ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ
Статистика- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 259
- 1/48двое суток
- 296
- 1/72трое суток
- 320
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
✨ ጉዞ በብሉይ ኪዳን ✨ የተወደዳችሁ የቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ እህት ወንድሞቻችን፣እነሆ ጉዞ በሐዲስ ኪዳን ብለን የጀመርነውን ጉዟችንን እንደ እግዚአብሔር መልካም እና ቅዱስ ፈቃድ ጉዞ በብሉይ ኪዳን ብለን ለመቀጠል እሁድ ነሐሴ 10 ቀጠሮ ይዘናል፣እናንተስ😊 ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ✨
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈሰ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሰባት ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ የምታበራ የብርሃን እናቱ እግዝእትነ ማርያም በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ተፀነሰች፡፡ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ የመንግሥተ ሰማያትን ምክፈቻ ቁልፍ የተቀበለበት ዕለት ነው። ✨ ጽንሰታ ለማርያም ✨ 🌿 የእመቤታችን ወላጆችዋ ኢያቄም እና ሐና ይባላሉ፣ ጻድቁ ኢያቄም እና ቅድስት ሐና በ እግዚአብሔር ፊት በቅንነትና በደግነት የሚኖሩ እውነተኛ አማኞች ነበሩ። ነገር ግን በጋብቻ ዘመናቸው ልጅ ባለመውለዳቸው ምክንያት እጅግ ያዝኑ ነበር። በወቅቱ የነበሩ የእስራኤል ልጆችም “ልጅ ያልወለደ ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው” እያሉ ያቃልሏቸውና ይነቅፏቸው ነበር። 🌿 ቅዱሳኑ ግን በሰው ነቀፌታ ተስፋ ሳይቆርጡ፣ “የአባቶቻችን የእስራኤል አምላክ ሆይ! ለአይናችን ማረፊያ፣ ለልባችን ተስፋ የሚሆን ፍሬ ስጠን” እያሉ ዘወትር በጾምና በጸሎት ወደ አምላክ ይለምኑ ነበር። 🌿 ከዕለታት አንድ ቀን ቅድስት ሐና በቤቷ አትክልት ስፍራ ሳለች፣ አንዲት ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት ተመለከተች። በዚያን ጊዜ ልቧ ተነክቶ፦ “አቤቱ ጌታዬ! ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ፣ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ?” ብላ ምርር ብላ አለቀሰች። ከዚህ በኋላ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ወደ ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ዘንድ በመሄድ ታላቅ ስዕለት ተሳሉ፦ “ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን እንዲያገለግል፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ውኃ ቀድታ፣ መሶበ ወርቅ ሰፍታ፣ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ እናደርጋለን” አሉ፤ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስም "እግዚአብሄር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስዕለታችሁን ይቀበልላችሁ" ብሎ አሳረገላቸው። 🌿 ከዚያም ቅድስት ቡርክት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ፦ ጻድቁ ኢያቄም፦ “ሰባት ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው፣ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” አለ። ❖ ‹‹ወፍ›› የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው፤ ‹‹ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› ማለቱ የኢያቄምን (የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው ዕወቅ ሲል ነው፡፡ ❖ ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባሕርይው ምልአቱ ስፍሃቱ ርቀቱ ልእልናው ናቸው፤ ቅድስት ሐና፦ “እኔም ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ፣ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ” አለችው። ‹‹ርግብ›› የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፣ ነጭነቷ ንጽህናዋ ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው፤ ‹‹ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ›› ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፅነሷን ነው፡፡ ይህንን ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው:: “ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን” ብለው ዕለቱን አልጋና ምንጣፍ ለይተው ለሰባት ቀን ያህል በጸሎት ተለይተው ሰነበቱ። 🌿 በሰባተኛው ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለጻድቁ ኢያቄም በተራራ ላይ ሲጸልይ በተገለጸለት ጊዜ፦ “ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች፤ ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን፣ ለብዙዎች የሕይወት ብርሃንና ድኅነት የምትሆን ሴት ልጅ ትወልድልሃለች” ሲል አበሰረው። መልአኩ ለቅድስት ሐናም ተገልጦ የጌታን ፈቃድ ነገራት። 🌿 በብስራተ መልአክና በፈቃደ እግዚአብሔር፣ እሁድ ዕለት በነሐሴ 7 ቀን ከሰው ሁሉ የበለጠች፣ ከመላእክትም የከበረች፣ የዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነችው አምላክን የምትወልደው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማኅፀነ ሐና ተፀነሰች። ✨ቅዱስ ጴጥሮስ (ሊቀ ሐዋርያት)✨ በዚችም ቀን የሐዋርያት አለቃ የከበረ ሐዋርያ ጴጥሮስ በዓል ነው ። በዚች ቀን ጌታችን የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እርሱ እንደሆነ በሐዋርያት መካከል ታምኗልና ። 🌿 በከበረ ወንጌል እንደተባለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል" ብሎ ጠየቃቸው እርሱ ልብን ኲላሊትን የሚመረምር ሰዎች የሚያስቡትን ሁሉ የሚያውቅ ሲሆን ። 🌿ያን ጊዜ ሐዋርያት ተጠራጣሪዎች ስለነበሩ ስለዚህ ያሰቡትን በልባቸው ያለውን እንዲናገሩ ከከተማ ውጭ አወጣቸው ። ከእነሱም ኤልያስ እንደሆነ የሚያስቡ አሉ ወይም ከቀደሙት ነቢያት አንዱ እንደሆነ የሚሉም ነበሩ ። 🌿ጴጥሮስም በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ "ለምን እንዲህ ታስባላችሁ እርሱ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነው እንጂ" አላቸው ። 🌿ስለዚህም የጴጥሮስን ሃይማኖት በመካከላቸው ይገልጥ ዘንድና ግልጥ ሊያደርግ ወደ ውጭ አወጣቸው ። እንዲሁም በጠየቃቸው ጊዜ ኤልያስ እንደሆንክ ወይም ከቀደሙት ነቢያት አንዱ እንደሆንክ ሰዎች ይናገራሉ በማለት እነርሱ የልባቸውን ተናገሩት ። ጴጥሮስ ግን አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ ብሎ በእውነት መሰከረ።(ማቴ 16÷16) 🌿ስለዚህም ጌታችን አመሰገነው የመንግሥተ ሰማያትንም ቊልፍ ሰጠው ። ከዚያች ቀን ወዲህ የሐዋርያት ሁሉ አለቃ ሆነ በእርሱም የሊቃነ ጳጳሳት የኤጲስቆጶሳት የቀሳውስትና የዲያቆናት ሹመት ተሰጠ ። የቤተ ክርስቲያንም መሠረት ተባለ ። የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና በረከት፣ የቅዱስ ኢያቄምና የቅድስት ሐና ጸሎት አይለየን።ከሊቀ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ረድኤት በረከት ያድለን፤ በጸሎቱ ይማረን!አሜን። ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ✨
