ማራኪ(ጥዑም)
Статистикаጥዑም ጥዑም የሆኑ ፅሑፎች የሚለቀቁበት ቻናል ማራኪ (ጥዑም) ይሰኛል t.me/daniwww21 For Ads:- t.me/Da_yabu የተለያዩ አስታየት ካሎት በዚህ ያናግሩን t.me/da_yabu በተጨማሪም..t.me/dani_yabu_bot
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 7
- 1/48двое суток
- 8
- 1/72трое суток
- 8
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️ 💁♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️ 👨🦱🧑🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️ ⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️ 🤵♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️ በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት 👇👇👇 @EOTC_-OPEN_channel @EOTC_-OPEN_channel @EOTC_-OPEN_channel @EOTC_-OPEN_channel
⛪️📚🙏 1, እመጓ 2, ዝጎራ 3, መርበብት 4, ዴርቶጋዳ 5, ዮራቶራድ 6, ዣንቶዣራ 7,መጽሐፈ ሄኖክ 8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ 9, ፍኖተ አእምሮ 9, አዳም እና ጥበቡ 10, ዝክረ መስቀል 11, ሰይፈ ሥላሴ 12, ፍትሐ ነገስት 13, መጽሐፈ መነኮሳት 14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና 16, ህግጋተ ወንጌል 17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን 18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል 19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ 20, ግድለ ተክለሃይማኖት 21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ 22, የወጣቶች ህይወት 23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት 24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት 25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ 📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖 ✝ ይቀላቀሉን ✝
