tgindex
ሥነ ግጥም

ሥነ ግጥም

Статистика

ሥነ_ግጥም ግጥሞችን በዩቱብ ለመከታተል👇👇👇 https://youtube.com/@maryam2116

Последний пост
11 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Видео
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
894
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
627
21 постов
Вовлечённость
70,1%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
88
1/48двое суток
100
1/72трое суток
108

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • አማራነኝ በዘር ተውሶ ደመ ከልብ ሆኜ ጎጆዬም ፈርሶ መልኬ ተድጧል ዘመን ደፍርሶ አማራነኝ የድል ወይፈን ለቅሶ ጩኸቴን ድምፄን ለማፈን በቀብሬ ላይ ታንጎ ሚዘፈን አማራነኝ ደሜ ጥቁር እንባዬ ምድርን ምንቢሸነቁር አጥንቴ ለግር የማይቆረቁር አማራ ነኝ የመረረኝ ነፍሴ ላትወጣ እያጣጣረኝ ላንድ ትንሳኤ ሺ'ሞት የቀረኝ አማራነኝ ዛሬም ነገም ወቅትን ሰይሜ ክረምትም በጋም የኔ ኑሮ ግን ነግቷል... አልነጋም?! አማራ ነኝ! 💔 ታዲዎስ አለማየሁ

  • @ethiopia2123 @ethiopia2123 @ethiopia2123

  • ሕወይት ውል የላትም እንዳሰቡት አይሆን፣ሕይወት እንዳቀዱት በእውን ተመኝተው፣በሕልም እንደሳሉት ይገጥማል አንዳንዴ፣ አውላላ ሜዳ ላይ ሳርለበስ እንቅፋት ዳገት እየወጡ ቁልቁል መንሸራተት ይገጥማል አንዳንዴ፣ ጣና ላይ ተኝቶ በውሃ ጥም መቀጣት ሰርግ ቤት ተቀምጦ ተርቦ መገርጣት ይገጥማል አንዳንዴ ወይን ሲጠብቁ በበለስ መወጋት መዋብ ያሻ ገላ በጣት ታሽቶ መድማት ይገጥማል አንዳንዴ እሩቅ እያሰቡ ኋላ ሸሽቶ ማደር ለ ሺህ እያለሙ ለአንድ እራስ መቸገር። እዝጎ... 🫳🏽ታደሰ ደምሴ ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @ethiopia2123 @ethiopia2123 @ethiopia2123

  • 27 мая489102

    ዳቦ የቸገረው ህዝብ የስንዴ ምስል ይሸከም ዘንድ ግድ ነው🤨

  • ሐበሻ ነኝ... . . . ለመሞት ሲሆን ነፍስ የማያጥረኝ ቁስል እንደ ልጥ ያስተሳሰረኝ ታሪኬ ሁሉ መድማት መጨነቅ ህመም ይቀዳል ወዜ ቢጨመቅ . . ሐበሻ ነኝ . . ቆርጬም ባልጥል ተስፋን እንደ እትብት እጄ ላይ ደስታ የማይሰነብት ህይወት ሳልቀምሳት የምትበርድብኝ ከመኖር ይልቅ ሞት የሚያምርብኝ . . ሐበሻ ነኝ . . ከሰው ለይቶ በደም የሰራኝ ለትግል ብቻ መርጦ የጠራኝ ከታፈንኩበት ጭስ ሆኜ ሳመልጥ ለግዜር ለሰይጣን የማልጨበጥ . . ሐበሻ ነኝ ... ✍Tadiwos alemayehu

  • ✍Vic tor🔥🔥

  • አልመከር አልን መካሪ በዝቶ... ልብ ሂያጅ ቢያስስ የመጣን ትቶ የእጅ እየጣልን የመሬት ለቅመን ብናንጠለጥል መከራ መክሮ እያልመለሰን፡ ነዶ ቢያቃጥል እያደር ጥሬ ከርሞ ልጅነት ናናው ካጓጓን ከደገሰችው ልንካፈላት የሕይወት ሰርጓን ምለናል እና ሐዘን መቃመስ ፡ እንባ መጠጣት አንችልም በቃ :ከአንዳንዱ ገደል ሞክረን መውጣት! ካፒን ግራ

  • ማነው የገነዘው የእመቤቴን ስጋ እሳት አይደለም ወይ  በሆዷ የረጋ! ማን አረፈች ቢሉ እሷ ሁለቱም ነች                    : ልጄ ልጄ አሏት ድንግል ስለሆነች እናቴም ተባለች ጌታን ስላቀፈች። አረፈች መሰለኝ ጠፋ ድምጿ ባገር እሷ እኮ በፊትም አትወደም መናገር ! ተከደነ አሉ ጌታን ያየ አይኗ እሷ እኮ በፊትም መች ትላለች ቀና! ምነው በየደጁ ሰው ሁሉ ያለቅሳል ባይኑ እየሳላት                        : ለእናቷም ለአምላኳም አንድ ብቻ እኮ ናት! 🥺 (elias shitahun)