без подписи
без подписи
✨ የመስቀል ወረብ ጥናት ✨ ሰላም ውድ የቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ልጆች እንዴት ናችሁ ? እንኳን ለእናታችን ለቅድስት አርሴማ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ከ32ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ለሆነችው ቅድስት ማርያም መግደላዊት የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! ዛሬ ማለትም ረቡዕ ነሐሴ 6 ለመስቀል ዕለት የምናቀርበውን የወረብ ጥናታችንን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጀምራለን። እስከ 11:30 ካፌ በር ጋር ተሰባስበን በጋራ የምንሄድ ይሆናል ፤ ሁላችንም ከእኀት ወንድሞቻችን ጋር በጋራ ተቀሳቅሰን በመምጣት የወረብ ጥናቱን እንድንሳተፍ ይሁን። ቦታ፡ ደብረ መዊዕ ቅ/ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን ሰዓት፡ 12:00 ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን! ☘ መዝሙር እና ሥነ-ጥበባት ክፍል☘ ┄┉✽»༺ ═ ✞ ═ ༻»✽┉┄ 📥 @Gibi_Gubae_hasab_bot ጻፉልን 🏷 @kidus_petros_mereja ተከታተሉን 📷 @peterosphotos የፎቶ ማኅደራችን Instagram | YouTube | Digitallibrary | ጉባኤ ዘቅዱስ ጴጥሮስ|Website ┄┉✽»༺ ═ ✞ ═ ༻»✽┉┄ ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ✨
✝️እንዴት ቆያችሁ ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች? ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን!!! እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ዛሬ ማክሰኞ በ05/12/18 የደብረ ታቦር (ቡሄ) መዝሙር ጥናታችንን የምንቀጥል ይሆናል። መምጣት የምትችሉ እና እስከዛሬ በየትኛውም የጥናት ቀን ያልነበራችሁ ሁሉ ከእኅት ወንድሞቻችሁ ጋር በመቀሳቀስ እንድትገኙ በልዑል እግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን። ቦታ፡ ደብረ መዊዕ ቅ/ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን ሰዓት፡ 11፡ 30 (ከግቢ የምንወጣበት ሰዓት) 💥ማሳሰቢያ፡ ለቦታው አዲስ የሆኑ ልጆች ስለሚኖሩ ሁላችንም እስከ 11፡ 30 ድረስ ካፌ በር ጋር ተጠባብቀን በጋራ የምንሄድ ይሆናል። በቶሎ እንድንጨርስ ሰዓት ይከበር!!! በአጋጣሚ አርፍዳችሁ ለምትደርሱ ቦታ ለመጠየቅ ከታች ያሉትን ስልኮች ተጠቀሙ። 👉0984540057 👉0938807056 🕊ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ!🕊 ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ✨
ማሳሰቢያ 1. ጾመ ፍልሰታን ካፌ 9፡00 ሰዓት ላይ ስለሚከፈት ላልሰሙ ወንድሞች እና እኅቶች እያሳወቅን በሰዓቱ እንድንገለገል ይሁን! 2. የአንድነት መርሐግብራችን መርሐግብሩ የሚካሄድበት አዳራሽ ለሱባኤ ስለተያዘ ለሚቀጥሉት 15 ቀናት አይኖርም። በእነዚህ ቀናት ስለሚኖሩን ሌሎች መርሐግብራት በቀጣይ የምናሳውቃችሁ ይሆናል። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን! ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ✨
