tgindex

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት / His Holiness Patriarch Office

Статистика
@EOTCPatriarichateанглийский
Последний пост
6 авг.
Последнее чтение
ещё не заходили
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
1 677
+3 за 2 дн.
Сутки
+3
+0,18%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
492
20 постов
Вовлечённость
29,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
362
1/48двое суток
414
1/72трое суток
447

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣በነገው ዕለት የሚጀመረውን የ2018 ዓ,ም የጾመ ፍልሰታ ሱባኤ በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። “መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ” በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፤ ኣሜን ! በሃገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” (ዮሓ14÷15)፤ ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፤ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡ ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፤ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፤ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው፤ ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል” በማለት ያስተምረናል፤ (1ዮሓ.4÷16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፣ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው” በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤ የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል፤ ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፤ ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፤ በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ” ተብሎ በግልጽ ተቀምጦኣል፤ የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡ ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፤ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፣ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤ በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት ! ከነሓሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔር ትእዛዝና ፍቅር ነው፤ እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብር ኣዞናል፤ከቅዱሳን ፍጥረታት መካከል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤ ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሷ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናከብራታለን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ከእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ከሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው፤ በኣራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው ኣባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር፣ ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፤ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፤ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ፡- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች፤ ከሱራፌልም ትልቃለች፤ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና” በማለት ኣስተምሮናል፡፡ በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናከብር ትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን፤ እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት “እናታችሁ” ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችሽ” ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፤ በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር፣ በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፤ ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የታመሙትንና የታሰሩትን በመጠየቅ፣ ቅዱስ ቊርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ በመጨረሻም፡- በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፣ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ የተባረከና የተቀደሰ ጾም ያድርግልን፤ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ፤ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ ኣሜን! ኣባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘኣኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የታላቋ ብሪታንያ አምባሳደር እና በአፍሪካ ኅብረት የቋሚ መልእክተኛ ክቡር ዳረን ዌልችን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። (ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ በኢትዮጵያ የታላቋ ብሪታንያ አምባሳደር እና በአፍሪካ ኅብረት የቋሚ መልእክተኛ ክቡር ዳረን ዌልችን (HE Darren Welch | UK Ambassador to Ethiopia & Permanent Representative to the African Union) በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። አምባሳደር ዳረን ዌልች ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ያደረጉትን ውይይት አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፤ በኢትዮጵያ እና በእንግሊዝ መካከል ከጥንት ጀምሮ፣ በኋላም ዘመናዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ከተመሠረተበት ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት አንስቶ ለዘመናት የዘለቀ ጠንካራ ታሪክ እንዳለ አስታውሰዋል። አክለውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበርካታ ጥንታዊ ታሪኮችና ቅርሶች ባለቤት፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ልዩ ገጽታና ትልቅ ቦታ ያላት የክርስቲያን መድረክ መሆኗን ገልጸዋል። ቤተ ክርስቲያኗ ለሀገሪቱ ሰላም፣ ታሪክ እና ማህበረሰብ የምታበረክተውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያከብሩ የጠቀሱት አምባሳደሩ፤ ኢትዮጵያ የተለያዩ ሃይማኖቶች በሰላም አብረው የሚኖሩባት ድንቅ የህብረት አርአያ መሆኗን ጠቁመዋል ። በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በቀጣይ ለአብሮነት እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ከነበረው በበለጠ አጠናክረው እንደሚሰሩ አክለዋል ። በመጨረሻም በኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች የሚስተዋሉ የሰላም እጦት እና የኢኮኖሚ አለመረጋጋቶችን ለመቅረፍ ከቤተ ክርስቲያኗ ጎን በመሆን ለጋራ ሰላም እና ለአብሮነት ተባብረው እንደሚሠሩ በመግለጽ፤ ለዚህም ሁሉም አካል የድርሻውን ኃላፊነት ሊወስድ እንደሚገባ አሳስበዋል። __________ #የቅዱስ_ፓትርያርኩ_ሓዋርያዊ_አገልግሎቶች እና ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮችን_ለማግኘት:- ከታች ያለውን link #share, Like & #follow ያድርጉ 👇👇👇👇 1.ድረ-ገጽ:- eotcp.org 2. ቴሌግራም:- https://t.me/EOTCPatriarichate 3 ፌስቡክ ;- https://www.facebook.com/EotcpatriarchateOffice?mibextid=ZbWKwL

  • __________ #የቅዱስ_ፓትርያርኩ_ሓዋርያዊ_አገልግሎቶች እና ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮችን_ለማግኘት:- ከታች ያለውን link #share, Like & #follow ያድርጉ 👇👇👇👇 1.ድረ-ገጽ:- eotcp.org 2. ቴሌግራም:- https://t.me/EOTCPatriarichate 3 ፌስቡክ ;- https://www.facebook.com/EotcpatriarchateOffice?mibextid=ZbWKwL