  • አንዳንዴ ማዳን ማንችለውን ነገር ለመቆጣጠር መሞከር ትርፉ ድካም ነው 𝓲𝓶𝓪𝓱

  • ተመስገን ዝም ብለን ላለፍናቸው ሀዘኖች ተመስገን ፈገግ ብለን ላለፍናቸው መገፋቶች ተመሰገን ከልባችን ለሳቅንባቸው ቀኖች ተመስገን መናገር ፈልገን ዝም ብለን እንኳንም ዝም አልን ላስባሉን ሁኔታዎች ተመስገን ጊዜ ለቀየራቸው ወዳጅነቶች ተመስገን እግዜር ለሰጠን ባለ ዕንቁ ልብ ሰዎች ተመስገን ላገኘነው ጠንካራ አቋማችን በዚ ሁሉ መውደቅ መነሳት ውስጥ ያልተወን አምላክ ይመስገን የተሻለ ነገ ይመጣል😊☺️ 𝓲𝓶𝓪𝓱

  • እግዚአብሔር የወደደውን አደረገ ነፍስህ በሰላም ትረፍ ነፂ😭💔

  • "የብልጦች ሀገር ሁሉም መላጦች ናቸው" 'ብልጥ ለብልጥ ዐይን ፍጥጥ': ይሄ የማይስማማኝ አባባል ነው፡፡ ብልጥ ነን ባዮች መፋጠጥ ከጀመሩ በመፋጠጥ አያቆሙም፡፡ ተረቱ ብልጦች ተፋጠው አርፈው ቁጭ የሚሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ጮሌዎች እየተያዩ ዝም አይባባሉም፡፡ ለመበላለጥ መሽቀዳደም ደንባቸው ነው፡፡ ('ብልጥ' የሚለው ቃል ውስጥ የ'መበላለጥ' ፅንሰ-ሀሳብ ከመጀመሪያው ተካቷል) ቀዳሚውና ተከታዩ ማን እንደሆነ መፈራረድ አለ፡፡ እስኪ ከእኩያ ቃል አቅጣጫ የተረቱን አጨራረስ እንይ፡፡ የብልጥ ተመሳሳይ 'ምላጭ' የሚለው ቃል ቢሆን፤ የሰከነ ተረት ከፈለግን መሆን ያለበት 'ምላጭ ለምላጭ ይላላጭ' ነው፡፡ ይሄም ጥሩ ተከታይ ታሪክ ይኖረዋል፡፡ የብልጦች ሀገር ሁሉም መላጦች ናቸው፡፡ ዛሬ ዛሬ አንዳንዶች ለመንደር ነጋ ጠባ ማቶስቶስን 'ንቃት' እያሉት ነው፡፡ በእንግሊዝኛ ሲያሳምሩት ናሽናል ኮንሸስነስ (National Consciousness) ይሉታል፡፡ ትክክሉ (tribal Consciousness) እንደሆነ ቢገባቸውም፣ በፅንሰ-ሃሳብና በመረጃ አልሆን ቢል በቃላት ያፋፉታል፡፡ በሌላ አባባል ብልጥ ሆኑ ማለት ነው፡፡ ብልጥ ራዕይ የለውም፡፡ በትክክል ምላጮች ናቸው፡፡ መአት የዚህ አይነት ምላጮች ሲሰባሰቡ አገሩ ጎፈሬ ማብቀል ይከብደዋል፡፡ ይሄን የሚደግፉ፣ በትንንሽ ዶላር የሚፎግሩን ባዴዎች ከዕለታት አንድ ቀን የተለየ ጭምብል ባጠለቁ ነጋዴዎች ለሁላችንም ሚዶና ጸጉር ሊሸጡልን ብቅ ይላሉ፡፡ *** 📖የስንብት ቀለማት አዳም ረታ

  • ለጮርቃ ሰው ላልበሰለ በሂወት ጦር ላልቆሰለ ባይድን እንኳን ላልታመመ ባይደርስ እንኳን ላላለመ ምን እያሉ ያወጉታል? እርሱ ባይተው ይተዉታል ለኔ ዓይነቱ ለከልካላው ባይወድ እንኳን ለማይጠላው ለሚያፈቅረው ጅል ለሆነ ለማይረባው ለባከነ እለት እለት ለሚያገጠው የላይ ላዩን ለሚውጣት ዓይነ ማዩን ሆድ ሲብሰው ለሚያለቅሰው ስቅስቅ ብሎ ለማይዋሸው በእናት ምሎ ለሚመከር ጠላት ውደድ ለተባለው እንኳን ለጠላት ልቡ ለወዳጅ መሆን ላልቻለው ምን እያሉ ያወጉታል? አይዞህ እንጂ ምን ይሉታል? ........! የአስቆሮጡ ይሁዳ