✨ጾመ ፍልሰታ✨ የተወደዳችሁ የቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ቤተሰቦች እንኳን ለምንናፍቃት ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን! 🌿 ፆመ ፍልሰታ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ከሰባቱ የአዋጅ አፅዋማት መካከል አንዱ ሲሆን ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ተብሎ ተወስኖ ይጾማል። 🌿 ፍልሰታ :-ፈለገ፣ ተሰደደ (ተገለጠ)፣ መከፈት፣ መገለጥ፣ ከሚለው የግእዝ ስውር ቃል የተገኘ ሲሆን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ትንሳኤ ያመለክታል። 🌿 የጾሙ ዋና ምክንያት ሐዋሪያት የእመቤታችንን የእረፍቷን ነገር አስመልክተው የጾሙት ፆም ነው። ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ 🌿 እመቤታችን በዚህ ምድር ስድሳ አራት ዓመት ከኖረች በኋላ ጥር 21 ቀን ዐረፈች ። ከዚያም ቅዱሳን ሐዋሪያት የእመቤታችንን ክቡር ሥጋ ወደ ጌቴሴማኔ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖረዋል። ዛሬ ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን ስለዚህ አስክሬኗን በእሳት እናቃጥላለን" ብለው ተነሱ። 🌿 ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሯን ጨበጠው መልአኩ ሁለት እጁን ቆረጠው፣ እጁ ከአጎበሩ ተንጠጥሎ ቀረ ።ከዚህ በኃላ መላእክት የእመቤታችንን ክቡር ሥጋ እና ወንጌላዊው ዮሐንስን ወስደው በኤደን በገነት አሳረፉት። 🌿 ቅዱስ ዮሐንስ ሲመጣ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡ 🌿 እነርሱም ነሐሴ አንድ ቀን በጾም በጸሎት ሁለት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀንም ጌታችን የእመቤታችንን ክቡር ሥጋ ሰጣቸውና በክብር በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን ዐርፋ ነሐሴ 14 ቀን ተቀብራለች፡፡ 🌿 እመቤታችንም በተቀበረች በሦስተኛው ቀን (ነሐሴ አስራ ስድስት) በልጇ ክርስቶስ ስልጣን ሞትን ድል አድርጋ ተነሣች፤ ቅዱሳን መላእክት አያመሰገኑ ወደ ሰማይ በደመና ስታርግ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሕንድ ሀገር ስብከቱ ሲመለስ ተመለከተ፣ 🌿 ከሚጓዝበት ደመና ላይም ለመውደቅ ወደደ፣"ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬ ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ" ብሎ ፣ እመቤታችንም "አይዞህ አትዘን ወንድሞችህ ሐዋርያት ትንሣኤዬን ዕረገቴን አላዩም አንተ አይተሃል፣ተነሳች አረገች ብለህ ንገራቸው" ብላ ምልክት ይሆነው ዘንድ የያዘችውን ሰበን ሰጠችው። 🌿 ቅዱስ ቶማስም ይህንን ለቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፣የሰጠችውንም ሰበን አሳያቸው፣ሰበኗንም ለበረከት ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሄዱ። እነርሱም ቶማስ ያየውን ትንሣኤ እና ዕርገቷን ማየት ፈልገው እንደገና በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ።ከዚያም በዐሥራ ስድስተኛው ቀን ጌታችን ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ ከእመቤታችን ጋር መጣ፣ስታርግም አሳያቸው። 🌿 በዚህም መሠረት እኛም እመቤታችን እንድትባርከን፣ማስተዋል ጥበቡን እንድትገልጥልን፣ የምንፈልገውን መልካም ነገር ሁሉ እንድትፈጽምልን ቅዱሳን ሐዋርያትን አብነት አድርገን እንጾማለን። ሰናይ ጾመ ፍልሰታ ለነፍስ የሚበጅ ያድርግልን🙏 ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ✨
без подписи
"ከብር ይልቅ ምክሬን፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ።" (ምሳሌ 8:10) 📚የንባብ ቻሌንጅ በፍልሰታ📚 ውድ የቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ልጆች እንዴት ናችሁ? እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ! በጾመ ፍልሰታ "የብርሀን እናት" መጽሐፍን እያነበብን የሕይወት ስንቅ የሚሆን እውቀት እንድናገኝ ለሁለት ሳምንት የሚቆይ የንባብ ቻሌንጅ አዘጋጅተናል። 📖 በ pdf 🎙 በ audio ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ የግቢ ጉባኤያችን ዲጅታል ቤተ-መጻሕፍት አባል በመሆን የንባብ ቻሌንጁን ይቀላቀሉ! https://t.me/kidus_petros_digital_Library መልካም ንባብ! ┄┉✽»༺ ═ ✞ ═ ༻»✽┉┄ ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ✨
