመዛግብቱ ያወጣል ወንጌል ማርቆስ ም· ፮ ቍ· ፵፯ – ፍ፡ም፡ ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ። እናስቀድስ መሠረተ ሕይወት ሚድያ

  • 31 июл.2131из AAsundayschool

    https://youtu.be/Vhq0jV0PY-M

  • 31 июл.20311из AAsundayschool

    https://youtu.be/2oKfrzBQ1yU?si=X07ea_Cz1Y1i7pSR

  • የማስተዋል መንገድ ሠላም እንዴት ናችሁ ? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን! መንገደኛው እባላለሁ። ሁሌ ስለምጓዝ የተሰጠኝ የመጠሪያ ስሜ ነው ። በምሄድበት ሁሉ የማያቸውን ነገሮች መመርመር እና መታዘብ ያስደስተኛል ። የኔ አረማመድ በጣም ይለያል ፤ የምሄደው በእግረ ህሊናዬም በእግሬም ነው። '' የምትሄድበት ዓላማ ምንድነው? " ካላችሁኝ ዓላማ የለኝም ። ምክንያቱም ህሊናም ሆነ እግር በሞት እስከ አላረፉ ድረስ መሄዳቸውን እና መታዘባቸውን መመርመራቸውን አያቆሙም። ምን አልባት ሞተውም በዛኛው ዓለም ሊሄዱ እና ሊመረምሩ ይችሉ ይሆናል ፤ በነገራችን ላይ በእኔ አስተሳሰብ ሁሉም ሰው መንገደኛ ነው። ግን ችግሩ የሚሄድበትን መንገድ አያስተውለውም ዝም ብሎ በደመነፍስ ይጓዛል።ይሄን ያህል ከተዋወቅን እስቲ በህሊናዬ ካደረኳቸው ጉዞዎች መካከል በጣም ያስገረመኝን እና ያስደነቀኝን ነገር ላውጋችሁ ። መንገዴን የጀመርኩት የአዳም ዘር ለምን በላቡ ጥሮ ግሮ እንዲበላ ሆነ ብዬ ነበር። እናም በዚህ ውስጥ ወደአሉት መንገዶች ሁሉ ተጓዝኩ አዳም እና ዘሮቹ እንዲህ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ለካ እባብ እና ሰይጣን ባደረጉት የመተዛዘል ጉዞ ነበር ። እባብም ወደገነት ከገባ በኋላ ያደረገው የሽንገላ ጉዞ ነበር ። በመጀመሪያ አዳም ጋር ሄደ።  በመቀጠል ሔዋን ጋር ። እባብ ወደ አዳም የሄደው መንገድ አልተሳካለትም የሔዋን ግን ከሚያስበው በላይ ሆነለት። ታሪኩን እንደምታውቁት ሔዋን ምንም ሳታንገራግር ቀጥታ ወደተሳሳተው መንገድ ጉዞ ጀመረች። ባሏ አዳምም አብሯት ገሰገሰ። አስቡት እባብ አዳምና ሔዋንን ለማሰናከል የተጓዘው የመንገድ ርዝመት እነርሱ ደግሞ የፈጣሪን ትዕዛዝ ለማፍረስ እና ለመሻር የተጓዙበት መንገድ ፍጥነት ። እባብ ከነገራት በኋላ ጊዜ አላጠፋችም መጽሐፍ እንደሚለን "ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ ለዓይን እንደሚያስጎመዥ ለጥበብም መልካም እንደሆነ አየች ከፍሬውም ወሰደችና በላች ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርሷ ጋር በላ" (ዘፍ ፫÷፮)   የምንሄድበትን መንገድ በጥንቃቄ ካልተጓዝን እና ውጤቱ ምን እንደሆነ ካላሰብን ከጅምሩ ባንጓዝ የተሻለ ነው። ካልሆነ ግን መጨረሻችን ሞት ስለሆነ። ብቻ ባጭሩ አዳም የእሳት ሰይፍ በያዘ ኪሩብ እየተገፋ ቀድሞ ይኖርበት ከነበረው ቤቱ ወጣ ። አዳም ከወጣ በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንዲመልሰው ወደ አምላኩ ማልቀስ ጀመረ። ደሙን መስዋዕት ማድረግ ጀመረ። ለዚህ ንስሐው ሲል ፈጣሪም 'ከ 5 ቀን ተኩል ጉዞ በኋላ ነው የማድንህ ' ብሎ ቃል ገባለት ከአዳም በኋላ የነበሩትም እነ አብርሃም ፣ ይስሐቅ ፣ ያዕቆብ ፣ ሙሴ ፣ ኤልያስ ፣ ንጉሥ ዳዊት ፣ ልጁ ሰሎሞን ሁሉም ነቢያት አዳም ከወጣበት ገነት ለመግባት ብዙ መንገድ ሄዱ ግን ሊደርሱ አልቻሉም። ያለ ፈጣሪ ፈቃድ የሚሆን ነገር ስለሌለ።