📌 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ? 📌 ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 📌 ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ 📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ 📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ 📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ 📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ 📌 ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን 📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው እና የሌሎችንም ........... የዘማሪዎችው መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት 🔻🔻🔻 👇👇👇 https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
🎉ከ17 ደቂቃ በኃላ ይጠፋል የ 200 ብር ካርድ የሚያሸልም ጥያቄ! የንኤስ_አንበሳ የተባለው ማን ነው ?
SkillMoney Complete tasks and manage your rewards. https://t.me/SkillMoney01_bot/earn?startapp=ref_935E950B
SkillMoney Complete tasks and manage your rewards. https://t.me/SkillMoney01_bot/earn?startapp=ref_935E950B
ልጅህ የማን ነው? በዚህ ዘመን በጣም አዋቂ ወላጅ ነው ብለህ የምታስበው ሰው ምን ዓይነት ነው ተብዬ ብጠየቅ “ልጁን ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚልክ” ብዬ የምመልስ ይመስለኛል። ልጅ መናገርና መራመድ ከጀመረ በኋላ ወደ ቤተ-ክርስቲያን አልወሰዱትም ማለት፣ ራስ ወዳድነት ነው፤ ከዚህም አልፎ ማስተዋል አለመቻል ነው። ልጅ በልጅነቱ የአምላኩን ስም እየጠራ ካላደገ፣ ዕጣን እየሸተተው ካልመነደገ አስቸጋሪ ፀባይ ልማድ ይሆንበታል። ልጅን ከራስ ጋር ብቻ ማቆየት ማለት፣ ከእግዚአብሔር እኔ እሻላለኹ እንደ ማለት ነው። ምክንያቱም ልጅህን ወደ ቤተ-ክርስቲያን ስትወስደው የእግዚአብሔር እያደረግከው ነው፤ ከዚህ ውጪ ከሆነ ግን ከጌታው እኔ እሻለዋለኹ ማለትህ እንደሆነ ጠንቅቅ። ዲ/ን መኩሪያ (ዘከተፋ) ጽዮን 17/10/2018 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ #ንነጽር_198 #ልጅህ #የማን #ነው
የእግዚአብሔር ቢሮ... ለእግዚአብሔር የቁርስ ሰዓት የለውም፤ ለእግዚአብሔር የምሳና የራት ሰዓትም የለውም። የእግዚአብሔር ቢሮ ሁሌም ክፍት ነው። ገበያ በሆንክ ሰዓት እግዚአብሔርን ማነጋገር ትችላለህ፣ ሥራ በሆንክ ሰዓትም እግዚአብሔርን ማነጋገር ትችላለህ። ተወዳጆች ሆይ! በፈለጋችሁበት ሰዓት እግዚአብሔርን ለመጥራት ብትፈልጉ፣ አጠገባችሁ እንዳለ ሳትዘነጉ #ማረኝ በሉት። የኃጥኡን ጸሎት ለመስማት የታመነ ነው። እሱ የቅርብ አምላክ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለም! ዲ/ን መኩሪያ (ዘኖርቻ) ጽዮን 06/11/2018 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ #ንነጽር_195 #የእግዚአብሔር #ቢሮ #ሁሌም #ክፍት #ነው
