tgindex
📖 የተቀደደው ማስታወሻ ©ሶፊ

📖 የተቀደደው ማስታወሻ ©ሶፊ

Статистика

​🗒️ እንኳን ወደ «የተቀደደው ማስታወሻ» በደህና መጡ! ​ይህ ቻናል በፈጠራ ታሪኮች እና ልብ-ወለዶች የታጀበ፣ በግጥም ስንኞች የደመቀ፣ እና የዕለት ተዕለት ውሎዎችን እንዲሁም እውነተኛ ስሜቶችን በደብዳቤ እንዲሁም postcard story መልክ የምናጋራበት የግል ማስታወሻችን ነው። ​ከቃላት በስተጀርባ ራስን ፍለጋ...

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
12
Всего постов
25
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Книги (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
7 262
+10 за 2 дн.
Сутки
+4
+0,06%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 421
25 постов
Вовлечённость
19,6%
к подписчикам
Постов в день
1,7
всего 25
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
968
1/48двое суток
1 109
1/72трое суток
1 196

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ስሚኝማ የተመኘሽ ሁሉ ይወድሻል ማለት አይደለም ። ምናልባት የተመኘሽ ስሜቱን መግራት የማይችል በቅሎ ሊሆንም ይችላል። attention አያስፈንድቅሽ ... ጭቅላትሽን መጠቀም መጀመር መቻል አለብሽ ።

  • ጠንከር ያለ ትችት እኔ እኮ የኔ ex ብቻ ትመስለኝ ነበር ... በድለውክ ይቅርታ እንድትጠይቃቸው የሚጠብቁ ደደብ ሰዎች እየተበራከቱ ነው ።

  • Masterpiece.

  • የሆኑ ትልቅ ሴትዮ ጃኬት ጀርባ ላይ ይሄን ተፅፎ አነበብኩ : "I'm a warrior, not a worrier." ፀዴ አ?

  • 🔥

  • 12 авг.1 1074913

    የሆንኩትን አልወደውም ፤ ግን መሆን የምፈልገውን አላውቅም ። ግራ ገብቶኛል ። ልክ የሆነ ቦታ ሊሄድ ፈልጎ ከቤቱ እንደወጣ ተጓዥ ፣ ከዛም መዳረሻው እንደጠፋበት ፤ እንደዛ ነው የሚሰማኝ ። የምመኘው ብዙ ነው ፤ ልይዘው የምፈልገው ብዙ ነው ፤ የማሳደው ብዙ ነው ፤ የምይዘው ግን የለም ። በዚህ ሁሉ chaos ውስጥ ሆኜ አንቺን መውደዴ credit የሚያሰጠኝ ተግባር ቢመስልም ፤ ምስጋና የሚገባው ላንቺ ነው ፤ እንዲህ አይነት ሰው መውደድሽ ይልቅ ያስገርማል ። እንዴት አይነት ገራገር ሰው ብትሆኚ ነው ? Undefined የሆነ ሰው የታገስሽው ስል አንዳንድ ጊዜ በልቤ አደንቅሻለሁ ። ዳሩ አለም ታግላ ስትጥለኝ ፤ ጥላ ስትታገለኝ ፤ ትግሌን እንዳላቆም የምታበረቺኝ አንቺ ነሽ ። እውነትም ፈጣሪ ሳይደግስ አይጣላም ። የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ

  • 12 авг.1 07719

    видео или голосовое, без подписи

  • 12 авг.1 123631

    Just so you know.

  • 11 авг.1 2962

    видео или голосовое, без подписи

  • 11 авг.1 223322

    ለእህታችን ቻሌንጅ! 10 ብር ለአንድ ሰው ትንሽ ቢመስልም ስንበዛ ግን ከኛ የወጣው 10 ብር ለሌላ ሰው ህይወቱን ማትረፍ ሊሆን ይችላል ከ10 ብር ጀምረን መላክ የምንችለውን እንላክላት... ለእህታችን እንድረስ❤️ CBE - 1000487578828 TeleBirr - 0911179293 Awash Bank - 013471629151800 ሁሉም አካውንት ስም - Rahel Aregay ከላካችሁ በኃላ ኮመንት ላይ ከScreenshot ጀምሮ እስከ ቴክስት መላክ ትችላላችሁ!

  • 9 авг.1 559684

    ካፌ በረንዳ ላይ ቁጭ ብያለሁ...በትልቁ መግ ማኪያቶ አስቀድቼ...ከዠመርኹት የሰነባበትኹትን በእንግሊዝ አፍ የተጻፈውን መፅሐፍ በማንበብ ላይ ነኝ...ዠምረን እንዳንጨርስ ግን ማን አዚም አደረገብን ? በአማርኛ ማንበብ የዠመርኋቸው ብዙ መፅሐፍ ነበሩ ግን ምን እንደሚነካኝ አላውቅም፤ድንገት ሌላ መፅሐፍ መግለጥ ያምረኛል። ለዚህ ችግሬ "የሴጣን ፈተና ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሻለሁ።ለዛ ነው ቋንቋ ቀይሬ መሞከር የፈለግኹት፤ሴጣንም አይገባውም ብሎ ስላሰበ ነው መሠለኝ ፈተናውን ቀንሶልኛል። ...መፅሐፉ ቶሎ እንዳያልቅብኝ እየሳሳኹ በጥቂት በጥቂት እያነበብኹ ሳለኹ...አንድ የሴት ድምፅ ከንባቤ ገታኝ..." ወንበሩ ሰው አለው? " አለቺኝ የቅብጠት ለዛ ባለው ድምፀት...ግራ በመጋባት ዙሪያውን አማተርኹ በሞላ ቦታ ፊት ለፊቴ መጥታ ግስጥ ማለቱን ለምን ፈለገች...? እንዴ ፈተና አልኹ ለራሴ። ልጅቷ መልሴን ሳትጠብቅ ወንበሩን ስባ ተቀመጠች...በጣም የምታር ሴት ጠይም፣ቁመናዋ የሚያስደነግጥ...ምንድነው ፕራንክ ነው? ካሜራው የቱ ጋር ነው ? በአይኔ ፈለግኹ።ወይስ በህልሜ ነው አይኔን አሸት አሸት አደረግኹ...እሙን ነው፤ልጅቷ አሁንም አለች። ጭራሽ ፈገግ አለች፤ ውበቷ እጥፍ ጨመረ፤ ይቺ ሴትዮ ልትገለኝ ነው? የማነበው ነገር ተፅህኖ አድርጎብኝ ነው መሠል ቆፍጠን ብዬ በእንግሊዝ አፍ ጠየቅኋት... "Do you remember me ?" ማለቴ ታውቂኛለሽ የእኔ እመቤት ? ምንድነው ህግ ባለበት አገር የሰው ቀልብ መዝረፍ ? ከት ከት ብላ ሳቀች...ኸረ ግዴላችሁም ወገን ይቺ ሴት ልትገለኝ ነው። ምንድነው? እየቀለድኹ መስሏት ነው? "ታስቃለህ...በእርግጥ አንተዋወቅም...ማለቴ እኔ አውቅሀለው አንተ አታውቀኝም...ብዙ ጊዜ እዚህ ተቀምጠህ አይሀለው። " ቀበል አድርጌ "አዎ እግዚአብሔር ይመስገን ስራ የለኝም።" አልኋት። ፈገግ ብላ ቀጠለች..."የእኔ ቢሮ እዛ ፊት ለፊት ነው...እና ለዛ ነው ብዙ ጊዜ የማይህ...ሳይህ ደስ ትለኛለህ...ብንተዋወቅ ደስ ይለኛል ብላ እጇን ዘረጋች..."እፁብ እባላለሁ..." የእጇን ልስላሴ እያደነቅሁ ጥቂት ዘገየው "ለገሠ...ለገሠ ነው ስሜ " አልኋት። እጄን በቀስታ ለቃ "ስለተዋወቅን ደስ ብሎኛል " ስትል የካፌዋ አስተናጋጅ ከ fantasy-ዬ አነቃቺኝ..." ልውሰደው?" ልውሰደው የምትለኝ የጠጣሁበትን የሻይ ብርጭቆ ነበር...ብስጭት ብዬ "ታዲያስ እናቱ ሻዩን ከጠጣኹ ብርጭቆው ምን ያደርግልኛል ? አልበላው። " "ብንሄድ ይሻላል - ከዚህ ካፌ ፤ ብዙዎች የሚመኙት እና የሚኖሩት ሂወት አልገጥም ሲላቸው አይደል፤መሄድ የሚመኙት? እኔ ግን ምኞቴን እወደዋለሁ፤ከእውኑ አለም ጥቂት ያሳርፈኛል። ከምኞቴ ስነቃ የማነበው መፅሐፍ እንደተገለጠ ነው...ያቺ ውብ ልጅ ግን የለችም..."Welcome to reality." "ደሀ በህልሙ..." ከ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ #re-edited ©ሶፊ