ከዚህ ሁሉ ግን በጣም የሚያስገርመው አምላካችን እግዚአብሔር ለአዳም የገባለትን ቃል የፈጸመበት መንገድ ነው ፤ የቃሉ መዠመሪያ የሆነው ቅዱስ ገብርኤል እና ክርስቶስ በያዙት የምስጢር ጉዞ ነው። ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወደ ምድር የሚያመጣውን መንገድ በፍጥነት ጨርሶ ወደ እርቅ አስፈጻሚዋ ብላቴና ደረሰ። ይህች ብላቴና መንገዷን ሁሉ የምትጓዘው በማስተዋል ነበር ፤ ቅዱስ ገብርኤል ወደ እርሷ ከደረሰ በኋላ ብዙ አወሩ ተከራከሩ ። ብላቴናዋ የሔዋን ዘር ብትሆንም እንደ ሔዋን ግን አይደለችምና በመጨረሻም ተስማሙ። እርሷም እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች በዚህ ቅጽበት ይህን ቃል ባወጣችበት ፍጥነት ቃል በማህጸኗ አደረ ። እባብ በተንኮል ሆኖ ተንኮል እያሰበ ተጓዘ ፤ ቅዱስ ገብርኤል በደስታ በቅንነት ተጓዘ ፤ እባብ ሔዋንን ለማሳሳት ወደ እርሷ ሄዶ የሽንገላ ቃልን ተጠቀመ ፤ ቅዱስ ገብርኤል ብላቴናዋን ለማሳመን የሚያረጋጋ እና የጥበብ ቃል ተጠቀመ ፤ ሔዋን የእባቡን ቃል ሰምታ ወዲያውኑ እፀ በለሱን በላች ለባልዋም አበላች ፤ ብላቴናዋ  የቅዱስ ገብርኤልን ቃል በማስተዋል ሰምታ ክርስቶስን በእርሷ አሳደረች ። (ለካ ሰው ጥሮ ግሮ የሚበላው ባለማስተዋሉ ምክንያት ነው አልኩ) እና ግን ከዚህ ጉዞዬ ስመለስ ሁለት ነገሮችን ተረዳሁ ። ፩;    ምንጊዜም ቢሆን ከክፋት ይልቅ ለፍቅር ከጸብ ይልቅ ለይቅርታ መፋጠን እንዳለብን አምላካችን እግዚአብሔር በዚህ አሁን ባየነው እርሱ እና ባለሟሎቹ ባደረጉት ጉዞ መመልከት ችያለው።     ሁለተኛው እና ዋነኛው ግን ፪;   የሰው ልጅ ማስተዋልን ገንዘብ ካደረገ በማስተዋል መንገድ ከሄደ እይደለም ምድሪዊ ነገሮችን ክርስቶስን በውስጡ ያደርጋል። ስለ ማስተዋል ብዙ ምሳሌዎች ሊጠቀሱ ይችሉ ይሆናል፤ ክርስቶስን ጸንሳ ከወለደችው ብላቴና በላይ ግን ምሳሌ ሊሆን የሚችል የለም ። እስቲ አንድ እንቆቅልሽ ልጠይቃችሁ ዓለም ሳይፈጠር እኔ ከእርሱ ጋር ነበርኩ ዓለም ሲፈጠርም አብሬው ነበርኩ ዓለም ከተፈጠረ በኋላም እኔ አለሁ ዓለም ቢያልፍም እኖራለው እኔ ማን ነኝ?   በማስተዋል መንገድ እንድንሄድ የእርሱ የአምላካችን ፈቃድ የቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጅነት አይለየን።   በባህርዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት የተሞላው ጠቢቡ ሰሎሞን እንዲህ አለ          "ከማስተዋል መንገድ የሚሳሳት ሰው በሙታን ጉባኤ ያርፋል" "ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና በማስተዋል ዘመኑን ዋጁ"             ✍ከ መንገደኛው መሠረተ ህይወት ሚዲያ ሠናይ ቀን!

መሠረተ ህይወት ሰ/ት/ቤት ❤️ — tgindex