He asked her, “አገልግሎት ላይ ፈተና በዛብኛል፤ በጣም ሰልችቶኛል።” She replied to him... “እንደ ክርስቲያን እህት አንድ መሠረታዊ ነገር ላስታውስህ ብቻ ነው ምፈልገው ። ከዚያ በፊት ...አንተን የገጠመህ ነገር በአንተ ላይ ብቻ የሆነ አይደለም። አንዳንድ ተሰጥዖ ያላቸው፣ ዕድሜዬን በማገልገል ማሳለፍ አለብኝ ብለው የሚያስቡ አገልጋዮች የሚገጥማቸውን ፈተና ነው። በአገልግሎት ብቻ አይደለም፤ በዓለማዊ ትምህርትም ብትለው አይደለም የሩቅ ሰው፣ የገዛ ጓደኛህ ባይነግርህም የአንተ ጥንካሬ ቅር ያሰኘዋል። ለምን? ክርስቲያን ነኝ ብሎ ያስባል እንጂ ክርስቲያን ስላልሆነ ነው። ላስታውስህ ምፈልገው ... አንተ ክርስቶስን በጥቂቱ ተረድተህ፣ ከዕድሜህ በጥቂቱ ለእርሱ ለመስጠት የወሰንክ ሰው ነህ። እንግዲህ ይሄ የክርስቲያን ሕይወቱ ነው። (እስከ ሕይወትህ ፍጻሜም ይቀጥላል) ክርስቶስ የተከበረ ንጉሥ ሆኖ ፊቱን ሊያዩት የማይገባቸው ሰዎች ሲተፍበት የታገሰው ዛሬ ላለኸው ለአንተ እንዲህ ያለ ፈተና ሲገጥምህ እንድትታገስ ብቻ አይደለም፤ የትዕግስትህም ጥግ የት ድረስ መሆን እንዳለበት ሊያስተምርህ ነው። እስከዛሬ የተማርካቸው፤ ለሰዎችም ምትነግራቸውን የቅዱሳንን ታሪክ ስለምን ወደ አንተ ሕይወት አምጥተህ አትኖረውም? እስከዛሬ እየተገረምክ የሰማኸውን እመቤታችን ካስተማረችህ ትህትና በሚገፍህ ሰዎች ፊት በቂም፣ በመከፋት ወይም በጥላቻ ሳይሆን በመተናነስ በፊታቸው በእግዚአብሔር ጸንተህ ማትቆመው ለምንድነው? የምር አንተ በአካባቢህ ያሉ ክርስቲያኖች እንደሚያደርጉት ሰይጣናዊ ሥራ፤ የክርስትናን ትክክለኛ አስተምህሮ ባለመረዳትና በህይወት ባለመኖር የሚኖር ራስን በማታለል እና በምናባዊ እንቅልፍ ውስጥ ላለመኖር የምትጥር ክርስቲያን ከሆንክ፤ መጀመሪያ የጀመርከው የክርስትና ሕይወት በዓለም የመከራ፤ የመገፋት እንደሆነ የተረዳኸውን በሕይወትህ በተግባር ሲያጋጥምህ መበሳጨት፤ መማረር እና ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን ያለብህ ትንሽም እንኳን ሳይከፋህ፤ ለሚገፍህ ሰዎች እግዜርን ላገልግል በሚል የሚያደርጉትን ክርስቶስ የማይወደውን ስራ ስለማያውቁት እንዲያሳውቃቸው ለእግዚአብሔር በትህትና ማመልከትን፤ የሚሉህን መጥፎ ንግግሮች ታግሰህ ብትችል በፍቅር መመለስ፤ ቢያንስ ግን እንደነሱ አለመሆንን መልመድ። ሌላውና ዋነኛው እየሆነብህ ያለው ነገር ሁሉ ከጠላትህ እንደሆነ፣ የአንተን በእግዚአብሔር ማመን ጥግ ለማወቅ እግዚአብሔር ይሄን በዘመንህ የገጠመህን ፈተና ትፈተን ዘንድ ፈቃዱ ሆኗል። ስለምን ፈቃደ እግዚአብሔርን አልቀበልም አልክ? ሁሌስ አንተ ያሰብከውን የፈቃድህን ብቻ ለምን ትፈልጋለህ? አስብበት..., መፍትሔ ብዬ ማስበው ፨የነገሮችን መጥፎ ጎን ብቻ አትመልከት ፨ ከዚህ ሁሉ ችግር ለመውጣት እንደ ክርስቲያን ምን እርምጃ ወሰድክ? ፨የምትፈልገውን ዓይነት አገልግሎት ወይም ቦታ (መሬት ላይ ያላገኘኸውን)ምንድነው? እና ለምን ፈለከው የምር የፈለከው ቦታ ክርስቶስ የፈቀደው ነው ወይስ አንተ በራስህ ይገባኛል ብለህ ምታስበው ነው? #ምክር ከሰዎች ጋር በአካል ማገልገሉ ካልሆነ ዘመኑ የ Technology ነው። Tiktok ን እንደነፈጉህ ዓውደ ምህረት ተጠቀመው፤ ለመታየት ሳይሆን ለማገልገል አስበህ። ከላይ ያሉትን ጥያቄዎች ለኔ ሳይሆን ለራስህ እና ለ እግዚአብሔር መልስለት። ምናልባት የገጠመህ ነገር ስለበረታብህ የጀመርከውን መንገድ አስረስቶሀል፤ ስለዚህ ይሄንን ማስታወስህ ይጠቅምሃል ብዬ ነው። ክርስቲያን ነህ፣ ክርስትያን ነህ፣ ክርስትያን ነህ... ይሄን ማሰብ ብዙ ጥያቄዎችን ይመልሳል!”
...ምን ይውጠን ነበር? እግዚአብሔርን መፈለግና እሱን መለመን ለቅዱሳን ብቻ የተሰጠ ቢሆን ኖሮ እኛ ኃጢአተኞች ምን ይውጠን ነበር? የእግዚአብሔር ስም በቅዱሳን ብቻ እንዲጠራ ቢያደርግ ማንን ተስፋ እናደርግ ነበር? ስሙን መጥራታችን ብቻ ተስፋችን ነው፤ እሱን መለመን መቻላችንና ስሙን እንደፈለግን እንድንጠራው መቻላችን ጥንካሬያችን ነው። ስንደነግጥም ሆነ ስንፈራ “እግዚአብሔር ቅደም!” ማለታችን ኃይላችን ነው። ይሄንን ስም ከጻድቃን እኩል እንጠራው ዘንድ የፈቀደው ፈጣሪ ይመስገን🙏 ዲ/ን መኩሪያ ዘደብረ ጽዮን 01/10/2018 ዲላ፣ ኢትዮጵያ #ንነጽር_192 #ምን #ይውጠን #ነበር
አንድ ወጣት ቄሱ ጋ ሄዶ በእድሜው የሰራውን ሀጥያት በሙሉ ይነግራቸዋል...ቄሱም አማትበው ምነው አንተ?!! ይሄንን ሁሉ በደል ሰርተህ ደሞ አይንህን በጨው አጥበህ ትመጣለህ??? ይህንንማ ፈጣሪ ይቅር አይለውም። እኔ ራሱ ስሰማው ከበደኝ በል ግቢውን ለቀህ ውጣ ይሉታል። ወጣቱም ደንግጦ.... እውነቶትነው አባ??? ይላቸዋል ሙት ስልህ!!! በእድሜ ዘመኔ እንዳንተ ያለ ሀጥያተኛም የለ!!! ብለው እንደመነሳት ሲሉ ወጣቱ ተናዶ ጥሏቸው ይሄዳል...በር ላይ ሲደርስ ግን የመኪና ቁልፉን ረስቶ ወደ ቄሱ ይመለስና ቁልፉን ሲጠይቃቸው ልጄዋ ቅድም ያልኩህን ግን ታስታውሳለህ?? አሉት ሰከን ብለው አዎ ፈጣሪ አይምርክም ብለውኝ የለ??አለ ወጣቱ ቆጣ ብሎ አዎዎዎዎ አየህ ያ ሁሉ ቅድም የነገርኩህ ነገር ሹክ የሚልህ ሰይጣን ነው። የአሁኑን አሸንፈህ መጥተሀል...ደግመ ልትመጣ ስትል ግን አይምርህም ሀጥያትህ ብዙ ነው ብሎ እዛው ያስቀርሀል። እየውልህ የመኪና ቁልፍክን አረሳከውም እኔ ነኝ የደበቅኩብህ ግን ያለ ቁልፍ መሄድ ስለማትችል ተመለስክ....ልጄ ብንመለስኮ ብዙ የጣልናቸው ትላንቶች ምግባሮች ልጅነቶች አሉ። ለመኪናህ ፈጥነህ እንደተመለስክ ጥለ ለሄድከው ፈጣሪም ሁሌ እንዲህ ተመለስ መኪና ያለ ቁልፍ ህይወትም ያለ እግዚአብሔር ባዶ ነው በል አሁን ቀኖናህን ተቀበል አሉት.... ጥለን የሄድነውን ልጅነታችንን ለመፈለግ እንመለስ። ከሰይጣን የስንፍና ምክር እንራቅ። ቢሞላም ባይሞላም ብናጠፋም ባናጠፋም ሁሌ ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ!
https://t.me/StarsSwapAutoBot?start=_tgr_Ip_NEdViOTA0