  • ይህም ኑሮ ሆነና እኛም ሰዎች ተባልንና ጦር - ህልማችን ላይ ቢሰቀሰቅ ህይወት - እጃችን ላይ ብትሞቀሙቅ ትኩስ ተስፋችን ሻገተ ፀአዳ ልባችን ሸተተ . . መከራ እንደ ሽርጥ ታጠቅን ሰላም እንደ ጡት ተነጠቅን ሀገር እንደቋት ተቦደሰች ፅንስ እንደ እንሽርት አፈሰሰች . . ቅጣት እንደዶፍ ይወርዳል ሞት እንደ ኑሮ ይለመዳል መሸሸጊያ መግቢያ የለም ሰማይ ምድሩ ተጠምቷል ደም ጫካው ገደሉ አይከለክል ቤቱ ምሽጉ አያስጠልል . . ልክ እንደ ትል እንደ ጉንዳን ወጥቶ መቅረት ተፈርዶብን የሚገድለን እንዳይራራ እግራቸው ስር እኛን ሰራ ታዲዎስ አለማየሁ

  • ፈውስ እየጠሉ ለሞት መስገብገብ በፀበል ውሀ ቡትቶ ማጠብ ዘራፍ ተብሎ የጠቅል አሽከር ፀፀት በጫንቃ ይዞ መሽከርከር ቆሎ እየናቁ አሻሮ መዝገን ለግዞት ኑሮ ቆርጦ መጀገን ምን ይሉት ግፍ ነው ምን ይሉት ፍርጃ ለራስ ላይ በደል የለውም ምልጃ? እንጃለት ብቻ ፤ አከራረሙን አያያዝ ጠፍቶት ቢቀናው እርሙን ያመናትላል መና እንደ ኩርማን ቅዳሴ ቆሞ ለርሀብ ቁርባን እንጃለት ብቻ እንጃለት እሱን እርም እየበላ ይገፋል ምሱን እንጃለት ብቻ... ታዲዎስ አለማየሁ

  • (በውቀቱ ስዩም) ከማዶ ሚመጣው ዘመድ ነው እንግዳ ከላይ የተለጋው ኳስ ነው ወይስ ናዳ፣ ብየ መች ጠየኩኝ መጪውን ጠበኩት ድንጋይ ላይ ቁጭ ብዬ፣ጸሐይ እየሞኩኝ፣ መከራም አላጣም፣ተድላም አልጎደለኝ፣ ደንታ ነው የሌለኝ፣ በአካል በስሜትም ታሞ ላገገመ፣ ወድቆ ለተነሳ እየደጋገመ፣ ለገንዛ ጉድጓዱ፣አጽሙን ለሚለቅም፣ ሞቱም ብርቅ አይደለም፣ትንሳኤም አይደንቅም። @ethiopia2123

  • ዐይኔ አረዘረዘ ፤ ልቤም ተሰበረ ፤ አንጀቴም ሆድ ባሰው ፤ ገና ሳይወለድ እንዴት ያረጃል ሰው !? ቴዎድሮስ ካሳ

  • ደራሲስ አውቃለሁ ባለቅኔ አውቃለሁ በቃላት የሚጽፍ : አይቼ አላውቅም ህይወት የሚቀይር እንደሚካኤል ክንፍ። - - - - / - - - - የዓይን እማኝ ነኝ! (elias shitahun)

  • አንዳንድ ነገሮችም ሳይ በጣም ይገርመኛል እንደ ሀገር እንደማህበረሰብም የወረደ የተጨማለቀ ሆነናል ሀበሻ ሲባል የሚመጣልኝ defination አሁን  ለራሴም ይገርመኛል ስርዓት አልባነት እና ልቅነት ባህል አድርገናል የ5ብር ፓኬጅ ሞልተን smart ስልክ ስለያዝን በ social media መጨማለቅ ራሳችንን እንደ አዋቂ እንድንቆጥር እያደረገን ነው እኔ ምለው ሀገራችን ብለን የምንመካበት ኩራታችን ብለን የምናወራለት ህዝብ የሚወደደው ምኑ ነው? እውነት እዚች ሀገር ላይ የሚያጓጓው ነገርስ ምንድነው? አውሮፓ አሜሪካ....እኮ ቢቀብጡም ሰርተው ነው ደሞኮ ማን እንደሀገር ሌላውን ስላላያችሁት ነው የምትሉ ሰዎች እስኪ ይሄ ይለየናል በሉ ባህላችን አትሉም መቼም? የትኛው ባህል ተደብቆ የኖረው የመሰዳደብ ባህል? ወይስ አብሮ መብላት መጠጣት እንዳትሉ በቀን 1 ለመብላት እንኳን ችግር የሆነበት ሀገር ላይ እየኖርን አሁን ድንበር ተከፍቶ እዚህ ሀገር መኖር የማትፈልጉ ውጡ ቢባል እኮ የሚቀር ያለ ይመስል😒

  • ያልሆነውን ናችሁ ተብለን ስንከሰሰ ባልሰማ ለራሳችን ጥብቅና ሳንቆም  የምናልፈው እውነት ጠበቃ ስለማያስፈልጋት  ዳኛም የቀረበለትን ማስረጃ ስለሚያምን ቢሆንስ? 𝓲𝓶𝓪𝓱