"የበጎ አድራጎት ጉዞ" ሰላም ውድ የቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ልጆች እንዴት ናችሁ ? እንኳን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ለአቡነ እጨጌ ዮሐንስ የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! እግዚአብሔር ቢፈቅድ በሚመጣው ቅዳሜ ነሐሴ 2 የበጎ አድራጎት ጉዞ በግቢ ጉባኤያችን የተዘጋጀ ሲሆን በዚህ የበረከት ስራ ላይ ሁላችሁም እህት ወንድሞቻችን እንድትሳተፉ እና በረከት እንድታገኙ በልዑል እግዚአብሔር ፍቅር እንጠይቃለን። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን! ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ✨
✨ የደብረታቦር መዝሙር ጥናት✨ መዝሙር ለእግዚአብሔር የምናቀርበው የከንፈር መስዋዕት ነው፣አምላካችንን ስላደረገልን ብዙ ድንቅ ነገር ከምስጋና በቀር ምን ልንከፍለው እንችላለን? ምንም! ደብረታቦር ጌታ ብርሃነ መለኮቱን ለሐዋርያት የገለጸበት፣አብም በደመና ሆኖ የመሰከረበት፣መንፈስቅዱስ በርግብ አምሳል የወረደበት ልዩ በዓል ነው። ታዲያ በዝማሬያችን ይህን እያነሳን በደብረታቦር በመንፈስ መዋል እና ይህን ድንቅ ምስጢር በአይነ ልቡና መመልከት እንዴት መታደል ነው! ምናልባትም እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ "በዚህ መኖር ለኛ መልካም ነው" ሳያስብለን አይቀርም😊 ደግሞ የመዝሙር ጥናታችንም ሊያልቅ ጥቂት ቀናት ስለቀሩት ይቺን መልካም አጋጣሚ ሳንጠቀምባት ቀርተን እንዳንቆጭ። ታዲያ ይህን ሁሉ በረከት የት እናገኛለን ብላችሁ እያሰባችሁ ነው አይደል? ዛሬ ማታ 11:30 በመዝሙር ጥናታችን ወደ ደብረታቦር ተጉዘን በምስጋና እንተማለን። አንተ፣አንቺ፣እናንተ ሁላችንም በአንድነት በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ቤተክርስቲያን እንገናኝ። የምናጠናቸውን መዝሙሮች ለማግኘት ይሄን ግሩፕ👇 ይቀላቀሉ። https://t.me/+f9HJXeyothNhMzg0 ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን! ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ✨
✨ጾመ ፍልሰታ ✨ ሰላም ውድ የቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ልጆች እንዴት ናችሁ ? እንኳን ለ ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ!! "ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥" {ትንቢተ ኢዮኤል 2:15} ግቢ ጉባኤያችን ሁሌም እንደሚያደርገው ለአጽዋማት ከተማሪዎች የሚገኘውን የቁርስ ዳቦ 🍞 — ለነዳያን እና — የግቢ ጉባኤውን ልማት ለመደገፍ ያውላል። ስለዚህ ሁላችሁም 👉 ስም 👉 ID 👉 Meal Card እና 👉 Department በ @Annecisu እና @Edubirhan ትልኩልን ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እናሳስባለን። ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ✨
без подписи
✨ጉዞ በሐዲስ ኪዳን✨ በዛሬው የጉዞ በሐዲስ ኪዳን ልዩ የመዝጊያ ጉባኤያችን:- መርሐግብራችንን በጸሎት ጀምረን፣ በውይይት ዐውዳችን ለሕይወታችን ስንቅ የሚሆኑንን ሃሳቦች ቀስመን፣እርስ በርሳችንም ተዋውቀን፣ በየመሀሉ የተጠየቁ ጥያቄዎችን በመመለስ የቅዱሳኑን ስዕለ አድህኖ ማስታወሻ ይዘን፣ ቀጣይ ስለታቀዱ ስራዎችም አጠር ያለ ማብራርያ ሰምተን፣ ጉዞ በሐዲስ ኪዳንን አንብበው ለፈጸሙ ቤተሰቦች ለቀጣይም እንዲበረቱ፣ ሌሎችም ልምድ እንዲወስዱ አነስ ያለች ስጦታችንን አበርክተን፣ በመጨረሻም ለከርሞ ያድርሰን ብለን መርሐግብራችንን በጸሎት ፈጽመናል። አሜን አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ከቁጥር ሳያጎድል ለከርሞ ያድርሰን! ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ✨