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። ሓምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት እንደሚከተለው ነው፦ መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!   "ገባሬ ሣህል እግዚአብሔር፥ ወይፈትህ ለኩሉ ግፉዓን፦ እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።" (መዝሙር ፻፪፥፮)   ከሁሉ በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትኖሩ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንን ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ለሚከበረው፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በእምነታቸው የጸኑትን ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን በመከራቸው መካከል እየተራዳ የእሳቱን ነበልባል እንደክረምት ውኃ ላቀዘቀዘበት፤ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን የታመኑትንም እስከ ሰማዕትነት ፍጻሜ ድረስ የሚያጸና መሆኑን ለምንዘክርበት ታላቅ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ የወንጌልን ብርሃን በማብራት፣ የሰላምን መንገድ በማስተማር፣ ፍትሕን በማጽናት፣ የተጨነቁትንም በማጽናናት፣ ሕዝብንና ሀገርን እየደገፈች የኖረች ናት። በዚህ ቅዱስ ተልእኮ ውስጥም መናንያን መነኮሳት እና መነኮሳይያት ዓለምንና ከዓለም የሚገኘውን ጊዜያዊ ክብር፣ ጥቅም፣ ምቾትና የመሳሰሉትን በፈቃዳቸው ትተው፤ በየገዳማቱ በበአታቸው በጾም፣ በጸሎት ተወስነው፤ ሕይወታቸውን በትሕትና ለእግዚአብሔር በመስጠት፤ ስለ ራሳቸው ብቻ ሳይሆን ስለ ሀገር፣ ስለ ሕዝብ፣ ስለ ሰላምና ስለ ዓለም ደኅንነት በመዓልትና በሌሊት የሚጸልዩ የምድራችን በረከቶች ናቸው። መስቀልን በተሸከሙ፣ ጸሎትን መከታ ባደረጉ፣ ለፍጥረት ሁሉ ምሕረትን በሚለምኑ፣ ራሳቸውን ለመከላከልም ምንም ዓይነት ቁሳዊ ዝግጅት በሌላቸው በእነዚህ መናንያን ላይ እጅን ማንሣት በእግዚአብሔር ዘንድ የተከለከለ፣ በታሪክ ፊትም የሚያሳፍር ድርጊት ነው።   የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን! በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅድስት አርሴማ፣ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በተፈጸመው ጥቃት የመናንያን መነኮሳይያት ሕይወት በግፍ መጥፋቱን፤ በርካቶች መቁሰላቸውን፤ በገዳሙና በንዋየ ቅድሳቱ ውድመት መድረሱን ከሀገረ ስብከቱ መግለጫ በከፍተኛ ሐዘን የሰማን ሲሆን፤ በተመሳሳይም በዚሁ ዕለት በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአምልኮ ሥፍራ በኃይል መፍረሱና በምእመናን ላይ ጥቃት መድረሱ የሚያሳዝንና በፍጹም ተቀባይነት የሌለው የተወገዘ ተግባር ነው። በመሆኑም የጸሎት፣ የትምህርት፣ የሰላምና የመንፈሳዊ እሴት ማዕከል የሆኑትን ገዳማት መጠበቅ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ክብርን፣ የሕግ የበላይነትንና የሀገር ሰላምን የማስጠበቅ ሓላፊነት ያላቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪ አካላት ጭምር እንደመሆኑ አሰቃቂ ጥቃት የፈጸሙት ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ፤ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅልን፤ ለተጎዱትም ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግልን ዛሬም አበክረን እንጠይቃለን ። በመጨረሻም ሕዝበ ክርስቲያንና መላው ኢትዮጵያውያን የጥቃት ሰለባ ከሆኑት ወገኖች ጋር በመንፈሳዊም ሆነ በሰብአዊ ድጋፍ አብራችሁ እንድትቆሙ ከአደራ ጭምር እያሳሰብን፤ በጽድቅ የሚፈርደው እግዚአብሔር አምላካችን ለተበደሉት ፍትሕን፣ ለቆሰሉት ፈውስን፣ በግፍ ሕይወታቸውን ለተነጠቁት ዕረፍተ ነፍስን፣ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ፍጹም ሰላምን ይስጥልን እያልን አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን። እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን።   አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ __________ #የቅዱስ_ፓትርያርኩ_ሓዋርያዊ_አገልግሎቶች እና ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮችን_ለማግኘት:- ከታች ያለውን link #share, Like & #follow ያድርጉ 👇👇👇👇 1.ድረ-ገጽ:- eotcp.org 2. ቴሌግራም:- https://t.me/EOTCPatriarichate 3 ፌስቡክ ;- https://www.facebook.com/EotcpatriarchateOffice?mibextid=ZbWKwL

  • без подписи

  • без подписи