ስናጣ የራቃችሁ፣ ስናገኝም አትቅረቡን! ✨ በመሰለን ሥራ ተሰማርተን ራሳችንን ለመለወጥ በምንጋደልበት ወቅት የእናንተ ከንፈር መምጠጥ አያስፈልገንም። ከማሽማጠጥና ተስፋ ከማስቆረጥ ይልቅ፣ በእውነት ልትረዱን ካሰባችሁ የሥራ ዕድል ስጡን፤ ቤታችሁን እናጽዳ፣ ጉልበታችንን እንገብር። በላባችን በምናገኘው ክፍያ ሕይወታችንን እንገነባለን እንጂ የእናንተን የምጽዋት እጅ አንጠባበቅም። ✨ ዛሬ በጉልበት ሥራ የምናገኘው ጥሬ ብር፣ ነገ በብዙ ጥረት ለሚገነባው ትልቅ ቤት መሠረት መሆኑን አትዘንጉ። ስለዚህ በጉዟችን ላይ እንቅፋት ከመሆን ይልቅ፣ ርቀታችሁን ጠብቁ። ድካማችን ለነጋችን ብርሃን፣ መዛላችን ለጥንካሬያችን፣ መታከታችንም አዲስ ሰው ሆኖ ለመወለድ መሆኑን ተረዱልን። ✨ ስናጣ የሄዳችሁ፣ ስናገኝም አትመለሱ። የእናንተ መራቅ ለእኛ መለወጥ ትልቁ ምክንያት ነው። ጎዶሏችንን በእናንተ ምጽዋት የምንሞላው ከሆነ፣ የነገ ጥንካሬያችን መሠረቱ ይናጋል። ✨ ሀብት ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ የተሰጠች ጸጋ አይደለችም፤ እኛም የራሳችንን ድርሻ ለማግኘት ነጻነት ያስፈልገናል። በችግራችን ወቅት ለሰጣችሁን ጥቂት ነገር እንደ ትልቅ ውለታ አትቁጠሩት፤ እንዲያውም ያ ባይሰጠን ኖሮ፣ ችግሩ አማሮን ዛሬ ካለንበት በበለጠ እንገሰግስ ይሆን ነበር። እርዳታችሁ ከሥራችን ይልቅ የእናንተን እጅ እንድንጠባበቅና እንድንሰንፍ ስለሚያደርገን፣ በትምህርትና በሕመም ወቅት ካልሆነ በቀር በሥራችን ጣልቃ አትግቡ። ✨ በማንኛውም የሥራ መስክ ብታገኙን “ይህ ሥራ ለአንተ አይመጥንም” በማለት ሞራላችንን አትግደሉ። ካልሆነ ግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዘላቂ የሥራ መስክ አመቻቹልንና ተዉን። ያኔ ለራሳችንና ለቤተሰባችን ብቻ ሳይሆን፣ እናንተንም ጭምር የሚጠቅም ትልቅ ደረጃ ላይ ደርሰን ትመለከቱናላችሁ። ✨✨✨ እያልኩ ያለሁት "ማንንም አትርዱ" አይደለም። ነገር ግን የእናንተ የእርዳታ እጅ ጥገኛ አድርጎ የሚያስቀምጥ ከሆነና እናንተም ስለረዳችኹ ብቻ ተረጂውን የምታሸማቅቁት ከሆነ.........! ስትረዱን እንድንለወጥ ከመፈለግ አንጻርና ያወጣችኹትን ቁስ ከፈጣሪ ለመቀበል ይሁን እንጂ፣ pls እኛን እንደ ትንሽ ለመቍጠር አይሁን።
❝ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በአቢይ ሀይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን አጋዕዞ ለአዳም ሰላም እም'ይዜሰ ኮነ ፍስሐ ወሰላሞ❞ "እንኳል ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለትንሳኤው በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ"!!!!!
“ጊዜ ቋሚ መሰላቸው፤ ጊዜ ቋሚ አይደለም። ከመኖር የተማርኩት አንድ ነገር ይህን ብቻ ነው።” አለኝ። “አዎ፤ እንቅልፍ እና እድሜ አንድ ናቸው። ሁለቱም ሲሄዱ አይታወቁም። እንቅልፍ ተኝተን መተኛታችንን የምናውቀው ስንነቃ ነው። እድሜም እንዲሁ ሲሄድ ሳይሆን ሲቆጠር ነው የሚታወቀው። 📓ርዕስ፦ አለማወቅ ✍️ደራሲ፦ ዳዊት ወንድምአገኝ /ዶክተር/
«ሆሳዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው» #ያሉት እነሱው ናቸው «ስቀለው!» ብለው የጮሁበት። እንኳን አደረሳችሁ።
🔋🔋🔋 #የስልክዎን ባትሪን ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም የሚያግዙ ነገሮች:- ❖የስማርት ስልኮች ባትሪ ቶሎ ቶሎ ማለቅ የቴክኖሎጂው ትልቁ ድክመት ሆኗል። አፕል ከቀናት በፊት የባትሪዎችን እድሜ ለማርዘም ሲባል የስልኮቹን የአሰራር ሥርዓት (ኦፕሬቲንግ ሲስተም) ዝግ እንዲል ማድረጉን ይፋ አድርጓል። ❖ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት በቶሎ የሚሞሉ ሊቲየም አየን ባትሪዎችን ሲሆን ዲዛይናቸውም ባትሪዎቹ ተጠጋግተው እንዲቀመጡ የሚያደርግ ነው። ❖የስማርት ስልኮች ግፅታና ዲዛይን ቶሎ ቶሎ መቀያየር ማሻሻያውን እንዳከበደውም እየተነገረ ነው። በርግጠኝነት ይህ ነው የሚባል ነገር ባይኖርም የስማርት ስልኮችን እድሜ ለማርዘም የሚረዱ ነገሮች አሉ። ❶. ደካማ በይነ መረብ ስልኮዎ በየሄዱበት ጥሩ የበይነ-መረብ (ኢንተርኔት) መስመርን ለማግኘት ይሞክራል። በተለይም ደካማ የበይነ-መረብ አገልግሎት ባለበት ወይም አንድ ቦታ ላይ ብዙ ሰዎች የገመድ አልባ ኢንተርኔትን (ዋይ ፋይ) ለመጠቀም ሲሞክሩ ስልክዎ ሙከራውን ያከረዋል። ምርጥ የሚባል መፍትሄ ባይሆንም ስልክዎን ኤርፕሌን ሞድ ላይ ማድረግ ጥሩ ኢንተርኔት ለማግኘት እየታገለ ያለው ስልክዎ ባትሪ እንዳይጨርስ ይረዳዋል። ❷. አንዳንድ መተግበሪያዎች (አፕልኬሽኖች) አንዳንድ መተግበሪያዎች ባትሪ ይጨርሳሉ። ስለዚህ የማይፈልጓቸውን መተግበሪያዎችን መዝጋት የባትሪን እድሜ ያረዝማል። በተጨማሪም ባትሪ የሚለው ክፍል ውስጥ በመግባት በከፍተኛ ሁኔታ ባትሪ እየጨረሰ ያለውን መተግበሪያ መለየት ያስፈልጋል። ❸. ያሉበትን ቦታ አመልካች (ጂፒኤስ) የቦታ አመልካችን (ጂፒኤስ) ማብራትም ባትሪ የሚጨርስ ነገር ነው። እንደ ትዊተር ያሉ አፕልኬሽኖች ደግሞ እርስዎ ሳያውቁት ሁሉ ያሉበትን ቦታ መዝግብው ይይዛሉ። ስለዚህ ያሉበትን ቦታ የሚመዘግቡ መተግበሪያዎችን ቁጥር ለመቀነስ የማይፈልጓቸውን እንዳይሰሩ ማድረግ ይቻላል። ❹.ከፍተኛ ሙቀት ሊቲየም ባትሪዎች ለከፍተኛ ሙቀት ከተጋለጡ በደንብ አይሰሩም። ምክንያቱም በውስጣቸው ያለው አየን ባትሪው ቶሎ ቶሎ ቻርጅ እንዲደረግ ያስገድዳልና። ስለዚህ ስልክዎ ለከፍተኛ ሙቀት ወይም ለከፍተኛ ቅዝቃዜ እንዳይጋለጥ ማድረግ አይነተኛ መፍትሄ ነው። 🔋🔋🔋🔋 .... #ክፍል ሁለት ይቀጥላል...
የስልኮን ባትሪ ለረዥም ጊዜ ማቆየት እንደሚችሉ🤔
ማራኪ(ጥዑም) pinned «አሪፍ እና ቁም ነገር ያለበት ቤት ነው ተቀላቁሉ ትጠቀሙበታላቹ🤗 https://t.me/NEKU_TEWLD10»
አሪፍ እና ቁም ነገር ያለበት ቤት ነው ተቀላቁሉ ትጠቀሙበታላቹ🤗 https://t.me/NEKU_TEWLD10