  • 9 авг.1 529403

    እንደ ነገሩ የተጫማችው ጫማ ድምፅ ከንባቤ ገታኝ ፤ ቀና ብዬ አላየዋትም ፤ ይልቅ የረበሸኝን እግር እንዳቀረቀርኩ በአይኔ ተከተልኩት...ቀይ የሴት እግር ጥቁር ጥፍር ቀለም የተቀባ ... የሚያምር እግር ...ፈጠን ብላ ተራምዳ ከፊት ካለው መቀመጫ ጋር ተቀመጠች ። እግሯ እንዲህ ካማረማ ... ፊቷን ማሰብ ነው የሚያቅትህ ሶፊ ቀና በል አልኩት ራሴን ። መፅሐፌን ከደንኩትና ውበቷን ለመታደም ዘና ብዬ ቁጭ አልኩ ። እንዳሰብኩት ቆንጆ አልነበረችም...ለጠጥ ብዬ ተመቻችቼ ቁጭ ካልኹ በኋላ የማስብ መስዬ እሷን እታዘባት ገባው...የሆነ ያስከፋት ነገር ያለ ይመስላል ። አስተናጋጇ ለለገሰቻት ፈገግታ አፀፋውን አልመለሰችም ። ስራዋ ነው ብላ ነው መሠል። ፊቷ ጨፍገግ አድርጋ ታስባላች ። ስልክ አትነካካም ፣ የተከፈተውንም ቴሌቭዥን ያስተዋለችው አይመስለኝም። እንደ psychopath አይኗን ወደ አንድ አቅጣጫ ተክላ ተቀምጣለች ። አስተናጋጇ ያዘዘቻትን ይዛላት ስትመጣ እንደቀድሞ ፈገግ ብላ አልነበረም ፤ አስተናጋጇም ስሜት አልባ ትመስል ነበር ። ተጋባባት ? አይደለም። አለም ሰጥቶ መቀበል ነው ፤ የሰጠቻትን ስላልመለሰችላት መስጠቷን አቁማ ነው ። አታምርም ። አለማማሯ ላይ መኮሳተር ጨምራበታለች ግን መብቷ ነው ። እኔም አይኔን ተክዬ ቀረሁ እኮ ተጋባብኝ እንዴ ? ሆ ©ሶፊ

  • 8 авг.1 670275

    видео или голосовое, без подписи

  • 7 авг.1 8714816

    ፍቅር እውር ነው ይላሉ ፤ የተሳሳቱ ይመስለኛል ። እኔ አለምን በሙሉ አይኔ ማየት የጀመርኩት አንቺን ካወቅሁ በኋላ ነው። የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ

  • 7 авг.1 8605012

    ብዙ ሰዎችን ይበልጥ በቀረብኳቸው እና ባወኳቸው ቁጥር ፤ ራሳቸውን የሸሸጉበት የመልካምነት ቅርፊት ፤ የማስመሰላቸው ቅርፊት እየተቀረፈ ፤ እንድጠላቸው ያስገድዱኛል። it's strange አንቺን ግን ... ሳውቅሽ ነው ይበልጥ የወድኩሽ። ሌላም ንገሪኝ ስላንቺ ? ልውደድሽ ፤ በፍቅር አበደላት ይበሉኝ። የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ

  • 7 авг.1 570492

    Most people are not focusing on the art...they focus on how many people liked it (ግር ማለት ስንወድ።) (From tiktok .)

  • 7 авг.1 857218

    የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ 🔥 ©ሶፊ

  • 5 авг.1 8836019

    ከማንም ጋር የማታወዳድሪው ሰው ይኖራል በህይወት ውስጥ ፤ አማራጭ ስለሌለ እኮ አይደለም ። ከአንቺ ወዲያ ማን ሊመጣ ነው ? ለምርጫ እራሱ አትቀርቢም። ... የቃላት ሀብታም ነህ ይሉኛል... አንቺ ላይ ስደርስ ግን ስሜቴን የሚገልፅልሽ ቃል ስላጣው እኮ ነው ዝም ብዬ የምወድሽ ። ብዬ ልነግራት ወኔ አጣው። ©ሶፊ

  • 5 авг.2 142669

    እሷ: እንዴት ነው የምትወደኝ ? እኔ : ይኽው እንደዚህ።

  • 3 авг.2 555738

    አንባቢ ሴት እወዳለው ሄጄ ላናግራት ይሆን ? ሄጄ ምን እላታለው? መረበሽ ይሆንብኛል ? ምን መፅሐፍ ነው የምታነቢው ? ብላት ምን ትመልስ ይሆን ? ቁጡ ሴት ከሆነች ምናገባህ ብትለኝስ ? እሺ ምን ልጠይቃት ስልኬ ዘግቷል አስደውይኝ ብዬ ወደ ራሴ ሚስኮል ላድርግ ? ሌባ ብመስላትስ ? ደግሞም ያለፍቃዷ ስልኳን መውሰድ አልፈልግም እኔ ሲግማ ነኝ። እኔም ሲንግል ነኝ አንቺም ሲንግል ከሆንሽ ተግባብተን ካፕል መሆን እንችላለን ብላትስ...ይሄ ፊልም ላይ ስክሪብት ሲሆን ነው የሚያምረው።( አይ ሶፊ ደግሞ ድፍረቱን ከየት አምጥተሽው ፤ እድሜሽ ገፍቷል ይሄን ተናግረሽ እንደጨረሽ ነው ድፍት የምትይው አለኝ ውስጤ ከቅርበታችን አንፃር አንቺ እያለ ነው የሚያወራኝ ።) እንደውም አላወራትም ታንብብበት ለሚወዱት ሰው ነፃነቱን ነው መስጠት በመተውም ቢሆን ፤ ባለማናገርም ቢሆን ። አ ላ ና ግ ራ ት ም ታንብብበት እኔ አንባቢ ሴት እወዳለሁ። ©ሶፊ https://vt.tiktok.com/ZS4fAKopQ/ አዶ ቡና is on fire 🔥

📖 የተቀደደው ማስታወሻ ©ሶፊ — tgindex