ሰላም ውድ የቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ልጆች እንዴት ናችሁ ? እንኳን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለቱ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ለሰማዕቱ ቅዱስ አሞን የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! የጉዞ በሐዲስ ኪዳን ቆይታችን እንዴት ነበር? ዛሬ ማለትም ሰኞ ሐምሌ 27 የጉዞ በሐዲስ ኪዳን ልዩ የመዝጊያ መርሐግብር ይኖረናል። የሚኖሩን መርሐ ግብራት:- ✨ ውይይት ✨ ቀጣይ ስላታቀዱ ነገሮች የተወሰነ ገለጻ ✨ ስጦታ ቦታ፦ ደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ቤተ ክርስቲያን(መሠረተ ወገራም) ሰዓት፦ 11:45 እነዚህን እና ሌሎች ልዩ መርሐግብራትን አሰናድተን እንጠብቃችኋለን፣ሁላችሁም በቤተሰብ ተቀሳቅሳችሁ በመምጣት ከዚህ ልዩ መርሐግብር በመሳተፍ በረከት እንድታገኙ በፍቅር ጠርተናችኋል😊 ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን! ┄┉✽»༺ ═ ✞ ═ ༻»✽┉┄ 📥 @Gibi_Gubae_hasab_bot ጻፉልን 🏷 @kidus_petros_mereja ተከታተሉን 📷 @peterosphotos የፎቶ ማኅደራችን Instagram | YouTube | Digitallibrary | ጉባኤ ዘቅዱስ ጴጥሮስ|Website ┄┉✽»༺ ═ ✞ ═ ༻»✽┉┄ ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ✨
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን። ✝ ሰላም የተወደዳችሁ የቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ልጆች እንደምን አላችሁ? ልክ እንደ እስከዛሬው በሚመጣው ጾመ ፍልሰታ ለፈቃደኛ ተማሪዎች የምጽዋት ሳጥን ተሰጥቶ ጾሙ እስኪያልቅ ወደ ሳጥኗ እየመጸወትን ከጾሙም ረድኤት በረከት ለማግኘት እግዚአብሔር በረዳን ልክ አስበናል ፤ የሚሰበሰበው ምጽዋት በሰሞኑ የተለያዩ social media ላይ ሲዘወዋር ለተመለከትነው ድንገተኛ አደጋ ለደረሰበት ለወንድማችን ለተማሪ አቤል ይሆናል። በበረከቱ መሳተፍ የምትፈልጉ እህት ወንድሞቻችን በቤተሰብም ሆነ በግል ከታች ያለውን ፎርም በመሙላት ሙዳየ ምጽዋቱን እንድትወስዱ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለን። 🌿ሞያ እና በጎ አድራጎት ክፍል🌿 https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSd3pYdLck9Y0GwK1HnlFnouuTeXTJKh6jWEXO9U8eZsQydDAg/viewform?usp=dialog ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ✨
ነገ ሰኞ ሐምሌ 27 ✨በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ከ11:45 ጀምሮ✨
✨የአንድነት መርሐ ግብር✨ "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።" {መዝ 122÷1} ሰላም ውድ የቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ልጆች እንዴት ናችሁ ? እንኳን ለጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ለቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ አባ ዘዮሐንስ እና ለሰማዕቱ ቅዱስ አባ ኖብ የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ዛሬ ማለትም ዓርብ ሐምሌ 24 የአንድነት መርሐ ግብር ይኖረናል። የሚኖሩ መርሐግብራት ꔰ ጸሎት ꔰ ትምህርተ ወንጌል ꔰ የጋራ ዝማሬ ቦታ፦ ደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ቤተ ክርስቲያን(መሠረተ ወገራም) ሰዓት፦ 11:45 ✝️ቅዱስ አባ ኖብ✝️ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ አራት በዚች ቀን ከደቡባዊ ግብጽ ከታችኛው ምድር አውራጃ ከንሒሳ ከተማ በ12 ዓመቱ ሰማዕትነትን የተቀበለው ቅዱስ አባ ኖብ አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ቅዱሳን ንጹሐንና የሚራሩ ነበሩ ። ይህንንም ቅዱስ ኖብን በወለዱት ጊዜ ዐሥራ ሁለት ዓመት እስኪሆነው ፈሪሀ እግዚአብሔርን እያስተማሩ አሳደጉት ። አንድ ቀን ቄሱንም ምእመናንን እንዲህ እያለ ሲያስተምራቸውና ሲያበረታቸው “ጣዖታትን ከምታመልኩ ክብር ይግባውና ስለ መድኃኒታችን ስለ ክርስቶስ ነፍሳችሁን ለሞት አሳልፋችሁ ብትሰጡ ለእናንተ መልካም ነው” ሲላቸው ሰማው። ከዚህ በኋላ ያለውን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ ። ከዚህም በኋላ ወደ ሀገረ ገምኑዲ ሔደ በዚያም ላለው መኮንን ስለ ጌታችን አምላክነት መሰከረ። በዚህም ብዙ አሰቃየው የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ አጽናናው። ከዚህም በኋላ መኰንኑ ወደ ሰሜን አገር ሲጓዝ የከበረ ኖብን ከእርሱ ጋራ በመርከብ ወሰደው በመርከቡም ምሰሶ ላይ ዘቅዝቆ ሰቀለው መኰንኑም ሊበላና ሊጠጣ ተቀመጠ በመኰንኑም እጅ የነበረው ጽዋ ወዲያውኑ እንደ ደንጊያ ሆነ የወታደሮቹም ዐይኖቻቸው ታወሩ የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ወርዶ አባ ኖብን ፈትቶ ከተሰቀለበት አወረደው በአፍንጫውና በአፉ የወረደውንም ደሙን አሻሸለት። በዚህም ወታደሮቹ አምነው ሰማዕትነትን ተቀበሉ። መኮንኑ ግን በብዙ አሰቃየው አቅፋሐስ ከሚባል አገርም ዮልዮስ መጣ ከእርሱም እንደ ተረዳ ገድሉን ጻፈ ። መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ አንገቱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ተገልጾለት አጽናናው እንዲህ ብሎም ቃል ኪዳን ሰጠው "ሥጋህ በሚኖርበት ቦታ ከእርሱ ታላቅ ፈውስ ይሆናል እንዲሁም በመከራው ጊዜ ስምህን በመጥራት ከእግዚአብሔር ርዳታ ለሚሻ ሁሉ ድኅነት ይደረግለታል፤ መታሰቢያህንም ለሚያደርግ ሁሉ የተራበ ለሚያጠግብ፣ የተጠማም ለሚያጠጣ፣ ለቤተ ክርስቲያንም በስምህ መባ ለሚሰጠው፣ የገድልህንም መጽሐፍ ለሚጽፍ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ መንግሥተ ሰማያትንም አወርሰዋለሁ።" ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡ ተጋድሎውንም ፈጸመ።ሥጋውንም ቅዱስ ዮልዮሰ አንሥቶ ከሁለት አገልጋዮቹ ጋራ ንሒሳ ወደ ሚባል አገሩ ላከው፤ የመከራውም ወራት በተፈጸመ ጊዜ አብያተ ክርስቲያናትን ሠሩለት በውስጣቸውም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ሁላችንም ከእኅት ከወንድሞቻችን ጋር ተቀሳቅሰን በመምጣት መርሐግብሩን እንድንሳተፍ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን! ┄┉✽»༺ ═ ✞ ═ ༻»✽┉┄ 📥 @Gibi_Gubae_hasab_bot ጻፉልን 🏷 @kidus_petros_mereja ተከታተሉን 📷 @peterosphotos የፎቶ ማኅደራችን Instagram | YouTube | Digitallibrary | ጉባኤ ዘቅዱስ ጴጥሮስ|Website ┄┉✽»༺ ═ ✞ ═ ༻»✽┉┄ ✨ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ✨
✝️ሰላም ለእናንተ ይሁን የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት ቆያችሁ? በእመቤታችን ዝክር ምክንያት ያራዘምነውን የደብረ ታቦር መዝሙር ጥናት ነገ ሐሙስ 23/11/18 የምንቀጥል ይሆናል። እርስ በእርሳችን በመቀሳቀስ ከእኅት ከወንድሞቻችን ጋር ተሰባስበን እንድንገኝ በልዑል እግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን! ቦታ ፦ መሰረተ ወገራም ሰዓት ፦ 11፡30 ሰዓት ይከበር!!! 🕊 የያዕቆብ ሌሊት ይሁንላችሁ!🕊